Tuesday, January 18, 2011

«መጥምቃውያን»

ይህንን ጽሑፍ ከመጻፌ ሦስት ደቂቃዎች በፊት ኮተቤ /ሲኤምሲ/ ሚካኤል ከቤቴ አሥር ሜትር ርቀት ላይ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ አልፏል፡፡ ስድስት ሰዓት አካባቢ ወደ ቤቴ ስገባ መንገዱን ሞልተው ይደረደሩ የነበሩት ወጣቶች ለመድኃኒት እንኳን ቢፈለጉ አይገኙም ነበር፡፡
  
ከኮተቤ አዲሱ መንገድ እስከ ሲ ኤም ሲ መንገድ ያለው ፒስታ መንገድ ቀኑን ሙሉ ውኃ ሲጠጣ ነበር፡፡ መቼም ይሄ መንገድ እንደ ዛሬ አልፎለት አያውቅም፡፡ ሰማዩ ደግሞ በአረንጓዴ እና ቢጫ ቀይ ባንዲራ አጊጧል፡፡ ከመንገዱ ግራ እና ቀኝ ያለው ሣር ታጭዶ የቼልሲን ስታዲዮም መስሏል፡፡

አሥር ሰዓት ተኩል ሲሆን ሕዝቡ እንደ ጎርፍ እየፈሰሰ መጣ፡፡ ነጭ ጎርፍ ታውቃላችሁ፡፡ ልክ ዓባይ ጢስ ዓባይ ላይ ሲንደረደር የምታዩት ነው የሚመስለው፡፡ ግራ እና ቀኝ በቢጫ እና ቀይ ከናቴራ የተዋቡ ሴቶች እና ወንዶች ወጣቶች መንገዱን እጅ ለእጅ ተያይዘው አጥረውታል፡፡ ሕዝቡ ከፊት እና ከኋላ ብቻ እንዲሆን ነው የተፈቀደው፡፡

አንድ ሃያ ወጣቶች ወደ አምስት መቶ ሜትር የሚደርስ ምንጣፍ እየዘረጉ ከታቦቱ ፊት ፊት ያነጥፋሉ፡፡ ከኋላ በኩል ደግሞ ሌሎች ወጣቶች ታቦቱን የያዙት ካህናት ያለፉበትን ምንጣፍ ይጠቀለላሉ፡፡ ከሲ ኤም ሲ ሚካኤል እስከዚህ ድረስ እንደዚህ እያሉ የደረሱ ይመስላል፡፡ ሲኤምሲ ሚካኤል ሳይሆን ታቦተ ጽዮን ከደብረ ሲና ወደ ከነዓን የምትሄድ ነው የሚመስለው፡፡

ፀጉራቸው የተቆጣጠረ፤ እንደ ዐፄ ቴዎድሮስ ሹርባ የተሠሩ፤ በሬ እስከ ገበሬው የሚያህሉ፤ ቢፈልጧቸው ሁለት ሰው የሚወጣቸው ጎረምሶች እና ወጣቶች ከካህናቱ በላይ አደግድገው ያለግላሉ፡፡ እንደነዚህ ዓይነት በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ተሠማርተዋል፡፡

ለመሆኑ እነዚህን ወጣቶች ማን ለዚህ አገልግሎት መረጣቸው? እንዴት ሊሰባሰቡ ቻሉ? ይህኛውን ዓይነት አገልግሎትስ ለምን መረጡት? የገንዘብ ምንጫቸው ከየት ነው? እንዴት እንደ አሸን በአንድ ጊዜ በሁሉም የሀገሪቱ ቦታዎች ሊፈሉ ቻሉ? ብዙ ጥያቄዎች ይነሣሉ፡፡

በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ክስተቶች ዘመን ዘመን አላቸው፡፡

ከ1940ዎቹ እስከ ስድሳዎቹ ያሉት ዘመናት ማኅበራት በመላ ሀገሪቱ እንደ ብርቅ እና እንደ ፋሽን የወጡ በት ዘመን ነበር፡፡ ያኔ ሰንበት ት/ቤቶች አልነበሩም፤ በየአጥቢያው የነበሩት የወጣቶች ማኅበራት ነበሩ፡፡ ከሰድሳዎቹ በኋላ የባሕታውያን ዘመን መጣ፡፡ ሀገሪቱ እንደ አባ መሼ በከንቱ ባሉ ባሕታውያን ተጥለቀለቀች፡፡ ከገጠር እስከ ከተማ ሠንሠለት የታጠቁ፤ ጠፈር ያነገቱ፤ ቆዳ የለበሱ፤ መስቀል ተሰላጢን የያዙ ባሕታውያን ሀገሪቱን ሞሏት፡፡ ይህም አለፈ፡፡

ከስድሳዎቹ አጋማሽ እስከ ሰባዎቹ ደግሞ የሰንበት ት/ቤቶች ዘመን መጣ፡፡ በየአጥቢያው፣ በየገጠሩ፣ በየከተማው ሰንበት ት/ቤቶች የማኅበራትን ቦታ ተክተው ወጡ፡፡ ከሰባዎቹ እስከ ሰማንያዎቹ መጀመርያ ድረስ የኃያላን እና የቆራጥ ሰባክያን ዘመን ነበር፡፡ እነ ጋሽ ተሰማ፣ ጋሽ ታዬ፣ ጋሽ ግርማ፣ ቄስ ጌጡ የኋላ እሸት፣ እና ሌሎቹ ተነሥተው ኃይል አና ቆራጥነት በተሞላበት መንገድ ኮሚኒዝምን ተጋፍጠው ትውልድ አተረፉ፡፡

ከሰማንያዎቹ መጀመርያ እስከ ሰማንያዎቹ አጋማሽ ድረስ ተመልሶ የባሕታውያን ዘመን መጣ፡፡ እነ «ባሕታዊ» ገብረ መስቀል፤ እነ «ባሕታዊ»  እና ሌሎቹ ሲሻቸው ማርያም ታየች፤ ሲሻቸው ራእይ ታየን እያሉ ሕዝቡን ባንዲራ አስለብሰው በባዶ እግሩ አስደገደጉት፡፡ ባሕታውያንን አለመከተል ክርስቶስን አለመከተል እስኪ መስል ድረስ ለአንድ መንደር አንድ ባሕታዊ ደረሳት፡፡

ትንሽ ቆይቶ ደግሞ የዝዋያውያን ዘመን መጣ፡፡ በብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ አማካኝነት በዝዋይ ሐመረ ብርሃን የተጀመረው የሰባክያን ሥልጠና ውጤት የሆኑ ወጣት ሰባክያን በመላዋ ኢትዮጵያ እያበቡ በመጡት የሠርክ ጉባኤያት ላይ ተሠማሩ፡፡ ከቤተ ክህነቱ መጽሔቶች እና ጋዜጦች ወጣ ያሉ አዳዲስ መንፈሳውያን መጽሔቶች እና ጋዜጦች ብቅ አሉ፡፡ የሠራተኛ ጉባኤያት በየመሥሪያ ቤቱ ተቋቋሙ፡፡

ከዘጠናዎቹ መጀመርያ በኋላ ደግሞ ስብከትን አንዱ መተዳደርያቸው ያደረጉ «የግል ሰባክያን» እና «ዘማርያን» ብቅ አሉ፡፡ የትምህርት እና የስብከት ካሴቶች ከተማውን እና ገጠሩን አጨናነቁት፡፡ ከትምህርት እና መዝሙር እጥረት ወደ ጥጋብ ተሸጋገርን፡፡ እርግጥ አንዳንዴ ከትምህርቱ ይልቅ ሰባኪው፤ ከመዝሙሩ ይልቅ ዘማሪው እየታወቀ ሌሌ ፈተናም አመጣ፡፡ ጉባኤያት ከዕለታዊነት ይልቅ ወደ ወርኃዊነት አዘነበሉ፡፡

ከዚሁ ዘመን ጋር በአንድነት እና ተከትሎ የማኅበራት ዘመን ተከሰተ፡፡ ለአንድ ሰው ሦስት ማኅበራት እስኪደርሱት ድረስ መንደሩ ሁሉ ማኅበር በማኅበር ሆነ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ብቻ ከአምስት ዓመታት በፊት ከ14000 በላይ የጉዞ፣ የጽዋ እና የነዳያን መጋቢ ማኅበራት ተቋቋሙ፡፡ የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን ማሠራት፤ ነዳያንን ማብላት፤ ጉዞ ማዘጋጀት፤ የተጎዱ ገዳማትን መርዳት ሕልም ከመሆን አልፎ የዕለት ተዕለት ተግባር ሆነ፡፡

ሁለት ሺ ዘመን ሲብት የጭቅጭቅ ዘመን ሆኖ ነበር የባተው፡፡ በአገልጋዮች እና በተገልጋዮች መካከል አያሌ ክርክሮች ነበሩ፡፡ በተለያዩ እምነቶች መካከልም ደም ያፋሰሱ ግጭቶች ተከስተው ነበር፡፡

እልፍ ብሎ ደግሞ የአዳራሽ ጉባኤያት ዘመን መጣ፡፡ ለአንድ ዓመት ተኩል ያህል የቆየው ይህ ዘመን ጉባኤያት ከቤተ ክርስቲያን ቅጽር ግቢ ወጥተው ወደ አዳራሽ እንዲያመሩ ያደረገ፤ ጉባኤያትን ከገቢ ማሰባሰብ ጋር ያዛመደ፤ የሰባክያኑ እና ዘማርያኑ ተክለ ሰውነት በፖስተር እና ቢል ቦርድ አማካኝነት እንደ የማስታወቂያውን ገበያ የተሻማበት ዘመን ነበር፡፡

በዚህ ዘመን መካከል ነው እንግዲህ እነዚህ አንዳንዶቹ በዘመነ ጥምቀት በመታየታቸው የተነሣ «መጥምቃውያን» እያሉ የሚጠሯቸው ከ25000 በላይ ወጣቶች ብቅ ያሉት፡፡ ከዚህ በፊት በሰንበት ት/ቤቶችም ሆነ በሠርክ ጉባኤያት ሊደረስባቸው ያልቻሉ፤ ከመንፈሳዊነታቸው ይልቅ በአስቸጋሪነታቸው የሚታሰቡ፤ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚሄዱትን በመላከፍ የሚታወቁ እነዚህ ወጣቶች ጥምቀትን ተንተርሰው አገር አጀብ አሰኙ፡፡

እነዚህ ወጣቶች የሚለዩባቸው የራሳቸው ጠብዐያት አሏቸው፡፡ ከንግግር ይልቅ ለተግባር ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ ሥራቸው ሁሉ ኃይል እና ድፍረት የተሞላበት ነው፡፡ አይቻልም እና አይሆንም የሚባል ነገር አያውቁም፡፡ እስካሁን በማንም ያልተሠሩ እና ያልተነኩ ተግባራትን አከናውነዋል፡፡ መደበኛ የሆነውን አሠራር አልለመዱትም፡፡ ማናቸውንም ዕንቅፋቶቻቸውን በማንኛውም መንገድ ያርቋቸዋል፡፡ ይሉኝታ እና ፍርሃት የለባቸውም፡፡ በዓላትን እና ጉባኤያትን በማድመቅ ይታወቃሉ፡፡

ምንም ይሁን ምን እነዚህ ወጣቶች መጥተዋል፡፡ በክርስትና ሕይወት ትልቁ ጥያቄ ክርስትናን የት እና መቼ ጀመርከው አይደለም፡፡ የት እና እንዴት ጨረስከው ነው፡፡ ከሽፍትነት፣ ከግብርና፣ ከቀራጭነት፣ ከንግድ፣ ከአሳዳጅነት፣ ከዓሣ አጥማጅነት፣ ከአመንዝራነት፣ ከንጉሥነት፣ ከወታደርነት፣ ከሌላም ከሌላም የጀመሩ ነበሩ፡፡ የጨረሱት ግን መንግሥተ ሰማያት መሆኑ አንድ አድርጓቸዋል፡፡

እነዚህ ወጣቶችም በምንም ይሁን በምን መጡ፡፡ እነዚህን ልጆች ሥርዓት ማስተማር፤ እንደ ገቡ እንዳይወጡ ማድረግ፤ ተከባክቦ ወደሚፈለገው ደረጃ ማድረስ የቤተ ክርስ ቲያኒቱ ድርሻ ነው፡፡ በርግጥ በኃይል የመጣ የኤሌክትሪክ ኃይል በተጠቃሚው ላይ አደጋ ሊያደርስ እንደሚችለው ሁሉ እነዚህ ወጣቶች ተአምራዊ በሆነ መልኩ እንድ ጎርፍ አበእንዴ በመምጣታቸው የሚከሰቱ ችግሮች ይኖሩ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ችግሮቹን መቋቋም እንጂ ኤሌክትሪክ አይኑር እንደማይባለው ሁሉ እነዚህንም ወጣቶች መከታተል ስላልቻልን ብቻ አይኑሩ ማለት ከኃጢአት የባሰ ኃጢአት ነው፡፡

እነዚህ ወጣቶች መዋቅር፣ ደረጃ፣ ሥነ ሥርዓት፣ የእዝ ሠንሠለት፣ መዋቅራዊ አሠራር፣ ላያውቁ ይችላሉ፡፡ የመጡበት ዳራ ይህንን ዐውቀው እንዲመጡ የሚያደርግ አይደለምና፡፡ አለባበሳቸውም ሆነ አነጋገራቸው፤ አሠራራቸውም ሆነ አቋማቸው ከለመድናቸው የሰንበት ት/ቤት ባህል ወጣ ያለ ሊሆንም ይችላል፡፡ ሁሉንም ነገር ግን መንፈሳዊነት ሊቀይረው እንደሚችል ማመን ግን ያስፈልጋል፡፡ እኛስ ባንለወጥ ኖሮ ከዚህ የባስን አልነበርንም እንዴ!

በቤተ ክህነቱ አካባቢ ትልቁ ጭጥቅጭቅ በየትኛው መምሪያ ይታቀፉ የሚለው ነው፡፡ መምሪያ ከሰው አይበልጥምና ለእነርሱ የሚሆን ጊዜያዊ መዋቅር ዘርግቶ፤ ጊዜያዊ መመርያም አውጥቶ ልጆቹን ማስተናገድም ይቻላል፡፡ እነዚህ ወጣቶች ከባዱን ገደል ተሻግረው፤ ትልቁንም ተራራ ወጥተው፤ አስቸጋ ሪውንም ጫካ ጥሰው መጥተዋል፡፡ እኛ በሃያ፣በሠላሳ እና በአርባ ዓመታት ገንዘብ ያደረግናቸውን እሴቶች በአንድ ቀን ካላደረጉ ብሎ ማስጨነቅ ነፍሳቸውን ማስመረር ነው፡፡

ታልሙድ በተባለው የአይሁድ መጽሐፍ የተጻፈ አንድ ታሪክ አለ፡፡ አንድ በፀሐይ የሚያመልኩ የዘጠና ዓመት ሽማግሌ ወደ አብርሃም ቤት ለማረፍ መጡ፡፡ አብርሃም እግራቸውን አጥቦ ተቀበላቸውና እራት አበላቸው፡፡ ከዚያም ወገባቸውን አረፍ እንዳደረጉ ስለ አምልኮ እግዚአብሔር ይነግራቸው ጀመር፡፡ ሽማግሌው ዘጠና ዓመት የኖሩበትን ኑሮ በአንድ ቀን ሊለቁት አልቻሉም፡፡ እንዲያውም በዚያ ቤት መቆየት ከበዳቸው፡፡

አብርሃም ደግሞ በቅንነት ያስተምራቸው ጀመር፡፡ በመጨረሻ ሽማግሌው ከቤት ወጥተው ሜዳ ላይ አደሩ፡፡ ሌሊት እግዚአብሔር ለአብርሃም ተገለጠለት፡፡ እንዲህም አለው፡፡ «እኔ ለዘጠና ዓመት የተሸከምኳቸውን ሽማግሌ አንተ እንዴት ለአንድ ሌሊት መሸከም አቃተህ?»

እግዚአብሔር ለብዙ ዘመናት የተሸከማቸውን እነዚህን ልጆች እስኪለወጡ ድረስ ለተወሰኑ ዓመታት መሸከም አቅቶን ይበተኑ፤ ይፈተኑ እያሉ መከራ ማሳየት ተመሳሳይ ጥያቄ እንድንጠየቅ ያደርገናል፡፡

መሪያቸው እና መነሻቸው ሳይታወቅ ተአምራዊ ሆነው የመጡት እነዚህ ወጣቶች ለመንግሥት ግራ ሊያጋቡት ይችሉ ይሆናል፡፡ ይህንን ኃላፊነት ወስዳ ልጆቹን ከሥጋትነት ወደ አጋርነት መቀየር ያለባት ቤተ ክርስቲያኒቱ ናት፡፡

ምናልባት በሌሎቹ ሊሠራ የማይችል በእነዚህ ወጣቶች ብቻ የሚሠራ አንዳች ተልዕኮ እግዚአብሔር ቢኖረውስ? ማን ያውቃል?45 comments:

 1. Yetwededk wenmach QHY! ENQUAN LEBRHAN TIMKETU ADRSEN! Ketwatu jemer men yengern yeho eyalku setabk ahun yehnen fetft belahu betam leb yaslksal amna esti beselam yadrsena and 50 T:shirt engezalachewalen beln ega zenganachew enasu gen tegbarachewn aresum. Ged yemeln addis mechin masdenber teten enkfachew european and wetat matat yetweld tebasa new yelalu! lebetekirstin habt nachu enyazachew betely yesebket wengelu asbon enazihn zegoch ye enat betkirstian habt endayderg mekerm tselotm yasfelgale. ESti abatochn yemnkerb sewoch yehn neger engerachew! +++ Ke toronto akbari betseboch!

  ReplyDelete
 2. A very nice observation!

  ReplyDelete
 3. oh! d.daniel egziabher edmena tena yesteh bizegeime ager bet beneberku gize yemetuten enezihen wetatoch segat becha yezon nefsachewn lmadan kmrote yelk memeriya yaskedemenbet gize tez alegn abetu yeker belen ydenegil mariam lige

  ReplyDelete
 4. Bemejmrya inqan adrshe Di, daneil Egzabher yesthe
  Deje selam laye yewtwein anbibe betam nebr yaznkut yemiyastmer mels nwe ysthellen dank Egzabher yebarkhe.

  ReplyDelete
 5. Bemjmriya Enqan lebrhan Timketu Adrshe Deje Seiam lay yewtwin anbeba betm neber yaznkut edme lante endtlmedwe yemiyastmer mlsse nwe ysthwe EGZABHER yesthe DANKE!

  ReplyDelete
 6. ውድ ዲ ዳንኤል እግዚአብሄር ረጅም የአገልግሎት ዘመን ይስጥልን ፡፡ወደቤቱ የገቡትን መንጋወቹን እረኛቸው እንዳይበተኑ ዪጠብቅልን፡፡የዘመኑ ጳውሎስ ቢሆኑስ?

  ReplyDelete
 7. ዲ/ዳንኤል እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም ከነ መላው ቤተሰብህ አደረሰህ እኔ በለሁበት አገር ግማሽ ለሊት አልፎል ግን ቁጭ ብዬ የማላውቀው ግን የምጠብቀው ነገር ነበር በዚህ ምክንያት የተለያዩ ብሎጐችን እየከፈትኩ እጠባበቅ ነበር ይህንን ጽሁፍ ድንገት ሳገኘው እስከ ዛሬ የጻፍከውን ጽሁፍ አንብቤ የማውቅ እስከማይመስለኝ ድረስ ተደሰትኩ መጨረሻውን ያሳምረውና ታቦታቱ በክብር ተመልሰው ለመስማት ያብቃን ምን ይደረግ ሃጢያታችን በዝቶ ታቦታቱ ወጥተው በሰላም መመለሳቸው ጥያቄ እየሆነ መጣ ወላዲተ አምላክ ከልጆ ታማልደን ግን ዳኔ እነኚህ ዛሬ ቲሸርት ለብሰው የምናያቸው ወጣቶች አምናም ዘንድሮም በአደባባይ ሞገስ የሆኗት ናቸው እኛ እስከ ዛሬ ሰልፍ አሳምረን ከመውጣት ውጪ በሚደምቅበት ከመዘመር ውጭ ምን አድርገን እናውቃለን እንደ ህዳር ሲታጠን እንኳን የታቦቱን መሄጃ ጠርግን ቆሻሻ አቃጥለን እንኳን የምናውቅ አይመስለኝም ምናልባት ከነሱ የምንሻለው ተሰጥኦ በመቀበል ይሆናል ብዬ አስባለሁ ስለዚህ ተዋህዶ የጥበብ ባለቤት ስለሆነች ዛሬ በራሳቸው ጊዜ ለአገልግሎት የተሰለፉትን ወጣቶች በደረቁ ከየት እንዴት ከኋላ ማን አለ በሚል ከምናሳድዳቸው ጐን ለጐን እውነተኛዪቱን ቤ/ክ ሥርዓቷን ፍቅሯን ተዝቆ የማያልቀውን ትምህርቷን ብናካፍላቸው የዛሬዎቹ 25000 ለከርሞው እጥፍ ይሆናሉ ብዬ አስባለሁ ምናልባትም እንዳልከው እግዚአብሔር በነሱ አድሮ የሚሠራው ቢኖረውስ የቅዱሳን አምላክ ድንቅ ሥራውን ይሰራ አሜን

  ከአቡዳቢ

  ReplyDelete
 8. selam d daneale, tinyneshe bandera bejachew meyaze kemengest yeteleku selaye woyem agazy wotader mehone alebachew enje orthodox beyhonu neche lebse lebso yezemeralou.
  egzabher ethiopian yebarke.

  ReplyDelete
 9. ዲን ዳንኤል እግዚአብሔር የልፋትህን ዋጋ ይክፈልህ። በልጆቹ ላይ ያለኝን አመለካከት ነው የቀየርኸው! እኔ በዚህ መልኩ አልነበረም ያየኳቸው። የአስጀመራቸው አምላክ የእኛንም አይነ ልቦና ከፍቶ ማስተዋሉን ይስጠን።

  ReplyDelete
 10. አረንጓዴው ጎርፍ በዓለም አትሌቲክስ መድረክ ብቅ ያለው ድንገት ነበር፤ እነሆ 30 ዓመታት ተቆጠሩ፤ መካከለኛና ረዥም ርቀት ዛሬም የኢትዮጵያ ነው፡፡

  እነዚህ የቀስተ ደመና ጎርፎች የዛሬ ዓመት ጎንደር ላይ ብቅ ሲሉ በእጅጉ አስደንቀውኛል፡፡ መንግሥትና የሃይማኖት መሪዎች የጠበቁት የሥጋት እሳተ ጎመራ ባልጠበቁት መንገድ ፈነዳ፡፡ ጥፋትና፣ ውድመት፤ ብጥብጥና ጠብ ሳይሆን ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ማንም ሊሞክረው ቀርቶ ሊያስበው የማይችለውን እግዚአብሔርና ማደሪያውን ያከበረ አገልግሎት ከመስቀል አደባባይ እስከ ባሕረ ጥምቀቱ ተነጠፈ፡፡

  ምንም ለማለት አይቻልም፤ በግሌ የአንድ ሳምንት እንጂ እንዲህ እንደቋያ እየተፋጠነ መላዋን ኢትዮጵያ የሚያዳርስና ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን የሚያስደስት መስሎ አልታይህ ብሎኝ ነበር፡፡ እንደእውነቱ ከሆነ ግን ጎንደር ዘንድሮም እንደአምናው የእነዚህን ብርቱዎች ፍሬ ማጨዷን ይህን ብሎግ ከመክፈቴ በፊት በስልክ ማወቅ ችዬ ነበር፡፡ ለዚህም ነው የዚህ ጽሑፍ እይታ ቢስበኝ ጥቂት አስተያየት ለመስጠት የተነሳሁት፡፡

  የትም ይጀመር የት ወጣቱ የጀመረው መንፈሳዊ አገልግሎት ከዚህ በፊት በመንፈሳውያን የአገልግሎት መርሐ እቅድ ውስጥ የነበረ አይመስለኝም፡፡ ማጎንበስ ማቃናቱ፣ መጠቅለል መዘርጋቱ፣ መሸከም መሮጡ የሚጠይቀው ጉልበት በሚንዠቀዠቀው ላበት ሊገለጽ ይችል እንደሆን እንጂ በቃላት ለማስቀመጥ የሚቻል አይመስለኝም፡፡

  ዛሬ ላይ ሆኜ የተረዳሁት ግን ከበዓሉ ድምቀት በስተጀርባ አንዳች መልካም የሆነ ጥሪ ወይም ደግሞ የደኅነት ሥራ ስለመኖሩ ነው፡፡ በንብ ጊዜ ዝብ ይነክሳል እንዲሉ አበው፤ ብዙ ንቦች (ካህን፣ሰባኪ፣ዘማሪ፣አስተዳዳሪ ወዘተ ንግግር ተኮር የሆኑ ነን ባዮች) ቢኖሩንም እግዚአብሔርን ማክበር ድካም በሚጠይቅ አገልግሎት ሠርተው እያሳዩን ናቸው፡፡ ንግግርን በተግባር፤ የቃላት ጨዋታን በሥራ ቀይረው ያሳዩን የተመሰገኑ ናቸው፡፡

  ቤተክርስቲያን እነዚህን ወጣቶች የምታውቅበት፣የምትመራበት፣ከአገልግሎታቸውም የምትጠቀምበት መዋቅር የግድ ይላታል፡፡ ብዙ ማኅበራትን እንደየተቋቋሙበት የአገልግሎት ዓይነት በመመዝገብ ማሰለፍ አገልግሎቱን ቅቡል ማድረግ ብቻ ሳይሆን የግለሰብና የጥቂት ቡድኖች ትምክህታዊ አካሄድንም ፈር ለማስያዝ በእጅጉ የሚጠቅም ይመስለኛል፡፡

  በነገራችን ላይ “ምን ዓይነት ሲኖዶስ ያስፈልገናል?” በሚለው ጽሑፍ የተገለጸው የተሻለና ወቅቱን እየዋጀ የሚቀረጽ አደረጃጀት አስፈላጊነቱ በዚህ ሳይገለጥ ይቀራል?


  እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 11. Good article but I don’t like your specifics about mentioning names of the people you don't like. If you start with general concept please finish it that way. Uniformity and consistency should be part of the article. We as your audience weigh the blogs credibility. Trust me if I read anything biased I will keep commenting. Eventually it will erode your credibility too. Remember No mentioning names in any article. Keep up the good work!

  ReplyDelete
 12. ማን ያውቃል?

  ReplyDelete
 13. KALE hiwot yasemalin Dn. Daniel.
  Is there anything we can do to help keep and teach these miracle children under the shadow of mother church? Any suggestions? Because it is like a miracle for me to see and hear about these one time hopless orthodoxawiyan to come to their sense and try to serve GOD. Please let's do something? Let's try to help them stay in their real home. Please let's discuss about it .These is our duty. Egziabher Yistilin. Atlanta

  ReplyDelete
 14. WELL SAID DEAR BRO.

  ReplyDelete
 15. Deacon Daniel, Egziabher yibarkh! Silenezih lijoch kefu ye miyasibewn chinqilat Egziabher yimelsew. Yenezih lijoch endezih be hibret menessat egna ye manawqew, neger gin Egzer ye miyawqew miknyat linor yichilal. Egziabher asteway lebuna yisten!

  ReplyDelete
 16. Qale Hiot Yasemalin Dani.EGZIABHER YITEBIKIH DN DANIEL.

  ReplyDelete
 17. Great article God bless you.

  ReplyDelete
 18. ዲ.ዳንኤል እግዚአብሔር አገልግሎትህን ይባርክ!
  በእውነቱ ተገቢና ወቅታዊ ጽሑፍ::

  ሀሳቤን ተስፋዬ የተባሉ ጸሐፊ በአግባቡ ስለገለጹልኝ አመሰግናለሁ:: እውነትም ከዚህ በፊት ያልተደረሰበት አገልግሎት!

  "ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለዕዳ አይሸከመውም" የሚለውን አገራዊ አባባል እውነታነት የተረዳሁት በዚህ ክስተት ነው:: በፊት ጥምቀትን ማክበር የሚገለጸው ታቦታትንና ካህናትን በመጋፋትና በማስጨነቅ ነበር:: ሌሎችም እኛን ተከትለው ለማቃለል የሚቀድማቸው አልነበረም:: ዛሬ ግን ለታቦተ ጽዮን ይሰጥ የነበረው ክብር በእነዚህ ወጣቶች ምክንያትነት በመላ አገሪቱ መታየቱ ጠላትን የሚያሳፍር ነውና ልንደሰት ይገባናለ::

  በምኖርበት በጎንደርና አካባቢው ዲ.ዳንኤል እንዳልከው ሰንበት ተማሪዎችን ከመላከፍና ከጥምቀት ሰውነት(ከወቅታዊነት) ወጥተው ግንባር ቀደም አገልጋዮች ሆነዋል:: እነሱ ዱርዬ እንደሆኑ ይኖራሉ ብሎ ማሰብማ አገልግሎታቸው በእግዚአብሔር ዘንድ ቦታ አላገኘም እነደማለት ነው:: የአገልግሎታቸውን ዋጋ ፈጣሪ እነሱን በሚደንቅ ሁኔታ በመቀየር እየገለጠው ነውና እንቅፋት አንሁናቸው::

  እግዚአብሔር ፍጻሜአችንን ያሳምርልን::

  ReplyDelete
 19. "እናንተ ዝም ብትሉ እንዚህ ድንጋዮች ያመሰግናሉ!!!" አዋቂ ነን ያልነው ስንኮፈስ፤በእኔ በልጥ ጭቅጭቅ ዘመናችንን ከንቱ ስናደርግ፤ግለሰባዊ.የማኅበር ዝና እና ገንዘብ ብቻ ሲታየን....እግዚአብሔር የተናቁትን አስነሳ።ማናችንም ያላሰብነውን በትጋት እየተወጡት ነው። በትክክል መዘመር አቅቶን ስንጥመለመል እንሱ መንገዱን አድላድለው ቄጠማ ደልድለው፤ ምንጣፍ ዘርግተው ታቦታቱን አከበሩ።ክርስትና የሚያወሩት ሳይሆን የሚኖሩት ህይወት ነው ይሏል እንዲህ ነው።የተለቀመ እንጨት በልጥ እንዲታሰር አገልግሎታቸው ለስጋ ወደሙ እንዲያበቃቸው እናስተምራቸው። ብዙም ያልጠቀመንን ቢሮክራሲ ትተን በወንጌል እናንፃቸው። ከማረሚያ ቤት የታዘብከውን እንደዘገብክልን ሁሉ አንድ ቀን እነዚህንም አገልግለህ እንድታካፍለን የአምላካችን ቅዱስ ፈቃድ ይሁን።

  ስለዘገባው ቃለ-ህይወት ያሰማልን።

  ReplyDelete
 20. ማር 9:40"ዮሐንስ መልሶ-መምህር ሆይ አንድ ሰው በስምህ አጋንንትን ሲያወጣ አየነው፡ስለማይከተለንም ከለከልነው።ኢየሱስ ግን አለ-በስሚ ተአምር ሰርቶ በተሎ በነ ላይ ክፉ መናገር የሚችል ማንም የለምና አትከልክሉት።የማይቃወመን፣ እርሱ ከእኛ ጋር ነውና።"ስለዚህ እንዲህ ታቦት ፊት ጠብ እርግፍ የሚሉ ተገኝተው ማን ነው የሚቃወማቸው?እንደተባለው፤በተ ክርስቲያን በመዋቅርዋ ልትጠብቃቸው ይገባል።እነዚህ አሁን ከክርስቶስ ጋር፤፡ከተዋህዶ በተ ክርስቲያን ጋር፤ከእኛ ጋር ስለሆኑ አይዝዋችሁ በርቱ፣እያልን ልናበርታቸው በጸሎታችን ልናስባቸው ይገባል።

  ReplyDelete
 21. dani ye egziabiher selamina tsega lante yehun kehulu yemigermegn logoh lay yalew nisir {egil}new menfesawie wnetawochin ymitayibet ainochihen yibarkachew tikikilegnaw hawarianetim yehe new {enante ye alem birihan nachihu teblo tetsifolinalina

  ReplyDelete
 22. ya brother i think so,"Lessu Min yisnwale bilek new"!!!
  Tnx Brother.

  ReplyDelete
 23. Dane kale hiwet yasemalen. Enquan lebrehane timketu kene melaew betesebh aderesh.

  ReplyDelete
 24. who knows? it is good beginning!!

  ReplyDelete
 25. በትክክል እንቅስቃሴያቸው የሚያስመሰግናቸው እንደሆነ ተረድተኸዋል ፡፡ ስሜታቸውን እንደጠበቁ የእምነታቸው እውቀት እንዲኖራቸው ማድረግ የግድ ይሆናል ፡፡ እነሱም ቢሆን ለእምነታቸው ለመስራት ስለ እምነታቸው ለመረዳት ወደኋላ የሚሉ አይደሉም ፡፡ እኔ በነበርኩበት የሃና ማርያም ላፍቴ አካባቢ አጥቢያ ወጣቶች አንተ እነደታዘብከው አካባቢ እንዳሉ ወጣቶች ነበር ተግባራቸው የሃና ወጣቶች የሚለዩት ከአካባቢው የኑሮ ሁኔታ አንጻር ግን ጥረታቸው ከየትኛውም ወጣቶች ሁሉ የሚመሰገኑ ሆነው አግኝቼዋለሁ ፡፡ እነሱንም ለማናገር እንደሞከርኩት ከሆነ የሚያቀርባቸው እና የሚያገለግላቸው ካገኙ ሙሉ ፈቃደኝነታቸውን ገልጠውልኛል ፡፡ በዚህ ጉዳይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሚመለከትን ሁሉ የቻልነውን ብናደርግ ይሻላል እንጂ ቤተክነትን መጠበቁ ብዙም አልተዋጠልኝም ፡፡

  ReplyDelete
 26. ዳኒ ቃለ ሕይወት ያሰማልን።
  ሌላ እውነት ልንገርህ። አዋሳ ላይ በከተራ ቀን ምንጣፍ ሲያነጥፉ ውለው ለዕለቱ ግን ተከልክለዋል። ምክንያት የተደረገውም ለሀገረስብከቱ ሰላም ማጣት በየዕለቱ የሚተጋውና ነጋዴው ያሬድ አደመ ስላለበት ነው። የጥር ሥላሴ በዓል ላይ በግልጽ ራሱ ያሬድ እንደተናገረው ብር እንዲዋጣና ወጣቶቹ እንዲያገለግሉ ብሎ ሲያውጅ ማንንም አላማከረም። ይህ አካሄዱ በሌላም በኩል እኔ ላስተምር፣ ወዘተ የሚል የበዓል ሽሚያ እና ከቤ/ክ/ ውጪ ጉባኤ ስለማካሄድ ጳጳሱ ባሉበት ያለኃፍረት ሲናገር የሚገርምህ ማንም አልፈቀደለትም ነበረ። እናም ጠንካራ ጥናት ሳይፈልግ አይቀርም፤ ምክንያቱም የማይታዩ ኃይሎች ስላሉ፤ ለወጣቶቹም መጽናት ዕንቅፋት እንዳይፈጠር። አይመስልህም?

  ReplyDelete
 27. Dn. Daniel yihenin issue lela blog layim anbibew neber gin menfese techenka neber beteley kesir yalu comments betam yirebshalu endiyawum yeteregaga ena meftihe azel menfesawi mereja felge mahiberekidusan mekane dir bigeba minim lagegn alchalkum ahun gin yanten tsihuf kanebebku behuala selam tesemagn tikikilegna neger yesemahu meselegn mekases yelebet egeke yihn yan ale yemil nitirik yelewum kalehiwotin yasemah legudayum amlak meftihe endisetew betinishiwa tselote esatefalehu.
  geta lemengaw yemirara eregna newuna.

  ReplyDelete
 28. Kale Hiwot Yasmalin, Endanferd Egziabhair Beante adro astemironalina

  ReplyDelete
 29. Hello,
  It is an interesting issue. D/n Daniel, I appreication your idea flow and the way you put things timely base. Please keep it up posting religious topics and issues related to church.

  Egziabher yistelign

  ReplyDelete
 30. ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር ይስጥልን
  በእውነት እነዚህን ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር በልዩ ልዩ መንገድ የጠራቸውን ሰዎች አያያዙ ላይ ሊታሰብበት ይገባል በቤተክርስቲያናችን የተለመደው እራስህን አድን እንጂ መንገዱ ይሄ ነው ብሎ ማሳየት ብዙም አይታይም በሌላ ጎን ደግሞ ስለመጡ ተብሎ እንዲሁ መልቀቁም ጥሩ አይመጣም ዋናው በሰል ያለ አያያዝ ያስፈልጋል
  ለሁሉም እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅ
  አሜን

  ReplyDelete
 31. ዲ.ዳንኤል እግዚአብሔር አገልግሎትህን ይባርክ! ይህንን አስተያየት ስሰንጥ እኔም አንዱ ወጣቶችን ሳስተባብር ስለነበረ ነው በእውነት ነው የምልክ እግዚአብሔር ታሪካችንን እየለወጠልን ነው ብቻ አንድ ነገር መናገር የምፍልገው ከጎናችን ሆናች እርዱን አግዝን አስተምሩን በ እግዚአብሔር ስም እለምናቺሁአለሁ የግቢ ገብርኤል ወጣቶቺን ወክዬ ነው
  እግዚአብሔር ሰላሙን ይስጠን

  ReplyDelete
 32. እኛም ዘንድ ልክ እንዲሁ ነበር፡፡ “እድሜ ልኬን ካየኋቸው አከባበሮች ሁሉ እጅግ ያማረው፣ የሠመረው አከባበር ይሕኛው ነው!” ብል ማጋነን አይሆንብኝም፡፡

  የቅዱስ ማርቆስንና የቅዱስ ሚካኤልን ታቦታት ይዘን ከጃንሜዳ ተነሥተን ስድስት ኪሎ የሚገኘው መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን እስክንደርስ ድረስ ታቦታቱ በቀይ ምንጣፍ ላይ፣ ጽንሐሕ የያዙ ካህናት እንዲሁም የመጾር መስቀልና ጥላ የያዙ ዲያቆናት ግራና ቀኝ ሆነን አሸብርቀን ነበር የገባነው፡፡ ሁኔታው ሁሉ እጅግ ያምር ነበር፡፡ ለዚህ ውበቱ ግን እኛ ካህናቱ አምፖሎች እንጂ “ጄኔሬተሮች” አልነበርንም፡፡ ጄኔሬተሮቹ ያንን ክብደቱ ወገብ የሚበጥስ ምንጣፍ ከኋላ ሲጠቀልሉ፣ ከፊት ሲያነጥፉ፣ መጥረጊያ ይዘው ሲያጸዱ፣ በእጆቻቸው ቆሻሻ ሲለቅሙ፣ እጅ ለእጅ ተያይዘው ሕዝቡን በመሥመር ሲመሩ፣ ፈረስ ላይ ሁነው ጡሩምባ ሲነፉ፣ ላባቸው ጠፍ እስኪል፣ ላንቃዎቻቸው እስኪደርቁ ድረስ ሲዘምሩ የነበሩት የተወደዱ እግዚአብሔር ልጆች ናቸው፡፡

  አንዳንዶቻችን “የመጥምቃውያኑ” ሰፈር የምናውቀው ማንነት እንጂ አደባባይ ላይ የምናየው ታዛዥነት አልዋጥ ይለን ይሆናል፡፡ ወደድንም ጠላንም ግን አንድ ሐቅ አለ፡፡ ይኸውም እነዚህ ወጣቶች ቢያንስ ለዚህች ቀን እግዚአብሔርን “እሺ!” ብላውታል፡፡ አቧራ ለመሸከም፣ ቆሻሻ ለመልቀም ያስጎነበሳቸው የኛ አብነትም ሆነ ስብከት አይደለም፡፡ እግዚአብሔርን በቀና ልቡና “እሺ” ማለታቸው እንጂ፡፡ አንድ ከመካከለኛው ምሥራቅ አካባቢ የመነጨ ጥንታዊ ተረክ እንደሚለው ሁል ጊዜ ከመምህሩ ቀድሞ በመነሣት የፊት ውኃ አሙቆ የሚያቀርብላቸው አንድ ወጣት ደቀ መዝሙር ነበር፡፡

  ይህ ደቀ መዝሙር መምህሩን እጅግ ይወዳልና አንድም ቀን ሥራውን አስታጉሎ አያውቅም፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ግን የጠዋት ዕንቅልፍ ጣዕም ጥሎት ሳለ መምህሩ ከዕንቅልፋቸው ነቅተው ከበረንዳቸው ላይ ሲንጎራደዱ ኮቴያቸውን ይሰማል፡፡ ብትት ብሎ ይነሣና ውኃ ፍለጋ ይሄዳል፡፡ ደግነቱ የውኃው ጉድጓድ እግቢው ውስጥ ስለነበር ብዙም አልተቸገረም፡፡ ውኃውን ቀድቶ ሲመለስ ግን አንድ ነገር ትዝ አለው፡፡ ለካ ለመምህሩ የሚቀርበው ውኃ ሊሞቅ ይገባል! እርሱ ደግሞ ገና እሳት እንኳ አላቀጣጠለም፡፡ ወይ ጣጣ! ጭንቅ አለውና ውሃ የቀዳበትን የጠዋት ቅዝቃዜ የወረሰው ኩስኩስት ወደ ደረቱ ጥብቅ አድርጎ ያዘው፡፡ አፍታም ሳይቆዩ መምህሩ ወደፊት መታጠቢያው ቀረብ አሉ፡፡ ይሄኔ ደቀ መዝሙሩ ምንም አማራጭ ስላልነበረው በኩስኩስቱ የያዘውን ውኃ ይዞ ቀረበና ይጨምርላቸው ጀመር፡፡ መምህሩ ከዕንቅልፉ አርፍዶ እንደተነሣ ብቻ ሳይሆን ውኃ ማሞቂያ እሳትም እንዳልተቀጣጠለ ተመልክተዋልና እጃቸው ላይ እየፈሰሰ ያለው ውኃ ሙቅነቱ ሊገለጥላቸው አልቻለም፡፡ ግራ መጋባቱ ሲበዛባቸው፡-

  “ውኃውን የት ጥደኸው ነው እንዲህ ባንዴ ያደረስኸው?” ብለው ጠየቁት፡፡
  እርሱም “ልቤ ላይ! መምህር ሆይ!” ብሎ መለሰላቸው፡፡

  ከልብ የሆነ ፍቅር ቀዝቃዛውን ውኃ ያሞቀዋል፡፡ የማይመቸውን ነገር እንዲመች አድርጎ ዳግም ይፈጥረዋል፡፡

  ምናልባት በአስደናቂ ኋላቀርነቱና በንትርክ ቤትነቱ ተወዳዳሪ የሌለው የማይመስለው የቤተክህነታችን አሠራር እነዚህን ወጣቶች ለማቀፍ ወገቡን ያመው ይሆናል፡፡ ምን ይደረግ ልማድ ሆኖበት ነው፡፡ ፍቅርም ኮ ካልተለመደ ችግር ነው፡፡ እንደቤተክህነታችን ንትርክና መዝረክረክ ቢሆንማ ኖሮ እንኳን እንዲህ የደመቀ የሦስት ቀን በዓል ይቅርና የግማሽ ሰዐት መደማመጥ የነገሠበት ውይይትም መከናወን ይችላል ብዬ ለማመን እቸገራለሁ፡፡ ደግነቱ ወጣቶቹም እግዚአብሔር የሚያሣምርላቸውን ሥራቸውን እንጂ ቤተክህነቱን አያስቡትም፤ ቤተክህነቱም እነሱን ስለነፍሳቸው ተጨንቆ የሚያስባቸው አይመስልም፡፡ ለነገሩ እንኳን በዓመት አንዴ የሚመጡትን ቀርቶ በየአድባራቱ በራሳቸው ፈቃድ ድንጋይ ላይ ቁጭ ብለው በማያውቁት ቋንቋ ውዳሴ ማርያም የሚቆጥሩትን አንዳንድ ሕጻናት እንኳ መች አሰበ?!

  ስለሆነም ቤተክህነቱ እነዚህን ትጉኃን እስኪያቅፋቸው ድረስ እናንተ የቤተክርስቲያን የወንጌል ሰባኪዎች ስለምን በየአድባራቱ እነርሱን የሚመለከቱ፣ ለመንፈሳዊ ደረጃቸው የሚመጥኑ ጉባኤያት አታዘጋጁላቸውም? ለምሳሌ በብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ለሾፌሮችና ለረዳቶች ተብሎ ይዘጋጃል፡፡ ልክ እንደዚሁ እነዚህን ወጣቶች የተመለከተ አንድ ጉባኤ በየአድባራቱ ማዘጋጀት ብዙም ከባድ የሚሆንብን አይመስለኝም፡፡ ትንሽ ጠንከር ስንል ደግሞ እነርሱ ብቻ የሚታቀፉባቸው ታላላቅ አድባራትንና ገዳማትን የሚጎበኙባቸው መርሐግብሮች ማዘጋጀት የበለጠ ፍቅራቸው እንዲጨምር የሚያደርግ ይመስለኛል፡፡ እስኪ በየአድባራቱ ያላችሁ የስብከተ ወንጌል ኃላፊዎች የእነዚህን ልጆች መንፈሳዊ ሕይወት እንዴት ማጎልበት እንደሚቻል እንደው ለሻይ ለቡና ስትገናኙ ተነጋገሩበት፡፡

  እግዚአብሔር ይርዳን!

  ReplyDelete
 33. መሐሪ ቃለ ሕይወት ያሰማህ

  ቤተክህነትን በተመለከተ ያቀረብከው ምናልባትም ውስጡን ስለምታውቅ ይሆናል ትክክለኛና ተመራጭ ያልሆነው አቅጣጫና መዋቅር ስለሆነ አንተ የመረጥከውን አማራጭ እእደግፋለሁ።

  ትንሽ ለየት የሚለው ሀሳቤ ግን ሰባክያኑ ሁኔታዎቹን ከሚያመቻቹ ይልቅ ሁሉም አጥቢያ ለወጣቶቹ ጥሪ በማድረግ ፕሮግራም ቢይዙላቸውና ሰባክያኑን ቢጋብዙ አካሄዱ በጣም ቀላልና ፍጥነት ይኖረዋል ብዬ አስባለሁ። ይህን ያልኩት ለሰባክያኑ የተለየ ቦታ በመስጠት ሳይሆን አጥቢያዎቹ ያለባቸውን ኃላፊነት ለማስታወስና የሰባክያኑ ጣልቃ ገብነት እንዳይፈጠር በማሰብ ነው። በእኔ እምነት ዲ.ዳንኤልን ጨምሮ ሌሎች ሰባክያን ለዚህ ፕሮግራም ቅድሚያ ይሰጣሉ የሚል እምነት አለኝ። ሰው በወደደ ሳይሆን እግዚአባሔር በፈቀደ አምጥቷቸዋልና።

  የቤተ ክህነትን ጉዳይ ግን "ለምን ሰብስባችሁ አስተማራችሁ?" የሚል ውዝግብ ይዞልን እኪመጣ ወደጎን ብናቆዬው።

  እግዚአብሔር ሀሳባችንን ይፈጽምልን።

  ReplyDelete
 34. just wow i really don't have any words...EGZABHER AMLAK YRADACHO

  ReplyDelete
 35. Thank you Dn Daniel.You explain it in a good way.
  But now a days I am so scared new things around church.I love the way as it is. But now you made it so clear and you tell us how positive we need to be. Thank you so much.

  ReplyDelete
 36. ሁሉንም ነገር ግን መንፈሳዊነት ሊቀይረው እንደሚችል ማመን ግን ያስፈልጋል፡፡ እኛስ ባንለወጥ ኖሮ ከዚህ የባስን አልነበርንም እንዴ!

  ReplyDelete
 37. WHAT MAKES ME HAPPY IS NOT WHAT D.DANIEL WRITES ONLY BUT THE COMMENTS TOO. THANKS BROTHERS AND SISTERS SUCH KINDS OF COMMENTS ARE TOO MUCH IMPRESSIVE AND SPIRITUAL THEY ARE DIFFERENT FROM WHAT I READ FROM OTHER BLOGS DANI I RELY THANK YOU VERY MUCH I ALSO RAD WHAT YOU WROTE IN A LOCAL NEWS PAPER ABOUT LIBERALISM I PROUD OF YOU GOD BLESS YOU

  ReplyDelete
 38. የዘመኑ የተሃድሶ እንቅስቃሴ...

  ሐይማኖት የምንቀበለውና የምንጠብቀው እንጂ የምንሰራውና የምናሻሽለው አይደለም።

  ድርጊቱን በዓይኔ ባልመለከትም በወሬ ግን ሰምቻለሁ።
  በመጀመሪያ መንፈሳዊ አገልግሎት ማለት ምን ማለት ነው?
  መንፈሳዊ አገልግሎት ማለት እኮ እንደ መስቀል ወፍ ከዓመት አንዴ ብቅ እያሉ መታዬትና የሰውንም ቀልብ መሳብ አይደለም።
  ይህን ለማድረግ እኮ ብዙ ጊዜንና አቅምንም ይጠይቃል።
  ደግሞም እኮ አንተ እራስህ ተናግረሃል፡ የገቢ ምንጫቸው የማይታወቅ በማለት።
  እናስ እስከ ዛሬ ድረስ የት ነበሩ? አዎ ገናም መሰሎቻቸውንና አባላቶቻቸውን አብዝተው የራሳቸውን ጎራ (ድርጅት) እስከሚከፍቱ ድረስ ማንነታቸውን አይገልፁም፡ ነገር ግን እርሱ አንድዬ የሁሉንም ልብና ኩላሊት ይመረምራልና አንድ ቀን መጋለጣቸው ግን አይቀርም። ለዚህ ደግሞ ማህበረ ቅዱሳንም የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት እላለሁ።

  ReplyDelete
 39. you already said our thoughts.You put it briefly the quality of these younger s!Our church has to use this chance.

  God bless you.

  ReplyDelete
 40. ዲ/ን ዳንኤል ተባረክ ረጅም የአገልገልግሎት እድሜ ይሰጥህ. ጌታ ይርዳን!!

  ReplyDelete
 41. thank you long live brother

  ReplyDelete
 42. Replies
  1. Anonymous Feb, 3 I read your comment, but you are looking every thing in negative direction. Why you are saying "Yezemenu Tehadiso Enkiskase" . These guys are called from street by Jesus Christ. "ye medan ken zare new" endetbalew. In any ways take care for your self, they are cured already. "mazen leras new" May God help you. By the way i would appreciate Dani for your comments and advises, thanks

   Delete
 43. wendime Daniel, E/gr yibarkih.

  ReplyDelete