Wednesday, December 22, 2010

«እንጀራ ከአልጫ እና ከቀይ ወጥ ጋር ወይንም ሞት»

 የዛሬ ሁለት ዓመት 2000 ዓም ነው፡፡ የገና በዓል አልፎ በቀጣዩ እሑድ፡፡ ከዚህ በፊት አጋጥሞኝ የማያውቅ አንድ አዲስ መርሐ ግብር ላይ ለመሳተፍ ጓጉቻለሁ፡፡ ባለፉት ሃያ ዓመታት በተለያዩ መድረኮች ላይ የዐቅሜን ያህል «አስተምሬያለሁ»፡፡ የዚህኛው ግን ይለያል፡፡
በጠዋቱ ዲያቆን ምንዳየ ብርሃኑ ቤቴ ድረስ መጥቶ በመኪናው ይዞኝ ሄደ፡፡ ስለ መርሐ ግብሩ እየተነጋገርን እና ይህንን ዕድል በማግኘታችን ዕድለኞች መሆናችች እያነሣን በቀለበት መንገድ ከነፍን፡፡ መርሐ ግብሩን ለፈቀዱት የማረሚያ ቤት ባለ ሥልጣናትም ምስጋናችንን አቀረብን፡፡ በማረሚያ ቤቶች ውስጥ እንዲህ ያለ የማናስበው ነገር በመደረጉ እዚህች ሀገር ውስጥ ሳናውቃቸው የተቀየሩ ነገሮች አሉ ማለት ነው) እያልን ነበር የምንጓዘው፡፡
እነሆ ቃሊቲ የሚገኘው ዋናው ማረሚያ ቤት በር ላይ ደረስን፡፡ እንደኛ ለመርሐ ግብሩ የተዘጋጁ እናቶች፣ እኅቶች፣ ወንድሞች አየን፡፡ ራቅ ብለው ደግሞ በወቅቱ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ የነበሩት አቡነ ይስሐቅ ከአንድ አባት ጋር መኪና ውስጥ ተቀምጠዋል፡፡
ለመግባት የሚያስፈልገን ሂደት ተጠናቀቀና በብጹእ አባታችን መሪነት ወደ ውስጥ ገባን፡፡ እኔ በዚህ መልኩ ወደ ማረሚያ ቤት ስገባ የመጀመርያዬ ነበር፡፡ እያንዳንዷን ነገር በንሥር ዓይን ነበር የማያት፡፡ እየሄድኩ ያለሁት በታሪክ መንገድ ላይ ነበርና፡፡
አንድ ትልቅ በር ተከፈተልንና በፖሊሶቹ አስተናጋጅነት ወደ ውስጥ ዘለቀን፡፡ የፖሊሶቹ መስተንግዶ ለመስተንግዶ ተብለው በተቀጠሩት አስተናጋጆች ዘንድ እንኳን የማይገኝ ዓይነት ነበር፡፡
ገባን፡፡
ዙርያውን በተገጠገጠ ቤት የተከበበ ግቢ ነው፡፡ ቤቱ በአራት መዓዝን ሪጋ የተሠራ ነው፡፡ ከቤቱ ፊት ለፊት መሐል ሜዳውን ከብቦ የግቢ አትክልት አስውቦታል፡፡ መካከለኛው ሜዳ ጽድት ብሎ ማረሚያ ቤት መሆኑን ያስረሳል፡፡ በሜዳው መካከል በቆርቆሮ ተሠርቶ በመስተዋት የተዋበ፣ በመጋረጃም የተጋረደ ሥዕል ቤት አለ፡፡
እኛ ስንገባ አንድ አረጋዊ ሰው ሄደው መጋረጃውን ገለጡት፡፡ አቡነ ይስሐቅ እንደ ቆሙ ጸሎት አደረሱ፡፡ ሁሉም በተጠንቀቅ ቆመዋል፡፡ ጸሎቱ እንዳበቃ በተዘጋጀልን መቀመጫ ተቀመጥን፡፡ ምንዳዬ ከአቡነ ይስሐቅ ጎን፣ እኔም ከምንዳዬ ጎን ተቀመጥን፡፡
በዚህ ጊዜ ጋቢ የለበሱ እና መቋሚያ የያዙ አንድ አዛውንት ከጎኔ መጥተው ቁጭ አሉ፡፡ ልቤ አንዳች ነገር ያወቀ መሰለው፡፡ መርሐ ግብሩን ያስተናግድ የነበረውን ልጅ ጠራሁትና በኋላዬ በኩል ጠየቅኩት፡፡ በአዎንታ ራሱን ነቀነቀ፡፡
ክው አልኩ፡፡
ከጎኔ የተቀመጡትን ሰው ለመጀመርያ ጊዜ በአካል ማየቴ ነው፡፡ የሦስተኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ባደግኩበት አካባቢ መጥተው ነበር፡፡ ያኔ ሲመጡ የሙዚቃ አስተማሪያችን የሰልፍ መዝሙር አስጠንተውን በከተማዋ መግቢያ መንገድ ላይ ተሰልፈን ነበር የተቀበ ልናቸው፡፡ እጅግ ብዙ መኪኖች ተከታትለው አልፈው መዝሙራችንን አበቃን፡፡ የተቀበልናቸው ሰው ማንኛው እንደሆኑ ለማየት አልቻልንም ነበር፡፡ ብቻ ስማቸውን በተከ ታታይ ሰምተናል «ጓድ ፍቅረ ሥላሴ ወግደረስ» እየተባለ ሲነገር፡፡
እነሆ አሁን ከጎኔ የተቀመጡት እርሳቸው ናቸው፡፡ በቴሌቭዥን አይቻቸው ዐውቃለሁ፡፡ የዛሬው ግን የተለየ ነበር፡፡ ወተት የመሰለ ነጭ ጋቢ ለብሰው፤ ወዝ የጠገበ መቋሚያ ይዘዋል፡፡ ትንሽ እንደማመም ያደረጋቸው ይመስላል፡፡ በግራ እጃቸው የተደጎሰ ዳዊት አለ፡፡
ምንዳዬ መዝሙር ሲዘምር ፍቅረ ሥላሴም አብረው ይዘምሩ ነበር፡፡ ምን እርሳቸው ብቻ፣ ለገሠ አስፋው፣ ፍሥሐ ደስታ፣ ሌሎቹም ሁሉ እያሸበሸቡ እና እያጨበጨቡ አብረውት ነበር የሚዘምሩት፡፡ እነዚህ ትናንት ሀገሪቱን ሲመሩ የነበሩ፤ በተለየ ታሪካቸው የምናውቃቸው፤ ቀይ ሽብር እና ነጭ ሽብር በዘመናቸው የተፈጸመ፡፡ በብዙ የሀገሪቱ መከራዎች ወስጥ ተጠያቂዎች የሆኑ ሰዎች ዛሬ ስታዩዋቸው እንደዚያ አይደሉም፡፡
የበዓሉ መዓድ ከመቆረሱ በፊት ጸሎት ተደርጎ ነበር፡፡ መጀመርያ ውዳሴ ማርያም ተደገመ፡፡ እኛ አይደለንም የደገምነው፡፡ መቋሚያቸውን ተደግፈው እነዚህ ታላላቅ የደርግ ባለ ሥልጣናት ናቸው የደገሙት፡፡ በአማርኛ እንዳይመስላችሁ፤ በግእዝ፡፡ የኪዳኑን ጸሎት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የሚቀበሉት እነርሱ ነበሩ፡፡
ትምህርት ሲሰጥ ሁሉም ጎንበስ ብለው ያነቡ ነበር፡፡ እኔ ከአሥራ አምስት ደቂቃ በላይ ማስተማር አልቻልኩም፡፡ የእነዚያን ሰዎች ዕንባ አይቼ መቆም አቃተኝ፡፡ ምናልባት እኛ ይቅር አላልናቸው ይሆናል፡፡ እግዚአብሔር ግን መሐሪ ነውና ይቅር እንዳላቸው ርግጠኛ ነበርኩ፡፡ በየቀኑ ኪዳን ይደረሳል፡፡ ዳዊት ይደገማል፡፡ ካህን አላቸው፡፡ ንስሐ ገብተዋል፡፡ ብዙዎቹ ቆራቢዎች ናቸው፡፡ ላለፉት ሃያ ዓመታት በዚህ መልኩ እግዚአብሔርን ተማጽነዋል፡፡ ታድያ እግዚአብሔር ዝም ይላል እንዴ፡፡
ምን ብዬ ላስተምራቸው? ኑሮ ራሱ አስተምሯቸዋል፡፡ ሕይወት ራሱ ለውጧቸዋል፡፡ ድምፁን ከውጭ ሳይሆን ከውስጥ ሰምተውታል፡፡ መስማትም ብቻ ሳይሆን አይተውታል፡፡ በየቀኑ ከእርሱ ጋር ይነጋገራሉ፤ እና ምን ልበላቸው? ኑሮውም፣ ጤናውም፣ ሃሳቡም አስረጅቷቸዋል፡፡
እነሆ ይህ ሥዕል በአእምሮዬ ተቀርጾ ይኖር ስለነበር በየጊዜው እነዚህ ሰዎች ይቅርታ ሊደረግላቸው ይገባል እያልኩ እንድናገር አድርገውኛል፡፡ አሁን ደግሞ መልካም ዜናዎችን እየሰማን ነው፡፡
ይህንን ነገር ላደረጉ የእምነት ተቋማት፤ በጎ ፍቃደኛነቱን ላሳየው መንግሥት፣ ተባባሪ ሆነው ታሪክ እየሠሩ ላሉ ተጎጅዎች የምናመሰግንበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡
እዚህ አሜሪካ ከመጣሁ ጀምሮ በየሬዲዮው፣ ፓልቶኩ፣ ዌብ ሳይቱ፣ ክርክሩ በዚህ ጉዳይ ላይ ሆኗል፡፡ ከሀገር ቤት እየደወሉ የሚከራከሩም ሰዎች አሉ፡፡
አንዳንድ ጊዜ «የምንፈልገውን ሁሉ ካላገኘን ምንም ነገር ባናገኝ ይሻላል» የሚል ዓይነት ክርክር እሰማለሁ፡፡ ዕርቁ እገሌን እና እገሌን የማያካትት ከሆነ፤ እነ እገሌም ካልተጨመሩበት ባይፈቱ ይሻላል ይባላል፡፡ ጎበዝ በዚህ ሁኔታ ስንናገር እግራችንን በተጎጅዎች መሬት ላይ እና በእሥረኞቹ መሬት ላይ ማቆም አለብን፡፡
«ወይ መሬት ላይ ያለ ሰው» አለ፡፡
የእነርሱ በዚሀ ሁኔታ ካለቀ የነ እገሌም ይጨመርበት ይባላል እንጂ «እንጀራ ስትሰጡኝ ከቀይ ወጡ ጋር አልጫ ከሌለው ረሃብ ይሻላል» ይባላል እንዴ፡፡ መጀመርያ ለእንጀራው እና ለቀይ ወጡ እናመስግን፤ ከዚያ ደግሞ አልጫ እንዲጨመር እንጠይቅ፡፡ «እንጀራ ከአልጫ እና ከቀይ ወጥ ጋር ወይንም ሞት» የሚለው መፈክር አሁንም አልለቀቀንም እንዴ፡፡
የይቅርታውን ሂደት የሚያከናውኑትን የሃይማኖት ተቋማትም ማመስገን፤ በርቱ ሥራችሁ የሚያስመሰግን ነው ብሎ ማበረታታት ይገባል፡፡ ባጠፉበት የምንወቅሳቸውን ያህል ሲያለሙ ማመስገን አለብንኮ፡፡ እናንተ ማን ናችሁና ይህንን ታደርጋላችሁ? እያሉ መራቀቅ ከአእምሮ ጅምናስቲክ ያለፈ ዋጋ የለውም፡፡ ማሩ ንጹሕ ነወይ? ከማለት ይልቅ ማሩን ማን አመጣው? እያሉ መወዛገብ በኅሊና ላይ ሌላ እሥር ቤት መክፈት ነው፡፡
በጎን ነገር ማንም ይሥራው፤ ከቻለ ሰይጣንም ይሥራው፤ ከሠራው ይደነቃል፣ ይመሰገናል፤ እነዚህ ተቋማት የሚችሉትን ሁሉ አድርገው እውነት እንደተባለው የይቅርታው ሂደት ከተከናወነ እሥረኞቹ ብቻ ሳይሆኑ እነርሱም ናቸው ከስንፍና የሚፈቱት እና ልናግዛቸውም፣ ልናደንቃቸውም ግድ ይለናል፡፡
መንግሥትም ቢሆን ሊመሰገን ይገባዋል፡፡ ይህንን ታሪክ በይቅርታ እና በዕርቅ ለመዝጋት በጎ ፈቃድ ካሳየ እሰዬው ነው፡፡ አጠፋ ሲባል ባገኘነው መንገድ ሁሉ ለመውቀስ የምንተጋ ሰዎች ሲያለማ ደግሞ ለማመስገን መሽቀዳደም አለብን፡፡
ግማሽ ብርጭቆ ውኃ የያዘውን ብርጭቆ ከየት በኩል ነው ማየት ያለብን? ለመሆኑ ብርጭቆው ግማሽ ሙሉ ነው ወይስ ግማሽ ጎደሎ?
አንዳንድ ጊዜ ዕንቁላሉን ተከባክቦ፣ ሙቀት ሰጥቶ እና ከድመት ጠብቆ ዶሮ እንዲሆን ከመርዳት ይልቅ «እኔ ዶሮ ነበር የምፈልገው» እያሉ ዕንቁላሉን የመስበር አባዜ ያለብን ይመስላል፡፡ የተገኘውን በጎ ነገር ይዞ፣ እርሱን አጎልብቶ፣ የቀረውን ችግር ለመፍታት ከመጓዝ ይልቅ ያለውንም አጠፋፍቶ በዜሮ መጫወት ምን ይሉታል?
የተጎጅ ቤተሰቦች ይህንን ታሪካዊ ሥራ ለመሥራት ስትነሱ ሕመማችሁን እናውቃለን፤ ጉዳታችሁም ይሰማናል፡፡ ከእኛ ይልቅ ለእናንተ ሁኔታው ከባድ ነው፡፡ ግን እየሠራችሁ ያላችሁት የጀግንነት ሥራ ነውና እናደንቃችኋለን፡፡ በእምነት ጽድቅ፣ በታሪክ ክቡር፣ በባህል ምስጉን የሆነ ሥራ ነውና በርቱ፡፡
የዕርቁን ሂደት የምታከናውኑ የእምነት ተቋማትም ይህንን ነበርና ስንጠብቅባችሁ የኖር ነው ይበልጥ አጠናክራችሁ ቀጥሉ፡፡ መጀመርያ የጀመራችሁትን ለፍጻሜ አድርሱ፡፡ ከዚያ ደግሞ የሚቀራችሁን ትሠራላችሁ፡፡ ከምትሰሙት ይልቅ የምትሠሩት ውጤት ያመጣልና ወደ ኋላ አትበሉ፡፡
መንግሥትም ይህንን ታሪክ ሀገርን በሚያኮራ፤ ወገንን በሚያረካ እና ስማችንን በዓለም ላይ ከፍ በሚያደርግ መልኩ ለመዝጋት ያሳየኸውን በጎ ፈቃድ ለውጤት አብቃው፡፡ ሌሎች መሠራት ያለባቸው፤ መሆን የነበረባቸው ነገሮች ይኖሩ ይሆናል፡፡ አሁን ግን እየሆነ ካለው ነገር እንነሣ፡፡ ምናልባት ይህ ታሪክ በራሱ ታሪክ ከመሆኑም በላይ ለሌላውም ታሪካችን በር የሚከፍት ታሪክ ሊሆን ይችላልና፡፡
የተጀመረው ይሳካ፣ ያልተጀመረውም ይቀጥል፡፡
ሁላችሁም እባካችሁ ክርክሩ ሰኞ ዕለት አልቆ ውዳሴውን ለመስማት አብቁን፡፡

64 comments:

 1. ዲ/ን ዳንኤል በጣም ጥሩ ሃሳብ ነው በቀድሞ ባለስልጣናት የተጎዱ ሰዎች እንዳሉ ይታወቃል ግን ሰው በቁሙ ሆኖ በሃጢያቱ ተጸጽቶ ይቅር በሉኝ ካለ ይቅር ማለት ይገባል፡፡ ስንጸልይ ይቅር በለን እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል እንል የለም ወይ ስለዚህ እባካችሁ ይቅር በሏቸው ያለፈውን ትተን ወደፊት እንመልከት ለቀጣዩ ትውልድ ይቅርታን እና እርቅን እናውርስ፡፡

  ReplyDelete
 2. oh Dany i am eggered to hear the last release of those ex- officials up on appolody of the victim and mercy of the current Gov.
  Let his Mercy and Glory with them. i think let alone those detained officials those rulling officials also learn how they repent about the past.

  ReplyDelete
 3. በእምነት ጽድቅ፣ በታሪክ ክቡር፣ በባህል ምስጉን የሆነ ሥራ ነውና በርቱ፡፡

  ReplyDelete
 4. በእምነት ጽድቅ፣ በታሪክ ክቡር፣ በባህል ምስጉን የሆነ ሥራ ነውና በርቱ፡፡ Beka this is so full. I really appreciate how u do things at the rite time. Egziher yemesgen.

  ReplyDelete
 5. Elelelelelelelelelelel.....
  Love Your Enemy. The hardest commandment to be followed by any human being... is't it all about forgivness? Now we are coming closer and closer to Christianity. Temesgen Geta Hoy.
  Dn. Daniel kale hiwot yasemalin. Atlanta.

  ReplyDelete
 6. “ሕዝብ ቢለማም ቢጠፋም በገዛ እጁ ነው፡፡” ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ


  ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ እውነት ብለዋል፡፡


  እነሆ በሀገራችን ይህ የኔትውልድ ሲሰማው ካደገውና በዓይኑ ካየው የመበላላት፣ የመጠፋፋት፣ የመበቃቀል ታሪክና ትርክት አልፎ ይቅር የመባባል ዘመን ሊወለድ እናት ኢትዮጵያ ምጥ ላይ ትመስላለች፡፡ ከልጅ ኢያሱ ጀምረን እስከ ራሳችን ዘመን ድረስ የሰማነው፣ ያየነው፣ የኖርንበት ታሪክ ተቀይሮ ማየትን እጅግ እንናፍቃለን፡፡
  እግዚአብሔር አምላክ ይህን ዕድል ተጠቅመንበት በደልን ከልብ አምኖ ይቅርታ የመጠየቅና ከልብ ይቅር የማለት ታሪክን በሕይወታችን እንድናይ ሊያደርግ ፈቃዱ ይመስላል፡፡ ይህን ዕድል የመጠቀምና ለትውልድ የሚተርፍ ይቅር የመባባል ታሪክን በወርቃማ ቀለም መጻፍና ባህሉንም በፖለቲካችን ባህል ማዳበር አልያም የመበቃቀል ታሪካችንን የሙጥኝ እንዳልን መሞት መብታችን ነው፡፡ ወይም በገብረ ሕይወት አገላለጽ “በገዛ እጃችን” ነው፡፡


  እርግጥ ነው በደልን ስንመለከት በዳይን ብቻ ሳይሆን ተበዳይንም ማሰብ ግድ ነው፡፡ ነገር ግን ራሳችንን በማመጻደቅ ሊሆን የሚገባ አይመስለኝም፡፡


  ይቅር ለማለትም፣ ይቅርታን ለማግኘትም፣ ይቅርታን ለማሰጠትም፣ ይቅርታን ለማየትም፣ “የሚያስተራርቁ ብጹአን ናቸው፤ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና፡፡” ያለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ይርዳን፡፡


  ጸልዩ!

  ReplyDelete
 7. How many of us do we think will get the life of repentance at the eleventh hour? When I read this article, I cried. I cried thinking how merciful God is, I cried for myself, my sin and trespasses. Dear Holy God, please give me a broken spirit as you gave it to those of your children, so that I can weep about my sin and trespasses. Please dear God pour your mercy upon me. Amen

  ReplyDelete
 8. May God forgive us all!!

  ReplyDelete
 9. i was also crying when i read this Dani. I am not part of any of them. But it really is touchy. እግዚአብሔር ይቅር ያለውን ማን ይከሰዋል?????? All please let us develop positive thinking about everything so that we all can grow together in everything.

  Tks dani
  Hiwot

  ReplyDelete
 10. Dn,Daniel enem bezena semche betam des beloghnal EMBETE techmerebet.

  ReplyDelete
 11. +++ Ejeg yetwedkh wendmachn QHY yeh telk melkt new! E/abher bawek huulachnm kederg balseltanoch tegodtenale wendmun kezam nebertun yalata man ale? neger gen enquans tesestw yekerna bayhon enquan Yikerta lenaderg ged new. Kebekela men enaterfalen tweldn kemgudat besteker men enaterfalen? wegenoch leyikerta lebona esti entselye adera adera eshi belo esum Amlakachn yesman!Melkamun zena yaseman +++ Ketoronto akabari betseboch

  ReplyDelete
 12. yigermal, lederesebet yiqirta madreg tilik kibir endehone yiredal. gin dani yagegnenewin sinadenk ewnetanim mastawes melkam new. be'eihadig yetebedelinis mechie new yiqirta yeminteyeqewina anjetachin yemifetaw? kemir eko libie qusil bilo dimtsachewin enkua yemalsemabet endalihed dihinet new yaseregn.

  ReplyDelete
 13. keep working about ethiopian orthodox church without individual difference.
  don,t hesitate with negative comment of any one.
  elemas yehases teftsamet ako wetinot.
  igziabher yasmer leke fetsameke.
  beynekonet wetinotye tewekfa mesele sehita.

  ReplyDelete
 14. እናቶቼ አባቶቼ እህት ወንድሞቼ የዛ መከራ ዘመን ችግር ቀማሾች ሁሉ እውነት ነው ቃል በማይገልጸው መልኩ ተጎድታችኋል ዛሬ ምንም ብንል የደረሰባችሁን ማቃለል አንችልም ግን አሁን በእስር ላይ ያሉት እድሜ ይፍታህ ቢፈረድባቸው ይሞቱ ይሰቀሉ ቢባል ያጣችሁትን የጎደለባችሁን አይተካውም የሚተካው ቢሆን እስከ አሁን እናንተም ዝም አትሉም ነበር ነገር ግን አሁን እንደ ቃሉ ልትቆሙ እስከ ዛሬ እንዲህ ብላችሁ ፀልዩ ተብሎ መጸሐፍ ቅዱስ እንዳስተማረን የበደሉንን ይቅር እንደምንል ስንል የኖርነውን ቃል እውነት ልታደርጉ የፈተና ቀን ከፍታችሁ ቆሞልና በርትታችሁ ድል አድርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ስጡ እሱ የሚያጽናና መልአክን ይልክላችሁ ዘንድ ታማኝ ነው እናንተም ይቅር ስትሉ ፈጣሪያችን ይቅር ይላችኋል እነሱንም ከልብ ተጸጽተው ከሆነ ይቅር ይላቸዋል ካልሆነም እንደ ቃሉ ይፈርድባቸዋል ወገኖቼ ካጣችሁት ከተጎዳችሁትም በላይ በነብሳችሁም አትጎዱ እግዚአብሔር ይርዳችሁ በርቱ የይቅርታ
  እጃችሁን ዘርጉ

  ከአቡዳቢ

  ReplyDelete
 15. በእምነት ጽድቅ፣ በታሪክ ክቡር፣ በባህል ምስጉን የሆነ ሥራ ነውና በርቱ፡፡

  ReplyDelete
 16. ሰዎቹ እስር ቤት ቢኖሩ እኛ የምናገኘው ጥቅም ምንድን ነው ?
  የሞቱት ዘመዶቻችንስ ተመልሰው ይመጡ ይመስል ! በቀል የእኔ ነው ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር
  ለሞቱት ዘመዶቻችን ነፍስ ይማርልን ፤እኛ ደግሞ ይቅርታ ለጠየቁት ይቅር እንበል በዕለተ ልደት 5500 ዘመን ተለያይተው የነበሩ ሰውና መላዕክት በአንድ ላይ እንደዘመሩ እኛም በአንድ ላይ እናመስግን
  ዳኒ በእስር ቤት ውስጥ በተደጋጋሚ ሄደህ ላገለገልከው አገልግሎትህ ብዙ ትምህርት ወደፊት እንደምትሰጠን ተስፋ እናደርጋለን

  ReplyDelete
 17. ዕንቁላሉን ተከባክቦ፣ ሙቀት ሰጥቶ እና ከድመት ጠብቆ ዶሮ እንዲሆን ከመርዳት ይልቅ «እኔ ዶሮ ነበር የምፈልገው» እያሉ ዕንቁላሉን የመስበር አባዜ ያለብን ይመስላል፡፡ የተገኘውን በጎ ነገር ይዞ፣ እርሱን አጎልብቶ፣ የቀረውን ችግር ለመፍታት ከመጓዝ ይልቅ ያለውንም አጠፋፍቶ በዜሮ መጫወት ምን ይሉታል?

  Sele honew hulu yeEgziabher semu yetemesegene yehun!
  Degenetu Egziabher endesew aydelem.
  sew lerasu endideregilet yemiwedewen lelelawem sidereg mayet liyasdestew yegeba neber.
  Abatochachin yemiyakora sera sertachihual bertu.
  Bemanem hiwot kemefred befit rasachinin esu bota lay askemten eneyew!

  Egziabher yemesgen!
  Dani Egziabher yestelin!

  ReplyDelete
 18. EgziEne yegeber keme fekede ,menu yebe lement geberke kemeze.
  Egziabher yesebah le senay fekadu.

  ReplyDelete
 19. የተጎጅ ቤተሰቦች ይህንን ታሪካዊ ሥራ ለመሥራት ስትነሱ ሕመማችሁን እናውቃለን፤ ጉዳታችሁም ይሰማናል፡፡ ከእኛ ይልቅ ለእናንተ ሁኔታው ከባድ ነው፡፡ ግን እየሠራችሁ ያላችሁት የጀግንነት ሥራ ነውና እናደንቃችኋለን፡፡ በእምነት ጽድቅ፣ በታሪክ ክቡር፣ በባህል ምስጉን የሆነ ሥራ ነውና በርቱ፡፡
  ድንቅ አባባል እግዚአብሔር ይስጥህ።

  ReplyDelete
 20. ጌታ ይርዳን ሁላችንንም፤ እቺ ሀገርንም!

  ReplyDelete
 21. ጌታ ይርዳን ብቻ ሌላ ምን ማለት ይቻላል!

  ReplyDelete
 22. Our brother Dn. Daniel I would like to thank for informing us their situation and for initiating us for forgiveness. I think if God will not forgive them the initiative will not be started I think this is the time. we pass so many holidays for the last 20 year but this issue is not raised the elders of religious institutions were there all this years but no excuse issue for me it is time for Gods doing. Cher were yaseman hulachininim yikir yibelen.

  ReplyDelete
 23. ምንዳዬ መዝሙር ሲዘምር ፍቅረ ሥላሴም አብረው ይዘምሩ ነበር፡፡ ምን እርሳቸው ብቻ፣ ለገሠ አስፋው፣ ፍሥሐ ደስታ፣ ሌሎቹም ሁሉ እያሸበሸቡ እና እያጨበጨቡ አብረውት ነበር የሚዘምሩት::
  ሰዎቹ እስር ቤት ቢኖሩ እኛ የምናገኘው ጥቅም ምንድን ነው ?

  ReplyDelete
 24. እኛ አስተሳሰባችን ለነፍስ ሊሆን ይገባል!! ሞት እንዳለም ልናስብ ይገባል!! ከሞትንም በሁዋላ የምንጠየቀው ባደረግነው ይቅርታና ትዕግስት መሆኑንም ልንዘነጋ አይገባም!!
  በርግጥ ጠቅላይ ሚንሰትር መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት የሰላም አምባሳደር ሆነው እንደነበር ግልፅ ነው (ይቅርታ ከተሳሳትኩ) ይህም በይቅርታ ሊጠናከር ይገባል!! ስለዚህ ተጎጂዎች ይቅርታን ታገኙ ዘንድ ይቅር በሉ!! ለዚህም እግዚአብሔር ይርዳን!!

  ReplyDelete
 25. ሰላም ዲ. ዳንኤል። እጅግ አስገራሚ የሆነ መልዕክት ነው። በእነዚህ ሰዎች ላይ ቂም አርግዠ እኖራለሁ። ሁልግዜም ውስጤ የሚነግረኝ የበቀል እርምጃየን እንዴት መፈጸም እንዳለብኝ ነበር። በእነሱ የተሳሳተ እርምጃ አባቴን አጥቼ አሁን በሕይወት ከሌለችው አያቴ ጋር እንዳድግ ሁኛለሁ። በአካል የማላውቀውን የአባቴን ፎቶ ግራፍ ታቅፌ ሁሌ ልቤ በንዴት ይንቦገቦጋል። በተለይ ከአያቴ የሰማሁትን በወቅቱ የነበረውን ድርጊት ሳስታውስ አንዳች ነገር ውስጤን ይነዝረዋል።አኒህን ሰዎች በአእምሮየ የሳልኩዋቸው በትዕቢት በተነፋ ስብዕናቸው ነው። አንተ አሁን ባቀረብኸው መልኩ አንድ ቀንም አስቤአቸው አላዉቅም። እውነት ወደ ፈጣሪ እንዲህ ከተመለሱና በደላቸውን አስበው በንስሃ ውስጥ ካሉ ይቅር ብያቸዋለሁ።እጅግ በጣም ገርሞኛል። ማን ያዉቃል በተግባር የተማሩትን የሕሊና ጸጸት ከአንደበታቸው እንሰማ ይሆናል። በተሳሳተ አመለካከት በውስጤ ይዤባቸው በነበረውን ቂም አምላኬም እኔን ይቅር እንዲለኝ እለምነዋለሁ። አንተንም ይህን የመሰለ መረጃ በመስጠትህ አምላካችን ሰማያዊ ዋጋ ይስጥህ። እኛ ከማናውቀው እሱ በልዩ ጥበቡ ከሚያውቀው ፈተና ይጠብቅህ።

  አንድ ማሳሰቢያ፡- የእኛን ጉዳት መጠቀሚያ እያደረጋችሁ ለሌላ ትርፍ ለሌለው ገበያ የምትሮጡ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ቆም ብላችሁ እንድታስቡበት በፈጣሪ ስም እለምናችሁአለሁ። በሰው ቁስል እንጨት ሲሰዱ---- እንዳይሆን።

  ReplyDelete
 26. የማይበላ እንዳያስበላ ያብላላDecember 23, 2010 at 1:18 PM

  "በእምነት ጽድቅ፣ በታሪክ ክቡር፣ በባህል ምስጉን የሆነ ሥራ ነው"

  ልብን የሚያረካ አገላለጽ ነው፡፡

  እግዚአብሔር ይስጥልን !

  ReplyDelete
 27. I really appreciate what is going on

  ReplyDelete
 28. የተፈጸመው በደል ከባድና ከሕሊና የማይጠፋ ነው ነገር ግን እነርሱም በስልጣን ዘመናቸው ፈጣሪ ያለ የማይመስላቸው ባለስልጣናት ወቅቱ ደርሶ እነርሱም ለዘመናት በእሰር ሆነው እግዚአብሄር መኖሩን ተረድተው በሰሩት በደል ተጸጽተው ይቅረታ መጠየቃቸው አግባብ ስለሆነ የተበደልን ሰዎች በሙሉ ይቅር ልንላቸው ይገባል ይቅር ላላችሁ ይቅር በሉ ይላልና ቃሉ፡፡

  ReplyDelete
 29. እግዚአብሄር ይርዳህ አሜን!
  ግን ወደ ፖለቲካዋ አትጠጋ እባክህ እባክህ ። ለአንተም ለእኛም አትሆንም።
  ስለዚህ ተጠጥቀቅ

  ReplyDelete
 30. ዳኒ ወላድ እንደ አንተ አይነቱን ሺህ ትውለድ! አንተ ንጹሕ ቅን የአባቶቻችን ሐበሾች ልጅ ነህ!
  አሁን ያለው ሐበሻ ግን የመበላላትና የመጠፋፋት ታሪኩን ቀይሮ የይቅርታና የፍቅር ሕዝብ ለመባል ይህ አጋጣሚ መልካም ነው:: በዚህ እንኳ ስማችን በበጎ ይነሳ እንጂ …?!

  ReplyDelete
 31. በእርግጥ ጥU ሥራ ነው ሁላችንም የጉዳቱ ሠላባዎች ነን፡፡ ግን እግዚአብሔር እንደ ሥራቸው ይስጣቸው ማለት ከበድ ነው ፡፡ በኣጠቃላይ ህይወታቸው በግፍ ያለፈ ወገንቻችን ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን እያልኩ እነርሱንም ይቅር እንበላቸው እላለሁ፡፡

  ReplyDelete
 32. በእርግጥ ጥU ሥራ ነው ሁላችንም የጉዳቱ ሠላባዎች ነን፡፡ ግን እግዚአብሔር እንደ ሥራቸው ይስጣቸው ማለት ከበድ ነው ፡፡ በኣጠቃላይ ህይወታቸው በግፍ ያለፈ ወገንቻችን ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን እያልኩ እነርሱንም ይቅር እንበላቸው እላለሁ፡፡

  ReplyDelete
 33. EGZIABHER EYETEBALE YALEW NEGER HULU KEFITSAMEW YADRISEW.KEZA BEHALA BE ETHIOPIA ADDIS TARIK TESERA MALET NEW.BE EDIMEYE YIHN MAYET METADEL NEW

  ReplyDelete
 34. በእርግጥ ጥU ሥራ ነው ሁላችንም የጉዳቱ ሠላባዎች ነን፡፡ ግን እግዚአብሔር እንደ ሥራቸው ይስጣቸው ማለት ከበድ ነው ፡፡ በኣጠቃላይ ህይወታቸው በግፍ ያለፈ ወገንቻችን ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን እያልኩ እነርሱንም ይቅር እንበላቸው እላለሁ፡፡

  ReplyDelete
 35. Ere Gud New
  Dn. Daniel, are you telling me that all those derg cadres were singing and really worshiping God in prison? Temesgen. I was thinking of one cadre who was our neighbor and had a son. His wife refused to take him to church for baptism because she was afraid of her husband finding out abou it...because all cadres were not allowed to worship God. My mother begged her avery single day until the child died of a simple fever befor he turns six months. Geta hoy thank you for your forgiveness.

  ReplyDelete
 36. ewenetem ere GUD NEW those DERGS we know them not alone they believe in GOD they were not behave like pure human being they were cruel and killers
  some are talking a lot but LEKEBARIW AREDDUT ENDE,IBBALEW NEW

  ReplyDelete
 37. +++

  20 ዓመት ተሰቃይተዋል:: ከዚህ በላይ ንስሃ አለ? የለም::

  ስለዚህ ቢፈቱ እና ከህብረተሰቡ ጋር በሰላም ቢቀላቀሉ ጥሩ ነዉ::

  ReplyDelete
 38. ዲ.ዳንኤል ርቀት የማይወስነው የትምህርት አሰጣጥ መንገድ መጀመርህ መልካም ጅማሬ ነው:: ፍጻሜውን እግዚአብሔር ያሳምር አንተንም በቸርነቱ ይጠብቅህ :: ተክለዮሐንስ ከጣልያን ብሬሺያ

  ReplyDelete
 39. i was also crying when i read z article it was so touchy! tnx Dani. YeDAWIT AMLAK YERDAN.

  ReplyDelete
 40. I really appreciate all what you posted here. forgiveness should be our symbol!
  we are ETHIOPIANS who have unique and beautiful things. so we have to keep our beauty by giving our forgiveness for everyone!

  GOD BLESS ETHIOPIA!

  ReplyDelete
 41. ዳኒ ይሄን ጽሁፍ አንብቤ እስከምጨርስ በእንባ ሲቃ ውስጥ ነበርኩ ለውጥ ከመጣ ጀምሮ ከላይ ከዋናው ጀምሮ እስከታች ባለስልጣናት ድረስ ምን አለ ንስሃ ዛሬ እንኴን ቢገቡ እያልኩ እመኝ ነበር ዛሬ እኔን ደካማውን ይህን ለመስማት ስላበቃኝ አምላኴን አመሰገንኩት እነሱ ከእስር እንኳን ባይፈቱ ነፍሳቸው ተፈታለችና።ብዙ የበደሉ ሰዎች እኮ ለቅድስና የበቁ አሉ ለምሳሌ መድህን አለምን በጦር የወጋው፤እዲሁም ለሞት አሳልፎ የሰጠው እረ ምኑ ተነግሮ ያልቃል ስንክሳሩ ሁሉ ብዙ ትነግረናል።መቼም አንተም እድለኛነህ በዚያ በመገኘትህ።

  ReplyDelete
 42. “ምንዳዬ መዝሙር ሲዘምር ፍቅረ ሥላሴም አብረው ይዘምሩ ነበር፡፡ ምን እርሳቸው ብቻ፣ ለገሠ አስፋው፣ ፍሥሐ ደስታ፣ ሌሎቹም ሁሉ እያሸበሸቡ እና እያጨበጨቡ አብረውት ነበር የሚዘምሩት፡፡ ….ትምህርት ሲሰጥ ሁሉም ጎንበስ ብለው ያነቡ ነበር፡፡ ምናልባት እኛ ይቅር አላልናቸው ይሆናል፡፡ እግዚአብሔር ግን መሐሪ ነውና ይቅር እንዳላቸው ርግጠኛ ነበርኩ፡፡ በየቀኑ ኪዳን ይደረሳል፡፡ ዳዊት ይደገማል፡፡ ካህን አላቸው፡፡ ንስሐ ገብተዋል፡፡ ብዙዎቹ ቆራቢዎች ናቸው፡፡ ላለፉት ሃያ ዓመታት በዚህ መልኩ እግዚአብሔርን ተማጽነዋል፡፡ ታድያ እግዚአብሔር ዝም ይላል እንዴ፡፡ ምን ብዬ ላስተምራቸው? ኑሮ ራሱ አስተምሯቸዋል፡፡ ....ሕይወት ራሱ ለውጧቸዋል፡፡ ድምፁን ከውጭ ሳይሆን ከውስጥ ሰምተውታል፡፡ መስማትም ብቻ ሳይሆን አይተውታል፡፡ በየቀኑ ከእርሱ ጋር ይነጋገራሉ፤ እና ምን ልበላቸው? ኑሮውም፣ ጤናውም፣ ሃሳቡም አስረጅቷቸዋል፡፡….«የምንፈልገውን ሁሉ ካላገኘን ምንም ነገር ባናገኝ ይሻላል» የሚል ዓይነት ክርክር እሰማለሁ፡፡…..የተጀመረው ይሳካ፣ ያልተጀመረውም ይቀጥል፡፡” ግሩም ትምህርት፡፡
  ዳኒ እነዚህ ሰዎች ምን ያህል ጨካኝ እና ጨፍጫፊ እንደነበሩ ተጎጅ ብቻ ሳይሆን እራሳቸውም ያውቁታል ብዬ አምናለሁ ብቻ ለተጎጅ በጣም ከባድ ቢሆንም እንደው ጽንፈኛ ሆኘ “ጽድቅና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም” እንኳን ብዬ ባስብ ይቅርታ ግድ ነው ብሎ ውስጤ ይነግረኛልና እኔ አልሙሳማ ብያለሁ፡፡ ሰው በስራው ተጸጽቶ ንስሀ ከገባ ሁሉም በእግዚአብሔር እጅ ነውና ያለው፡፡

  ReplyDelete
 43. ከልብ ... ከልብ ይቅር እንበላቸው!!

  ReplyDelete
 44. inameseginalen Dn dani. betam des yalegn gin bakoseluat ina basadeduat betekiristian sir kumew nisha mekebelachew new.
  Dingil fitsamewun tasamirilin!!!!

  ReplyDelete
 45. Egeziabehere yehen amet yeereke zemen yadrgelen!

  ReplyDelete
 46. ዲያቆን ዳናኤል ጥሩ ሃሳብ ነው ያቀረብከው ሁሌም ለነገ ላገራችን ጥሩ ነገር ትተን ማለፍ አለብን ልጆቻችንን ስለቂም ስለበደል እየነገርናቸው ማሳደግ የለብንም ይህ ነግር አንድ ቦታ መቆም አለበት መስዋቱን ደግሞ መጀመሪያ መክፈል ያለብን ተጎጂዎቹ ነን ምንም ቢከፋ እግዛብሄር ይቅር ያላቸውን እኛም ማለት አለብን እኛ ዛሬ የምናደርገው ነገ ላገራችን ጥሩ ይሆናል ጥላቻን ቂም በቀልን ወደ አለፈ ታሪክ እየተመለስን መወቃቀስ የስቀራል ያ ደግሞ አገርንም ያሳድጋል በዚህ ይብቃን የሃይማኖት አባቶችም የሚስመሰግን ስራ ነው የሰራችሁት መንግስትም በዚሁ ይቀጥል አገር የሚያድገው በልማት ብቻ አይደለም መጀመሪያ እርስ በርሳችን እንማማር

  ReplyDelete
 47. Dani I have one question
  Enzieh sewoch eko Menfes kidusen sisdebu yenoru nachew ( lotu sibhat ) meshaf kidus degmo menfes kidusen yesdebe Hatiatu yekir aybalem yelal.

  ReplyDelete
 48. Wendema Daneal bemegemerya Selam Leante yehune yehen belog say eskeahune yeker yalalcuachewn sewech yeker endel aderekeg ena benegeh sewech gef wendmochan saldersebachew atechachewalew eskeahun yekert leba west alneberem tebekay amlak gen yerasu lyaregachew asebo yehonal edma yesetachew hulachenem yeker enbelachew wendmochachenen becha sayehone agerachenenem yegedelu nachew gen kethare gemera yeker beyachewalew

  ReplyDelete
 49. እውነት ብለሃል፡፡ ከልብ ይቅር ልንላቸው ይገባል፡፡ እስካሁን በእስር ቤት የቆዩት ጊዜ ይበቃቸዋል፡፡

  ReplyDelete
 50. dir d/dani
  የተጎጅ ቤተሰቦች ይህንን ታሪካዊ ሥራ ለመሥራት ስትነሱ ሕመማችሁን እናውቃለን፤ ጉዳታችሁም ይሰማናል፡፡ ከእኛ ይልቅ ለእናንተ ሁኔታው ከባድ ነው፡፡ ግን እየሠራችሁ ያላችሁት የጀግንነት ሥራ ነውና እናደንቃችኋለን፡፡ በእምነት ጽድቅ፣ በታሪክ ክቡር፣ በባህል ምስጉን የሆነ ሥራ ነውና በርቱ፡፡

  ReplyDelete
 51. በድለዋል፡፡
  በዚያው ልክ ተፀፅተዋል፡፡ተቀተዋል፡፡
  ለተጎጂ ቤተሰቦች ልብ ታላቅ የጀግንነትና የቅንነት ፈተና ነው፡፡
  ለመጪው ትውልድ ግን ከምንም ነገር በላይ የከበረ ውድ የታሪክ ስጦታ ነው፡፡
  ካለፈው የሚመጣው ይበልጣልና በቃ ከልብ ይቅር እንበላቸው፡፡ይኸን ስናደርግ እነርሱ የሰሩትን ስህተት ማንም አይደግመውም፡፡

  ReplyDelete
 52. emmmmmmm... It is hard to believe, to decide, even to think...I don't know what I have to say. It is dilemmatic in nature. But when I start to think about GOD my dilemma evaporates and forgiveness is the only way..............

  ReplyDelete
 53. የበዓሉ መዓድ ከመቆረሱ በፊት ጸሎት ተደርጎ ነበር፡፡ መጀመርያ ውዳሴ ማርያም ተደገመ፡፡ እኛ አይደለንም የደገምነው፡፡ መቋሚያቸውን ተደግፈው እነዚህ ታላላቅ የደርግ ባለ ሥልጣናት ናቸው የደገሙት፡፡ በአማርኛ እንዳይመስላችሁ፤ በግእዝ፡፡ የኪዳኑን ጸሎት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የሚቀበሉት እነርሱ ነበሩ፡፡

  ReplyDelete
 54. ዳኒኤል አንተ ምንም አላየህም እና ዝም በልዳኒኤል አንተ ምንም አላየህም እና ዝም በል

  ReplyDelete
 55. ወንድሞቼ እስከመቼ በጥላቻ እንኖራለን
  እነሱ እኮ የንን ሁሉ ሰው ሲጨርሱ እግዚአብሄር
  ስለፈቀደ ነው ስለዚህ እባካቹህ ወገኖቼ በርሱ ስራ
  አንግባ ይቅር እንበል ደግሞ ተበቃይ እኮ ጌታ ነው፡፡

  ፍቅሩ ስባኒ ከልደታ አካባቢ

  ReplyDelete
 56. please yikerta enelmed

  ReplyDelete
 57. egzihabher yistilin

  ReplyDelete
 58. በቅድምያ ጸጋውን ለአበዛልህ እግዚአብሔር ምስጋናዬን እያቀረብኩ ይህንን ጽሁፍ(መረጃ) አግኝቼ ያነበብኩት አመታትን በተሻገረ ጉዳይ ቢሆንም ጉዳዩ እልባት አግኝቶ የተቋጨ ይሁን አይሁን አላውቅም ነገር ግን በይቅርታ አልቆ ከሆነ የአምላካችን ስም የተመሰገነ ይሁን እያልኩ ይቅርታን ለሰጠች ልብ ክብር ሊቸራት ይገባልና የእግዚአብሔር ምህረት በአንቺ ላይ ለዘላለም ይሁን አሜን! ጉዳዩ በይቅርታ የልተጠናቀ ከሆነ ይቅርታ እየተጠየቅሽ ያለሽው ነፍስ በመስቀል ላይ ዋጋ የከፈለልሽን አምላክ ብቻ አስቢ እድለኛ ነሽ ይቅርታ በማለትሽ ብቻ በመጨረሻው ሰዓት እናንተ የአባቴ ብሩካኖች... የሚለውን የአምላክ ቃል ለመስማት ዛሬ ተመርጠሸል እባክሽ ይቅር በይና ጠላት ሰምቶ ይፈር ለዚህም እግዚአብሔር ይርዳሽ ፀሎቴ ፡፡

  ReplyDelete
 59. praise God. forgiveness should come from the bottom of the heart

  ReplyDelete
 60. wow.. thanks to God,, dani,,, its my first time to read ur page... በጣም በጣም ከሚገባ በላይ ወድጄዋለው.... እስከ ዛሬ ያንተን ድረገፅ ሳላውቅ በመቆየቴ ባዝንም ካሁን በሃላ ቀንደኛ ተከታታይህ እና ደጋፊህ ነኝ.... ጌታ እግዚሄር እንደናንተ ዓይነቱ ሰባኪዎች እና አዋቂዎች ምድራችንን ከጥፋት ለመታደግ ስለተሰጣቹሁን... እግዚአ
  ብሄርን እናመሰግናለን... ተባረክ

  ReplyDelete
 61. wow.. thanks to God,, dani,,, its my first time to read ur page... በጣም በጣም ከሚገባ በላይ ወድጄዋለው.... እስከ ዛሬ ያንተን ድረገፅ ሳላውቅ በመቆየቴ ባዝንም ካሁን በሃላ ቀንደኛ ተከታታይህ እና ደጋፊህ ነኝ.... ጌታ እግዚሄር እንደናንተ ዓይነቱ ሰባኪዎች እና አዋቂዎች ምድራችንን ከጥፋት ለመታደግ ስለተሰጣቹሁን... እግዚአ
  ብሄርን እናመሰግናለን... ተባረክ

  ReplyDelete
 62. እግዚአብሔር ይስጥልን ረጅም ዕድሜን ከጤና ጋር የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክልህ!!!!

  ReplyDelete
 63. ትንሽ አልተጋነነም ዘገባው?

  ReplyDelete