ዐፄ ቴዎድሮስ ንግሥናቸውን ያወጁበት ሕንፃ |
አንድ ጥንታዊ ባለ ሁለት ፎቅ ሕንፃ በዚህ ቦታ ይገኛል፡፡ ወደ ሕንፃው በደረጃ በኩል ትወጣላችሁ፡፡ ከከዚያም በደረጃ ወደ መጀመርያው ፎቅ ስትወጡ በፊት ለፊቱ በኩል በረንዳ ታገኛላችሁ፡፡ ወደ በረንዳው ዝለቁ፡፡
እነሆ አሁን የኢትዮጵያን ታሪክ በቀየረ አንድ ታሪካዊ ቦታ ላይ ቆማችኋል ማለት ነው፡፡ እዚህ ሠገነት ላይ ቆመው ነበር ዐፄ ቴዎድሮስ ንጉሠ ነገሥት መሆናቸውን ያወጁት፡፡ የዘመነ መሳፍንት ማብቂያ እና ኢትዮጵያ ወደ አዲሱ ዘመን መሸጋገርዋ የታወጀው እዚህ ቦታ ላይ ነበር፡፡ ዘመናዊው የኢትዮጵያ ታሪክ የሚጀምረው ከዚህ ሠገነት ላይ ነው፡፡
ሠገነቱን ለቅቀን ካህናቱ በሰጡን መሰላል አማካይነት ወደ ላይኛው ፎቅ ወጣን፡፡ የፎቁ ወለል የሆነው እንጨት በዕድሜ ብዛት አርጅቶ ፈራርሷል፡፡ ለታሪክ ታድሎ ታሪኩን የሚረሳ እንደኛ ያለ ማነው፡፡ ይህንን የዘመናዊት ኢትዮጵያ መነሻ ሕንፃ መጠበቅ አቅቶን ይኼው ወለሉ እዚህ እና እዚያ ተለያይቷል፡፡
ዐፄ ቴዎድሮስ ንግሥናቸውን ያወጁበት ሠገነት |
እንዳንወድቅ እየተጠነቀቅን ወደ ላይ ወጣን፡፡ ከአናቱ በተያያዘ ከባድ እና ረዥም ብረት የታሠሩ ሁለት ደወሎች አሉ፡፡ ትልቁ ደወል አሥራ አምስት የፈረስ ጉልበት አለው ይባላል፡፡ ይህንን ደወል ከጀርመን ያመጡት ዶክተር ዊልሔለም ሺምበር ናቸው፡፡ ደወሉ በአሁኑ ጊዜ በዓመት ሦስት ጊዜ ብቻ ይደወላል፡፡ ለኅዳር 21፣ ለኅዳር 25 ለመርቆሬዎስ በዓል እና ለጥር 21 ቀናት፡፡ በጥንት ዘመን ደወሉ ሲደወል ከደረስጌ በግምት 200 ኪሎ ሜትር እስከሚርቀው ወገራ ድረስ ይሰማ ነበር ይባላል፡፡
በትንሹ ደወል ላይ እኔ ለጊዜው ትርጉሙን ያላወቅኩት ጽሑፍ ተጽፏል፡፡ Aloysij Lucenti Funde Romae ይላል፡፡ እስኪ የምታ ውቁት ተርጉሙት፡፡ በትንሹ ደወል ዙርያ እንዲህ የሚል ጽሑፍ ይነበባል louis Del A Strasbourg L’an 1848 faite par
ትንሿ ደወል |
ከደወሉ ሥር ያለው መቆሚያ እንጨት ቃቃቃ ይላል፡፡ በአንድ እጄ ደወሉ የታሠረበትን አግዳሚ፣ በሌላ እጄ ራሱን ደወሉን ይዤ በትልቁ ደወል ላይ በዙርያ የተጻፈውን ጽሑፍ ለማንበብ ሞከርኩ፡፡ ሙሉቀን ባትሪ ያበራል፡፡ እኔ በላዩ ላይ ያደራውን ሸረሪት እየጠረግኩ ጽሑፉን እመዘግባለሁ፡፡
አንድ እግሬ ተንጠለጠለ፡፡ ዝቅ ብዬ አየሁት፡፡ በጨለማው ውስጥ ወለሉ ይታኛል፡፡ ቄሰ ገበዙ «ተጠንቀቅ፤ አደገኛ ነው» ይላሉ ከሥር ሆነው፡፡ በተለይም በስተ ጀርባ ያለውን ጽሑፍ ለማንበብ የግድ እግሬን ለቅቄ ደወሉን በያዘው አግዳሚ ተንጠልጥዬ ማለፍ አለብኝ፡፡ ሙሉቀን እየደገፈኝ ተንጠላጠልኩ፡፡ ቃቃቃ፡፡
ተመስገን፡፡ በሰላም የወለል እንጨቱ ላይ እግሬ ዐረፈ፡፡ ግን እርሱም ቢሆን ቃቃቃ እያለ ምሬቱን አሰማ፡፡ «አትጠግኑን እና ስንፈርስ ዝም ብላችሁ እዩን» እያለን ይሆን አልኩ በልቤ፡፡ የደወሉ ውፍረት ወደ ሃያ ሳንቲ ሜትር ይጠጋል፡፡ ከአግዳሚው ጋር በሚገባ በብረት ታሥሯል፡፡ አግዳሚው ደግሞ ከግድግዳው ጋር ተጎዳኝቷል፡፡
ጽሑፉ እንዲህ ይላል In Honorem Dei AC Beatae Marae birginis Anno Domini MDCCXLIII
በትልቁ ደወሉ ላይ ያለው ጽሑፍ |
ደወሉ ያለበት ሕንፃ ላለፉት አንድ መቶ ዓመታት አገልግሏል፡፡ አሁን ጥገና የሚያ ስፈልገው ይመስለኛል፡፡ እንጨቱ አንዳች ድጋፍ ካልተደረገለት አንድ ቀን እንዳይለቀው እፈራለሁ፡፡ የቅርስ ባለሞያዎች እዚህ ቦታ ላይ ዜግነታዊ እና ሃይማኖታዊ ግዴታቸውን መወጣት አለባቸው ብዬ አምናለሁ፡፡
እንደምንም ከተንጠለጠልንበት ወረድን፡፡ መሰላሉን እየተቀ ባበልን፣ አንዳችን ለሌላችን እየደገፍን ወረድን፡፡
ደረስጌ ማርያምን እንዲህ በቀላ ጎብኝቶ መፈጸም አይቻልም፡፡ የሚነገሩ፣ የሚታዩ፣ የሚዳሰሱ ብዙ ነገሮች አሏት፡፡ የሚገርማችሁ ቤተ ክርስቲያንዋን የሚጠብቃት ኃይለ እግዚአብሔር ነው፡፡ ኢጣልያ ኢትዮጵያን እንደ ወረረ በ1928 ዓም መጋቢት 3 ቀን ለሦስት ሰዓታት ያህል በደረስጌ ማርያም ላይ የቦንብ ናዳ ከአውሮፕላን አወረደባት፡፡ አእንደ ሠለስቱ ደቂቅ ጢሱ እንኳን አልነካትም እነኳን እሳቱ፡፡
በዓመቱ የቦንብ ናዳውን ያዘዘው የጣልያን ጦር አዛዥ ወደ አካባቢው ሲመጣ በቤተ ክርስቲያንዋ ላይ ምንም እንዳልተከሰተ ያያል፡፡ «እኔ ዬስ ጉግሳ ቤተ መንግሥት መስሎኝ እንጂ እንዲህ ያለች ባለ ተአምር ቤተ ክርስቲያን መሆንዋን መቼ ዐወቅኩ» ብሎ ተፀፀተ ይባላል፡፡
ይህ ባለ ሥልጣን ከቤተ ክርስቲያንዋ ዐጸድ ለባንዴራ ማንጠልጠያ የሞሆን እንጨት ሊያስቆርጥ ሲነሣ ካህናቱ «ተው መቅሰፍት ይወር ድብሃል፤ እንኳን ዛፏን ቆርጠው በአጠገቧ በበቅሎ አታሳልፍም» ይሉታል፡፡ እርሱ ግን የሚመጣውን አየዋለሁ ብሎ ማስቆረጥ ይጀም ራል፡፡ ወዲያው በግቢው ውስጥ በበቅሎ ሲያልፍ ከበቅሎው ወድቆ ተሰበረ፡፡ አጃቢዎቹ ወዲያው አፋፍሰው ወደ አንምድ ጥግ ሲወስዱት ሞተ፡፡
1930 ዓም ደግሞ ሌላው የጣልያን ጦር አዛዥ ለሞቱበት ወታደሮች በግቢው መቃብር ሊያስቆፍር ሲነሣ የደብሩ አለቃ እና ሽማግሌዎች ከለከሉት፡፡ በዚህ ተናድዶ ሕዝቡን እፈጃለሁ ብሎ ሲነሣ መብረቅ ሐምሌ 21 ቀን ወርዶ እርሱን እና ባንዴራውን ለይቶ መታው፡፡
ከደረስጌ ወጣሁ፡፡ የካህናቱ ትኅትና፣ የአቶ አደራጀው መስተንግዶ፣ ከኅሊናዬ አይጠፋም፡፡ አሁን የወረዳው መስተዳድር እና የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ሙዝዬም ሠርቶ ቅርሱን ለመጠበቅ በዝግጅት ላይ ነው፡፡ ወደ ስሜን ተራሮች የሚመጡ ጐብኝዎች ሃምሳ ኪሎ ሜትር ብቻ ተጉዘው ሊያዩዋት ይችላሉ፡፡ ከጎንደር ደረስጌ ወደ ሁለት መቶ ኪሎ ሜትር ያህል ብቻ ነው፡፡
ሙዝየሙን ለመሥራት ሁላችንም ብናግዛቸው የትውልድም፣ የሃይማኖትም ግዴታችንን ተወጣን ማለት ነው፡፡ ያለበለዚያ ባዶ ቁጭት ይሆንብናል፡፡ እኔ አበቃሁ፡፡ ወደ ጎንደር ልመለስ ነው፡፡ ሰላም ያግባን፡፡
Egziabher yistilin dani, enagizalen.
ReplyDeleteAmen Dani beselam gibu.
ReplyDeleteEndet yemetasdenik Emebet nat?
Kale hiwot yasemalin.
Egnam Gedetachinin lemewetat lib yesten.
ዳኒ እባክህ ትንሽ ቆይ! አልጠገብናትም ኮ!
ReplyDeleteእግዚአብሔር አምላክ ንጉሠ ነገሥት ዘደረስጌ
ያነውኅ ዓመታቲከ ወያጽጊከ ከመጽጌ
Thankyou Dn. Daniel, It was like watching the History channel without adverts and interruptions, above all with the spiritual incense in it. May God Protect the church and all His children from every evil. We all need to figure out our share in structuring and contributing all the positive efforts.
ReplyDeleteዳኒ ጌታ ይባርክህ
ReplyDeleteስሞኑን የአንተን ጽሁፍ እያነበብኩ በሃሳብ ወደ ጎንደር ሄድኩ
ReplyDeleteባለፈው ጎንደርን ነካክተህ ነበር ወደ ደረስጌ የሄድከው ስለ መ/መ/መድኃኔለም ጉባኤ፣ በአታ ቤተክርስቲያን እና ተማሪዎች፣ ቁስቋም ቤተክርስቲያን ዮሐንስ ቤተክርስቲያን፣ ባሕረ ጥምቀቱ፣ አርባዕቱ እንሰሳ፣ ስላሴ፣ሎዛ ማርያም፣ አበራ ጊዮርጊስ፣አባ ጃሌ ተክለኃይማኖት፣ ልደታ ማርያም ከእነዚህ የተወሰኑትን ለንባብ ታበቃናለህ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ
Dn Dani you make us realy a good turist by your blog. Believe me I can't have such image if I see it fisically. Your view is very impressive and deep that makes us a good turist who accomplish his mission succesfully except the "bereket" you have got from the holy place. Thank you again for your insight and pleace keep it up. I hope we will see many things by you. Amilake kidusan Yitebikilin Amen.
ReplyDeletebetam des yemil new! kale hiwot yasemalwe
ReplyDeletethank you dany. let God pay your rewards.
ReplyDeleteall things you privde us is what is empressive.
dani kedewelu lay yalewun tirgumin sitawukewu post enditadergilin
ReplyDeleteDear Daniel,
ReplyDeleteBundle of thanks!!!!!
Translations...using Google Translate
ReplyDeleteIn Honorem Dei AC Beatae Marae birginis Anno Domini MDCCXLIII
... In honor of the blessed Mara birginis in the year 1743 AD
It seems that the bigger bell was made in 1743 just about 260 years ago
+++ Ejege yemnwedh wendmachn QHy men enlalaen yen betlye endh negn ለታሪክ ታድሎ ታሪኩን የሚረሳ እንደኛ ያለ ማነው? awo lebona yesten beand hasab tesmamten leagerachn le betkirstian asabiwoch yadrgen! esti behekbachw botawoch huulu yehn tewld kednzazanet endaynkan abatoch betselot endasbu negerlen. Antes yedrshan eytwtah new. +++ Ke toronto akbari betseboch
ReplyDeleteMade by Louis Del, in Strasbourg, in the year 1848, Strasbourg is a city in France , very near by to where I live
ReplyDeleteዲያቆን ታሪክን እንደ ወተት እየጋትከን ነው
ReplyDeleteፈጣሪ ፀጋውን ያብዛልህ
God Bless you Dani,
ReplyDeleteI used Google translation :
Aloysij Lucenti Funde Romae (Italian) = Luce Fund Aloysij Romae
louis Del A Strasbourg L’an 1848 faite par(Franch)= Louis Del In Strasbourg The year 1848 made by
In Honorem Dei AC Beatae Marae birginis Anno Domini MDCCXLIII(Latin) = In honor of the Blessed of God and the Mara birginis In the year of the Lord 1743
ዲ/ን ዳኒ እግዚአብሔር ያበርታህ እየከፈልክ ያለኸው ትልቅ መስዋእትነት ነው
ReplyDeletehow can we support the church?
ReplyDeletebereketun yadeleh egna kuch bilen tarikun ayenew
ReplyDeletelelochenem endehu astewawken berta ammlake kidusan yirdah.
ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልህ!
ReplyDeleteበጎንደር ቆይታህ ብዙ ነገሮችን አስቃኘኸን፣ ብዙ ነገርም ተማርን፡፡ በቀጣይም ይህን መሠል ጉብኝት በማድረግ ሌሎች ጽሑፎችን እንደምታስነብበን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
እመቤታችን በደረስጌ ያደረገችው ተዓምር እጅግ አስደናቂ ብቻ ሳይሆን አስተማሪም ነው፡፡ በተለይም የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ምክር ቸል ያልን እና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተገቢውን ክብር የማንሰጥ ሁሉ ቆም ብለን እራሳችንን እንጠይቅ፡፡ አለበለዚያ “ተዘልፎ ተዘልፎ አንገቱን ያደነደነ ድንገት ይሰበራል ፈውስም የለውም” የሚለው ቃል በእኛ እንዳይፈጸም፡፡
ውድ ወንድማችን በጉዟችሁ ሁሉ እግዚአብሔር ይቅደምላችሁ፡፡
እግዚአብሔር በቸርነቱን ይጠብቀን!
ወድ ወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል አግዚአብሔር በረከቱን ያድልህ!
ReplyDeleteበጎንደር ቆይታህ ብዙ ነገሮችን አስቃኘኸን፣ ብዙ ነገርም ተማርን፡፡ በቀጣይም ይህን መሠል ጉብኝት በማድረግ ሌሎች ጽሑፎችን እንደምታስነብበን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
እመቤታችን በደረስጌ ያደረገችው ተዓምር እጅግ አስደናቂ ብቻ ሳይሆን አስተማሪም ነው፡፡ በተለይም የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ምክር ቸል ያልን እና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተገቢውን ክብር የማንሰጥ ሁሉ ቆም ብለን እራሳችንን እንጠይቅ፡፡ አለበለዚያ “ተዘልፎ ተዘልፎ አንገቱን ያደነደነ ድንገት ይሰበራል ፈውስም የለውም” የሚለው ቃል በእኛ እንዳይፈጸም፡፡
ወንድማችን በጉዟችሁ ሁሉ እግዚአብሔር ይቅደምላችሁ፡፡
እግዚአብሔር በቸርነቱን ይጠብቀን!
thank you dn.daniel. it is good that you told us about our own history of our ancestors who kept the church till this day.but i have one fear. people reading this literature are many , including thieves who sold our relics. i think the police there should be alert well that organized teams may come in and destory our history.
ReplyDeleteግሩም
ReplyDeleteእግዚአብሔር ይስጥልን!
የቅርስ ባለሞያዎች እዚህ ቦታ ላይ ዜግነታዊ እና ሃይማኖታዊ ግዴታቸውን መወጣት አለባቸው ብዬ አምናለሁ፡፡
ReplyDeleteዲ/ን ዳኒ እግዚአብሔር ይስጥልን!
ዲ/ን ዳንኤል ቃለ ህይወት ያሰማልን መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን፣ በደባርቅ ሳልፍ ደረሰጌ በመምጣቴ በጣም እንዲቆጨኝ አድርገሃል፡፡ ይኸውም ታሪኩን ካለማወቄ የተነሳ ነው፡፡ እግዚአብሐር ፀጋውን ያብዛልህ፡፡
ReplyDeleteእግዚአብሔር ብሩህ ጭንቅላት ጨምሮ ይስጥህ
ReplyDeleteእኔ እንኳን ትላንት በኢቲቪ 2 አንድ ፕሮግራም ሲተላለፍ ተከታተልኩትና እኔ ስለ ታሪክ ምንም ነገር አላውቅም በተደጋጋሚ ንጉስ ነጋሺ ሲሉ ሰማኋቸው ባለፈውም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እና በኢቲቪ ይህንኑ የፈጠራ ወሬ ያወሩ ነበር ታዲያ ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል የሚባል ተረት አለ የእኛ ቤተክርስቲያን በዚህ ጉዳይ ላይ እጇን አጣጥፋ መቀመጥ እንደሌለባት እና በጠረጴዛ ዙሪያ ተነጋግሮ ታሪክን አስጠንቶ ከዚህ በኋላ ንጉስ የሚባል ነገር እንደሌላቸው መረዳት እንዳለባቸው ይታየኛል ምክንያቱም እያሉ ያሉት ታሪካችንን አገር ይወቀው ነው
ሌላ በጥናቱ እንደተናገሩት ፍትሀ ነገስት እና ሌሎች ብዙ መጻህፍት ከአረበኛ እንደተተረጎሙ ይናገሩ ነበር ይህስ ምን ያህል እውነት የዛሬ ሳምንት ሀሙስ የእኛ ቤተክርስቲያን ሰዎች ስለ ግዕዝ እና ቅዱሳን ስዕል እናቀርባለን ብለዋል እና ስለዚህ ጉዳይ እውነታው ቢታወቅ
ይህንን አስተያየት በዚህ ብሎግ ላይ እንዳታወጣው ምክንያቱም …………….
every thing you fade us is very interesting and timely. Dan, you are doing all the best go go go go. let God be with you and your colleagues.
ReplyDeleteእግዚአብሂር፡ይስጥልን።
ReplyDeleteእንዲት፡ነው፡መርዳት፡የምንችለው?
እግዚአብሔር ይስጥልኝ በአያቶቼ ስሰማው የነበረውን የትውልድ ቦታዬን ታሪክ በጽሁፍህ ስላስጎበኘኽኝ::
ReplyDelete