Thursday, January 20, 2011

ከታሪክ ትውስታ


ኢትዮጵያ በብልጽግናዋ ዘመን ጥገኝነት የሚጠየቅባት ልዕለ ኃያል ሀገር፤ የንግድ ግንኙነት የሚመሠረትባት ባዕለ ጸጋ ሀገር ሊወርሯት የምትፈራ ብርቱ ሀገር ነበረች፡፡ ይህንን ማንነቷን የሚመሰክሩ መዛግብት ከመጽሐፍ ቅዱስ እስከ ሄሮዱቱስ ድረስ ይነበባሉ፡፡ ተቆፍረው የሚወጡትም ሆኑ  ተጽፈው የተቀመጡት መረጃዎችም ይተርካሉ፡፡

ተስፋ አለን፡፡ እንደ ለመንን መልሰን እንሰጣለን፤ እንደ ተሰደድን ተመልሰን እንመጣለን፤ እንደ ተበደርን እናበድራለን፤ በሌሎቹ ሥልጣኔ እንደቀናን በኛም ይቀናል፤ የዓለም መገናኛ ብዙኃን ስለ ኢትዮጵያ ጥጋብ እና ድሎት የሚዘግቡበት ዘመን ሩቅ አይሆንም፡፡

እስኪ ለዛሬው አዲስ ዘመን ጋዜጣ መስከረም 23 ቀን 1940 ዓም ያወጣውን አስገራሚ ዜና ከ60 ዓመት በኋላ እንተዝተው፡፡ ቁም ነገር መጽሔት በታኅሣሥ/ጥር 2003 እትሙ አውጥቶታልና፡፡


ኢትዮጵያ እንግሊዝን ረዳች

ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት በክረምቱ ኃይለኛነት ምክንያት ጉዳት ለደረሰበት ሀገር የገንዘብ ርዳታ ልከዋል፡፡ ይህም ርዳታ በሌጋሲዮናችን በኩል ሲላክ ቀጥሎ ያለው ደብዳቤ አብሮ ተልኳል፡፡

ለሎርድ ሜዮርክ ኖሽናል ዲስትሬስ ፈንድ ለንደን፡፡

ምንም እንኳን እኛም ራሳችን በሕዝባችን ላይ ያለአግባብ የደረሰበትን ጉዳት በማቃለል ሥራችን ላይ ብንሆንም ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቀው ኃይለኛና ጨካኝ በሆነው ክረምት ሁልጊዜ በምናስባት በለምለሟ ውብ በሆነች ሀገርዎ ላይ ለደረሰው ጥፋት መጠነኛ የገንዘብ ርዳታ መጠየቅዎን ስለሰማን የገንዘቡ ቁጥር ምንም ከፍ ያለ ባይሆን የኛንና የሕዝባችንን ርዳታ ለመግለጽ ያህል አንድ ሺህ ፓውንድ በሌጋሲዮናችን በኩል ልከንልዎታል፡፡

22 comments:

 1. “England the Workshop of the World” “The Sun Never Sets on the British Empire”

  እነዚህ አባባሎች የ1970ዎቹ መጨረሻ ላይ የነበርኩበትን የሁለተኛ ደረጃ የታሪክ ትምህርት እንዳስታውስ አድርገውኛል፡፡ የዛሬው ሥርዓተ ትምህርት ስለምን እንደሚያስተምር መረጃ ባይኖረኝም በእኔ ጊዜ 1- የኢትዮጵያ ታሪክ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ አንስቶ እስከ “ፈነዳው” አብዮት ዋዜማ ያለውን፣ 2- የቅኝ አገዛዝ ዘመንን፣ 3- ከጥንታዊ የጋርዮሽ ሥርዓተ ማኅበር እስከ “በዝባዡ” የኢንዱስትሪ ካፒታሊዝም ብሎም እንደፈለጉ የሚታፈስበትን “የምኞት” ሥርዓት ሶሺያሊዝምን 4- በዚህም ሥር አብዮቶችን የኢንዱስትሪ አብዮት፣የፈረንሳይ አብዮት፤የቦልሼቪኮች አብዮት፣ የሞንጎሊያ፣ የማኦ ሴቱን ሎንግ ማርች … ብዙ ነው፡፡
  የዳንኤል ጽሑፍ ከላይ የተገለጡትን ሁለት አባባሎች አንዳስታውስ በማድረጉ ቀጥሎ ያለውን አጭር አስተያየቴን ላጋራ ተነሳሁ፡፡
  የኢንዳስትሪ አብዮት ዓለም ከፊውዳላዊ ጉልበት ተኰር የኢኮኖሚ ሥርዓት ወደ ሜካኒካዊና ማሽን ተኰር የአመራረትና የአኗኗር ዘይቤ የተሸጋገረችበት ሂደት ሲሆን ጀማሪዋ እንግሊዝ በመሆኗ የዘመናዊ ሥልጣኔ ማኅደር የሚል ካባን ከ17ኛው መቶ ክ/ዘመን ጀምሮ ደረበች፡፡ በቅኝ አገዛዝ ዘመንም እንደእርሷ በአራቱም አቅጣጫ ልቆ የሄደ አንደኛ ባለመኖሩ በምስራቅና ደቡባዊ ምሥራቅ እስከ ኮሪያና አውስትራሊያ፣ በምዕራብ ሃገረ አሜሪካ፣ በደቡብ እስከ ደቡብ አፍሪካ የተንሠራፋች ነበረችና በታላቋ እንግሊዝ ፀሐይ አትጠልቅም የሚለው አክሊል ተደፋላት ፡፡ እውነትም በምሥራቅ አውስትሪሊያና ኮሪያ የምትፈነጥቀው ፀሐይ በምዕራብም አሜሪካ ላይ የምትወጣው ናትና ታላቋ እንግሊዝ የ24ሰዐት የፀሐይ ዑደት የሚያደምቃት ብቸኛ ገዢ ነበረች፡፡
  ይህቺ ገዢ ዛሬ ማኅደረ ሥልጣኔ አይደለችም፤ ፀሐይም ይጠልቅባታል፡፡ የሥልጣኔ ፀሐይ፣የገዢነት ፀሐይ፣የሃይማኖት ፀሐይ እየጠለቀባት ያለች አገር ናት፡፡ አውሮፓና አሜሪካ የሥልጣኔ፣የገዢነት፣የረጂነት ብርሃን እየደበዘዘባቸው በምትኩ ምሥራቃውያን ፀሐይዪቱ እየደመቀችላቸው ነው፡፡ ቻይና በትረ ሥልጣኑን ከአሜሪካና አጋሮቿ እጅ እየፈለቀቀች፤ እነርሱም ሳይወዱ በግድ አምነው እያስረከቡ ነው፡፡ ከቻይና ጋር መሥራት አያዋጣም የሚሉ ካሉ አልገባቸውም፤ ኢትዮጵያም ጮራው እየፈነጠቀላት ነው፣ ይኸው ትናንትና እንኳን ኃያሏ አሜሪካ ለ200ሺህ የአሜሪካ ነዋሪዎች የሥራ ዕድል የሚፈጥር የ45ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ለማከናወን ነው ሁን የጠራሁት አለች አይደል፡፡ ዘመኑን መዋጀት የግድ ነው፡፡
  በቃ ጊዜው የምሥራቃውያን መሆኑን በመረዳት ፀሐይ አትጠልቅም የሚለው ስነልቡና ገዳይ አመለካከት ተሰብሮ ፀሐይ በኢትዮጵያ ትደምቃለችን ማስቀደም አለብን፡፡ በአንድም ምክንያት ሆነ በሌላ ምዕራባውያን በምሥራቃውያኑ ፈጣን የኢኮኖሚና የቴክኖሎጂ ምጥቀት እየተዋጡ ነው፤ ቁም ነገሩ ትንሽ ቀዳዳ ያለው ግዙፍ መርከብ እየሰጠመ መስጠሙ ግን ወዲያው እንደማይከሰት ማለት ነው

  ReplyDelete
 2. Ere gud naw
  Ewnet egna Englizen eredtenal????? Yigermal. Keengdyh tesfa alkortim.

  ReplyDelete
 3. Thank you for sharing the decades old article that has powerful message for those who think that nation is hopeless. As you said, when our people and all the government institutions are free, there is no doubt we can be one of the strongest countries. Given the existing condition, though, it is a nightmare. I mean we must come to unite and think positive, work for justice, fight tyranny by any means and above all believe in all humans are equal.

  ReplyDelete
 4. Wud d/n Daniel QHY! Awo ye terabnew tegben, ye tesedednew wede agerachn temelsen ye minigebabet ...etc gize ruuq ayhonm. Mesededachin ena be alem lay mebetenachin ye rassu miknyat yinorewal. Zare be teleyayu alemat wust ye Ethiopia Orthodox Tewahdo haymanot eyetesebeke, ahzab be timket ye Egziabhern lijinet eyetegonatsefu ye minastewlibet zemen lay enigegnalen. Mebetenachin legnam yatanewn ewqet endinigebey, tibebn endinagegn, maninetachinin ye belete endinireda, wede libunachin endinimeles redtonal. Japanoch zare yalubet dereja lay ye deresut eko ke sidet behuala new. Egnam temelisen ye agerachinn sim be bego ye minasterabetn, hizbachinin ye minitadegibetn, bete christianachinn ye minaskebribetn libuna Egziabher yisten. WSlE

  ReplyDelete
 5. Wey Gud!
  Ewinet kehon betam yemiyasgerm tarik!
  Minale tarik bayhon noro!!
  Cher yigitemen

  ReplyDelete
 6. edmelikachin tarik mawurat wunetim yehun wushet anakomim ende? esti tewet argenew lewedfitu anasbim?

  ReplyDelete
 7. hooo... one can judge how we are going to backward from the past.but as every body know our gvt. is always saying we are developing. ohee...just full of laying.let God give justice to our innocent people.

  ReplyDelete
  Replies
  1. mayet yetesaneh! mengedu sisera, university sisfafa, bekirbu degmo abay sigedeb, babur menged mejemerun atayim? enie yemigermegn hul gize lemin chigrin bicha enaweralen? ante techegireh yemitnor kehone lelawum chigeregna new malet aychalem. ethiopia eyadegech new tadgalechm!

   Delete
 8. no justice in our country the gvt.is lying about the development as if it is written in the constitution to lie is every body's right.

  ReplyDelete
 9. ayeee... ante kelay tarike anawera yemetelew it is clear how much you are so ignorant. you are looking only in one direction.how can a country live with out history. of course it is your right to be as ignorant as you expressed above but it is shame for you to tell us about the depth of your ignorance.

  ReplyDelete
 10. thank you dani you are so knowledgeable. we are proud of you being our brother in Christ.
  let God gives you long service year.

  ReplyDelete
 11. the emperor being generous is not an indication of our wealth rather it is the indication of our lack of understanding as to what is going on in the world and the inability to see the near future of Ethiopia.if we want to be proud lets be proud of axumite and zagwe and medieval time kings like zerayaqob and queen ELENE,which i admire most given the conditions of medieval Ethiopia.

  ReplyDelete
 12. hiy dane. betam betam yemgrm new.besdat unoh
  yein yemasl negar mesmat yasedsetal.
  egzyaber yestlin.
  sisay asfaw

  ReplyDelete
 13. thank you dani :- what you advise us by my understanding if we star to series work now, we re pit the privies history.
  tayacheweshetie@yahoo.com

  ReplyDelete
 14. thank you D/n Dani about this historical news. it have grate hope. & also it change our bad image.to be like 1940s all we Ethiopians we have to come unity.
  Hailemesekel Maputo.

  ReplyDelete
 15. Thanks for the article, but that aid was merely a good-will gesture by the then emperor and does not mean that we were rich enough to help other nations at that time.

  ReplyDelete
 16. ዮናስ .......ከአዲስአበባ  ቤተሰብህ እድሜ ከጤና ጋር እየተመኝሁ ከ1980ዋቹ መጨረሻ አካባቢ ጀ በአካል ሳይሆን በካሴትና በሲዲ ከቶችህ ስማር ከዛ ተጉትቼ የአዲስነገር ታዳሚ ስሆን አዲስነገር ሲቆም የተበሳጨሁት የዳንኤልን ፅሁፍ እንዴት አገኛለሁ በሚል ሲሆን ከዛ በዚህ ጡመራ .....ለዚያዉም እንዲህ ከተሳትፎ መድረክ ጋር መሆኑ ይበልጥ ያስደስታል። ግን ፀሀፊዉ (ጦማሪው) ሰው እንደሚከታተል ካወቀ ለአዲስነገርይተጋል ስል እኔም ተሳትፎዬን ከነአስተያየቴ አደረኩት። እንሆም ለ3ኛ ግዜ ዳኒ በርታ አንተም ፃፍ እኛም እናነባለን እናስነብባለን:: እግዚአብሔር ይርዳን! ይህን አመለካከትህን አይቀይርብህ

  ReplyDelete
 17. I hope folks will see what I have seen. I saw in this way- I think we are still helping the world. Guys think about immigrants who are living in the US. There are millions of Ethiopians' around the world helping the world itself such as like labor work, giving great ideas and so on. Ideas! Do u know what I mean? Yes great ideas came up from Ethiopians' mind!

  ReplyDelete
 18. Dani!!! do you have hope??? you are strong. But I do not think. It becomes worse and worse.

  ReplyDelete
 19. የኔ ጥያቄ እንግለሊዝ ብድሩን መልሳለች ወይ ነው?

  ReplyDelete
 20. ሽልንጌን ያያችሁ……….
  እናገኘዋለን አይቀርም ደሞ!!!!

  ReplyDelete
 21. It is unforgettable that we,recently,also helped japan when the country hit by big tsunami!

  ReplyDelete