በደረስጌ በር አጠገብ ያሉት እድሜ ጠገብ ዛፎች |
ብርዳማው የመካነ ብርሃን ሌሊት አለፈ፡፡ ከጠዋቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ተነሣን፡፡ የወረዳው የባህል እና ቱሪዝም ጽ/ቤት ባለሞያ የሆነው አደራጀው አካባቢውን የሚጎበኙትን ሁሉ ከቡና በሚመረጠው ፈገግታ ለማስተናገድ ያለው ዝግጁነት ያስቀናል፡፡ እርሱ መካነ ብርሃን ላይ ባይኖር ኖሮ ጉብኝታችን ሁሉ ውኃ ይበላው ነበር፡፡
የደረስጌ ማርያም ካህናት በግብርና ሥራ ራሳቸውን የሚያስተዳድሩ ናቸው፡፡ ክህነትን እንደ ሥራ ማየትኮ በቅርብ ዘመን የመጣ ጠባይ ነው፡፡ ቀደምቶቻችን እያረሱ የሚቀድሱ እና የሚያስተምሩ ነበሩ፡፡
የቤተ ክርስቲያኑ ዓምደ ወርቅ |
ቤተ ክርስቲያኗ ከአንድ ኮረብታ ግርጌ ትገኛለች፡፡ ዙርያዋ በኖራ በተመረገ የድንጋይ ግንብ ታጥሯል፡፡ የግቢው ውስጥ በጥንታውያን ዛፎች የተሞላ ነው፡፡ በሩ እንደ ጎንደር ዘመን በሮች በሰቀላ የተሠራ ነው፡፡ ከበሩ በስተ ግራ በኩል ታቦት ሲወጣ በሚያርፍበት ቦታ ላይ ከመቶ ዓመታት በላይ የሆናቸው የግራር ዛፎች ለታሪክ ታዛቢነት ቆመዋል፡፡
ገባን፡፡
ከወርቅ የተሠራው የደረስጌ ጉልላት |
ቤተ መቅደሱ ክብ ሆኖ አናቱ ላይ የወርቅ ጉልላት አለው፡፡ በሮቹ እስከ ሦስት ሜትር በሚደርሱ ግዙፍ ግንዲላዎች የተሠሩ ናቸው፡፡ የመቅደሱ ወለል ከቅርቀሃ እና ከጠፈር በተሠራ አቴና የተሞላ ነው፡፡ አቴና በጥንቱ የቤት አሠራር ጥበባችን ወለሉን ለማልበስ እንጠቀምበት የነበረ ዘዴ ነው፡፡
ደረስጌ ጽርሐ ጽዮን ማርያም ትክሏ በአድያም ሰገድ ኢያሱ ዘመን መሆንዋን የደብሩ ሽማግሌዎች ይገልጣሉ፡፡ ነገር ግን አሁን ያለውን ቤተ መቅደስ አሠርተው የደበሯት እና ዛሬ ያላትን ክብር የሰጧት በ1810 ዓም ደጃዝማች ውቤ ናቸው፡፡
የቤተ ክርስቲያኑ ጥንታዊ ኮርኒስ፣ በልዩ የእጅ ጥበብ የታነፀ |
እንጨቱ ተፈልፍሎ ልዩ ልዩ ዲዛይን የወጣለት የደረስጌ መስኮት |
ደጃዝማች ውቤ ትግራይን እና ስሜንን ሲገዙ ዋና መናኸርያቸውን ደረስጌ ላይ አድርገው ነበር፡፡ በዚያ ቦታ ላይ ቤተ መንግሥት እና የመሣርያ ግምጃ ቤት ነበራቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያንዋን ለማሠራት ከሀገር ውስጥ እና ከባሕር ማዶ ዕውቅ መሐንዲሶችን አሰባስበው ነበር፡፡ ከውጭ ከመጡት መካከል ጀርመናዊው ዶክተር ዊልሔለም ሺምበር ይጠቀሳል፡፡
የደብሩ ክልል ሦስት ጋሻ መሬት ሲሆን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ በሁለት ቅጽር እና በዐጸድ የተከበበ ነው፡፡ የመጀመርያው ቅጽር በጎንደር ከተማ እንደሚገኘው የዐፄ ዮሐንስ ቤተ መንግሥት በዕንቁላል ቅርጽ የተገነባ ግንብ ይገኝበታል፡፡
ወደ ቤተ መቅደሱ ስትዘልቁ ደጃዝማች ውቤ ያስሳሉትን ሥዕል ታገኛላችሁ፡፡ የቤተ መቅደሱ በር እና መስኮት ለእያንዳንዱ እንጨት ተፈልፍሎ ጌጥ እየወጣለት የተሠራ ነው፡፡ ያንን እንጨት ፈልፍሎ በላዩ ላይ ከመቶ ዓመት በላይ የሚዘልቅ ጌጥ የሚሠ ራው ማሽን የት ሄደብን? ከበሩ ግራ እና ቀኝ ሁለት ነጋሪቶች አሉ፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስ ሲነግሡ ያስጎሰሟቸው ይሆኑ ይሆን?
በዚያ ዘመን የተሠራው ለማኅሌት እና ቅዳሴ ጊዜ መብራት ይሰጥ የነበረው የዘይት መቅረዝ ዛሬም ለታሪክ ይገኛል፡፡
ዐፄ ቴዎድሮስ የነገሡት በዚህ ነጋሪት ይሆን? የተቀመጠበት ወለል ነው አቴና የሚባለው |
አቡነ ሰላማ እና የግብጹ ፓትርያርክ አቡነ ቄርሎስ፣ በደረስጌው ሰዓሊ ዓይን |
የመቃብር ቤቱ ግድግዳው እና ጣራው በታሪካዊ ሥዕሎች የተሞላ ነው፡፡
የደረስጌ ማርያም የግድግዳ ላይ ሥዕሎች |
ደጃዝማች ውቤ ኃይለ ማርያም፤ በደረስጌው ሰዓሊ ዓይን |
ደጃዝማች ውቤ ቤተ ክርስቲያኗን ያሠሩት ከኖራ፣ ከድንጋይ እና ከጭቃ ነው፡፡ ሽማግሌዎቹ እንደ ሚናገሩት ኖራው ሰባት ዓመት ይቀበራል፡፡ በየጊዜውም ውኃ ይጠጣል፡፡ በሰባት ዓመቱ ይወጣና ከጭቃው ጋር እየሆነ ድንጋዩ ይያያዝበታል፡፡ ከዚያ በኋላ ንቅንቅ የለም፡፡ ኖራው ተቀብሮ የቦካበት ቦታ ለታሪክ ዛሬም ድረስ ይታያል፡፡ ሲሚንቶ እንዲህ ተወድዶ ወገባችንን ከሚቆርጠን ምነው ይህንን ነባር ቴክኖሎጂ አዳብረን ብንጠቀምበት? ደጃዝማች ውቤ እንዴት ባለ ልዩ ውበት እንዳሠሯት አንደኛውን የዐፄ ቴዎድሮስ ዜና መዋዕል የጻፈው ወልደ ማርያም «ከባሕር ወዲህ እንደ እርሷ ድንቅ ተብሎ የሚነገር ሥራ የለም» ሏታል፡፡
የደጃች ውቤ መቃብር |
አሁን ከቤተ መቅደሱ እንውጣ፡፡ በስተ ቀኛችን ወዳለው ዕቃ ቤትም እናምራ፡፡
god bless u dani
ReplyDeleteI am facing a font problem ... I can't read the Amharic font ... please help
ReplyDeleteyedresge kahnat American hager kihnet agelglot sayhon profation endehonu besemu menyelu yihon???
ReplyDeleteG from MN,USA
ያንን እንጨት ፈልፍሎ በላዩ ላይ ከመቶ ዓመት በላይ የሚዘልቅ ጌጥ የሚሠ ራው ማሽን የት ሄደብን?eqa bet west yigegne yihone?
ReplyDeleteDn Danie tebark!!!
ያንን እንጨት ፈልፍሎ በላዩ ላይ ከመቶ ዓመት በላይ የሚዘልቅ ጌጥ የሚሠ ራው ማሽን የት ሄደብን?eqa bet west yigegne yihone?
ReplyDeleteDn Danie tebark!!!
ዳኒ ከመላው ቤተሰብህ ጋር አምላክ ይባርካችሁ ፡፡ ከካናዳ
ReplyDeleteGOD BLESS U.KALEHIWOT YASEMALN!
ReplyDeleteDani I can't see the pics that u post with the blogs so how can I get to see them ?
ReplyDeleteturizem mendenew ende yemiseraw ways tarik beztobachew priority list awtetew new alyas ensum ayawkutm ?
ReplyDeleteMekane birhan lesira heje neber.gin min yadergal yih hulu endale yesemahut ketemelesihu behuala neber. Bikochegnim Dn. Danielin ameseginalehu. God bless YOU.
ReplyDeleteThank you Dn Daniel. I hope that there are enough safety measures in place to protect the golden 'gulelate', especially after today.
ReplyDeleteEnameseginalen Dn. Daniel... agelgilotikin Egziyabiher abizito yibark!!.. Yework amdu ena Yework Gulilatun ezi bota lay metkesu mnalbat lesergogeboch ena leleboch endemetekom enadayihon kewedihu kelay wendimachin endalew dehininetahiwn maregaget yehulachinim alafinet mehon alebet.
ReplyDeleteክህነትን እንደ ሥራ ማየትኮ በቅርብ ዘመን የመጣ ጠባይ ነው፡፡ ቀደምቶቻችን እያረሱ የሚቀድሱ እና የሚያስተምሩ ነበሩ፡፡
ReplyDeletebizu neger endinak hadirgekal. betam new yeminameseginew. kezi belay yemiserabetm edime yistlin.
ReplyDeleteነንገጉሰሴ
ReplyDeleteዳኒ ተባረክ ፍርሐተ እግዚአብሔር እንጅ የጠፋብን ጥበቡ ዛሬም ሊኖር ይችል ነበር፡፡
ድኒ እድሜ ከጤና ጋር እግዚአብሔር ይስጥህ። ብዙ ነገር እያስወከን ነው። አሁን ጎንደርን ለመጎበኘት ሳስብ ምን ማየት እንዳለብኝ በደንብ ተረድቻለሁ።
ReplyDeleteበአንድ ወቅት በግቢ ጉባኤ ሳለን ምሥጢራተ ቤተክርስቲያንን ያስተምሩን የነበሩት ካህን ምሥጢረ ክህነት ላይ ደርሰው ሲያስተምሩን ከቆዩ በኋላ ወደ ማሰሪያው ላይ “ልጆች ክህነት የትርፍ ሰዐት ሥራ አይደለም፡፡” አሉን፡፡ ዲያቆን ዳንኤል የጠቀሳቸው ካህናትም የሚቀድሱት ከእርሻ በተረፋቸው ሰዐት እንዳይመስለን አደራ! እነርሱ እርሻን የሚያርሱት ከክህነት በተረፋቸው ሰዐት ነውና፡፡
ReplyDeleteአንድን ገበሬ ካህን “ሥራዎ ምንድነው?” ብትሏቸው
“ግብርና፡፡” ይሏችኋል፡፡
“እርስዎ ምንድነዎት?” ብትሏቸው ግን መልሳቸው
“ካህን” የሚል ነው- ክህነት ማንነታቸው እንጂ ሥራቸው አይደለምና፡፡
እንዳለመታደል ሆኖ ቤተክህነትና ቤተመንግሥት በይፋ ከተፋቱ በኋላ ክህነት እንደ አገልግሎት ሳይሆን እንደሥራ እየተቆጠረ በመምጣቱ ከጽሕፈት ቤቱ ጀምሮ እስከ ቤተመቅደስ ድረስ የሚታየውና የሚሰማው ሕገወጥነት ወረሰን፡፡ ክህነትን ምድራዊ ሽልማት የምንሽላለምበት፣ “ለሕያውና ተወዳጁ” ሥራችን “ሐውልተ ስምዕ” የምንገትርበት፣ ለሹመት የምንጋደልበት፣ “ለትርፋማነት” የምንተጋበት አደረግነው፡፡ "ምነው?" ቢሉ ሥራ ነዋ! ያላመኑትን ከማስተማር ይልቅ ሳይሆን ያመኑትን አማረርን፡፡ በዚሁ ከቀጠልን “ማኔ ቴቄል ፋሬስ” በእኛ ላይ መደገሙ አይቀርም፡፡ ለነገሩ “ለጥፋት ያሏት ከተማ ነጋሪት ቢጎስሙባትም አትሰማ፡፡” እንደተባለው ተረት ሆኖብን ነው እንጂ የያዝነው ጎዳና ለእኛም ቤተክርስቲያንም እንዳይበጅ እናውቀዋለን፡፡ ምን ይሻለናል በፈጣሪ?
ዲ. ዳኒ አንተ በ3500 ትራንስፓርትና ሌሎች ወጪዎች የጎበኘሀቸውን እኛ በነፃ እነኮመኩማለን፡፡ምናልባትም ሄደን ጎብኝተንም ቢሆን በአንተ ገለጻ የተረዳነውን ያህል መረዳታችንን እጠራጠራለሁ፡፡በረከቱን ያብዛልህ
ReplyDeleteበቬጋሶች ቀናሁባቸው፤ እኛስ ሚኒሶታውያን ምን ይጠበቅብን ይሆን፡፡ብርታቱን ይስጠን
አዜብ ዘሚኒሶታ
dani betam egziabehere yisetelen ye egziabehere fekade hono hedan lemayete eskeminichel ante silasegobegnehen emebetachen tibarekehe.
ReplyDelete