Tuesday, December 28, 2010

ሻካራ እጆች

የአንድ ኩባንያ ባለቤት ለደርጅቱ ብቁ የሆነ ሥራ አስኪያጅ ለመቅጠር ማስታወቂያ አወጣ፡፡ ላወጣው ማስታወቂያ ባቀረቡት ማስረጃ ተወዳድረው ካለፉት ሦስት ሰዎች መካከል በዕድሜ ትንሽ የሆነውን ለቃለ መጠይቅ ጠራው፡፡
ወጣቱ በተጠራበት ቀን አለባበሱን አሳምሮ መንፈሱንም አንቅቶ ጠበቀ፡፡ የኩባንያው ባለቤት የወጣቱን የትምህርት እና የሥራ ሁኔታ የሚገልጠውን መረጃ አገላብጦ አየው፡፡ የተማረው በሀገሪቱ ውስጥ አንቱ በሚባሉ /ቤቶች ነው፡፡ የመጀመርያ እና ሁለተኛ ዲግሪውን የሠራው እጅግ በጣም ሀብታሞች በሚማሩባቸው ኮሌጆች ውስጥ ነው፡፡ ያገኛቸው ውጤቶች ምርጥ ከሚባሉት ውጤቶች ውስጥ ናቸው፡፡ በየደረጃው ከነበሩ መምህራን እና የትምህርት ባለሞያዎች ሽልማቶችን እና ማበረታቻዎችን አግኝቷል፡፡
የኩባንያው ባለቤት «ይህንን ሁሉ የትምህርት ክፍያ ይከፍልልህ የነበረው አባትህ ነው)» ሲል ጠየቀው፡፡ ልጁም «አይደለም፤ አባቴን በልጅነቴ ነው ያጣሁት» ሲል መለሰለት፡፡ « ይቅርታ፤ ታድያ ስኮላርሺፕ አግኝተህ ነበር)» አለው፡፡
«እስካሁን በትምህርት ጉዞዬ ስኮላርሺፕ የሚባል አላጋጠመኝም» ብሎ ፈገግ አለ፡፡
«መቼም ከዘመዶችህ አንዱ የተሻለ ገቢ ያለው ሰው መሆን አለበት)» አለና የኩባንያው ባለቤትም ፈገግታውን በፈገግታ መለሰለት፡፡
«እኔ ሀብታም ዘመድ የለኝም፤ ኧረ እንዲያውም ዘመድ ራሱ የለኝም» አለው ወጣቱ፡፡
የኩባንያው ባለቤት እየተገረመ «ታድያ ይህንን በመሰሉ /ቤቶች ገብቶ ለመማር እኮ ከፍተኛ ገንዘብ ይጠይቃል፤ ማን እየከፈለልህ ነበር የምትማረው)» ሲል በአግራሞት ጠየቀው፡፡
 «የምትከፍልልኝ እናቴ ነበረች» አለና ወጣቱ በኩራት መለሰ፡፡
«እናትህ ምን ዓይነት ሥራ ነው የምትሠራው)» አለው ባለቤቱ፡፡
 «እናቴ የሰዎችን ልብስ እየሰበሰበች የምታጥብ ሴት ናት» አለው ወጣቱ፡፡
 «ልብስ እያጠበች ነው አንተን ይህንን በመሳሰሉ /ቤቶች ያስተማረችህ)»
«አዎ»
«አንድ ጊዜ እጅህን ለማዬት እችላለሁ» አለው የኩባንያው ባለቤት፡፡ ወጣቱ እጁን ወደ ባለቤቱ ላከው፡፡ እጁ ከኬክ የለሰለሰ ነበረ፡፡
«ለመሆኑ እናትህን በልብስ አጠባው ረድተሃት ታውቃለህ)»
«አላውቅም»
«ለምን)»
«እናቴ እኔ ምንም ሥራ እንድሠራ አትፈልግም፤ እንድማር፣ እንዳጠና እና እንዳልፍ ብቻ ነው የምትፈልገው፤ ስለዚህ ሥራ ሠርቼ አላውቅም»
«በጣም ጥሩ» አለ የኩባንያው ባለቤት «ቃለ መጠይቁን ነገ እንቀጥላለን፤ አሁን ወደ ቤትህ ሂድና አንድ ነገር አድርግ» አለው፡፡
ወጣቱ እየገረመው «ምን)» አለ፡፡
«የእናትህን እጆች እጠብ፤ ከዚያ የሆነውን ነገ ትነግረኛለህ»
በቃለ መጠይቁ የተሻለ ነገር አድርጌያለሁ ብሎ እያሰበ በደስታ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡
ቤቱ ገብቶ እናቱን እጇን ለማጠብ ጠየቃት፡፡ አዲስ ነገር ሆነባትና ጠየቀችው፡፡ እርሱም ዛሬ ያጋጠመውን ነገር አጫወታት፡፡
ውኃ እና ሳሙና አቀረበና የእናቱን እጆች ማጠብ ጀመረ፡፡ የተኮራመቱ፤ የተሰነጣጠቁ፤ የቆሳሰሉ፤ የተጠባበሱ፤ እጆች፡፡ የእርሱን እና የእናቱን እጆች እያስተያየ ማልቀስ ጀመረ፡፡ ከሚያጥብበት ውኃ ይልቅ እርሱ የሚያነባው ዕንባ በለጠ፡፡ እነዚህ እጆች እንዲህ የሆኑት እርሱን ለማስተማር መሆኑን አሰበ፡፡ እነዚህ ጠባሶች የእርሱ ጠባሶች ናቸው፡፡ እነዚህ ቁስሎች የእርሱ ቁስሎች ናቸው፤ እነዚህ እጆች ናቸው ለእርሱ የትምህርት ውጤት መሠረቶቹ፣ እነዚህ እጆች ናቸው እርሱን ለአካዳሚያዊ ውጤት ያበቁት፤ እነዚህ እጆች ናቸው ዛሬ ለቆመበት ታላቅ ደረጃ ያበቁት፡፡
የእናቱን እጆች አጥቦ ሲጨረስ የቀሩትን ልብሶች ሁሉ ከእናቱ ጋር አጠበ፡፡ በዚያች ሌሊት ልጅ ከእናቱ ጋር ለረዥም ሰዓት ሲያወሩ አደሩ፡፡ ነግራው የማታውቀውን ታሪክ ነገረችው፤ ሰምቶት የማያውቀውን ታሪክም ሰማ፡፡
በማግስቱ ወጣቱ ወደ ኩባንያው ባለቤት ዘንድ ሄደ፡፡ የኩባንያው ባለቤት የወጣቱን ዓይኖች ሲያይ የዕንባዎቹን ፈለግ ተመለከተ፡፡ እናም «ትናንት ያደረግከውን እና ያጋጠመህን ልትነግረን ትችላለህ)» ሲል ጠየቀው፡፡
«የእናቴን እጆች አጠብኳቸው፡፡ የእናቴ እጆች እንደዚህ መሆናቸውን አላውቅም ነበር፡፡ ብዙ ነገር ነገረችኝ፤ ልብሶቹንም አብሬያት አጠብኩ» አለው፡፡
«ታድያ ምን ተማርክ)» አለው የኩባንያው ባለቤት፡፡
«ሦስት ነገሮችን ተምሬያለሁ» አለ ወጣቱ፡፡ «መጀመርያ ነገር አድናቆት እና ምስጋናን ተምሬያለሁ፡፡ እናቴ ባትኖር ለእኔም ያንን ሁሉ መከራ ባትቀበል ኖሮ ዛሬ የደረስኩበት ልደርስ አልችልም ነበር፡፡ ስለዚህ እናቴን ምንጊዜም ላመሰግን በሄድኩበት ቦታ ሁሉ ቀድሜ ስሟን ልጠራ፤ ስለ ራሴ ከመናገሬ በፊት ስለ እርሷ ልናገር እንደሚገባ ተረድቻለሁ፡፡ ሁለተኛ ደግሞ እናቴ ያለፈችበትን እውነተኛው ነገር መረዳት የቻልኩት አብሬያት ሆኜ ሥራዋን ስጋራት ነው፡፡ በሱታፌ ካልሆነ በቀር በነቢብ እና በትምህርት ብቻ የአንድን ነገር ርግጠኛ ጠባይ እና ሁኔታ መረዳት አይቻልም፡፡ ሦስተኛ ደግሞ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ መኖር ብቻ ሳይሆን ቤተሰባዊ ትሥሥርም ወሳኝ መሆኑን አይቻለሁ፡፡» አለው
የኩባንያውም ባለቤት «የምፈልገው ሥራ አስኪያጅ አሁን ተገኘ፡፡ ለእርሱ ሕይወት ሌሎች የከፈሉትን ሰማዕትነት የሚረዳ፤ አብሮ በመሥራት ችግሮችን መቅመስን እና መፍታትን የተማረ፤ የሥራ ግቡ ገንዘብ ማግኘት ብቻ ያልሆነ ሰው አሁን ተገኘ» አለና ቀጠረው ይባላል፡፡
ከኛ ሕይወት ጀርባ ስንት ሰዎች አሉ) ለመሆኑ ዋጋ እንሰጣቸዋለን) እናመሰግናቸዋለን) ስማቸውን እንጠራለን) የቀመሱትን መከራ እናውቅላቸዋለን) ችግራቸውን እንሳተፍላቸዋለን)
ፕሬዚዳንት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ሚኒስትር፣ ፓትርያርክ፣ ጳጳስ፣ ሼህ፣ ዑላማ፣ ምሁር፣ ሳይንቲስት፣ ነጋዴ፣ አትሌት፣ አርቲስት፣ ሰባኪ፣ ፓስተር፣ ሐኪም፣ ፖለቲከኛ፣ ገበሬ፣ ጋዜጠኛ፣ ደራሲ፣ ወዘተ፣ ወዘተ ስንሆን ብቻችንን ነበርን) እኛ እዚህ እንድንደርስ ስንቶች ሰማዕትነት ከፈሉ) የስንት ሰዎች ወዝ ፈሰሰ፣ ላብ ተንቆረቆረ፣ ገንዘብ ተከሰከሰ፣ ጨጓራ ተላጠ፣ አንጀት ተቃጠለ)
አምፖሎቹ ዝም ብለው አልበሩም፡፡ አምፖሎቹ እንዲበሩ ያደረገው ጀነሬተሩ ነው፡፡ ጀነሬተሩ ግን አይታይም፡፡ የሚታዩት አምፖሎቹ ናቸው፡፡ ሰዎችም የሚያውቋቸው አምፖሎቹን ነው፡፡ አብዛኛው ሰው አምፖሎቹን ለማሳመር እና በአምፖሎቹ ውበትም ቤቱን ለማሳመር ይጥራል እንጂ ስለ ጀነሬተሩ አይነቅም፡፡ ወሳኙ ግን እርሱ ነው፡፡
ጀነሬተሮቻችን እነማን ናቸው፡) እነዚህ ጀነሬተሮች ናቸው በሃይማኖት ቅዱሳን፣ በሀገር ቀደምት አባቶች፣ በዕውቀት ፋና ወጊዎች፣ በነጻነት አርበኞች፣ እየተባሉ የሚጠሩት፡፡ ያለ እነዚህ እምነት፣ ሀገር፣ ነጻነት፣ ክብር፣ ዕውቀት፣ ጥበብ፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ዕድገት፣ ብልጽግና የሚባሉ ቃላት ውኃ አይቋጥሩም ነበር፡፡
የዚያ ልጅ ችግሩ መማሩ አልነበረም፣ የተሻለ ውጤት ማምጣቱም አይደለም፤ የተማረበትን እና የተሻለ ውጤት ያመጣበትን ምክንያት መርሳቱ ነው፡፡ መማሩን ያውቃል፤ እንዴት ሊማር እንደቻለ ግን አያውቅም፡፡ ለዚያ ውጤት ያበቃው ማጥናቱ፣ ተግቶ መሥራቱ እና የአእምሮ ብቃቱ ብቻ መስሎ ሊታየውም ይችላል፡፡ ግን አይደለም፡፡ እነዚህ ሁሉ መሠረታቸው እናቱ ናት፡፡ እናቱ መሥዋዕትነትን ለመክፈል ዝግጁ ባትሆን ኖሮ እነዚህ ሁሉ ገደል ይገቡ ነበር፡፡ ስንት አእምሮ ያላቸው ሰዎች ደጋፊ በማጣት ጎዳና ላይ ቀርተዋልኮ፤ ስንት ተግተው ማጥናት የሚችሉ ጎበዝ ተማሪዎች አጋዥ በማጣት አቋርጠዋልኮ፡፡
ለቀደምቶቻችን ዋጋ ካልሰጠን ለኛ ዋጋ የሚሰጥ ትውልድ አይፈጠርም፡፡ መነሻችንን ካላወቅን በመድረሻችን አናመሰግንም፡፡ ችግሮችን ካልቀመስን አማራሪዎች እና ጨካኞች እንሆናለን፡፡ ለእኛ ሕይወት ሌሎች ለከፈሉት ngR ዋጋ ካልሰጠን እኛም ለሌሎች ሕይወት ምንም አንከፍልም፡፡ እኛ እንድናድግ ያደረጉትን ከዘነጋን ሌሎች እንዲያድጉ አናደርግም፤ ለኛ ሲባል ቀደምቶቻችን የቀመሱትን መከራ ካላሰብን እንዴትስ ለሌሎች ብለን መከራ እኛ እንቀምሳለን)
ሕይወት እንደ አውሮፓ ዋንጫ ጥሎ ማለፍ አይደለችም፡፡ ይዞ ማለፍ እንጂ፡፡ ምኒሊክን እየናቅን አዲስ አበባ ላይ መኖር፤ ዐፄ ፋሲልን ረስተን ጎንደር ግንብን ማስጎብኘት፤ ንግሥተ ሳባን ዘንግተን አኩስም ጽዮንን ማንገሥ እንዴት ይቻላል) ኃይሌ ገብረ ሥላሴን ያለ አበበ ቢቂላ እንዴት ማሰብ ይቻላል)
እናቱም ይህንን ሁሉ ብታደርግም አንድ የሚቀራት ነገር ግን ነበር፡፡ አልነገረችውም፡፡ የስኬቱን ምሥጢር አልነገረችውም፡፡
ወላጆች ለልጆቻቸው መንገር አለባቸው፡፡ የሚገዛው ኬክ፣ የሚገመጠው ዳቦ፣ የሚጫወቱበት መጫወቻ፣ የሚዝናኑበት ገንዘብ፣ የሚማሩበት ምርጥ /ቤት ክፍያ፣ የሚለብሱት ውድ ልብስ፣ የሚተኙበት ምቹ አልጋ እንዲሁ እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ የመጣ አይደለም፡፡ ደም ተተፍቶበት የተገኘ ነው፡፡ ይህንን ማወቅ አለባቸው፡፡ ቢያንስ ቢያንስ ሌላ ማድረግ ቢያቅታቸው የወላጆቻቸውን ሻካራ እጆች ማጠብ አለባቸው፡፡ ስሜቱን ስሜታቸው፣ ጉዳቱን ጉዳታቸው ማድረግ አለባቸው፡፡ ያለበለዚያ ወላጆ ቻቸውን አያመሰግኑም፣ አያደንቁም፣ አያከብሩም፡፡
የበሉበትን ወጭት መሥበር፣ ያጎረሰን እጅ መንከስ፣ ያሳደገን ትከሻ መርገጥ፣ ያሳደገው ሀገርም፣ ሕዝብም ተቋምም፣ ማኅበርም የለም፡፡ እንድንኖር ሲባል የሞቱ፤ እንድንድን ሲባል የቆሰሉ፤ እንድንማር ሲባል ያልተማሩ፤ እንድንጠግብ ሲባል የተራቡ፤ እንድንለብስ ሲባል የታረዙ፤ እንድንበለጽግ ሲባል የደኸዩ አሉ፡፡ እነዚህ አካላት ከፍ ያለ ክብር እና ምስጋና ይገባቸዋል፡፡ ስማቸው ከስማችን፤ ክብራቸው ከክብራችን መቅደም አለበት፡፡ ሻካራ እጆቻቸው የስኬታችን መሠረቶች ናቸው፡፡ እናጥባቸዋለን፤ እንስማቸዋለን፣ እንኮራባቸዋለንም፡፡
 ያለ እኛ ኖረዋል፡፡ ያለ እነርሱ ግን አንኖርም ነበር፡፡ እነርሱ በእኛ ያበቃሉ፤ እኛ ግን በእነርሱ እንጀምራለን፡፡
 • ሻካራ እጆች ሆይ ከፍ ከፍ በሉ፤ ክብር እና ምስጋና ለእናንተ ይሁን፡፡ እኛ በእናንተ እንኮራለን፤ እናንተም በእኛ ትጠራላችሁ፡፡ ያለ ሻካራ እጆች ለስላሳ እጆች ከየት ይገኙ ነበር፡፡
 • ሸካራ እጆች ሆይ፤ ለሸካራነታችሁ ሰላም እላለሁ እኔን አለስልሶኛልና
 • ጠባሳ እጆች ሆይ፤ ለጠባሳችሁ ሰላም እላለሁ፤ እኔን አስውቦኛልና
 • የቆሰሉ እጆች ሆይ፤ ለቁስላችሁ ሰላም እላለሁ፤ እኔን አድኖኛልና
 • ጎርባጣ እጆች ሆይ፤ ለጎርባጣነታችሁ ሰላም እላለሁ፤ እኔን አክብሮኛልና፡፡
ኮርኮራን መንገድ፣ ቨርጂንያ፣አሜሪካ
ይህ ጽሑፍ በሮዝ መጽሔት ላይ የወጣ ነዉ

50 comments:

 1. dany amesgenehalew yakoyehe men malet new
  ngR

  ReplyDelete
 2. O ! d.dani hoY enegn lemiyarimugn thihufochih selam elalehu erasen enday argewigalina !

  yemigerm eyita new. be rose methihet lay anibibew neber. zarem ende adis liben nekitotal. sile ewinet zare kef yaregun shakara ejoch kibir yigebachewal!
  balewletawochun yemayizenega tiwilid yargen.
  egziabher bezih thega yitebikih berta

  ReplyDelete
 3. 10Q Dani.
  This story memorize my mother. She devoted sooooo many things for me & my sister.By this instance I would like to thanks my mom.
  E.B

  ReplyDelete
 4. በትክክል ለቀደምቶቻችን ዋጋ ካልሰጠን ለኛ ዋጋ የሚሰጥ ትውልድ አይፈጠርም፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear Daniel Kebret God bless you!!! thanks explain my internal feeling briefly . O God please give matusala's age for hem !!!

   Delete
 5. አዎ ይህ መልክት በትምህርት ላለፈውም አሁን በመማር ላይ ላለውም ሰው አሪፍ መልክት ያስተላልፋል .የሰማነውን በልቦናቺን ያኑርልን.አመስግናለሁ !!

  ReplyDelete
 6. Dn Daniel Egziabher Yistilin
  Those of us who grew up in Ethiopia really know and appreciate our mother...well atleast most of us. But i'm worried for the children who are born and raised outside Ethiopia. Would they ever appreciate what their parents went through to raise them? Please God make them grateful!!!! Atlanta

  ReplyDelete
 7. Dn. Dani,

  Yihe tsihufih lik ende Gemena dirama mesetegnina anebebkut. Keziya sile Generator yawerahat neger and sibketih layim silemawukat ezih sitameta endegena meliso wesedegn wede Gemena.

  Yegemena dirama bale werk shilimat yehonut ende ampul kefit yetayun bicha neberu. Neger gin kejerba yalutin generatoroch man yastewulachewu wodaje....

  Egziabher yistilign

  Abaginbar (Florida)

  ReplyDelete
 8. ሻካራ እጆቻቸው የስኬታችን መሠረቶች ናቸው፡፡

  ReplyDelete
 9. selam Dn Daniel

  you make me to cry and go back to remember my family's life how was my mam.

  I don't have a word to say bicha EGZIABHER anten yitebiklin.

  ReplyDelete
 10. DN,Dani Egzeabeher yestlen yemigermu shakara ejoch nachew egnane yasdegu.

  ReplyDelete
 11. DANI,yemegermu shakara ejoch nachew yasadegun betam yemigerm eyta new Dani wede rase endmelketena yalfkubeten gize enday adregne,Dani EGZIABHER bechrnetu yetbkih.

  ReplyDelete
 12. But I have different views , many of the Ethiopian familiies as oppossed to many countries, usually sees thire childrens as an iverstement having a big return..at the end of the day families are subjected not only to be separted but also decide to stop communications...Therefore you should look the matter in othesides cos u r very talented observant.....even you can suggest solutions in this regard bcos most of the time this is related to cultural practices...thank you
  F.D.

  ReplyDelete
 13. እውነት ነው ማማራችን በሻካራ እጆች ነው::አሁን ላለንበት ደረጃ የደረስነው ከፍተኛ መስዋትነትን በመክፈል ከበስተጀርባችን ባሉ መሰረቶች ነው::ልናመሰግናቸው : ልናከብራቸው:ከእኛ በስተጀርባ በመሆን የከፈሉትን መስዋትነት ባገኘነው አጋጣሚ መመስከር ይጠበቅብናለ::
  ዳኒ አንተም ከበስተጀርባችን ያሉትን መሰረቶች እንድናስታውስ ስላረክ እጅግ በጣም ማመስገን እፈልጋል::
  ከዚህ በላይ የምሰራበት ዕድሜ እግዚያበሔር ይስጥልን::

  ReplyDelete
 14. Thank You very much Dani, This message write directly for me.

  ReplyDelete
 15. kale hiwot yasemalign dn daniel beewnetu yene,yehulum hiwot yedase tshuf new biye amnalehu,mamen bicha sayhon Amlake biredagn keengidih etamenbetalehum.
  God bless you and your work!!!

  ReplyDelete
 16. “• ኦ ሸካራ እጆች ሆይ፤ ለሸካራነታችሁ ሰላም እላለሁ እኔን አለስልሶኛልና
  • ኦ ጠባሳ እጆች ሆይ፤ ለጠባሳችሁ ሰላም እላለሁ፤ እኔን አስውቦኛልና
  • ኦ የቆሰሉ እጆች ሆይ፤ ለቁስላችሁ ሰላም እላለሁ፤ እኔን አድኖኛልና
  • ኦ ጎርባጣ እጆች ሆይ፤ ለጎርባጣነታችሁ ሰላም እላለሁ፤ እኔን አክብሮኛልና፡፡”
  መልእክቱ መልካም ቢሆንም አገላለጹ ግን አልተመቸኝም ዳኒ አባባሌን የምትረዳው ይመስለኛል!!
  ዲምፕል

  ReplyDelete
 17. DANI,I think our ancisiters' are doing this.But we don't remind this kind of activity.Just look the spritual persons what are they doing in the monastries .

  ReplyDelete
 18. You made me remember the price my parents paid in their life to keep me alive. Thank you very much!

  ReplyDelete
 19. “በኵሉ ልብከ አክብሮ ለአቡከ
  ወኢትርሳዕ ሕማማ ለእምከ፡፡” ይቤ ሲራክ ወልደ ኢያሱ፡፡

  ይህ የሲራክ አባባል አባቶቻችን መተርጉማኑ

  “አባትኽን በፍጹም ልህ አክብረው፤
  እናትህም ፀንሳ መውለዷን፣ ከወለደችህም በኋላ አጥብታ ማሳደጓን አትርሳ፡፡” ማለት እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡

  እንደኔ እንደኔ ይህን ያባቶቻችንን ትርጓሜም ሆነ የሲራክን ብሂል በሥነሕይወታዊው መንገድ ብቻ ልንረዳው አይገባም፡፡ በሕይወታችን ውስጥ ታፍነን ልቀር እንችልበት የነበረውን ማሕጸነ መከራ አፍኖ እንዳያስቀረን ይልቁንም መከራውን አልፈን እንድንቆም ለማድረግ የጣሩ፣ የደከሙ ሰዎች ሁሉ ከመከራው ተግዳሮት በኋላ ለተወለደው አዲስ ሰብእናችን ወላጆቻችን እንደሆኑ አምናለሁ፡፡ በመሆኑም “ዘያከብር አባሁ ይትፌሳሕ በውሉዱ ወበዕለተ ጸሎቱ ይሰምዖ ፈጣሪሁ” (አባቱን የሚያከብር ልጆቹ ሲያከብሩት አይቶ ደስ ይለዋል፤ በጸለየም ጊዜ ፈጣሪው ፈጥኖ ይሰማዋል፡፡) ተብሎ የተጻፈው በረከት እንዲደርስልንና የሥጋ ልጆቻችን ብቻ ሳይሆኑ በውለታ የምንወልዳቸው ሰዎች የይሁዳ ልጆች እንዳይሆኑብን እኛ የውለታ ወላጆቻችንን ልናከብር ግድ ይላል፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ “አንተ ከሌላው ያላገኘኸው ምን አለ?” እንዲል ከሌላው ያገኘነውን ነገር አክብረን አስገኚውን እናከብር ዘንድ እግዚአብሔር ይሻል፡፡ በተራዛሚው ሳስበው ሲቸግረን ያበደረን ብቻ ሳይሆን ሲደብረን ያዝናናን፣ ስናዝን ያጽናናን፣ ግራ ሲገባን መንገድ ያለከተን ሁሉ ልናከብረው የሚገባ ሻካራ እጅ ነው- ለኛ ሲል አንዳች ነገር አድርጓልና፡፡

  ፈረንጆቹ የሚበልጡንም በዚህ ይመስለኛል- እኛ ሰው ካልሞተና ካልኼደ ምስጋናን አናውቅም፡፡ እነሱ ግን ሁሉን ማለት ባንችል እንኳ ብዙ ልሒቃን ሰዎቻቸውን በቁማቸውም በሞታቸውም ያከብሯቸዋል፤ የሚገባቸውን ክብር ይሰጧቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ ልጆቻቸውን ሰውን ማክበርንና ለሰው የሚበጅ ሥራ በመሥራት በታሪክ ዓምድ ላይ መቀረጽን ያስተምራቸዋል፡፡ እንዲህ እንዲህ እያለ የመከባበር ባህል ይተከላል፡፡ መከባበሩ ደግሞ በእግዚአብሔር ዘንድ በረከትን ያስገኛል፤ ሞገስን ያጎናጽፋል፡፡ “መድኅረ አብ ያጸንዕ አብያተ ውሉድ፤ ወመርገመ እም ይሤሩ መሠረተ፡፡” (የአባት ምርቃት የልጆችን ቤት ያጸናል፤ የእናትም መርገም ሥር መሠረትን ያጠፋል) ተብሎ ተጽፏልና፡፡ ዳግመኛም “ዘያከብር አባሁ ይትኃደግ ሎቱ ኃጢአቱ” ያለውን መተርጉማን “አባት እናቱን ካከበረ ረድኤት አይለየውም፤ ረድኤት ካልተለየውም ኃጢአት አይሠራምና ቢሠራም የሚሠረይለት ስለሆነ አስቀድሞ ያለመሥራቱን ፍዳ ያቀልለታል፡፡” ብለው ያስረዳሉ፡፡

  አንዳንዶቻችን በረከት እንደራቀን የሚሠማን ሰዎች ሕይወታችንን በዚህ በኩል መመርመር የለብንም ትላላችሁ?

  ReplyDelete
 20. nothing to say more, but i waqnt to underline that እንድንኖር ሲባል የሞቱ፤ እንድንድን ሲባል የቆሰሉ፤ እንድንማር ሲባል ያልተማሩ፤ እንድንጠግብ ሲባል የተራቡ፤ እንድንለብስ ሲባል የታረዙ፤ እንድንበለጽግ ሲባል የደኸዩ አሉ፡፡ እነዚህ አካላት ከፍ ያለ ክብር እና ምስጋና ይገባቸዋል፡፡ ስማቸው ከስማችን፤ ክብራቸው ከክብራችን መቅደም አለበት፡፡

  ReplyDelete
 21. I cried when i read this & remind me my parent especially my Dad. I want to thank him but he is gone.I am sad most of the time since i did not appricate enough while he was around.For those people who are luky to have your Generator try to appricate them today before they are gone.

  ReplyDelete
 22. እናቴ ያለፈችበትን እውነተኛው ነገር መረዳት የቻልኩት አብሬያት ሆኜ ሥራዋን ስጋራት ነው..................ሕይወት እንደ አውሮፓ ዋንጫ ጥሎ ማለፍ አይደለችም፡፡ ይዞ ማለፍ እንጂ፡፡

  ReplyDelete
 23. Dn Dani thankyou

  Tsihifu ejig betam astemari niw. possible to say a senario of all Ethiopians. But ydirsanaten yasasafe zeda bezihi milku lelala tsihuf metekem endemichal alawekem niber

  “• ኦ ሸካራ እጆች ሆይ፤ ለሸካራነታችሁ ሰላም እላለሁ እኔን አለስልሶኛልና
  • ኦ ጠባሳ እጆች ሆይ፤ ለጠባሳችሁ ሰላም እላለሁ፤ እኔን አስውቦኛልና
  • ኦ የቆሰሉ እጆች ሆይ፤ ለቁስላችሁ ሰላም እላለሁ፤ እኔን አድኖኛልና
  • ኦ ጎርባጣ እጆች ሆይ፤ ለጎርባጣነታችሁ ሰላም እላለሁ፤ እኔን አክብሮኛልና፡፡”

  or yetetekemikibet yeteleya mikeniyat yinor yihon????

  Egziabher Yetebikehe

  ReplyDelete
 24. Awo Ema yeanchi erizat lenie libis honegn!!!!!!!!
  Ema yeanchi merab le enie tigab honegn !!!!!!!!!!
  Wuletashin Egziabhire yikfelishi

  ReplyDelete
 25. ይህ ጽሁፍ በትክክል እኔን ነው የሚመለከተው፡፡ ትልቁ ወንድሜ ቤታችን ውስጥ የመጀመሪያ ልጅ እንደመሆኑመጠን በጣም ብዙ ሃላፊነቶች እንዲወጣ ይጠበቅበት ነበር፡፡ ከነዚህም ውስጥ አንዱ የእኛን የእህቶቹን እና የወንድሞቹን ሙሉ ወጪ መቻልም ነበረበት፡፡ እርሱ በአመት አንድ አዲስ ልብስ ሳይለብስ እኛን በአል በመጣ ቁጥር አዳዲስ ልብስ ይገዛልናል ት/ት ያስተምረናል……ምን ልበላችሁ በቃ ወንድሜ ከአባትም በላይ ነበር ለኛ…ታዲያ እንዲ ስላችሁ…. አባቴ አቅም ስላጣ እንጂ በሂይወት ሳይኖር ቀርቶ ወይም የሚያገኘው ለልጆቼ ሳይል ቀርቶ አይደለም…..ትልቅ የሚባል ቤተሰብ ስላሰን ነበር፡፡ ታዲያ ይሄ ወንድሜ…ይህን ሁሉ እየሆነልን እኛም ለቁምነገር በቃን አሱም ደስ በሚል ሰርግ አገባ…ግን ምን ዋጋ አለው አግብቶ አመትም ሳይሞላው በጠና ታሞ ይችን አለም ተሰናበተ፡፡ በወቅቱ እኔ ገና ከዩኒቨርሲቲ ተመርቄ ስራም አልያዝኩም ነበር እውነት ለመናገር እሱን ሳስታምም ስራም የምፈልግበት ጊዜም አልነበረኝም…ስራውንም ባገኝ እደማልሰራ አውቅ ነበርና ነው…እሱን ለማን ትቼ…እናቴ እሱን ማስታመም በጣም ይከብዳትል፡፡ ሶስት አመታት ቢያልፉትም እኔ ግን አሁንም እራሴን እወቅሳለሁ..በወቅቱ ስራም ስላልነበረኝ ምንም ነገር ከኪሴ አውጥቼ ገዝቼለት አላውቅም … የተገዛውን ከመስራት ውጪ…በርግጥ ክብሩ ይስፋ ለመድሃኒያለም የጎደለው ነገር አልነበርም… ቢሆንም …. ይህን ሁሉ መስዋእነት ከፍሎ ያሳደገኝንና ያስተማረኝን ወንድሜ….አድርሶኝ ላልደረስኩለት ወንድሜ…በወቅቱ ስራ ይዜ በገንዘብም በጉልበትም ብደግፈው ይሻል ነበር ወይስ….ካጠገቡ ሆኜ ማስታመሜ ያሻለል እላለሁ………. ሁሌም ከአይምሮዬ የይጠፋም….በነገሮች ሁሉ አስታውሰዋለሁ…..ምን አለ እንደው ኢዚ ደረጃ መድረሴን እንካን አንዴ ቢያውቅ እላለሁ…..ለዛ ነው ይሄ ጽሁፍ እኔን ይመለከተኛል የምለው……እግዚአብሔር ነብሱን ይማርልን!!.....ወንድሜ ሆይ…..ስላደረክልን መልካም ነገር ሁሉ እጅግ አድርጌ አመሰግንሃለሁ……እወድሃለሁ፡፡

  ReplyDelete
 26. ይህን ''ሻካራ አጆች '' ካነበብኩ በሁአላ ሁለ በ አይምሮዬ ሲመላለስ የነበረው ጉዳይ ትዝ አለኝ ። የ ፅሁፉ ፀሐፊ ብዙ ነገር ያስታውሰናል።አኔ ግን በ መንገድ ስሄድ ትዝ ስለሚሉኝ አሁን በ ሕይወት ስላሉት ወቅታዊ ''ሸካራ አጆች'' ላውራ።
  ይሄውም በ አትዮጵያ አሁን በ ከተሞች ሆነ በ ሀገራቀፍ ደረጃ ያለውን የመንገድ ግንባታ ላይ ለውጤቱ መሳካት የማይሞገሱ ያልታዩ '' ሻካራ አጆች'' ናቸው።
  መንገዶቹን ቻይና ይስራቸው ጃፓን፣ የ አዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አና የ አትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ቢሮ ውስጥ ያሉ ባለሙያ መሀንዲሶችን ስለ ተከፈተው መንገድ ማብራርያ አንዲሰጡ ከመጠየቅ ባለፈ ስንት ቀን ምሳ አና አራታቸውን አየተዉ፣ አያመሹ ብሎም ከ ቤተሰባቸው ጋር የምአሳልፉበት ጊዜ አያጡ ሲሰሩ አንደዋሉ አና አንደምያድሩ ማን ያይላቸዋል።ምናለበት አነኝህን ፈርጥ የሆኑ ባለሙያዎች በ መገናኛ ብዙሃኞቻችን ልምዳቸውን አንድያካፍሉን፣ውጣ ውረዱን አንድነግሩን ቢያደርጉ መንገዱን መንገድ ለማረግ የነበረውን ውጣ ውረድ ሲያወሩን ውለው ያድሩ ነበር።በ ሚልዮን ለሚቆጠር ብር መታመን አና ማስተዳደር ምን ያሀል ሃገርን መውደድ መሆኑን፣ምን ያህል ታማኝነትን አንደሚጠይቅ ቢያስረዱን። በሁአላም ብሸለሙልን ምናለበት። አነሱስ ስንት ''ሸካራ አጆች'' ይዘው አረስተናቸው መንገዱ ሲያምር አያልን ሌላ ሌላውን ስናሞግስ ይሄው አለን ''ሻካራ አጆችን ''ችላ ማለት በለመደ አይናችን አያየናቸው።

  ReplyDelete
 27. ኦ ሸካራ እጆች ሆይ፤ ለሸካራነታችሁ ሰላም እላለሁ እኔን አለስልሶኛልና!
  ግሩም ምልከታ ነው ዳኒ፡፡ እናቴን በጣም ነው የማከብራት የማደንቃትም፡ የእናቴ እጆች የሚገርም ሻካራ ነበር፡፡ እጆቼ ብቻ ሳይሆኑ እግሮቼም ከእናቴ እጆች ይልሰልሱ ነበር፡፡ ይህን ውለታውእን መቼም ከፍዬ እንደማልጨርሰው ይሰማኛል፡፡

  እግዚአብሔር ይባርክህ

  ReplyDelete
 28. dani yalefikubetin astaweskegn ameseginalew egzihabher wiletachewin yimelisilign enema bemine echilewalew gin eske hiwote fitsame destachewin kedestaye laskedim kal gebichalew

  ReplyDelete
 29. Shakara hands...
  Beatam astemari tehuf newena D.Dani kale hiwot yasemalen.
  God bless you.

  ReplyDelete
 30. ስለዚህ ጽሁፍ ያለኝ አስተያየት
  1.ዝም
  2.ዝም ዝም
  3.ዝም ዝም ጭጭ

  ዳንኤል አመሰግናለሁ።

  ReplyDelete
 31. Oh tnks,i got my self in your paper...
  Erasen aychibetal!!!!

  ReplyDelete
 32. "ለቀደምቶቻችን ዋጋ ካልሰጠን ለኛ ዋጋ የሚሰጥ ትውልድ አይፈጠርም፡፡ መነሻችንን ካላወቅን በመድረሻችን አናመሰግንም፡፡"
  በጣም ትክከል እኔ መምህር ንበርኩ መምህርነትንም እወዳለሁ ግን ባጠቃላይ ለመምህርነት በተለይ ለቀደምት መምህራን የሚሰጠው ክብር በጣም የወረደ መሆኑ እኔን ጨምሮ ብዙ ወጣት መምህራን በስጋት እንድንለቅ ሆነናል፡፡

  ReplyDelete
 33. I ALWAYS READS ROSE MAGAZINE DUE TO D.N DANEIL KIBERT HE RAISE ISSUE SOCIALLY,ECONOMICALLY SPIRITUAL AND IT IS AMAZING SPECIFICALLY GIFT OF X-MASS IT TEACH ME AL OT D.N DANEIL KEEP IT UP

  ReplyDelete
 34. wow Daniel you are the real commentator for every scenario here in the nation. i appreciate you so much

  ReplyDelete
 35. በትክክል ለቀደምቶቻችን ዋጋ ካልሰጠን ለኛ ዋጋ የሚሰጥ ትውልድ አይፈጠርም፡፡

  ReplyDelete
 36. nebyu from bahirdarApril 9, 2011 at 9:45 PM

  thank you for touching me sooooooooooooo much

  ReplyDelete
 37. 10Q D.daniel
  u made me to remember my parents & other guys sacrifice.I decide the article "SHAKARA EJOCH HOY KEF KEF BELU KIBIR NA MISGANA LENANTE YHUN" to be last word of my year book.
  kelemework z PEDA(BDU)

  ReplyDelete
 38. አብዛኛው ሰው አምፖሎቹን ለማሳመር እና በአምፖሎቹ ውበትም ቤቱን ለማሳመር ይጥራል እንጂ ስለ ጀነሬተሩ አይጨነቅም፡፡ ወሳኙ ግን እርሱ ነው፡፡
  መነሻችንን ካላወቅን በመድረሻችን አናመሰግንም፡፡
  አመሰግናለሁ።

  ReplyDelete
 39. thnaks, it is not just story ,it is most of our life

  ReplyDelete
 40. D/Daneil ye abatean shekara ejoche astawesikegne bemiamir meliku slegeletsekew e/r lebelete sira yabertah.

  ReplyDelete
 41. እነርሱ በእኛ ያበቃሉ፤ እኛ ግን በእነርሱ እንጀምራለን፡፡

  ReplyDelete
 42. ሻካራ እጆቻቸው የስኬታችን መሠረቶች ናቸው፡፡

  ReplyDelete
 43. dani betam new mamesegnew egziabher ybarkh

  ReplyDelete
 44. ሻካራ እጆች ሆይ ከፍ ከፍ በሉ፤ ክብር እና ምስጋና ለእናንተ ይሁን፡፡ እኛ በእናንተ እንኮራለን፤ እናንተም በእኛ ትጠራላችሁ፡፡ ያለ ሻካራ እጆች ለስላሳ እጆች ከየት ይገኙ ነበር፡፡
  ኦ ሸካራ እጆች ሆይ፤ ለሸካራነታችሁ ሰላም እላለሁ እኔን አለስልሶኛልና
  ኦ ጠባሳ እጆች ሆይ፤ ለጠባሳችሁ ሰላም እላለሁ፤ እኔን አስውቦኛልና
  ኦ የቆሰሉ እጆች ሆይ፤ ለቁስላችሁ ሰላም እላለሁ፤ እኔን አድኖኛልና
  ኦ ጎርባጣ እጆች ሆይ፤ ለጎርባጣነታችሁ ሰላም እላለሁ፤ እኔን አክብሮኛልና፡፡

  ReplyDelete