Monday, January 31, 2011

የኔን ሕይወት ምን ትሉታላችሁ


ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት

ይህን ጽሁፍ ያነበብኩት ጓደኛዬ ፎርዋርድ አድርጋልኝ ነው፡፡ የኔን ሕይወት ስለምታውቅ ነው ፎርዋርድ ያደረገችልኝ፡፡ ከዚያ በኋላ ይህንን ጽሁፍ ከብሎጉ ሄጄ አየሁት፡፡ የሰዎችን አስተያየትም አየሁ፡፡ አንዳንዶቹ የኔን መሰል ሕይወት ስላልገጠማቸው ነው እንዲያ ያለ ሃሳብ የሰጡት ብዬ አሰብኩ፡፡

ብዙ አስተያየት ሰጭዎች ያቀረብከውን ሃሳብ የተረዱት አይመስልም፡፡ እኔ ግን ደርሶብኛልና ይገባኛል፡፡ እኔ በአንድ አለም አቀፍ ድርጅት በሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰርነት እሠራለሁ፡፡ ካገባሁ ስድስት ዓመት ሲሆን የሁለት ልጆች እናት ነኝ፡፡

ከባለቤቴ ጋር ስንጋባ በጣም ተዋድደን ነው፡፡ ጥሩ ጠባይም ነበረው፡፡ እርሱ ነጋዴ እኔ ሠራተኛ ነበርን፡፡ ከተጋባን ከዓመት በኋላ ጠባዩ ተቀየረ፡፡ መሳደብ፣ ማመናጨቅ፣ አልፎ አልፎም መማታት አመጣ፡፡ ታገሥኩት በጓደኞቹም አስመከርኩት፡፡ የንስሐ አባታችንም መከሩት፡፡ እየባሰበት እንጂ እየተሻሻለ አልመጣም፡፡

ጓደኞቹ እና የኔ ጓደኞች እንዲህ ብታደርጊ፣ እንዲያ ብታደርጊ እያሉ የነገሩኝን ሁሉ ባለማሰለስ አደረግኩት፡፡ ለርሱ ጊዜ መለስጠት፣ አብሬው ለመሆን፤ የሚፈልገውን ዓይነት ምግብ ለመሥራት፣ ከሥራ ሲመጣ አምሬ ተውቤ ለመቅረብ ሁሉ ሞከርኩ፡፡

እንጦጦ ኪዳነ ምህረት በሄድኩ ቁጥር ጸሎቴ የቤታችን ጉዳይ ነበር፡፡ ልጆቼም ተማረሩ፡፡ የኔ እና የርሱ መጣላት የልጆቼን ህይወት በጠበጠው፡፡ ወላጆቼም በየጊዜው የኔን ልቅሶ መስማት ሰለቻቸው፡፡

ይመታኛል፡፡ አንዳንዴም ሲመታኝ ያድራል፡፡ ፊቴ አብጦ፣ የጥፊ ሰንበር ተሠምሮበት ቢሮ መግባት ሁሌ ያሰቅቀኛል፡፡ አለቆቼ እና ጓደኞቼ ሲጠይቁኝ መመለስ ሰለቸኝ፡፡ ሚዲያ ፊት በዚያ አይነት ስሜት እና ገጽታ መቅረቡ አሳፈረኝ፡፡

በተለይ አንድ ቀን የአበባ ማስቀመጫውን አንሥቶ ወርውሮ ፊቴን ገመሰው፡፡ ደም በደም ሆንኩ፡፡ ሐኪም ቤት ሄጄ ታክሜ ስመጣ ፊቴ ሁሉ ተለጣጥፎ ነበር፡፡ የሚገርመው ነገር በማግሥቱ ከአለም አቀፍ ሚዲያዎች ጋር ቃለ መጠይቅ ነበረኝ፡፡ ምን ልሁን? ቀጠሮውን ስሰርዝስ ለአለቃዬ ምን ልበለው?

በመጨረሻ ለአለቃዬ እያለቀስኩ ነገርኩት፡፡ አለቃዬ በጣም አዘነ፡፡ ጉዳዩ ካለፈ በኋላ የሚሠራበት ቦታ ሄዶ አናገረው፡፡ የሚገርምህ እርሱን ሰድቦ መለሰው፡፡ የንስሐ አባታችንንም ሰደባቸው፡፡ በመጨረሻ መረረኝ፡፡ ልጆቼ አባታቸውን ለማየት ተሰቀቁ፡፡

በዚህ ሁኔታ ከቀጠልኩ ሕይወቴ መበላሸቱ ነው፡፡ ይህ ሰው ያመነዝራል ብዬ ልናገርለት የምችል ሰው አይደለም፡፡ ነገር ግን ቀስ በቀስ እየገደለኝ ነው፡፡ እናም ለመለያየት ወሰንኩ፡፡ ያልሞከርኩት አማራጭ አልነበረም፡፡ ሁሉንም ግን እምቢ አለ፡፡ በፍርድ ቤት ፍቺውን አደረግኩት፡፡

አንድ ቀን ከመሥሪያ ቤቴ አምሽቼ መጥቼ የግቢዬን በር አስከፍቼ ስገባ ጥይት ተተኮሰ፡፡ በተከታታይ ሦስት ጥይት ነው የተተኮሰው፡፡ እግዜር ረድቶኝ እግሬን ሥጋ ለሥጋ ሄዶ ብቻ አቆሰለኝ፡፡ በአካባቢው ፖሊስ ስለነበር ተሯሩጠው ማሰስ ሲጀምሩ አንድ ሰው መኪናውን አስነስቶ ሲሄድ ተከተሉት፡፡ በመጨረሻ ሲያዝ ባለቤቴ ነበር፡፡

አሁን ተለያይተናል፡፡ እርሱም ተፈርዶበት ወኅኒ ቤት ነው፡፡ ለልጆቼ እና ለእኔ እሠጋለሁ፡፡ አንዷ ሴት ልጄ እድሜዋ አምስት አመት ነው፡፡ በቀደም እኔ ባል ማግባት አልፈልግም፡፡ እንደ እናቴ ያሰቃየኛል አለች ብላ ሠራተኛዬ ነገረችኝ፡፡

አሁን እኔ ምን ማድረግ እችል ነበር? ካለ ዝሙት መለያዬት አይቻልም በሚለው ሕግስ እኔ እዬሞትኩ መቀጠል ነበረብኝ? የልጆቼስ እጣ ፈንታ ምን ይሆን ነበር? የዚያ ትዳር ጠባሳው ፊቴ ላይ እና እግሬ ላይ አለ፡፡ ይህንን ያህል መከራ ከምንቀባበል፤ ዳንኤል እንዳለው አብረን ለመኖር ካልቻልን፤ ሕይወት የሚያጠፋ ነገር ከማድረግ መለየቱን እመርጣለሁ፡፡ ምክራችሁን እጠብቃለሁ፡፡

/ አዲስ አበባ

34 comments:

 1. Wow. I hope he regret well at some point and time in his life or he is dade for good. Here I am not judging but most of the time that is what happen. I hope people won't say this and that to make you feel guilty. God is a God who understand once situation in life. You did all the right thing. Your next step will be recovering the young minds. Children are very susceptible for fracture so you have to give them a confidence with God. Tell them stories that are in the Bible where a person went through vast amount of hard ship only to harvest the sweetness of life. Teach them to accept their dad for who he is. Tell them what happened is between you to guys. Teach them how to love. Through love comes the grace of God. Show them the world is full of hardship and everyone gets it on their own way. Make them spend some times with homeless kids so they can understand their are people who are having it even harder. Then they will just accept the situation as one occurrence in life not something that makes them feel like it is the end of the world. pray for him as a family and personally. One it is the right thing to do, second it will help you recover sooner. I wish well. God be with you.

  ReplyDelete
 2. 'aye meret yal sew'

  ReplyDelete
 3. 1. Was Your marriage in 'KIDUS KURBAN AND/OR TEKLILE?

  2. If so did you (both wife and husband) continue in the spiritual road.... was the life TSOM, TSELOT, MIGBAR in your life????

  ende ene ende ene ... ende Dn. Daniel yalu yewongel memehran endi yalu temhretochen bayaberetatu tiru new, ... coz there will be a risk of misconception ... ye egna hiwot enquanes zenbobesh endiaym teza nesh newna.... meleyayet tiru new yemibalew hasab endiseresen ketefelegem betidar misale baydereg tiru new... endi yalu liberal amelekaketoch yemiyadersun zare ye western world kederesebet ziktet new biye asebalew

  ReplyDelete
 4. so sad to read such things any ways may GOD WILL GIVE YOU THE STRENGHT TO OVERCOME ALL THE OBSTACLES.

  ReplyDelete
 5. በእውነት ልብ የሚነካ ነው፡፡ እግዚአብሔር ባወቀ እንዲህ ባለው ለመንፈሳዊም ለሥጋዊም ሕይወት መከራ እና ጭንቅ በሆነ ሁኔታ እንድንኖር የአምላካችን ፈቃዱ አይመስለኝም፡፡ ይልቁንም ፍቺ የተፈቀደው በዝሙት ምክንያት ብቻ እንደሆን ነው ብለን ምክንያቱን ብቻ ማገንዘቡ በቂ አይመስለኝም፡፡
  ብዙዎቻችን የጓደኝነት ሕይወትን ስንመሠርት የነበረን ከዚያም ስንጋባ የሚኖረን ፍቅር ፣ ሰላም፣ መልካምነት ፣ መንፈሳዊነት ፣ በጎነት ፣ ቅንነት … አብሮን ለመዝለቁ ምን ያህል እርግጠኞች ነን ? ይህ ነው ትልቁ ጥያቄ ፤ ሁልጊዜ አካላችን ብቻ ሳይሆን ልቦናችንም ከእግዚአብሔር ጋር እንደሆነ ማስተዋልና ማረጋገጥ ካልቻልን ያን ጊዜ ያላሰብናቸው ፣ ያልጠበቅናቸው ፣ እንግዳ የሆኑ ባሕርያት ይመጣሉ፡፡ ታዲያ ይህ እንዲያው የሚመጣ አይደለም፡፡
  ‹‹ባልና ሚስት ለጸሎት አብረው መቆም ሲተዉ ያን ጊዜ ልባቸው መለያየት እየጀመረ ነው›› በሌላ ገጹም ብንመለከተው ተመሳሳይ ነው፡፡ ባለትዳሮች ድሮ የነበራቸውን መተሳሰብ ፣ መፋቀር…እየተሸረሸረ ከሄደ ያን ጌዜ የተደበቀ ችግር እንዳለ ማስተዋል ያሻናል፡፡ ምክንያቱም ግጭቶች ፣ አለመስማማቶች … በትዳር ውስጥ ብቻ አይደለም በየትኛውም የሕወታችን ጉዞዎች የሚኖሩ ፣ ልናስወግዳቸው ፈጽሞ የማንችለው ነገር ግን ልንቀንሳቸው ብሎም አቅማችን እስከፈቀደ ልንታገሳቸው እንችል ይሆናል፡፡

  በባለ ትዳሮች መካከል ያለውን ልዩ የሚያደርገው ግን እንደሌላው ተወዋ/ተይዋ የምንለው አለመሆኑ፡፡ የሚከፈልለት መስዋዕት እንዲህ በቀላል የምናወራው አለመሆኑ ነው፡፡ ከባድ ነው፡፡ እህታችን የከፈለችው መስዋዕትነት እጅግ ከባድ ነው ፤ በዚህ ዘመን እንዲህ ታጋሽ ሆኖ ስለ ትዳሩ መስዋዕት የሚሆን በጣም አናሳ እንደሚሆን ስላማስብ፡፡ መቼም ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው እንዲባል ፣ በእውነት ርዕሰ ጉዳዩን ዲ. ዳንኤል ክብረት ስላነሳው ብቻ ሳይሆን እሰኪ ያገባንም ራሳችንን በዚህ ሚዛን ላይ እናስቀምጠው ፤ ያላገባንም ደረጃ በደረጃ በኅሊናችን እንሳለውና ይህ ሁሉ መከራና ፈተና ሲደርስብን ምን ይሆን የምናደርገው፡፡ እህታችን እኮ ይህን ሁሉ መስዋዕትነት የከፈለችው እርሷ ስለሆነች ነው ፤ እንደ ቀደሙት እንደ እናቶቻችን ፤ ትዳሬን ማትረፍ ቢቻለኝ ብላ ፣ ለልጆቼ ብላ እንጂ የዚህ ዘመን ሰዎች ጽናቱ አለን ወይ ? መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን ወይ ? ስለዚህ ርዕሰ ጉዳዩ በእውነት ሊነሳ የሚገባ ነው፡፡ ምክንያቱ ችግሩ በደንብ የተብላላለት ርዕሰ ጉዳይ ሃምሳ እጁ መፍትሔ እንዳገኘ ያህል ስለሚቆጥር ችግሩን ማወቁ ፣ መረዳቱ እግዚአብሔር በሚፈቅደው መንገድ ለመጓዝ እና በሕይወት ለመኖር የግድ ይላል ፤ ማለትም ቢቻል ትዳርን አጽንቶ ለመኖር ካልሆነ ግን ተለያይቶም በንስሐ ሆኖ እግዚአብሔርን እያገለገሉ መልካም ሰው ሆኖ ለመኖር ፍጹም ሊታሰብበት ይገባል፡፡
  እንደ ቀደሙት ቅዱሳን አባቶቻችን ዓይነት ሕይወት መኖር ታላቅ መስዋዕትነትና ቁርጠኝነት የሚፈልግ ሕይወት ቢሆንም ባልተመቸ ትዳር መኖር ለሥጋዊም ለመንፈሳዊም ሕይወታችን ጋሬጣ ስለሚሆን ከሚመለከታቸው አካላት (በቅድምና ከፈጣሪያችን ከእግዚአብሔር ፣ ከንስሐ አባቶቻችን ፣ ከሽማግሌዎች…) ጋር በመመካከር ሰላማዊ ፣ ፍቅር የመላበት የይቅርታ ፍሬ ማፍራት ካልተቻለ አማራጭ የሆነውን እርምጃ መራመድ ራስንም ከእግዚአብሐር ጋር ለማኖር ፣ ልጆችንም በአግባቡ ለመጠበቅ ብቸኛ መፍትሔ ነው ብይ አስባለሁ፡፡ ዋናው እንደ ሰውነታችን የሚገባንን ማድረግ ፣ ንጹሕ የይቅርታ ልቡና ራሳችን እንዲኖረን በመለመን አግባብ የሆነው ውሳኔ የተሸለ ሕይወት የምንኖርበት አንዱ ነው፡፡

  እናም ወገኖቼ እንደ እኔ እህታችን የወሰነችው ውሳኔ የሚገባ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ምክንያቱም አንድ ጊዜ በተክሊል ፣ በቤተክርስቲያን ፣ በሕግ ስልተጋባን እስክ ሞትም ቢሆን ልቻለው አይባልም፡፡ የሥጋችን ጉዳት ነፍሳችንንም ይጎዳታልና:: ‹‹ ከዝሙት በስተቀር …በሌላ ምክንያት ሚስቱን አይፍታ›› ሲል ለሁለቱም ግዴታቸውን አስቀምጦ እነጂ እንዲሁ ለአንዱ መብት ሰጥቶ አንዱን ነፍጎ አይደለም ፤ ስለዚህ ሁለቱም የሚጠበቅባቸውን ማድረግ ካልቻሉ እንዴት ትዳሩ ሊጸና ይችላል ? በአንዱ ብቻ መስዋዕትነት ? በፍጹም ! እጅግ ከባድ ነው፡፡
  ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው ሲሆን ብቻ እንጂ
  ‹‹ባል ሚስቱ ባታከብረው እንኳን አብዝቶ ይውደዳት ፤ ሚስትም ባሏ ባይወዳት እንኳን አብዝታ ትታዘዘው ፣ ታክብረው ፤ ይህን ያደረጉ እንደሆነ ሁለቱም ሕግን ይፈጽማሉ››
  ይብቃኝ
  እግዚአብሔር አምላካችን በቸርነቱ እህታችንን እና እንደ እርሷ ያሉትን ያጽናናልን ፤ ያበርታልን ፤ ደግሞም በትዳር ያለነውን ትዳራችንን ይጠብቅልን፡፡
  እንዲህ የሚጠቅመንን ፣ ግን ያልደፈርናቸውን ችግሮቻችንን በማንሳት የሚያወያዩንን እነ ዲ. ዳንኤልን እግዚአብሔር ረጅም እና የተባረከ የአገልግሎት ዘመን ይስጥልን ፤ ቤተሰባችሁን ይጠብቅንል፡፡
  የሰው ፍጻሜው ሲያምር ነውና ደጉ ፣ የሁላችንንም ፍጻሜ ያስምርልን፡፡

  ዘደብረ ካራን

  ReplyDelete
 6. Fornication is not only going to another person for sexual desire. There is fornication over authority, fornication over someone's trust, fornication over faith

  ReplyDelete
 7. Selam Lehulachew

  I it is heartbreaking message. My dear sis , thank you very much for sharing your real life. I hope now you will focus on your childern and pray for your childern father. Pray for him, that is the heart of Christianity. If possible visit him in person with his kids, tell him as you forgive him. Who knows he may return to his heart. I may be telling you the difficult thing, but forgivenes is the fruit of spirituality.

  Dn Daniel, in your side, this issue is very toxic. You need to handle it with great care. Even though, there is this kind of bad example there are thousands of people who leave peacefully with respect. So please write one more article on it the positive side. If feel there is some loophole in this article.

  Melakm ken

  ReplyDelete
 8. This history is enough to convince those who did not accept dany's opionion. The marrige should not necessarily be in kidus kurban or so, but it is a general idea -that is if it is not possible to continue in the available options it is better to quit the previous relationship type. That is exactly wonderful idea! Kiristenam Tilke Selehon besefiwi mayet yifeligal

  A.A

  ReplyDelete
 9. አዬ እንደው ትዳር መድኃኔዓለም ካልባረከው የሰዉን እድሜ ከሚያሳጥሩት አንዱ ሆኖ ሊመደብ ይችላል… ባይታደል እንጂ ሰውየው ከዱላ ይልቅ በፍቅር እና በዝምታ … ይኼን ሁሉ መከራ ድል ይነሳው ነበር፡፡ በከርቸሌ ከመኖር በሞቀ ቤቱ መኖሩ ይሻላው ነበር፡፡ … እኔን ተመልከቱ እሳት የሆነች ባለቤት ነበረችኝ ይኼን ስል እንደው ለትምህርት ብዬ እንጂ ገበናዬን ለመግለጥ አይደለም፡፡ ነበረችኝ ስልም ተለያይተን አይደለም፡፡ አሁንም አብረን ነን ልብን ያለቀዶጥገና የሚቀይር አምላክ ልቧን ቀይሮት እንጂ … ስወጣ ስገባ በነገር ስትጎነጥለኝ … ከአቅሜ በላይ እንድኖር ስታሮጠኝ … እንደራሴ ሳይሆን እንደጎረቤቶቼና እንደጓደኞቼ እንድኖር ስታስገድደኝ … በደስታ የምሰራበትን መስሪያቤት ቀይሬ የተሸለ ደሞዝ እሚከፍል ድርጅት እንድቀጠር ነጋ ጠባ ስትወጥረኝ … አልፎም ምግብ እንኩዋ በቅጣት መልክ ስከለከል … አልፋ ተርፋ ቤትዋን ጥላ ካንዴም ሁለቴ ስትሄድ ..ለማንም ትንፍሽ ሳልል … ክፉ ሳልናገር .. ዱላ ሳልመዝ … እጄን ሳልሰነዝር … ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ገብርኤል ያማልደኝ ዘንድ አልቅሼ አዋየሁት … መቼስ ይህ ከርቸሌ ያለሰው ቢጠየቅ ምክንያቱን ቢናገር አይከፋም ነበር … አሁንም እርስዎን እህታችንን እንኩዋን እግዚአብሔር አተረፈዎ፡፡ ከርቸሌ ያሉትም መድኃኔዓለም ይቅር ብሎ ለንስሀ ሞት ያብቃቸው፡፡ … መልአኩ ደግ ነው የኸው አማልዶ … እየኖርኩኝ ነው፡፡ ዝምታ ትእግስት ጸሎት እና ይቅርታ የማይሰብሩት ድንጋይ ልብ የለምና … ታግሶ ትዳርን መንከባከብ ያስፈልጋል፡፡ አንድ ጉዳይ በሰው አፍ በገባ ቁጥር … ፈተናውም በዛው ልክ ይበዛል … በተለይ የትዳርን ጉዳይ ለሰው ከማዋየት በፊት አስቀድሞ ለፈጣሪ በእንባ ቢነግሩት ሳይሻል አይቀርም፡፡
  ወልደኪዳን ከ ስድስት ኪሎ

  ReplyDelete
  Replies
  1. Wow, i have really learned alot from you, it a nice and elderly advice. thank you!

   Delete
 10. Talew D. (kidanemariam zeBorena)January 31, 2011 at 5:50 PM

  You are one of the strongest sisters I have ever heard of, what can you do more than this?! you have a right to live, recover well, get stronger, you followed GOD's way. He deserves to be in jail. He spoiled not only your life but also his Children's.

  ReplyDelete
 11. እህታችንን ይህን ያክል ብርታት የሰጣት አምላክ ለወደፊቱም ያበርታት:: ትክክለኛ ውሳኔ ወስደሻል ባይ ነኝ ምክንያቱም የሚጠበቀውን ሁሉ አድርገሻል::

  ልጆችሽን ተከታተያቸው አስፈላጊ የሆነ ምክር ያስፈልጋቸዋል::

  ReplyDelete
 12. There are many specific cases like this.We should also not forget many cases which we can coat for improvement towards peace and agreement after worse situation.The mater is not proving our ideas by some examples.But what matters is How do we integrate our thought with our religion basic principles.
  If this idea could have been written by some one who is an academician or a psychologist,we may simply read it and pass it easily.But when we here it from you,Dn.Daniel,it will not be easy to pass it as if you are correct.Because most of your articles are contractive which can wake up and construct each and ever bodies spiritual and psychological being.Such articles makes hopeless for those in trouble.There are many ways to go away from darkness.There might be many in the process towards to change learning from their mistakes.
  Generally we cannot generalize with one specific case ''separation in peace''is the only solution.
  At last let us remind to those of you who support Daniel's Idea.Our lord Jesus who gave us peace and eternal life with his death.We are his followers.
  'Egziabeher kehulachen gara Yihun'

  ReplyDelete
 13. እህቴ...

  ሁሉም ነገር ልክ አለው::ቅዱስ መጽህፍም .... ሁሉም ነገር በስርአት ይሁን ነው የሚለው::መጀመሪያ ነገር ጋብቻ ቅዱስ ነው ማለት..'ቅጣት' ነው ማለት አይደለም::ከጻፍሽልን ታሪክ እንደተረዳሁት ካንች የሚጠበቀውን ፈጽመሻል ብየ አምናለሁ::ደግም ነገር አድርገሻል:: እግዚአብሄር ይጠብቅሽ

  ዘላለም...

  ReplyDelete
 14. Ehta, begetemesh neger hulu azgnalehu. Tigistshinm adenkalehu maderg yalebshin hulu adrgeshal. slezih kzih belay sqayna mekera mekebel yalebshi aymeslegnm. beshi "teywu" wusanashinm leljochish ngeriachewuna keri hywotshin lebichash mesrchi.

  Le hulum egziyabhar keanchi gar yihun, emebeta atleyshi.

  Melkamun hulu emegnlshalehu, Selam

  Temesgen Kassa

  ReplyDelete
 15. እንዲህ ያለውን ሰው North America ነበር ማምጣት ……ልክ ይገባ ነበር:: የእግዚአብሔር ህግ ያልገዛውን ሰው አለማዊው ህግ ልክ ያገባዋል አንዳንዴ አልፈርድባቸውም እዚህ North America መጥተው ሴቶች እህቶች መብታቸው ከልክ ያለፈ ሆነ ሲባሉ ተበላሹ ሲባል ግን …..ለ’እንዲህ አይነቱ ሰው ግን ጥሩ መቅጫ ነው። እንኳን እቃ ወርውሮ ፊትሽን ሊሰብረው…..… እግዚአብሔር መፍትሔውን ያቅርብልሽ።

  ReplyDelete
 16. ይገርማል? አንቺን ይህ ነው የማይባል ትዕግስት ሲሰጥሽ እሱ ደግሞ ልክ እንደ ይሁዳ ህሊናውን የተነሳ ሰው ነው። ላይችል አይሰጥ ይባል የለ? አንዳንዴ እግዚአብሔር ከትዳር በፊት ሲናገረን ሳንሰማ በርሱ ፍቃድ ካልሔድን መጨረሻችን መከራ ይሆናል መፍረዴ ሳይሆን ማለቴ ከጋብቻ በፊት እግዚአብሔር ሲናገረን በ ፍቅር ሰበብ ጆሮ ዳባ የምንለው ብዙ ነገሮች አሉ እነዚያ ነገሮች ተዘርተው… አድገው….. ሲታጨዱ ..ያኔ ነው መከራው የሚታየን ግን …… አምላክ ፅናቱን ያድልሽ ምንም ይሁን ምን ከመከራ በኃላ እግዚአብሔር በረከት አለው ደግሞም ፍጥረቱ ስለሆንሽ ላንቺም ያዝንልሻል አይዞሽ መከራ ለተሸከመው ከባድ ለሰሚ ግን ቀላል ነው።እግዚአብሔር የመከራሽንም መውጫ አብሮ ያዘጋጅልሽ ።

  ReplyDelete
 17. ውድ readereotc

  እንዲህ ዓይነት ችግሮችን መወያየት እንጂ አፍኖ ቁጭ ማለት እሳተ ገሞራን ለማዳፈን የመሞከር ያህል የዋኅነት ይመስለኛል፡፡

  እንዲህ ያሉ ሥጋን፣ ነፍስን፣ ቤተሰብን ብሎም ማኅበረሰብን ሊያጠፉ የሚችሉ ትዳር በቀል ችግሮችን እየነቀስን መወያየትና መፍትሔውን መጠቋቆም ለብዙ ሰዎች መውጫ መንገድ እንደሚያስገኝ ልንዘነጋው አይገባም፡፡ እንዲህ ዓይነት ውይይቶች ሊበራል አመለካከት የተጫናቸው ሊባሉም አይችሉም; ምክንያቱም ጉዳያቸው ሰብአዊ ህላዌ (existence) ወይም የመኖር ጥያቄ (a matter of survival) እንጂ ተዝናኖትን መፍጠር፣ ቀንበርን መፍታት አይደለምና፡፡

  አንዳንድ ፈላስፎች “ህላዌ ምንትነትን ይቀድማል::” (existence precedes essence) ይላሉ፡፡ እዚህ እያየናቸው ያሉ ጉዳዮች ደግሞ ይህንኑ ያስረግጣሉ፡፡ እኅታችን ወ/ገ ክርስቲያን ሆኖ ለመገኘትም ሆነ ልጆቿን ክርስቲያን አድርጎ ለማሳደግ በቅድሚያ የእርሷ ህልውና መረጋገጥ ነበረበት፡፡ ያደረገችውም ይህንኑ ነው፡፡

  እርግጥ ነው ጣት ቆሸሸ ተብሎ ተቆርጦ አይጣልም- በውኃ፣ በልዩ ልዩ ሳሙና ይታጠባል፡፡ ነገር ግን ከሰውነት አካላችን አንዱ በካንሰር ቢጠቃ ያንን የተጎዳ አካል እናስወግደዋለን እንጂ ገና ለገና ስንወለድ ይዘነው ስለተወለድን በሰውነታችን ሁሉ ተሰራጭቶ እስኪገድለን ቁጭ ብለን አናየውም፡፡ እንቆርጠዋለን፡፡ ከዚያም ሌሎቹን ጤነኛ የሆኑ አካላት ይዘን መኖር እንቀጥላለን፡፡ ይህ የህልውና እንጂ የቅንጦት ጥያቄ አይደለም፡፡ በዓለሙ ሁሉ ተቃራኒ ጾታ ሞልቶ ሳለ “ተመሳሳዬን ካላገባሁ ሞቼ እገኛለሁ!” ዓይነት ቅብጠት ወለድ ዝቅጠትም አይደለም፡፡ “ሳይቃጠል በቅጠል” እንዲሉ በአንዱ መከራና ተሞክሮ ሌላው ሊማርበት እንዲችል ለማድረግ መትጋት ነው እንጂ፡፡

  ሰዎች የምንለውን ነገር ባሻቸው መንገድ ሊረዱት ይችላሉ፡፡ በተሳሳተ መንገድ እንዳይረዱት ለማድረግ እንሞክራለን እንጂ ማኅበራዊ ጥመቶችን በሃይማኖተኝነት ካባ ጀቡነን ዝም ማለት ለማንም አይበጅም፡፡ እንወያያለን፡፡ መፍትሔም እንፈልጋለን፡፡ የአባቶቻችንን ሃይማኖት ይዘን የዘመናችንን ችግር እንዴት እንደምንፈታው እንመካከራለን፡፡ ምክንያቱም የህልውና ጥያቄ ነውና፡፡

  ገና ብዙ እንጠብቃለን!

  ReplyDelete
 18. your patiency is more and beyond what expected from the current stituation of equality of men and women in family matters and a woman who is at the status of you are working as you explain. This is to make your family safe and sustain your marriage. By the way husbands does not want the status of thier wife more than him in the social, ecomonical and political affairs.He feel like he has been degraded by her.That is why most outstanding women are with our marriage.
  though your patiency for your family is maximum and you tried to convince him by elders and other guys he did not renounce his oout look and continue beating you and injured you. For me no one shall be beaten. the best solution after advise is separtion which is safe. I don't want to be angree and uopset somany time for the sake of marriage. every one need peace, if no peace, being alone is the best peace not to hear 'chikich' let alone beating. i know a woman like you who were denied her peace for seven years and she resume her peace by divorce. As a human right activist we shall not give up our peace for marriage and property.
  God be with you, I hope you will get soon your peaceful marriage with another person who at least equal with you in the society and please don't refuse any one for marriage by thinking the previous one. all are not the same. the only thing you need to do is be frank for him who may contact you.

  ReplyDelete
 19. ዲያቆን ዘሚካኤልFebruary 1, 2011 at 1:22 PM

  ይህ ሰው ለሰይጣን ፈቃድ ላለመታዘዝ የዕውቀትና መንፈሳዊ ልምምድ ያጥረው እንደነበረ ግልጽ ነው፤ ሆኖም በታላቅ መንፈሳዊ ኃላፊነት በተክሊል አገባ። እዚህ ጋር አንዳንድ አባቶች እንደሚመክሩት መንፈሳዊው ጽናት እስኪመጣ በማዘጋጃ መጋባት ጥሩ ነበረ እላለሁ። መንሥኤው ግን የገጠመውና ያልተናገረው ከባድ ችግርም ሊኖር እንደሚችል፣ ይህንም ለማውራት ባለመቻሉ በራሱ መላምት ባለቤቱን የችግሮች ሁሉ መንሥኤ አድርጎ በማሰብ የተበቀላት/በውስጣዊ እርካታ/ ይመስለኛል።
  አሁንም የሚጸጸትበት ቀን ሊኖር ስለሚችል በትእግሥት ጠብቂው፤ ደህንነቱን በመጠየቅና የሚቸግረውን በወህኒ እያለም እርጂው፤ ይሄን በማድረግ ክርስቶስን መምሰልሽን ፈጽሚ ብዬ እመክራለሁ። ትልቅ መንፈሳዊ ጥብዓት ስለሚፈልግ ግን የክርስቶስን መከራና የቅዱሳንን ተጋድሎ በማንበብ ጸሎትን አዘውትሪ፤ ሁላችንም አንድ አቡነ ዘበሰማያት ብንደግምላትም ጥሩ ነው። ምናልባት ሳይጸጸት ከወጣ ግን ለቤተሰብሽ ሕይወት ተጠንቀቂ።
  እመ አምላክ አትለይሽ።

  ReplyDelete
 20. It is quite clear that how hard your life was.We all Ethiopian know this kind of life from our own family or people around us.I believe everything can be changed with the help of God with in time.I want to ask you one question and I need you to ask your heart.You told us how you struggled to keep him on the way.Instead of telling to people and 'niseha abat', how hard did you pray ? How hard ?
  Please pray us long us it takes to bring your life back.As a child, I know how difficult it is to loose a peaceful family.

  ReplyDelete
 21. Dn Daniel,
  1. we are in a great difficult time especially in marriage. I see no effort by our church clergy to educate the essence of marrage. I strongly suggest you openup a separate blog or venue where such and other marriage related problem are discussed and required help is rendered before getting worst
  2. I trust the lady need professional counselling in addition to spiritual help. I suggest that we help her by arranging a meeting with a professional in this area.
  Thanks

  ReplyDelete
 22. መልአኩ ደግ ነው የኸው አማልዶ … እየኖርኩኝ ነው፡፡ ዝምታ ትእግስት ጸሎት እና ይቅርታ የማይሰብሩት ድንጋይ ልብ የለምና … ታግሶ ትዳርን መንከባከብ ያስፈልጋል፡፡ አንድ ጉዳይ በሰው አፍ በገባ ቁጥር … ፈተናውም በዛው ልክ ይበዛል … በተለይ የትዳርን ጉዳይ ለሰው ከማዋየት በፊት አስቀድሞ ለፈጣሪ በእንባ ቢነግሩት ሳይሻል አይቀርም፡፡

  ReplyDelete
 23. በመጀመሪያ ለዲ/ን ዳንኤል ክብረት ያለኝን አክብሮትና መልካም ምኞት ሁሉ ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡
  ባለታሪኳ በምን ምክንያት ይህንን እንደሚያደርስባት አልገለፀችልንም/የፀባቸውን መንስኤ አልገለፀችልንም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያውያን ባሎች ማህበረሰቡ በሰጣቸው "የወንድነት" ሚና ማለትም፡- ሚስቶችን የመሳደብና የመማታት አባዜ ይህንን እየፈፀመ ሊሆን ይችላል፡፡ አይወዳትም እንዳንል የፍቺ ጥያቄ አላነሳም በተጨማሪም የፍቺው ጉዳይ በፍ/ቤት ከተፈፀመ በኋላም ለምን በሚል ይመስላል እንደኔ በመናደዱ የግድያ ሙከራ አካሂዶባታል፡፡ ስለዚህ በእጅ ያለወርቅ እንደመዳብ ይቆጠራል፡፡ "ሰው ካልሄደ ወይም ካልሞተ አይመሰገንም" ይባላልና እስራቱ ይህንን እውነት/አባባል/ ሊያሟላ ይችላል ብዬ አምናለሁ፡፡ በመሆኑም በተወሰነ ጊዜ እየሄድሽ በመጠየቅም ሆነ ልጆቹን እንዲያይ በማድረግና መልካም ነገር በማሳየት በእርግጥም ለአንች ፍቅር እንዳለውና እንደሌለው መገንዘብ/ማረጋገጥ/ ይቻላል፡፡ ካለው ይፀፀት ይሆናል፡፡ ከሌለው ደግሞ በጽሁፉ ዳንኤል እንደገለፀው በሰላም መለያየት የተሻለ ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል ተስማሚ ምግብ በማቅረብ፣ ጥሩ ጥሩ አለባበስ በመልበስና መልካም ገጽታ በማሳየት ብቻ ግንኙነትን ለማሳመር በቂ አይሆንም ከዚህም በዘለለ ሃሣብ ለሃሣብ፣ ስሜት ለስሜት መጣጣም ያልቻላችሁባቸው ሁኔታዎች ካሉም መለስ ብሎ መቃኘት ተገቢ ይሆናል፡፡
  በተረፈ የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላዕክት ተራዳኢነት አይለይሽ፡፡ አንችም በፀሎት መበርታት አለብሽ ለእርሱም የመፀፀቻ ልቦናን ያድለው አሜን፡፡

  ReplyDelete
 24. Dear sister
  you have realy sacrified a lot to keep your marriage. and God also knows what you paied for it. Dont worry about what happend at the end.That is the only option as far as your case concerned.So keep strong and continue praying for the betterment of your family future.

  with any criteria, your case is not different from "divorce due to "Zimut" ".

  But as a way forward , Dn. Daniel should take this issue up to end till we get a direction from church fathers. I think the holy senodos should also take the lion part in adressing such issues.

  Finally, dear sister , dont forget God is always with you so you are supposed only to pray. leave all your worries to him.
  May God be with all of us.

  Abiot k oldenburg

  ReplyDelete
 25. I was just reading the story with awe. I am really so sorry for what happened to you (the writer) and I wish God be with you and give you all the strengths. as per the story you husband is totally at his worst behavior and it was a total disaster proceeding with him for the rest of your life but one thing which i didn't read or i didn't understand was what was his motive to act like that? why was he acting like that and making you feel bad every day despite your dedication to make him happy. most of the time knowing the motive or the source of the problem will make it easy to solve the problem instead of trying all the possible options we think are right. the other thing is I really don't know how people are relating patience with negligence. we much have concrete and satisfactory reasons to be patient in any case. sometimes our patience becomes negligence and then could lead to a lot of disaster instead of earning the results of our patience. when your husband started acting weird from the start I don't see that you were supposed to be patient for all this time. the reason is because his weirdness was simply increasing from time to time and that was totally an acceptable. beng patient this way means being powerless. i think it will be one big topic if we will talk about patience and what are the limits to take action

  yonas

  ReplyDelete
 26. I am so sorry for your grief, our sister. You did what is expected from you. Specially you tried to solve the problem through the church. This was the most you could do. By any circumstances, abusing and (most satanic decision) tried to kill is absolutely abnormality. Oh!!! Our sister, you were late to claim divorce. May God give you strength and mercy for him.

  ReplyDelete
 27. I just got marred last week, wish would say alot of thing however I only know marrage by book ? may God help u

  Dn 000000

  ReplyDelete
 28. If it is your Children's mentality that is worrying you, i think you ought to be grateful that they are too young giving you a lot of chance to manipulate their mind in to thinking positive, you could help them to picture this world like the way GOD meant it to be 'A Perfect World'....But, as for you, am glad that you made it out alive, and its my personal believe that we have a reasonable God who knows and understands a lot more than we give him credit for....we shouldn't define him and put him in a box, b/c he always measures intensions with outcomes...

  ReplyDelete
 29. በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ። አሜን!!

  በእርግጥ ጉዳዩ ምንም ይሁን ምን ያሳዝናል።ብዙ ጊዜ ግን እኛ ሰዎች ስለ ሰው ክፉ ነገር ማውራት ስንፈልግ ስለ ራሳችን አንድም ነገር ማውራት አንፈልግም። በተለይ በትዳር በኩል በሚነሳ ፀብ አንዳችን ፍፁም መስለን ለመቅረብና ጥፋታችንን ለመግለፅና ለማመን አለመሞከር የተለመደ ነገር ነው። በእርግጥ አንዳችን እኩይ ተግበባር ሊኖርብን ይችላል። ነገር ግን አንዳችን ጥሩ ብንሆን መጥፎውን በእግዝአብሔርም እርዳታ ጭምር ልንቀይረው እችላለን። አንዳችን ጥሩ ሆነን ነገሩ አልቀየር ቢለን እንኳን እንደዚህ ስር የሰደደ ችግር አያጋጥመንም። ትዳር ላይ ችግር አያጋጥምም ማለት ያሰቸግራል ሆኖም ከዝሙት ውጪ ላለው ቀላል ነገር ተቻችሎ መኖር ቢቻል እግዝአብሔርንም አናሳዝንም ነበር። እህታችንም ልትረጂው የሚገባው ነገር ቢኖር አንቺ መጥፎ ነሸ እያልኩ ሳይሆን አንድ ነገር ግን እንደደበቅሽን ተሰምቶኛል። ባለቤትሽ መልካም ሰው ከነበረ አለአንዳች ምክነያት ይህን የሰይጣን ፀባይ ከግዜ በኋላ ከየት አመጣው? ለባልሽ መልካም ነገር ለማድረግ የሰውና የጓደኞችሽ ግፊትስ ለምን አስፈለገሽ? ቀድሞውኑ መልካም እንዳታደርጊና መልካም እንዳታስቢ ምን ያዘሽ? አሁንም፡ አይ እኔ መልካም ነበርኩ። ባለቤቴም ያለምንም ምክነያት ከግዜ በኋላ ያመጣው ፀባይ ነው ካልሽን አንቺ ፍፁም ሴት ነበርሽ ማለት ነው።

  ቸሩ ፈጣሪያችን መልካም እንድናስብና መልካም እንድንሰራ ይርዳን። አሜን!!
  መርከቤ ንጉሴ/ከአዲስ አበባ/

  ReplyDelete
 30. ayizosh yalifal meseley bicha new mefitihiew ,enidanichi yekefa bayihonim temesasay chigir agatimognal,bagebagn benegataw tekeyirobign be 5 werie tefatichalehu. gin 5 wer silish ye midir gahaneb nebere gin be esu biso kebietu enidiweta betazezikut meseret bietun tichie wetahu.EGIZIHABIHIER hul gizie alama alew enigi sayayen kerito enidayimesilish, ayizosh

  ReplyDelete
 31. This is really a sad story. She has done everything she should have done. If it wasn't for God's will, he (the ex-husband) would have killed her. @ readereotc,even though I understand what you are trying to say, would you bear it if you were in her place. What would you have done differently. I don't think it makes sense to stick with someone just because it's not the rule to divorce someone other than adultery reasons. I would actually
  categorize this under religious problem. Even if the guy did not change his religion, he is not following any of our religion's dogma. So what exactly makes him a christian?
  Enatye, emebete kanchi ga tihun...ende Lewawiw sew beQuslish ly zeyit yemiyafes sew yistish

  ReplyDelete
 32. ይሄን የመሰለ ልብ የሚሰብር የህይወት ገጠመኝ ያየሁት ዘግይቼ ስለሆነ አዝናለሁ አሁን የምሰጠውንም አስተያየት ምናልባትም ባለችግሯ ላያዩት ይችላሉ፡፡ ይሁንና ለሕሊና እንዳይቆጭ ማለት ያለብኝን እላለሁ፡፡ ብዙ ወንድሞችና እህቶች ብዙ ጠቃሚ ሀሳቦችን ጠቁመዋል፡፡ የእኔ ሃሳብ ሰው መጀመሪያ የነበረውን ባህሪ በቀላሉ ሊለውጥ አይችልም ዋናው ችግር የበጐ ነገር ጠላት የሰውን ልጅ የሚጠላ ሰይጣን ሸምቆ ሲያደባ እንደቆየ የተገነዘበው እንዳልነበረ በዚህ ቤተሰብ ውስጥ ለመታዘብ ችያለሁ፡፡ እናንተ ጋብቻችሁ በስርዐተ ተክሊልና ቅዱስ ቁርባን ይመስለኛል፡፡ በቀጥታ የተፃፈ ሃሳብ ስላላገኘው ተጠራጥሬ ነው፡፡ ብቻ በዓለም የሚደረገውም ጋብቻ ቢሆን በአንድ ባልና ሚስት ፀንቶ የተመሠረተ እስከሆነ ድረስ ሕግ ጠባቂዎች ናችሁና የከበረ ጋብቻ ነው፡፡ ይህንን ቃል ኪዳን ነው ሰይጣን ለመበተን የሚፈልገው፡፡ ሰው እንኳን በትዳር በሌላ የማህበራዊ ግንኙነት በፍቅርና በስምምነት የተደረጉ ውለታዎችንና ኑሮዎችን መበጥበጡና ማወኩ አይቀርም፡፡ ስለዚህ ከሁለታችሁ መካከል አንዱ ደከም ያለ መንፈሳዊ ትጋት ካለው ሰይጣን ምን ሩቅ ሰው አስፈለገው ደካማውን በቀላሉ በመደለል ይበጠብጠዋል፡፡ እንግዲህ የነቃበት የለም ያልኩት በዚህ ጊዜ ነው ሌላ ሽማግሌ ወይም ሳይካተሪስት አይደለም የሚያስቆመው፡፡ ያ ክፉ ባሪያ አንዱን መክሊት ቀብሮ እንደተቀጣ በምስጢራዊ አፈታት ነፍስ ከተፃራሪው ጠላት ሥጋን ጠብቃ ለትሩፋት አብቅታ አለመገኘቷ ነው የመጀመሪያው ጥፏቷ፡፡ ሲቀጥልም ሌሎችን ወገኖች ዘክራና መክራ ረድታ አለመገኘቷ ተጨማሪ ጥፏቷ ይሆናል፡፡ ስለዚህ የመጀመሪያ የክርስቲያኖች ጠበቃና ታዳጊ እግዚአብሔር አምላክ ነውና እምነታችን ሳይወላውል በጽኑ ልብ ይህንን መሰሪ እንዲያስረው ወይም እንዲያስቆመው መፀለይ ነው፡፡ ልባችን ያለጥርጥር እግዚአብሔርን መከታ ካደረገ ሸማቂው ይከስራል፡፡ እኛ ግን እግዚአብሔርን ሩቅ አድርገን ሌላውን ከሞከርን በኋላ ባጣ ቆየኝ መጨረሻ ወደ እሱ እንመጣለንና ችግሩ ስር ይሰድና ያሳዝነናል ወይም ጉዳቱ ይከፋል፡፡ ብዙ የማይመለሱ ኪሳራዎች በህይወታችን ላይ ይደርሳሉ፡፡ ለማንኛውም እግዚአብሔር በ11 ሰዓት ለመጣም ልዩነት ያለው ዋጋ አይከፍልምና በትጋት ፀሎት ማድረግ ግዴታ ይገባል፡፡ ልክ የደም ግፊት፣ የስኳር፣የኤች.አይ.ቪ. ወዘተ መድሃኒቶች አንድም ቀን ሳይቋረጡ እንደሚወሰዱ በትጋት እህታችን ሊፀልዩ ይገባል፡፡ እርግጠኛ ነኝ እግዚአብሔር ይህንን ችግር ይፈታዋል፡፡ ብዙ ድሆች በፍቅር የሚኖሩት በጾም በፀሎት ተጠምደው፣በቅዱሳን ፀሎት፣በመላእክት ጠባቂነት፣በእመቤታችን አማላጅነት፣በእግዚአብሔር ቸርነት ታምነው ነውና እባክዎትን ይህንን ያድርጉ፡፡ በሌላው አስተያየቴ ደግሞ ዘመኑ ሰይጣን በቀጥታ የሚያጠቃበት አይደለምና በእናንተ እድገት፣የኑሮ መሳካት፣ፍቅርና ሌሎችም ሁኔታዎች ቀናተኛ ይነሳልና ሰው ዓይነ ልቡናው እውር እስከሚሆን ድረስ ጠመንጃ እስከመምዘዝ የሚያደርስ ተልእኮ የተሰጠው ሰይጣን አለና ፀበል መጠመቅም ያስፈልጋል፡፡ እንግዲህ እነዚህ ሁሉ እንዳሉ ሆነው ወንድማችንን በገጠማቸው የእስር ቤት ህይወት መጐብኘት ይገባል፡፡ እግዚአብሔር የይቅርባይን ፊት አይቶ በተግባሩ ሠላም ያወርዳልና፡፡ እኛም እግዚአብሔር እንዲረዳዎት በዳካማው ህይወታችን በፀሎታችን እናስበዎታለን፡፡ እግዚአብሔር ይህንን ህይወት ለውጦ መልካም ዜና እንዲያሰማን እንመኛለን፡፡

  ዲ/ን ዘላለም

  ReplyDelete
 33. ልብ የሚነካ ጉዳይ ነዉ በእወነት! እግዚአብሄር አብ ካንቺጋር ይሁን! ዳኒ እግዚያበሄር ይስጥህ! ትልቅ ትምህርት ሆኖኛል!

  ReplyDelete