Wednesday, November 17, 2010

መልስ በሞባይል

እስኪ እዚያው ጎንደር ውስጥ አንድ ቀን እናሳልፍና ዐፄ ፋሲል ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ቁጭ ብለን ከመምህራኑ ጋር እናውጋ፡፡

እኔ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ስማር በፈተና ሰዓት የሆነ አንድ ነገር ሁሌም ትዝ ይለኛል፡፡ በአንድ ክፍል ውስጥ አንድ ጎበዝ ተማሪ ነበር፡፡ ከእርሱ ቀድተው ለማለፍ የተዘጋጁ ደግሞ ብዙ ተማሪዎች፡፡ ታድያ ፈታኙ መምህር ጥብቅ ሆነና ዓይኑን እንደ ሰጎን ዓይን ተከለባቸው፡፡ ሊያነቃነቅ አልቻለም፡፡ የፈተና ማብቂያው ሰዓት ደግሞ እንደ ጎርፍ እየተንደረደረ ይነጉዳል፡፡

ከጎበዙ ተማሪ አጠገብ ያለው አንዱ ተማሪ አንዳች ነገር ዘየደ፡፡ መልሱን ከጎበዙ ተማሪ ቀዳና በአንድ ቁራጭ ወረቀት ላይ አሰፈረው፡፡ ከዚያም ከእርሱ ወንበር ባሻገር ያለው ተማሪ መምህሩን ለጥያቄ ጠራው፡፡ መምህሩ ጎንበስ ብሎ ያኛውን ተማሪ ሲያስረዳ ይኼኛው ተማሪ የመልሱን ወረቀት ከመምህሩ ጀርባ ላይ በፕላስተር ለጠፈው፡፡

ከዚያማ በየቦታው መምህሩን ለጥያቄ መጥራት ሆነ፡፡ እዚያ ሄዶ ጎንበስ ሲል አንዱ ይቀዳል፡፡ እዚህ መጥቶ ጎንበስ ሲል ሌላው ይቀዳል፡፡ እያጎነበሰ ሲያስቀዳ ዋለ፡፡ በመጨረሻም ተማሪዎቹ ከተሰጣቸው ጊዜ ቀድመው ጨረሱና የፈተናውን ወረቀት ይዞ ወደ ቢሮው ሄደ፡፡

የፈተናውን ወረቀት ቢሮው አስቀምጦ ወደ መምህራኑ ሻሂ ቤት ሲገባ ነበር መምህራኑ ሁሉ በሳቅ የፈነዱት፡፡ አጅሬ ተንቀሳቃሽ ሰሌዳ ሆኖ መልስ ሲያስገለብጥ ማርፈዱን አላወቀውም፡፡

ከዚህ የሚመሳሰል አንድ ወግ አንድ መምህር ቀጥሎ ያወጋናል፡፡

ተማሪዎችን ለዓመቱ የመዝጊያ ፈተና ፊዚክስ ሊፈትን ወደ አንድ ክፍል ይገባል፡፡ የፈተናውን ወረቀት አድሎ አንዱን ጥግ ይዞ ተፈታኞቹን ይመለከታል፡፡ ማንም ቀና የሚል የለም፡፡ ፈተናው ከብዷቸዋል መሰል ሁሉም አቀርቅረዋል፡፡ ለመኮራረጅ የሚሞክር ቀርቶ የሚያስብ የለም፡፡ እፎይ አለና ወንበር ስቦ ቁጭ አለ፡፡ አልፎ አልፎ በድንገት እየተነሣ ቢያያቸውም የመኮራረጅ ጠባይ አይታይም፡፡

ደነቀው፡፡ እዚህ የተመደበው በጣም በመኮራረጅ የታወቀ ክፍል ነው ተብሎ ነው፡፡ እርሱ ደግሞ የሚኮርጅን ተማሪ በመያዝ በት/ቤቱ ውስጥ የተዋጣለት ነው ይባላል፡፡ ዛሬ ግን ያለ ቦታው እንደተመደበ ገባው፡፡ አለያም ተማሪዎቹ የጠባይ ለውጥ አምጥተዋል፡፡

ብቻ የአንድ በሽተኛ ተማሪ የሳል ድምጽ ይሰማል፡፡ እየደጋገመ ይሰላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ አንዴ ስሎ ያቆማል፡፡ ሌላ ጊዜ ሁለት ሦስት ጊዜ ይስላል፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ባለ ማቋረጥ ይስላል፡፡ አልፎ አልፎ ደግሞ ጉሮሮውን እንደ መጠራረግ ያደርጋል፡፡

ፈታኙ መምህር ይህንን ተማሪ ያውቀዋል፡፡ በት/ቤቱ ውስጥ አሉ ከሚባሉት ጎበዝ ተማሪዎች አንዱ ነው፡፡ አንጀቱ ተንሰፈሰፈ፡፡ በዚህ አስቸጋሪ ሰዓት መታመም አልነበረበትም አለ፡፡ ምን ያድርገው፡፡ እየሄደ ያጽናናዋል፡፡ «አይዞህ ጊዜ ካነሠህ እጨምርልሃለሁ» ይለዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እንዲህ ባለ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ለመፈተን መምጣቱ አስደንቆታል፡፡

ልጁም እየሳለ፤ ተማሪዎቹም ጸጥ ብለው፤ መምህሩም በተማሪዎቹ ሥነ ምግባር እየተደነቀ የፈተናው ሰዓት አለቀ፡፡ የፈተናውን ወረቀት ሲሰበስብ በሁሉም ላይ የደስታ ስሜት ያነብብ ነበር፡፡ ያ በሽተኛ ተማሪ አንኳን ያንን ያህል ሰዓት የሳለ አይመስልም ነበር፡፡

እነሆ የፈተናው ጊዜ አበቃ፡፡ ከአንድ ሳምንት በኋላ ተማሪዎቹ ወረቀት ለመውሰድ መጡ፡፡

ጉድ ተባለ፡፡ የአንድ ክፍል ተማሪዎች ፊዚክስን ተጫወቱበት፡፡ ሁሉም ከ95 በላይ አመጡ፡፡ ፊዚክስ እንዲህ ተደፍሮ አያውቅም ተባለ፡፡ ፈታኙ መምህር ተጠየቀ፡፡ ፈጽሞ የመኮራረጅ ነገር አለማየቱን ምሎ ተገዝቶ ተናገረ፡፡ በመምህራኑ መካከል በድጋሚ መፈተን አለባቸው የለባቸውም የሚል ክርክር ተፈጠረ፡፡ ምንም ዓይነት የመኮራረጅ ነገር ሪፖርት ሳይደረግ እንዴት አድርገው ድጋሚ ይፈትኑ፡፡

የተማሪዎቹ ውጤት ጸደቀ፡፡

ከወራት በኋላ የፈተናው ምሥጢር ተገለጠ፡፡ ለካስ ያ በሽተኛ ተማሪ እያስኮረጀ ኑሯል፡፡ ተማሪዎቹ ቀድመው ተመካክረዋል፡፡ አንድ ጊዜ ሲስል «ኤ»፣ ሁለት ጊዜ ሲስል «ቢ»፣ ሦስት ጊዜ ሲስል «ሲ»፣ በረዥሙ ሲስል ደግሞ «ዲ» ማለቱ ነው፡፡ በተማሪዎቹ መካከል የውጤት ለውጥ የመጣው ይህንን ምሥጢራዊ ኮድ በመተርጎም እና ባለመተርጎም መካከል ነበር፡፡

እነዚህ ታሪኮች ዛሬ ጊዜ አልፎባቸዋል፡፡ መኮራረጅም ሃይ ቴክ ሆኗል፡፡ አሁን እነዚሀን የሚያነሣ ፋራ ብቻ ነው፡፡

የሠለጠነውን የመኮራረጅ ታሪክ ልንገራችሁ፡፡

ለጎበዝ ተማሪ አስቀድሞ ይከፈለዋል፡፡ ሞባይሉም የሆለት መቶ ብር ካርድ ይሞላለታል፡፡ ከዚያም ሁሉም ሞባይሉን ከፍቶ መጠበቅ ነው፡፡ እርሱ ሠርቶ እንደጨረሰ በሞባይሉ መልሱን ቴክስት ያደርገዋል፡፡ ከዚያ እድሜ ለቴክኖሎጂ እያሉ መገልበጥ ነው፡፡

ይሄንን ነገር መምህራኑ ነቁ፡፡ ከዚያም ሞባይል እያስቀመጣችሁ ግቡ ተባለ፡፡ ሴቶቹ ደግሞ መሸፋፈን መብታችን ነው አሉ፡፡ ሞባይሉን ብብታቸው ውስጥ ከትተው ማዳመጫውን ደግሞ በመሸፋፈኛቸው ውስጥ ያስገቡታል፡፡ ያ መከረኛ ጎበዝ ተማሪ ቶሎ ቶሎ ይሠራና አንድ አሥራ አምስት ደቂቃ ሲቀር ሰጥቶ ይወጣል፡፡ ከዚያም ውጥ ሆኖ ስልክ ይደውላል፡፡

እቱም በመሸፋፈኛዋ ውስጥ በሰካችው ማዳመጫ መልሱን እየተቀበለች ትሞላና ፈገግ ብላ ትወጣለች፡፡ መምህራኑ እንዳጫወቱኝ ሞባይሉን በፓንታቸው ሥር ሸሽገው የሚገቡ ተማሪዎችም አሉ፡፡

አሁን መምህራኑን የሕግ አለመኖር እያስጨነቃቸው ነው፡፡ አንድን ተማሪ ሞባይል አትያዝ ለማለት የሚያስችል ሥልጣን አላቸው ወይ? ሞባይል የያዘን ተማሪስ ለመቅጣት የሚያስችል ምን ሕግ አለ፡፡ እስካሁን በሞባይል እያወሩ ስለማሽከርከር እንጂ ሞባይል ት/ቤት ውስጥ ይዞ ስለመግባት የወጣ መመርያም ሆነ ሕግ ያለ አይመስለኝም፡፡ ወደፊት ግን ሳያስፈልግ አይቀርም፡፡ «መልስ በሞባይል» የትምህርት ቤቶች አዲሱ ፈተና ሆኗልና፡፡


29 comments:

 1. This is very interesting. "Yidres le timihirt Minister"!

  ReplyDelete
 2. Dear Dn Daniael

  Thank you very much for sharing our social problems. The problems need the eye of Education ministry, it is critical problem, for the quality of the education.

  ReplyDelete
 3. ለምን አንድ አስቂኝ አጋጣሚ አልጨምርም!

  ከጥቂት ዓመታት በፊት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሆነ ነው፤ ጥሩ የሚሠራው ተማሪ አሰራሩን በሞባይል ቀርፆ በብሉቱዝ እንዲልክላቸው ያስማሙታል፤ለዚህም ዘመናዊ ሞባይል ያውሱታል።እሱም ሰርቶ ሲጨርስ መምህሩ እንዳያየው ተጠንቅቆ በቀረፃው እራሱን አድክሞ እንደተነጋገሩት ይልክላቸዋል።አስቂኙ ነገር የተከሰተው ፈተናው አልቆ ከወጡ በኋላ ነው።ተማሪዎቹ ተበሳጭተዋል፤ ለካ ከዘመናዊው ሞባይል ጋር በደንብ ስላልተለማመደ ሲቀርፅ የነበረውና የላከላቸው በወረቀቱ ፋንታ የእራሱን መልክ ነበር...

  ምንም ዓይነት ሞባይል ወይም መሸፋፈን ፈተና ላይ መፈቀድ የለበትም ባይ ነኝ

  ReplyDelete
 4. ትምህርት ቤቱ የራሱን ህግ መከተል ይችላል።ማንም ተማሪ ሞባይል ይዞ ፈተና ክፍል እንዳይገባ
  የውስጥ አሰራር መመርያ አውጥቶ መከልከል ይችላል።

  ReplyDelete
 5. +++ Ejege yetwededk wendmachn. Betam asgeramiwochenon beyzemnu yealen dekamoch mehonachn yasaferal yehunen endseltane kotren gobezun tedegfen rasachnen yersan tewled. betam yemgermw europe weset temer laye eyalu teyakewen kalterdut tetawet yewtalu kemmherachew gar " RE-EXAM" yewsduna temertun ablaltwet rasachw awekwt yalfalu ahun gen beyeametu tent bozene eyaferan endhone 10 kefele wetet yefreden! ERWEGEN LEHAGER LEWGEN MASEBU BEKBDEN ESTI ERASACHNEN ENQUAN ENADEN! Bekirstos akbari betseboch ke toronto

  ReplyDelete
 6. ዘቢለን ጊዮርጊስNovember 17, 2010 at 8:25 PM

  ውድ ዳኒ ይህ የሚያሳየው የትምህርት ጥራት አለመኖሩን ነው ። እንደ ጊዜው የአኮራረጅ አይነቱ እየተለዋወጠ በራሱ የሚተማመን ተማሪ እየጠፋ ነው።ስለዚህ መንግስትና የሚመለከታቸው አካላት በትምህርት ጥራት ላይ ሊሰሩ ይገባል እላለሁ።አንዳንድ መምህራንም እያወቁ የሚያስኮርጁ አሉና ከዚህ ድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል።

  ReplyDelete
 7. በስዕለ ማርያም ጀርባ ላይ አጠሬራ የሚጽፉትን ምን ትላቸዋለህ?ዴስክ ላይ አስቀምጠው መምህር ሲመጣ ይስሙታል በጣም ይገርማል

  ReplyDelete
 8. Ha...ha..ha

  Ye Fasiledes neger ayalkim...

  Thanks Dn..dani

  ReplyDelete
 9. Hi Dani, it is really a good observation. As far as I am a teacher is concerned, I always ask the same quedtion. I think schools at grassroot level and the Ministry of Education at the top should look for a remarkable solution. Besides, we teachers should seek for solutions.

  Ab

  ReplyDelete
 10. Besile mariam lay aterera kemiyizus emebrhanin kelib bilemnuat ende aba Giyorgis tibebun tigeltilache neber. Atererawn gin endelemedu bememirachew jerba yiletifut. Ayi memihir! jerbaw lay eskiletef yemaysema.

  ReplyDelete
 11. ዲያቆን መሐሪ ገብረማርቆስNovember 18, 2010 at 3:19 PM

  “ዘመናዊ” እየተባለ የሚጠራው የትምህርት ሥርዓታችን ፍልስፍናው አለመታወቁ በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ ላሉ ችግሮች ዐቢይ ድፍርስ ምንጭ ይመስለኛል፡፡ በየትምህርት ቤቱ የማያቸው ነገሮች ተማሪው ይቅርና መምህራኑና ትምህርት ሚኒስቴርም ራሳቸው እዚህ ሀገር ላይ ትምህርት ቤት ለምን እንደተከፈተ የሚያውቁ መሆናቸውን እንድጠራጠር ያደርጉኛል፡፡

  ReplyDelete
 12. ሀገር ቤት መምህር ሳለሁ ብዙ የመኮራረጅ አይነቶችን አይቻለሁ ሰምቻለሁ፡ "በስዕለ ማርያም ጀርባ ላይ አጠሬራ የሚጽፉትን ... ዴስክ ላይ አስቀምጠው መምህር ሲመጣ ይስሙታል" የተባለውን አይቸም ሰምቸም ስለማላውቅ በጣም ገረምኝ አሳቀኝ ።

  በነገራችን ላይ አንድ መምህር ተማረዎች ይኮራረጁበታል ብሎ የሚይስባቸዉን ነገሮች ሁሉ ተማረዎች እንዳይጠቀሙ መከልከል (ያልተጻፈ)መብት አለዉ ። ስከለክልም ነበር።

  እዚህ ባለዉበት ውጭ ሀገር ማባይልም ሆን ሳይንትፈክ ካልኩሊተር በፈተና ሰአት ይዞ መፈተን አይፈቀድም።

  አሁን የጨነቀኝ እየሳለ የሚያስኮርጀው ምን ይደረጋል። እንዳያስል መከልከል? ወይስ ለብቻዉ ሊላ ክፍል መፈተን? ሊላ ፈታኝ ሊመደብለት? ሊላዉ በመሸፋፈኛ የሚለብሱት ምን ይባላሉ? መከልከል? በዚህ ወቅት የሚያዋጣ አይመስልኝም።

  ስለዚህ ኩረጃን ለመቀነስ መሞከር ነዉ ማትፋት አይቻልም። ሰነፈ ተማረ ቡዳ ነዉ (ስራው ሁሉ ከማጥናት ይልቅ የአኮራረጅ ስልት ሲቀይስ ነዉ የሚዉለው)።

  ReplyDelete
 13. As a teacher, this was my greatest challenge for some time. But later i used to code objective type questions. That helped a lot. Besides, i always make sure that half of my exams are open questions that need describing, analazing, interpreting etc. But this is possible in a university context, may be difficult for a secondary school teacher who has to teach 30 hours a week. It depend on the teacher's time and number of students.

  I was suspecting this kind of cheating to be the cause for the results obtained in the grade 10 and 12 exams of 2002. So funny.

  ReplyDelete
 14. here are what I consider to be the solutions from my experience both at home and abroad, as a student and as a teacher: 1) change the curriculum and the study design such that students are encouraged and supported to learn, instead of 'forcing' them to remember everything and evaluate them by based on what they forget or not
  2) evaluating knowledge of a student by introducing active evaluation methods, rather than passive questions....eg. more proportion of essay type questions instead of multiple choice questions
  3) applying complex codes to multiple choice type of questions.

  ReplyDelete
 15. the problem tuches all of us. better to fight with such bad habits!

  ReplyDelete
 16. ስልክ ይዞ መግባት የሚከለከልበት ትምህርት ቤት አለ፡፡ ከያዙም ሞባይሉን ቀምተው ወላጅ ይጠራሉ ወላጅም መቶ ብር ይቀጣል፡፡ ስሙን መጥቀስ ባያስፈልግም ሌሎች ትምህርት ቤቶች ከዚህ ተሞክሮ ቢወስዱ መልካም ነው እላለሁ፡፡

  ኪዳነማርያም ዘደብረ ይድራስ

  ReplyDelete
 17. ቃለ ሕይወት ያሰማልን።

  ReplyDelete
 18. የማይበላ እንዳያስበላ ያብላላNovember 20, 2010 at 6:07 AM

  ተዉ ስማኝ አጘሬ

  የናት የወገኔ ተፈትኗል ፍቅሬ

  ReplyDelete
 19. ዲ.ዳኒ ግሩም ጽሁፍ ነው፡፡የአገር ቤቱን ትዝታ አመጣህብን፡፡ምነው ታዲያ የአንተዋ ዘዴ የትኛዋ እንደሆነች ሳታጫውተን ቀረህ፡፡

  ReplyDelete
 20. በስዕለ ማርያም ጀርባ ላይ አጠሬራ የሚጽፉትን ምን ትላቸዋለህ?...This is too much.
  "MOBILE"..agul meseliten kalhone...what does it do for elementary or high school student?Minale lijochachinen belela neger endiseletinu binaskedem. I had heard lot of disappointing stories that are happening at schools during my last visit home. lijen qeteto masadeg eko ayigodawum...machemaleku new eyatefaw yale...ere enimeker...

  ReplyDelete
 21. For all readers- who haven't tried to cheat or to copy someone's work? I think we all do. D.Daniel brought this notion only about cheating or copying at school. We do a lot guys. For instance, we copy cds, we copy books without authors permission, we copy somebody's an idea so on and so on. Sadly however,I(we) are addicted of copying or cheating. This is the core issue we have to discuss about it. Amazingly we are copying the most::::: WE can say much about it! :) Whatever I do on these things, that are immoral.

  ReplyDelete
 22. Deacon Mehari GebremarqosNovember 22, 2010 at 12:36 PM

  Some of you seem to be only laughing at what is happening at our schools. To me this is unacceptable. Dani put what he observed or retrieved from people's experiences not only because they are funny but also they show some uninteresting features about the coming Ethiopia. He points at those features in order to nudge us to do something about it, not just to laugh. So, beside laughing share us something that you think is the way out of this problem.

  I know some people who are teachers now but who were cheaters at school. They just became teachers because that was the only easily accessible job right after college.

  Are these people worth teaching your child?

  ReplyDelete
 23. As usual excellent observation Dn Daniel. I try not to suffer from the so called 'governmental' or 'higher body' solution poblems. When we talk about educational quality let us not forget that parents plays big big role. If all family follow how their kid is doing in school and give him/her the necessary support before the exam, like planning his study time, we can significantly reduce the problem. For God sake we can not expect the teachers or ministry of education to do this? This is parental obligation! I think that is the big gap in our education system! Somebody might ask what will happen when he/she is in college or university? But if we are thought how to study and displine our self at early stage there is high chance for us to continue doing so when we are left alone at later stage. Why do we see majority of students from well of families perform better in school? Because they have better parental guidance! I think this aspect of education should be looked into! This is not to say that we have the perfect educational system, but the big chunk of the current problem can be solved if everybody play his/her role!

  ReplyDelete
 24. ጥሩ እይታ ጥሩ ምልከታም ነው ፡፡
  እንደ እኔ ሀሳብ
  ት/ት ለአንዲት ሀገር እድገት ጠቃሚ ብቻ ሳሆን ወሳኝም ነው ፡፡ ይህ ለሀገር እድገት ወሳኝ የምንለው ነገር የምንፈልገውን ለውጥ እንዲያመጣ ግን የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ጥረት እና ቁርጠኝነትን ይጠይቃል ፡፡ አንዳችን በአንዳችን በማሳበብ የምንፈልገውን ለውጥ ልናመጣ አንችልም፡፡ ተማሪው የተማሪው ቤተሰቦች(በተለይ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች) መምህራን የት/ት ቤቶች አስተዳደር አካላት የት/ት ሚንስተር ……ወዘተ፡፡ ሁሉም በተናጠል እና በጋራ ሊሠሯቸው የሚገባቸውን ሥራዎች መሥራት ሲችሉ የምንፈልገው ለውጥ ይመጣል ብዬ አምናለሁ፡፡ እኛ ከላይ ከተጠቀሱት ባለድርሻ አካላት በአንዱ መመደባችን ስለማይቀር የበኩላችንን ድርሻ ለይተን አውቀን በተገቢው መንገድ ልንወጣ ይገባል አላለሁ፡፡ ግን ግን የትኛውም አገልግሎት እና ሥራ ላይ እኛ የሚል ባለድርሻ አካል ቢኖር እኔ አይመለከተኝም ከሚል የስንፍና አነጋገር አያድንም ትላላችሁ?፡፡

  ReplyDelete
 25. HI DANIEL I AM APPRECIATING YOU
  የሚገረም ነው ትውልዱን ወደ ጥፋት ጎዳና እየመራው ነው

  ReplyDelete
 26. Hi Dani, endante aynet sewechin egiziabher le ethiopia yabizalat. Amen

  ReplyDelete
 27. Dn Daniel !!

  God bless U after all. Of course it is very interesting but dangerous for our generation. And horrable when we think about knowledge.

  Not only the teachers but all of us should feel about the responsibility.

  ReplyDelete