የደረስጌ ዕቃ ቤት |
የወርቅ ከበሮ |
የደረስጌ ካህናት በአንድ ነገር ይመሰገናሉ፡፡ ደጃች ውቤ ከሰጡት ቅርስ እና ንዋያተ ቅድሳት መካከል አንድም እስካሁን አልጠፋም፡፡ በጣልያን ዘመን እንኳን ቤተ ክርስቲያንዋን ለመዝረፍ የመጣውን ጣልያን ቀጥታ ከዚህ በኋላ አልደርስም እነዲል አድርጋዋለች፡፡ በ1928 ዓም መጋቢት ሦስት ቀን ጣልያን በደብርዋ ላይ ያዘነበው የአውሮፕላን ቦንብ እንኳን እሳቱ ጢሱ አልነካትም፡፡
የወርቅ አክሊል |
የቱሪዝም ቢሮ ባለሞያው አቶ አደራጀው እንደነገረን የደረስጌ ቅርስ ተሠፍሮ ተቆጥሮ በሚገባ የተመዘገበ ነው፡፡ በየዓመቱ ቆጠራ ይደረጋል፡፡ የሚገርመው ግን ቅርሱን ለመቁጠር ሁለት ወር ከአሥራ አምስት ቀን መፍጀቱ ነው፡፡ የአካባቢው ገበሬ ለቅርሱ ከፍተኛ ጥበቃ ነው የሚያደርገው፡፡ ዕቃ ቤቷ እና የያዘችው ዕቃ ሲተያዩ ወርቅን በቀዳዳ ኪስ እንደ ማስቀመጥ ነው፡፡ ከኖራ እና ከድንጋይ ተሠርታለች፡፡ ቅርሱ በቅርስ ላይ ተነባብሮ ተቀምጦባታል፡፡ በቅርቡ ደረጃውን የጠበቀ ሙዝየም ለመሥራት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አቶ አደራጀው ነግሮኛል፡፡ ለማየት ያብቃን፡፡
የወርቅ ጽዋ |
ደጃዝማች ውቤ ደረስጌ ማርያምን ሲሠሩ አንድ ምኞት ነበራቸው፡፡ ዘመነ መሳፍንትን አክትመው በደረስጌ ማርያም መንገሥ፡፡ ለዚህም አቡነ ሰላማን ከግብጽ አስመጥተው ነበር፡፡ እናም የተሟላ ንዋያተ ቅድሳት ለደብሯ አበርክተዋል፡፡ የብር እና የወርቅ ከበሮ፤ ከፋርስ እና ከግብጽ የመጡ ምንጣፎች፤ ከብር እና ከወርቅ የተሠሩ የፈረስ ኮርቻዎች፤ 70 ሳንቲ ሜትር ርዝመት ያላቸው ከጎሽ ቀንድ የተሠሩ ዋንጫዎች፤ ለደብሯ ሰጥተ ዋታል፡፡
ይህም አልበቃቸው 483 ጋሻ መሬት ለቤተ ክርስቲያኑ ከመስጠታቸውም በላይ የአካባቢውን ገበሬዎች ከማንኛውም ግብር ነጻ አድርገዋቸው ነበር፡፡ የሰው ሃሳብ እና የእግዚአብሔር ሃሳብ ይለያያል፡፡ ደጃዝማች ውቤ እና ደጃዝማች ካሣ የካቲት ሦስት ቀን 1845 ዓም ቧሂት ላይ ጦርነት አደረጉ፡፡ ደጃዝማች ውቤም ተማረኩ፡፡ ቤቴል በሚባለው አምባ ላይም ያስቀመጡት ዕቃ ሁሉ ተማረከ፡፡ ዳጃዝማች ካሣም በአቡነ ሰላማ እጅ ተቀብተው በዚህችው በደረስጌ ማርያም የካቲት አምስት ቀን 1845ዓም ዐፄ ቴዎድሮስ ተብለው ነገሡ፡፡
ደጃዝማች ውቤ ሲማረኩ ዐፄ ቴዎድሮስ ሀብትዎን ያምጡ አሏቸው፡፡ ደጃች ውቤም «ይህንን ሁሉ ገንዘቤን ለእግዝትነ ማርያም መስጠቴ የምድር እና የሰማይ መከራ እንዳታሳየኝ ነበር፤ አሁን እንዴት ላድርግ ከእርሷ ይቀበሉ እንጂ፡፡» አሏቸው፡፡ የደጃች ውቤ ሠራዊትም እየሸሸ ደረስጌ ገብቶ ደወለ፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስም «ስለ እግዝትነ ማርያም ብዬ ምሬዋለሁ» ብለው ዐዋጅ ነገሩ፡፡
ምንም እንኳን ደጃች ውቤ በዚያ የመከራ ሰዓት አላዳነችኝም ብለው ቢፀፀቱም፤ ዐጽማቸውን አክብራ፣ታሪካቸውን አኑራ ትውልድ እንዲያስታውሳቸው ያደረገች፣ እስከ ዛሬም በጸሎተ ቅዳሴ እንዲታሰቡ ያደረገች ይህችው የደከሙላት ደረስጌ ማርያም ናት፡፡ የሰማዩንም እንደማትነሣቸው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
ከጎሽ ቀንድ የተሠራ ዋንጫ |
አሁን ከዕቃ ቤቱ ወጥተን ወደ ግራ በኩል እናምራ፡፡
ዉድ ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር የበለጠ ፀጋ ሃብት ያድልህ ፡፡ በእዉነት የኛነታች ን መገለጫ መኩሪያችን የሆኑትን ብርቅየ ሃብቶቸችንን እያሳወከን ነዉ፡፡ በተለይም ደግሞ እናት ቤተክርስቲያን በዉስጧ የያዘቻቸዉ እጅግ አያሌ ሃብት ንብረቶቿ በእንዲህ መልኩ ቢተዋወቁላት ምንያህል ገቢ ልታገኝባቸዉ እደምትችል መገመት አያዳግትም፡፡ነገር ግን አንድ ፈላስፋ እደተናገረዉ" ሁልጊዜ የሰዉልጅ ስላለዉ ሳይሆን ስለሌለዉ ሲያስብና ሲጨነቅ ይኖራል"እንገጨዳለዉ በዉጭ ሃገር ደንቃራ ነገር ራሳችንን አሳዉረን የራሳችንን ዉድ ንብረቶቻችን መመልከት አቅቶናል፡፡እናም የፀጋ ስጦታ ልዩ ልዩ ነዉ መልፈስ ግን አንድ ነዉ እዳለ መፃፍ አንተም በተሰጠህ ፀጋ እግዚአብሔርን ታገለግለዉ ዘንድ ፈቅዷልና ሌሎች ብርቅዮ ሃብቶቻችንን ማወቅ እንፈልጋለንና በርታልን፡፡ በዚህ አጋጣሚ ዳኒ እኔ ሰዉ ከእቅልፉ ሲነሳ በስመ አብ እዲል እና ደግሞ የስራየ መጀመሪያ የአንተን ሳይት መመልከት ነዉ ፡፡ከዚያም አልፎ ለታሪክ ለቀሪ ትዉልድ ፕሪት እያደረግሁ ሁሏንም ነግር አያስቀመጥሁ ነዉ፡፡
ReplyDeleteሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን
አሜን
ገ/ስላሴ ከአራት ኪሎ
ቃለ ህይወት ያሰማልን መምህር፡፡
ReplyDeleteግን እንዲያው እነዚህን የመሳሰሉ የቤ/ክ እና የአገር ንዋየ ቅድሳት
እነ ብልጣሶርና እነ ይሁዳና እነ እንትና …..
አይተው ደረስጌ እንዳይሰለፉ እፈራለሁ፡፡
እግዚአብሔር ይጠብቅልን፡፡
ሰው እነዚህን የሚያስደንቁ ንዋየ ቅድሳት ብቻ ተመልክቶ ክርስቲያን የሚሆን ይመስለኛል፡፡
ReplyDeleteHow far is the distance b/n Deresge Mariam and Gonder towns? And how is the town of Deresge. Please elaborate a bit.
ReplyDeleteThanks a lot.
A reader.
Dejen
ReplyDeletewud wendmachin dn. Dani kale hiwot yasemalin rejim edme ena tsega yadililin.betekristianachin kemetshaf yezelele lemanawk bizu asawikehinal ena ye-ewkket balebet kubre bahiri liul egziabiher ewketun abzito yistilin AMEN. gin wendimachin yih tarik ena yebetekristianitu habt letelat tikoma endayhonibin tsihufun sitcheris leanbabian mikir azel tsihufih enditilegsen ematsenalehu.
ዲ. ዳንኤል እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡
ReplyDeleteስዕሎቹን ብቻ አይቼ ጠገብኩኝ፡፡
ዲ/ን ዻኒ እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልህ። የሚገርምህ የማላውቀው ቦታ አሁን አንተ ስተርክልኝ ቦታው በአይምሮዬ ወስጥ ተሳለ።
ReplyDeleteall things are good. But one thing makes me frietened. that is publicising of church properties and valuable materials,which may lead for theft and we lost it after the information date.
ReplyDeleteso, confidential possession is, i think, vital for those endangered materials, which our church maintained still now.
however, your looking is interesting.
Uuuuuuuuuu
ReplyDeleteDn Daniel
Your briefing is good but, you are making the treasures at risk. you know that there are gang groups who loot treasures and sell in exile with big money. Please write this kind of things once the muzuim is constructed and and every itm be secured in it. Unless you will be asked by history in future.... Melkam ken
ዲ. ዳንኤል እግዚአብሔር ይባርክህ፣ እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልህ።
ReplyDeleteዲ/ዳኒ እግዝእትነ ማርያም ትጠብቅህ አንተ ዳገት ወተህ ቁልቁል ወርደህ ሙቀቱንና ብርዱን ታግሰህ የሰበሰብከውን እኔ እቤቴ ቁጭ ብዬ ለማየት ቻልኩ፡፡ አሁንም ደግሞ ደጋግሞ አምላከ ቅዱሳን የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክ!
ReplyDeleteዳኒ አንድ ነገር በጣም ፈራሁ ቅርሶቹን ሳይ እኔ እንዳየሁት ጠላት አይየው፡፡ የትላንት አባቶቻችን ቅርሶቻችንን ከውጭ ጠላት ጠብቀው በክብር አውርሰውናል፡፡ ዛሬ ደግሞ እኛ ግሩም የውስጥ ጠላት ሆነናልና ያስፈራል፡፡ የደረስጌ ካህናትንና ገበሬዎችን ልቦናቸውን አይለውጥባችሁ፡፡ በክብር የወረሳችሁትን በክብር ለማውረስ ያብቃችሁ ብያለሁ
አሁን ከዕቃ ቤቱ ወጥቼ ወደ ግራ በኩል ለማምራት ተዘጋጅቻለሁ፡፡
ዳኒ አንተም ቅርስ ስለሆንክ ከቅርስ ዘራፊዎች እመብርሃን ትጠብቅልን
ReplyDeleteIt is very interesting to know it but I am scared to death we ganna lose those expensive items and we can`t replace them.I am so proud of those who belive in God and kept his stuff upto date.stil I am worried about those who worship money they ganna steal it.
ReplyDeleteG from mn ,usa
Dear deacon dani,Thankyou for your explanation.
ReplyDeleteThe precious & respected materials are not secured by humanbeings,but by God willingnes,so continue your explanation.
May God respect you & blessing Ethiopia.
Teshager
እግዚአብሔር አምላክ ክብርና ሞገስ ይሁንልህ። ገና ብዙ ታሳየናለህ። እመ አምላክ መንገድህን የቀና ታድርግልህ። እንዲህ ያለ የክብር እና የማንነት ታሪክ በዚያ ቦታ ይኖራል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር። አንተን የሰጠን አምላክ ክብር ምስጋና ይድረሰው።አሜን።
ReplyDeleteGood and interesting as usual. May God be with you and your family and give our leaders true ethiopian mind so that they think about their country in the right way.
ReplyDelete