Wednesday, January 5, 2011

ስለ ገና በዓል እና ጾም አንዳንድ ጥያቄዎች

የገና እና የጥምቀት በዓላት ሲደርሱ በምእመናኑ ዘወትር የሚጠየቁ ጥያቄዎች አሉ፡፡ እነዚህን እና መሰል የሕዝቡን የዘወትር ጥያቄዎች መልስ የያዘ የማያዳግም ጥራዝ ማውጣት ከሊቃውንት ጉባኤ የሚጠበቅ ነው፡፡ አብዛኞቹ ጉዳዮች አበው ቀድመው ሥርዓት የሠሩባቸው እና ማብራርያ ብቻ የሚያስፈልጋቸው ናቸውና፡፡ ለዛሬ ሦስቱን ብቻ እንመልስ፡፡

ገና እና ጥምቀት ዓርብ እና ረቡዕ ቢውሉ ይበላባቸዋል ወይስ ይጾማሉ?

ፍትሐ ነገሥት፡ ዳግመኛ በየሳምንቱ ዓርብ እና ረቡዕን መጾም ነው፡፡ በዓለ ሃምሳ፣ የልደት እና የጥምቀት በዓል የተባበሩባቸው ጊዜ ካልሆነ በቀር /ዐንቀጽ 15፣ ቁ566/

የዓርብን እና የረቡዕን ጾም ግን ከልደት፣ከጥምቀት እና ከበዓለ ሃምሳ በቀር ዘወትር ይጹሙ /ዐንቀጽ 15፣ቁ 603/

የገና እና የጥምቀት ቅዳሴ ስንት ሰዓት ነው?

ፍትሐ ነገሥት፡ ስለ ልደት እና ጥምቀት ግን በዚያ ዘመን በኒቂያ የተሰበሰቡ ሊቃውንት ቅዳሴው በሌሊት ይሆን ዘንድ አዘዙ /ዐንቀጽ 15፣ ቁ 595/

ልደት ጋድ አለው?

ፍትሐ ነገሥት፡ የልደት እና የጥምቀት በዓላት ጋድ አላቸው /ዐንቀጽ 15፣ ቁ 566/

     ትንታኔ፡ የገና ጾም 44 ቀናትን ይይዛል፡፡

                   40 ጾመ ነቢያት

                     3 ጾመ አብርሃም ሶርያዊ

                    1 ጋድ

               ድምር 44

የገና ጋድ ከጾሙ ተያይዞ የተቀመጠ እንጂ ለብቻው የተቀመጠ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ሰሙነ ሕማማት ለብቻው የሚቆጠር ጾም ነው፡፡ /ዐንቀጽ 15፣ቁ 565/ ነገር ግን አንድ ሰው ዐቢይ ጾምን ሳይጾም ከርሞ ሕማማትን ለብቻው መጾም አይችልም፡፡ የገናም ጋድ እንዲሁ ነው፡፡

ይህንን ጋድ የልደትን ጾም የማይጾሙ ሰዎች እንዲጾሙት የተሠራ ነውን?

መልስ፡ በቤተ ክርስቲያን ላልተጠመቁ፣ ለማይቆርቡ፣ ንስሐ ለማይገቡ፣ ለማያስቀድሱ፣ ለማይጾሙ ሰዎች ተብሎ የተሠራ ልዩ ሥርዓት የለም፡፡ በፍትሐ ነገሥት ዐንቀጽ 15፣ ቁ 565 እንደተገለጠው ሰባቱ አጽዋማት «ለክርስቲያን ሁሉ» የታዘዙ ናቸው፡፡ ስለዚህም የገናን ጾም ክርስቲያን ሁሉ ጾመው በበዓለ ልደት ሊገድፉ ይገባቸዋል፡፡ ፍትሐ ነገሥት ስለ ገና ጾም ሲገልጥ «መጀመርያው የኅዳር እኩሌታ ፋሲካው የልደት በዓል ነው» ይላል /ዐንቀጽ 15፣ ቁ 568/፡፡ ይህም ከገና ጾም ተሸርፎ የሚጾም ነገር እንደሌለው ያሳያል፡፡

መልካም በዓል

33 comments:

 1. Thank You D/N daniel i read something else on another website that no matter what we should always fast wed and fri except on beale amsa. Now i know the truth from Fitha Negest thank you for explaining this clearly. God bless your service.

  ReplyDelete
 2. Thank you.d/n daniel.
  i was confusing .but i get the right answer. GOD BLESS U MELKAM GENA

  ReplyDelete
 3. Thank you so much for this quick answer. I specially appreciate your citing of the reliable source, i.e., Fitiha Negesit.

  I wish you would have added or asked someone to say a bit about how the Kidasse is celebrated. I mean, when will it start and will finish.

  Thank you so much and may God bless you.

  Orthodox child

  ReplyDelete
 4. ሦስት ጥያቄዎች አሉን

  1. ቅዳሴው በሌሊት ይሁን ካለ ለምን ከእኩለቀን እስከ 9 ሰዓት ሆነ?
  2. የኅዳር እኩሌታ ፋሲካው ይሁን ማለት እንዴት ሆኖ ጾም ይሁን የሚል ትርጉም አመጣ? በዓሉ /ገናው ይሁን የሚል ይመስላል እንጂ
  3. ሐዋሪያት ስላደረጉት የሚል ሳይሆን ግልጽ በሆነ መልኩ ጾመ ነቢያትና ጾመ ሐዋሪያትን ሁሉም ሰው እዲጾመው የሚያዘውን የመጽሐ ክፍል ብትገልጽልን ? እናመሰግናለን

  ReplyDelete
  Replies
  1. Yikirta wondime/ ehte! yemawukatin liglets. 1.kidasew lelit yetebalew le timketina lidet new. 2. mejeriyaw sil yemijemerew be hidar ekuleta hono yemifesekew ( yemiyalkew) be lidet new. 3. በፍትሐ ነገሥት ዐንቀጽ 15፣ ቁ 565 እንደተገለጠው ሰባቱ አጽዋማት «ለክርስቲያን ሁሉ» የታዘዙ ናቸው፡፡
   Tsomenebiyat yeEmebetachin tsom bemebalim yitawekal. Emebetachin Getan yemiyahil endet endihu eweldewalehu sitilbetsom betselot tekeblawalechina.

   Delete
  2. Yikirta wondime/ ehte! yemawukatin liglets. 1.kidasew lelit yetebalew le timketina lidet new. 2. mejeriyaw sil yemijemerew be hidar ekuleta hono yemifesekew ( yemiyalkew) be lidet new. 3. በፍትሐ ነገሥት ዐንቀጽ 15፣ ቁ 565 እንደተገለጠው ሰባቱ አጽዋማት «ለክርስቲያን ሁሉ» የታዘዙ ናቸው፡፡
   Tsomenebiyat yeEmebetachin tsom bemebalim yitawekal. Emebetachin Getan yemiyahil endet endihu eweldewalehu sitilbetsom betselot tekeblawalechina.

   Delete
 5. ዲ/ን ዳንኤል ቃለ ሕይወት ያሰማልን የብዙ ሰው ጥያቄ ነው የመለስከው በየዓመቱ ይሄ ነገር ያከራክራል ለወደፊትም በሰፊው ብታስተምረን ጥሩ ነው፡፡

  ReplyDelete
 6. Gad yemibalewen yetsom kifil betemelekete tiru ena gilts mabraria yesete tsihuf new Egziabeher yebarkih melkam Gena.

  ReplyDelete
 7. Thank you D.Danial bezu giza gera yemiyagabagne neger neberena meles agechebetalew. God bless you.
  Bi/le

  ReplyDelete
 8. ቤዛ አዳም መድኅን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ተገልጦ ወንጌለ ምንግስትን ከሰበከልን ከሁለት ሺህ ኣመታት በኋላ፤ የታደሉት ቅዱሳን ምግብን ምምረጥ ሳይሆን መመገብን በተዉበት ጊዜ፤ ዛሬም አንድን ቀን ስለመብላት እና ስለመጠጣት ለሚከራከሩ ስንፍና የተጫናቸው ምእመናን እንዲሁም የቤተክርስቲያኒቱን ቀኖናዊ ውሳኔ ሳሆን ስንፍናቸውን ለመሸፈን ከራሳቸው አንቅተው የተሳሳተ ትርጓሜ ለሚያስተምሩ ሃሰተኛ መምህራን ሁሉ የሚያሽር መልስ ነው፡፡ (ትንሽ ከማጠሩ በስተቀር)
  ለወንድማችን ጤና ይስጥልን!
  መልካም የልደት በዓል

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ante Egizeabhare bemiawuqew kemayitsomut wegen neh. Betam asimesay. Sewoch yaligebachewun beteyiqu chigiru mindinew? Ante eyaweqih yematitsom mehonihin tawukewaleh. Kiristina bemetabeyina bemasimesel ayihonim. Bayigerimih metsom bichwun waga yelewum. Leterabe yabela, letareze yalebese, yetamemewun yeteyeqe, yetetemawun yateta, yeteserewun yegobegne yemitsedik erisu new. Lelawu hulu ewuket, tsom, wezete.... hulum enegnihin yefirid qene tiyaqewoch endeseru kaladeregu kentu nachew. Tsomehal? Biluy kehadis temirehal? Sebake neberik ? Yemel tiyaqe Yelem befirid ken. Hulum neger legizeaw bicha nachew. Kentu nachawu. Wanaw yetsidik Ken tiyaqe lememeles menor new. Enam sewoch biteyiqu lik kiristinan endemenor sew atasimesil. Lerasih mejemeria.

   Delete
 9. ቃለ ህይወት ያሰማልን
  ….. እኛ ምን ይሻለናል ሁሌ አዲስ እንሆናለን

  ReplyDelete
 10. kale hiwet yasemalen

  ReplyDelete
 11. Egziabher Yistilin
  Dn Daniel, would you please tell me what fitiha negest is and its source? Don't lough at me. Atlanta

  ReplyDelete
 12. 10Q dani telek neger new yenegerken
  GOD BLESS U

  ReplyDelete
 13. please brothers and sisters pray for coptic orthodox followers in egypt

  ReplyDelete
 14. Christians how on earth one read
  *ፍትሐ ነገሥት ስለ ገና ጾም ሲገልጥ «መጀመርያው የኅዳር እኩሌታ ፋሲካው የልደት በዓል ነው» as የኅዳር እኩሌታ ፋሲካው ይሁን ?
  *የገና እና የጥምቀት ቅዳሴ ስንት ሰዓት ነው?
  ፍትሐ ነገሥት፡ ስለ ልደት እና ጥምቀት ግን በዚያ ዘመን በኒቂያ የተሰበሰቡ ሊቃውንት ቅዳሴው በሌሊት ይሆን ዘንድ አዘዙ"as ቅዳሴው በሌሊት ይሁን ካለ ለምን ከእኩለቀን እስከ 9 ሰዓት ሆነ?

  ReplyDelete
 15. ውድ chiristians አንተ ብቻ ሳትሆን መናፍቃኑም ሲያነቡ ወይ ፊድል ወይ ቃላት በመግደፍ ሌላ ነገር ይረዳሉ።
  ለጥያቄህ እራስህ ምላሽ ማግኘት ትችላለህ።
  እንደገና ቀስ ብለህ አንብበው። 1. የልደትንና የጥምቀትን ቅዳሴ ማለት ነው። ሁለቱም የሚቀደሱት በሌት ነዉ።
  2. ፍትሐ ነገሥት ስለ ገና ጾም ሲገልጥ «መጀመርያው የኅዳር እኩሌታ ፋሲካው የልደት በዓል ነው» ይላል /ዐንቀጽ 15፣ ቁ 568/፡፡
  መጀመሪያዉ ህዳር እኩሌታ ፋሲካው/የሚፈሰክበት/ የልደት በዓል የሚገልፀው ስለፆሙ መጀመሪያና ማብቂያ ነው።አንብበው ደግመህ
  3. ፍትሐ ነገስት የቤተክርሲቲያን መፃሀፍ ነው። ከእነ አንቀፁ ጠቀሰልህ።
  እኔም አመሰግናለሁ
  ሙላቱ
  ከሐረር

  ReplyDelete
 16. አንድ ሰው ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል 18 ሰዓት መጾም አለበት ለገና ለፋሲካ ለጥምቀት ቅዳሴው ሌሊት ስለሆነ ከ18 ሰዓት በላይ መጾም የማይችል ሰው ጠዋት 1 ሰዓት ላይ መብላት ይችላል ወይ?
  በመጀመሪአው ጥያቄአችን ላይ ያለው ጥያቄ 1 መልሱን ከጽሑፉ አግኝተናል ለበአላቱ እለት ብቻ ስለሆነ
  ሌሎቹን ግን ዘርዘር ያለ መልስ እንጠብቃለን

  ReplyDelete
 17. Tanxs alot Danni,Do yu know why " betekihinet" is not telling people such a confusing issues???...anyways we expect such a professional clarification from yu young Generation..May the almighty be wiz yu ever!!
  Blessings

  ReplyDelete
 18. ዲ.ዳንኤል በጣም ነው የማመሰግነው እግዚአብሔር ይስጥልኝ:: እኔ በየዓመቱ በልደት ቀን ስለመበላቱ እርግጠኛ ብሆንም የ44 ቀኑን ትንታኔ ግን እንዲህ በግልጽ የተረዳሁት ገና ዛሬ በመሆኑ ከአሁን በኋላ ለሚጠይቁኝ ሁሉ በርግጠኝነት የተሟላ መረጃ መስጠት እችላለሁና ደስ ብሎኛል:: እግዚአብሔር ምስጢሩን ይግለጥልህ! መልካም የገና በዓል ይሁንልህ::

  አክባሪ እህትህ

  ReplyDelete
 19. kale hiwot yasemalin dn.daniel thanks for ur excellent and timed explanation about fasting of ጋድ in fasting Christ-mass.but i would like to ask 1.is there any difference b/n ጋድ and "gehad"
  2.if so which one is applicable for fasting of Christ-mass and/or epiphany
  finaly i"d like to say some thing for chiristians said...ሦስት ጥያቄዎች አሉን for ur question z answer is from z post. for Q#
  1.our GOD(the son of holy father and st marry)was born at night
  2.i think the post is about fasting"መጀመርያው የኅዳር እኩሌታ ፋሲካው የልደት በዓል ነው"
  3.ፍትሐ ነገሥት plus to that read rome13:7

  ReplyDelete
 20. mewdwd what happen for COC of egypt?

  ReplyDelete
 21. Gena doesn't have 'gehad'.Don't confuse people.You like controversy.Refer Abune gorgorious' book.

  ReplyDelete
 22. ጥሩ መልስ ነው። ነገር ግን ለምን አባቶች ጋድን እንደጨመሩበት ብታብራራልን ጥሩ ነው።

  ReplyDelete
 23. it is good answer thanks a lot in the name of God.
  be blessed.
  Hailemeskel from Maputo

  ReplyDelete
 24. D/N Dani it is good updating thanks. but i have another confusion . why our(Ethiopian) calender is different with European? please if you can say something.
  Megersa

  ReplyDelete
 25. በቤተክርሰቲያን ለመነኮሳት፣ለካህናት፣ለምእመናን የተለያዩ ስርዓቶች አሉ።ምእመናን እንደ መነኮሳት ሊኖሩ አይችሉም ስለዚህም በመጽሐፈ መነኮሳት ላይ በመመራት አይኖሩም/መኖር አይችሉም። ካህናትም እነደ ምእመናን ሊኖሩ አይችሉም/አይገባም ስራቸው የእግዚአብሔርን ቃል ማስተማር/ማስፋፋት ብቻ እንደሆኑ ሰዎች/ሕይወታቸው በገዳም ውሱን እንደሆኑ ሰዎች ምእመናን በአለማዊ ስራ የተጠመዱም ተመሳሳይ ክርስቲያናዊ ግዴታ ሊኖራቸው አይችልም።
  የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ለምን ከቅዱስ ስጋውና ክቡር ደሙ ይርቃሉ? ዘወትር ከሚያስቀድሰው ምእመን 5% የማይበልጠው ብቻ ነው ከቅዱስ ቁርባን ተሳታፊ የሚሆነው።ግን ለምን???? በቅዳሴ መግቢያ ላይ ‘በቅዳሴ ግዜ ከምእመናን ወገን ወደቤተክርስቲያን የገባ ሰው ቢኖር ቅዱሳት መጽሐፍትን ሰምቶ የቅዳሴውን ጸሎት እስኪጨርሱ ባይታገሥ ከቁርባንም ባይቀበል ከቤተክርስቲያን ይለይ።የእግዚአብሔርን ሕግ አፍርሷል እና የነፍስና የሥጋ ንጉሥ በሚሆን በሰማያዊ ንጉሥ ፊት መቆምንም አቃሏልና ሐዋርያት በሲኖዶሳቸው እዲህ እዳስተማሩን።’ እንደዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ አስተያየት ብዙ ምእመናን ከቅዱስ ቁርባኑ ተሳታፊ እንዳይሆኑ የሚያደርጋቸው በግልጽ ለመቀበል የሚያስችሉና የማያስችሉ ነገሮችን/ድርጊቶችን ስለማይማሩ ነው እንጂ ቢያንስ 50% ያህሉ መቀበል የሚያስችል ሁኔታ ውስጥ ነው ያሉት። ብዙ ጊዜ ለመነኮሳት የተሰራን ሥርዓት ለምእመናን እንደሆነ አድርጎ ማስተማር፣ምንም እንኳን ክርስቲያን ከኃጢያት ዘወትር መራቅ የተገባው ቢሆንም ወደቁርባን እንዳይቀርብ በቅዳሴ ሰዓት ከሚታወጀው አዋጅ ውጪ እንዲቀርብ ሳይሆን እዲርቅ የሚያደርጉ ስብከት መሰል ጩኸቶች ስለሚተላለፉ፣በመጽሐፍ ያልተጻፉና በቤተክርስቲያን ያልተሰሩ ብዙ የተለምዶ/የመንደር ሕጎች ስለበዙ፣ ወዘተ ምእመናን ከዘላለማዊ ሕይወት ርቀው ይታያሉ።ይህ አስቸኳይ ስራ ሊሰራበት የሚገባው ጉዳይ ነው።የግብጽ ምእመናን 90% ያህሉ ካስቀደሱ በሗላ ይቆርባሉ ከኢትዮጵያ ክርስቲያኖች የተሻለ የእለት ተእለት ምግባርና የእምነት ብቃት ኖሯቸው ነው? ወይስ ምንድነው? ደግሞም እኮ ከሃጥያት የሚያርቅ ጽድቅ የሚያሰራው እርሱ ነው! ስንት ምእመን ሲያስቀድስ ኖሮ ከቅዱስ ቁርባን ሳይቀበል በሞት ተለየ? እንደኔ በቁርባን ሰዓት መምህራን የሚያስተምሩት ትምህት ስለዚህ ጉዳይ ብቻ መሆን አለበት። አንድ ሰው ለመቀበልና ላለመቀበል የሚያስፈልጉት ነገሮችን ብቻ። ይቆየን።

  ReplyDelete
 26. just don't wit en the wises write about ur know how?

  ReplyDelete
 27. ሦስት ጥያቄዎች አሉን

  1. ቅዳሴው በሌሊት ይሁን ካለ ለምን ከእኩለቀን እስከ 9 ሰዓት ሆነ?
  2. የኅዳር እኩሌታ ፋሲካው ይሁን ማለት እንዴት ሆኖ ጾም ይሁን የሚል ትርጉም አመጣ? በዓሉ /ገናው ይሁን የሚል ይመስላል እንጂ
  3. ሐዋሪያት ስላደረጉት የሚል ሳይሆን ግልጽ በሆነ መልኩ ጾመ ነቢያትና ጾመ ሐዋሪያትን ሁሉም ሰው እዲጾመው የሚያዘውን የመጽሐ ክፍል ብትገልጽልን ? እናመሰግናለን

  .....................
  ቃለ ሕይወት ያሰማልን - ዲ/ን ዳኔል..........ጥያቄውን እኔ ልመልስ
  1.ቅዳሴ በሌሊት ይሁን የተባለው የበዓሉ ቅዳሴ (ታኅሳስ 29 ወይም 28) ነው እንጂ መዋዕለ ጾሙማ(43 ቀናት ሰንበታቱን ሳይጭምር)ከሰዓት በኋላ ነው የሚቀደሰው
  2.የኅዳር እኩሌታ የጾሙ መጀመሪያ እንጂ ፋሲካ ነው አልታባለም
  3.ሰለ ስባቱም አጿማት ፍትሐ ነገስት ይደነግጋል። ሐዋርያት ፣ ነቢያት...የጾሙት መባሉ የመጀመሪያ ጿሚዎቹን ለመግለጽ እንጂ ያለ ሕግ የሚታዘዝ/ ይታዘዘ ጾም ይለም - በቤ/ክ.
  ሰላም

  ReplyDelete
 28. ቃለ-ሕይወት ያሰማልን! ስለ ጾሙ ጥሩ ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ሁልጊዜ የሚያከራክር አለ ይሄውም በዘመነ ዮሐንስ ሲሆን ነው፡፡ በዚህ ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ቢሰጥበት ምልካም ነው፡፡ እኔ እንደተረዳሁት ልደት በታህሳስ 28 ይሆናል፡፡ ይሄውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢሱስ ክርስቶስ (ለሥም አጠራሩ ክብር ይግባውና) በእናቱ (በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም) ማኅጸን 9 ወር ከ5 ቀን ቆየ የሚለው ሚስጥር እንዳይዛባ ነው፡፡ ጾሙ 44 ቀን ነው ካልን ደግሞ መጀመሪያው በህዳር 14 ይሆናል ማለት ነው፡፡ ከተሳሳትኩ ልታረም፡፡

  ReplyDelete
 29. ቃለ-ሕይወት ያሰማልን!

  ReplyDelete
 30. እዚህ ጋር አንድ ነገር ልንገርህ ዲያቆን ዳንኤል ፡፡ ፍትሃ ነገስቱ እንደሚለው እንተም ከላይ ያን ማጣቀሻ አድርገህ እንደጠቀስከው በፍትሃ ነገስቱ /ዐንቀጽ 15፣ ቁ 568/ ላይ እንደተጠቀሰው የገና ጾም መጀመርያው የኅዳር እኩሌታ ፋሲካው የልደት በዓል ነው» ይላል፡፡ ይህ ማለት የህዳር ወር እኩሌታ ህዳር 16 ሆኖ ሳለ ህዝበ ክርስትያኑን ህዳር 15 ላይ ገና ጾምን ስለምን የዘመኑ ሹመኞች ነን ባዮች ያስጀምሩታል፡፡ ደሞ ለምን ሲባሉ ፍትሃ ነገሰስቱን ላፋለሱበት አስተምርሆዎቻቸው ሳያፍሩ ሰልስቱ ምእልት በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የወሰኑትን ቀኖናን ያፋለሱበትን በደል ለመሸፋፈን "ለጾም አድሉ" በሚለው ሰነፍ ምክንያታቸው ይዘብታሉ፡፡ እውን አሁን ይህ ሲኖዶስ ከሰልስቱ ምእልት የበለጠ ጽድቅናና ተቀባይነት በልዑል ቅዱስ እግዚአብሔር ፊት ኖሮት ነው? በተዋህዶ ኦርቶዶክስ ሃያማኖታችንስ የምንለው በሰልስቱ ምእት ሃይማኖት እንማናለን አደል? እውነት ሰልስቱ ምእልት የጾም ትርጉሙ ሳይገባቸው ቀርቶ ነው በህዳር እኩሌታ ጾመ ገናን ያዙ ያሉት፡፡ እውነት ያሳዝናል? ጾም ስርአት አለው፡፡ ስርአቱም መከበር አለበት፡፡ ፍትሃነገስቱንም ማንም እየተነሳ እንደመንግስት አዋጅ ማሻሻያ እያለ ማሻሻል አይችልም፡፡ እወቁት፡፡

  ReplyDelete