Tuesday, January 25, 2011

«ልርሳህስ ብል ብርዱ መቼ ያስረሳኛል»


ከአንድ ባሕታዊ ጋር ቁር በበዛበት ተራራ ላይ የተጠጋ አንድ ወጣት ነበር፡፡ ያገኟትን እያካፈሉት፤ ከዋሻቸው እያስጠጉት ጥቂት ጊዜያት ተቀመጠ፡፡ ልጁ ከባሕታዊው ጋር መቀጠል አልፈለገም፡፡ የእርሳቸው የኑሮ ሥርዓት ከእርሱ የኑሮ ሥርዓት ጋር ሊገጥም አልቻለም፡፡ ግን ደግሞ እንዴት አድርጎ ይለያቸው፡፡
አንድ ቀን ባሕታዊው ምግብ ፍለጋ ሄደው ዘገዩ፤ ልጁም በጣም ራበው፡፡ ከመራቡ ብዛት አዞረውና ወደቀ፡፡ ባሕታዊው ምግቡን ይዘው ሲመጡ ልጁ ወድቋል፡፡ ውኃ አፍስሰው ጸሎት አድርሰው ከተኛበት አነቁትና ወደ ዋሻው ውስጥ አስገቡት፡፡ ያመጡለትንም ምግብ አቀረቡለት፡፡
ልጁ በደረሰበት ነገር አዘነ፡፡ አኮረፈ፤ ቂምም ያዘ፡፡
በማግሥቱ በጠዋት ተነሥቶ አንዳች የሚያህል ዱላ ቆርጦ መጣ፡፡ ባሕታዊው ጸሎታቸውን እያደረሱ እያለ ከጀርባቸው መታቸው፡፡ ደንግጠው ወደቁ፡፡ በገመድ እጃቸውን አሠራቸው፡፡ የጸሎት መጽሐፎቻቸውን ሁሉ ወሰደ፡፡ የቀዱትን ውኃ ደፋው፡፡ በዚያ ብርድም የለበሱትን የተቀዳደደ ልብስ እና ደበሎ ገፈፋቸው፡፡ ከዚያም
«አባቴ በጸሎትዎ አይርሱኝ» ብሏቸው መንገድ ሲጀምር
«አይ ልጄ ልርሳህስ ብል ብርዱ መቼ ያስረሳኛል» አሉት ይባላል፡፡
ሰዎች ተፋቅረው፣ ተስማምተው፣ ተግባብተው፣ ተገናዝበው፣ ተባብረው ቢኖሩ የማይደሰተው ሰይጣን ብቻ ይመስለኛል፡፡ ችግሩ ግን ሁልጊዜ ይህ አይገኝም፡፡ መፋቀር እንዳለ ሁሉ መጣላት፣ መስማማት እንዳለ ሁሉ አለ መስማማት፣ መግባባት እንዳለ ሁሉ አለመግባባት፣ መገናዘብ እንዳለ ሁሉ አለመገናዘብ፣ መተባባር እንዳለው ሁሉ መለያየት ያጋጥማል፡፡
ሰዎች ከሰዎች ጋር አንዳች ዓይነት ግንኙነት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ የፍቅር፣ የጋብቻ፣ የዝምድና፣ የማኅበር ተኛነት፣ የንግድ ሽርክና፣ የጓደኛነት፣ የሥራ አጋርነት፣ የእምነት ወዳጅነት፣ ሌላም ሌላም፡፡ እነዚህ ግንኙነቶች እህል ውኃቸው ነጥፎ መቋጨት ቢኖርባቸው መንገዱ ምንድን ነው?
በመልካም እንደጀመሩ በመልካም መጨረስ፣ በፍቅር እንደጀመሩ በፍቅር መጨረስ፣ በሰላም እንደጀመሩ በሰላም መጨረስ አይቻልም?
የመጀመርያው ችግር እውነቱን ካለመቀበል የሚመጣ ይመስለኛል፡፡ አብረን ልንሆን አልቻልንም፡፡ ተፋቅረን ልንኖር አልቻልንም፡፡ ሽርክናችን ሊሠራ አልቻለም፡፡ ጋብቻችን ሊጸና አልቻለም፡፡ አብሮ መኖር አላዋጣም፡፡ በአንድ ቤት መኖራቸው አላስኬደም፡፡ ይህ አሁን የጀመርነው ዓይነት ግንኙነት አላዋጣንም፡፡ ይህንን እውነት መቀበል ያስፈልጋል፡፡ በሃይማኖትም፣ በባህልም፣ በቤተሰብም፣ በሕግም፣ በጓደኝነትም፣ በሌላም መልኩ አንድነቱ፣ ኅብረቱ፣ ጓደኛነቱ፣ ዝምድናው እንዲቀጥል ተሞከረ፡፡ ግን አልተቻለም፡፡ ወይንም አንደኛው ወገን አልፈለገም፡፡ በቃ፡፡
ይህንን እውነታ እያወቅነው ለምን እንቋሰላለን፡፡ በአንድ ቤት ሁለት ትዳር፣ በአንድ ንግድ ሁለት ሌቦች፣ በአንድ ጓደኝነት ሁለት የሐሜት አንደበቶች፣ በአንድ ማኅበር ሁለት አመራር፣ በአንድ ፓርቲ ሁለት ርእዮተ ዓለም፣ በአንድ እምነት ሁለት ሥርዓት ለምን እንዘረጋለን፡፡
ለይሉኝታ ሲባል፣ ተመሳስሎ ለመኖር ሲባል፤ ክብርን ለመጠበቅ ሲባል፣ ስምን ላለማስጠፋት ሲባል ብቻ ለምን በገዛ እጃችን ሲዖልን ቤታችን ውስጥ እንመሠርታለን፡፡ በቃ አልቻልንም የሚለውን ለምን አናምንም፡፡ ንግዱ እየተጎዳ፣ ትዳሩ እየተጎዳ፣ ኅብረ እየተጎዳ፣ ፓርቲው እየተጎዳ፣ ተቋሙ እየተጎዳ፣ ልባችን እየተጎዳ ለምን አንድ ነን እንላለን፡፡ ተለያይተናልኮ፡፡ እህል ውኃው አልቋልኮ፡፡
ችግሩን አምኖ መፍትሔውን መፈለግ አይሻልም፡፡
በአንድ ወቅት በጫካ ወስጥ ረሃብ ሆነና ጅቦች ሁሉ አለቁ፡፡ አንድ ብልጥ ነኝ ያለ ጅብ የከብት ቆዳ ለብሶ፤ አረማመዱን አስተካክሎ፤ ጠባዩን አሳምሮ ወደ ከብቶቹ ጠጋ አለ፡፡ እነርሱም ከብት ነው ብለው ተቀበሉት፡፡ ውሎ አድሮ ሲላመድም አንዲት ላም አገባ፡፡ ለጊዜው እየተደበቀ የመንደር ሥጋ ስለሚበላ ችግሩ አልታወቀውም፡፡ እየቆየ የጾሙ ወራት ገብቶ ሥጋ ከአካባቢው ሲጠፋ ግን ተቸገረ፡፡
ቤት የሚቀርበው ሣር እና ውኃ ነው፡፡ የሚተኛው በረት ውስጥ ነው፤ የሚሠማራው መስክ ላይ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከብቶቹ እንደሚጮኹት ለመጮኽ ይሞክራል፡፡ ነገር ግን የውስጡን ጩኸት ስለማይ ጮኸው አይወጣለትም፡፡ ሁልጊዜም «እንዴው እባካችሁ የት ሄጄ ልፈንዳ» እያለ ይጨነቃል፡፡
ትዳሩን አልቻለውም፤ ከብትነትም ሰለቸው፤ ሣርም ሊያረካው አልቻለም፡፡ አንድ ቀን ሲመርረው በከብ ቶቹ መካከል እንደ ጅብ እያጓራ አስነካው፡፡ ሁሉ ከብት ደንብሮ በየበረቱ ገባ፡፡ እረኛውም ምን መዓት መጣ ብሎ ሸሸ፡፡
«እንዲህ እውነቱን ተናግሬ መፈንዳት ስችል ልሙት እንዴ፤ በቃ ጅብ ነኝ በቃ ጅብ ነኝ» እያለ ጫካ ገባ ይባላል፡፡
መሸፈን ችግርን ይፈታዋል? ዝምታስ መልስ ይሆናል? አልጋ ለይተው፤ ሰላምታ ተነፋፍገው፣ ቃላት ሳይለዋወጡ፣ የሂሳብ አካውንት ለያይተው፤ ጀርባ ተሰጣጥተው የሚኖሩ ስንት ባል እና ሚስት አሉ፡፡ ለሠርግ ሲጠሩ ግን «ከባለቤትዎ ጋር» እየተባሉ የሚጠሩ፡፡ ለምን እውነታውን አምነን መፍትሔ አንልግም፡፡ ያለበለዚያ ደግሞ ሳንጎዳዳ በሰላም  ለምን አንለያይም፡፡
እኔ  ከምንጎዳዳ በሰላም እንለያይ የምልበት ምክንያት አለኝ፡፡ ካልተስተካከለ አንድነት የተስተካከለ ልዩነት ይሻላልና፡፡ ተለያይተው፣ ተጣልተው፣ ተኳርፈው፣ ምን አለ? ምን አለች? ምን አደረገ? ምን አደረገች እየተባባሉ መረጃ እየተጠያየቁ የሚኖሩ፡፡ በባል እና ሚስቱ መለያየት ምክንያት የቤት ሠራተኞች ግራ እየገባቸው ሳያስቡት የቤቱ ባለቤት የሆኑ፤ ልጆቻቸው እየተምታታባቸው የሚኖሩ ባል እና ሚስት የዚህ ጉዟቸው መጨረሻ ምን ይመስላችኋል?
በመኖራቸው ፍቅር ካልሰበሰቡ ቂም እየሰበሰቡ ነው ማለት ነው፤ ሰላም ካልሰበሰቡ ጠብ እየሰበሰቡ ነው ማለት ነው፡፡ ቀለበት ካወለቁ ሠንሠለት ታጥቀዋል ማለት ነው፡፡ መጎራረስ ካቆሙ ጩቤ እየሳሉ ነው ማለት ነው፡፡ ቂም ይቋጠራል፣ ጠብ ይከርራል፣ በነገር መፈላለግ ይጀመራል፤ ከዚያስ? ከዚያማ መጠቃቃት ይመጣል፡፡ መጎዳዳት ይቀጥላል፡፡
መለያየት የማይቀር ከሆነ፡፡ እሀል ውኃ ካለቀ፤ አብሮ መኖር ካልተቻለ፡፡ መንገዱ የማይቀጥል ከሆነ፤ ተጎዳድተን ለምን እንለያያለን፡፡ ልጁ ከእኒያ ባሕታዊ ጋር መለያየቱ አልነበረም ከባዱ ወንጀል፡፡ ጉዳቱን አድርሶ እንዳይረሱትም አድርጎ መለያየቱ እንጂ፡፡ «ልርሳህ ብል ብርዱስ መቼ ያስረሳኛል» ነውኮ ያሉት፡፡ ዛሬምኮ ብዙዎች አሉ፤ ተወው/ተዪው፣ እርሳው/ እርሺው ሲባሉ «ልርሳው ብልስ እንዴት ያስረሳኛል» የሚሉ፡፡ የተጎዱ ልቦች፣የተጠቁ ነፍሶች፡፡
ጠብ በሚዋደዱ ሰዎች እንደሚብስ የታወቀ ነው፡፡ ሳልሠራለት፤ ሣልሠራላት፤ ማንነቴን ሳላሳየው/ሳላሳያት የሚሉ ቃላት ሞትኩልህ/ሞትኩልሽ ሲሉ ከነበሩ አንደበቶች ብትሰሙ አይግረማችሁ፡፡ «ሲያልቅ አያምር» ብሎ አበሻ የተረተው ይህንን ማለቱ ነው፡፡
እንዲህ ስሜት ግን ከየት ይመጣል?
       ይቀጥላል

28 comments:

 1. thank you for sharing this idea but let me ask you one question Dani what is the rule of the EOC says about divorce I mean if its the problem is worth and you get married in matrimony (teklil) what is the exact rule I need to know in detail.

  thanks alot

  ReplyDelete
 2. Who wrote 'Lemetadu Sibal '?.I heard it from you.I think it contradicts from what I read from your articles.Why do you forget room for improvement?.What about Praying to have change with the help of GOD ?.I thin you wrote it with emotion.I don't agree with your Idea.

  ReplyDelete
 3. +++

  በጣም ጥሩ እና ወቅታዊ ትምህርት ሰጭ ነዉ:: ግን ስትጨርስ አደራ በርቅ አድርገዉ::

  ቃለ ህይዎት ያሰማልን::

  በርታ

  ReplyDelete
 4. ዳንኤል መልካም ነጥብ አነሣህ፡፡ አንድ ማኅበረሰብ በሰላም እንዲኖር ሰላማዊ የመለያየት ጥበብ ያለው ኅብረተሰብ መገንባት አለበት፡፡ ልዩነቶች ሁሉ በጦርነት፣በመጠቃቃት እና በመጎዳዳት፣ በመገዳደል እና በአካላዊ ጉዳት መጠናቀቅ የለባቸውም፡፡ በዚህም ሆነ በዚያ ተብሎ ዕርቅ ካልመጣ፤ መለያየትም ግድ ከሆነ ለምን በሰላም አይሆንም፡፡ የማንም ልብ ሳይጎዳ፡፡

  ReplyDelete
 5. +++
  First of all Qale Hiwoten Yasemalen. But am really surprised. Egezeabheren eko be emenete honen kelemenew, ketseleyene yemesanew neger yelem. Divorce and being apart will not be the solution. Ye Merefe kedada yahele emenete benorachew terarawen....ayedel? Eagerly waiting the rest of the part.

  thanks

  ReplyDelete
 6. Dn Daniel. Egziabher yibarkih
  I completely disagree with what you are writing today. Are you becoming westernized? I don't thik so. This is not for Christians. It is for the non beleivers. Atlanta

  ReplyDelete
 7. Dn. Daniel, this is realy western principle. Tecnically I agree with this idea but It is dangeries If you look at this idea from diferent angle. In my opnion this problem is coming from differnt reason but the soulutinon is praying to Almighty God and practice chrstian life He (our Father)can change the bad into good.in my opnion the western principle can work for this world but may be not for christanity. Specialy in merage(tidar) life it is very special relationship we have to fight our enemy devil by praying and endurance. I know some people after alot of big problem in their life they got peace and love at the end. T. Tesfaye

  ReplyDelete
 8. Kale Hiwot yasemalin
  Ameha Giyorgis & FikrteMariam
  DC

  ReplyDelete
 9. dani it is good but not!!!

  ReplyDelete
 10. በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሕዱ አምላክ። አሜን!!

  ዲ/ን ዳንኤል ክብረትን ይቺን ኮንፒዩተር ስነካካ ነው የማውቀው። እና በዚች ብሎግ ላይ የሚያነሳቸውን ሐሳቦች በስሱ አነባቸዋለሁ። የሚያነሳቸው ሐሳቦች ጥሩ እንደሆኑ ባውቅም እንኳን አፍ የሚያስከፍት ወንጌል ሰባኪ መሆኑን ቀርቶ ፀሐፊና ውድ የተዋሕዶ ልጅ መሆኑንም እምብዛም አላውቅም። በአገር ውስጥ የሚኖርም አይመስለኝም ነበር። ነገር ግን በ12/05/03 በሐዋርያው ዜና ማርቆስ ቤተ-ክርስቲያን በሚገርም ሁኔታ ወንጌልን ሲያስተምረኝ ዳንኤል ማን እንደሆነ ገና አወኩት። ይህ እንግዲህ በሐይማኖትህ የለህም ሊያስብለኝ ይችላል ግን እውነቱን መናገር አለብኝ። ስለ ሐይማኖቴም ለማወቅ እጅግ እጓጓለሁ ግን ለማወቅ አልቻልኩም። በዚህ ደግሞ በጣም አዝናለሁ።

  ይህንን በዚህ ላብቃና ዳንኤልን ለዛሬ አንድ ጥያቄ ልጠየቀው። በዚህ ርዕስ ላይ "አልጋ ለይተው፤ ሰላምታ ተነፋፍገው፣ ቃላት ሳይለዋወጡ፣ የሂሳብ አካውንት ለያይተው፤ ጀርባ ተሰጣጥተው የሚኖሩ ስንት ባል እና ሚስት አሉ፡፡ ለሠርግ ሲጠሩ ግን «ከባለቤትዎ ጋር» እየተባሉ የሚጠሩ፡፡ ለምን እውነታውን አምነን መፍትሔ አንፈ ልግም፡፡ ያለበለዚያ ደግሞ ለምን አንለያይም፡፡" ብለሐል። ይህ አባባልያለ ዝሙት ምክነያት ብቻ እንዳንለያይ የሚያዘንን ቅዱስ ቃሉን አይቃረንም?

  የእመቤታችን አማላጅነት የእግዝአብሔር ቸርነት አይለየን። አሜን!!
  መርከቤ ንጉሴ/ከአዲስ አበባ/

  ReplyDelete
 11. I share your idea with all types of relations but not in marriage.Getting separated for married people is not a solution because they already became one by Holy Spirit. They rather need to get back where they have been at the beginning of the marriage.

  ReplyDelete
 12. Thank you Dani,

  @ the 2nd Anonymous comment. I think you should probably read 'Lemetadu Sibal' again then this current article then 'Lemetadu Sibal' again. From there I promise, you will understand the main messages of both articles.

  According to me this is how I see them:

  'Lemetadu Sibal': Marriage is a very big deal, so here it was advising to leave very silly arguments for the sake of marriage. "wuhawu ketene eyalu...." endayihon. For instance, if a husband came home upset outside, even if there are some mistakes, for the sake of their marriage it will be nice if the wife gets things calm down. They can discuss things afterwords.

  Current Article: We all might have experienced different marriages in our life. Some end up with some tragedy (killing each other). In this regard it is better to agree not to disagree on any arguments because of the consequences. That is why in an educated society we see divorced couples living a friendship life. There is no ignorance at all. They greet each other sometimes they invite each other for coffee around. But, us we say " ayinun lafer, ayinuan lafer"

  That is why Dani said this: እኔ ከምንጎዳዳ በሰላም እንለያይ የምልበት ምክንያት አለኝ፡፡ ካልተስተካከለ አንድነት የተስተካከለ ልዩነት ይሻላልና፡፡

  Masitewalun Yisiten.

  ReplyDelete
 13. የማይበላ እንዳያስበላ ያብላላJanuary 26, 2011 at 11:54 AM

  TO WHOM IT MAY CONCERN

  Matthew 19:9 (King James Version)
  And I say unto you, Whosoever shall put away his wife, except it be for fornication, and shall marry another, committeth adultery: and whoso marrieth her which is put away doth commit adultery.

  "except it be for fornication"


  Matthew 19:9 (New Living Translation (©2007)
  And I tell you this, whoever divorces his wife and marries someone else commits adultery--unless his wife has been unfaithful."

  "unless his wife has been unfaithful"


  1 Corinthians 7:15 (King James Version)
  But if the unbelieving depart, let him depart. A brother or a sister is not under bondage in such [cases]: but God hath called us to peace.

  "A brother or a sister is not under bondage in such [cases]"  ONLY THE TRUTH SETS US FREE !


  God Bless You Dn. Daniel.

  ReplyDelete
 14. Dn dani, thank you for all you think.
  Those you mentioned type of people are already not living together rather they are sharing single house,may be they to solve their house rent problem or other family (children)problems.
  so they were not one,and shall be separated their house.

  ReplyDelete
 15. This is so UNDaniel and it discredit your previous contributions. Aren't you the one who preach unity and tolerance? Where all that goes?

  ReplyDelete
 16. hailemichael zedallasJanuary 26, 2011 at 7:20 PM

  memeher

  i don't know why i am afraid dani.

  ReplyDelete
 17. let we judge after the article finishes...B/c the article is not finished...

  ReplyDelete
 18. ቃለ ህይዎት ያሰማልን፡፡

  ወቅታዊ ነገር ስለሆነ ጥሩ ነው፡፡ ሁሉም በሰላም ወደስምምነት ቢመጡ ዕሰዮ ነዉ፡፡ ካልሆነ ግን በሰላም መለያየቱ ይበጃል ማህበረሰቡን ከመበጥበጥ፡፡

  በርታ; ከክናፈርግብ

  ReplyDelete
 19. ቃለ ህይዎት ያሰማልን፡፡

  ወቅታዊ ነገር ስለሆነ ጥሩ ነው፡፡ ሁሉም በሰላም ወደስምምነት ቢመጡ ዕሰዮ ነዉ፡፡ ካልሆነ ግን በሰላም መለያየቱ ይበጃል ማህበረሰቡን ከመበጥበጥ፡፡

  በርታ; ከክናፈርግብ

  ReplyDelete
 20. Dani i do loooove u soooo much as always. but i really am sad bse i know why u write this.

  anyone can't gain peace as easy as that. if someone knows well about diabilos and what his aim is, then he has to be patient enough to always win him. standing against or separating from sth u build all ur life ( like marriage)is..... don't know what to day. That is not solution. and it cannot be solution. never. and that is not Gods way. and it is not what we need to here from u after all this advises. May God protect everyone from making mistakes.

  ReplyDelete
 21. ቃለ ህይዎት ያሰማልን፡፡
  በርታ

  ወቅታዊ ነገር ስለሆነ ጥሩ ነው፡፡ ሁሉም በሰላም ወደስምምነት ቢመጡ ዕሰዮ ነዉ፡፡ ካልሆነ ግን በሰላም መለያየቱ ይበጃል ማህበረሰቡን ከመበጥበጥ፡፡

  ReplyDelete
 22. Kale Hiwot Yasemalen Dani.
  I don't wont to judge u hier but if i understood u corrrectly that u want to say for those people (belivers & nonbelivers)in social life,work place,everywhere what we do Daily life. I agree with u b/c even we belive ours God & we do All things in wrong dirction.If u mean that u have Rights also we know what the bible say but we don't use it in our's life. thanks dani.

  ReplyDelete
 23. ውድ እህቴ ከምስጋናዬ በፊት አድናቆቴን አቀርብልሻለሁ፡፡ በግብዝነት አይደለም ከዚህ በሚከተለው ምክንያት እንጂ፤ ብዙዎች ብዙ ጊዜ ብዙ ዘመን የሚነግሩን፣ እቤታቸው የሚያቀርቡልን፣ የሚተርኩልን የሕይወትን(የሕይወታቸውን) የፊት ገጽታ የተቀባባውን፣ ሁሌም በሰው ፊት እንዲያምር የሚደረገውን ብቻ ነው፡፡ አንቺ ግን የሕይወትን ጀርባ አሳየሽን፡፡ ለመሆኑ ጀርባ ለመንገደኛው፣ ለሚያውቁት ሁሉ የሚገለጥ የሰውነት አካል እንዳይደለ ለሁሉም ግለጽ ነውና፡፡
  በበኩሌ ሕይወትሽ አላሳዘነኝም፡፡ ምክንያቱም አንቺ የምታሳዝኚ ሴት አይደለሽም፡፡ ጀግና ነሽ፡፡ የኑሮ ውጣ ውረድ የጋረጠብሽን መሰናክል ለማለፍ የሚያስችል የውጊያ ትጥቅ ያለሽ፡፡ የተማርሽ ሆነሽ ሳለ እንዳልተማረ የማጀት ጭቆናን በፈቃድሽ የታገስሽ፣ መፍታት እያለ መሞት የሚለውን ዘይቤ ንቀሽ የኑሮሽ ዋልታ እንዳይዘም ለማቃናት ለረዥም ዘመን ፈተናውን በትዕግስት የተጋፈጥሽ፤ዘመናዊነት፣ጥሩ ደመወዝ፣ከተሜነት አሸንፎሽ በአንድ ቀን ጭቅጭቅ ሳይሆን በዓመታት ቦክስና ቡጢ ያልተንበረከክሽ፣ እውቀትና ገንዘብ ሳይሆን እግዚአብሔርን ማመን፤ በአንገትሽ አስረሽ፣ በልብሽ ቀብረሽ የምትኖሪ፤ በእግዚአብሔር እንደታመንሽ ሁሉ እግዚአብሔርም ከአንቺ ጋር የሆነልሽ ሴት ነሽ፡፡ ለዚህ እኰ ነው በሦስት ጥይት መካከል ሽርሽር ያልሽው፡፡(ልብ በይ አሜሪካኖቹ እስከዛሬ ድረስ እንደእርሱ ዓይነት እውነተኛ ፕሬዚዳንት አላገኘንም የሚሉለት ኬኔዲ በእነዚያ ጥንቁቅ ጠባቂዎቹ መካከል ነው ግንባሩ የተበረቀሰው፣ ላንቺ ግን በአካል ጠባቂ አልነበረሽም፣ ጊዜው ምሽት፤ ክፉ ካሰበ በቀር በዓይን ለማየት የሚያዳግትበት) በመከራ ብዛት መሰቀቅን ሳይሆን ጽናትን በጽኑ ፈለግሻት እግዚአብሔርም ባረከሽ፡፡ አንቺ ታዲያ ምንሽ ነው የሚያሳዝነው፡፡ እንኳን ጥይት የፖሊስ ፊሽካ ሲጮህ በርግገን የምንጠፋ፣ ትዳርን ያህል መቅደስ፣ ባልን ያህል ራስ፣ ሚስትን ያህል ዘውድ ሲታጣ፤ ማነው በዚህ ዘመን ተስፋ የማይቆርጠው? በእግዚአብሔር ላይ የማያንገራግረው? የቀደመ የሃይማኖት ትጋቱን አውልቆ የማይጥለው? ከዓለም ጋር ተሞዳሙዶ ዓለምን መስሎ ለመኖር የአቅጣጫ ለውጥ የማያደርገው? አንቺ ግን ከዚህ ሁሉ የለሽበትም፡፡ በፍልሚያው ውስጥ አሸናፊ ሆነሽ ወጥተሻል፡፡ ይህን ታሪክ እኰ የጻፍሽልን ስላሸነፍሽ ነው፡፡ ተሸናፊነትን ለመጻፍ የሚችሉ የሉም ባይባልም ጊዜያችን የሚያሳየን ግን ተሸናፊነትን ማንም ለመተረክ ፈቃደኛ አለመሆኑን ነው፡፡ እናም ምን ልበለው የአንቺን ሕይወት “መጽሐፈ ምክር?”
  ለዳንኤል፣
  እጠብቃለሁ ያልከው ነገር እየመጣ ይመስላል፡፡ በበኩሌ እንደዚህ ዓይነቱ ታሪክ ነገ መጽሐፍ አይሆንም ማለት አይቻልም፡፡ ከዚያ አልፎ ፊልም ይወጣዋል፡፡ የዚህ ብሎግ ተከታታይ ቁጥር ምን ያህል ነው? ተደራሽነቱ በብዙ ምክንያቶች ውስን ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ታዲያ የብሎጉ ተከታታይ ለሆነውም ሆነ በሌላ መንገድ ለሎችን ለመጥቀም እንዲቻል በአእምሮዬ የቃጨለውን ከዚህ በታች ለምሳሌ አቀረብኩት፡፡ እባክህ ይህን ሰፊና ጥልቅ የሆነ የማስተማሪያ ርዕስ እንድንጠቀምበት በልዩ ትኩረት ሂድበት፣
  የመጽሐፉ ርዕስ፣ ልርሳህስ ብል ብርዱ መች ያስረሳኛል
  ምዕራፍ አንድ፣ የሕይወት ጀርባ
  ክፍል አንድ፣ የእኔን ሕይወት ምን ትሉታላችሁ?
  ክፍል ሁለት፣ .........................
  ክፍል ሦስት፣ .........................
  ክፍል አራት፣ .........................

  ከኦርቶዶክሳዊት

  ReplyDelete
 24. ኦርቶዶክሳዊት ምን አይነት ቋንቋ፣ ምስል ከሳች ገለጻ ነው ምትጠቀ(መ/ሚ)ው ጃል!
  በርዕሱን ልደመም ወይስ በአስተያየት?ለማንኛውም ቦታው እዚህ ነው ወይ?
  Blog Moderator እባክህ በርዕሱ ስር እንዲለጠፍ/እንዲጦመር ተባበረው።it is good to be moved and put under the topic(የእኔን ሕይወት ምን ትሉታላችሁ).

  ReplyDelete
 25. በ እ ው ነ ተ እኔም በኦርቶዶክሳዊት አስተያየት ተገረምኩ እግዚአብኤር ይጠብቅህ ሌላው ዲ. ዳንኤል "ልርሳህስ ብል ብርዱ መች ያስረሳኛል" ...... የብዙዎችን ችግር የሚነካካ ጉዳይ ይመስለኛል እናም በርታ በተለይ ለመፍትኤዎቹ

  ReplyDelete
 26. qale hiyiwot yasemalin,danieye tebarek

  ReplyDelete
 27. በጣም ግሩም የሆነ ሐሳብ ነው:: እኔ በምኖርበት ውጪ ሐገር በተጋቡ ባልና ሚስት መካከል የማየውና የምሰማው በጣም የሚያስጠላ ኑሮ ነው የሚኖሩት! የጋራ የሚባል ነገር አያውቁም! ባልና ሚስት ሳይሆኑ room mate ሆነዋል! እናም ሁሌም ከዚህ በፊት ከፃፍከው ላይ (የሚያሸንፍ ፍቅር ውስጥ አንድ አልጋ ላይ መተኛትና አንድ ላይ መተኛት የተለያዩ ናቸው)የሚለው ለኔ መልስ ነው
  ተባረክ አብዝቶ እውቀቱን ይስጥህ:: ¨እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!አሜን!¨

  ReplyDelete