Thursday, December 9, 2010

ምን እናድርግ?

ኃይለ ገብርኤል ከአራት ኪሎ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

የአምላከ ቅዱሳን የልዑል እግዚአብሔር ሰላምና ፍቅር ከዚህ የጡመራ መድረክ ጦማሪ (ዲ/ን ዳንኤል) እና ከመላው የመድረኩ እድምተኞች ጋር ለዘላለም ፀንቶ ይኑር፤ አሜን።

የተከበራችሁ ወንድሞችና እህቶች፤ ሁላችንም እንደምናውቀው ወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል በዚህ የጡመራ መድረኩ አማካኝነት በቅርብም በሩቅም ያለነውን ያለ ማንም ጎትጓችና ቀስቃሽ ልዑል እግዚአብሔር ባነሳሳው መጠን ደከመኝና ሰለቸኝ ሳይል ዘወትር በየሳምንቱ ማክሰኞና አርብ ከቅርቡ ጀምሮ ደግሞ ቅዳሜ አንዳዴም እንደአስፈላጊነቱ በሌሎቹም ቀናት በመጠቀም በአንዲት መአድ (የዳንኤል እይታዎች)ምግበ ነፍስና ምግበ ስጋን ሲመግበን ቆይቷል፣ አሁንም እየመገበን ይገኛል፣ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ ወደፊትም ከዚህ በበለጠ ያጠግበናል።

ይህንን የጡመራ መድረክ ከጀመረ ወዲህ በተለያዩ ማኅበራዊ ክንዋኔዎች እና አስተሳሰቦች ላይ በእርሱ እይታ አንጥሮ አውጥቶ ለነገሮች ያለን ግንዛቤ እንዲጎለብት እንዲሁም የአስተሳሰብ አድማሳችን እንዲሰፋ፣ በመንፈሳዊ እና በስጋዊ ተጋድሏቸው አንቱታን ያተረፉ ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት በስጋቸው ከመቃብር በታች የሆኑ ወገኖቻችን በህይወት እያሉ የሰሯቸው በጎ ስራዎች አንፀባራቂ እንደነበሩ ሲያመላክተንና ይህ ስራቸውም ለትውልድ እንዲተላለፍ ሲተጋና እኛንም የማንነታችን መገለጫ የሆነውን ታሪካችንን ጠንቅቀን እንድናውቅ ሲያስገነዝበን፣ በመንፈሳዊ ህይወታችንም ማወቅ ያለብንን እንድናውቅ እና የሚጠበቅብንን ክርስቲያናዊ ግዴታ እንድንወጣ ሲመክረን እና ሲያነቃቃን ቆይቷል።

ዲ/ን ዳንኤል ይህንን ሲያደርግ እና በተቻለው መጠን ሁሉ መልካም ነገሮችን ሲያገኝ ደስ ብሎት ደስታው የኔ ብቻ ይሁን ብሎ ሳይሰስት ለሌሎች ሲያካፍል፣ አሉታዊ ጎን ያላቸውንም ክስተቶች ሲመለከት ወይም ሲሰማ ብዙዎቻችን እንደምናደርገው እንዳላየ እና እንዳልሰማ ሆኖ እንዲህ ብናገር እንደዛ ልሆን እችላለሁ ወይም ሌላ ነገር ይመጣብኛል በማለት አላስፈላጊ ፍርሐት በልቦናው በማሳደር፣በግዴለሽነት እና በቸልተኝነት ሳያልፍ በቂ መረጃን በመያዝ ፊት ለፊት በመጋፈጥ የዜግነትና የመንፈሳዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ ነገሮች ሁሉ አልጋ ባልጋ ሆነውለት እንዳልሆነ ይልቁንም በአባታችን በቅዱስ እግዚአብሔር ቸርነትና በወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤትና በረከት መሆኑ መቼም ምስክር አያሻውም።

ወንድሞች እና እህቶች፤ ሁላችንም እንደምንገነዘበው ቅዱስ እግዚአብሔር እኛን ልጆቹን ለማስተማር፣ መብትና ግዴታችንን ለማሳወቅ እና የፅድቅና የኩነኔን ምንነት ለማሳየት እኛ ያላስተዋልናቸውን ብዙ መንገዶችን ይጠቀማል። ከእኛ የሚጠበቀው በዕለት ተዕለት ኑሯችን የሚያጋጥሙንን ክስተቶች ከገጠመኝነታቸው ባለፈ ትኩረት ሰጥተን ማስተዋል ነው። በመሆኑም ዲ/ን ዳንኤል በዚህ የጡመራ መድረክ ላይ የሚያወጣቸውን ቁምነገሮች እንደው ለመዝናኛ እንዳይመስለንና እንዳንሳሳት እሰጋለሁ። ስለዚህ በወንድማችን ላይ አድሮ ይህንን መድረክ እንዲጀምር በማነሳሳት፣ በስራም ይሁን በትምህርት እንዲሁም በሌላ ምክንያት በተለያዩ ቦታዎች (ከሀገር ውጪም ጭምር) ለምንኖረውና ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በምታደርጋቸው የተለያዩ እንቅስቃሴዎች በቀጥታ መሳተፍ ለማንችል ወገኖች ከማር በጣፈጠ አቀራረብ አስፋፍቶና አብራርቶ እንዲያሳውቀን ያደረገውን አምላክ እያመሰገንን እንደየአቅማችንና እንደየስጦታችን ፍሬ ልናፈራበት ይገባናል። እንዴት አትሉኝም?

ከላስቬጋስ ልጆች ምን ተማርን?

በመጀመርያ ደረጃ ዲ/ን ዳንኤል ይህንን የጡመራ መድረክ የጀመረው በቅዱስ እግዚአብሔር አነሳሽነት በመሆኑ አቅሙ በፈቀደ መጠን የሚችለውን ለማድረግ እንጂ በማንኛውም ሁኔታ ከማንም ምንም ዓይነት እገዛ ይደረግልኛል በማለት እንዳልሆነ ጥርጥር የለውም። ምክንያቱም ጡመራ ከጀመረበት ወቅት ጀምሮ አንድም ጊዜ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ይህንን ዓይነት ጥያቄ ሲያንፀባርቅ አልተስተዋለም። የሚገርመው በተለያዩ ጊዜያት አንዳንድ አስተያየት ሰጪ ወንድሞችና እህቶች የራሳቸውን አስተዋፅዖ ለማድረግ ለኢንተርኔት እና ለተለያዩ ነገሮች የሚያወጣው ወጪ ታስቧችው በምን መልኩ እናድርግ እያሉ ሲጠይቁት እንኳን ምላሽ አልሰጠም። ይህም የተነሳለትን ዓላማ በግልፅ ያሳያል። እግዚአብሔር አምላክ ይህንን አስተዋይነቱን እና አርቆ አሳቢነቱን ከእርሱ ጋር ያፅናልን።

ይህንን ፀባዩን ጠንቅቀው የተረዱት ላስቬጋሶች ታድያ በሀገራችን ያለውን የኢንተርኔት አጠቃቀም ችግር በመረዳት አርአያነት ያለው ተግባር ፈፅመዋል። ከበረከቱም ተካፍለዋል። እናነተ የላሰቬጋስ ልጆች ላደረጋችሁት በጎ ተግባር ቅዱስ እግዚአብሔር ሰማያዊ ዋጋ ይክፈላችሁ። ፍሬ ማፍራት ማለት እንዲህ ነው። ሌሎቻችንስ የላስ ቬጋስ ልጆችን ባደረጉት አስተዋፅዖ እነሱን ከማመስገንና ከማድነቅ ባለፈ መንፈሳዊ ቅናት አላደረብንም ወይ?

ከ”ጉዞ ወደ ደረስጌ” ምን ተገነዘብን?

ከጎንደር ወደ ጃን አሞራ ያደረገውን ጉዞ ከስር ከስር ለእኛ ትኩስ ተኩሱን አየተረከልን እነሆ ክፍል አራት ላይ በሁኔታዎች ገዳቢነት ብዙ ቀሪ ታሪኮችና ሀብቶች እያሉ ተጠናቀቀ። በድጋሜ ላሰ ቬጋሶችን ዕድሜ ይስጥልን አያልኩኝ የማንነታችን ሕያው አሻራ የሆኑ ቅርሶቻችንን በፎቶ ለማየት ቻልን። ለነገሩ ወንድማችን የሚጠቀማቸው ቃላቶችና የአገላለፅ ብቃቱ ፅሑፉንም ስእላዊ እንዲሆን አድርጎታል። ለምሳሌ ያህልም («ሰው ሆይ አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ» ለተባለው ቃል የሰነድ ማስረጃ መስለናል፡፡ አሁን ተሠርተን ገና ጭቃችን የደረቀ ይመስላል) እንዴት የሚያምር አገላለፅ ነው? ይህ ዓይነቱ አተራረክ በአንዲት መኪና እኛን ሁሉ አሳፍሮ በመጓዝ በዋለበት እንድንውል ባደረበት እንድናድር እድርጎናል። ከዚያም በደረስጌ ማርያም ያለውን ታሪክ አባቶችን እየጠየቀ ሊያካፍለን እንዲሁም በዓይኑ የሚያየውን በአይናችን እንድናይ በእጁ የሚዳስሰውን ሁሉ በእጃችን እንድንዳስስ ከዚያም በሚያስገርመው እንድንገረም፣ በሚያስደስተውም እንድንደሰት እና በሚያስቆጨውም እንድንቆጭ በስጋችን በያለንበት ብንሆንም በመንፈስ ግን ደረስጌ ላይ ሰበሰበን።

በዚያች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በውጭ እና በውስጥ ያለውን ፀጋ እግዚአብሔር ተመልክተን እፁብ ድንቅ አልን። በሰማነው ታሪክ፣ ባየነው እና በዳሰስነው ሁሉ መገረማችንና መደነቃችን እንደተጠበቀ ሆኖ ለታሪካችን፣ ለቅርሳችንና ለማንነታችን መገለጫ ለሆነው ሀብታችን የምናደርገው ጥንቃቄ እና ክብካቤ ምን ያህል የወረደ እንደሆነም ልናሰምርበት ይገባናል። ይህንንም በደረስጌ በሚገባ ተገንዝበናል። ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ሁላችንም በሚገባ ስለተመለከትነው እያንዳንዱን ነገር መዘርዘር አስፈላጊ አይመስለኝም።

የተከበራችሁ ወንድሞች እና እህቶች፡- ቅዱስ እግዚአብሔር ወድዶና ፈቅዶ ዛሬ ደረስጌ ማርያምን ተመለከትን እንጂ እንደዚህ ያለ እና ከዚህም የባሰ ችግር ላይ ያሉ ስንቶች ይሆኑ??? እኛስ እስከመቼ ነው ኃላፊነታችንን ከንፈር በመምጠጥ የምንወጣው? መቼም ከንፈር መምጠጥ መፍትሔ ቢሆን ኖሮ እኛ(ኢትዮጵያውያን) እና ችግር የሰማይ እና የምድርን ያህል በተራራቅን ነበር። በተለያዩ ጊዜያት ቅዱስ እግዚአብሔር በተለያዩ መምህራን እያደረ የተለያዩ ችግሮችን ሳይከሰቱ በፊት እንዴት መጠንቀቅ እንደምንችልና ባጋጣሚ ቢከሰቱም መውጫ መንገዱን አስተምሮናል። ይሁን እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስ በትንቢተ ሆሴዕ ምዕራፍ 4 ቁጥር 6 ላይ እንደምናነበው ቅዱስ እግዚአብሔር ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቶአል ይላል። ዕውቀት ማጣትን አባቶች ሲያስተምሩ አንደኛ ባለመማር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ተምሮ ባለማወቅ ነው። ሁለተኛውን ምክንያት ሲያብራሩትም የሚማረው ሰው ብዙ ነው የሚያውቀው ግን ጥቂት ነው። በትምህርት ላይ እያለ ሰምቶ አድንቆ የሚሄድ አለ። የብዙዎቻችን ችግር አለመማር ሳይሆን የተማርነውን አለማወቅ ነው። ታድያ አሁን በደረስጌ ማርያም የተማርነውን እፁብ ነው ድንቅ ነው ብለን ብቻ ልናልፈው ይሆን??? እኛ እኮ ተጠያቂነታችን በልዑል እግዚአብሔር ብቻ አይደለም። በመጪው ትውልድም ጭምር እንጂ። ምክንያቱም አባቶቻችን በተለያዩ መከራዎች ውስጥ አልፈው ያቆዩልንን ሀብት እኛም በተራችን አስፈላጊውን ክብካቤ በማድረግ ልንጠብቀውና በአደራ የተቀበልነውን በአደራ ልናስረክብ ይገባናል።

አንዳንድ ጊዜ ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሆነ ችግር ስንሰማ ብዙዎቻችን ችግሩ የሚፈታበትን መንገድ ከመፈለግና የራሳችንን ኃላፊነት ከመወጣት ይልቅ እግዚአብሔር እንዲህ እና እንዲያ ያድርግ ወደ ማለቱ እናመዝናለን። የአቅማችንን አስተውፅዖ በማድረግ ቀሪውን እርሱ ይሙላው ማለት እና እጅና እግራችንን አጣምረን በመቀመጥ ሁሉንም እርሱ ይስራው ማለት በእጅጉ ይለያያሉ። ቅዱስ እግዚአብሔር አይደለም ችግሩን መፍታት እንዳይከሰትም ማድረግም ይችላል። ነገር ግን እኛም የራሳችንን ድርሻ እንወጣ ዘንድ ይፈልጋል። የቻልነውን ያህል ሞክረን ቀሪውን እርሱ እንዲባርክልን መጠየቁ ተገቢ ነው። ምንም ሳንንቀሳቀስና ሊባረክ የሚችል ጥቂት ነገር ሳይኖረን በረከትን መጠየቁ የክርስቲያን ወጉ አይደለም።

ዲ/ን ዳንኤል ደረስጌ ማርያም ላይ ቆይታውን አጠናቆ ወደ ጎንደር ከመመለሱ በፊት ለሁላችንም የሚሆን የበረከት ጥሪ አስተላልፎልናል። እንዲህ በማለት “ሙዝየሙን ለመሥራት ሁላችንም ብናግዛቸው የትውልድም፣ የሃይማኖትም ግዴታችንን ተወጣን ማለት ነው፡፡ ያለበለዚያ ባዶ ቁጭት ይሆንብናል፡፡”

ታድያ ምን እናድርግ?

ዋናው ጉዳይና በሁላችንም ልብ የሚመላለሰው “ታድያ ምን እናድርግ?” የሚለው ጥያቄ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ። እስቲ እኔ ምፍትሔ ነው ወደምለው ልውሰዳችሁ። በደረስጌ ማርያም ካለው በረከት ለመሳተፍ እንዲሁም በቀጣይም ልዑል እግዚአብሔር በወንድማችን እያደረ ከሚያመላክተን የበረከት ቦታዎችም የበረከቱ ተካፋዮች እንሆን ዘንድ እና በትውልድም ተወቃሽ ከመሆን እንድን ዘንድ ለምናደርገው ጥረት ወንድማችን እንዲተባበረን አድርገን በስሙ አካውንት ይክፈትልን። ከዚያም እንደ አቅማችን የየራሳችንን አስተዋፅዖ በማድረግ ከቁጭትና ከወቀሳ ድነን የሰማያዊ በረከት ባለቤቶች እንሁን።

ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ። ያዕቆብ ፩- ፳፪

ቸር ያሰማን፤ አሜን።


34 comments:

 1. Egiziabher yistilin.
  I live in Atlanta and I realy want to know who to contact in order to contribute for this cause. If you give some idea we can get together and do what we can for our precious church and Dn. Daniel.

  ReplyDelete
 2. What a noble idea! I agree with it

  ReplyDelete
 3. Lord greetings all!

  That is good point! Wendem Dn.Daniel, I hope you will help us with the matter.

  Blessings!

  ReplyDelete
 4. እባካችሁ:ይህን ሃሳብ ያፈለቃቹ ወገኖች: አደራጁን;ምሩን;ሰሜን አሜሪካ የጸሎት እንጅ የገንዘብ ችግር የለም ; እባካችሁን የዚህ በረከት ተካፋዮች አድርጉን.....ካናዳ (ኤድመንተን)

  ReplyDelete
 5. It is really interesting and a serious issue because D/n Daniel described how much our precious wealth will be lost due to lack of attention. As our brother said open the account and organized the implementer group which live around the derasgie mariam church then we can make a difference if we really condomend ourselves for our mother church.
  The account we will open it may working for other church problems which will raised by D/n Daniel in his next articles. unity makes a difference. thanks to raise such concrete idea.

  ReplyDelete
 6. ኃ/ገብርኤል እግዚአብሄር ያክብርህ በዚህ ጉዳይ ላይ ኃላፊነትህን በመወጣትህ። ሃሳቡ በጣም ጥሩ ነው ሁላችንም ወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል የጀመረው ትልቅ መስዋዕትነት በመሆኑ ሁላችንም አለን በርታ እንበለው። ለሃገራችንም ለሃይማኖታችን ደራሽ አኛ ሃገሬዎቹ ነን።

  ReplyDelete
 7. እኔም ይህንን ሃሳብ እደግፋለሁ። ለማረጋገጥ ያክል፤ አንድ መጽሐፍ ቢያንስ ባለሁበት ሀገር $10 ይሸጣል። ዲ/ን ዳኒአኤል ደግሞ በነጻ እስካሁን ቢያንስ $10 መጽሐፍትን አስነብቦናል። ያውም በተለያየ ጽንሰ ሀሳብ ላይ፤ የዳኒ ጽሁፎች ተነበው የሚጠገቡ ሳይሆኑ ለልጅ ልጅ የሚተርፉ መዐዛቸው ከአእምሯችን የማያጠፉ ጣፋጭ ናቸው።
  ዳኒ ይህ ለውዳሴ ከንቱ ሳይሆን ስለ እውነት ነውና በርትትህ ጻፍልን እኔም እንደ ኃይለ ገብራኤል የቻልኩትን ላዋጣ ቃል እገባለሁ። እባክህ አካውንት ክፈትና ንገረን

  ዮሴፍ ከአሜሪካ

  ReplyDelete
 8. ከተክለ ጊዮርጊስ

  ውድ ወንድሞች እኔ በተነሳው ሃሳብ ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ ነገረር ገግነን ዲ/ን ዳንኤልን ከተለያዩ አሉባልታዎች ለመጠበቅ ይህ ስራ ቤተክርስቲያን ዙሪያ ተሰባስው የቤተክርስቲያን አገልግሎት በመሚደግፉ ማኅራት በኩል (ለምሳሌ ማኅህበረ ቅዱሳን) ቢሆን የሰሩትን ስራ ሪፖርት ቢያደርጉ የሚሰበስቡትንም ገንዘብ ለዚሁ ስራ ብቻ እንዲያውሉ ውል መዋዋል ቢቻል (ይቻል አውቃለሁ) እና ስራው በአጠቃላይ ኦዲት ቢረግ የሚል ሃሳብ አለኝ
  ዲን ዳንኤል ሃሳብ ሊሰጥበት ይችላል

  ReplyDelete
 9. Eshitachin yebeza new , wendim Hailegebriel

  ReplyDelete
 10. tiru hasab new. kemawurat (comment kemadereg becha) wedemesrat leneshegager new. yejemer.

  ReplyDelete
 11. ወንድማችን ኃይለ ገብርኤል በሃሳብህ በጣም ተስማምቻለሁ። ምን ማድረግ ይገባኛል እያልኩ ሳስብ ነበር። ስለዚህ በጣም ጥሩ ሀሳብ ስልሆነ አካውንቱ ይከፈትና ቁጥሩ ይነገረን የቻልነውን እናድርግ። ዺ/ን ዳኒ እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልህ፡፡

  ዮናስ ከአዲስ አበባ

  ReplyDelete
 12. ሙሉ ሃሳቡን እቀበለዋለሁ:: ነገር ግን በዲን. ዳንኤል ሥም አካውንት መክፈቱ መልካም መስሎ አልታየኝም:: አንደኛ ለእርሱ ፈተና እያዘጋጅንለት መሆኑን ልብ እንበል! ዛሬ አሉን ያልናቸው ሰባኬአነ ወንጌል አባቶች እና ሌሎች አገልጋዮች በዚህ ጾር ወድቀውብናል:: ሁለተኛ እኛ (ህዝባችን) ትንሽ ነውና የሚበቃን በሃሜት አንለቅ:: ዲን.ዳንኤል በማስተባበር እና ትክክለኛውን መንገድ በማመላከት የተዋጣለት ነው: ይህም ከእግዚአብሔር የተሰጠው ሥጦታ ነው:: ስለዚህ በአካባቢው የሚኖሩ እና በአዲስ አበባ የሚኖሩ ወገኖችን ሰብስቦ ግልጽ እና ተጠያቂነት በተሞላው መልኩ ሥራውን ይጅምር እላልሁ:: እኔም ከበረከቱ ተሳታፊ ለመሆን ዝግጅ ነኝ::
  አብርሃም

  ReplyDelete
 13. it is a wonderful idea and D/n Daniel will help us what we are feeling about our churches treasure and his job. this is also our obligation those who are living in Ethiopia too. i am ready to contribute what i can, please anybody who are a close friend of D/n Daniel tell him to make this effort soon. we stand together if we are in unity but fall in division. may the peace of our God Jesus Christ be unto us forever.

  ReplyDelete
 14. that is realy noble idea what if mahibere kidusan open a separet account for this cause (renovating & resoreving historic sites)

  ReplyDelete
 15. በወንድሞቻችን አድሮ መልካም ስራን እንድንሰራ ያነቃቃን አምላክ ክብር ምስጋና ይግባው። ለወንሞቻችንም ረዥም እድሜል ከሙሉ ጤና ጋር ይስጥልን። በእውነቱ ወቅታዊ የሆነ ሃሳብ ነው። በል ዺ/ን ዳንኤል ቶሎ ብለህ አካውንቱን ክፈትና አሳውቀን። እኛም የበረከቱ ተሳታፊዎች እንሁን።

  ReplyDelete
 16. መልካም ሀሳብ ነዉ
  ግን ለትችት በማያጋልጥ መልኩ ዬምደረግበት መንገድ ማመቻቸት ያስፌልጋል
  ቸሩ አምላክ ሁላችንንም አንድ ያድርገን
  አሜን
  ድ\ን ፍሬው

  ReplyDelete
 17. Dear All,
  I respect your thoughtful aspiration. However, I disagree on the idea that Dn. Daniel should open an account for this purpose. His role should be limited to showing us the way to help and motivating us towards that objective.

  If Dn. Daniel gets involved in these things, its like giving the devil one big opening for his devilish propaganda. We need to be very very careful.

  Let the monastery or legal associations do this.

  ain't I right?

  Fikre Youhaness

  ReplyDelete
 18. የማይበላ እንዳያስበላ ያብላላDecember 10, 2010 at 3:24 PM

  What a great idea. This will be such a blessing for all of us. I think It will be better to come up with a consistent and continuous plan instead of making it an occasional thing.Here are some suggestions.

  By using Dn. Daniel's blog can we start...
  1. Monthly contribution (or)
  2. Found raising every few months .

  እግዚአብሔር ይስጥህ ኃይለ ገብራኤል !

  ReplyDelete
 19. Dear All

  It great to hear evry one heart beat to contribut his share for our church. As most of you mentioned, I also prefer to support the Muzuim constraction dirctly to their account. When we finish this one Dn Daniel will recommend us . By no means Dn Daniel never open an account...

  ReplyDelete
 20. Dani,
  Yihe Fetena Endayihonibih Segahu.
  Liset Yasebe Ketita Yilak. Alebeleziya Bank account Kefto birun Sebebesebe Endayiluh, weyinm leloch Sebakiyanim Yihich Fer Yizew... Lela Endayiketilu. "Wusha Bekededew Ayidel Yemibal"

  ReplyDelete
 21. የሰው ሃሳብ በመስረቅ ክስ ቢኖር ዲ. በከሰስኩት ምክንያቱም ዲ.ዳን አሁን ፍሪ አፈራ ይሄ ከተሰራ አለበለዚያ የሰው በልቶ ዝም የለምና ቢያንስ አምላካችን በውድ ልጁ ሲያስትምረን ልጆቹ ደግሞ በረከትን በተግባር መተግበር አለብን አምላካችን ሁላችንም ይርዳን አሜን

  ReplyDelete
 22. ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን፤
  የተነሳው ሃሳብ መልካም ነው፣ ልንወያይበት የሚገባም ነው።
  ሁለት ነገሮችን ግን በተናጠል ለይተን መመልከት አለብን፤ እየወጡ ያሉት ጽሑፎች ማህበራዊና ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን ከመዳሰሳቸው አንፃር የእኛ ድርሻ ሊሆን የሚችለው

  1. ገዳማቱንና ታሪካዊ ቅርሶቹን መጠበቅ ለዚህም እርዳታ ማድረግና
  2. ለዲ. ዳንኤል የጽሑፍ አገልግሎት ቀጣይነት የሚቻለውን ድርሻ መወጣት ነው

  በቁጥር አንድ ለተጠቀሰው የታሪካዊና ሃይማኖታዊ ቅርሶች ጥበቃ ለተሳትፎ የሚሆኑ የተለያዩ መንገዶች ይኖራሉ።በእኔ አመለካከት ይህን ኃላፊነት ለዳንኤል ብቻ መስጠት ይቸግራል፤ ይህ እርሱ እየሰጠ ካለው አገልግሎት ጋር በቀጥታ የሚገናኝ አይደለምና።የእርሱ ዋና ተግባር እኛ ልናስተውላቸው፣ልንጎበኛቸው ያልቻልናቸውን ብንጎበኛቸው እንኳን ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ዋጋቸውን ያልተረዳንላቸውን ማህበራዊ እሴቶች ማመላከት ነው።

  ለገዳማትና ታሪካዊ ቦታዎች እርዳታ አድርስልን ብለን ሌላ ሰፊ ጥናትና ጊዜ የሚጠይቅ ኃላፊነት መስጠትን እርሱም የሚስማማበት አይመስለኝም። ይህን እገዛ ለእምነት ተቋማቱ ከሆነ በቤ.ክ መዋቅር ተሰባስበን፣ ለሀገር ቅርሶቹ ከሆነ ደግሞ በሲቪል ማህበራት(ማህበር፣ዕድር..)ማድረግ ይሻላል ባይ ነኝ። ለምሳሌ ለእምነት ተቋማቱ በአጥቢያ ቤተክርስቲያናችን ስም እርዳታ አሰባስበን ባመንበት ተወካይ እንዲደርሳቸው ማድረግ እንችላለን ወይም ከሰበካ ጉባኤ አባላት ጋር ተመካክሮ የተሻለውን መወሰን ይቻላል፤ በቤ.ክ ደረጃ መሰባሰብና መነጋገር ያልቻልን ደግሞ ከምንቀርባቸው ሰዎች ጋራ ተመካክረን እገዛውን ማድረግ እንችላለን፤ ያም ባይሆን (በህብረት ካልሆነ) በግል በ'ኢንተርኔት' የእርዳታ መስመር ባዘጋጁ እንደማህበረቅዱሳን ባሉ ሳይቶች ላይ ገዳማትን ለመርዳት አስተዋጽኦ ማድረግ ይቻላል።

  ዲ. ዳንኤል እዚህ ላይ ከዋና ተዋናይነት ይልቅ ይህን ተመካክረው በህብረት ለሚያደርጉ ምዕመናን የማማከር አገልግሎት ሊሰጥ ይችላል፤ ቦታዎቹን በአካል ተገኝቶ ከማየቱና ችግሩንም በቅርበት ከመመልከቱ አንፃር ማለት ነው።ለዚህ ተዘጋጅተው የተሰባሰቡ ምዕመናን ይህንን አካል ለማገዝ እኛ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሰናል በምን መልኩ ልንቀጥለው፣ ልንፈጽመው እንችላለን የሚል ውይይት ከእርሱ ጋርም ሆነ ከሌሎች ለሁኔታው ቅርበት ካላቸው ሰዎች ጋር በኢሜይልም ሆነ በአካል ሊያደርጉ ይችላሉ፣ ለምሳሌ የእርሱ አድራሻ እዚሁ ብሎግ ላይ ይገኛል።

  በተራቁጥር ሁለት ለተቀመጠው ዓላማ ወይም የጽሑፍ አገልግሎቱን ቀጣይና ፍሬያማ ለማድረግ ግን እንደመጀመሪያው ዓይነት አካሄድ ሊኖረን አይችልም። እገዛው በቤተክርስቲያን ወይም በእርሷ መዋቅር ውስጥ ባለ አካል እንዳይደረግ ጽሑፎቹ መንፈሳዊ ይዘት ያላቸው ብቻ አይደሉም፤ በተለያዩ ማህበራዊ ርእሶች ላይም የግል ምልከታዎች ናቸው።

  በጸሐፊው እንደተገለጸው በግሉ ለኢንተርኔት አገልግሎት የሚያወጣው ወጪ፣ ጽሑፎቹን ለማዘጋጀትና የተለያዩ ምንጮችን ለማግኘትና ለመዳሰስ የሚሰጠው ጊዜ፣ ታሪካዊ ቦታዎቹን በአካል ተገኝቶ ለመመልከትና ለመዘገብ የሚኖረው የመጓጓዣና በጉዞ ቆይታው ወቅት የሚኖርበት ወጪ ወዘተ ጽሑፉን ለመከታተል የሚፈልግን ሰው ሁሉ ይመለከታል። ቀጣይ ታሪካዊ ዳሰሳዎችን፣ የቤ.ክ ውይይቶችን፣ የማህበራዊ ህይወት ክፍተቶችን ለማንበብ ሁሉም የሚችለውን ማድረግ አለበት።

  ይህን ያህል ታዳሚ ያለበት ጽንፍ ያልያዘ የንባብና የመወያያ መድረክ እስካሁን አልነበረምና ቀጣይነቱን ሁሉም የሚፈልገው እንደሆነ ግልጽ ነው።

  ስለዚህ ጸሐፊውንም ማገዝ የጽሑፉን አንባቢያን ሁሉ ይመለከታል። ለዚህ አንዱ አማራጭ በመጀመሪያ ከትንሽ(መጠኑ ተወስኖ)የገንዘብ አስተዋጽኦ ጀምሮ አቅም የፈቀደውን የገንዘብ እገዛ ለማድረግ ፈቃደኛ የሆኑና የሚችሉ አንባቢያን ቁጥር በግልጽ ማወቅ ነው። ለዚህም ብሎጉ ላይ ይህን የሚጠይቅ፣የሚቆጥርና የሚያሳይ አነስተኛ ክፍል ለጊዜው ማድረግ ይቻላል። ከዚህ በኋላ አማካይ ወጪውን ጸሐፊው አስልቶ የአንድ ሰው ትንሹ ድርሻ ስንት እንደሆነ ማሳወቅ ይችላል።ፈቃደኛ የሆነ ሰው ይህን ለግለሰብ እንደተደረገ እርዳታ ሳይሆን ገዝቶ እንደሚያነበው ጋዜጣና መጽሔት አይቶ ለዚህ በተዘጋጀ አካውንት ማስገባቱ ጎጂ ሆኖ አይታየኝም።ልብ አንለውም እንጂ የፈለግነውን ሳናገኝበት ጥቂት የማይባል ገንዘብ ያወጣንበት ብዙ ማህበራዊ ነገር አለ።በትንሹም ቢሆን የገንዘብ አስተዋጽኦ ለማድረግ በተለያየ ምክንያት የማይችሉ አንባብያን ግን ከሁሉ በሚበልጠው በጸሎት ጸሐፊውን ሊያግዙ ይችላሉ።

  ሌላው ለወደፊቱ ሊሰራበት የሚችለው አማራጭ ደግሞ ሁሉም አንባቢያን እጅግ ትንሽ ወጪ እየከፈሉ ብሎጉን የሚያነቡበት(with subscription) መንገድ ማዘጋጀት ነው። ይሄን በዚህ ሰዓት ማድረግ ግን ገና ጸንቶ ያልቆመ የንባብ ልምዳችንን ከጀርባ መግፋት ነውና ለጊዜው ይህን አማራጭ ማዘግየቱ መልካም ነው። ለማንኛውም እንዲህ በአካሄዱ ላይ መወያየቱ የተለያዩ ሃሳቦችን አይቶ ወደአንድ የተሻለ አቅጣጫ ያመጣናል፣ ከሃሳብ ግጭት መልካም ነገር ይገኛል።

  ReplyDelete
 23. ወንድማችን ጥሩ ሀሳብ ነው ያነሳው፤ ነገር ግን አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች እንዳሉት አካውንት በስሙ መክፈቱ እሱን ለፈተና እና ለ አጉል ስም አሳልፎ መስጠት ይመስለኛል። ዳንኤል እራሱ ግን መረዳት ያለበትን ቤተ ክርስቲያን እና እንዴት መርዳት እንደምንችል ቢያመላክተን ለበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን ይረዳናል ብዬ እምናለሁ።

  ReplyDelete
 24. me and my sisters agree with the idea.we will weating how we going to help.


  thankyou and GOD bless!!!!!!!!

  ReplyDelete
 25. ወንድሜ እውነቱን ብለሃል ሁላችንንም ፈጣሪ እውነቱን ያናግረን
  ዲ|ን ዳንኤል በጽሑፉ እያስተላለፈ ያለው መልዕክት ሃይማኖታዊ ሀገራዊ ታሪካዊና ዓለም አቀፋዊ ነው ማወቅ የምንፈልግ አሁንም እያወቅን ነው ወደፊትም በስፋት እናውቃለን ጽሑፉ የሚጠገብ አይደለም በበኩሌ ሁልጊዜ በጉጉት ነው የምጠብቀው እርግጠኛ ነኝ አብዛኛዎቻችን ነን

  ምድርና ሰማይን ያለዋልታ ያቆመ አምላክ በፀጋው ያቁምልን
  ወደ ተነሣሁበት ልመለስና ወንድማችን ጥሩ ሃሳብ ነው ያቀረብከው ድር ቢያብር አንበሣ ያስር እንዲሉ ሁላችንም ያቅማችንን ከልባችን ብንሰጥ
  የሰውን ልብና ኩላሊት መርምሮ የሚያውቅ አምላክ በቸርነቱና በረድኤቱ ያበዛዋል

  ዲ|ን ዳንኤልም የሂሣብ መዝግቡን ከፍቶ የሂሣቡን ቁጥር እንደሚያሣውቀን ባለሙሉ ተስፋ ነኝ


  እግዚአብሔር ሁላችንንም በአንድነት ያቁመን

  ReplyDelete
 26. Dear all,
  I do not agree with the idea of opening an account by a name of Dn. Daniel. Please, think sprituall, but not emotionally. However, I concur with two of my firends who commented, saying that it has to be through an association (like Mahibere Kidusan;other Sunday schools;or other strong associations) that can effectively handle and implement the projects that we want to fund. No one should think of opening an account by a name of individual, including Dn. Daniel.
  Dn. Daniel is a good writer. That is all!!!!!!. He is not a special person, he is serving our church by a gift he gets from God. Period!!!. Please, think spritually, not emotionally.

  Amlak Yitebiken,
  Dhuguma negne ke Bishofitu.

  ReplyDelete
 27. Dear all,
  I do not agree with the idea of opening an account by a name of Dn. Daniel. Please, think spiritually, but not emotionally. However, I concur with two of my friends who commented, saying that it has to be through an association (like Mahibere Kidusan; other Sunday schools; or other strong associations) that can effectively handle and implement the projects that we want to fund. No one should think of opening an account by a name of individual, including Dn. Daniel. It leads those individuals to tempt and ditch in their spiritual life.
  Dn. Daniel is a good writer and preacher among others. No more, no less, that is all!!!!!!. He is not a special person; he is serving our church by a gift he gets from God. Period!!!. Please, think spiritually, not emotionally. We have to think about the impact of our comments on others life.
  ይህ ሙገሳና ሰውን ፃድቅ አድርጎ የማየት አባዘ ነው ብዙ መነኮሳትን፤ ካህናትን፤ ጳጳሳትን እና ሰባኪያንን ለውድቀትና ለውርደት የዳረገው። ቤተ ክርስቲያን እንዳስተማረችን ካነበብን በኃላ ‘ቃለ ሕይወት ያሰማልን፤ ፀጋውን አብዝቶ ይስጥልን፤ መንግስተ ሰማያትን ያዋርስልን’ ማለት ለሁላችንም ይበጃል።
  ስለዚህ፤ ገንዘብ ያልፈተነው ሰው በዚህ ዘመን ማግኘት አስቸጋሪ ስለሆነ በግለሰብ ስም የባንክ አካውንት መክፈት ባታስቡ መልካም ነው። የተለያዩ ጠንካራ ማኅበራት ስላሉ በእነሱ በኩል ወይም በዚያው በአጥቢያው በኩል መርዳት ይሻላል እላለሁ።
  አምለክ ይጠብቀን፤ መልካሙን ሃሳባችንን ያሳካልን።

  ቃለ ሕይወት ያሰማልን፤ ፀጋውን አብዝቶ ይስጥልን ወንድማችን ኃይለ ገብርኤል
  ዱጉማ ነኝ ከቢሾፍቱ

  ReplyDelete
 28. ጥሩ ሃሳብ ነው ነገር ግን ለዳንኤል ስራ እንዳይበዛበትና መጻፉን እንዳይቀንስ

  ReplyDelete
 29. Great initiative but I am afraid it is not a great idea to open bank account in Dn Daniel's name. We can share the bills to keep the blog running and cover other expenses like traveling. In addition, I do not think we lack platforms if we are determined to preserve our history. We can use Mahiber Kidusan, if we have any problem with that we can use "atebiya sebake gubae" ... or other associations with similar initiatives. But I still do believe that we can follow the foot steps of brothers and sisters from Las Vegas and help him keep the blog running. How we can do it? Dn Daniel can help us in that aspect. One good way might be allowing businesses to advertise in his blog. The other way is we can organize ourselves like Las vegas and cover his internet bills. Any other better ways are welcome and let us take the advantage of this initiative to come up with a pertinent solution!

  Cherenetu Yebezalene

  ReplyDelete
 30. First I would like to acknowledge the writer for putting your view forward. But I don’t think you gave enough thought before posting the so called “contribution’. Dear brothers/sister, We have right to say our view, but don’t be ‘FETENA’. If you really get the messages what Dn. Daniel wanted to pass, and really want to help the church, this is not the way. What do you want to contribute for? Do you want to help, the monastery…as you mentioned…ዛሬ ደረስጌ ማርያምን ተመለከትን እንጂ እንደዚህ ያለ እና ከዚህም የባሰ ችግር ላይ ያሉ ስንቶች ይሆኑ??? እኛስ እስከመቼ ነው ኃላፊነታችንን ከንፈር በመምጠጥ የምንወጣው? You are right, he just mentioned what he observed, a few, but there are a lot been not only visited but also proposed with a possible solution. Please go to Mahiber kidusan and ask them, they have a list of monasteries needs our hands in priority order.
  I know, Dn. Daniel is a preacher and a writer who tried his best to help the church and the country. I agree that he is doing his best and his view is very important especially at this time. But as he mentioned in his previous posts, the cause of the current problem of our church is the existence of individuals in a position that are not related to their profession. He is a preacher and a writer, never been a charity. If you want to help him, you can help him and support him in a way that help him continue writing and preaching. He is doing great and no need to divert his direction. There is an organization already doing this……at least Mahibere kidusna (http://www.mkus.org/) since 1992 E.C. and others…
  Dn. Daniel.. I believe you will not be down by this small Fetena. To be honest, I don’t like, the idea even posting this message. Though you are not the author of the current post, you could have avoided posting it. Even now, I will expect you to help those people by directing them to ,‘MK GEDAMAT and ADBART ”.
  Egzio Mahiren……..Yefetna memcha aytawok
  Egziabhe Yirdah

  ReplyDelete
 31. ደብረ ቁስቋም
  በሃሳብህ እስማማለሁ ችግሩ በፅሁፍ ብቻ እንዳይሆን እሰጋለሁ ዲያቆን ዳንኤል ለዚህ መፍትሄ ያጣል ብዬ አላስብም እሱ እንደምንም ቢትባበረን እጅግ በጣም ብዙ ነገር መስራት ይቻላል ብዬ አስባለሁ ምክንያቱም ብዙዎቻችን ተበታትነን በተለያየ ሀገሮች ስለ ሆነ ያለንው በፅሁፍ ሀሳብ ከመዘርዘር የዘለለ ብዙ ልናረገው የምንችለው የለም::እና ወንድማችን እባክህ አንድ ነገር በለንና ሁላችንም የበረከቱ ተሳታፊዎች አድርገን
  አምላከ ቅዱሳን ሀገራችንን ዳርዋን እሳት መሀልዋን ገነት ያርግልን

  ReplyDelete
 32. let us contribute our share for this initiative!

  BY THE WAY DANI WHY DON'T U ADVERTISE THE OTHER BLOGS SUCH AS THAT OF KESIS DEJENE FULL OF THE BASICS OF OUR SALVATION -I FOUND IT FEW DAYS AGO!

  u HAVE TO INFORM OTHER readers!

  ReplyDelete