Sunday, November 21, 2010

ለቤተ መጻሕፍትዎ

                                              የፒያሳ ልጅ

ደራሲ -  ፍቅሩ ኪዳኔ

አከፋፋይ - ዓይናለም የመጻሕፍት መደብር

ዋጋ - 70 ብር

የታተመበት ዓመት - 2001 ዓም

ከጋሽ ይድነቃቸው ተሰማ ጋር ለብዙ ዘመናት የሠራው፤ የመጀመርያውን የስፖርት ዘገባ በሬዲዮ በቀጥታ ያስተላለፈው፣ በኢንተርናሽናል ስፖርት ፌዴሬሽኖች የፕሬስ ኮሚሲዮን እና በ1986 የሜክሲኮ የዓለም ዋንጫ የፊፋ የአንዱ ምድብ የፕሬስ ኃላፊ የመጀመርያው ጥቁር፤ የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ስፖርት ጋዜጠኞች ማኅበራት መሥራች ፍቅሩ ኪዳኔ በሚያምር የአራዳ ቋንቋ ስለ ፒያሳ ልጆች በ457 ገጾች ያወራናል፡፡

ከሃምሳ ዓመት በፊት ፒያሳ አካባቢ የነበሩ ሲኒማ ቤቶች፣ ሻሂ ቤቶች፣ ጮርናቄ ቤቶች፣ የልብስ መደብሮች፣ ጠጅ ቤቶች እና ጠላ ቤቶች የማናውቀውን ሁሉ ያስኮመ ኩመናል፡፡ በዚያ ዘመን ታዋቂ የነበሩትን ፊልሞች ያስቃኘናል፡፡ የዘመኑን አራዶች ፈሊጥ፣ የዘመኑ የእግር ኳስ ዳኞችን አሠራር፣ የተጫዋቾቹን አለባበስ እና አጨዋወት ከጎናችሁ ሆኖ የሚያወጋችሁ በሚመስል አቀራረብ ጽፎታል፡፡

የጥንቶቹ ልብስ ሰፊዎች፣ የመጀመርያዎቹ የአዲስ አበባ ፀጉር ቆራጮች፣ የመጀመርያዎቹ ታክሲዎች እና የታክሲ ሾፌሮች ምን እንደሚመስሉ በፎቶ ግራፍ ያሳየናል፡፡ የመጀመርያዎቹ ባለ ሱቆች፣ ባለ ሽቶ ቤቶች፣ ባለ መኪኖች፣ ባለ ቡና ቤቶች እነማን ነበሩ? ለሚለው መልስ ይሰጠናል፡፡

በታሪክ ብቻ የምናውቃቸውን የሀገራችን ትልልቅ ሰዎች የልጅነት ትዝታ፣ ምን ይጫወቱ እንደ ነበር፣ ሲጫወቱ ስንት ብር እንደተበሉ ሳይቀር ይተርክልናል፡፡

አቶ ፍቅሩ በ188 የዓለም ሀገሮች የዞረ ምናልባትም ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ሊሆን ይችላል፡፡ የየሀገሩን ሁኔታ በዘመኑ ከነበረው የኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር እየተነተነ ያስኮመኩመናል፡፡

ቁጭት እንዲያድርብን የዘነጋናቸውን ታላላቅ ሰዎች ያነሣል፣ የሠሩትን ሥራ ያዘክራል፣ ቅርሶቻችን የት የት እንዳሉ ያሳስበናል፡፡ የፒያሳ ልጅ፡፡

አዲስ አበባ እየተቀየረች ነው፡፡ ልደታ እና አራት ኪሎ በአዳዲስ ሠፈሮች እየተተኩ ነው፡፡ ነገም ፒያሳ በአዳዲስ ግንባታዎች እና ሠፋሪዎች ይቀየር ይሆናል፡፡ እንደ አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ መጻሕፍት ያሉት መዛግብት ምናልባት ብቸኛ መረጃዎቻችን ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከነ ሙሉ ትዝታቸው፡፡

አልታደልንም እንጂ አቶ ፍቅሩ ዛሬ በመላ ኢትዮጵያ ኮሌጆች እና ትምህርተ ቤቶች እየዞረ የማነቃቂያ ንግግር እንዲያደርግ፣ ሥልጠና እንዲሰጥ፣ ምክር እንዲለግስ፣ በሌሎች ጉዳዮችም እንዲጽፍ ማድረግ ነበረብን፡፡ ትልቅ ሰው ማውጣት እንጂ በትልቅ ሰው መጠቀም መቸም አልቻልንበትም፡፡

መጽሐፉ በየአዟሪዎች እጅ ይገኛልና አንብቡት፡፡ እርሱን ያላነበበ ሰው ከኢትዮጵያ ታሪክ አንድ ትልቅ ቁራጭ ይቀርበታል፡፡

መልካም ንባብ


12 comments:

 1. you are really wonderful.i like your blog and i have seen many changes in my reading habits.you save me from ignorance .tanks my Hero Markos

  ReplyDelete
 2. "ትልቅ ሰው ማውጣት እንጂ በትልቅ ሰው መጠቀም መቸም አልቻልንበትም፡፡"
  ከትልቅ ሰው ለመጠቀም ስለምፈልግ መጸአፉን ገዝቼ የማነበው ይመስለኛል። ደስ የሚል ጊዜ ከራሱ ልምድ በመነሳት ያለ ክፍያ ስለመጽፍት የሚነግረን ማስታወቂያ ሰሪ። ቆሎም እየበላው ቢሆን በምታወጣው ልክ ለመሄድ እሞክራለው። የተሻለ ልምድ ያላቹ እባካቹን(ቆሎ ከመብላት)። ዳኒ እናመሰግናለን።

  ReplyDelete
 3. Dani I know about FIKRU KIDANE he is a good sport journalist and now he is coming an autor thanks for locate the book with good suggestion. before this time i listen about fikru book from VOA it is a good work of his.I am Very thankyuuuuuuuuuuuuuu.
  ..........PLEASE CONTINUE YOUR SELECTION & INDICATE.

  ReplyDelete
 4. ትልቅ ሰው ማውጣት እንጂ በትልቅ ሰው መጠቀም መቸም አልቻልንበትም፡፡
  really. books are not enoughly available for readers in relation to their price tag. the price of books is high that can not be aforded by our society.our reading exeperience is poor. for this or another reason we lose our Icons. In other countries govermnet institutions and others concered in education, business and market, history and heroesim envite elders who had the fate of the event and exeperiences give their knowledge to the current generation. by nature huamn being percieve what they see and listen than what they read. so, ትልቅ ሰው ማውጣት በትልቅ ሰው መጠቀም መቻል አለብን፡፡
  thank you dany.

  ReplyDelete
 5. thnks Dn. Dani

  how to get the book abroad?

  ReplyDelete
 6. "ትልቅ ሰው ማውጣት እንጂ በትልቅ ሰው መጠቀም መቸም አልቻልንበትም፡፡"
  ከትልቅ ሰው ለመጠቀም ስለምፈልግ መጸአፉን ገዝቼ የማነበው ይመስለኛል። ደስ የሚል ጊዜ ከራሱ ልምድ በመነሳት ያለ ክፍያ ስለመጽፍት የሚነግረን ማስታወቂያ ሰሪ። ቆሎም እየበላው ቢሆን በምታወጣው ልክ ለመሄድ እሞክራለው። የተሻለ ልምድ ያላቹ እባካቹን(ቆሎ ከመብላት)። ዳኒ እናመሰግናለን።

  ReplyDelete
 7. የእኔ አሳብ በመንፈሳዊ ኮሌጅ ተፈጠረ ሚባለው ነገር ላይ ነው፡፡ምክንያቱም ይህ የቤተ ክርስቲያናችን ትልቅ ተቐም ነው፡፡
  ትናንትና በጀርመን ራዲዮ የኮሌጁ አስተዳደር በሰጠው አሳፋሪ መልስም በእጅጉ አዝኛለሁ፡፡የቤተ ክርስቲያን የወደፊት እጣም ያስጨንቀኛል፡፡እኔ እንደተረዳሁት የተማሪዎቹ አሳብ ትምህርት ቤቱ ውስጥ በዘመን ርዝማኔ የሸበተውን ኢ መንፈሳዊና ኢ ፍትሃዊ አስተዳደር አጎፍረን አልያም እያበጠርን አንቀጥልም የሚል ይመስለኛል፡፡ይህ ደግሞ የሁላችንም ጥያቄ ነው፡፡በእርግጥም እንዲህ ያለው ነገር መላጨት ይኖርበታል፡፡ለቤተ ክርስቲያን የምናስብም ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ከዓላማው ጎን ልንሰለፍ ይገባል እላለሁ፡፡

  ReplyDelete
 8. I like Fikru Kidane.I read as he was the first and front line contributer for Ethiopia Sport. YE ETHIOPIA SPORT MESRACH ABATOCH KE ENE YIDNEKACHEW GAR ABATACHIN NEW.
  By the way his voice is still shouting in my ears.His reading style has beuty.Sheger Radio chaweta program lay lemin aykerbim?
  Shegeroch yihin kalaregachihuma gud new!!!
  Getachew

  ReplyDelete
 9. where r u? we miss u too much please keep ur promise nothing almost full week.

  ReplyDelete
 10. Dear Ato Fikur kidane thankyou very much for the Book "Ye Pyassa lejoch" really it very interesting book. and we expect more from pyassa lojoch you started it other will continue ere ye pyassa lojoch tenesu... and also i expect from the old sefer's Autobiys tera lejoc, kuas meda, mesalemai, kera, Arat kilo, Jal meda, sidest kilo where are u gays pls write and let us read the old stories and to transfer to our lejoch. have a nice day.

  Jemal ke Pyassa

  ReplyDelete
 11. I just finished the book and find out HOW WE LOST OUR GREAT PEOPLE,GREAT COUNTRY .I HIGHLY RECOMMEND ALL ETHIOPIAN TO READ THE GREAT GENERATION OF OUR TIME. THANK YOU FIKRU.I CANT WAIT TO READ 'BOLETIKA',GOD BLESS FIKRU AND HIS FAMILY.
  BRAVO !! YEPISSA ENA YEEETHIOPIA LEJE!!!!!

  ReplyDelete