Tuesday, January 11, 2011

የገና ስጦታ

አንዲት ማየት የተሳናት ጓደኛ የነበረችው ልጅ ነበረ፡፡ ይህች ማየት የተሳናት ልጅ ዘወትር አንድ ምኞት ነበራት፡፡ ይህንን የሚወድዳትን ጓደኛዋን እና እርሱ የሚያየውን ዓለም ለአንድ ቀን እንኳን ቢሆን ማየት፡፡
ይህንን ምኞቷን ሲሰማ ጓደኛዋ ያዝን ነበረ፡፡ ምን ማድረግ እንዳለበት ያወጣና ያወርዳል፡፡ ነገር ግን መፍትሔ ያጣለትና ወደ ቀድሞው አኗኗሩ ይመለሳል፡፡ አሁንም በድጋሚ ያንኑ ምኞቷን ስትናገር ይሰማታል፡፡
እንዲህ ሲወጣ እና ሲወርድ አንድ ቀን ኅሊናው ወደ አንድ ቦታ መራው፡፡ እርሱም የኅሊናውን ምሬት ተከትሎ ተጓዘ፡፡ እንደሄደም አልቀረ አንድ ሐኪም ቤት ደረሰ፡፡ ሐኪሙ ዓይናቸው ማየት ለማይችል ሰዎች ዓይን በመስጠት የታወቀ መሆኑን ሰምቷል፡፡ እርሱም ለዚህ ነበር የመጣው፡፡
«ነገሩ ቀላልም ከባድም ነው» አለው ሐኪሙ፡፡ «ቀላል የሚሆነው ልጅቱ በሕይወት ካለ ሰው ዓይን ካገኘች ልትድን መቻሏ ሲሆን ከባዱ ደግሞ በሕይወት እያለ ዓይን የሚሰጥ ሰው ሊገኝ አለመቻሉ ነው»፡፡ የምሥራች እና መርዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ መታው፡፡
አሁንም አወጣ አወረደ፡፡ ሕይወት በተቃርኖ ውስጥ የምታልፍ መርከብ ናትና ኅሊናው ተማታ፡፡ ምን ማድረግ ይችላል? አንዳች ደግ ሰው መፈለግ አለበ" ብሎ ወሰነ፡፡ እናም ፍለጋውን ጀመረ፡፡
አንድ ሌላ ቀን ጓደኛውን እንዲህ አላት፡፡
«ግን ማየት ብትችይ እኔን አትጠይኝም ደነገጠች፡፡
«እንዴት? እንዴትስ ተደርጎ፤ ይሄ ሁሉ ምኞቴ አንተን ለማየት አይደል እንዴ)» ተቀየመቺው እንዲህ በማሰቡ፡፡
«ርግጠኛ ነሽ አኮረፈችው፡፡ ይህ መቼም ከሰይጣን እንጂ ከምትወደው ሰው የሚወጣ ነገር አልመሰላትም፡፡
«ማየት ብትችይ ታገቢኛለሽ ጠየቃት፡፡
«ዛሬ ጤነኛ ነህ አለችው ተናድዳ፡፡ «ታድያ ማንን ላገባ ኖሯል
«በይ የዛሬ ሳምንት ማየት ትጀምሪያለሽ» አለና ሐኪሙ የነገረውን ነገር ተረከላት፡፡ ቀናትን በሰዓታት ሳይሆን በሰኮንዶች መለካት ጀመረች፡፡
ቀኑ ደረሰ፡፡
ቀዶ ጥገናውም ተከናወነ፡፡
ለአንድ ሰዓት ያህል ድብን ያለ ዕንቅልፍ ውስጥ ቆየች፡፡
ነቃች፡፡
ወዲያው እንደነቃች ያንን የምትወድደውን እና የሚወዳትን ፍቅረኛዋን ለማየት ጠየቀች፡፡ ሰው ሁሉ ከወጣ በኋላ የምትወድደው ሰው መጣ፡፡ በአንድ እጁ ዓይነ ሥውራን የሚይዙትን «ኬን» ይዟል፡፡ ስታየው ደነገጠች፡፡ ስትወድደው የኖረችው ሰው ይህ ባይሆን መረጠች፡፡ ምናለ ሌላ በሆነ ብላም አሰበች፡፡ ግን እርሱው ነው፡፡
ድምጿ ቀዘቀዘ፤ ልቧም አብሮ ቀዘቀዘ፤ ተስፋዋም አብሮ ቀዘቀዘ፡፡
«አሁንስ ትወጅኛለሽ አላት፡፡ መልሱን ለመስጠት ረዥም ሰዓት ወሰደባት፡፡ መልሱ ግን መልስ አልነበረም፡፡ ጥያቄ እንጂ፡፡
«ምናለ አንተ ባትሆን ኖሮ ነበር ያለችው፡፡
«ለምን አላት
«ዓይነ ሥውር መሆንህን አላውቅም ነበር አለችው ከቧሂት ውርጭ ይልቅ በቀዘቀዘ ድምፅ፡፡
«ይኼው አሁን ዐወቅሽ»
«አንተን ማግባት አልችልም» በግብጻውያን ላይ ከወረደው በረዶ ይልቅ እየቀዘቀዘ የሚማታ ቃል ነበር፡፡
«ማየት ስለማልችል? እኔ አንቺ ማየት በማትችይበት ጊዜ ወድጄሽ አልነበረም»
ኅሊናዋ የሚጮኸውን ጩኸት አንደበቷ ማውጣት አቃተው፡፡
ተሰናብቷት ወጣ፡፡
ከብዙ ቀናት በኋላ እነሆ አንድ ፖስታ መጣላት፡፡ አየቺውም፡፡
«ዓይኖችሽ ዓይኖቼ ናቸው፡፡ እኔ ዓይነ ሥውር የሆንኩት አንቺ እንድታዪ ብዬ ነው፡፡ እነዚያ ዓይኖች ከእኔ የተወሰዱ ናቸው፤ ተንከባከቢያቸው፤ የኔ የገና ስጦታዬ የገዛ ዓይኔ ነው» ይላል፡፡
በስንቶቹ ዓይን አይተን እነርሱን ጠላናቸው መሰላችሁ፡፡ ሀገር የዕውቀትን ዓይን ሰጠችን፡፡ በእርሷ ገንዘብ ተማርን፤ የዕውቀትንም ዓይን አገኘን፡፡ ታድያ ዓይናችን ሲበራ አየናትና እንደምንጠብቃት ሆና ልናገኛት አልቻልንም፡፡ የኔን ዓይን እንዳበራሽው ሁሉ ያንቺን ዓይንም ማብራት አለብኝ ብለው መከራ የተቀበሉላት አሉ፡፡
 በሌላም በኩል እንደ ልጅቱ ማየት ሲጀምሩ ሃሳባቸውን የቀየሩ፤ የሸሿት እና የጠሏትም አሉ፡፡ ለካስ ኢትዮጵያ ይህቺ ናት? ለካስ ሀገሬ ብዬ የምኮራባት ይህቺ ናት? ለካስ በታሪክ ስማራት የኖርኩት ኢትዮጵያ ይህቺ ናት? ብለው ተስፋ ቆረጡ፡፡ ዓይኗ ሊበራላት አይችልም ብለው ደመደሙ፡፡ እኛ በበራልን ዓይናችን የራሳችንን እንጀራ እንጋግራለን አንጂ ያንቺን ዓይን እናበራለን ብለን መከራ መቀበል የለብንም ብለው ወሰኑ፡፡
ሕዝብ እና ሀገር ዓይናቸውን አውጥተው ሰጥተዋቸው ባሕር ማዶ ተሻግረው ዕውቀት ሸምተው የመጡ አንዳንድ ወገኖች ዓይን የሰጠቻቸውን ሀገር ማየት ሲጀምሩ ናቋት፡፡ ታሪኳን፣ ባህልዋን፣ እምነቷን፣ ቅርሷን መናቅ እና ማቃለል፤ መስደብ እና መተቸት፤ የማትጠቅም እና የማያልፍላት መሆንዋን መተንተን ልማዳቸው ሆነ፡፡ የኢትዮጵያ የሆነውን ሁሉ መናቅ የመመረቂያ ጽሑፋቸው ሆነ፡፡
አልተቆረቆሩላትም፡፡ እኛ እንድናይ ብለሽ አንቺ ይህንን ሁሉ ተቀብለሻልና እኛም እንድታዪ እናደርግሻለን አላሏትም፡፡ ማወቃቸውን ለቁጭት ሳይሆን ለትችት አደረጉት፡፡ ለማቃናት ሳይሆን ለማናጋት አዋሉት፤
ከማየታችን በፊት ቃል የገባንባቸው ስንት ጉዳዮች ነበሩ፡፡ እንዲህ እና እንዲያ እናደርጋለን ብለን፡፡ ታጋዮች ሆነን በረሃ እያለን፡፡ የከተማውን ሕይወት ከማየታችን፤ በምቾቱ አልጋ ላይ ከመተኛታችን፤ በተሽከርካሪ ወንበር ላይ ከመሽከ ርከራችን፤ በሚዘምሩ መኪኖች ላይ ከመዘመናችን፤ በዘመኑ ፋሽኖች ከመፈ ሸናችን በፊት ለዚህ ሕዝብ፣ ለዚህች ሀገር፣ ለዚህ ወገን ስንት ቃል ገብተን ነበር፡፡
በኋላ ግን ምን ሆነ፤ ማየት ጀመርን፡፡ ሕዝቡ የራሱን ዓይኖች ሰጥቶን ነበር እንድናይ የተደረገው፡፡ እርሱን አላወቅንም፡፡ ማየት ስንጀምር ግን ናቅነው፡፡ ሃሳባችንን ቀየርን፡፡ ላንተ ያልነውን ለእኔ፤ ለሀገሬ ያልነውን ለዘመዴ አደረግነው፡፡ እንደዚህ መሆኑን አላወቅኩም ነበር ማለት ጀመርን፡፡ በየዋሕነት ነው፤ ከተማውን ባለማወቄ ነው፤ በበረሃ ሞራል ነው ቃል የገባሁት አልን፡፡ እናም የዓይኖቻችንን ውለታ ሳንመልስ ቀረን፡፡
ባለውለታን ማዋረድ ሥልጣኔ፤ ዓይን የሰጠን ማቃለል ዘመናዊነት ተደርጎ የሚቆጠርባት ሀገር ሆናለችኮ ኢትዮጵያ፡፡ ከኛ በፊት የነበሩ ሰዎች ሲያስቡ እንዳልኖሩ፤ እንዴው የክፋት ሥራ ብቻ ሲሠሩ እንደ ከረሙ፤ ሆን ብለው ሰው ለመጨ ቆን እና ለመግዛት እንደ ተፈጠሩ፤ ነገር ሁሉ አሁን ከኛ እንደ ተወጠነ መታሰብ ጀምሯልኮ፡፡ የሚገርመው ግን ይህንን የምናይበትን ዓይን ያገኘነው ከእነርሱ ነው፡፡
እሁን በሀገራችን የሚያስፈልግ አንድ ባህል አለ፡፡ የምስጋና ባህል፡፡ ለሀገር፣ ለወገን፣ ለትውልድ፣ ለዓለም፣ ለእኛ ውለታ የዋሉ፤ ታሪካዊ ሥራ የሠሩ፤ ዓይን የሰጡ ባለውለታዎችን እግዚአብሔር ይስጥልን፤ እናመሰግናለን፤ ማየት የቻልነው በእናንተ ዓይኖች ነውና ለዚህ ውለታችሁ ክብር ይስጥልን የምንልበት ብሔራዊ የምስጋና ቀን ያስፈልገናል፡፡
በየአካባቢያችን፤ በየቀበሌያችን፣ በየወረዳችን፣ በየክልላችን፣ በየእምነታችን፣ በየቤተሰባችን፣ በየጓደኝነታችን ዓይን የሰጡንን የምናስብበት፣ ፎቶአቸውን አውጥተን ሰቅለን የምናደንቅበት፤ ለተተኪው ትውልድ ስለ እነርሱ የምንናገርበት፤ በሕይወት ካሉም የምንሸልምበት ቀን ያስፈልጋል፡፡
በሀገር ደረጃም ሥራ ለሠሩ፤ ይህቺ ሀገር ዛሬ ታይ ዘንድ ዓይኖቻቸውን የሰጡ ባለውለታዎች የሚመሰገኑበት፣ ታሪካቸው የሚነገርበት፣ የተረሱት የሚታወሱበት፣ በስማቸው መታሰቢያ የሚደረግበት፣ ሥዕላቸው እና ፎቶአቸው የሚሰቀልበት፤ መጽሐፋቸው እና ፖስተራቸው የሚሸጥበት፤ በሕይወት ካሉም ቀርበው የሚሸለሙበት፤ ተሞክሯቸውን የሚናገሩበት ሀገራዊ የምስጋና በዓል ያስፈልጋል፡፡
ማንነትን የመናቅ፣ የማቃለል እና በማንነት የማፈር ትውልዳዊ ስብራት የሚጠገነው በዚህ መልኩ ይመስለኛል፡፡ ላለፉት ዋጋ ሰጥተን ነው ሌሎች ዋጋ ከፋይ ዜጎች ማፍራት የምንችላው፡፡ እኛ ዓይን የሰጡንን ካመሰገንን፤ እኛም ዓይን ሰጥተናቸው የሚያመሰግኑን ትውልድ መፍጠር እንችላለን፡፡
ምንጊዜም ቢሆን ቀጣዩ ትውልድ ካለፈው በተሻለ ማየቱ የማይቀር ነው፡፡ ያኛው ትውልድ ያላየውን ይኼኛው ትውልድ ያየዋል፡፡ ማለት ግን ይህኛው ትውልድ ያኛውን ትውልድ መናቅ፣ ማቃለል እና መክሰስ አለበት ማለት አይደለም፡፡ ይህኛው ትውልድ ካለፈው በተሻለ እንዲያይ ያደረገው ያኛው ትውልድ ዓይኑን ስለሰጠው ነውና፡፡
ማን ላይ ቆመሽ እግዜርን ታሚያለሽ እንዲሉ በማን ዓይን እያየን ማንን እንንቃለን?

ኮርኮራን መንገድ፣ ቨርጂንያ፣አሜሪካ

ይህ ጽሑፍ በሮዝ መጽሔት ላይ የወጣ ነዉ

39 comments:

 1. wow Dani, it is a gorgeous out look I do not know what to say even words are extremely weak to evoke my appreciation, it tells us to value and give respect for those who gave us their time, knowledge, treasure, wisdom, administration and managerial skill....etc. their historical journey helped us to define our identity and all a shared value as an Ethiopian. black and white it pin point we Ethiopian must learn how to respect, appreciate, recognize, thanksgiving....the role of others in each day of our life, a person cannot be full in his personal life if he/she miss the things mentioned above. I got a good lesson thanks once again dear Dani. But I want to ask you one question while reading this topic it reminds me one issue which I must know that is about organ donation and blood, what is EOTC teaching and faith regarding this theme. Is that possible to engage in such activities as a Christian or there is a ban? God bless you dear!
  Antonio Mulatu
  Mekelle, Ethiopia

  ReplyDelete
 2. 10Q ! Dn. Dani
  እዉነት ነዉ! " እምየ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ ፣ የሞተልሽ ቀርቶ የ ገደለሽ በላ "
  =
  "ባለውለታን ማዋረድ ሥልጣኔ፤ ዓይን የሰጠን ማቃለል ዘመናዊነት ተደርጎ የሚቆጠርባት ሀገር ሆናለችኮ ኢትዮጵያ፡፡ "
  E.B

  ReplyDelete
 3. kalehiwot yasemalin dn. daniel tiru meleekit new yastelalefikilin SHEKARA EJOCHIN NA YAHUN RIES BETELEY LESIM ETHIOPIAWIAN YEHON GELACH NEW BIYE WESJEWALEHU"ከማን ላይ ቆመሽ እግዜርን ታሚያለሽ እንዲሉ በማን ዓይን እያየን ማንን እንንቃለን?"neber negeru gin yih ababal sinyochachin enawkewa yihon?tinantina yeneberu sewochin eyawaredinna zik zik eyaderegin yeminadg meslon kehone enja....yenberew siratachin akahedachin mekebaberachin tilen yebaed temelkachina rasachin lerasachin adinakiwoch hunen endanker gin eyasebin new?eski bazagnitu yekedemut bego sirachew enadinik legna demo leloch yadinkun weyim yinakun....

  ReplyDelete
 4. Dn. Daniel ante asfiteh behager ayehew enji egnako beweledun yeminafir lebetesebochachin kibir yemaniset honenal ene betananashoche rasu azinalehu bitash neger lemadireg enesu min aderegulign yemilu honewal ... andande yihe yenesu wutet yihon elalehu gin lewendimoche yihen enegrachewalehu enesun yemikesubetinim ayin bihon yagegnut kenegna azagnina ruhruh betesebochachew new enegna yihe kehone etachew nege eko bidir yiseferal yenegni lijoch min yemilu yihonu?

  ReplyDelete
 5. ከማን ላይ ቆመሽ እግዜርን ታሚያለሽ እንዲሉ በማን ዓይን እያየን ማንን እንንቃለን?

  ReplyDelete
 6. ''የገና ስጦታ'' የምትለው የ ዳቆን ዳንኤል ፅሁፍ (http://www.danielkibret.com/2011/01/blog-post_11.html#more ) ልብ ላላት አጅግ አስተማሪ ነች። አንድ በትምህርትቤት የማውቀው የ ሰፈሬ ልጅ (ዛሬ ትልቅ ነጋዴ ሆኗል) አንድ ደጋግሞ የምላት አባባል አይምሮዬ ላይ ታንቃችላለች።ነጋ ጠባ ስታገኙት በወሬ መሃል ተጣጥሮ ስለ አትዮጵያ ድሃነት፣ስለ ህዝቡ ችግር፣ወዘተ ለማውራት ሲጣጣር ታገኙታላቺሁ።ሸራተን ሻይ ብትጠቱ አሱ ሸራተን ሲሰራ ስለጎደለው ጥራት አያወራ ማግኘት ልማዱ ነው።አጅግ ሰይጣናዊ የሆነ የ አትዮጵያውያን አና አትዮጵያዊነት ጥላቻ አንደመርፈ ተቸንክሮበት አንዳለ ለማወቅ ሳይንቲስት መሆን አያስፈልግም። መቸም በ አትዮጵያችን ግለሰብ፣ባለስልጣን አልያም ጎረቤት አናዶን ይሆናል። ግን የ አነሱን ሀጥያት በ ሀገር ላይ አና በ ሀገሪቱ ጥቅም ላይ ሁሉ መዝመት ያውም አትዮጵያ ውስጥ ዳዴ ብሎ አድጎ፣ አፈር ፈችቶ፣ ውሃ ተራችቶ፣ተምሮ ተድሮ፣ልጅ ወልዶ፣ሀብት አፍርቶ፣ዛሬም ኢንቨስትመንት ቢሮ አየተመላለሰ ከሚገኝ ሰው ስትሰሙት ''አይ የ አትዮጵያ አምላክ!'' ያስብላችሁአል።ለ አዚህ ሁሉ ዋና ስሩ መሰረቱ ግን አናቱ አትዮጵያ አይኗን አጥፍታ አይን ከሰጠችው በሁአላ መሆኑ ያሳዝናል።
  አስኪ ልብ ብላችሁ አዩ። የ አትዮጵያን ባድራ ሲያይ ንዴት የሚይዘው ሰው ገትሟቺሁ አያውቅም? ግን ለምን ስትሉ ምክንያቱ ዛሬ ጎስቆል ብላ የታየች አናት ፊት ላለመታየት የምትደረግ አጉአጉል በሽታ ነች።
  አሁን አሁንማ ባለ ባንዲራ ጥለት ነጠላ አና ስካርቭ ማረግ ''አጉል አክራሪነት'' አና ''የድሮዎቹን ስርዓቶች ናፋቂነት ነው'' በምትል የማታለያ ''አባባል'' ብዙዎች ልብሳቸውን፣ወዘተ ባንዲራ አንዳይኖረው ስጠነቀቁ መታየት ተጀምሯል።
  ያሳደገችውን ሃገሩን የከዳ አናቴን አና አባቴን አወዳለሁ ቢል የጠራ ውሸት የማይሆንበትን ምክንያት አስኪ አምጡ? አፍሪካ ውስጥ ከ ፳ ሀገሮች በላይ ሰንደቅ አላማቸው አቀማመጡ ይለያይ አንጂ ከ አረንጉአዴ፣ቢቻ ፣ቀይ የሆነው የ ነፃነት ተምሳለዋን አትዮጵያን አይተው መሆኑን ዛሬም በኩራት አየተረቁልን ነው።

  አስኪ የ ዳቆን ዳንኤል ፅሁፍ '' የ ገና ስጦታ'' የምትለዋን ከ ፀሐፊው ብሎግ ላይ ያንቧት (http://www.danielkibret.com/2011/01/blog-post_11.html#more )

  ReplyDelete
 7. Interesting article.

  ReplyDelete
 8. D.Daniel Thank You verrrrrry much,that mean you are the one.God bless you & our country.

  ReplyDelete
 9. ጤና ይስጥልኝ ዳኒ ፤ ምልከታህን ወድጄዋለው፡፡ ሁሌም ከ ዜሮ ካልጀመርን ለሚሉ ግትር እና ሞኝ ሰዎች
  ጥሩ ምክር ይመስለኛል፡፡

  አውሮፓዎቹ አሁን ላሉበት ስልጣኔ መሰረቶቻቸው ከነሱ የቀደመው ትውልድ እንደሆነ
  ያምናሉ፡፡
  እኛ እንዳለመታደል ሆኖ ይሁን አለማወቃችን እንጃ ” ጣልያን በገዛን ይሻል ነበር‘ የሚሉ ገጥመውኛል፡፡
  አያት ቅድመ አያቶቻችን ለዚህች አገር የሞቶት ይህ ትውልድ በነፃነት ይኖራል ብለው ነው ፡፡ ነገር ግን ይህ ትውልድ
  ያኛውን ከመውቀስ ይልቅ እነርሱ(የቀደመውን ትወልድ ማለቴ ነው) በነበራቸው እውቀት እና አቅም የሰሩትን በጎ ነገር
  በማሻሻል ካልሆነም እንዳይበላሽ በመጠበቅ ለመጪው ትውልድ የማስተላለፍ ኃላፊነት አለብን፡፡
  ስህተትም ከነበረ ውጤቱ ላይ ከማተኮር ይልቅ ምክንያቱን መርምሮ ከስህተት መማር ጊዜንም ድካምንም ይቀንሳል
  ፀጋ ከሀገር ቤት

  ReplyDelete
 10. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።ዉድ የዚህ ጡመራ ታዳሚዎች እንዲሁም ዲ.ዳንኤል እንኩዋን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በሰላም አደረሳችሁ።ዳኒ ብዙ ጊዜ የምትፅፋቸዉን ፅሁፎች በተመስጦ ነዉ የማነባቸዉ።የዛሬዉ ፅሁፍህ ደግሞ እኔም ሲከነክነኝ የነበረን ጉዳይ በማንሳቱ እኔም ሀሳቤን ልገልጥ ወደድኩ።የእዉነት ግን አይናችን ሲገለጥ ነዉ እንዴ ሽሽት የሚያምረን?ትንሽ ስንማር፣ትንሽ ሀብት ስናገኝ፣ትንሽ ታዋቂነት ስናገኝ የመጣንበት ጀርባችንና ያለፍንበት መንገድ ያሳፍረናል።ታዲያ ይቺ የፈረደባትን ምስኪን ሀገር ከሰዳቢ ጋር ተደርበን እንሰድባታለን።ግን በእዉነት ሁላችንም ጣታችን ወደሌላዉ ከመቀሰር ይልቅ እኔስ ለሀገሬ ምን አደረኩ?ለወቀሳ ቸኮልኩ እንዴ?ብለን እንጠይቅ ። ለማንኛዉም እግዚያብሄር ልብ ይስጠን።

  ReplyDelete
 11. ይምትጽፈውን ታስተውላለህ በመጀመሪያ የራስህን ዓይን የበራልህን ቦታ እየተቸህና እያጥላላህ እንዲት ስለሌሎች ለመናገር የሞራል ብቃት ሊኖርህ ይችላል?

  ReplyDelete
 12. Yedrowen tewlede yemnamsegnebet lebona embete testen.

  ReplyDelete
 13. "የኢትዮጵያ የሆነውን ሁሉ መናቅ የመመረቂያ ጽሑፋቸው ሆነ፡፡"
  I came with 4 of my friends to gerermany for PhD study and am still their.

  As we arrived in Germany our tame of discussion was totaly changed and become about the bad sides of ethiopia. I was realy impressed when I read ur views. We, PhD candidates, were blaming our country and those leaders and even the people. The way things were expressed is seems like a very nice research paper presentation. If the same was done to raise a new constructive ideas, I belive it will change the country

  Any Way
  This is a turning point to change our mind. The change will not come with out a change in mind. The change should begin by building a positive look towards to all those who have contributed for our welbeing of today.

  Thank you

  ReplyDelete
 14. DN DANIEL
  Not even to hate my country, I never take my my mind from my country for seconds, I am dreaming after finishing my study what as I will do for my beloved. I know the road is coursey, but I prefer to pass through it and die... that is it. I hope there are thousands who think like this...

  ReplyDelete
 15. MInew Kebe, I think either you did not understand what Dani said or you can not read beyond the line.

  ReplyDelete
 16. it's very true!!!!!!!!!  God bless you!!!

  ReplyDelete
 17. እጅግ በሚገርም መልኩ ነው የገለፅከው……. መጀመሪያ ሰትዮዋን ነበር የወቀስኩት ዝቅ በዬ ሳነብ እራሴን…..እውነት አለው……እኔከረጅም ግዜ በኋላ ሀገሬ ለመግባት የምናፍቀው ናፍቆት ህይ ነው አይባልም ነበር ግን ስገባ …..የነበረኝ ስሜት እጅግ የሚገርም ነበር ለማየት የጓጓሁትን ያህል …..የጠበኩትን ስሜት ውስጤ አለማግኘቴ ……..አሳዝኖኛል……እርግጥ እውነት አለው ልባችን ከሚያየው ነገር ጋር…ተላምዶ አይን ሲርቅ ልብ ይርቃል እንደሚባል እንዳልኖርንበት እንዳላደግንበት …….ሁሉን ስንረሳ……ከዚያም አልፎ እንደኛ አይናቸው ሊገለጥ የሚጓጉትን ሰዎች ደሞ “ አይናችሁ ባይበራ ይሻላችኋል” እያልን ስናስፈራራቸው……..በጣም ይገርማል .. በውስጤ ላራሴ ብዙ ነገሮችን እንዳስተውል ያደረገኝ ጽሁፍ ነው። ቃለ ህይወት ያሰማልን.

  ReplyDelete
 18. ቃለ ህይወት ያሰማልነ ዳኒ

  ReplyDelete
 19. ላለፉት ዋጋ ሰጥተን ነው ሌሎች ዋጋ ከፋይ ዜጎች ማፍራት የምንችላው፡፡
  yonas

  ReplyDelete
 20. D.Daniel Thank you verrrrrrrrry much,You are the one.God bless You & our country

  ReplyDelete
 21. dani 10q ,10q egezeabeher ye agelgelot zemenehen yarzemeleh

  ReplyDelete
 22. Kebede, What is the meaning of "Moral" for you?

  ReplyDelete
 23. Kebede, are u "WEYANE"? If so accept the truth and make adjestement on ur behalf that all anybody does, it is not about what u call "MORAL" which I do not know how u defin it. Open ur mind and try to learn what is good 4 u, ur family and then Ethiopia.

  Thanks,

  ReplyDelete
  Replies
  1. pls, don't mix politics with ideas presented here. i don't agree with the way you said (Melataw) and Kebede's blaming.
   i really appreciate D/n Danial's presentation which can inspire all of us to love our country.

   Delete
 24. It was awesom!Tnks.I have the same question like my brother can crestian doinate body organs? i need to know pls

  ReplyDelete
 25. ለወደፊቱ ስትጽፍ ምንጭ ጥቀስ በመግቢያህ ላይ የተጠቀምከውን ጽሁፍ "በሚጠሉኝ መሐል የሚወደኝን አገኘሁት" የሚል መጽሐፍ ላይ አንብቤዋለሁ፡፡ በተረፈ በርታ!

  ReplyDelete
 26. Dear Brother,
  I appreciate you explanation.
  It is one of the diseases most of us are infected with.
  May God help us to come out of this illness.
  God bless our country.
  Meseret,

  ReplyDelete
 27. ቃለ ህይወት ያሰማልነ ዳኒ

  ReplyDelete
 28. Great dani u initiet me to love more ethiopha.

  ReplyDelete
 29. It's so nice article that made me to consider deeply and gives me 'the love of my country and our elders mom and dad" and for those warrier that gives our original country with its own religions,belief, nations and nationalities.
  Dani,I think this day is also still celebrated in our country to remember those citizens that makes our country free from other external enemies such as "Italian war".in this day we remember our earliest heros and their work to this country is remembered all over the nations.

  ReplyDelete
 30. I appreciate dani for all things your good view I was changing my mind view, was when reading this views thank you Dani''
  Addisu Hailu

  ReplyDelete
 31. God bless you!!! Great job.

  ReplyDelete
 32. tena yistlin daniel. Mastewaln yemiset article new ye tsafkewu. egziabher yanurlin.

  ReplyDelete
 33. Rejim edime yistilin

  ReplyDelete
 34. "ሕዝብ እና ሀገር ዓይናቸውን አውጥተው ሰጥተዋቸው ባሕር ማዶ ተሻግረው ዕውቀት ሸምተው የመጡ አንዳንድ ወገኖች ዓይን የሰጠቻቸውን ሀገር ማየት ሲጀምሩ ናቋት፡፡ ታሪኳን፣ ባህልዋን፣ እምነቷን፣ ቅርሷን መናቅ እና ማቃለል፤ መስደብ እና መተቸት፤ የማትጠቅም እና የማያልፍላት መሆንዋን መተንተን ልማዳቸው ሆነ፡፡ የኢትዮጵያ የሆነውን ሁሉ መናቅ የመመረቂያ ጽሑፋቸው ሆነ፡"

  ReplyDelete
 35. ዲ/ን እግዚአብሄር ይባርክህ!
  ግን እርሱ ተመልሶ አይመጣም?
  እርሷስ ተጸጽታ አትመለስ ይሆን! ይህንን እናፍቃለሁ።
  እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!

  ReplyDelete
 36. ቱሪዝም በዳዉሮ
  ጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክ

  የዳዉሮ ዞን ከኢትዮጵያ ዉብ ገፅታ ማሳያዎች አንዱ ነዉ፡፡ ዞኑ በደቡብ ክልል የሚገኝ ሲሆን የዞኑ ዋና ከተማ ታርጫ ትባላለች፡፡ ታርጫ ገስጋሽ ነገር ግን በሚሌኒየሙ ከተወለዱ ከተሞች አንዷ ናት፡፡ ከሐዋሳ በ282 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ ደግሞ በሻሸመኔ አድርገዉ በወላይታ ሶዶ የሚጓዙ ከሆነ 455 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ በሌላኛዉ መንገድ በጅማ አርገዉ የሚጓዙ ከሆነ ደግሞ በ479 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚያገኟት ከተማ ስትሆን ከተማዋ በየግዜዉ እያስመዘገበች ባለዉ እድገት ሳቢያም የብዙዎችን ትኩረት ስባለች፡፡

  በደቡብ ከጋሞ ጎፋ በምዕራብ ከኮንታ ልዩ ወረዳ በሰሜን ምዕራብ ከኦሮምያ ክልል በሰሜን እስከ ሰሜን ምስራቅ ከከንባታ ጠንባሮ ዞን በምስራቅ ከወላይታ ዞን ይዋሰናል፡፡ ከሰሜን ምዕራብ እስከ ደቡብ ጫፍ ድረስ በጎጀብና በኦሞ ወንዞች ተፋሰስ የተከበበዉ የዳውሮ ዞን የብዙ እሴቶች ማዕከል እና እንብርት ነዉ፡፡ ከአምስት በላይ በሆኑ ብሄረሰቦች መከበቡ ዳውሮን ልዩ የባህል አምባ ያደርገዋል፡፡
  4403 ስኩዌር ካሬ ኪ.ሜትር የቆዳ ስፋት ያለዉ የዳውሮ ዞን የተሰባጠረ መልከአ-ምድር ያለዉ ሲሆን ወይና ደጋማዉ የአየር ንብረት ሰፊዉን ድርሻ ይይዛል 38 በመቶ ቆላማ እና 21 በመቶው ደጋማ ነዉ፡፡ ከዝቅተኛዉ የኦሞና የዝግና ወንዞች ምድር እስከ ከፍተኛዉ የቱታ በተጫ ወረዳ ከ500-2820 ሜትር ከባህር ወለል በላይ የሚደርስ መልከአ-ምድራዊ አቀማመጥ አለዉ፡፡ በየዓመቱ 2.9 በመቶ እድገት ያሳያል የተባለዉ የዞኑ የህዝብ ብዛት በ2002 ዓ.ም አጠቃላይ የዞኑ ህዝብ ብዛት 539 ሺ በላይ ይሆናል ተብሎ ይገመታል፡፡
  ጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክ
  ከሃያ ዘጠኝ የሚበልጥ አጥቢ የዱር እንስሳትን በዉስጡ የያዘዉ እና ማራኪዉ የጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክ የብዙዎችን ትኩረት እየሳበ መጥቷል፡፡ በደቡብ ክልል ከሚገኙ አምስት ብሄራዊ ፓርኮች አንዱ የሆነዉ የጨበራ ጩርጩራ ብሄራዊ ፓርክ በዳዉሮ ዞን አሰራርና ቶጫ ወረዳዎች የሚገኘዉን ሰፊ ጋሻ መሬት እና አረንጓዴ ዉብ ሰፊ ደን ጨምሮ እስከ ኮንታ ልዩ ወረዳ የሚዘልቀዉን የጨበራ ጩርጩራን ደን ያካተተ ነዉ፡፡

  በፓርኩ ዝርያዉ እየተመናመነ የመጣዉ የአፍሪካ የዝሆን ዝርያን ጨምሮ እንደ ጎሽ ዲፋርሳ ከርከሮ ሳላ እና አጋዘን ያሉ የዱር እንስሳት የሚገኙበት ነዉ፡፡ የጨበራ ጩርጩራ ፓርክ በደን ሽፋኑ ይበልጥ ጎልቶ ስሙ የሚነሳ ፓርክ ነዉ፡፡ በፓርኩ ዉስጥ የሚርመሰመሱት እና እነኚህን ጥቅጥቅ ደኖች የሚያቋርጡ በርካታ ወንዞች ይገኛሉ፡፡ ዝግና የተባለዉ ታላቅ ወንዝ የፓርኩን ክፍል ለሁለት የከፈለ ወንዝ ነዉ፡፡ በፓርኩ ደን ዉስጥ ከአምስት ያላነሱ ሃይቆችም ይገኛሉ፡፡ ጨበራ ጩርጩራ ለአረንጓዴ ቱሪዝም ማሳያ የሚሆን የሃገሪቱ ታላቅ መስኽብ ነዉ፡፡

  የሶሎ ተፈጥሮ ደን

  ቃራዎ ከተማ የሶሎ በጌና ወረዳ ዋና ከተማ ናት፡፡ ከከተማዋ 20 ኪ.ሜ ገደማ ከጋዞ ኮይሻ ቀበሌ ምስራቃዊ ጫፍ ጀምሮ ወደ ሰሜን የተዘረጋ ዉብ ደን ነዉ፡፡የብዙ ብዝሃ ህይወት መጠጊያ የሆነዉ የሶሎ ደን ዝርያቸዉ ብርቅ የሆኑ ልዩ የዛፍ እና የአዕዋፍ ዝርያዎችን የያዘ ነዉ፡፡ እንደ ጥቁር እንጨትና ኮሶ ያሉ ዛፎችም ይገኙበታል፡፡ ይህ ደን ተጠብቀ በስፋት ቢተዋወቅ የብዙ ጎብኚዎችን ቀልብ ይስባል፡፡

  ከሃላላ ካብ (ሃላለ ኬላ) እስከ ካቲ ሁሉቋ

  ከቅርብ ግዜ ወዲህ የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ጭምር እየሳበ የመጣዉ ረጅሙ የንጉስ ሃላላ ድንጋይ ካብ መገኛ ዳዉሮ ዞን ነዉ፡፡ ሃላላ ካብ ከ175 ኪ.ሜትር በላይ ርዝመት ያለዉና አሰራሩ አስገራሚ የሆነዉ ይኽዉ የድንጋይ ካብ ከቀደምት የዳዉሮ ነገስታት መናገሻ ወይም ስርዓተ-መንግስት የሚያከናዉኑበት ካቲ ጋዷ በዋናነት በሎማ ወረዳ ሲገኝ የመንፃት ስርዓት የሚፈፀምበት ዋሻ ሌላዉ የቱሪስት መስኽብ ነዉ፡፡ በዳዉሮ ዞን አስራ አራት የሚደርሱ የተፈጥሮ ዋሻዎች ቢኖሩም ካቲ ሁሉቆ ዋሻ ግን በርካታ ልዩ የሚደርጉት ነገሮች አሉ፡፡ ከስያሜዉ ብንነሳ ካቲ ሁልቆ ማለት የንጉስ የመንፃት ስረዓት የሚፈፀምበት ማለት ነዉ፡፡ ዋሻዉ በሎማ ወረዳ ሸምቢ ቀበሌ ሻሌ በተባለ ልዩ ቦታ የሚገኝ ሲሆን ከዛሬ 242 ዓመት በፊት ከ1757-1782 ዓ.ም ዳዉሮን ሲያስተዳድሩ በነበሩ ንጉስ ሃላላ ዘመን የተሰራ ንጉሱ እራሳቸው ይጠቀሙበት እንደነበር ታሪክ ይናገራል፡፡ የካቲ ሁሉቆ ዋሻ መግቢያና መዉጫ በር ያለዉና የንጉስ ሃላላ ባህላዊ የመንፃት ስነ-ስርዓት ያከናወኑበት ዋሻ በመሆኑ በበለጠ ስሙ ጎልቶ እንዲነሳ አድርጎታል፡፡

  የዋሻዉ የላይኛዉ መግቢያ በር ገደላማ ሆኖ ስፋቱ 29 ሜትር ቁመቱ ደግሞ 12 ሜትር ነዉ፡፡ የታችኛዉ መዉጫ በር ደግሞ ሜዳማ ሆኖ ስፋቱ 46 ሜትር ቁመቱ ደግሞ 21 ሜትር ነዉ፡፡ ዉስጥ ለዉስጥ ስልሳ ዘጠኝ ሜትር ርዝመት ሲኖረዉ ከአንዱ ግድግዳ እስከ ሌላዉ ያለዉ የዉስጥ ስፋት ሀያ ስምንት ሜትር ነዉ፡፡ ከወለሉ እስከጣራዉ ደግሞ 7 ሜትር ርዝመት አለዉ፡፡

  የዳዉሮ ዞን ከአስር የሚበልጡ ፍል ዉሃዎች ፏፏቴዎች ትክል ድንጋዮች የተፈጥሮ ዋሻዎች ጥንታዊ ቤተ መንግስቶችና አበያተ ክርስቲያናት እና ሌሎችም መስኸቦች በሚገባ መልማት እና መተዋወቅ ከቻሉ ለሃገሪቱ ቱሪዝም ልማት ሌላ ተጨማሪ አቅምን መፍጠር ይችላሉ፡፡
  Like us on Facebook: https://www.facebook.com/dawru.tube

  ReplyDelete