Wednesday, January 26, 2011

«ልርሳህስ ብል ብርዱ መቼ ያስረሳኛል»

ክፍል ሁለት
አንዳንዶች ይህ ስሜት የሚመጣባቸው «የኔ ያልሆነ ሁሉ የማንም መሆን የለበትም» ከሚል የራስ ወዳድነት ¼ego centrism/ በሽታ ነው፡፡ ይህ በሽታ የለከፋቸው ሰዎች አንድ የእነርሱ ሊሆን ያልቻለ ነገር ወይንም ሰው፤ ያለ እነርሱ በሰላም ወይንም በደስታ ሲኖር ለማየት ዐቅም የላቸውም፡፡ ከተከራዩት ቤት ሲለቅቁ ተጣልተው፣ ተሰዳድበው፣ ከቻሉም ተደባድበው ነው፡፡ ከተቀጠሩበት ቦታ ሲለቅቁ ዕቃ ሰብረው፣ አበላሽተው፣ መረጃ ደብቀው፣ ስም አጥፍተው ነው፡፡ ከሚወድዱት ሰው ሲለያዩ አስለቅሰው፣ ልብ አድም ተው፣ አንከራትተው፣ ሀብት አሽሽተው፣ ስም አጥፍተው፣ ምሥጢር አውጥተው፣ በሐሰት ከስሰው፣ ከቻሉም ተደባድበው ነው፡፡

  የእነርሱ የነበረ ነገር የሌላ ሆኖ ወይንም የማንም ሆኖ ማየት ያማቸዋል፡፡ ሲኖሩ ያጠሩትን ሲለዩ ይበጠብጡታል፤ ሲኖሩ የሠሩትን ሲለዩ ያፈርሱታል፤ ሲኖሩ የተስማሙበትን ሲለዩ ይቃወሙታል፡፡
አንድ እዚህ ከተማችን የተፈጸመን ታሪክ ልንገራችሁ፡፡ ልጂቱ እና ልጁ በፍቅረኛነት አንድ አምስት ዓመት ኖረዋል፡፡ የልጁ ጠባይ ግን የሚሆናት አልሆነምና ሳይደርቅ በርጥቡ፣ ሳይርቅ በቅርቡ ብላ ለመለያየት ወሰነች፡፡ ብዙ ጓደኞቻቸው መከሩት፣ እታረማለሁ እያለ እየባሰው መጣ፡፡ ይፈራቸዋል በሚባሉ የሃይማኖት አባቶች አስመከረችው፤ የርሱ መታረም ለዕለት ብቻ ሆነ፡፡
በመጨረሻ ተለያዩ፡፡
ከተወሰኑ ወራት በኋላ እርሱ ጓደኞቹን እያለቀሰ እንዲያስታርቁት ለመናቸው፡፡ እነርሱም ነገሩ እንግዳ ነገር ቢሆንባቸው እሺ ብለው ልጂቱን በእግር በፈረስ፣ ከላይ ከታች እያሉ ለመኗት፡፡ እርሱም እግሯ ሥር ወድቆ አለቀሰ፡፡ ልጂቱ ልቡ ተመልሷል ብላ ታረቀችው፡፡ ሁለት ወራት ያህል ጠባዩ እንደ ወይን ጣፋጭ፣ እንደ ገነት ምቹ ሆነ፡፡ ሽማግሌ ላከ፡፡ የሠርጉ ቀን ተቆረጠ፡፡ ዝግጅቱ ተጧጧፈ፡፡ ፈረስ የሚያስጋልብ አዳራሽ ተከራዩ፤ ዘመድ ወዳጅ ተጠራ፡፡ ቀኑ ደረሰ፡፡ 
የሠርጉ ዕለት ሙሽራዋ ተዘጋጅታ ሙሽራውን ትጠብቀው ጀመር፡፡ ተጠበቀ፤ አልመ ጣም፤ ተጠበቀ አልመጣም፤ ሞባ ይሉ ላይ ተደወለ፡፡ ዝግ ነው፡፡ ጓደኞቹ ጋር ሲደወል «ሠርጉ መቅረቱን ትናንት ነግሮናል» አሉ፡፡ ቤተሰቡን አፈላ ልገው አገኟቸው፡፡ እነርሱ ስለ ሠርጉ የሰሙት ነገር የለም፡፡ በስማቸው ስለታተመው የጥሪ ወረቀትም አያውቁም፡፡
የተጠራው ሰው አዳራሹን ሞላው፡፡ ምግቡ መጠጡ እንደተዘረጋ ነው፡፡
ሲጣራ ልጁ በጠዋቱ ወደ ኡጋንዳ በርሯል፡፡
ማታ ከኡጋንዳ አንድ የስልክ መልእክት መጣላት «ልትጫወችብኝ ነበር ተጫወትኩብሽ፤ ቻዎ» ይላል፡፡
አብሮ መኖር ካልተቻለ ሰላማዊ መለያየት የሚባልም አስጠሊታ አማራጭ /necessary evil/ አለኮ፡፡ ይህ ሁሉ መጎዳ ዳት፤ የልጂቱን ቅስም መስበር፤ የቤተሰቡን ክብር መንካት፤ በማኅበረሰቡ ነባር እሴት ላይስ እንዲህ መቀለድን ምን አመጣው?
ሌሎቹ ደግሞ አሸናፊነትን ብቻ ስለሚፈልጉ ያለ ጠብ መለያየት አይችሉበትም፡፡ እንዲያውም የሚያሸን ፉበት አጋጣሚ እስኪፈጠር ድረስ አኩርፈው እየሳቁ፤ አዝነው እየፈገጉ መኖር ይችሉበታል፡፡ ያቺ አሸናፊ የሚሆኑባት ቀን እና ሰዓት ስትደርስ ግን ይነሣሉ፡፡ ተአምራዊ በሚመስል መንገድ ይለወጣሉ፡፡ አብሯቸው የሚኖረው አካል በድንገት ተለወጡ ብሎ ይገርመዋል እንጂ እነርሱ ከተለወጡ ቆይተዋል፡፡ ግን አልተገለጡም፡፡
እነዚህ ለሰላም ከመሸነፍ በጠብ ማሸነፍ፤ ለፍቅር ከመሸነፍ በጦርነት ማሸነፍ የሚመርጡ ናቸው፡፡ ያኛውን ወገን ጎድተው፣ አስለቅሰው፣ አንበርክከው፣ አንከራትተው፣ አሣስረው፣ አስርበው፣ አደኽይተው ካልሆነ በቀር የተለያዩ አይመ ስላቸውም፡፡ በል ቻው፣ በይ ቻው የሚለው ቃል እንደ መጠቃት ያማቸዋል፡፡ እንደነዚህ ዓይነቶቹ ዐውቀውትም ይሁን ሳያውቁት ሰይጣናዊ ስሜት ውስጣቸው አለ፡፡ ስለዚህም እንርሳው ብንል የማያስረሳ ነገር ካልጣሉብን በቀር አይለዩንም፡፡
ቺካጎ ውስጥ የተፈጸመ አሳዛኝ ታሪክ ላውጋችሁ፡፡ ልጁ አሜሪካ ነው የሚኖረው፡፡ ከሀገር ቤት አንዲት ልጅ ያገባል፡፡ አንድ ልጅም ያፈራሉ፡፡ ሂደቱን ጨርሰው እርሷም አሜሪካ ገባች፡፡ ለተወሰነ ጊዜ አብረው እንደኖሩ አንድ ቀን ከሥራ ሲመጣ ቤት ውስጥ አጣት፡፡
«ልትፈልገኝ ብትነሣ ለራስህ ፍራ»
የሚል መልእክት ብቻ አገኘ፡፡
አልተዋትም አፈላልጎ ጓደኛዋ አገኛት፡፡ እዚያ ቤት ሄዶ ወደ ቤቷ እንድትመለስ ሲለምናት ፖሊስ መጣ፡፡ ጓደኛዋ «ሐራስ እያደረጋት ነው» ብላ መሰከረች፡፡ ፖሊሶቹ እርሱን ይዘውት ሄዱ፡፡ በስንት መከራ ከእሥር ተረፈ፡፡ ነገር ግን ከተወሰነ ሜትር በታች ወደ እርሷ ላይቀርብ፤ ልጁንም ለተወሰነ ጊዜ ላያይ /ሐራስ እንዳያደርጋት/ ተወሰነበት፡፡
ልጁ ሊያብድ ሲል በአካባቢው የነበሩ መንፈሳውያን ወገኖቹ በስንት ጥረት አተረፉት፡፡
ምናለ ሲሆን ችግሩን በመልካም መንገድ ብትፈታው፤ ካልሆነና ከእርሱ ጋር መኖሩን ካልፈለገችው ይህንን ያህል የልጁን ሕይወት እስከ ማበላሸት እና አእምሮውን እስከ ማንካት የሚደርስ ጉዳት ማድረስን ምን አመጣው? ሰውን ማሸነፍ በመጉዳት ብቻ ነው እንዴ? በደግነት ማሸነፉ አይበልጥም?
ሌሎቹ ደግሞ አንድ ግንኙነት በሌላ ዓይነት ግንኙነት ሊተካ እንደሚችል የማያምኑ ናቸው፡፡ ግንኙነት ዘርፈ ብዙ ነው፡፡ ለኛ ብቻ ተብሎ እንደ አበሻ ቀሚስ በዕውቅ የተሠራ ሰው የለም፡፡ ስለዚህ «በዚህ መንገድ የኔ መሆን ግዴታው ነው» ሊባልለት የሚችል ሰው የለም፡፡ ፍቅረኛ መሆን አልቻለችም፤ ጓደኛ ግን ልትሆን ትችል ይሆናል፤ ባል ሊሆን አልቻለም፤ ወንድም ግን ሊሆን ይችል ይሆናል፤ የንግድ ሸሪክ ሊሆን አልቻለም፤ አማች ግን ይሆን ይሆናል፤ ጎረቤት መሆን አልቻለም የንግድ አጋር ግን መሆን ይችል ይሆናል፤ ማኅበርተኛ መሆን አልቻለም፣ ሠፈርተኛ መሆን ይችል ይሆናል፡፡ ሠራተኛ መሆን አልቻለም፣ አንዳች የምናውቀው ሰው ሆኖ መኖር ግን ይችል ይሆናል፡፡
ከዚያ ሰው ጋር ባልተስማማንባቸው ነገሮች ትተን በተስማማንባቸው ነገሮች ብንቀጥል ምናለ፡፡ ባል እና ሚስት መሆን አልቻልንምና ተፋታን፡፡ ከዚያ በኋላ ከቻልን እኅት ወንድም፣ ካልቻልን አንዳች ትዝታ ያለን የምንተዋወቅ ሰዎች ሆነን መቀጠል አይቻልም? ለምን ሁሉንም የግንኙነት መሥመር እናበላሸዋለን፡፡ ተለያየን ማለት ተጣላን ለምን ይሆናል? መቼ ይሆን የተለያየነውን ሰው ጥሩነት ለማውራት የምንችለው? ለምንስ ይሆን እህህ የሚያሰኝ፣ ቂምን የማያስረሳ የቤት ሥራ ተሰጣጥተን የምንለያየው?
ለምሳሌ የአንድ ፓርቲ አባላት የነበሩ ሰዎች በአመለካከት በአስተሳሰብ፣ በርእዮተ ዓለም፣ በአሠራር ተለያዩ፡፡ አብሮ መኖሩ ችግሩን አልፈታው አለ፡፡ እንዲያውም አብሮ መኖሩ ከመለያየቱ በባሰ ችግሩን አባባሰው፡፡ ሁለት ንጉሥ በአንድ ሀገር፣ ሁለት ርእዮተ ዓለም በአንድ ፓርቲ ሊኖሩ አይችሉም፡፡ ይህ ነገር ሲከሰት አብሮ መኖር ካልተቻለ ቀሪው አማራጭ መለያየት ነው፡፡
ጥያቄው እንግዲህ እዚህ ላይ ነው፡፡ ሁለት የተለያዩ አመለካከቶች ያሏቸው ፓርቲዎች ናቸው መሆን ያለባቸው ወይስ ሁለት እርስ በርሳቸው የሚጣሉ ፓርቲዎች? ለምንድን ነው ሁለት ጠላቶች ከምንሆን ሁለት የተለያዩ መሆን የማንችለው፡፡ ባህል አለ፤ እምነት አለ፤ ወግ አለ፣ ሕግ አለ፤ በእነዚህ በሁሉም ወይንመ በመረጥነው መንገድ መለያየቱን ሰላማዊ እና ለሌላ ግንኙነት በሩን ያልዘጋ አድረገን መተው አንችልም?
ካልተካሰስን፣ አንዳችን በሌላችን ላይ መግለጫ ካልተሰጣጣን፣ አንዳችን ሌላችንን ካላጋለጥን፣ አንዳችን ሌላችንን ጭራቅ አስመስለን ካልሳልን፣ ካልተወራረፍን እና ካልተሞ ሸላለቅን መለያየት የማንችለው ለምን ይሆን» እንደ ባሕታዊው የግድ «እንርሳው ብንል የማያስረሳ ጠባሳ» አንዳችን በሌላችን ላይ መተው ይኖርብናል»
እንዲያውም ተጣልተው ለመታረቅ፣ ተለያይተው ለመገናኘት፣ ተራርቀው ለመቀራረብ የቻሉትን ብዙ ተጓዳኞች ሁኔታ ብንመረምር መለያየታቸው ሰላማዊ የሆነላቸውና ምንም ዓይነት ቂም፣ በቀል እና ስብራትን ያልመዘገቡት ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከመለያየት በኋላ ለመገናኘት ከባዱ ነገር ያለያየው ምክንያት አይደለም፡፡ በመለያየት እና ከመለያየት በኋላ የተፈጠሩ ነገሮች ናቸው፡፡ የቤተሰብ አገባብ፣ የጓደኞች ንግግር፣ የተለዋወጧቸው ቃላት፣ የተጎዳዱት ጉዳት፣ በንብረት እና በገንዘብ ላይ የተወሰኑ ውሳኔዎች፤ አንዱ ስለሌላው ያወሯቸው ወሬዎች፣ ወዘተ ነገሩን ከጉዳዩ በላይ ያከሩታል፡፡
እናም እንደ እኔ በአንድነት፣ በፍቅር፣ በመተሳሰብ፣ በሽርክና፣ በማኅበር መኖር የተሻለ የሚያስፈልግ ነው፡፡ የመለያየትን መንገዶች ሁሉ መዝጋትም ተገቢ ነው፡፡ ግን በሁሉም መንገዶች ተብሎ ተብሎ ካልተቻለ፤ መለያየትም የመጨረሻው አማራጭ ከሆነ፤ ያለ መጎዳዳት፣ ያለ ስብራት፣ በሰላም እና በጎ ትውስታን ሊጥል በሚችል መልኩ ብቻ እናድርገው ሰላማዊ የመግቢያ መንገድ ብቻ ሳይሆን ሰላማዊ የመውጫ መንገድም ያስፈልገናል፡፡
እስኪ በዚህ ረገድ በተለያዩ አቅጣጫዎች እንወያይበት፤ ሃሳቦቻችሁን እጠብቃለሁ

33 comments:

 1. Dn Daniel Kale hiwot yasemalin.
  I have read part one yesterday and i completely disagreed with you because i thoght we are christians and can overcome anything. But after reading part two today, I agreed with you a thousand percent. Just like you, i know a friend who was almost hospitalized because she was hurt by her husband. What he did was, they were together for years before they got married and they finally got married and had kids. Then he left her with the kids and go around told everyone that he wants to see how she would handle it by herself. The reason he did that is because he had a grudge of their disagreement before thay got married. I was shocked!!! God Bless You!!!

  ReplyDelete
 2. መጀመሪያ ባቀረብከው ሃሳብ ክፍል አንድን ሳነብ ቅር ብሎኝ ነበር ምክንያቱም አንተን የማውቀው ስለትዳር ባስተማርከው ጠንካራ ትምህርትህ ስለሆነ። አሁን ግን ሳስበው በጣም ትልቅ ትምህርት ነው የሰጠሀን ብዙ ልብ የሚሰብሩ ነገሮች አሉ ለይቅርታ አንኩዋን አንዴት ከሆዴ ሳይዎጣ ይቅር ልበል የሚያስብል። አኔ የማውቀውን አንድ ሰው አስታዎሰኝ ሁለት ጉዋደኛሞችም ጎረቤታሞችም ነበሩ አንዱዋ በኑሮም በተሻለም ሥራ ከቤተሰቦቿ ጋር ወደ አዲስ አበባ መጥተው ይኖራሉ ከጉዋደኛዋ ጋር ይጠያየቁ ነበር በጥቂት ነገር ስቀያየሙ ግን ነገሩ መሄድ ከሚገባው በላይ ነው የሄደው ያቺን ሰውና ቤተሰቡዋን ለመጉዳት የምትኖርበት አከባቢ ድረስ አየመጣች አሱዋ አኮ ቡዳ ናት በጠናዋ መሰላችሁ ካገሩዋ የዎጣቺው ብላ ስሙዋን በማጥፋት ሰላም አንድታጣ አድርጋታለች። ነገሩ አልፎ በ አግዚአብሔር ቸርነት አና አውነት ነገሩን ቢቀይሩትም ይቅር ለመባባል የሚከብድ ነገርን ትቶ አልፎዋል። መቀያየም መጣላት መለያየት አለ ነገር ግን ይቅር መባባል አንዳይኖር አናድርገው።

  ReplyDelete
 3. ዳን የኔ ሃሳብ ሰዎች በተለያየ ምክንያት ሊጣሉ ይችላሉ። ግን በተታሉበት ጊዜ የተጣሉት ሰው በተመለከተ የሚከተሉትን ቢገነዘቡ አላለለሁ።አኔም አንደዚህ አስባለሁ።
  ፩ የተጣሉት ሰው ዛሬ በፈለጉት መንገድ ስሙን ሊያጠፉ ቢሞክሩም ከ አዚህ በፊት በ ስራው ሁሉ በጎ ነገር አንደነበረው ባይረሱ፣ ዛሬም አፋቸው አንጂ ህሊናቸው ሊዋሽ አንደማይችል፣
  ፪ ያ ሰው አንደሰውነቱ ሁሉን የማድረግ መብት የሚባል ነገር አንዳለው ብያውቁለት። የ መብላት ፣የመራመድ፣የመፃፍ፣የመተቸት፣ትክክል የመስራት አና የመሳሳት ሁሉ መብት አለው፣
  ፫ ሰዎች የራሳቸውን ሥራ መስራት ትተው ድሮ የተጣሉት ሰው የት አንደዋለ፣ዛሬ ከማን ጋር አንዳወራ፣ ነገ ምን አንደምያስብ ስቸነቁ ባይውሉ፣
  ፬ ቢያንስ ያ ሰው ዛሬ መስራቱ፣መሻሻሉ ሲሆን በተዘዋዋሪም ቢሆን አነርሱኑ አንደምተቅማቸው ቢያስቡ።ይህን ባይችህሉ አንኩአ ቢያንስ ማደጉ አና መሻሻሉ አንደማይጎዳቸው ቢያስቡ
  ምን ያጣላል የትናንት አንድ አይነት ሃሳብ ዛሬ ለምን አንድ ሆኖ አልቆየም ብለው ስቸነቁ ባይውሉ አና ባያድሩ፣
  ብዙ ሰዎች ብዙ የተለያየ ሃሳብ ይኖራቸዋል መልካችን አንደምለያይ ሁሉ።ታድያ ሰው ሁሉ አኔ አዳሰብኩት ያስብ ማለት የ ኮምፑተር ሶፍትዋር ሁሉ አንድ አይነት አሰራር ቢሆነው ማለት ይመሳሰላሉ አና ሰዎች ሀሳባቸው ቢለያይም በ አካል በሰውነት ግን ብንወዳቸው ብዬ አስባለሁ።
  ዳን ሀሳብህን ሁሉ አጋራለሁ። መለያየት የሚለው ላይ ግን ላለመለያየት በ ሃሳብ መለያየት ጠቃሚ ነው አላለሁ። ላለመለያየት በ ሃሳብ መለያየት ውይይት ይወልዳል ውይይት ደሞ መማር ይወልዳል።
  ጌታቸው

  ReplyDelete
 4. ውድ ዲ/ን ዳኒ ቃለ-ህይወት ያሰማልን። ክፍል ሁለቱ የተሻለ እና በብዙ አስተማሪ የሆነ ጽሑፍ ነው። ካንተ ጸጋዎች ውስጥ አንዱ አንባቢዎችህን በደንብ ማወቅ ነበር ዛሬ ግን የሚያድናግሩ ሀሳቦችን አንሸራሽረሀል። ለምሳሌ ተጋቢዎች አብሮ መኖር ካልቻሉ ቢፋቱ፤....."ልጂቱ እና ልጁ በፍቅረኛነት አንድ አምስት ዓመት ኖረዋል፡፡...." እንደዚህ አይነት ምሳሌዎች ካንተ ባይሰነዘሩ ጥሩ ይመስለኛል።

  ReplyDelete
 5. I think I might be wrong, but I didn't quite get it. Is the article talking about the seperation of ideas or the seperation of wife and husband, generally with people? I think it talks about both. But it is always good to have disputes in everything in some extent to generate another ideas. And of coures, it would be great to come up in one agreement! Unfortunately, our community should work a lot on these stuff. Just like you have been doing D/N Daniel.God Bless You!

  ReplyDelete
 6. አሜን ወአሜን!January 27, 2011 at 5:30 AM

  ወገኖች በሙሉ የጌታ ሰላም ይብዛላችሁ።
  ወንድም ዳንኤል፤ ምንም እንኳን መሰረታዊ እምነትህን ባልጋራም፤ በምትጽፋቸው ቁም-ነገር የተሞሉ መጣጥፎችህ ክዚህ ቀደም ብዙ ትምህርቶችን ቀስሚያለሁ። አሁን የጻፍከው ጽሁፍ ግን፤ በተለይ ክርስትያናዊ ጋብቻን በተመለከተ ፍጹም መጽህፍ ቅዱሳዊ ባለመሆኑ በጣም አዝኛለሁ። ብዙ ጥቅስ ልሰጥ እችላለሁ። ነገር ግን እግዚአብሔር ፍቺን እንደሚጠላ መጥቀሱ ብቻ በቂ ነው። እኔና ባለቤቴ ይህንን በማወቃችን ከብዙ ፈተና ልንዘልቅ ችለናል። ፍቺ በክርስትያናዊ ጋብቻ ውስጥ በምንም አይነት ሁኔታ አማራጭ አይደለም።
  ጌታ ይባርካችሁ።

  ReplyDelete
 7. hello dear Dn Daniel, I was waiting till you finish your idea regarding this article and not want to be in rush for the compliment because as much as possible I would like to follow the saying which says 'THINK BEFORE YOU POST!' this is not just for the sake of not doing a mistake sometimes we can learn by making a mistake. My intention was to get a deep insight on the article. This is the ultimate reality which we never escape from it, especially in relationship even if separation is not the only solution but there is a situation that obliged us to do so. As for me all these things could emerge due to our personal behavior and desire (hidden motives). Some behaviors will appear that we two never know it before since there is a change in physical, biological, emotional and psychological which is inevitable in our daily life. What matters here is that our response and experiences to our changes. When strange behavior emerges we should first aware of it and describe to our friends or anybody who is in relationship with us, then discussing (discussion will help us to avoid ignorance and arrogance under the shadow of friendship, in contrary when the two overlaps it become the most dangerous thing to solve and discuss over it.). Discussion is a spice in human’s life to shave a black spot in relationship, everyone can has his own thought and assumption this doesn’t mean that we should be part and parcel of one idea. Whatsoever our idea or thought discussion makes light things we assume as a big deal. In any kind of relation no one can be the same and will agree in each point but at least will have a consensus on major issues which are mandatory to their relationship. This doesn’t mean that we must ignore the silly once (even sometimes a silly thing will provoke a bigger problem).
  ‘NEVER GO TO THE BED ANGRY AT YOUR WIFE/HUSBAND’
  After all having a good understanding and discussion will shape everything to normal, people may fight, disagree over certain issues the main thing is that the mechanism we use to solve it. And having an apology heart for the wrong deed, revenge and hatred is not the manifestation of real relationship because if our relationship went for revenge and hatred initially it was based on fictional togetherness. What make things worst in relationship most of the time we focus or give to much credit for the problem rather than the solution, the more time given for the problem the coping mechanism will result in adding extra problem finding for a problem. Ones problem was identified the next step is rushing for a best solution that will perpetuate the initially established relationship. In general love only can’t assure us to live together before discussing what is our behavior, needs, emotions, strong and weak side should be stated or discuss on the verge of being in relationship. Sometimes it will help us knowing the experiences of others how they deal with problems, get along with others, make decision on certain issues which is critical to their relationship, knowing what makes your wife or husband happy and sad, is there things which you hide it from your husband/wife….bla bla. On these regard we must be careful while taking the experience of others, it may not work if we try to implement on our relationship.
  DO YOU THINK THAT WE NEED MARRIGE COUNSELLOR IN OUR RELATIONSHIP?
  The idea is great but I’m I afraid that if we are going to discuss everything which makes trouble our relationship with the counselor and even the profession is not familiarized in our country context but still we can use the service indirectly from friends or religious father and so on. What the couple doesn’t know their problem how could a counselor could make it visible.
  Lastly, the article is impressive it will help us to be rational than emotional and trigger to have a different perspective on some issues which need a clear understanding and problem identification and solving skill. MAY GOD BE WITH US!

  ReplyDelete
 8. በመጀመሪያ ቃለ ህይወት ያሰማልን፣ ፀጋውን ያብዛልህ፡፡
  በመቀጠል ያልከው ነገር ትክክል ነው በዚህ እስማማለሁ፡፡ እኔም በዚህ ብሎግ ያሰፈርከው የአንተን ስለማስብ ባጋጣሚ ፆታየም ሴት በመሆኑ አንዳንድ ወንዶች ሲቀርቡኝ በንፁህ እህትነት እቀርባቸውና ሃሣባቸውን ሲቀይሩ እኔ በእህትነት ብቻ ልቀርባቸው እንደምችል አሣምኜ በጓደኝነቴ አቀራረቤን ሣልቀይር ስቀርባቸው ለፆታዊ ግንኙነት ፍላጐት እንዳለኝ አድርገው በማሰብ በድጋሚ ጥያቄያቸውን ያቀርባሉ ካሁን በፊት እንደማይሆን ተነጋግረን እንደነበረና ለምን አሁንም ጥያቄያቸውን እንደሚያነሱ ምክንያታቸውን ስጠይቃቸው ፍላጐቱ ከሌለሽ ለምን ትቀርቢናለሽ ይሉኛል፡፡ እኔም ለፍቅረኝነት ባልሆን ለጓደኝነት መሆን እንደምችል ስነግራቸው ያኮርፉኛል፣ ይጣሉኛል፡፡ ምናልባት አብዝቸ ስጠራቸው በተደጋጋሚ የደረሰብኝ ለመጥቀስ ስለሆነ መቸም እንደምትረዳኝ ተስፋ አለኝ፡፡ እናም ብዙ ሰዎች በአንድ መንገድ ካልሆነ በቀር በሌላ መንገድ መገናኘት እንዳለ አይረዱትም እና ይሄንን ሁሉም እንዲያነቡት በተቻለኝ አቅም ጥረት እንደማደርግ ቃል እገባለሁ ምክንያቱም ውስጤን በጣም ስለገለጽክልኝ፡፡ እግዚአብሔር ይስጥልን

  ReplyDelete
 9. ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡
  ምን ይባላል?ምንስ ይጨመርበታል?ጨርሰኸው ስታበቃ።
  አንብቦ የምንረዳበትን አይምሮ ለኛ ላንተም ጥበቡን እንዲያድል መመኘት በቂ ተሳትፎ ነው። በቃ ተወያየንበት ተመስገን።በሌላ ጦማር እንገናኝ።

  ReplyDelete
 10. Dear Daniel,

  I know a story that personally happend in my family. One of my family members went to Ethiopia and signed papers for a girl friend of another family memeber, after coming to america within four months the girl left saying she couldn't live with the family member. It was really shocking and nothing we expected. We all felt that she betrayed us specially the family memeber who trusted her and loved her. We cut all communications with her, because it is not bad enough that she did that, but after she left the house she talked major lies about the family to another family who we consider not our friends. So it made everything worse....Meleyayet Kifu new gin if it has to happen lets make it peaceful.

  ReplyDelete
 11. with regard to marrage
  no need to establish new rule. It is already stated by our spritual fathers and better to advice your readers to follw it. I think it cant be changed by discussion. I understand your intention but what you wrote today lucks the spritual tone,and ignors the power of pray, the support of GOD and saints. This also works for all types of relationships. departures should be peaceful but for non marriage relationships.

  Marrage is different from all other types of relationships.

  Abiot,
  Oldenburg, Germany

  ReplyDelete
 12. I agree with all the parts(one and two).This is a wonderful article. we should see it practically. The examples are really impresive and surprisingly convincing. Look! everybody, what would you feel if the same story happened for you like the one whose fiance flew to Uganda during the wedding day.
  Amlake Esrael kefetena tebikegn. sint gud ale!
  "kifun bekifu atikawomu..."
  And I appreciate you all who wrote against the article. "kale hiwot yasemalin " bicha ayitekimim. This is his view, not a general truth that everybody should agree with.
  mekuanint

  ReplyDelete
 13. last two anonymous
  what is something new that makes u agreed with this topic ! i found nothing new. still i am not agreed!<>

  ReplyDelete
 14. ዲ.ዳንኤል

  የእግዚአብሔር ቸርነት አይለይህ

  ሀሳብህን ወድጄዋለሁ እንደአጋጣሚ ሁለት በቅርብ ከትዳራቸው የተፋቱ ዘመዶች አሉኝ ሁለቱም በፍርድ ቤት ንብረት በመከፋፈል ላይ ናቸው፡፡ አንደኛቹ ጥንዶች ፍርድ ቤት ሁሉ አብረው ሄደው በሰላም አብረው ውለው ከዚያም መልስ አንዳስፈላጊነቱ አብረው ከጋራ ወዳጆቻቸው ጋር ጥሩ ጊዜ ያሳልፋሉ በተቃራኒው ሌላኞቹ ደግሞ ፍርድ ቤት ውስጥ ሲሰዳደቡና ሲገለማመጡ ውለው ይለያያሉ፡፡ የዛኛው ቡድን ወንዱና የዚህኛው ሴቷን በአጋጣሚ አንድ ላይ ቤተዘመድ ሁሉ ባለበት ተገናኝተን ስንጫወት ግማሹ ከተጣሉ አይቀር እንዲህ ነው፣ በሰው ፊት እየሰደበች ማዋረድ ነው እንጂ አንተማ ወንድ አትባልም ደሞ ከተለያዩት ሰው ጋር በፍቅርና በሰላም መዋል እያለ ሲወተውት እኔ ደሞ በፍቅር መለያየት ለልጆችም ለቤተሰብም ጥሩ ነው ከሚለው ወገን ነበርኩ፡፡ እና ይሄ በሰላም የመለያየት ነገር ቢዳብር ከሐይማኖትም አንጻር ቂምን ለመተው እና በፍቅር አብረን ለመኖር ይረዳናል የሚል ሀሳብ ነው ያነኝ፡፡

  ቸሩ መድሃኒአለም ፍቅሩን ያብዛልን

  ReplyDelete
 15. የማይበላ እንዳያስበላ ያብላላJanuary 29, 2011 at 12:36 PM

  Related to our church, for all genuine Ethiopian Orthodox Tewahedo followers there is nothing makes us happy than watching all of our church fathers come together, reconcile and build a very strong EOTC. In fact, this has been a long time dream for all of us. However, our dream is going to change to nightmare just like what happened to the bride and her families by the evil plan of the pretender groom who avoided the wedding and left to Uganda. Unlike the bride and her families, we exactly know what the plan of the reconciliation is. The whole reconciliation initiative at this time is designed not to build our church but to destroy it. The initiators of this reconciliation and the enormous destruction they have been doing is out there in the open for every body to see, so for most of us to keep silent is so outrageous to say the least.

  ReplyDelete
 16. "መቀያየም መጣላት መለያየት አለ ነገር ግን ይቅር መባባል አንዳይኖር አናድርገው።"

  ReplyDelete
 17. ዳንኤል በጣም ጥሩ ሃሳብ ነው፡፡ ሁላችንም ልንወያይበትና የህይወት ገጠመኝ ካለንም ልናካፍልና ልንማማርበት የምንችልበት መድረክ ነው፡፡ ህይወታችን የብቀላ ፡ የአልሸነፍ ባይነት የሚበዛበት ከሆነ ብዙ ልንማርበት እንችላለን፡፡ መለወጥ ከራስ ነውና የሚጀምረው እራሴን ጨምሮ የጡመራው ተከታታዮች ብዙ እንደተለወጣችሁ ተስፋ አደርጋሁ፡፡


  ከተለያዩ በኃላ በሆነ አጋጣሚ መገናኘት ላይቀር ምናለ አፋችንን ባናበላሽ፡፡ እኛስ ለምን ህሊናችን እንዲወቅሰን እድል እንሰጠዋለን፡፡ ሰው እኮ በተፈጥሮው የሚያመዛዝንበት አዕምሮ አለው፤ ጭካኔን ፡ መጥፎ ንግግርን ያደረጉ ሰዎች እራሳቸው ከተለያዩ ከጥቂት ጊዚያት በኃላ ይጸጸታሉ፡፡ ለዚህም ይመስለኛል አንዳንዶቹ አዕምሮአቸው ሰለሚያቆስላቸው፡ በደለኝነታቸውን ስለሚነግራቸው ራሳቸውን እስከማጥፋት የሚደርሱት፡፡ ለትንሽ ጊዜ ራሳችንን መቆጣጠር ተስኖን ዝንታለም ለምን ህሊናችን ሲወቅሰን ይኖራል፡፡ ወንዶች፡ ሚስታችን ብትጣላን የልጆቻችን እናት እኮ ናት ሌላው ቢቀር በጋራ ስላሳለፍናቸው ዓመታት ና ጊዚያት ስንል ምናለ በሰላም ብንለያይ፡፡ ሴቶችስ ፤ ባሎቻችሁ እኮ የልጆጃችሁ አባት ናቸው በተጨማሪ ጥሩ ጊዜያትን አንድ ላይ አሳልፋችኃል እና ስለዚህ ብላችሁ ምናለ በፍቅር ብትለያዩ፡፡

  ትዳር እንደ እኔ ከሆነ በጣም አስቸጋሪ ግንኙነት ነው፡፡ ትዳር አያስፈልግም ለማለት አይደለም፡፡ መጀመሪያውኑ ከማግባት በፊት ትልቅ ዝግጅትን የሚጠይቅ ይመስለኛል፡፡ ገንዘብ ፤ ቤት መኪና … ሌላም ሌላም አይደለም፡፡ የአዕምሮ ዝግጅት ፡ በሃሳብ መስማማት፤ መተዋወቅ፡፡ ሌላው የትዳር አጋር ሙሉ በሙሉ እኛ በምንፈልገው መልኩ ማግኘት የምንችል አይመስለኝም ምክንያቱም እንደ እኔ የሚያስብ እንደ እኔ ነገሮችን ሊያከናውን የሚችል ሰው አንድ እኔው እራሴ ነኝ፡፡ ስለዚህም የሃሳብ ልዩነት እንደሚኖር ልናምን ይገባል፡፡ ዋናው ቁምነገሩ ግን አንድ ተግባር ለመፈጸም ልዩነት ካለ እንዴት ነው ልዩነትን ማጥበብ የሚቻለው መሆን አለበት፡፡ በጸሎት በምክር በመተሳሰብ ትዳር መጎልበት ይገባዋል ብየ አስባለሁ፡፡ ከሁሉም በላይ በመሸነፍ ማሸነፍ እንዳለ ማመን ተገቢ ይመስለኛል፡፡ ለነገሩ ግን ትዳር መጀመሪያውንም የመሸናነፊያ መድረክ አይደለም፡፡ ተጋግዘው ህይወትን የሚመሩበት እንጂ፡፡ ባጠቃላይ የእኔ ሃሳብ፡- በትዳር ውስጥ ችግር ሲፈጠር ቢቻል በቻል በእንጨጩ (ራሳቸው ተጋቢዎቹ) ካልሆነ ግን የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም መሞከር፡፡ ካልሆነ ግን በሰላም ቢፋቱ ይሻላል እላለሁ፡፡ በፖሊስና ኅብረተሰብ ዝግጅት እንደሚቀርቡ አሳዛኝ ገጠመኞች እንዳይሆኑ፡፡

  ከትዳር ውጭ ያሉ የማኅበረሰባችን ግንኙነቶችንን (ሥራ ፡ የንግድ ተጋሪነት) ግን ከትዳር በበለጠ በቀላሉ ልንፈታቸው የምንችላቸው ይመስለኛል፡፡ ሥራ ከሆነ ሥራ ነው ያገናኘንና ሥራው ላይ ትኩረት ሰጠን መንቀሳቀስ፡፡ ህግ በራሱ እንደዚህ አይነት ነገሮችን ለመቆጣጠር የሚችል ይመስለኛል፡፡ በሁሉም ቦታ ግን ሌላ ጊዜ መገናኘት ላይቀር መደማማት መቆሳሰል አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡ በመደማማትና በመቆሳሰል ያለቀ ግንኙነት በእኛ አገር ደግሞ የይቅርታ ባህልም ስለሌለን መቼም አይስተካከልም፡፡

  ምንጊዜም ቢሆን አስተዋይነቱን አምላክ ይስጠን፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 18. ያጣነው ትምህርት ቤት
  ሴትየዋ ከሰው ጋር አብሮ የመኖር ዕቅድ ያዙና ትንሽ መንገድ አበረው መጓዝ ጀመሩ፡፡ በዚህ የአብሮነት መንገድ ከተጓዙበት ይልቅ በመንፈሳዊ አገልግሎት በንጹሕ ባልንጀርነት ያሳለፉት ጊዜ በሰባት ያህል ጊዜ ይበልጣል፡፡
  ቀደም ሲል ነበብኳቸውና በተለያዩ አርዕስት የወጡ ጽሑፎች በሙሉ ትኩረታቸው የላሸቀውን የማኅበረሰብ ማንነት (እሴት) በመገንባት ላይ የሚያተኩሩ ናቸው የሚል እምነት አለኝ፡፡ አገር የምንለውን ሥዕል መፍጠር የሚቻለው በመልካም መሠረት ላይ የተገነባ ማኅበረሰብ ነው፡፡ ለዚህ ደግማ ሃይማኖት፣ሞራል፣ወግ (myth)፣ሕግ ያለው ሕዝብ ያስፈልጋል፡፡ ሕግ የሚከበረው የሞራልና የሃይማኖት መሠረቱ የቀደመውን ማኀበረሰብ ወግና ልማድ በመጠበቅ ላይ የተገነባ ማኅበረሰብ ሲኖር ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ፍቅር፣ጥላቻ፤ መወዳጀት፣መለያየት፤መጋባት መፋታት፤ ደግነት፣ሴራ በየትኛውም ማኅበረሰብ መኖራቸው የግድ ቢሆንም በኢትጵያችን የሚታየውን የሃይማኖት፣የሞራልና የወግ መላሸቅ አሳሳቢነት በቸልታ ማለፍ የሚቻል አይመስለኝም፡
  ከዚህ አንጻር ይህ ጽሑፍ በጥቅሉ ከሚቀርብ ይልቅ በዝርዝር እያንዳንዷን ክስተት እየፈለፈለ፣ አያበሰለ ቢሆን ተጠቃሚው ወገን ብዙ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ስለጾታዊ ጓደኝነት፣ስለእጮኛነት፣ስለጋብቻ፣በሥራና በትምህርት ምክንያት ተለያይቶ ስለመኖር፣ስለባልንጀርነት፣ስለጉርብትና፣ስለፖለቲካዊ አቋም … ወዘተ እያለ ቢቀጥል ታዳሚው የየራሱን የሕይወት ተሞክሮ እየቀመረ አስተዋጽኦ በማድረግ በዚህ ጽሑፍ በምሳሌነት የቀረቡት ጥቂት ማስረጃዎች በተትረፈረፈ ማስረጃ ተጠናክረው መቅረብ ይችላሉ፡፡ ይህም በመሆኑ አንደኛው ለሌላኛው ወገን የራሱን እሳት በማዋስ የመማሩ ሂደት ሦስተዮሻዊ ይዘት ይኖረዋል፡፡ የሚፈለገው ቁብነገር እነዚህ የክርስትና ሕይወት፣ የመልካም ማኀበረሰብ ጠንቅ የሆኑ እኩዮች ቢቻል እንዲጠፉ ካልሆነም በመጠን እንዲቀንሱ ማዳረግ ነውና፡፡ ልብ ብለን እንደሆነ ለሥራና ለሞያ የሚፈስፈልገንን ትምህርት ለማግኘት በማንቸገርበት ዓለም ፈልገን ልናገኝ ያልቻለው ትምህርት ቤት ቢኖር ይህን ነውና ሰፊ፣ጠልቅና ዘላቂ ትምህርት ቤት ብናደረገውስ?

  ReplyDelete
 19. በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ። አሜን!!

  ለዲ/ን ዳንኤል ክብረት በክፍል አንድ ላይ ትንሽ አድናቆት ቢጤና እንዲህ የሚል ጥያቄ አዘል አስተያየት ሰጥቼ ነበር። “በዚህ ርዕስ ላይ "አልጋ ለይተው፤ ሰላምታ ተነፋፍገው፣ ቃላት ሳይለዋወጡ፣ የሂሳብ አካውንት ለያይተው፤ ጀርባ ተሰጣጥተው የሚኖሩ ስንት ባል እና ሚስት አሉ፡፡ ለሠርግ ሲጠሩ ግን «ከባለቤትዎ ጋር» እየተባሉ የሚጠሩ፡፡ ለምን እውነታውን አምነን መፍትሔ አንፈልግም፡፡ ያለበለዚያ ደግሞ ለምን አንለያይም፡፡" ብለሐል። ይህ አባባል ያለ ዝሙት ምክነያት ብቻ እንዳንለያይ የሚያዘንን ቅዱስ ቃሉን አይቃረንም?” የሚል ነበር። እናም ክፍል ሁለት ይቀጥላል ሲል መዝጊያውን ሊቀይረው ይችላል። ሳይጨርስ አስተያየት ለመስጠት ለምን ቸኮልኩ? እያልኩ ነበር። ነገር ግን ያንኑ ሐሳቡን በማዳበሩ እጅግ አዘንኩኝ። እንደኔ እምነት ምንም ይሁን ምን መለያየትን የሚያበረታታ ይህን አይነት ሐሳብ እንኳን ከአንድ ከተወደደ የቤተ-ክርስቲያን ሰው ይቅርና እኔ መሐይሙም ቅዱስ ቃሉን እንዲህ ለማቃለል አልደፍርም።ደግሞም ቅዱስ ቃሉን ከመቃረንና ከመዳፈር በላይ ምን ጥፋት አለ? ዳኒ አበጀህ በርታ የምትሉትስ እሱ ተወዳጅና የተከበረ የተዋህዶ ልጅ ስለሆነ አይሳሳትም ብላችሁ ነው? ወይስ በዘፍ 2፡24 በማቴ 19፡5-6 በማቴ 19፡9 እና በሌሎችም የተቀመጠውን የእግዝአብሐረን ቃል ካዳችሁ? አንዳንዴ እኮ ዲ/ን ዳንኤል ሲሳሳት በስሜት ተነድተን ያልተገባ አስተያየት ከምንሰጥ ተሳስተሐል ብንለው ምናልባት እሱ ራሱ ሊቀበለው ይችላል።

  እግዝአብሔር አስተዋይ ሕሊና ቅን ልቦና እንዲሰጠን የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን። አሜን!!
  መርከቤ ንጉሴ/ከአዲስ አበባ/

  ReplyDelete
 20. በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ። አሜን!!

  ለዲ/ን ዳንኤል ክብረት በክፍል አንድ ላይ ትንሽ አድናቆት ቢጤና እንዲህ የሚል ጥያቄ አዘል አስተያየት ሰጥቼ ነበር። “በዚህ ርዕስ ላይ "አልጋ ለይተው፤ ሰላምታ ተነፋፍገው፣ ቃላት ሳይለዋወጡ፣ የሂሳብ አካውንት ለያይተው፤ ጀርባ ተሰጣጥተው የሚኖሩ ስንት ባል እና ሚስት አሉ፡፡ ለሠርግ ሲጠሩ ግን «ከባለቤትዎ ጋር» እየተባሉ የሚጠሩ፡፡ ለምን እውነታውን አምነን መፍትሔ አንፈልግም፡፡ ያለበለዚያ ደግሞ ለምን አንለያይም፡፡" ብለሐል። ይህ አባባል ያለ ዝሙት ምክነያት ብቻ እንዳንለያይ የሚያዘንን ቅዱስ ቃሉን አይቃረንም?” የሚል ነበር። እናም ክፍል ሁለት ይቀጥላል ሲል መዝጊያውን ሊቀይረው ይችላል። ሳይጨርስ አስተያየት ለመስጠት ለምን ቸኮልኩ? እያልኩ ነበር። ነገር ግን ያንኑ ሐሳቡን በማዳበሩ እጅግ አዘንኩኝ። እንደኔ እምነት ምንም ይሁን ምን መለያየትን የሚያበረታታ ይህን አይነት ሐሳብ እንኳን ከአንድ ከተወደደ የቤተ-ክርስቲያን ሰው ይቅርና እኔ መሐይሙም ቅዱስ ቃሉን እንዲህ ለማቃለል አልደፍርም።ደግሞም ቅዱስ ቃሉን ከመቃረንና ከመዳፈር በላይ ምን ጥፋት አለ? ዳኒ አበጀህ በርታ የምትሉትስ እሱ ተወዳጅና የተከበረ የተዋህዶ ልጅ ስለሆነ አይሳሳትም ብላችሁ ነው? ወይስ በዘፍ 2፡24 በማቴ 19፡5-6 በማቴ 19፡9 እና በሌሎችም የተቀመጠውን የእግዝአብሐረን ቃል ካዳችሁ? አንዳንዴ እኮ ዲ/ን ዳንኤል ሲሳሳት በስሜት ተነድተን ያልተገባ አስተያየት ከምንሰጥ ተሳስተሐል ብንለው ምናልባት እሱ ራሱ ሊቀበለው ይችላል።

  እግዝአብሔር አስተዋይ ሕሊና ቅን ልቦና እንዲሰጠን የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን። አሜን!!

  ReplyDelete
 21. አንደምን አለህ ወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል? ይህ ያነሳሀው ሃሳብ ጥሩ ነው በተለይ ያንተን ሃሳብ ገልፀህ የኛንም አንድንገልፅ ስላቀረብቀው ደስ ብሎኛል። አብዛኞቻችን ባቀረብከው ሃሳብ አንስማማለን ብዬ አስባለሁ ስለትዳር ከተነሳው ውጭ። መፅሐፍ ቅዱስ አንደሚነግረን አንተም ስለትዳር ባስተማርከው ትምህርትህ ከሃይማኖት አና ከዝሙት ምክንያት ውጭ ፍቺ መኖር አንደሌለበት አስተምረሃል ነገር ግን አየሆነ ያለው በተቃራኒው ከጋብቻ ይልቅ ፍቺ የበዛበት ወቅት ነው ከዛም ብሶ ደግሞ ከፍቺ በውሃላ ያለው የመቆሳሰል ነገር ስናየው ለፍቺ ካበቃቸው ምክንያት በላይ አየጎዳቸው የባሰ ችግር አና ሰላም ማጣት ውስጥ አየከተታቸው ስለሆነ ለምን በሰላም አብረው መኖር ካልቻሉ ለምን ተለያይተው አንኩዋን ሰላም ለመፍጠር አይሞክሩም ወደሚለው ሃሳብ ሊመራን ይችላል። ነገር ግን አናንተ መምህራኖች ስትመክሩን ትዳርን በተመለከተ ከዝሙት በስተቀር ትዳርን ሊፈታ የሚችል ምንም ምክንያት አንደሌለ ሁሌም በአጽንኦት መሆን አለበት ምክንያቱም አንደዚህም አስተምራችሁ አልሆነምና ነው።

  ReplyDelete
 22. Danie, It is difficult to do that unless we believe God could make us strong. You see when we grow up, our society (family, neighbors, school, government and all around us)taught and made us to practice on that way. We build this since we are in our mothers womb. It needs great effort to change the software in our mind. The church mainly, the government and each of us should go for revolution. We may have hope for the coming generation. I got great lesson from your positive approach. Amilake kidusan yirdan. May God bless you.

  ReplyDelete
 23. አሁንም ቢሆን እኔ ሃሳቡን ደጋፊ ነኝ:: እንዴው በሆነ ባልሆነው ካልሆነ በስተቀር ተብሎ .....ተመክሮ.....ለውጥ ከለለ ስለምንድን ነው አብረው የሚኖሩት::ለምን ጥቅስ እየጠቀስን እናወናብዳለን:: እስኪ ሁላችሁ ፍረዱት :: የቱ ይሻላል? በጥላቻ ኑሮ ወደገሃነም መውረድ ወይስ ተለያይቶ በፍቅር ኖሮ የመንግስቱ ወራሽ መሆን ? አሁንም ማለት የምፈልገው ያለ ፍቅር ይእግዚአብሐር ልጅ መሆን ሰለማይቻል እጅግ ከፍተኛ ሙከራ ከተደረገ በሁዋላ ካልተቻለ መለያየት ይሻላል::
  የሰው ልጅ ግን ለምን እውነትን ይደብቃል? ለምን እውነት የሆነውን ነገር እናጣምማለን?
  "እኩይ ብእሲ ሃይማኖተ ያቀድማ ለነገሩ" እንዲሉ እንዳይሆንብን?

  ReplyDelete
 24. በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡
  በመጀመሪያ ሰዎች ልትረዱት የሚገባ የተባለው ተለያዩ/ትዳራችሁን ፍቱ/ አይደለም ነገር ግን አብሮ ለመኖር የሚያስችል ሰላምና መሠረታዊ የሆኑ ነገሮች ከሌላችሁ ሳትጐዳዱ መልካም ጓደኝነትን መስርታችሁ በትዳር ያላችሁም መልካም ጐረቤት ልትሆኑ ትችላላችሁና ከመጐዳዳት፣ የማይረሳ ጠባሳ ከመተው ይልቅ በሰላም መኖር እንደሚቻል የገለፀበት ጽሁፍ ነው፡፡ በርግጥ የሁላችንም አረዳድ የተለያየ ስለሆነ አልፈርድባችሁም ነገር ግን ሰውን ከመተቸት ጽሁፉን ደጋግማችሁ ብታነቡት መልካም ነው፡፡ ከግሞም እርሱ እውነትን ስለፃፈ እንጅ በየቤቱ አስመስለው እየኖሩ፣ እየተበጣበጡ የልጆችን ስለ ልቦና የሚጐዱ ትዳሮች ስንቶች ናቸው ቤቱ ይቁጠረው ትውልድን የሚገድሉ ቀጣዩ ትውልድ ትዳርን እንዲጠላና ለትዳር ያለው አመለካከት እንዳምታታበት ያደረጉ ስንቶች ናቸው፡፡ ብቻ እግዚአብሔር በቸርነቱ ማስተዋልን ይስጠን፡፡
  ወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል ፀጋውን ያብዛልህ፡፡

  ReplyDelete
 25. ዳኔል....

  የሁሉም ነገር መነሻና መድረሻ አለው:: ስንጀምርም ስንጨርስም በበጎ እና በቀና አስተሳሰብ ቢሆን: የራሳችንን አስተሳሰብ እና ፍላጎት ብቻ አስቀድመን ባይሆን: ያንዳችን ብርህን ለሌላኛችን ውበት ሆኖን ጨለማውን ማቅለጥ በተቻለን ነበር::ይህ እንዲሆን እንትጋ

  ድንቅ እይታ ነው....ተባረክ

  ReplyDelete
 26. +++
  በዚህ ብሎግ ውስጥ ሰፋ አድርገን ብናያቸው ብዬ የማስባቸው ነገሮች አሉ፡፡ የመጀመሪያው ወንድማችንን ዲ. ዳንኤል ክብረትን የምናውቅበት መገለጫው አለ ፤ ያም እጅግ ጥሩ የሆነና ሕይወታችንን የሚለውጡ የቤተክርስቲያናችን መምህር ነው ፤ አገልጋይ ነው ፤ ለቤተክርስቲያናችን የሚጠቅሙ ሰፋፊ እን ጥልቅ የጥናት ሥራዎችን የሚሠራ ተመራማሪ ነው ፤ አዳዲሰ ሀሳቦችን በማፍለቅ የሚመለከታቸውን በማወያየት ለለውጥ የሚተጋ ነው፤…
  በሁለተኛ ገጹ ደግሞ በጥቂቱ እንደማውቀው ባለትዳር ነው ፤ የልጅ አባት ነው ፤ የራሱ ኑሮ አለው ፤ የራሱ አስተሳሰብ አለው ፤ የራሱ ገጠመኝና የሕይወት ልምድ አለው ፤ ….
  ስለሆነም በሚጽፋቸው ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሁሉ የጽሑፎቹ ዳራ በመንፈሳዊ ሕይወት ዙሪያ ብቻ ፣ በቃ ጥሩ ጥሩ ነገር ብቻ እንዲነሳ መጠበቅ የለብንም፤ ይልቁንም እነዚህን ሁለት አቅጣጫዎች በማጣጣም ቢሆን የእኛም የእይታ አድማሳችን የሚሰፋ ይመስለኛል፡፡ በተጨማሪ የተለያዩ ሰዎች በሚሰጧቸው አስተያየቶች ፣ ትችቶች…የእኛም የእይታ አቅጣጫ እንዲሰፋ እንደሚያደርጉ አስባለሁ፡፡
  አለበለዚያ የሚሆነው መልካም ያልሆኑ የሕይወት ገጽታዎች ሲነሱ ፣ ጥሩ ያልሆኑ የሕይወት ገጽታዎች ይዘነጉና ችግሮች ሲገጥሙን ለመፍትሔዎቹ የዘገየነን እንሆናለን፡፡ እናም አመለካከታችን የሰፋ የሚሆነው ነገሮችን ከተለያዩ አቅጣጫዎች ከመልካሙም ከክፉውም አንጻር ስንመዝነው ነውና የዚህ ዓይነቱ የውይይት ይዘት በአዎንታዊ መልኩ ሊዳብር ይገባዋል፡፡
  ሌላው ስንቶቻችን ገና በጓደኝነት ሳለን በትዳር ስለሚኖሩ ችግሮች እንወያያለን ? ለምሳሌ ልጅ ባንወልድስ እንዴት ነው የምንኖረው ? አይበለውና እንደው የከፋ ግጭት ብንጋጭ እንዴት እንፈታዋለን ? አንዱ አካል በጥፊ ቢማታ ወይ ቢመታ … ወዘተ እስኪ አስቡት ስሜታችን ምን ሊሆን እንደሚችል፡፡ ቀድሞውኑ በውስጡ የመረጋጋት ፣ ችግሮችን የመፍታት ፣ የሰከነ ስሜት ያለው የርዕሶቹ መነሳት አያስደነግጠውም ፤ ምን ሊያደርግ እንደሚገባው ፣ የእርሱ አቅም እስከምን እንደሆነ ለማሰብ ይሞክራል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ችግርን የመፍታት የትዕግስታችን መጠን አናሳ ከሆነ ስሜታዊ ሆነን አሁን እንዲህ ያለውን ሀሳብ ምን አመጣው በሰላሙ…ልንል እንችላለን፡፡
  ስለዚህ ትዳራችንን ለመጠበቅ እንዲሁ በመልካም ሀሳቦች መሞላት ፣ መልካም በማውራት የሚሰምር ፈጽሞ አይደለም፡፡ ይልቁንም በመንፈሳዊ ሕይወት የመኖር ፣ በአመለካከት ታጋሽ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ነገሮችን የመመዘን አቅማችን እየተሻሻለ ሲሄድ ፣ የመቻቻልን መሰረታዊ እውነታ መረዳትና በሁለቱም ወገን ተግባራዊ የማድረግ ልማድን በማዳበር እና በመሳሰሉት እንጂ፡፡
  ስለሆነም ያገባንም ያላገባንም የሀሳቦችን ፣ የሕይወት ገጠመኞችን ከመልካም ገጽታቸው አንጻር ብቻ ለመስማት አንፈልግ፤ የሚከፈልለትን ዋጋ እንዳንረዳ ያደርገናል፤ የእኛን አቅም እንዳንመዝን እና እንዳናሻሽል ይከልለናል፡፡
  ገነት መንግስተ ሰማያት ለመግባት እኮ መልካሙን ዜና ብቻ እየሰሙ መኖር በቂ አይደለም፤ መከራውን ፣ ፈተናውን ፣ ምን ዓይነት መስዋዕትነት እንደሚከፈልለት ማወቅም መኖርም እንጂ፡፡ አለበለዚያ ልክ አሁን ብዙዎች እንደምንኖረው ብቻ እያወራነው ከሆነ ብርሃናችን በሰው ፊት ሊበራ ይቅርና ለራሳችንም ሳንሆን እንቀራለን፡፡
  ስለዚህ ትዳራችን እንዲጸና ፣ መልካም ትዳርም እንዲሰጠን ለራሳችንም ፣ ለቤተሰባችንም ፣ ለወገንም ፣ ለሀገርም እንድንሆን በመንፈሳዊ ሕይወታችን ፣ በማኅበራዊ ሕይወታችን አብዝተን ልንተጋ ልንሻሻል ይገባናል፡፡
  እናም ወንድማችን ዲ. ዳንኤል ክብረትን እግዚአብሔር አምላክ ይጠብቅልን፡፡
  የዚህ ዓይነቶቹ ሀሳቦ መነሳታቸው ጠቀሜታ ስለሚኖረው አንሽሸው፡፡

  ዘደብረ ካራን

  +++

  ReplyDelete
 27. In So Many Parts when Our Lord Jesus Christ talked about Marriage he specifically said a husband and wife are one. And The Apostle St. Paul said Just like Jesus Loved the church a husband should love his wife and vice versa. Jesus Loved the church till death, A husband is the head of his wife as Christ is the head of the church. " So i have a question what happens if the husband doesn't love the wife, as Christ loved the church? If he is shooting at her and hitting her with any thing he found on his way, or abusing her beyond imagination what happens then?

  ReplyDelete
 28. You are 100% right. I couldn't agree more. What you were trying to say was: if people are in position to disagree or decided to never agree to anything what is the use of wasting our and the other person's life. Daniel is not supporting divorce. He is saying if they could not love their partner they should separate amicable. This is no sin because they could no more love their partner. What is actually sin is pretending that you love your partner until you meet your evil goal( Like the Uganda and Chicago case).

  You are trying to express your view. It could be wrong or right. That is entirely subjective.I may not agree with you all the time. That is natural because no one is perfect. I commend you for expressing your mind without reluctance. There is no such thing " Think twice before you post"

  ReplyDelete
 29. ወንድማችን ዲ. ዳንኤል ስላስነበብከን ነገር እግዚአብሔር ይስጥልን፤፤

  እስኪ ሁለት ነገር ልጠይቃችሁ የዲ. ዳኒ ሀሳብ ያልተዋጠላችሁ ሰዎች ፣ መለያየት የማይቀርለትን ማንኛውም ግንኙነት የትዳርም ሆነ ሌላ ግንኙነት የመለያያ መንገዱ
  በሰላም ( ጉዳት ሳይደርስ ማለትም ውጤቱ ሰላምን የሚሰጥ ለማለት ፈልጌ ነው) ቢሆን ይሻላል ወይስ ጉዳት አድርሶ ጠባሳ ጥሎ ሕይወት ጠፍቶ ፣ አንደኛው ወገን አብዶ፤ የተለያዩ ማሕበራዊ ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ስነ ልቦናዊ ችግሮችን አስከትሎ ቢፈፀም የትኛው ይሻላል

  ሌላው ያለዝሙት ምክንያት መፍታት አይቻልም የሚለውን ህግ ብቻ ይዘን ሰዎች መግባባት አቅቷቸው የአንዱ ሕይወት ጥያቄ ውስጥ ገብቶ ( ወደ ሞት አፋፍ ቀርቦ) ፤ አካሉ ቢጎዳ መፋታት የለባቸውም ብለን አሁንም ባቋማችን እንጸናለን እግዚአብሔርስ ደስ ይለዋል ብላችሁ ታስባላችሁ

  አካል ተጎድቶ፤ የአንዱ ሕይወት ጠፍቶ ( ዘላለማዊ ፍቺ ተፈጽሞ /በፀብ ሕይወት እስካለፈ ድረስ/ ) ከሚፋቱ እነዚህ ነገሮች ከመፈጸማቸው በፊት ጊዜውን ወደዚህ በማምጣት በሰላም ቢለያዩ አይሻልም ትላላችሁ /
  አደራችሁን ቀኑ ስለደረሰ ነው የሞተው ፤ አካሉ የተጎዳው የሚል argument እንዳታመጡ እሱ እራሱን የቻለ ርዕስ ነው ለማለት የፈለኩትን ብቻ ተረዱኝ፤፤

  በደንብ መጽሐፍ ቅዱስን ስለማላውቅ ከተሳሳትኩ መልሱኝ እስራኤላውያን አንደኛው ወገን ካልሞተ በቀር መፋታት አትችሉም አንድ ወንድ ለአንድ ሴት ሲባሉ እርስ በርስ መጠፋፋት ሲጀምሩ ሌላ ህግ ወጣላቸው ስለልባቸው ክፋት ሲባል ይህ ምንድነው
  የሚያስተምረን ሌላው ደሞ መጽሐፍ ቅዱስ እና ሌሎች ቅዱሳት መጻህፍት ለዚህ መልስ ያላቸው ይመስለኛል አንድ ጥቅስ ብቻ ይዘን ግራ እየተጋባን ይመስለኛል መጽሐፍ ቅዱስን በደንብ ባላውቅም ምሉዕ ነው ብዬ ስለማስብ ለዚህ የሚረዳ ነገር አይጠፋውም አንድምታ ትርጓሜ ያለው በመሆኑ ቃል በቃል ብቻ አንብበን ስለማንረዳው፤፤ በተጨማሪም ሌሎች ቅዱሳት መጻሕፍት ለዚህ መልስ አላቸው ብዬ
  አስባለሁ፤፤ በዚህ ዙሪያ ዳኒና ሌሎች እውቀቱ ያላችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ ብታስረዱን
  ጥሩ ነው፤፤

  ወንድማችንን እኔ የተረዳሁት መለያየት ግድ ለሆነበት ትዳር ( ሌሎችም ግኑኝነቶች) የመለያያ መንገዱ ሰላማዊ ጠባሳ የማይጥል ቢሆን ጥሩ ነው፤፤ ይሄ ታዲያ ልክ እኮ ነው እሱ እኮ ያለው በረባውም ባረባውም እንድንፋታ ሳይሆን ፍቺ ግድ በሆነበት ጊዜ
  ያለጉዳት ብንለያይ ጥሩ ነው ፤ በርግጥ ስለ ትዳር ጥሩነት በትዳር ውስጥ ስላለው መቻቻል በደንብ አድርጎ ነግሮናል በስብከቱ ላይ ፣ ይሄ ማለት ግን ከሚናገረው ጋር ይጣረሳል ማለት አይደለም፤ አንዳንዴ ደሞ አንድ ሰው የተለያየ ነገር ሊናገር ይችላል ግን የተላያየ ነገር ለተለያየ case ሊሆን ስለሚችል የግድ አንዱ ለሁሉም case ይሁን
  አይባልም፤ ንግግሩም ተጣረሰ ማለት አይቻልም ከምን አንግል እንደተባለ መረዳት አለብን እንጂ የመጨረሻ መደምደሚያውን ብቻ ይዘን ባንደነጋገር ጥሩ ይመስለኛል፤፤

  እግዚአብሔር አንድነታችንን ይባርክልን ይጠብቅልን

  ReplyDelete
 30. ዲ.ን ዳንኤል እግዚአብሄር ያገልግሎት ጊዜህን ይባርክልህ
  እኔ እየኖርኩበት ያለሁበትን የስቃይ ህይዎት እንዴት በሠላም መፉታት እንዳለብኝ ተምሬበታለሁ

  ReplyDelete
 31. ሰላም ላንተ ይሁን ዲያቆን የስንቱን አይምሮ ኮረኮርከው ተባረከው እድሜህ ይርዘም!!!!!!

  ReplyDelete
 32. ወንድም ዲ/ዳኒ ያለሁበትን ህይወት ስለሆነ በብዙ እየተማርሁበት ነዉና ይቀጥል!!!!!!!

  ReplyDelete