Saturday, January 8, 2011

ለቤተ መጻሕፍትዎ

 አንዳፍታ ላውጋችሁ፡ በግል ሕይወቴ ከደረሰውና ካጋጠመኝ

አዘጋጅ ጌታቸው ኃይሌ
የታተመበት ዘመን 2000ዓም
የገጽ ብዛት 327
ስለ ደራሲው
ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ በኢትዮጵያ የጥንት መዛግብት ላይ ጥናት በማድረግ ከሚታወቁ ጥቂት ኢትዮጵያውያን አንዱ ናቸው፡፡ የቤተ ክህነትን ትምህርት ከአባታቸው እና ከሌሎች መምህራን ተምረው፣ በዐፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ዘመናዊ ትምህርትን በቅድስት ሥላሴ ትምህርት ቤት እና በሌሎቹም ተምረው፤ ከዚያም ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ ተምረው ከተመለሱት 1950/እና 60ዎቹ ምሁራን አንዱ ናቸው፡፡
በተለይም ደግሞ በግእዝ ጽሑፎች ላይ ባደረጓቸው ጥናቶች እና ምርምሮች፤ ባሳተሟቸው የጥናት ወረቀቶች እና ባወጧቸው መጻሕፍት ይታወቃሉ፡፡ አንዳንዶች እንዲያውም የኢትዮጵያን የብራና መጻሕፍት የጌታቸው ኃይሌን ያህል የሚያውቃቸው የለም ብለው ደፍረው ይናገራሉ፡፡ እኔም ደጋግሜ ምርምር ወደ ሚያደርጉበት ኮሌጅ ቪል ቅዱስ ዮሐንስ ዩኒቨርሲቲ ስሄድ ከነዚያው የብራና መጻሕፍት ውስጥ ገብተው በዋልድባ እና በማኅበረ ሥላሴ፣ በደብረ ሊባኖስ እና በደብረ ቢዘን፣ በደብረ ዳሞ እና በደብረ ሲና፤ በጣና እና በዝዋይ ገዳማት ውስጥ ሲጓዙ ነው የማገኛቸው፡፡
በፖለቲካዊ አመለካከታቸው፣ በአንዳንድ ቤተ ክርስቲያናዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ባሏቸው አስተያየቶቻቸው የማይደግፏቸው ሰዎች አሉ፡፡ አንዳንዶቹም ይህ ፖለቲካዊ ተሳትፏቸው ለኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸው በዛ ያሉ የምርምር ጽሑፎቻቸውን በአማርኛ ጽፈው እንዳያቀርቡ አድርጓቸዋል ይላሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በብዛት እያቀረቡልን ያሉትን መጻሕፍት ከሃያ ዓመት በፊት ጀምረውልን ቢሆን ኖሮ ከእርሳቸው አንድ ትልቅ ኢትዮጵያዊ ቤተ መጻሕፍት እናተርፍ ነበር ብለው የሚቆጩም አሉ፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የእርሳቸው የፖለቲካ ተሳትፎ የሚደገፍ ነው የሚሏቸውም አሉ፡፡ አብዛኞቹ ምሁራን ከራቁበት የፖለቲካ ሱታፌ ውስጥ ገብተው የመሰላቸውን ሃሳብ መሰንዘራቸውና ባመኑበት መንገድ አስተዋጽዖ ማድረጋቸው ሊመሰገኑበት የሚገባ ጎን ነው በማለት ይከራከሩላቸዋል፡፡
አንዳፍታ ላውጋችሁ
ጌታቸው ኃይሌ ግልጽነት በተሞላበት መንገድ የሕይወት ጉዟቸውን ያወጉናል፡፡ ከወላጆቻቸው የትውልድ ቦታ ኩሎ ኮንታ እስከ ሸንኮራ፣ ከአዲስ አበባ እስከ አሜሪካ ይደርሳል ትረካቸው፡፡ የአባታቸውን የሕይወት ታሪክ እና የርሳቸውን የልጅነት ትዝታ እንደ ተረት በሚጣፍጥ አማርኛ  ያቀርቡታል፡፡
በሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ከአባታቸው ጋር ሲኖሩ ያጋጠማቸውን ነገር፣ ከሀገር ወጥተው ግብጽ ውስጥ የነበራቸውን የተማሪነት ሕይወት ሲተርኩት ፊልም ይመስላል፡፡ አልፎ አልፎ የሚያቀርቧቸው የሚያስቁ ገጠመኞች፣ በአበሻ ሕይወት ውስጥ የሚያሳፍሩ የሚመስሉ ገጠመኞችን የሚያቀርቡበት መንገድ የሥነ ጽሑፍ ችሎታቸውን ይመሰክራል፡፡
በተለይም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የነበራቸው ቆይታ ከመምህራኑ ጋር የነበራቸው ግንኙነት የጌታቸው ኃይሌን ጠባይ እና አብሯቸው የዘለቀውን ኃይለኛነት እና ቀጥተኛነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ በተለይም ደርግ ሥልጣን በያዘ በሁለተኛ ዓመቱ መስከረም 23 ቀን 1968 ዓም ሊይዟቸው ከመጡት አካላት ጋር በግቢያቸው ያደረጉት ጦርነት የሆሊውድን የጦርነት ፊልም የምታዩ እንጂ ዛሬ በምሁር ነታቸው የምናው ቃቸውን የጌታቸው ኃይሌን ታሪክ እያነበብን ያለን አይመስለንም፡፡
ይህ ለጉዳታቸውም በውጭ ሀገር ለኖሩበት የቀረው እድሜያቸውም ምክንያት የሆነው የአልበገር ባይነት ጦርነት በኋላም ዘመን በጽሑፎቻቸው ላይ እናስተውለዋለን፡፡
ከእርሳቸው የግል ታሪክ ባሻገር በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ፋይዳ ያላቸውን ሌሎች ነገሮችም በመጽሐፉ ውስጥ እናገኛለን፡፡ የቀድሞው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ /ቤት ሁኔታ፤ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በአቡነ ቴዎፍሎስ ዘመን ግብጽ ውስጥ የነበራት ተሰሚነትና የታሠሩትን ፓትርያርክ ለማስፈታት አቡነ ቴዎፍሎስ ያደረጉትን መንፈሳዊ ወኔ የተሞላ ተግባር፤ ስለ ፊደል ሠራዊት፣ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፣ ፕሮቴ ስታንቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ሲሠሩ ተዋውለውት ስለ ነበረው ውል፤
ስለ አማርኛ አካዳሜ፤ ስለ ኢትዮጵያ የብራና ማይክሮፊልም ድርጅት፤ ስለ 1966 የወሎ ድርቅ እና ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ድርቁን ለማጋለጥ ስላደረጉት ጥረት፤ 1966 ተቋቁሞ ስለነበረው የቤተ ክርስቲያን ኮሚቴ እና ሊቁ አለቃ አያሌው ጠንካራ አቋም፡፡ አቡነ ቴዎፍሎስን ለማውረድ ስለተ ሸረበው ሤራ፤ እና ሌሎችንም በተመለከተ ጌታቸው ኃይሌ የሚያውቁትን እና የነበሩበትን ያካፍሉናል፡፡
ትዝታን የሚቀሰቅሱ ፎቶዎች በየመካከሉ፤ በመጨረሻው ደግሞ መጠቁም /Index/ የተዘጋጀለት ይህ መጽሐፍ ከአንድ ኢትዮጵያዊ ሽማግሌ ምሁር ለትውልድ የቀረበ ትረካ ነው፡፡
ጌታቸው ኃይሌ ይህ ብቻ አይበቃቸውም፡፡ በሚያቀርቡቸው ጉዳዮች ብንስማማም ባንስማማም ሊጽፏቸው የሚገቡ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ብዙ ኢትዮጵያውያን ምሁራን የጥናት ጽሑፎቻቸውን በእንግሊዝኛ ስለሚ ያሳትሙ የገዛ ወገናቸው ሳያውቃቸው ይቀራሉ፡፡ ጌታቸው ኃይሌ አሁን በብርቱ ይህንን ብሂል እየሻሩ ነውና ይቀጥሉ፡፡ በተለይ አሁን የእረፍት ጊዜዎት ስለሆነ ብዙ እንጠብቃለን፡፡
ድግስ ቤት የተጠራ የቆሎ ተማሪ ድግሱ ሲጣፍጠው
ጠላ ከመ ወይን ጣዕሙ
እስኩ ድግሙ ድግሙ
እስኩ ድግሙ
እያለ ያሸበሽባል፡፡ እኛም ለፕሮፌሰር ጌታቸው ይህንኑ እንላለን፡፡
በመጽሐፉ መጀመ ላይ መጽሐፉን ለማግኘት
                           And Afta Lawgachihu
                              p.o.box 113
                            Avon,MN,56310, USA ይጠይቁ ይላል

መልካም ንብባ

13 comments:

 1. ሰላም ዲ.ዳንኤል፡-ማንነታችንን ሳናዉቅ በራሳችን ጠፍተን የምንባዝን ወንድሞችህና እህቶችህን ስለሃገራችን የተከተቡትን እንድናነብ እንደ ድልድይ ሆነህ ለምታስተዋውቀን እንዲሁም አንተም እየ ጦምርህ ለምታስነብበን አምላክ የልፋትህን ዋጋ ይስጥህ። ይህ ማንነታችንን እንድናውቅ፤አስተዉለን እንድንራመድ፤የሞራል ሰው እንድንሆን ይረዳናል። ቢያንስ እኔ ይህ እየተሰማኝ ነው። አሁን በአእምሮየ የሚመላልሰው ጥያቄ፡ ዲ.ዳንኤል ይህን የጡመራ መድረክ ዕለታዊ ማድረግ የሚችለው መቼ ነው? እንዴት ነው ቀጣይነቱን ማስጠበቅ የምንችለው?ከእኔ ምን ይጠበቃል? የመሳሰሉ በርካታ ጥያቄዎች አሉኝ። ለእኔ ይህ መድረክ በሁለንተናዋ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚያስችል አንዳች ሃይል አለው። ያስቸመረህ እግዚአብሔር ይርዳህ።

  ReplyDelete
 2. d/n daniel thanks where it reached that u rase about foundation to preserve/control ethiopian church monastries & abinet memihiran &also students.say some thing about that.

  ReplyDelete
 3. Selam Dn Daniel,

  Please try to see Kolo timihrt bet from modern teaching point of you especially from the concept of transferring knowledge by efficient means like being student centered.

  To your surprise, one of my professor told me that Kolo timhrt bet is the old version of PhD study where one can see a perfect student center concept particularly after completing " Ha, Hu and Abugida"

  I, on my side, do accept my professor's idea however let us think and take a good teaching style from KoLo Tibhirt bet as it has substantial importance with respect to transferring knowledge..... a lot can be said but I am not the right person to do that..

  Best,

  HM,USA

  ReplyDelete
 4. ብስራተ ገብርኤል ከአሜሪካJanuary 9, 2011 at 5:25 PM

  01/09/11
  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።
  እኔ እንኳን መናገር የፈለግሁት ስለ ራሳችን ነው።ዲያቆን ዳንኤል እንደኛ ቤተሰብ ያለው ሲሆን
  እኛን /ቤተ ክርስቲያንን/ለማገልገል በማለት ሳይሰለች የተጠራበት ቦታ ሁሉ በመገኘት የማይ
  ጠገብ ትምህርትና አገልግሎት ሲሰጥ ረዽም ጊዜዎችን አስቆጥሯል።ዛሬ ደግሞ በኢንተርኔት እውቀትን እየቸረን ይገኛል።እኛስ ለሱ ምን ማድረግ ይገባን ይሆን?ከዚህ የበለጠ አገልግሎት
  እንዲያበረክት ምን ማድረግ ይገባናል?እንደ ሌላው ማለት ዛሬ ዘማሪውን ሰባኪውን ብትጠሩት
  በቅድሚያ ምን እንደሚላችሁ በሰማችሁ-ለማንኛውም ፍቃደኛ የሆንን እንደሌላው ባይንፈላሰስም
  እንደ ልቡ ከቦታ ቦታ እንዲዘዋወርና እኛን መንፈሳዊ ምግብ እንዲመግበን ከአቅማችን በታች የሆነችውን ልንረዳው ብንሞክር።ለምሳሌ 200 ሰው $5.00ዶላር ብናዋጣ ለሱ የተወሰነች
  ድጋፍ ልትሆነው ትችላለችና እስቲ መላ እንበል ምህመናን፤እግዚአብሔር አገልግሎቱን ይባርክለት

  ReplyDelete
 5. +++
  Bisrate Gebreal ....your Idea is very appreciated and also what we have to think about it and take an action.Let us be organized and do what we can able to do.So who is going to be first and lead us?????

  Edmonto,Canada

  ReplyDelete
 6. ዘየረር
  ዲ.ን ዳንኤል ሃሳብህና ጥያቄ አመላለስህ እጅግ በጣም ጥሩ ነው፡፡አብዛኞቹ ጥሩ ጎንህን ስለሚጽፉልህ እኔ ይኼንን እዘለዋለሁ፡፡
  • የገና ጾም 43ት ቀናት ሆነው ሳለ አንተ ግን ጋድን ጨምረህ 44ት ማድረግህ ግልጽ አልሆነልኝም(አልገባኝም) ምክንያቱም ጾመ ጋድ ለብቻው የሚቆጠር ከ7ቱ አጽዋማትም አንደኛውና ለብቻው የሚቆጠር ሆኖ ሳለ አነተ ግን አንድ ለይ ነው የቆጠርከው፣የጥምቀትን ጋድንም ብንመለከት ለብቻው ይቆጠራል እንጅ….
  • ያንተን ብሎግ የሚከታተል እንዲያው በጣም ቢበዛ አንድ ሚሊዮን ቢደርስ ነው፡፡ ነገር ግን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ተከታይ በሃገር ውስጥ ብቻ እንኳን ከ45 ሚሊዮን በላይ ነው ታዲያ ለዚህ ሁሉ ሕዝብ ቀኖናን(ሥርዓትን) ማሳወቅ፣ማስተካከል፣መቀየር፣መለወጥ፣ማወጅም የሚችለው ቅዱስ ሲኖዶስ(በስሩ የሚገኙትን የሊቃውንት ጕባኤ በማማከር በተለይም የፍትሐ ነገሥት ሊቃውንትን/ሊቀ ማዕምራን/ደረጃ ላይ ያሉትን) ብቻና ብቻ ነው፡፡ አንተ የጀመርከው ላደናጋሪ ነገሮች ግልጽ ምላሽ መስጠት እጅግ በጣም ጥሩ ቢሆንም ያንተን ብሎግ የሚከታተሉ በቀኖና ላይ የበሰሉ፤ያንተን ብሎግ የማይከታተሉ ከ45ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ደግሞ ጥሬዎች እንዳይሆኑ ስጋቱ ስላለኝ የተኙ አባቶቻችንንና የሊቃውንት ጕባኤ አባላትን ከተኙበት በመቀስቀስ በእነርሱ አማካይነት እንዲታወጅ፣እንዲታወቅ ብታደርግ፣…ምክንያቱም ሎሎችም ብዙ አከራካሪም ነጥቦች ስላሉ(ለምሳሌ የገናን ጾም የጾመም ያልጾመም በጋድ እለት እስከ ፀሐይ መጥለቂያ ድረስ ይፁሙ የሚል ሥርዐት፣በቅዱስ ላሊበላ አቢያተ ክርስቲያናት የሚገኙ ምዕመናን፣እንዲሁም ቅባቶች በአራት ዐመት አንዴ በዘመነ ዮሐንስ ገናን በ28ኛው ቀን ማክበራቸው፣ጾሙን ነቢያት የጾሙት 40 ቀን ሆኖ ሳለ 44 ቀን መጾሙ በ4ት ዐመት አንዴ ግን 43ት ቀናት መጾሙ ፣ጋድ ለብቻው ራሱን ችሎ የሚጾም እንጂ አንድ ላይ አለመቆጠሩ የሚሉ ፣ጋድ አብሮ ከገና ጾም ጋር የሚጾም ነው የሚሉ፣የጾሙ መግቢያ በፍትሐ ነገሥቱ እንደተጻፈውና አሁን እየተጾመ አንደሚገኘው በኅዳር እኩሌታ(ኅዳር 15) እያለ ከጥቂት ዐመታት በፊት ግን ጾሙ ሲገባ የነበረው ኅዳር 16ት(በ4ት ዐመት አንዴ ብቻ ኀዳር 15) ነበር ኋላ በ4ቱም ዘመናት ኅዳር 15ት ጾሙ ይግባ ተብሎ ሲታወጅ ብዙ መምህራን የተቀየረበትን ምክንያት ሲናገሩ ‹‹አድልዑ ለጾም›› የሚለውን ምክንያት እንጅ የፍተሐ ነገሥቱን ብያኔ ብዙም ሲያስተምሩት አልሰማሁምና፣…. ይህን ሁሉ ማስተካከል የሚቻለው የተኙትን ቀስቅሶ በእነርሱ ታውጆ ሁሉም ሕዝብ አውቆት ሲጠቀምበት እንጅ ገማሹ ጥሬ ግማሹ ብስል እንዳይሆን ስጋት አለኝ፨

  ReplyDelete
 7. Why the author did not sell the book online, on Amazon.com?

  ReplyDelete
 8. dani,pr.getachew sile dekike estifanos kalachew amelekaket gar beteyayaze ante min tilaleh?

  ReplyDelete
 9. Dear Deacon Daniel,

  the problem now is the destruction of the Highest Ethiopian Orthodox Church Schools(Abinet Schools) like Bethlehem, Zuramba, Koma Fasiledes, Tekle Aquaquam, Andabet,Washera, Wadla, Gondar City Schools(Laybet, Tachbet, Tirguame...) and others. these are the corner stones of ethiopian orthodox church. but no one is to save them from destrcution. this is the geratest misery i have ever seen. May God Save them. Amen!

  ReplyDelete
 10. ኩሎ ኮንታ??? make it ዳዉሮ
  Edigetu from university of Gondar/UoG/

  ReplyDelete
 11. its cool! keep clam and Like Dawro/ዳዉሮ on Facebook: https://www.facebook.com/dawru.tube

  ReplyDelete