የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን የአብነት ሊቃውንት ስናስታውስ ብዙ ጊዜ ስማቸው የሚነሡት ወንዶች ናቸው፡፡ ጥንታዊው ባህላችን ሴቶችን በልጅነታቸው ስለሚድር ከፍ ወዳለው የትምህርት ማዕረግ እንዲደርሱ አላደረገም፡፡ በርግጥ ውዳሴ ማርያም አጥንተው፣ ዳዊት ደግመው ሌላውንም የቃል ትምህርት የሚሞካክሩ እናቶች በየቦታው ሞልተው ነበር፡፡
አልፎ አልፎ እንደ ተወርዋሪ ኮከብ ብቅ ብለው ታሪክ የሚቀይሩ እናቶችም ነበሩ፡፡ በ16ኛው መክዘ የተነሡት የቅኔዋ ሊቅ እማሆይ ሐይመት፣ በቅርቡ ዘመናችን በቅኔ ችሎታቸው የታወቁ የነበሩት የጎንጅዋ እማሆይ ገላነሽ ለዚህ አብነት ሆነው ይጠቀሳሉ፡፡
በተለይም የነ እማሆይ ገላነሽ ታሪክ በየቦታው መነገር እና በየሚዲያው መነሣት ሌሎችንም እኅቶች ወደ አብነት ትምህርቱ እንዲገቡ እና ችግሩን ሁሉ ተቋቁመው በመምህራኑ ወንበር እንዲቀመጡ እያደረገ ነው፡፡
እማሆይ ወለተ ሕይወት ይባላሉ፡፡ እድሜያቸው ወደ 45 ዓመት ይሆናል፡፡ የሚገኙት በአኩስም ጽዮን የቅዱስ ያሬድ ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ውስጥ ነው፡፡ አኩስም የቅዱስ ያሬድን ዩኒቨርሲቲ ለማቋቋም በተመሠረተው ኮሚቴ ስለማገለግል በተደጋጋሚ አሄዳለሁ፡፡ እዚያ አንዲት የአብነት መምህርት እንዳሉ እሰማ ነበር፡፡
እኒህን እናት ለማነጋገር እና እንዴት ከውሻ ጋር ታግለው፣ ኮቾሮ ለምነው፣ አገር ላገር ዞረው፣ በሴነት የሚያጋጥመውን ፈተና ተቋቁመው ለዚህ ሊበቁ ቻሉ? የሚለውን ለማወቅ እጓጓ ነበር፡፡ ጉዞዬ የስብሰባ መዓት እየወረደበት አላገጣጥም ብሎኝ ሁለት ሦስት ጊዜ አሳለፍኩ፡፡
ባለፈው ለአኩስም ጽዮን በዓል ወደ ሥፍራው በሄድን ጊዜ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ማረፊያችን በቅዱስ ያሬድ ከፍተኛ መንፈሳዊ ት/ቤት ግቢ ውስጥ ሆነ፡፡ እኔም ዕድሉን አገኘሁና እዚያ ያገኘኋቸውን ተማሪዎች ስለ ጉዳዩ ጠየቅኳቸው፡፡
እነሆ ከእማሆይ ጋር ተገናኘን፡፡
«በ1975 ዓም ነው ቤተሰቦቼን ትቼ በምናኔ ወደ አኩስመ የመጣሁት፡፡ እዚህ እንደ መጣሁ ስለ መጋቤ ምሥጢር ሄኖክ ሰማሁ፡፡ የትርጓሜ መጻሕፍት ሊቅ የሆኑት መጋቤ ምሥጢር ሄኖክ ሴቶች መማር አለባቸው የሚል አስተያየት እንዳላቸው ሰማሁ፡፡ ከዚያ እኔም ወደ እርሳቸው ሄድኩ፡፡
«የቤተ ክርስቲያን ትምህርትን የጀመርኩት እዚያ ነው፡፡ የትግራይ ተማሪ ለሴቶች ያዝንልናል፡፡ ያበረታቱናል፡፡ ለምነው ያመጡልናል፡፡ እንድንቸገር አይፈልጉም፡፡ መጋቤ ምሥጢርም ለሴት ተማሪዎች ክብካቤ ያደርጋሉ፡፡ ደግሞ አኩስም የተለመደ ነው፡፡ ከኔ በፊት ታላቋ ባለ ቅኔ መምህርት መብራት በዚሁ ቦታ ቅኔ ማስተማር ጀምረው ነበር፡፡»
እማሆይ በ1984 ዓም ቅኔ ለመማር ወደ ጎጃም ጎንጅ ጽላሎ ወረዱ፡፡ እዚያም የቅኔውን መምህር የኔታ ያሬድን አገኟቸው፡፡ የኔታን ለመማር እንደመጡ ሲነግሯቸው፡፡ ተጨነቁ፡፡ እንዴት አድርገው መማር እንደሚችሉ ያስቡ ነበር፡፡ መጀመርያ እምቢ አላሏቸውም፡፡ ጎጆ ይሠራላት ብለው በተማሪዎቹ አሠሩላቸው፡፡ «ትጸናለች ብለው አላሰቡም ነበር፡፡ እንዴው ትንሽ ቆይታ ስትቸገር ትሄድ ይሆናል ብለው ነው የተቀበሉን» ይላሉ እማሆይ ሲያስታውሱት፡፡
ተማሪዎቹ ረዷቸው፡፡ የተማሩትን በማስተማር፣ በማስቀጸል፣ ከሚበሉት በማካፈል፣ ከአደጋም በመጠበቅ ተከባከቧቸው፡፡ «በትምህርቱ እንደገፋሁበት ሲያውቁ የኔታ ከእርሳቸው ቤት አጠገብ አደረጉኝና ከራሳቸው ምግብ ይመግቡኝ ጀመር፡፡ ለተማሪዎቻቸው ማስተማርያ አደረጉኝ» ይላሉ እማሆይ፡፡
እስከ 1987 ዓም ጨጎዴ ሐና ቆዩ፡፡ ከዚያም ቅኔውን አስመስክረው ወደ አኩስም ተመለሱ፡፡ አኩስም ላይም ወንበር ተክለው ማስተማር ጀመሩ፡፡
ዛሬ እማሆይ ቅኔ እና ትርጓሜ መጻሕፍት ያስተምራሉ፡፡ አሥር የመጻሕፍት ተማሪዎች እና 30 የቅኔ ተማሪዎች አሏቸው፡፡
እንዴው ይህንን አገልግሎትዎን ይበልጥ ለማሳካት ምን ቢደረግልዎ ይወድዳሉ? አልኳቸው፡፡
«ለተማሪዎቼ ቤተ መጻሕፍት ቢኖራቸው፤ የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት አንድ ላይ አግኝተው ሊያነቡ የሚችሉበት ዕድል ቢኖራቸው፤ ይህንን ነው የምፈልገው» ነበር ያሉኝ፡፡
MInew Astarekew Dani
ReplyDeletekalehiwot yasemalin dn daniel
ReplyDeleteEOTC should be acknowledge for the contribution made for ethiopias modern education.
Emahoyen yetebekilin
Abiot k oldenburg germany
asabhin egziabiher yasakalih.
ReplyDeletebirtatun yistih kekifu yitebkih amen.
Good job,keep going. we should support the work of Emahoy by whole means,she can be a model for the rest of emerging womens scholar in Ethiopia. may the protection and grace of God be with Emahoy!
ReplyDeleteAntonio Mulatu
ሰላም ደ ዳንኤል ቃለ ሕይወት ያሰማልን ድኒ እድሜ ከጤና ጋር እግዚአብሔር ይስጥህ። ብዙ ነገር እያስወከን ነው።ስለ ጽሑፎች ሁሉ ማመስገን ምንም የማያጠያይቅ ጉዳይ ነው፡፡እግዚአብሄር በአገልግሎትህ ያበርታህ !!!yonas
ReplyDeleteእንዴው ይህንን አገልግሎትዎን ይበልጥ ለማሳካት ምን ቢደረግልዎ ይወድዳሉ? አልኳቸው፡፡
ReplyDelete«ለተማሪዎቼ ቤተ መጻሕፍት ቢኖራቸው፤ የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት አንድ ላይ አግኝተው ሊያነቡ የሚችሉበት ዕድል ቢኖራቸው፤ ይህንን ነው የምፈልገው» ነበር ያሉኝ፡፡ ታዲያ እኛ አሁን ለዚህ ካልሆንን ክሽን ያለ ጽሁፍ እያነበብን ዝም የምንል ከሆነ ምን እንጠቅማልን? ምንስ እንጠቀማለን? ስለዚህ ነገር እናስብና እነዘጋጅበት፤ ዳኒ ይሀንን ጉዳይ አንተም ጠቆም አድርገሃል ግን ጫን ብታደረገው የዳንኤል ክብረት እይታዎች አንደኛ ዓመት በሚከበርበት ወቅት አስተባብረህ እነግዶች ሁሉ አንድና ከዛበላይ መጽሐፍ ቢያበረክቱና የእማሆይን ህልም ዕውን ማድረግ ብንችል፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ የተመረጡ የመጽሐፍት መዘርዝር ቢዘጋጅና እዚህ የህዋ ግድግዳ ላይ ቢለጠፍ፤ እኔ በበኩሌ ሁለቱን ለማምጣት ቃል እገባለሁ፡፡ የቤተ-ክርስቲያን አምላክ ይጠብቀን!!!
yihen sanib enbayen mekotater akitognal. be-and bekul tefan, feresin eyalin tesfa sinata; belelaw endezih aynet yemaytamen sira yasayenal. tadia egnihin kalredan mindinew sirachin. ebakachihu endet enagizachew?
ReplyDeletedani egzer yastawusih.
Aksum ye kidus yared menfesawi keftegna timirtbet bet sile Kidus yared lealem yemilew yinoral wedefit tilik yemirimir tekuam yihonal KE menfesawi bashager. Berta Dani.kale hiywet yasemalin.
ReplyDeleteመርአተ ድንግል ዘጎንደር
ReplyDeleteበመጀመሪያ ከሁሉ አስቀድሞ እግዚአብሔር አምላክ የተመሰገነ ይሁን፡፡ዲ/ን ዳንኤል ፕሮግራምህን ያነበብኩት ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን በጣም ደስ ብሎኛል፡፡እንደዚህ አይነት እናቶች በአሁኑ ጊዜ መገኘታቸዉ ለእኛ ጽናት ይሆነናል፡፡ዳኒ ሁሉን እንድናደርግ የሚረዳን አምላካችን የተመሰገነ ይሁን፡፡ ከመንፈሳዊ ኮሌጆች ለእኝህ አናት የትምህርት እድል ቢሰጣቸዉ እና የተማሩትን የቅኔ ትምህርት በሰፊዉ ማስተማር እንዲችሉ ቢመቻችላቸዉ ለሌሎች እንደዚህ አይነት ፍላጎት ላለን እህቶች ሞራል ይሆናል፡፡በተጨማሪም ቅኔያቸዉ ተቀናብሮ በመጽሐፍ ወይም በሲዲ ተዘጋጅቶ ቢወጣ ይጠተቅማል፡፡ ሌሎችንም እህቶች ያበረታታል፡፡ ዳኒ እግዚአብሔር አምላካችን አገልግሎታችንን ይባርክ፡፡አሜን
ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር በ አገልግሎትህ ያበርታህ፡፡
ReplyDeleteአንዲት ዕማሆይ (ስማቸዉ ተዘንግቶኛል)በ ግንቦት 2002 ዓ/ም በ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ የ ኢ/ኦ/ተ/ ቅዱሳን ጳጳሳት ና ቅዱስ ፓትርያሪኩ በተገኙበት ቅኔ ሲአቀርቡ አይቼ በጣም አድንቄ ተደስቼአለሁ፡፡
ስለኝህ ዕማሆይ (ስማቸዉ ተዘንግቶኛል)ከመድረክ በ ዲማህ ጊዮርጊስ የ ቅኔ መምህርት እንደሆኑ ሲነገር ሰምቻለሁ ...
ዲ/ን ዳንኤል ስለኝህ ዕማሆይ (ስማቸዉ ተዘንግቶኛል)ብትፅፍልን ...
E.B
every body has to give attention for women.
ReplyDeleteየእማሆይን ሃሳብ ለማሳካት ተተኪዎችን ለማፍራት እንዲሁም ሌሎች በመንገድ ላይ ያሉ እማሆይን የመሳሰሉትን እናቶች ብርታት ለመሆን የሚያስተባብር ከተገኘ የእማሆይ ሃሳብ እውን የሚሆንበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም ምክንያቱም እንዴት በምን መንገድ ምን በማድረግ የሚለውን ሃሳብ ማቀናጀትና ወደ ተግባር መለወጥ ነው እንጂ የሚያቅተው መንገዱን የሚመራው ካገኘ ህዝበ ክርስቲያኑ በገንዘቡም በጉልበቱም የሚፈለገውን ለማድረግ ወደ ኋላ የሚል አይመስለኝም እና በማስተባበሩ ብንበረታ
ReplyDeleteAD
ምን ነው ዲን ዳንኤል የሰጠሁትን አስተያየት በዚያው በላኸው? ወይ መጀመሪያ ጠቆም ባላደረግህ ከሆነም መከልከል የለብኝም ነበር። ፈራህ እነዴ? የቤተ ክርስቲያን አንጡር ሃብት በምራቡ አለም ባልተናነሰ ወደ ትግራይ እየተጫነ ነው። በዚህ ከቀጠለ መንበረ ጵጵስናውንም አባ ጳዎሎስ ወደ ትግራይ ይዘው የሚሄዱ ይመስለኛል። ነገረ ስራቸው አልጣመኝም! እንደ መለስ እሳቸውም እኔ ከሌለሁ ላሳር ብለው የተቀመጡ የዘመናችን ይሁዳ ይመስሉኛል። ለማንኛውም ድንግል ትርዳን!
ReplyDeletehoo! d.dani thehufeh betam yedenekal gena setoch bemehaber zim yebelu lemilew terguame men enbelachew? beterefe yebete metaheftu guday klaye endalew bitasebebet eneme yemechilewn 1 metahef esetalew from greec.athence
ReplyDeletekale hiwot yasemalin dn.daniel yihi neger be simea tsidik weyim begubae kana legib gubae temariwoch bidersen tiru new ehitochachinim yiberetataluna
ReplyDeleteቃለ ህይወትን ያሰማልን፡
ReplyDeleteእኔ ለመማር ካለኝ ጉጉት የተነሳ የዳዊት መዝሙር ንባብ ልጨርስ ነው፡፡ ነገር ግን ባለትዳር እና የልጆች እናት እንደመሆኔ መጠን ወደሌሎቹ ትምህርት የመዝለቄ ነገር እግዚአብሔር ነው የሚያውቀው፡፡ የሚቆጨኝ ነገር ቢኖር ግን ገና ትዳር ሳልይዝ ያሳለፍኩት ጊዜ ነው እንደው ዝም ብሎ መዝሙር ለመዘመር ሰንበት ትምህርት ቤት ከመመላለስ የአብነት ትምህርቱን ያኔ ብማር ኖሮ አሁን . . . . ብቻ ይሁን አሁንም የስላሴ ፈቃድ ይሁን እንጂ ከመማር ወደኋላ አልልም፡፡ እናቶች እንዲህ ሆነው ሳይ እንዴት ደስ ይለኛል፡፡
ቸር ይግጠመን
እማሆይ ወለተ ሕይወት ይባላሉ፡፡ እድሜያቸው ወደ 45 ዓመት ይሆናል፡፡ የሚገኙት በአኩስም ጽዮን የቅዱስ ያሬድ ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ውስጥ ነው፡፡ዛሬ እማሆይ ቅኔ እና ትርጓሜ መጻሕፍት ያስተምራሉ፡፡ አሥር የመጻሕፍት ተማሪዎች እና 30 የቅኔ ተማሪዎች አሏቸው፡፡ቃለ ህይወትን ያሰማልን፡
ReplyDeleteእኔ ለመማር ካለኝ ጉጉት የተነሳ የዳዊት መዝሙር ንባብ ልጨርስ ነው፡፡ ነገር ግን ባለትዳር እና የልጆች እናት እንደመሆኔ መጠን ወደሌሎቹ ትምህርት የመዝለቄ ነገር እግዚአብሔር ነው የሚያውቀው፡፡ የሚቆጨኝ ነገር ቢኖር ግን ገና ትዳር ሳልይዝ ያሳለፍኩት ጊዜ ነው እንደው ዝም ብሎ መዝሙር ለመዘመር ሰንበት ትምህርት ቤት ከመመላለስ የአብነት ትምህርቱን ያኔ ብማር ኖሮ አሁን . . . . ብቻ ይሁን አሁንም የስላሴ ፈቃድ ይሁን እንጂ ከመማር ወደኋላ አልልም፡፡ እናቶች እንዲህ ሆነው ሳይ እንዴት ደስ ይለኛል፡፡
ቸር ይግጠመን
ፈራህ እነዴ? የቤተ ክርስቲያን አንጡር ሃብት በምራቡ አለም ባልተናነሰ ወደ ትግራይ እየተጫነ ነው። በዚህ ከቀጠለ መንበረ ጵጵስናውንም አባ ጳዎሎስ ወደ ትግራይ ይዘው የሚሄዱ ይመስለኛል። ነገረ ስራቸው አልጣመኝም! እንደ መለስ እሳቸውም እኔ ከሌለሁ ላሳር ብለው የተቀመጡ የዘመናችን ይሁዳ ይመስሉኛል። ለማንኛውም ድንግል ትርዳን!
ReplyDelete*...ጎጃም ጎንጅ ጽላሎ ወረዱ* as far as I know ጨጎዴ ሐና is at quarit Wereda not Gonji wereda!
ReplyDelete