Monday, December 13, 2010

ምን እናድርግ ክፍል ሁለት

ኃይለ ገብርኤል ከአራት ኪሎ

የተከበራችሁ ወንድሞች እና እህቶች የሕያው አምላካችን ፍፁም ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን።


በመጀመሪያ ደረጃ ጊዜያችሁን ሰውታችሁ ፅሑፉን በማንበብ ቀጥላችሁም ነገሮችን በሁሉም አቅጣጫ በመመልከት የአካሔዱ እና የአፈፃፀሙ ሒደት እንዴት መሆን እንዳለበት በውስጣችሁ ካለው ስጋት ጭምር በግልፅ በመግለፃችሁ ቅዱስ እግዚአብሔር ቃለ ሕይወትን ያሰማልን፤ አሜን።

በጣም ደስ የሚለው ነገር ከሁሉም አስተያየት ሰጪዎች መረዳት እንደሚቻለው ሀሳብ እና ፍላጎቱ በሁላችንም ዘንድ የነበረ መሆኑ ነው። የቤተ ክርስቲያን ልጅነት ማለት እንዲህ ነው። ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መቆርቆርና እኔም አለሁ ብሎ ከልብ መነሳሳት በእውነት ልብን በሐሤት ይሞላል። የእኛን የልጆቹን እንዲህ ከልብ መነሳሳት ሲመለከት ቅዱስ አባታችን እግዚአብሔር ትንሿን ጥረታችንን ባርኮ እና ቀድሶ ለታላቅ ቁምነገር እንደሚያበቃልን በፍፁም ልባችን እናምናለን።

አንድ ልንገነዘበው የሚገባ ነገር ይታየኛል። አንድን ነገር ለመስራት ስንነሳ ነገሮች መጀመሪያ እንዳሰብናቸው አልጋ ባልጋ ላይሆኑ ይችላሉ። የመጀመሪያው ፈተና በእኛው ውስጥ ያለው አላስፈላጊ ፍርሓት ነው። ይኸውም ሰው እዲህ ወይም እንዲያ ቢለኝስ የሚለውን ሀሳብ በመንገዳችን ላይ ስናስቀምጥ ሀሳባችን በውጥን ይቀራል። ሳይጀመር ይጠናቀቃል። ሁለተኛው ደግሞ እኛ ራሳችንን አሳምነን፣ ግራ ቀኙን ተመልክተንና አመዛዝነን ለመስራት ስንዘጋጅ ከሌሎች የሚመጣብን የሀሳብ ስርቆት ነው። እነዚህን ሁለቱንም የፈተና አይነቶች ወንድም ዲ/ን ዳንኤል “ውሾቹም ይጮሃሉ ግመሎቹም ይሔዳሉ” በሚለው ፅሑፉ በሚገባ አብራርቶታል። ከዚህ ፅሑፍ ውስጥ የሚከተለውን እንመልከት።

,,,,,በዚህ ጊዜ አባትዬው ከአህያዋ ወረደና ለልጁ እንዲህ አለው፡፡ “አየህ ልጄ በዚህ ዓለም ምንም ነገር ብትሠራ ሰውን ሁሉ ማስደሰት አትችልም፡፡ ሰዎች እንዲህ ይሉኛል እያልክ የምትፈራ ከሆነ ምንም ነገር ማድረግ አትችልም፡፡ ሰዎች ምንም ብታደርግ የሚሉት አያጡምና፡፡ አንተ ሰውን ሳይሆን ስሕተትን ፍራ፡፡ ትችትን ሳይሆን ኃጢአትን ፍራ፡፡ ሰዎች ስላሉት ብቻ

የምትቀበል ከሆነ ሃሳብህን መቶ ጊዜ ትቀያይራለህ፡፡ መቀበል ያለብህ የሚሉት ነገር ትክክል ከሆነ ብቻ ነው፡፡” አለው፡፡ ከዚያም አባት እና ልጅ እየተጨዋወቱ መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡

በመሆኑም እነዚህ ፈተናዎች በምንም መልኩ እንቅስቃሴያችንን ሊያውኩብን አይገባም።

ሌላው እንደዚህ ዓይነት እገዛ ለቤተ ክርስቲያን ማድረግ ከተፈለገ በሌሎች ማኅበራት በተለይ በማኅበረ ቅዱሳን በኩል ቢሆን ይሻላል ያላችሁ ወንድሞች እና እህቶች አላችሁ። በልዑል እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ተቋቁሞ አሁንም በእርሱ በባለበቱ በቅዱስ እግዚአብሔር ጥበቃና ቸርነት እንዲሁም በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃና በረከት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ ስራዎችን በመስራት ላይ የሚገኘው ማኅበራችን ማኅበረ ቅዱሳን ለተጎዱ አድባራትና ገዳማት እንደዚህ አይነት ስራዎችን የሚሰራ ክፍል አቋቁሞ በስፋት እየተንቀሳቀሰ መሆኑ እንኳንስ ለተዋሕዶ ልጆች ለሌሎቹም ግልፅ ነው። ነገር ግን ከችግሩ ስፋትና ጥልቀት አንፃር ስራዎችን ሁሉ ማኅበረ ቅዱሳን ብቻ ይስራቸው ማለት ተገቢ አይመስለኝም። ዓባይን በጭልፋ ነውና። ማኅበሩ በሚያከናውናቸው ተግባራት እንደየስጦታችን መሳተፍ እንችላለን። ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ በዲ/ን ዳንኤል የጡመራ መድረክ ላይ ለተዋወቅናቸውና በተለያየ መልኩ እገዛ ለሚሹት ቦታዎች እንዲሁም አስታዋሽ ላጡ ሊቃውነተ ቤተ ክርስቲያን በኅብረት ሆነን አቅማችን የፈቀደውን ማድረግ ብንችል መልካምነቱ የጎላ ነው።

በተጨማሪም እኛ እየተነጋገርንበት ያለነው ሃሳብ ለአድባራትና ገዳማት የራሳችንን አስተዋፅዖ ከማድረግ ባለፈም በተለያዩ ማሕበራዊ ጉዳዮች ውስጥም መሳተፍ የሚያስችለን ነው። ሁላችንም እንደምናውቀው ሃገራችን የኔ የምትላቸውና ከሌላው ዓለም የምትለይባቸው እጅግ ብዙ የሆኑ እሴቶች አሏት። እነዚህ የማንነታችን መገለጫ የሆኑና ኢትዮጵያዊን ኢትዮጵያዊ ያደረጉት ሃብቶቻችን ከሌላው የሚለዩበት ድንበር ሆን ተብሎም ይሁን በስህተት እየተናደ የእኛነታቸውን እስከምንጠራጠርበት ደረጃ እየደረስን ነው ያለነው። ታድያ እኛም የአባትህ ቤት ሲዘረፍ… እንደሚባለው ለጥፋቱ ተባባሪ የምንሆነው እስከመቼ ነው? በዚህ ጉዳይም የዜግነትና የትውልድ ድርሻችንን ልንወጣ ይገባናል።

እንዲሁም እግዚአብሔር በፈቀደላቸው መጠን በተለያዩ ዘርፎች ለህዝባችንና ለሃገራችን ጠቀሜታቸው የላቀ የፈጠራ እና የምርምረ ስራዎችን ለሚሰሩ የሃገራችን ልጆች ስራቸው ትኩረት እንዲያገኝ አና ከዚያም የበለጠ ነገር እንዲሰሩ ለማበረታታት፣ በአርኣያነታቸው ሌሎችን እንዲያስከትሉ ለማድረግና ለጥረታቸው እና ለድካማቸው ተገቢውን ቦታ አንዲያገኙ በምንችለው መጠን ብንረዳቸው ኃላፊነታችንን ተወጣን ማለት ነው።

የተከበራችሁ ወንድሞች እና እህቶች ሌላው ነገር ዲ/ን ዳንኤልን መርዳት ማለት ምን ማለት ነው? እንደ እኔ አመለካከት ገንዘብ ሰብስቦ መስጠት አይደለም። ይልቁንም ዘወትር ያለመታከት የሚጮህበትንና የሚደክምበትን ሀሳብ ከግቡ እንዲደርስ በቻልነው ሁሉ ብቻውን እንዳልሆነና አብሮነታችንን በመግለፅ ዓላማው ዓላማችን ሕልሙም ሕልማችን መሆኑን በመገንዘብ ጥረቱና ድካሙ በሃሳብና በንግግር ብቻ ሳይቀር የሚታይና የሚዳሰስ ለውጥ እንዲያመጣ በሚጓዝበት አቀበታማ እና ቁልቁለታማ መንገድ ሁሉ አብረነው መጓዝ እንዲሁም በጉዟችን ወቅት እያንዳዳችን እንደየ ስጦታችን የየራሳችንን አስተዋፅዖ ማድረግ ነው። የዚያን ጊዜ ወንድማችንን “ረዳነው” ማለት ነው። “ረዳነው” ማለት እንደው የአገላለፅ ጉዳይ ሆኖ ነው እንጂ የየራሳችንን ኃላፊነት ነው የተወጣነው። በቤተ ክርስቲያናችንም ሆነ በሃገራችን የፈለግነውን ነገር ብንሰራ ዲ/ን ዳንኤል በተለየ መልኩ የሚያገኘው የተለየ ጥቅም ኖሮት አይደለም። ነገር ግን በእርሱ ቀስቃሽነትና ያላሰለሰ ድካም እና በሌሎች ወንድሞችና እህቶች መልካም ትብብር ለውጦች ሲመጡ ሲመለከት እርካታን ያገኛል።

ወደ ዲ/ን ዳንኤል ስመለስ፤ በእውነት የእኛን የወንድሞችህንና እህቶችህን ሃሳብ ወደ ጎን ሳትል ይልቁንም የእያንዳዳችንን ፍላጎት ከስጋታችን ጭምር በጥሞና ተመልክተህ ሀሳባችን ፍሬያማ ሊሆን የሚችልበትን አካሄድ ስላመላከትከን ልዑል አባታችን ቅዱስ እግዚአብሔር ያክብርንል፣ ረዥም ዕድሜ ከሙሉ ጤና ጋር ይስጥንል፤ አሜን።

አሁን እንግዲህ ቀሪው ነገር ለሚቋቋመው ፋውንዴሽን ግብዓት የሚሆኑ ነገሮች ላይ መወያየትና መወሰን ከዚያም እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ ወደ ተግባር መሸጋገር ብቻ ነው። ስለሆነም ወንድሞችና እህቶች እስቲ አንድ ሁለት በሉ።

ቸረ ያሰማን፤ አሜን።

13 comments:

 1. The idea is very fantastic.I can summerized my idea with the below poem.Some of us sayinig in your comment above''...why not mahibere kudsuan do? why not mr.x do?....etc'' I think all this comments are originated from the word ENE MIN AGEBAGN. Please let us do our share.or help for those who would like to work. Any way read the poem.
  Getachew.

  አኔ ምን አገባኝ

  ''አኔ ምን አገባኝ የምትሉት ሐረግ፣


  አሱ ነው ሃገሬን ያረዳት አንዴ በግ፣


  የሚል ግጥም ልፅፍ ስሜት አንዘርዝሮኝ ብድግ አልኩኝና፣


  ምን አገባኝ ብዬ ቁጭ አልኩ አንደገና።''


  አንድ አፍኝ ግጥሞች ከተሰኘው የ ኑረዲን ኤሳ በ 2002 ካሳተመው

  ReplyDelete
 2. Kale hiwot yasemalin.
  Tiru jimir mew. I hope Hilegabriel will lead us through the process. What to do next. Please inform us. Egziabher yistilin. Emebetachin tiketelachihu. Atlanta

  ReplyDelete
 3. betam tiru hasab new. esti neza bekul muyategnoch tenagerunina egnam hasabachinin enibel.
  egzer yirdan

  ReplyDelete
 4. tiru hasab new. egiziyabiher kena gar yihun

  ReplyDelete
 5. @ Getachew, you are right sometimes we think those things are none of our business. But I also want to mention that, what about all the comments rolling around were because of fear. We have thousands of organizations (whether NGO or not) but we are not lucky to see all of them being fruitful except which u can count 1,2, probably 3 org that is all. I am not also saying we should not have many of these kinds, but what I am saying is let all of us have clear understanding of what we are going to do. This happens only if we discuss. I suggest every one to forward all suggestions, fears.

  I would love to see an organization or a foundation:

  1)with no conflict of interest, just it should only work for what it stands for.
  2)with no competition game as most of Daniel's blog thought us. To work collaboratively with others for a better development rather than fighting,... pointing figures on others.

  In conclusion, from my view I like the idea of this foundation specially if we make sure what is its scope. From what I can see, this has a broader vision as we can reach lots of issues"... አንድ ፋውንዴሽን ብናቋቁምና በዚህ ብሎግ ላይ ወጥተው ጥገና፣ እገዛ፣ ለሚያስፈልጋቸው ቅርሶች፣ ግንባታ ለሚያስፈልጋቸው ሙዝየሞች እና ዕቃ ቤቶች፣ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሊቃውንት፣ ኅትመት ለሚያስፈልጋቸው ጥንታውያም መረጃዎች፣ ሽልማት ለሚያስፈልጋቸው ኢትዮጵያውያን አንዳች የምንችለውን ነገር ብናደርግ፡፡..."

  Forward all your ideas brothers and sisters.
  Gebre Z Cape

  ReplyDelete
 6. Dear All
  for the word 'Foundation', can we find some Amharic word please

  ReplyDelete
 7. ሃሳብህ ግሩም ነው የኮሚቴ ብዛት ለውጥ አያመጣም ዛሬም ፋውንዴሽን ማቋቋሙ ብዙ አይታየኝም ። ተተማረ ብሎም የተደራጀ የሰው ኃይል ገና ከምንሰበስብና ከምናደራጅ
  ለምን በማሕበር ቅዱሳን እንዲሰራ ሃሳብ አናቀርብም ። ብዙ የሥራ ልምድም በማሕበሩ ወስጥም አለና።

  ReplyDelete
 8. I agree with those who say that there are a number of NGOs who are already doing this but may be lack the resources (funding/man power/institutional...)

  IMO, A foundation does not have to do the ground work. The foundation can be a source of funding for those that are doing the ground work.

  Any NGO doing this type of work can apply to the foundation for getting the funds and the foundation will choose and fund those it thinks are a worthy cause.

  Also the foundation keeps track of which NGO delivered on the promise (used the funds awareded to it responsibily). Any NGO which did not deliver on its promise will be black listed as an NGO which will never be funded.

  And if in doing so, the foundation sees that the existing NGOs can not (are not enough to) implement its vision, it can start an arm that does the actual ground work.

  So starting a foundation still is a good idea.

  ReplyDelete
 9. መልካም ነገር ሰሞኑን እያነበብን ነው የ ዲን ዳንኤልን ጽሑፎች ምን ያህል ወደውስጣችን እያስገባን እንደሆነ አመላካች ነው ፡፡ እውነትም የቅዱስ ጴጥሮስ/የአባቶቻችን/ ልጆች መሆናችንን አመላካች "ምን እናድርግ?" ማለታችን እና አጅግ ውጤታማ ሀሳቦችን መሰንዘራችን እግዚአብሔር ይመስገን ፡፡ የተቸገርነው ቃለእግዚአብሔር ሰምቶ ስለቤተክርስቲያኑ የሚያስብ እና ለለውጥ የሚነሳ /ማስተዋልን ታደለ/ እንጂ በተለይ ሀገር ቤት የነ እንቶኔ ተማሪዎች መጨረሻ ውጤታቸው አድናቂህ ነን ከማለት የዘለለ ኤደለም ይህ የሚያሳየው የዘመኑ አገልጋዮች የአባቶቻችን ልጆች አለመሆናቸው እና አገልግሎታቸው የራስን ጥቅም እና ዝና እንዲሁም የሌሎች ቅጥረኛ መሆናቸውን ነው ፡፡ በእኔ በኩል የተነሱት ሀሳቦች እውነተኞችን የሚያሰባስብ እና ለውጥ የሚያመጣ በመሆኑ በሙሉ ኃይላችን ተሳታፊ ነን ፡፡ የአባቶቻችን አምላክ ከኛ ጋር ይሁን አሜን፡፡

  ReplyDelete
 10. Selam Haile... I am ready to do my little part.Anytime contact me i will be part of it.Thank you

  ReplyDelete
 11. የማይበላ እንዳያስበላ ያብላላDecember 15, 2010 at 11:08 PM

  Dear Dn. Daniel, as we all know that organizing and creating a good foundation in a short time it might not be easy as we think. If that is the case, is there any thing we could do in the mean time?. I think like some of the people suggested, if there are some projects which are already prepared by Maheber Kidusan, don't you think it will be effective to highlight the projects by posting them on your blog with their associated cost (monthly, annually or the whole project cost), so most of us could sponsor any project individually or as a group through Maheber Kidusan by choosing what ever project we could afford. I think doing this is not only enable us to finish many projects, but also it creates a way for us to engage actively. In addition, It is also encourages us to participate more vigorously in our new future foundation by creating a sense of pride from knowing what our contribution could accomplish. At this moment from watching the comments on your blog, it seems a lots of brothers and sisters including me are fired up to be a part of this blessing. I think for all of us this is best opportunity not to miss.

  እግዚአብሔር ለመፈጸም ያብቃን!

  ReplyDelete
 12. I am up for it. I hope the next issue will be on how we will get it done!!!

  ReplyDelete
 13. wodet wodet new negeru? please just stop and think twice.why this will be done in one persons name while we have many organizations which anyone can trust just because it is reasonable.Akahedu yasferal anyway Egiziabher mastewalun yisten amen.

  ReplyDelete