Friday, December 3, 2010

ለቤተ መጻሕፍትዎ

         የነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ ሥራዎች

                      አሳታሚ  የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ

                     ጊዜ 2002

                      የገጽ ብዛት 186
 
                                                    ዋጋ 35

ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ የሃያኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ኢትዮጵያ የምሁራን ቁንጮ እየተባሉ ይጠራሉ፡፡ በ1878 ዓም በአድዋ ከተማ የተወለዱት ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ኤርትራ ምጽዋ አጠገብ ምንኩሉ በተባለ ቦታ በሚገኝ የሚሲዮን ት/ቤት የመጀመርያውን ትምህርት አገኙ፡፡ ከዚያም በመርከብ ተደብቀው ወደ አውስትርያ ተጓዙና የሕክምና ትምህርት ተማሩ፡፡ በዚያውም የምዕራቡን ዓለም የፖለቲካ ኢኮኖሚ ዕውቀት ገበዩ፡፡

እንደተመለሱ መጀመርያ የዐፄ ምኒሊክ ሐኪም ሆነው ነበር፡፡ የፈረንጅ ሐኪሞች ግርግር አልመቻቸው ሲል ወደ ሱዳን ሄዱ፡፡ በዚያም እያሉ የሱዳንን እና የኢትዮጵያን የልማት እና የኢኮኖሚ ሁኔታ ማነፃፀር ያዙ፡፡

ገብረ ሕይወት ነጻነት ያለ ኢኮኖሚ ዕድገት ዘላቂ ሊሆን እንደማይችል መመርመር ጀመሩ፡፡ ኢትዮጵያ ለብዙ ሺ ዘመናት በነጻነት ብትኖርም የኢኮኖሚ ዕድገቷ ግን ኋላ ቀር ነበር፡፡ በሃያ አንደኛው መክዘ ያለ ኢኮኖሚ ዕድገት ነጻነትን ጠብቆ መሄድ አስቸጋሪ መሆኑን ደረሱበት፡፡

ይህንን ሁኔታ ሲያብሰለስሉ ከቆዩ በኋላ ዐፄ ምኒሊክ እና ኢትዮጵያ የተሰኘውን መጽሐፍ በወቅቱ በመንበር ላይ ለነበሩት ለልጅ ኢያሱ ጻፉላቸው፡፡ ገብረ ሕይወት የኢትዮጵያ ኋላ ቀርነት አንገብግቧቸዋል፡፡ በድንቁርናው የሚኖር ሕዝብ ውሎ አድሮ ይደመሰሳል ብለው አሰቡ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ መንግሥት እና የሕዝብ አስተዳደር በሚለው ሁለተኛው መጽሐፋቸው የመጀመርያውን ሃሳብ ከአውሮፓ እና ከጃፓን እድገት ጋር እያነፃፀሩ ይገልጡታል፡፡

ነጋድራስ ገብረ ሕይወት በነበረው ሥርዓት ላይ ቀጥተኛ እና ጠንካራ ሂስ ሠንዝረዋል፡፡ ኢትዮጵያ መመራት ያለባትን የአስተዳደር እና የኢኮኖሚ አቅጣጫ ጠቁመዋል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖ ሚክስ ፕሮፌሰር የሆኑት ዓለማየሁ ገዳ እንደሚሉት «በደቡብ አሜሪካ በ1950ዎቹ ተፈጠረ የሚባለውን የመዋቅራዊ ኢኮኖሚክስ structural economics ሃሳብ (በመዋቅራዊ ችግሮች ላይ ያተኮረ የኢኮኖሚክስ ትንተና) በተለይ ደግሞ የፕሬብሽንን እና የፕሮፌሰር ሲንገርን ሥራዎች፣ የታዋቂዎቹን የእንግሊዝ ኢኮኖ ሚስቶችን የፕሮፌሰር ፒጉ እና ኬንስን፣ እንዲሁም የፖላንዱን ዕውቅ ኢኮኖሚስት የፕሮፌሰር ሚካኤል ካልስኪን ሥራዎች እርሳቸው ቀድመው ዐውቀው በመጽሐፋቸው ገልጠውት ነበር»፡፡

በ1970ዎቹ የፈረንሳዩ የፖለቲካ ኢኮኖሚስት አርጌ ኢማኑኤል እና የግብፁ አቻው ሳሚር አሚን ታዋቂ ለመሆን የቻሉበትን «ያደጉ እና ያላደጉ ሀገሮች ያልተመጣጠነ ንግድ ሁኔታ ትንተናን» ገብረ ሕይወት ከእነርሱ 50 ዓመት ቀድመው በ1905 አካባቢ በመጽሐፋቸው አቅርበውት ነበር፡፡ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በአውሮፓ እንደ ተፈጠረ የሚነገርለትን የልማት ኢኮኖሚክስ development economics እርሳቸው ቀድመው ደርሰውበት ነበር፡፡ በእነዚህ ጉዳዮች ዝርዝር መረጃ የሚፈልግ የፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገዳን ሳይት ቢመለከት ይጠቅመዋል www.alemayehu.com

ግን ምን ያደርጋል ገብረ ሕይወትን የሚያሳውቃቸው እና በዓለም ላይ የሚናገርላቸው ትውልድ አጥተው እንኳን ዓለም እኛም ሳናውቃቸው ቀረን፡፡

ክስደት ተመልሰው መጀመርያ የምድር ባቡር ኢንስፔክተር፣ ከዚያም በነጋድራስነት መዓርግ የድሬዳዋ ጉምሩክ ኃላፊ ሆነው ሠርተዋል፡፡ ኢትዮጵያ በሰጧት ሃሳብ ተጠቅማ እርሷም ሳትሻሻል እርሳቸውንም ሳታውቃቸው በ33 ዓመት እድሜያቸው በ1911 ዓም ዐረፉ፡፡

ዐፄ ምኒሊክ እና ኢትዮጰያ የታተመው በ1905 አካባቢ ነበር፡፡ መንግሥት እና የሕዝብ አስተዳደር የሚለው መጽሐፋቸው ደግሞ እርሳቸው ከሞቱ በኋላ መጀመርያ በ1916 ዓም፣ በኋላም በ1953 ዓም ታትሞ ነበር፡፡ አሁን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ሁለቱን በአንድ አድርጎ ከባለሞያዎች ትንተና ጋር አሳትሞታል፡፡

ይህንን መጽሐፍ ስታነብቡ ቀደምቶቻችን ከመቶ ዓመታት በፊት ለዚህች ሀገር ምን ያስቡ ምን ይመኙ እንደነበር ታያላችሁ፡፡ ኢትዮጵያ ልጆቿን እንደ ድመት እየበላች ወደ ኋላ ቀረች፡፡ ምዕራባውያን እና ምሥራቃውያም በልጆቻቸው ዕውቀት አደጉ ተመነደጉ፡፡ እኛ ግን ሲኖሩም ሲሞቱም እየቀበርናቸው ይኼው ነጻነታችንን ያለ ብልጽግና ታቅፈነው ቀረን፡፡ እንደ ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ያሉ ሊቃውንት ትልቁ ጥፋታቸው ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ነው፡፡ ይኼኔ የሌላ ሀገር ዜጋ ቢሆኑ ኖሮ በየመማርያ መጽሐፎቻችን እናገኛቸው ነበር፡፡ እንግሊዛዊ እና ፈረንሳዊ ቢሆኑ ደግሞ እንደ ቸርችል እና ደጎል አደባባይ በአዲስ አበባ አያጡም ነበር፡፡

ስታነብቡት ከቁጭታችሁ የተነሣ ቢያንስ ሦስት ፀጉር እንደምትነጩ ርግጠኛ ነኝ፡፡ መጽሐፉን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጽሐፍ መሸጫ፣ በየመጻሕፍት መደብሩ እና፣ በአዟሪዎች እጅ ታገኙታላችሁ፡፡

መልካም ንባብ፡፡

20 comments:

 1. እንደ ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ያሉ ሊቃውንት ትልቁ ጥፋታቸው ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ነው፡፡

  ReplyDelete
 2. Thanks D.N Daniel,

  It is an interesting book I read it. If you read Adam Smith's "An Enquiry in to the Cause and Nature of the Wealth of Nations" and compare with "MENGIST INA YEHIZIB ASTEDADER" You would be amased. By any standard for me Gebrehiwot should have given the same status with A. Smith. I appereciate the effort Proffessor Alemayehu is exerting to promote Gebrehiwot and his works.

  Is the price correct? I think it is 35 Birr.

  ReplyDelete
 3. " ኢትዮጵያ ልጆቿን እንደ ድመት እየበላች ወደ ኋላ ቀረች፡፡ " ምን የሚሉት
  መርገምት ነው።

  ReplyDelete
 4. Thank u!Altadelenem Embete Tehunen.

  ReplyDelete
 5. መጽሐፉ ሊነበብ የሚገባው መጽሐፍ ነው፡፡…………………. እውነት
  ኢትዮጵያ ልጆቿ የመብላት አባዜ አለባት፡፡…………… እውነት
  ሁኔታው ያሳዝናል፡፡…………………. እውነት

  ግን በዚህ ብቻ አላበቃም ይልቁንም ሁላችንንም የምጠይቀው ጥያቄ አለኝ፡፡
  ከእኛ መካከል ይህንን የመበላላት ባህል ያልወረሰ ማን ነው?
  እስኪ ሁላችንም ራሳችንን እንጠይቅና ጓደኞቻችንን ምን ያህል በሥራቸው እናደንቃቸዋለን? አንድ ሰው በሠራው ሥራ ከማመስገን ይልቅ ሕጸጾቹን በመንቀስ የምናጠፋው ጊዜ አይበልጥም? ሀገር ማለት እኮ ወንዙ፣ ተራራው፣ ሸንተረሩ አይደለም፡፡ እኛ ነን፡፡ እናንተ፣ እናንቺ፡፡ ወንዙ ተራራውማ ልጆቿን የምትቆረጥመው ድመትም፣ ለልጇ የምትወጋው ጎሽም ቢኖሩበት ከማኖር ውጪ ተቃውሞ የለውም፡፡ ልጆችን መውለድና ማሳደግም ሆነ ልጆችን መውለድና መብላት የሚችሉት በውስጡ የሚኖሩት ጎሾቹና ድመቶቹ ናቸው፡፡
  አውቀንም ይሁን ሳናውቅ አብዛኞቻችን “ሀገሪቱ እንዲህ አደረገች፤ እንዲያ ዓይነት ርግማን አለባት፡፡” የምንለው “እኔ ከችግሩ ነጻ ነኝ፡፡” “እኔ እንዲህ አላደርግም፡፡” በማለት ችግር ማላከኪያ ፍለጋ ይመስለኛል፤ externalize ለማድረግና ከሥነ ልቡናዊ ጫናው ለመገላገል፡፡

  በየዩኒቨርሲቲዎቻችን የምናየው የባለዲግሪዎች የመናናቅ አባዜ፣ ቤተክህነትን ወደ ቤተ-ትክነትነት የቀየረው የአሽሟጣጭነት በሽታ፣ በወጣቶቻችን ላይ የምናየው ያለመደማመጥና የጭፍን ተከታይነት ነቀርሳ፣ በየቤታችን የሰፈነው “እኔ ዛሬን በልቼ ልኑር” እብደት የመበላላት ክፋቱን እንደወረስነው አያሳይም ትላላችሁ?

  ኔልሰን ማንዴላ “Sometimes it falls upon a generation to be great. You be that great generation.” ይላሉ፡፡ ሁላችንም ራሳችንን እንመልከት፡፡ አባቶቻችን ካወረሱን የድንበር ነጻነት በተጨማሪ የምጣኔ ሀብት ነጻነት፣ የትምህርት ነጻነት ለልጆቻችን ለማውረስ ምን ያህል ዝግጁ ነን? አባቶቻችንን በመርገም ጊዜው እንዳያልፍብን፡፡

  ነገን ታላቅ አድርን "ታላቅ" ተብሎ ለመታወስ እሱም ቢቀር በመጪው ትውልድ ላለመረገም አንተ፣ አንቺ፣ እኛ ምን እየሠራን ነው?

  ReplyDelete
 6. ዳኒ እግዚአብሔር ይስጥልን

  እንደ ነጋ ድራስ ገብረ ሕይወት ከኖሩበት ጊዜ ቀድመው በመነሳታቸው ለአለም የሚተርፍ ሥራቸው ሳይታወቅ ማንነታቸው ሳይገለጥ ያለፉ ምሁራንን ለዚህ ትውልድ ማስተዋወቁ የሚያኮራ ሥራ ነው::

  ReplyDelete
 7. ገብረ ሕይወት ነጻነት ያለ ኢኮኖሚ ዕድገት ዘላቂ ሊሆን እንደማይችል መመርመር ጀመሩ፡፡ግን ምን ያደርጋል ገብረ ሕይወትን የሚያሳውቃቸው እና በዓለም ላይ የሚናገርላቸው ትውልድ አጥተው እንኳን ዓለም እኛም ሳናውቃቸው ቀረን. ኢትዮጵያ በሰጧት ሃሳብ ተጠቅማ እርሷም ሳትሻሻል እርሳቸውንም ሳታውቃቸው በ33 ዓመት እድሜያቸው በ1911 ዓም ዐረፉ፡፡Endiyaw egziabher amlak endene Gebrehiwet yemeselu liqawuntina muhuran edmena tena setito le hagerachew yemiyagelegelubet mewa'el bisetilin, Ethiopian be Economi edget beteley rasiwan tichil neber. Hulum le bego new endale, Egziabher amlak hagerachin ke dihinet maqe be cherinetu endigelagilat kidus fekadu yihunilin. Thanks, Dn Daniel.

  ReplyDelete
 8. By the time when we were the proudest ancient nation in the world, we were the first to give credits. Now it's a different era where we don't give credits. We are the only nation with out appreciations to our people or people around us. " ኢትዮጵያ ልጆቿን እንደ ድመት እየበላች ወደ ኋላ ቀረች፡፡ " I completely agree with this, let us stop doing this. Let us create opportunities for our fellow Ethiopians to shine in this world.

  May GOD guide us the right way forward as He is the Almighty, AMEN!!!

  ReplyDelete
 9. Dear Dn. Daniel:
  Is there a way how to get this books for those who live abroad? Do you know any website to order to? or any phone number to call?
  Can you suggest?

  ReplyDelete
 10. ዳኒ እናመስግናለን!!
  ሌሎችንም ኢትዮጵያ ባታሰውቀንም አንተ እንደምታሳውቀን (ንሴፎ)፡፡

  ReplyDelete
 11. ዲያቆን በእይታ መነፅርህ እየበረበርክ እንድናያቸው
  ስለምታደርገው ተጋድሎህ ብርታትን ይስጥህ
  የማያልቅበት አምላክ ማወቅን ያብዛልህ
  ተከታይ ዳንኤሎችን ለማየት ያብቃን

  ReplyDelete
 12. ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር ይባርክህ እንደ ገብረ ሕየወት ያሉ ታላላቅ ሊቃውንትን ለሕዝብ በማስተዋወቅህ
  ይገርማል እኔ ዩኒቨርሲቲ እያለሁ history of Economic Thought ስማር term paper የሰራሁት የእሳቸው ፅሁፍ ላይ ነበር እና በጣም ተገርሜ ነበር ይህን የመሰሉ ታላቅ ኢኮኖሚስት ሀገራችን በተለይም ዩኒቨርሲቲዎቻችን ለማስተማሪያነት አይጠቀሙበትም ከጥቂት አስተዋይ መምህራን በስተቀር ይህ የሆነበት ምክኒያትም የሌሎቹን እንጂ የራሳችንን ያለመመልከታችን ክፉ አባዜያችን ነው፤፤ አንድ የተባረከ መምህር ነው ለኔና ለክላሱ ተማሪዎች ያስተዋወቀን ሲያስተምረንም According to Gebre-Hiwot እያለ ነበር የሚያስተምረን እሱ ባያስተምረን ኖሮ ገብረ ህይወት ባይከዳኝ የሚባል ኢትዮጵያዊ እንዳለ የማናውቀውቅ የኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች እንሆን ነበር ፤፤
  ሌላ ዩኒቨርሲቲ የተማሩ አቻ ጓደኞቼ እና እኔ የተማርኩበት የተማሩ ነገር ግን እሱ ያላስተማራቸው ተማሪዎች ስለ ገብረ ህይወት የሚያውቁት ነገር የላቸውም ምክንያቱም
  የእሳቸውን ጽሁፍ እንደነ አዳም ስሚዝ፣ ሪካረዶ፣ ኬኔስ፣ ቶማስ ……… ሀገራችን (ዩኒቨርሲቲዎቻችን) ስለማይጠቀሙባቸው ነው፤፤ እኔ ካነበብኩት ቀን ጀምሮ የሚያቃጥለኝ ነገር ነበር ፤፤ ይሄን የመሰሉ modern economist እንኳን አገራችን አለም ሊያውቃቸውና ሊጠቀምበት ሲገባ እንዲህ መሆኑ ያሳዝናል፤፤

  ከአሁን በኋላ እንኳን መጠቀም ብችል ጥሩ ነው እላለሁ ፤ ዳኒ በእውነቱ ይህ ዝክረ ሊቃውንት ነው በርታ ቀጥልበት

  ReplyDelete
 13. ye egziabeher selam kehulachen Gar Yihun Amen::
  Mawek Teru New Selemetetsfacheew Tsehufoch Betam Adenekehalehu Dani Gin Ene Qale Egziabehern Becha Yemetasetemer Yimeselegn Neber Ye Poletica Eweketum Alehe Malet New:: neger Gin Ahun Yerasachenen Bet Mister Hulu Beyedejeselamu Senewerawer Qale Egziabeheru Teresto Menafik Muslimu Eyezelele Mesakiya Honen Ebakihe Endene Qesis Dejene Sheferaw Ye Egziabehern Qal Ketelebet Abatochachenenem Enakiber Kebate Abesha Enhun Bahelachenenem Aneresa Yebekagn Yemejemereya Aseteyayete Bemehonu Dani Tebarek ::

  ReplyDelete
 14. Dn Daniel you are blessed every thing that you teach as according to Ethiopian Ortodox Church. I wish God will give you to you long years with peace and grease.

  ReplyDelete
 15. Dn.Daniel Igziabher Yibarikih keant garim yihun ketechaleh degmo yemeweyaya risi azegajilin na yedenbegnochihin astayet teqebeli.bye

  ReplyDelete
 16. Thank You Dani,
  Keep on the Very Best Recommendation on Ourselves as Ethiopians.
  For your information I bought the book on 85.00 Birr as it was posted at the back.
  God Bless

  ReplyDelete
 17. Igziabiher le D/N Daniel yesetewun birtat ina qininat le hizbe kristiyan hulu yist!!

  ReplyDelete
 18. ዳኒ እንዳልከው መጽሐፉን ሳነብ በጣም ነው የተናደድኩት ምክንያቱም እኛ ከመካከላችን ያሉትን(የነበሩትን) ሳናይ የውጭውን ዓለም ምሁራን የህይወት ታሪካቸውን ሳይቀር ስንሸመድድ መኖራችን ያሳዝናል፡፡ እንደዚህ ትውልዱ በሚገባ ያላወቃቸውን ሀገር በቀል ምሁራንን ማስተዋወቅህን ቀጥልበት፡፡ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፡፡

  ReplyDelete
 19. "Nebey Behageru Aykeberem" Yared From Addis Ababa

  ReplyDelete