Tuesday, February 1, 2011

ምን ይሻለኛል ትላላችሁ?


ይህ ጉዳይ ከተነሣ በኋላ ብዙ አንባብያን ሃሳባቸውን እና ገጠመኛቸውን በመላክ ላይ ናቸው፡፡ ከነዚህ መካከል ለሌሎችም ትምህርት የሚሰጡትን እና ልብ የሚነኩትን በዚህ ሳምንት አቀርባቸዋለሁ፡፡ ላሁኑ የሚከለውን አንብቡ፡፡ ሃሳባችሁንም አካፍሉ፡፡ በተለይም የሕግ፣ የሥነ ልቡና፣ የማኅበራዊ ኑሮ ባለሞያዎች እና የጋብቻ አማካሪዎች ሃሳብ ብታካፍሉ መፍትሔዎቹ ይሆናሉ፡፡

አንደምን አለህ ወንድማችን / ዳንኤል

ይህ ያነሳሀው ሃሳብ ጥሩ ነው በተለይ ያንተን ሃሳብ ገልፀህ የኛንም አንድንገልፅ ስላቀረብቀው ደስ ብሎኛል።  እኔ ግን የተቀራረበ ጥያቄ አለኝ፡-

 ገብረ ሥላሴ እባላለሁ የአርባ አንድ ዓመት ጎልማሳ ነኝ፡፡ ባለትዳር እና የሶስት ልጆች አባትም ነኝ፡፡ ባለቤቴ የሰላሳ ሶስት ዓመት ወጣት ነች፡፡ ባለቤቴን ከምንም በላይና ከራሴም አብልጨ በጣም እወዳታለሁ÷ መግለጽ ከምችለውም በላይ አክብሬና ፈርቼ ነበር የያዝኳት÷ እርሷን ደስ የማያሰኛትን ነገር ሁሉ ለማድረግ ፈጽሞ አስቤውና አልሜው አላውቅም፡፡  

እንደውም ከትንሽ ወንድሜ ጋር እዚህ ግባ በማይባልና በማይመለከታት ይልቁንም ሊያስቆጣ በማያስችል ነገር በመጣላቷ መነሻነት ከወንድሜም ሆነ ከሌሎች ቤተሰቦቸ ጋር ቅር በመባባሏ እርሷን በመከተል የእኔም ከቤተሰቦቸ ሁሉ ጋር የነበረኝ ግንኙነት እንደበፊቱ አይደለም ÷ችግር ላይም ወድቋአል፡፡ በሌላ በኩል እኔ ለእርሷ ቤተሰቦች የማልሆነው ነገር የለኝም በክፉና ደጉ ነገር ሁሉ ከእግዚአብሔር በታች የቤተሰቡ ተስፋና አለኝታ ሁኛለሁ ብል ማጋነን አይሆንብኝም÷ በቤቴም እና በንብረቴም ሁሉ ላይ ከእኔ በበለጠ አዛዥ እና ተጠቃሚ እነርሱ ናቸው፡፡

 በተጨማሪም የእርሷን ቤተሰቦች አንዱ ሲለቅ አንዱን እያመጣች ታስተምራለች የፈለጉትንም ሁሉ ታደርግ ላቸዋለች÷ እኔም ተቃውሜ አላውቅም፡፡ ይህን ሁሉ ቀንበር ለእርሷ ካለኝ ፍቅር የተነሳ ተሸክሜ አንድም ቀን ቅር ተሰኝቼ እና አማርሬ አላውቅም÷ እንደውም ተስምቶኝ አያውቅም ነበር፡፡ ይሁን እንጅ በቤቴ ውስጥ ካደገ ÷ ከሌሎች ቤተሰቦቻችን በበለጠ እንደልጃችን አይተንና ተንከባክበን ካሰደግንው ይበልጡንም እኔ እርሱን ለማስተማር ብዙ ከደከምኩለት የአክስቷ ልጅጋር ያላት የቀረበ ግንኙነት ከቤተሰባዊነት ያፈነገጠ እየመሰለኝ ስለመጣ ግንኙነታቸውን በተመለከተ ሳልሰለችና ሳልቆጣ በተደጋጋሚ መስመር እንድታሲዘው ከፈተናም ላለመውደቅ በጣም ልትጠነቀቅ እንደሚገባት ሳሳስባት እየማለችና እየተገዘተች ምንም ዓይነት የተለየ ግንኙነት እንደሌላቼው ነግራኝ ነበር፡፡

አሁን ግን እኔ ለፊልድ ሥራ ቤተሰቦቼን ተሰናብቼ ከወጣሁ በኋላ መንገድ ላይ መኪናችን በመሰበሩ በምሽት ወደ ቤቴ ስመለስ ቤቱን እንኳን በመዝጋት ጥንቃቄ ሳያደርጉ በቅዱስ ጋብቻ በተኛንበት አልጋችን ላይ ከዚሁ ልጅ ጋር ተኝተው ራሴ ደርስኩባቼው÷ በወቅቱም የተሰማኝ ሀዘን ከፍተኝ ቢሆንም አሁንም ለእርሷ ያለኝ ፍቅር ከልክ ያለፈ ስለሆነ ምንም ዓይነት እርምጃ ለመውሰድ አልደፈርኩም ልጁም ወዲያውኑ ከቤት ወጥቶ ሄደ፡፡ ይህ ሁሉ ነገር ተፈጽሞብኝ አሁንም ቢሆን ውስጤ ከእርሷ ሊለይልኝ አልቻለም÷ ልጠላት አልቻልኩም፡፡ 
እንደውም የንስሐ አባታችንን ጨምሮ ሌሎች ሽማግሌዎችን ይዛ ጥፋቷን አምና ከዚህ በኋላ ወደዚህ ዓይነት ተግባር እንደማትመለስ ምላ ተገዝታ ይቅርታ ስለጠየቀችኝ÷ ፍቅሬ አስገድዶኝና የልጆቼ ሕይወት በእናትና አባት መለያት የሚኖረው አስተዳደግ ጨንቆኝ የቅርታዋን ተቀብዬ በንስሐ አባታችን የተሰጠንን ቀኖና ፈጽመን በሥጋወደሙ ትዳራችንን አድሰናል፡፡ ይሁን እንጅ ያሳለፍኳቸውን አስርአንድ የትዳር ዓመታት በዚየም ውስጥ እኔ ለትዳሬ የነበረኝን ታማኝነትና አክብሮት÷ ለልጁ ታደርጋቸው የነበሩትን ነገሮች አንድ በአንድ በማሰብ እያደር መበሳጨት ጀምሬያለሁ፡፡
 በሌላ በኩል በትዳሬ ላይ ይህንን የመሰለ ጥፋት የፈጸመብኝንም ልጅ መበቀል እየተመኜሁ መጥቻለሁ÷ በአልጋዬ ላይ ተኝተው አግኝቻቼው እርምጃ ሳልወስድ መቅረቴ እና ከዚያ በኋላም ቁስሌ በቁስል ሳይደርቅ ፈጥኜ ይቅርታ አድርጌ ሥጋወደሙን መቀበሌም በጣም እያጸጸተኝ ነው፡፡ አሁንም በእኔ የፍቅር ትዳር ላይ መርዝ ነስንሶ ባለቤቴንም ወደፊት በመንም መንገድ ማመን እንዳልችል ያደረገኝን ልጅ በሕይወት መኖር እየሰማሁ እኔ በሕይወት መኖር እንደማይገባኝ ወስኛለሁ፡፡ አሁን ደግሞ ትዳሩንም ማፍረስና ተለያይቶ መኖርን እያሰብኩኝ ነው ግን ደግሞ በጣም ስለምወዳት ከእርስዋ መለየት ይጨንቀኛል፡፡ ምን ይሻለኛል ትላላችሁ?

27 comments:

 1. ዲ/ን ዳንኤል ይህንን የመወያያ ሀሳብ ስላመጣህ እግዚአብሔር ይባርክህ!!
  ወንድማችን በውነቱ ከሆነ በጣም ነው ያዘንኩት እንዲህ አይነት በደልን በመታገስህም በጣም አከበርኩህ!! ነገር ግን ይህንን ትግስትህንም ዳግመኛ በአመድ (በበቀል) ልትበጠብጠው አገባህም፡፡ በንስሀ አባታችሁ በኩል ይቅርታ ከጠየቀችህ ተዋት ይቅር በላት፡፡ ዲ/ን ዳንኤል ከዚህ በፊት ስለ ይቅርታ የፃፋቸውን አንብባቸው፡፡ የበቀል ስሜት በተሰማህ ጊዜ ፈጥነህ ወደ ቤተ-ክርስቲያን ሂድ በዚያም የምትፀልየው ቢጠፋህ እንኩዋን በዚያ ዝም ብለህ ተቀመጥ እግዚአብሔር ትግስቱን ይሰጥሀል፡፡ በተረፈ ግን ላንተም ይሁን ለሱዋ ቤተሰብ ያለህን አክብሮት ሚዛናዊ እንዲሆን ጥረት ብታደርግ ጥሩ ነው፡፡ ደግሞ ሚዛናዊ ባልሆነ መንገድ በጣም እወዳታለሁ በሚል ስሜት ብቻ ዝም ብለህ አትጓዝ!! ለዚህም ያደረሰህ እሱ ይመስለኛል፡፡ አሁንም ቢሆን አብዛኛው ጊዜህን ለቤተ-ክርስቲያንና ከንስሀ አባታችሁ ጋር አሳልፉ፡፡ እግዚአብሔር ትግስቱን፣ብርታቱን፣ፅናቱን፣ በረከቱን ይስጥህ!!

  ReplyDelete
 2. Wiy Egziabher sntun taseman, ke ene yabsem ale ende...

  ReplyDelete
 3. ዲ/ን ዳንኤል በከፈትከው አነጋጋሪና አስተማሪ ርዕሰ ጉዳይ ምክንያት የብዙዎቻችንን ጓዳ ሚስጥር አውጥተን እንድንወያይበት አስችለኸናልና እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን፡፡
  ችግሩ የክቡር ወንድማችን የአቶ ገብረ ስላሴ ብቻ ልዩ ሚስጥራዊ ችግር ነው ብለን የተሳሳተ ግንዛቤ እንዳንወስድ ለማሳሰብ እወዳለሁ ምክንያቱም ብዙዎቹ አይናገሩ እንጂ ችግሩን ችለው በትዳራቸው ለመቀጠል የሚታገሉ ወይንም መቋቋም አቅቷቸው ለፍቺ የደረሱ ጥቂት የማይባሉ ተመሳሳይ ታሪክ ያላቸው ሰዎችን እኔ እንኳን በግሌ አውቃለሁ፡፡
  ስለዚህ ታሪኩ አወያይና አስተማሪ እንደሚሆን ግልጽ ነው፡፡ እንደኔ እንደኔ "አይጥ ወልዳ ወልዳ ጅራቱ ሲቀር..." እንዳይሆንብህ የሚል ሃሣብ አለኝ ምክንያቱም አሁን ያለህ መጥፎ የበቀል ስሜትና ውጤት መከሰት የሚገባው ቢሆን እንኳን ሊፈፀም ይችል የነበረው ድርጊቱ ሲከናወን በአይንህ ባየህበት ሰዓት ነበር፡፡ አንተ ግን እግዚአብሔር በሰጠህ ትልቅ ትዕግስት ይህንን ከባድ ፈተና አልፈኸዋል፡፡ ሰይጣን መጀመሪያውኑ ይህንን ድርጊት እንዲፈፀም ያደረገው፡-
  1ኛ. ሁለቱ በኃጢአት እንዲወድቁ ለማድረግ
  2ኛ. የአንተን ትዳር ለማፍረስ ነበር
  ይሁን እንጂ የሰይጣን ትዳርህን የማፍረስ ዕቅድ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በአንተ ትዕግስት ሊከሽፍ ችሏል፡፡ ቢሆንም ሁሌም የኛን መውደቅ የሚፈልግ በመሆኑ በተለያዩ አስታዋሽ ምክንያቶች የተነሳ ወደኋላ ተመልሰህ ወደ በቀል ስሜት እንድትገባ እየሆንክ ነው፡፡ ይህም አንዱ በሰይጣናዊ ስሜት የመጣ ፈተና መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ሁለታችሁም ንስሀ ገብታችሁ ስጋ ወደሙ በመቀበል ወደ ሰላማዊ ኑሮ መመለሳችሁን ገልፀህልናል፡፡ ይሁን እንጅ "እስከ መጨረሻው የፀና እርሱ ይድናል" የሚለውን ሁሌ እያስታወስክ በዚሁ አቋምህ ብስፀና፡-
  1ኛ. የሚስትህን ስጋዊና መንፈሳዊ ህይወት
  2ኛ. የልጆችህን በሙሉ ስብዕና ተኮትኩቶ ማደግ
  3ኛ. የአንተንም የመንፈሳዊ ህይወት ተጋድሎ ጥያቄ ውስጥ ከማስገባት ልትታደግ ትችላለህ፡፡
  በመጨረሻም የእመቤታችን የቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም አማላጅነትና ፀሎት የቅዱሳን መላዕክት ተራዳኢነት ከአንተ ጋር ይሁን፡፡ አንተም በፀሎትህ በርታ፡፡

  ReplyDelete
 4. Bekirstost yetwededk wendmachn G/selassie, yedrsbhn fetna sanb enbayen megtat akategn betlyem E/abher yadlhn tigist lewesed beyikerta yalfkewn bedl rasen wedmtelat ena wedbekel lewsdh eyasb selhofn (tamirat) meker beden anbebaw ayzoh Dengeln tirat huulachn eko melku yelyay enji shekm alen gen "Hayeln Bemiseten Bekirstos huulun echlalhu !" bemilew melket betelyem Kirstian bezih meder erest selalew betigisth tsena! Adera ayemlh gen FIKER AYADALAM! Esua Betsebochwan Endamtakeber huulu Yantenm makber endalbat Ke nesha Abath gar honach fetut Yenasu tselot merkat eko keleln waga yelnm! Fiker betelaye lesuwa yaleh mezanawi (Kirstanawi) yehun Zem belo mendat eko neg zefen betlhs? ayekbdhm? Selazh Aymerohn bemulu le Amlakh enji lesew madreg Kirstna aydelm!

  Berta Tselot huulun yekayeral "All things are possible in GOD!" besu berta Aberachu tselyeu betely Lejojachun yezachu westach kena selhon betachu yebarkale eshi wendmachn! Yeh bedel beyikerta selalfkew leman atnager adera ya telat enkerda yezeal ena ! Gedamat hidu betselot endi yasbuachu leabatoch negeru! Tidar ekulenet andenet endjilela almhonun endamtawek negerat! Ayzoh! Lehullum Amlak Kidusan yetabkh Be kirstos Betseboch Ketoronto

  ReplyDelete
 5. Dear brother

  "ymimeru bitsuhan nachew yemaraluna" Mat 5:7

  yehn kalegziabher betegibar fitsemehewal. Awehun libehin wedehuwala lememeles yemetagelih yehinin bereket endatagign yemefilige diablos newena ayzoh tagelew. Ofcourse it is too difficult and am not undermining the difficulty of the situation but you did the best in front of God so I think struggling to keep it will be again the best solution.

  May God be with you
  Abiot k oldenburg

  ReplyDelete
 6. ዳን ዳነአል በትሁፍ በታመ
  ጠሩ ነው የሰውየዉን ታሪክ ያሳዘናለ
  አንገደሀ በርታቱነን የስተው
  በጣም ያልተንኩ አረሶች አሉ
  ለምሳሌ ሰለ ዎለድ (ቤተሰብ መጣኔ ) መቆታተርአ
  ቤተ ከርስትአን ምን ተላለቸ
  አባክሀ በዘሀ ድገሞ ketel

  ReplyDelete
 7. ግን ትዕግስት ምንድነው…? አንዳንዴ እኮ የእኛን ስሜት ብቻ እየጠበቅን እያለ በምናሳልፈው ከባድ ጊዜያት ትዕግስት ያለን ይመስለናል ስሜታችን በሌላ ነገር ተሸፍኖ ነገሮችን ሳናስተውል ቆይተን ስንነቃ ትዕግስት የመሰለን ግን ያልሆነው ስሜታችን ይመጣል።
  ወንድሜ እስቲ ነገሮችን በእግዚአብሔር አንጻር እና በባለቤትህ ጸባይ እየውን። ለምን ይቅርታ አልክ አይባልም…?ይህ የይቅርታ ስሜት ከሷ የመጣው እውነት በጸጸት ነው ወይስ እግዚአብሔር ስላጋለጣት በሽንፈት የተሞላ የእፍረት ይቅርታ ነው..?….. ንሰሀ ከልብ አዝኖ እና ተጸጽቶ በራስ አነሳሽነት ሲፈጸም ንሰሀ ነው። አንተ በዚያ ሌሊት ባትመጣ ኖሮ ለንሰሀ የተገባ ህሊና ይኖራት ይሆን…? ሌላው ደግሞ አንተ ተቻኩዬ ቆረብኩ ብለሀል …..አንተን ከ ቁርባን የሚከለክልህ ነገር ምን አድርገሀል…?እሰዋ በሰራው ክፋት ከቅዱስ ቅርባን ስለራቀች አንተም እንደበደልክ አድርገኅ መቁረብህ ለምን ጸጸተህ..?ስጋውና ደሙ በፍረሀት እና በንሰሀ የተሞላ ሆኖ ህይወት ይሆነኛል ብለህ ማድረግህን አስብ።
  በወቅቱ የተደረገው ይቅርታና ንሰሀ ሁሉ ከሷ በመጣው ግፊት እንደሆነ ከንግግርህ ይገልጸዋል……አንዳንዴ እኮ ነገሮች የሚገለጹልን ቀስ ብለን ስንረጋጋ ነው። አንዳንድ ሰው ደግሞ ንዴቱን ወዲያው የሚያገነፍል ሰው አለ። አንድ እና አንድ ላንተ እሚበጅህ ነገር ምን መሰለህ። የህሊና ቁስል ወይም የውስጥ ፈተና በቃለ እግዚአብሔር ካልሆነ በሌላ አይጠፋም። የበቀል ስሜት እንዲሰማህና ህሊናህ የደረሰብህን በደል እንድታስብ ይገፋፋሀል በዚህ ጊዜ ያሳለፍከውን የፍቅር ጊዜ አስብ። ውይም ከ መጸሀፍ ቅዱስ ውስጥ ይህንን ህሊናህን የሚረብሽህን ስሜት የሚያጠፋልህን። የቅዱሳን ታሪክ አንብብ …….. የደረሰብህን በደል በበጎ በማሸነፍህ…… ይህ ነው የማይባል ትልቅ በረከትን አምላክ ይከፍልሀል እግዚአብሔር ያለ ዋጋ አያስቀርህም። በሀይማኖት የምታገኘውን ነገር ካሰብክ ህሊናህ ከበቀል ይከለከለከላል አልያ ግን በስጋ የደረሰብህን ካሰብክ መቼም የበቀል ስሜት ወይም ነዴትህ አይጠፋም። መከራ መቀበል ማለት እንዲህ ነው። ንሰሀ ዘማውን ድንግል ታደርጋለች የተባለው ደሞ ህያው ቃል ነው።
  አንተን በሷ ቦታ አስቀምጠህ አስበው አንተ ብትሆን ይህንን ያደረከው…እሷ ደሞ ይቅርታ ብታደርግልህ …ትዳርህ ቢታደስ ምን ይሰማሀል…?.ምናልባት ውስጥህ ፍቅር ተሟጦ አልቆ ቢሆን እንኳን የማይረሳ ውለታና ፍቅር ይጨምርልሀል ማን ያውቃል እሷ ውስጥ ያለውን የህሊና ወቀሳና የተሸከመችውን ሰቀቀን? በፍቅር ያሸነፍከውን ሰው በራሱ ላይ የሳት ፍም እንደተጨመረበት ነው። እሷ ባንተ አማካኝነት እግዚአብሔርን ያየች ከሆነ አንተ ደግሞ ከመንገድህ እንዳትወጣ አደራ። አጥብቀህ ጸልይ። እሷን ሳይሆን በሷ ድካም የገባውን ዲያብሎስ ስላሸነፍከው…አንተን ከመረበሽ አይተኛምና ንቃበት። እግዚአብሔር አምላክ ህሊናህን ሁሉ የሚያልፍ ፍጹም ሰላም ያብዛልህ።

  ReplyDelete
 8. ውድ ወንድሜ ዲያቆን ደንኤል! የዘወትር ሠላምታዬ ይድረስህ። ይህ ርዕስ በመንፈስ የተጎዱ ወገኖቻችን ስለ ደረሰባቸውን በደል የሚገልጹበት፣ ይህንን መነሻ አድርጎ መንፈሳዊና ሥነ ልቦናዊ ምክር የሚሰጥበት፣ እነዚህ ወገኖቻችን ወደ ሠላማዊ ኑሮ የሚመለሱበት ሁኔታ የሚመቻችበት እንደሚሆን ይሰማኛል። ምንም እንኳ ለአንዳንድ ወገኖች የሚያነቡት ነገር የሚከብዳቸው ቢሆንም የርዕሱ መነሳት ጠቀሜታው እጅግ የጎላ ነው።
  ወንድሜ ገብረሥላሴ! የደረሰብህ ነገር የሚያሳዝን ነው። ቢሆንም ለፍቅር ስትል ይቅር ማለትህ ደግሞ በአብዛኞቻችን ላይ የማይታይ ታላቅ ነገር (quality) እንደሆነ ልገልጽልህ እወዳለሁ። ከዚያም በላይ ደግሞ ይቅርታ ተባብሎ በሥጋ ወደሙ ትዳርን ማጠንከር የሚያስመሰግንህ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።
  ሆኖም፣ እንደ ገለጽከው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ክፉ መንፈስ እየተፈታተነህ እንደሆነ ለመረዳት ችያለሁ። እንኳን በሥጋ ወደሙ የተወሰነን ሰው ይቅርና ከዚያ ውጪ ሆነው በትዳር ላይ በሚነሳ አለመግባባት በሰይጣን የሚፈተኑ ብዙዎች ናችው። ወንድሜም ይህ የእርኩስ መንፈስ ፈተና መሆኑን ተረድተህ ራስህን ከክፉ አሳብና ከኃጢአት ልትጠብቅ እንደሚገባህ ልመክርህ እወዳለሁ።
  "ተበደልን" የምንል ሰዎች ብዙ ጊዜ የምንኮንነው "በድሎናል" የምንለውን ሰው ነው። ያንተ ነገሮችን እያዩ እንዳላየ ማለፍ በሷ ዘንድ የፈጠረው አሉታዊ ተጽዕኖ ሊኖር ቢችልስ? "ስለማይወደኝ ነው የማይናገረኝ" ብላ አስባ ሊሆንም ይችላል። አንተ ካለህ ፍቅር የተነሳ ገንዘብን ወይም ወጪን በተመለከተ መልካም ነገር ለሷም ሆነ ለቤተሰቦቿ እንዳደረክላት ገልጸሃል። ብዙ ወንዶች የምንሳሳተው እዚህ ላይ ነው። ፍቅር የሚገለጸው በማቴርያል ብቻ እንደሆነ የምናምን ብዙዎች ነን። የምንወዳቸውን ልጆች ፍቅር እንስጣቸው። እንንከባከባቸው፣ እናክብራቸው፤ እናስብላቸው፣ እናዳምጣቸው፣ ደስታችንንና ቅሬታችንን በግልጽ እናወያያቸው፣ እናግዛቸው፣...ወዘተ። ይህንን ካልነሳናቸው አብዛኛውን ጊዜ ልባቸው አይሸፍትም፤ የሰይጣን ፈተና እንዳለ ሆኖ። በመሆኑም በትዳር ላይ ለሚፈጠረው አለመግባባት የሁለቱም ወገኖች አስተዋጽኦ እንዳለ ልንረዳ ይገባናል።
  ወንድሜ ገብረሥላሴ! በይቅርታ የተዘጋው ፋይል አሁንም በእውነተኛ ይቅርታ ሊዘጋ ይገባዋል። ከራስህ ጋር ተቀመጥና (ፈረንጆቹ self-talk ይሉታል) ስለ ባለቤትህ "በኔም ሆነ በሌላ ምክንያት፣ ልጁም አሳስቷትም ይሁን ስህተት ላይ ወድቃለች፤ እኔ ይቅር ብያታለሁ፤ እግዚአብሔር አምላክ ይቅር በላት" ብለህ ለአምላክህ ንገረው። በዛች ቅጽበት ሸክምህ ሁሉ ከላይህ ላይ እንደሚሄድ ላረጋግጥልህ እወዳለሁ። ከዚህ በተጨማሪ ክፉው መንፈስ የሚፈታተንህ ከሆነ "ዞር በል፣ እምነቴ በእግዚአብሔር ነው" ብለህ ከአዕምሮህ አብርረው። ከአቅምህ በላይ ከሆነ የንስሐ አባትህን አማክራቸው፤ በጸሎት ይረዱሃል። አለበለዚያ ግን ነገሩን ባሰላሰልክ ቁጥር ንዴትና ብስጭት ስለሚያስከትልብህ ለጨጓራ፣ ለደም ብዛትና ለልብ ሕመም ትዳረጋለህ። በዚህ ጉዳይ ባለቤትህን ባሰብክ ወይንም ልጁን ባየህ ቁጥር ለበቀል ስለሚያነሳሳህ የከፋ ወንጀል ላይ ትወድቅና "ለልጆቼ ስል ትዳሬን መረጥኩ" ያልከው ቀርቶ ልጆችህን ያለ አባት ወይም እናት ታስቀራቸዋለህ። ወደ ተግባር ከተለወጠ በኋላ ግን ፀፀቱን ዕድሜ ልክህን ልትሸከመው ያዳግትሃል። እግዚአብሔር አምላክ "ይቅር እንድላችሁ ይቅር በሉ" ያለውን አትዘንጋ! እግዚአብሔር ይርዳህ!

  ReplyDelete
 9. I admire your patience. But try to understand why she became like this. She might not get what she wants. Sometimes we don't ...
  Abiy

  ReplyDelete
 10. Pray to get rid of this feeling.i am sure now you are feeling like your feeling will never be gone by any means.For sure this feeling comes from evil spirit and you can beat it with Holy Spirit.I had this kind of feeling for people who were not good to me.But with 'Mikire Niseha Ababat' I prayed and fast for a very short time and the bad feeling totally changed to a good thought.
  Believe in God, I am sure you will get rid of it.
  Selam lanite yihun

  ReplyDelete
 11. "አሁን ደግሞ ትዳሩንም ማፍረስና ተለያይቶ መኖርን እያሰብኩኝ ነው ግን ደግሞ በጣም ስለምወዳት ከእርስዋ መለየት ይጨንቀኛል" ጥያቂ ለባለ ጉዳዩ ወንድሜ
  1-ከወንድ ጋር ተኝታ ያየሃትን ሚስትህን " እውዳታለሁ ፤ ከእርስዋ መለየት ይጨንቀኛል" የምትል ከሆነ ማንን ሃጢአት ለማስገባት ነው ገመናዋን የምትናገር? እርስዋም ልበ ልፍስፍስ መሆንህን አዉቃ ነው የምትቀልድብህ ። ገና ብዙ .....
  2- ሚስትህን ለማስደሰት ብለህ ቤተሰቦችህን መራቅ ነበረብህ ? እግዚአብሄር ሲቆጣ በትር አያነሳም ይላሉ የእነሱ /የወላጆችህ/ ሃዝን ሊሆን ይችላል ብለህ ራስህን ጠይቀህ ታውቃለህ?
  ምክር- ሰውን ሲወዱ ከነ ንፍጡ ሲጠሉም ከነ ንፍጡ ነው እና እንዲህ አይነቷን ሚስት እውዳታለሁ ካልህ ትክሻህን ደልደል አድርገህ መቻል ነው። "ፍቅር" አይደል?
  ለዲ/ን ዳነኤል፦ የራሳቸውን ቤተሰቦች እንደፈለጉ እየረዱ የባልን ወይም የሚስትን ቤተስብ እንደ ጊንጥ የሚናደፉ ጨካኝ ሚስቶች/አብዛኞቹ/ ወይም ባሎች/አልፎ አልፎ/ ምን ትላለህ

  ReplyDelete
 12. ሠብለወንጌልFebruary 2, 2011 at 2:05 PM

  በርግጥ ከባድ ነገር ነዉ የደረሰብህ ገን ከታገግሱት እኮ ሁሉም ያልፋል እኔ የምመክርህ ነገር ቢኖር ይሄ አይነቱን ስሜት ለማሸነፍ መፍተሄዉ ወደ ገዳም ሂድና ለአንድ ሳምንት ሱባኤ ግባ እርገግጠኛ ነኝ በድል እንደመምተትወጣዉ
  እግዚአብሄር ካንተ ጋር ይሁን፡፡

  ReplyDelete
 13. +++
  በእውነት በምንም ዓይንና እንዴት ባለ አመለካከት እንየው በቃ ወንድማችን አቶ ገብረሥላሴ በወቅቱ ከአንድ እውነተኛ ክርስቲያንና የእግዚአብሔር ሰው የሚጠበቀውን ትዕግስት አድርገዋል፡፡ ይህ ደግሞ በዋነኝነት ከእግዚአብሔር ሲሰጥ እንጂ ከምንም የሚመጣ አይደለም፡፡ ሰው ሰውን ቢወደው ወይ ቢወደድ እግዚአብሔር የመውደድንም ይሁን የመወደድን ጸጋ ሞገስ ሲሰጥ ነው፡፡
  በቤተክርስቲያናችን ይቅርታ ከሁሉ በፊት ሁሉን ለማድረግ መፈጸም የሚገባን እንደሆን የማንደራደርበት ጉዳይ ነው፡፡ ‹‹አባታችን ሆይ…በደላችንን ሁሉ ይቅር በለን እኛም የበደሉንን ይቅር እንል ዘንድ…›› ከዚህ የዘወትር ጸሎታችን እኮ የምንረዳው ተበድሎ ይቅር ማለት ምንም መሆኑን ነው፡፡ ለእኛ የከበደብን አብዛኞቻችን ውሸታም የስም ክርስቲያኖች ስለሆንን ፣ የጋን ውስጥ መብራት ሆነን እንኳን ሰዎች የእኛን የትዳራችንን መልካምነት ፣ ይቅር ባይነታችንን አርአያ ሊያደርጉ ቀርቶ ‹‹ እርሱን/ሷን ብሎ ክርስቲያን..›› የምንባል አይደለንም፡፡ የወንድማችንም ትዕግስት የእውነተኛ ክርስቲያን ፍሬ ነው፡፡
  ‹‹የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።›› ገላትያ 5፡22
  እናውቀዋለን እኮ! ቅዱስ ዳዊት ጠላቱ ሳኦል ሊገድለው ባሳደደው ጊዜ…ሳኦልንም እግዚአብሔር በእጁ አሳልፎ ሰጥቶት ሳለ…እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጄን አላነሳም እንዳለ፡፡ ታዲያ ጠላትን መወደድ መገለጫው ይህ ሆኖ ሳለ ወዳጅ የነበረች የአካላችን ክፋይ እንድንወዳት ቃል የገባነው…ከአቅም በላይ የሆኑ ችግሮች እንኳን ሲፈጠሩ እንዲህ ያለውን ይቅርታ ማናችን እናደርገዋለን ? እጅግ ብዙዎቻችን ከዚህ ወገን አይደለንም፡፡
  እናም ወንድማችን ያደረጉት ትዕግስት ያሳዩት ስነ ምግባር በእውነት የሚደነቅ ነው፡፡ ነገር ግን ፍጻሜው መልካም እንዲሆን አብዝተው ሊተጉ ግድ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ጸጋ የሚገኝባቸውን መስመሮች ብንመለከት ወነኞቹ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያንን ስንፈጽም ነው፡፡ እነዚህም ምሥጢረ ጥምቀት በ40 በ80 ቀናችን ሀብተ ወልድ ስመ ክርስትናን ስንቀበል ፣ ምስጢረ ክህነት ክህነት ስንቀበል…ምሥጢረ ተክሊል - በተክሊል ስንጋባ ፣ ምስጢረ ንሥሐ - ሁሌም ከኃጢአት ስለማንጸዳ ንስሐ ስንገባ የምንፈጽመው እና ምሥጢረ ቁርባን - የሁሉ ማሰሪያ ከጌታችን ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት የምናደርግበት ነው፡፡ ይህን ሁሉ ያልኩበት ምክንያት በየደረጃው ጸጋ እግዚአብሔርን ስንቀበል ለቅጽበት የማያንቀላፋ ጠላታችን ዲያብሎስ ዝም ብሌ አያየንም ፤ እኛ ጸጋችን በተለያዩ መንፈሳዊ ፍሬዎች ሲበዛ እርሱ ደግሞ ጦሩን ይጨምራል ፣ ስልት ይቀይራል፡፡ ቀድሞ በትዳራችን ኑሮ ያለመሙላት ይፈትነን ከነበር ታግለን ስንሻሻል ፣ ድግሞ በቅናቱ ይፈትነናል ፤ ደግሞ እርስ በእርስ እንጋጭ ከነበረ እርሱን ስንፈታው ከቤተሰቦቻችን የምንጋጭበትን ክፋት ይጠነስሳል…ስንቱ ይነገራል (የዲያቢሎስ ውጊያዎች የሚለውን የአቡነ ሺኖዳ መጽሐፍን ያላነበብን እናንብበው ያነበብንም እንከልሰው) እናም ወንድማችን ከባዱን የይቅርታ በር ከፍተው ዲያብሎስን ድል ሲነሱት ፣ በታላቁ ጸጋ እግዚአብሔር ቅዱስ ቁርባን ሲያስሩት አጅሬ ዲያብሎስ ዝም ብሎ የሚያይ ይመስለናል ? በፍጹም! ሳይታክት እርሳቸውን ድል የሚነሳበትን መንገድ ያጠነጥናል እንጂ፡፡
  ስለዚህ ወንድማችን እኔ ይህን ማለት የሚገባኝ ብርቱ ሰው ባልሆንም እግዚአብሔር ባወቀ መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች
  ሀ. ከባለቤትዎት ጋር በመሆን አብዝታችሁ ቃለ እግዚአብሔርን መማር በንስሐ አባታችሁ በኩል ሊሆን ይችላል ፣ እነ ዲ. ዳንኤል ክብረትንና የመሳሰሉ ሰዎችን በማግኘት ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም ቃለ እግዚአብሔር በማንም እንዴትም ሆኖ ይነገር ትክክለኛውና ከምንጩ ከሆን መጽናናትን ይሰጣል ፤ ዲያብሎስን ድል መንሻ ይሆናል ፤ ለጸሎት ፣ ለበጎ ምግባር እና ለትሩፋት ያነሳሳል እንድንፈጽም ያደርገናል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው በተጨማሪማ ባለዎት ጊዜ ሁሉ መንፈሳዊ መጸሐፍትን ቢያነቡ ቢቻልዎ ደግሞ ከእጅዎት በምንም መልኩ መንፈሳዊ መጽሐፍትን አይለዩ ፤ ያልሆነ ሀሳብ በመጣ ጊዜ ገልጠው ያነቧቸዋልና…
  ለ. ንስሐን በተቻሎት ጊዜ የዘወትር ተግባር ማድረግ ፤ ላይመቻች ይችላል ግን አባቶቻችን እግዚአብሔር ይፍታህ ሲሉን ‹‹…በኀልዮ (በማሰብ) ፣ በነቢብ (በመናገር) ፣ በገቢር (በመሥራት) ከሠራነው ኃጢአት ሁሉ እግዚአብሔር ይፍታ›› እንደሚሉን ፣ ወንድማችን አሁን ጠላታችን እየፈተኑ ያሉት በኀልዮ (በማሰብ) ነውና ሀሳቡ ወደ ንግግር ፣ ንግግሩም ወደ ተግባር እንዳይለወጥ ዘወትር ንስሐ መግባቱ ትልቅ በር መዝጊያ ነው፡፡
  ሐ. በቅዱስ ቁርባን ያተሙትን የይቅርታ በር አሁንም ለማጽናት ቅዱስ ቁርባንን ከንስሐ አባታችሁ ጋር በመመካከር በተወሰነ ጊዜ ብትቄርቡ
  መ. አቅደው በሚመች መልኩ እና በመመካከር ፣ አስፈላጊ ከሆነም ንስሐ አባትዎን በማሳተፍ ገዳማትን ወጣ ብላችሁ ብትሳለሙ (አዲስ አበባ ከሆነ ያሉት እንደ እነ ደብረ ሊባኖስ ፣ ወጨጫ ማርያም ፣ አንጦጦ ማርያም ፣ አዳዲ ማርያም…) ይህም ለመንፈስም ለሥጋም ማረፊያና መጽናኛ ናቸውና፡፡ ልክ ሞባይላችን ባትሪው ሲደክም ቻርጅ እንደምናደርገው ፣ ሕይወታችን ሲዝልብን ማጽኛዎች ይሆኑናል፡፡
  መ. መጪው ወቅትም የጾም ስለሆነ አምላካችን እንዳስተማረን ‹‹…ይህ ፈጽሞ ከጾምና ከጸሎት በቀር አይወጣም…›› እንዳለው መታገል ያስፈልጋል፡፡
  ሌላው ፈተና ከእሩቅ አይመጣም ፣ ከሚስት ወይ ከባል ፣ ካልሆነም ከቤተሰቦቻችን ፣ ካለፈም ከወዳጆቻችን… ስለዚህ ቤተሰብዎት ጋር ያለውን ክፍተት ለመሙላት በጸሎት ከማሰብም ጀምሮ ተግባራዊ የሆኑ እርምጃዎችን መሞከር ያስፈልጋል፡፡ በመጽሐፈ ሲራክ ‹‹…የእናት እርግማን መሠረትን ይነቅላል …›› እንዲል ቤተሰብዎት በእርሶ አዝነው እንሆነም እርሶም ይቅርታ ማለት ይኖርቦታል፡፡ በተቻል ይህን ክፍተት ለመሙላ ይሞክሩት እርሶም በልጆችዎት የሚቀበሉትን ፍዳ ያርቁ ዘንድ
  እንግዲህ ከማንምና ከምንም በላይ እግዚአብሔር ያበረታው ልቡና ፣ ያጸናው ልቡና መሠረቱ በአምላኩ ነውና እርሶም ከማንም በላይ መታመኖት ፣ የመኖርዎት ምሥጢር በእግዚአብሔር ላይ ይሁን፡፡ ርህርተ ኅሊና እመቤታችንንም አብዝተው ይለምኗት ፣ ያልቅሱባት…ስለነፍስ ብለው፡፡ የሥጋችን ጉዳት ነፍሳችንንም ስለሚያጠፋት፡፡
  በተረፈ ነገር ቢያበዙት በአህያ አይጫንም እና የሁላችን እናት እመ ብርሃን ጽናቱን ብርታቱት ታድልዎት፡፡ ስለ እኛ ዘወትር ታነባለች እና የእርሷ አማላጅነት የእርስዎን የቤተሰብዎን ፍጻሜ ያሳምርልዎት፡፡
  ደግሞም አይፍሩ አይጨነቁ በእውነት ይህን ያህል ያበረታዎት አምላክ ይረሳዎት ይመስልዎታል ? በፍጹም እርስዎ ብቻ ልቦናዎትን ያጽኑ፡፡
  ‹‹..እመቤቴ ሆይ ሰይጣን ማስፈራራቱን አብዝቶታል ፤ አባክሽን ድምጽሽን አሰሚው…›› አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
  ዘደብረ ካራን
  +++

  ReplyDelete
 14. According to my view, the problem can be arose from two sourse, if the couple really loves each other, he/she concerns about her/him, not himself/herself. This is the principles in Christianity. No haters has places in this true love. According to Dn Birhanu Admase's (Tmiherete Haimanot ze gibi gubae),"Fikre malet yegodelen memulat newe". If it is so each of the couples never be selfish. Each of them always concern the happiness of the other. This is the first thing that the true christian life definitely makes the marriage peaceful and lovable. The other thing is illiteracy. I believe that at least education can change our way of thinking in many aspects including our social life's including marriage. The saying "Yetemare yigdelegn" can be seen in this aspects for the ability to solve problems and the wisdom to live in society. Lehulum Egziabhere libona siset newna Libona yisten. Thank you Dn. Dani.

  ReplyDelete
 15. "..ጨካኞች ሚስቶች/አብዛኞች/ ወይም ባሎች/አልፎ አልፎ.." ያልከው ሰው.. በህይወትህ አንዳች ትዕግስት የሚያስጨርስ መከራ ያለፈብህ ይመስላል ለምን ያንተን ጉዳት አውጥተህ አትናገርም? አንዳንዴ እኮ መናገር መፍትሔ ያመጣል....ብቻውን ከራሱ ጋር የሚያወራ ሰው ብዙ ጊዜ ወደ በቀል ወይም ሰው ወደመጥላት ይደርሳል ወይም ደግሞ አንተ እንደገለጽከው አብዛኞች....ሰዎች እያለ ሰዎችን መውቀስ ይመርጣል። ሰዎ ሁሉ ዋሾ አደለም፣ ሰዎ ሁሉ ጥሩ አደለም፣ ውይም መጥፎ..ግን ትዳር ማለት የምንሰራው የምናሳድገው የምንንከባከበው ነገር ነው። መንከባከብ እንዳለባቸው ሳያቁ ቦታ ያልሰጡት ሰዎች። ከጥፋት በኃላ ይነቃሉ ያኔ ትዳራቸውን ለማዳን ይጥራሉ። የወንድማችንም ጥረት ይህ የመስለኛል።

  ReplyDelete
 16. Did you give her enough time? Do guys communicate each other? Not only the communicatoin of social life but also your relationship in sex. IF so, how?

  ReplyDelete
 17. Dear Daniel

  selam endet neh ..eyerusalem temtalh beye eytebekhu new.. ---but

  I think you lost control of your blog after you changed it to such type discussions. It contradicts the objective of your blog.
  It is better to direct it to any other blog or create similar for these articles. Other wise you loose me in a very short time.

  thank you

  Solomon D

  ReplyDelete
 18. የሰው ልጅ ፈተናው ብዛቱ ይገርማል እኛ ሚስት አጥተን እንሰቃያለን ሌላው ደሞ ሌላ...ወንድሜ ገ/ስላሴ ብርቱ ሰው ብርቱ ክርስቲያን ነህ ብዙ ፀጋ እንዳለህ ይታየኛል አንተ የሚያስፈልግህ እርዳታ ብቻ ነው ያልታየህን የሚያሳይህ ጉድለትህን የሚሞላልህ እንዲህ አይነት እርዳታዎች ደግሞ ሁሌ ከነፍስ አባት ብቻ አይገኙም የአለም ነገርና የሰው ፀባይ ከገባቸው ሰዎችም ጭምር ነው ለምሳሌ የስነልቦና ምሁራን አስተዋይ የእድሜ ባለፀጎች እንዲህ አይነት የመወያያ መድረኮች...ናቸው ያንተ ችግር ነው ብዬ የምለው ልክ የሌለው፣ ማስተዋልና፣ ግራና ቀኝ ማየት የከለከለህ ለሷ ያለህ ፍቅርና፣ በዚህም ምክንያት ፍቅር እና እሷን ብቻ መፍራት፣ ለእሷ ብቻ መንቀጥቀጥ እንጂ በመግባባትና በእኩል መንፈስ ሁሉን ነገር ልኩን ልክ ስህተቱን ስህተት እየተባባላችሁ የመነጋገር ህይወት በመካከላችሁ አለመኖሩ ነው። እሷም ደግሞ ያለህን ፍቅር ስለምታውቅ በግድየለሽነት ተጠቀመችብህ እርሷ ብቻ መጥፎ ሆና ሳይሆን ያንተ በእሷ ፍቅር መገዛት/ የፍቅር ህይወታችሁን ማኔጅ ማድረግ ያለመቻል/ ፈተና ሆኗት ተሸንፋ ነው። እስኪ አስብ ለሷ ያለህ ፍቅር እንዳለ ሆኖ ፍቅር አገላለፅህን በተቃራኒ በአግባቡ ቢሆን የሚኖራችሁን እፁብ ህይወት አስብ። ይገርምሀል እኔ እንደታዘብኩት ሁለት አንዱ ያለውን በርሜል ሙሉ ፍቅር ባንድ ሌሊት እግሯ ላይ በሚዘረግፍ እና ሌላው ያለውን በርሜል ሙሉ ፍቅር እያሰበ እየመጠነ እየቀዳ እየቀዳ በሚያቀርብ/ሴቷ ለወንዱም ሊሆን ይችላል/ አፍቃሪዎች መካከል ያለ ልዩነት ስለእውነት እንደ ገነትና ሲኦል መሆኑን ነው። ይገርማል። ስለዚህ ፍቅርህን በአግባቡ አድርገው በፍቅር ጎርፍ ከምትጠቃብህ መዘርገፍህን አቁም እና ያለህን በርሜል ፍቅር እየመጠንክ እየቀዳህ አጠጣት። ሌላው ለጥሩ ነገር አይመሽም ይባላል እና ተግባቡ ተወያዩ አናግራት ከንሰሀ ከይቅርታ ከፀፀት ባሻገር እንደውይይት አይነት በዝርዝር ስላለፈውም ስላሁኑም ተወያዩ አንተም የልብህን በውይይት መልክ ተናገር እሷም በጥፋቷ ሳትሸማቀቅ ዘና ብላ የሚሰማትን ትናገር ተወያዩ እርስ በእርስ ስትነጋገሩ ያልተሰማማችሁትን ሁሉ አውጥታችሁ አንተ በፍቅር ሳትታወር ሳትሳሳላት ስት ወ ያ ዩ ስለልጁም ጭምር ያኔ ይወጣልሀል። ከዛ ውጭ ስለንስሀህ ስለስጋወደሙ መቀበላችሁ ስለይቅርታችሁ ፈፅሞ አትፀፀት ይልቁንም እግዚአብሄርን አመስግን። ከሰይጣን ዋነኛ ትጋቶቹ አንዳንዶቹ መጀመሪያ እኛን በሀጥያት ካምላክ መለየት ንስሀም እንዳንገባ ማፍዘዝ ብንገባም ተስፋ ማስቆረጥ አለመርካትን የሚያመጡ ሀሳቦችን ማምጣት ወደሁዋላ ማሳየት በበጎ ስራ ፀፀት ማሳደር...ናቸው። ያገኘኸው ህይወት ነውና ባደረግከው በጎ ስራ ተደሰት እግዚአብሄርን አመስግን። ይቅር በማለትህ ስጋና ደሙን በመቀበልህ ለአካልህ ለሚስትህ ሁለተኛ እድል በመስጠትህ የቅድስናን ህይወት አግኝተሀል ነገደ መላእክት ተደስተው በእግዚአብሔር ፊትና በኑሮዋችሁ ውስጥ እየዘመሩ ነው ከእግዚአብሔር ጋራም እየኖርክ ነውና ምን አጥተህ ትፀፀታለህ በረከትህ አልታይህ ብሎህ እንጂ። አንተ ብርቱ ሰው አይዞህ ብቻ ብልህነትን አብዛ እንጂ ምንም አትል። የቅዱሳን አምላክ ሥሉስ ቅዱስ ፀጋህን ያብዛልህ። በስጋውና በደሙ ያከበራችሁ የይቅርታ ጌታ መድሀኒተ አለም ኢየሱስ ክርስቶስ ከፈተና ይጠብቃችሁ ማስተዋልና ጥበቡን ይስጣችሁ።
  አንድ ጥያቄ ለዲ.ዳንኤል በመጀመሪያ አንተንና መሰል አገልጋዮችን ሀብት ሰጥቶ ህዝቦቹን ለሚያንጽ ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይግባው። ጥያቄዬ ለምን አንዳች የተሰማህን አስተያየት አውጥተህ የኔንና የመሰሎቼን ችግር ለውይይትና ለመፍትሄ ሀሳብ አታቀርበውም እንዲህ ነው ነገሩ ምኖረው ነጮቹ አገር ነው እድሜዬ ሳላውቀው 40 ገባ/ በደንብ የገባኝ ለት የደነገጥኩትን መደንገጥ አትጠይቀኝ/ የረባ የፍቅር ህይወት ኖሮኝ አያውቅም ያልረባ ግን ነበረኝ በወኔ እና በራስ መተማመን እጦት የሚሰማኝን ሳልነግራት ዝም ብዬ ለብዙ አመታት በፍቅር እቃጠል የነበረውን ማለቴ ነው/ፍቅር ከተባለ/። መፅናት እያቃተኝ በዝሙት የወደቅኩበት ጊዜያት እንዳሉ ሆነው ማለት ነው። አቃተኝ እንጂ እኔ የምፈልገው እንደቤተክርስቲያን ልጅነቴ ቃሉን ስጠጣ እንደመኖሬ በጋብቻ ተወስኜ እንደ ጌታ ቃል መኖር ነበረ። አንዳንዴ እድል እንጂ ዘዴም ምክርም የለውም ብዬ ስለማስብ ከሰው ጋር አላወራውም። አምጨ አምጨ እቺ መሆን አለባት ያልኳት ወይ ጣቷ ላይ ቀለበት አላት ወይ እንዲህ ባትሆን ኖሮ የምለው ነገር አላጣም። ከዚሁ አገር ሚስት ለማግኘት ምን ላድርግ? ወይስ አገር ቤት ሄጄ የማላውቃትን ላግባ?ድንገት የኔ አይነት ችግር ያለባቸው ካሉ /መቼስ ብቻዬን አልተፈጠርኩኝ/ እንማርበታለንና እባክህ? የእህቶቻችንስ ችግር ሳይሆን ይቀራል ብለህ ነው? ቢያንስ ቢያንስ የኔዋ አጥንት ችግር ነው። አጥንቴን ፍለጋ ያለብኝን ስቃይ አታውቅ።ይገርማል እህቶች ሳይጠፉ 40 ዘመን።
  ሰላም ሁን።

  ReplyDelete
 19. specialy wonem are not free to discuses abut sexual life.I think you should discuse about it.I was reading all comenet ,it is nice comment please keep it for your future lif
  you are a winer regardenes of God.My husbuned did the same thing to me but I forgive him but I do not forget it.This is commene also I am not the one biteryed him so I am happy .
  The person who did it never forget what he did .Please keep your hoppyness for your fmely.

  ReplyDelete
 20. በሚድን ምክንያት ጋብቻ አይፍረስ::

  I appreciate you for what you did.

  I am not sure if I am in a mood to express my feeling. let me start from the reason which makes you to feel revenge, in my suggestion.
  You are feeling revenge because you are considering her "bad action" as the biggest of all sin. But it is only one of the sin.
  Second please why you memorize it? ለምን ደጋግመህ ታስበዋለህ? Of course it is difficult to forget while you are seeing the action live. But after that just you gave them your forgiveness. That means you gave your forgiveness for the sack of goodness, it is not for evil. It is not to postpone your revenge.በደሉን ለመርሳት አብራችሁ( ከባለቤትህ ጋር) ተዝናኑ:: አብራችሁ ብዙ ግዜ በመዝናናት አሳልፉ::
  Third you did a great thing. It may be rare to found a type of person who can do like what you did. But after that, you are regretting why you did forgiveness. Look, if you are regretful for being good, what you will do after your revenge? ጥሩ ነገር ሰርተህ ጸጸት ከተሰማህ በደል ብታደርስ ምን እንደሚሰማህ ገምት?In my opinion you may be insane after revenge. So just accepting the reality will result in a happy life. But going for the revenge will add your regret and increase your discomfort, It will put you in a long lasting suffer and regret. Look if you forget the case, it has an end. But if you go for revenge, you will not get an action which gives you satisfaction. So why?

  The other big thing here is your babies. Even me I suffered being with a step mother and step father.My families are separated while I was about 2 year young. When I feel my dad, they take me to his place and when I feel my mama they take me to her. While I was baby, it was good for me. But after the age of 7, things has got worst. Oh, my God. I suffered a lot, only me and GOD knows what I suffered. But it was not only me who suffered; both my father and my mama did. Never separation for those who delivered a baby, as long as possible.
  Look, I was a cleaver student. But I did not feel like I am an important person. If I went to my mama, my step father is not favoring (he doesn’t scarify) for my life. If I went to my dad, my step Mather even can't arrange a wash of my cloths.
  But at last I feel like I am lonely and I developed a feeling of less important person for the society. Even my feeling for my families got deteriorated, I start to think why they separated while they have baby that is me!!! If they had a feeling for me, they may discuss and reconcile their conflicts for the sack of me. But they separated.
  Even after I joined the universality, I just go to church and pray to GOD. I was not feeling any family business. Now I am 27 years, but still I am not feeling to make family.

  Even I am not visiting neither of them. Just I drop some money to them and their sons & daughters, my have brothers & sisters. Look I had not grown up with any of them, how can feel as I have a brother or sister, they are just sons and daughters of my families.
  These all happened on me because of my non-responsible families. Dear owner of the story, what will be the life of your babies? you are in hurry to put you self in prison and you may do something on your wife, then your babies will go to street. Are you feeling these?
  By the way I only try to tell you my life experience. I am not good in teaching the bible word, but it is my blood and heart. St Mary, the mother of Jesus, in her holiness let she avoid all your evil thoughts and let she reminds what you did when you back at that bad night.

  ReplyDelete
 21. bewnet lemenager grum,denk tigest kewnetegn crstian yemitebek .egziaber yebarkih,gen yehin yadereg diablos mehonnun atzenga,tefetenk alfahal temelseh lemewdek wedehuala atimelket.saytan yasebew slaltesaka bizu neger yasasebhal ante gen selalefew chersah ataseb yalefew alfual selemimetaw aseb yehen bemareghtewodesh enge altenakhim wodiawm degmo tsadik be hatiategn yefetenal yemilewn asib.yemebetachen amalaginet ayeleyh egziabher kefetena yawtah.

  ReplyDelete
 22. aye Gebre Selasse, in short you r a big coward and a loser at the same time. you may be sexually incompetent that she played all this stupid game in ur life. gura endaymeslbgn enji setin megzat yichalal. kibruan tebko gin degmo belik endtadir madreg yichalal. betesebnm enderasua sewoch endtakebr madreg kebad aydelem. but u missed the point. She shared your bed with a relative to fill that gap. ur view is confusing. I still love here you said. For me that implies u r a loser, coward, and out of a gut....

  ReplyDelete
 23. Do you know the starting point to all of it is you, you are so week you can not manage your wife, love does not mean becoming meaningless, you have to teach her how mach she betrayed you, do not revenge both of them simply teaches her.

  ReplyDelete
 24. ወንድሜ ገ/ስላሴ ሰይጣን የሚውጠውን ፍለጋ በደጅ እያንዣበበ ነውና አደራህን አደራህን በርታ አሁን እኮ ሁሉም ነገር አብቅቷል፡፡የድል አክሊልም ተዘጋጅቶልሃል፡፡አንተ ደግሞ የጌታ ልጅ ነህና ክርስቶስ የደረሰበትን አስብ ያደረገውንም ትእግስት አስብ ሰውን ይቅር ማለት ከ ጌታ ነው ሰውን ለመበቀል ማሰብ ደግሞ የዲያብሎስ ነው፡፡
  አንተስ ብዙውን ፈተና አልፈህ ትዳሩንም ይዘኸው ነው በሱም ትጽናናለህ ስንቶች እህቶች ነን የክርስቶስን ስም በሚጠሩና ክርስትያን በሚመስሉ አስመሳይ ወንድሞች ክህደት ከክብራችን አንሰን ከምንም ሳንሆን ሁሉን ለእርሱ ሰተን እያለቀስን በቤታችን ያለን እና በክርስትና እየበረታን በሄድን ቁጥር አምላክ ወደኛ ስለሚመለከት ሴይጣን ሁል ግዜ ክስ ስለሚያበዛብን አምላክ በኛ በመተማመን(እዮብን ማየት ይቻላል)ወደኛ ሊልከው ይችላልና ወደ ክፉ ውሳኔ ከመሄድ ይልቅ ሰይጣንን በማሳፈርህ እናም በማሸነፍህ ደስ እያለህ መኖር እንጂ እርፍ ጨብጦ ወደ ኋላ የለምና በጀመርከው ጥንካሬ ወደፊት መቀጠል ይኖርብሃል፡፡አንተ አንድ ግዜ ይቅር በማለትህና በማለፍህ አይግረምህ 7x70 አይደል የሚለው እና ወንድሜ በበቀል ወደባሰ ችግር የገባ እንጂ እፎይ ያለ አላየሁምና በትግስትህና በጸሎት በርታ ሊነጋ ሲል ይጨልማል፤፤ሁሉን ልታሸንፍ ስትል ዲያብሎስ የበቀል መንፈስ ላከብህ እናም እንቢ በለው ያኔ ካንተ ይርቃለ፡፡
  ወላዲተ አምላክ ትርዳህ፡፡
  ፍቅርተ ማርያም
  ከአዋሳ ደ/ም/ቅ/ገብርኤል ገዳም

  ReplyDelete
 25. Full Egxeyabher yebarkeh..le አንተ ደግሞ የጌታ ልጅ ነህና ክርስቶስ የደረሰበትን አስብ ያደረገውንም ትእግስት አስብ ሰውን ይቅር ማለት ከ ጌታ ነው ሰውን ለመበቀል ማሰብ ደግሞ የዲያብሎስ ነው፡፡

  ReplyDelete
 26. በፍክር አልፈርድም ፍክር ሀያል ነዉ ግን ብዙ በመለያይ ታሪክ በይኖረኝም የምትወደው ሰዉ ሲበድለህ ያህል ምራራ በድል ግን በጣም ይሰማል ለዛዉም ቅድስ ትዳር ! እዉንት እዉንተ ከዛም ከዚም በማይት ብትዳርህም ሆነ በህይዎትህ ክምትመስቃቀል ያኔድሮ ብትወስን ጥሩ ነበር ግነ እኔ ምለዉ እንደዉ ድፈረተዋ አሰደንግጡዋት ነዉ ይቅርታ ያለችህ ወይስ ከልበዋ ይመስልሀል! እኔግን ሴትን መመን ገም መዝገን ከሚሉት ነኝ በተጨባጭ ይተለየ የባህሬ ለዉጥና የመጸጸት ስሜት ካለይህ በቸ ምን አለፋሀ መጥፎ እለመክረህም ግን እስረ ገዜ ለካ እንዴ ቅረጥ ስወ በ ስዉ ገወደኛም በግደኛ ሴትም በ ሴት ይተካል ሀለም ያልፋል! ጊዜሀንም አታበክን! ባለቤትህንም እንተንም ልቦና ይስጥልን እግዚአብሄር ይርዳን!አሜነ!

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንዴ ይቅርታ ካደረግህ ሁሉን ነገር ለእግዚአብሄር መስጠት ነው።በተለይ በስጋ ወደሙ ከተወሰናችሁ ይህን ማሰብ ቂም በቀል መያዝ አይገባም።እግዚአብሄር ትዳርህን ይባርክ።

   Delete