የስሜን ተራሮች |
ከጎንደር ተነሣን፤ እኔና ሙሉቀን ዘጎንደር፡፡ አንዳንዶቹ የልደታ ምክትል መልአከ ስብሐት ይሉታል፡፡ የሰበካ ጉባኤው ምክትል ሊቀ መንበር ስለሆነ፡፡ የምንጓዝበትን መኪና ያመቻቸልኝ የአዲስ አበባው ሙጨ ነው፡፡ ምንም እንኳን 3500 ቢያስሰክፉንም፡፡ ከጎንደር ወደ ጃናሞራ መውጫው በር ብልኮ ይባላል፡፡
መኪናችንን አስፈታትሸን እና ነዳጅ ሞልተን ከብልኮ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ተነሣን፡፡ እስከ ዳባት ያለው መንገድ ከጎንደር ተራሮች አንፃር እንደሜዳ የሚቆጠር ነው፡፡ ሜዳ በሌለበት ዳገት ሜዳ ይሆናል ሲባል አልሰማችሁም፡፡
ፀሐይ እና ብርድ ለማሸነፍ ይፎካከራሉ፡፡ በመካከል እኛ ካፖርት በመልበስ እና በማሞቅ ዕንቆቅልሽ እንሠራለን፡፡ የወገራ ወረዳ ዋና ከተማ የሆነችውን አምባ ጊዮርጊስን አለፍናት፡፡ መኪናዋ እህም፣ እህም፣ እህም እያለች ታዘግማለች፡፡ ቻይና እዚህም አለች፡፡ ይህንን የስሜን መንገድ እንደ ጨጓራ ትገለብጠዋለች፡፡ ከጎንደር ወደ ደባርቅ የሚወስደው መንገድ በአዲስ መልኩ እየተሠራ በመሆኑ በተለዋጭ መንገድ እንፈጨዋለን፡፡
ዝንጀሮ አቋረጠን ምን እንሆን ይሆን? |
በምቃራ በኩል አልፈን 830ኛው ኪሎ ሜትር ላይ ደባርቅ ላይ ወረድን፡፡ ምሳ የሚበላው እዚያ ነው፡፡ የወረዳው የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ምሳ ጋበዙን፡፡ ሜዳው እዚህ ያበቃል፡፡ መንገዱም ለሁለት ይከፈላል፡፡ ወደ ሽሬ እና ወደ ጃናሞራ፡፡
ሊማሊሞን ዳገት ወጣሁት በዳዴ
እንደ ዘጠኝ ወር ልጅ አርግዤህ በሆዴ
የጭላዳ ዝንጀሮ ማኅበር |
ከደባርቅ ወጣን፡፡ የደባርቅን ጉልት ገበያ አቋረጥናት፡፡ የጃን አሞራን መንገድ ያዝነው፡፡ ታዋቂው ስሜን ብሔራዊ ፓርክ የሚገኘው በዚህ ነው፡፡ አንድ ሃያ ኪሎ ሜትር እንደሄድን ወደ ፓርኩ ክልል ገባን፡፡ መኪናችንን እህህ ማለት ትታ፣ አዬዬ እያለች ማማረር ጀመረች፡፡ ለዝንጀሮ የተዘጋጀን ተራራ ይህች ያረጀች መኪና በምን ልቧ ትውጣው፡፡ በግራ በኩል ከሰማይ ጋር የተሳሳመው ተራራ ይታያል፡፡ በቀኝ በኩልም የርሱ መንትያ ተገትሯል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች የገበሬዎች እርሻ ቢታይም አካባቢው ግን ከሰው መኖርያነት ነጻ የሆነ ይመስላል፡፡
የቧሂት ተራራ |
እኛን ሲያዩ ወደ ዳገታቸው ሸሸት ሸሸት አሉ፡፡
ከእነርሱ እልፍ ብሎ ለቱሪስቶች የተዘጋጁ ሎጆች አሉ፡፡ እዚያው ሲጎበኙ ውሎ፣ እዚ ያው አምሽቶ እዚያው ማደር ይቻላል፡፡
መኪናችን እያማጠች እያ እየተመሰጥን ጉዞ ቀጠልን፡፡ እነሆ ዋልያ፡፡ ሁለት ጓደኛሞች የት እንደቆዩ አይታወቅም ከተራራው ላይ እየተጫወቱ ወረዱ፡፡ እኛ ስናያቸው መንገዱን አቋርጠው ፈረጠጡ፡፡ ካሜራዬ ግን አንዱን ሲዘል ያዘችው፡፡ ዋልያን ከነ ሕይወቱ ሳየው የመጀመርያዬ ነው፡፡
ስሜን ተራራ በኢትዮጵያ ታሪክ ዝናው ከፍ ያለ ነው፡፡ የጎንደር ሥርወ መንግሥት መሥራች ዐፄ ሠርጸ ድንግል ከአካባቢው ፈላሾች ጋር ብዙ ውጊያዎች አድርገውበታል፡፡ የጦር አዛዣቸው ዮናኤል በ1572 ዓም ረዳኢ ከተባለው የፈላሾች መሪ ጋር የተዋጋው እዚህ ቦታ ነው፡፡ በኋላም በ1579 ዓም ጎሼን ወግቶበታል፡፡
ማደን ክልክል ስለሆነ በካሜራ አደንናት |
በግራ በኩል በማዶ የጠመጠመ የሰሜን ካህን መስሎ ራስ ደጀን ይታያል፡፡ እኔ ወደዚያ ለመድረስ ጊዜ አልነበረኝምና በሩቁ ተሳልሜው አለፍኩ፡፡
አሁን ቧሂትን እያለፍነው ነው፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስ ከደጃች ውቤ ጦር ጋር ተዋግተው ያሸነፉበት አስቸጋሪው ተራራ ነው ቧሂት፡፡ የደጃች ውቤ ጦር በጃን አሞራ ሲከትም ደጃዝማች ካሣ «ስሜን ስሜን እነግርሃለሁ» ብለው ነበር አሉ ወታደር ያስከተቱት፡፡ እንዳሉትም ቧሂት ላይ ተዋግተው ስማቸውን ስሜን ላይ ነገሩት፡፡
ዋልያ ከነ ቤተሰቡ፣ ከሩቁ |
መካነ ብርሃን ገባን፡፡ ከቀኑ አሥር ሰዓት ሆኗል፡፡ የዚህ ሀገር ፀሐይ ደግሞ ካልገባሁ እያለች ነው፡፡ መብራት እነደ ልብ ባለበት ከተማ ቀስ ብላ የምትገባው ፀሐይ እዚህ ምን ልሁን ብላ ትቸኩላለች፡፡ «ሰው ሆይ አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ» ለተባለው ቃል የሰነድ ማስረጃ መስለናል፡፡ አሁን ተሠርተን ገና ጭቃችን የደረቀ ይመስላል፡፡
የመካነ ብርሃን ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን የሠርክ ጉባኤ፣ በትልቅ ዋርካ ሥር |
እኛና ውኃ ተገናኝተን ስንለቃለቅ አስራ አንድ ሰዓት ሆነ፡፡ በመካነ ብርሃን ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን የሠርክ ጉባኤ ለመካፈል ወደዚያው ሄድን፡፡ እንዲህ ዓይነት የሠርክ ጉባኤ ካየሁ ብዙ ዘመን ሆኖኛል፡፡ ከአንድ ትልቅ ዋርካ ሥር በተጋደሙ እንጨቶች ምእመናኑ ተሰብስበዋል፡፡ እዚያው እየተማርን እዚያው መሸ፡፡
ብሉ ነገ ደረስጌ ላይ እንገናኝ፡፡ ደኅና እደሩ፡፡
በነገራች ላይ
ከዳያል አፕ ኢንተርኔት ወደ ኤቪዶ እንድሸጋገር የላስ ቬጋስ ልጆች ድጋፍ በማድረጋቸው ይሄው ፎቶዎችን ትኮመኩማላችሁ፡፡ እስኪ እግዜር ይስጣችሁ በሏቸው፡፡
anten kale hiwot yasemalen! le lasvegas lejoch degemo EGZIABHER yestachew.
ReplyDeleteቬጋሶችን እናመሰግናለን!!!
ReplyDeleteኢትዮጵያ ውስጥ እየኖርን ኢትዮጵያን ከመጻሕፍት በዘለለ ለማናውቃት ለኛ በጣም መልካም ነገር አቀብለኸናልና እናመሰግናለን፡፡ ግን ተጨማሪ ቀልብ ገዢ ፎቶዎችን እንጠብቃለን፡፡
leul au
ReplyDeleteegiziabher yistilin.
.........benatih! benatih! benatih!
esty degmo yehone menfesawi liboled neger asnebiben!
lik ende "venesia" ayinet...yemiastemir
Antenina lasvegasochin EGZIABHER YISTILINNNNNNNNN
ReplyDeleteበጣም እናመሰግናለን። ዳኒ ፎቶዎቹ ግን ትናንሽ ከመሆናቸዉ የተነሳ በደንብ ማየት ተስኖናል፣ ክሊክ ስናደርጋቸዉ ሙሉ መጠን የሚሆኑበትን አካሄድ ብትጠቀም ጥሩ ይመስለኛል። መድሀኒአለም ሰላሙን ያብዛልህ።
ReplyDeleteዳኒ ጉዞህን የበረከት ያድርገው አንተ ብትደክምም እኛ ተጠቀምን እግዚአብሔር መጨረሻህን ያሳምረው እንዳልከውም ላስ ቪጋሶች ሊመሰገኑ ይገባቸዋል እግዚአብሔር በረከቱን ያብዛላቸው አንተንም ያበርታህ ያጽናህ
ReplyDeleteAD
መምህር ዳኒኤል የተመቸ እንዲሁም ትልቅ ቁምነገር ያለዉ ታሪክ አነሳህ
ReplyDelete"ይኼው ታቦት ነው በኋላ ዘመን ጎንደር ላይ ተተክሎ አደባባይ ኢየሱስ የተባለው፡፡ ታቦቱ የመጣው ከወላይታ መሆኑን የዐፄ ሠርፀ ድንግል ዜና መዋዕል ይናገራል፡፡ እንግዲህ ጎንደሬም ወላይቴ፣ ወላይቴም ጎንደሬ ነው ማለት ነው፡፡ "
እናመሰግናለን ዳንኤል! ታሪክ ለማያዉቁ፡ ወይም ለሚክዱ ሰዎች የዐፄ ሠርፀ ድንግል ዜና መዋዕልን ማጣቀሻ ቢያደርጉት ጥሩ ይሆን ነበር። ግን ሊያነቡት ፈቃደኛ ይሆኑ ይሆን?
ለማንኛዉም በርታ። ጻፍ። መጻፍ የታሪክም የፈጠራም ማህጸን ነዉ።
ሸንቁጥ አየለ
Memhir Kale Hiwot Yasemalin.
ReplyDeleteGOD Bless Lasvegas contributers that is the true root of Tewahido.
We shoud use the recent technology as much as posible.
እግዚአብሄር ይስጣችሁ…..በወጣው ይተካ…..አንተም ቃለ ህይወት ያሰማልን…አሜን!! harry from Addis
ReplyDeleteወንድም ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር አምላክ አብዝቶ ይባርክህ። የላስ ቬጋስ ልጆችን ደግሞ አምላከ ቅዱሳን ልዑል እግዚአብሔር በቸርነቱ ይጎብኛቸው። በጣም በሚገርም ሁኔታ አንተ እና ምክትል መልአከ ስብሐት ሳታስተውሉኝ ያለ ምንም ወጪ መጋራት እናንተ በተከራያችሁት መኪና አብሬያችሁ ሰጓዝ ፣ እናነተ የተጋበዛችሁትንም ምግብ አብሬ ስመገብ (ለካስ ምግቡ ቶሎ ቶሎ ያልቅብን የነበረው ... ግን እንዳትለኝ)፣ ያያቸሁትን ሳይ፣ የታዘባችሁትን አብሬ ስታዘብ፣ ስትታጠቡእኔም ስታጠብ ከዚያም በመካነ ብርሃን ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን የሠርክ ጉባኤ ለመካፈል ወደዚያው ስትሔዱ አብሬ ሄጅ እኔም ተካፍዬ...... አዚሁ ቢሮዬ ውስጥ ቁጭ ብዬ::
ReplyDeleteThanks alot. Egziabher Yitebikih. U have so many visions. This is really a unique gift to U from God. Keep it up.
ReplyDeleteR we going to miss Limalimo? How can I come and see it before it is sold with dollar!?
It is good journey. Hope you will come to end of GUATSIYON, the historic place of KIBUR HADIS Alemayehu's Fikre eskemekabir.
ReplyDeleteዳኒ- ተዋህዶን የሰሜን ኢትዮጵያውያን ብቻ አስመስለው በማቅረብ ለማታለልና የቤተክርስቲያንን ልጆች ከጉያዋ ለማስወጣት ለሚፋትሩ መናፍቃን «እንግዲህ ጎንደሬም ወላይቴ፣ ወላይቴም ጎንደሬ ነው ማለት ነው፡፡»ብለህ ያቀረብከው የአደባባይ ኢየሱስ ታሪክ ጥሩ መልእክት ነው፡፡
ReplyDeleteዳኒ፡ ፎቶዎቹ እየታዩን ስላልሆነ እንዳልከው መኮምኮም ባንችልም ማየት ስለሚችሉት ሰዎች ግን ቬጋሶችን እግዚአብሜር ይስጥልን
+++Yetwededk wendmach Qhy! bejegu E/abher Amlak yetabk I'm feeling I'm there! May God Bless Lase Vegas volunteers! This what expect from all of us! Yedershachnen mewetat!Beselam yemalsh. Ketoronto akbari betseboch +++
ReplyDeletethank u Vegas and to u daniel i really like what u are writhing and u have the eagle eye.
ReplyDeletedani antenm khy vegasochen degmo beweta yeteka beyalehu
ReplyDeleteDn Dani be-egrochih eytguwazen,be eynocheh egnam eytmelketen seminen eyqagnen new!!!Egziabher endih be-ant adro eystmaren new mesgan yigbaw,antenem tisgwen yabzaleh.muluqine zegonderenem amsgenelen.endihum lequzoh miqanat yetbaberuhen hulu egziabher yistelen elalhu.ye-lasvegas lijcoh egziabher yibarkachew.keep it up!!!!
ReplyDeletei have got the oportunity to see your blog only recently.iam very happy with that since i am living abroad for the moment.what you have been doing so far is great but may be dangerous for our enemies in and outside of the church!
ReplyDeletebe careful foryou as an individual and for mahbere kidusan as association.as i said befor i discovered this blog accidently while i was searching for spritual songs and the like...
i have seen blogs and sites targeting you and MK criticizing,defaming and insulting...
i think you may be fully aware of that
since the rulunig party and his agents inthe church are have a history of dividing and demolishing their enemies,you have to take charge of your responsibility of safe guarding the association from those memebers (new and regular) that may act as secretily to fulfil the objectives of your enemies!
may God be with you and mk
wher is my comment??/
ReplyDeleteግሩም ጽሁፍ ነው፡፡ቃለ ህይወት ያሰማልን፡፡
ReplyDeleteግን ካሜራ ማን ብትሆን የሚያዋጣህ ይመስለኛል፡፡
አደራ ጥር ላይ ስለማገባ የፎቶውን ነገር በአንተ ላይ ጥዬዋለሁ፡፡
ላስ ቬጋሶችን በርቱ በዚሁ ቀጥሉ ‹‹ ድር ቢያብር አንበሳ ያስር ››
ነውና ሁሉም በተሰጠው ፀጋ ይተባበር እንላለን፡፡
I really Appreciate for your Information.Lets God be with you our Bro.
ReplyDeleteበጣም ደስ የሚል አቀራረብ ነው ወንድማችን። ላስ ቬጋሶችንም ከለልብ እናመሰግናለን በወጣ ይተካ ብያለሁ። ዲ/ን ዳንኤል በ "ለቤተ መፃሕፍትዎ መድረክህ" በእኛ ቤተ ክርስቲያነ እምነትና በካቶሊክ እምነት መካከል ያለውን መሰረታዊ ልዩነት በግልፅ የሚያስተምር መፅሐፍ እባክህን ጠቀቁመኝ። እግዚአብሔር አምላክ ፀጋውን ያብዛልህ።
ReplyDeleteለሁሉም እግዚአብሔር ይስጥ
ReplyDeleteሁሉም እንዲሳተፍ የሲም ካርዱ ቁጥር ቡገለጽ ሁሉም እንደ አቅሙ አስተዎጾ ያደርጋል የሚል እምነት አለኝ፡፡
አመሰግናለሁ!
ዳኔ በርታ ምን እላለው ከእንግዲ ወይ ጃን አሞራ ለካ እንዲህ ነስ
ReplyDeleteየወርቅ ክበሮ አለ አሉ ደረስጌ
ደግሞ አጤ ቴድሮስ የነገሱ በዚሁ ነው ይባላል
በጣም ጓጓው
k dawntawen chicago
Thanks Dani, we follow U and visit northern mountains via Ur journey’s article (የጉዞ ማስታወሻ (ትረካ)),
ReplyDeleteAdditional information about Limalimo, Elders of the area believed that, Limalimo who is the designer of that admirable road was a university student at the time when he designed it. He prepared the design for the in fulfillment of his first degree in engineering department.
Comment:- U told us that both Dabat & Debark lies 830km far from the capital. How could that be? If U started your journey from a historic land Gondar, You find Dabat first after you drive 75 km and Debark 25km after Dabat. so,…
- If you have time I will advise you to see another impressive road construction on the road to Shire known as Dagusit which is not valued by many & swallowed by the grace of Limalimo. It found around 30 km from Limalimo or Dibbahir(rural village lies at the bottom of Limalimo) on the road to the head of Ethiopian Monasteries-Abrentant MEDAHINIALEM-Waldiba.
- I was surprised when I see u in using e-video at one moment when I get U occasionally.I got the answer now- ላስ ቬጋሶች በሰማይ ቤት ሰይጣንን ከሳሽ እናንተን ተከሳሽ እኛን ምስክር አድርጎ ያቁመን፡፡
- Finally, we are waiting for you anxiously to hear (read)more about St. Yared Monastery so long as it is near to Janamora or Semien Park. In fact the shortest way to St. Yared is through Maitsemry which is the boarder small town between Amhara & Tigray regions.
Dn Daniel(memehirachin) Anten Kale hiwot yasemalin yeagelgilot Zemenehin yarzemileh kenemelawu betesebeh yitebekeh ,guzohin yebereket yadergeleh.Bizu yemalelewu wagah Besemay endihon selemefelig newu.
ReplyDeleteYe Las Vegas wendimoch amlake kidusan yenantenim yeagelgilot wagachehun besemay yikfelachewu uih tiu agelgilot newu ena.
Las vegas christians did two things,
ReplyDelete1. they helped dani get a good internet connection
2. they showed us how we can cooperate for good cause.
I feel that we still have brothers and sisters who are experts in IT. I Hope people can make it even better with full featured interactive site so that we will be able to download pictures, audio and video documents,submit our resources and share...degmo lebererket!!
Thanks Dn Daniel, and brothers and sisters from Vegas. Hope the initiative from Vegas will be picked up by others.
ReplyDeleteThanks a lot for being kind and so nice.Many of us from the central, east &west region of Ethiopia have no detail idea about the nort of part of our beloved country.Please take my heartfull appreciation for helping us to visit our country from distance.I also highly appreciate your effort to make this long distance trip and your willingness to share all what you get with your fellowship citizens. I hope, when this site is fully equipped with A/V we all can learn a lot from you. I would like to send my words to those brothers & sisters who resides in vegas for their ultimate supprt, let the almighty god bless them and ofcours Daniel Kibret.
ReplyDeleteThanks
Nazareth (12/3/2010)
Gobeze Lebe Yalew Lebe Yebel!!!!
ReplyDeleteYezegeyew.