Saturday, November 13, 2010

ጎንደር ስትረሳ እና ስታስታውስ

ጎንደር ቁስቋም በጥንታዊው ዕቃ ቤት ውስጥ
ዘመናዊ ሙዝየም ገንብታለች
አሁን የጎንደር ከተማ መነቃቃት ጀምራለች፡፡ መንገዶቿ አስፓልት እየለበሱ ነው፡፡ ሪል እስቴቶችም ብቅ ብቅ ብለዋል፡፡ ታላላቅ ሕንፃዎችም እየበቀሉ ናቸው፡፡ አብያተ ክርስቲያናትም ሙዝየሞችን በማሠራት ላይ ናቸው፡፡

ጥንታዊቷ የእቴጌ ምንትዋብ ቤተ ክርስቲያን ጎንደር ቁስቋም በጥንታዊው ዕቃ ቤት ውስጥ ዘመናዊ ሙዝየም ገንብታለች፡፡ የአስራ ስድስተኛውን እና የሥራ ሰባተኛውን ዘመን የሚያሳዩ ንዋያተ ቅድሳት፣ የወግ ዕቃዎች እና መጻሕፍት ለእይታ ቀርበዋል፡፡ ምንም እንኳን ቦታው ጠበብ ያለ ቢሆንም የአሥራ ሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሕንፃ በመሆኑ ጉብኝቱን በታሪክ ላይ መሄድ ያደርገዋል፡፡

አስጎብኝው መሪጌታ ዳንኤልም መጻሕፍቱን ያነበቡ፣ታሪኩን የጠገቡ፣ አክበሮትን ከትኅትና ጋር የተላበሱ መሆናቸው በእቴጌ ምንትዋብ የግብር አዳራሽ የተጋበዛችሁ ያስመስላችኋል፡፡ ሕንፃው ሲሠራ መስኮት ስላልነበረው መብራት በማይኖር ጊዜ ጧፍ ይጠቀማሉ፡፡ ይህ ሁኔታ ግን ቅርሶቹን ለእሳት አደጋ ሊያጋልጣቸው ይችላልና በተለ ይም በአሜሪካ እና በአውሮፓ የምትገኙ የቅርስ እና የታሪክ ወዳጆች በኤሌክትሪክ ቻርጅ ተደርጎ ለረዥም ሰዓት ሊያገለግል የሚችል ጠንካራ ባትሪ ብትልኩላቸው ስማችሁ ሁልጊዜ በጸሎት ይታሰብ ነበር፡፡

የእቴጌ ምንትዋብ አዳራሽ እና ቤተ መንግሥት በደርቡሽ ጊዜ ፈርሶ ትዝታን ብቻ እያሳየ ቆሟል፡፡ የዓባይን መነሻ አገኘሁ ያለው የ17ኛው መክዘ አሳሽ ጄምሰ ብሩስ የኖረው እዚህ ቦታ ነው፡፡ እቴጌ ምንትዋብ ልዩ ክብካቤ ታደርግለት ነበር፡፡ የኢትዮጵያን ታሪክ ያጠናበት የነበረው ቤት ዛሬ ፍርስራሹ ይታያል፡፡

በአጣጣሚ ሚካኤልም ሙዝየም ተከፍቷል
እንደ ቁስቋም ሁሉ በአጣጣሚ ሚካኤልም ሙዝየም ተከፍቷል፡፡ በተለይም የጎንደር ፋሲል ቤተ መንግሥት ጎብኝዎች ከሚወጡበት በር አጠገብ መከፈቱ ለጎብኝዎቹ ምቹ እንዲሆን አድርገውታል፡፡

ጎንደር ላይ ሀገረ ስብከቱም ሙዝየም ከፍቷል፡፡ በተለይም የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ ሊቁ የሊቀ ሊቃውንት መሐሪ ትርፌ/ አቡነ ጴጥሮስ/ ቅርሶች ከአደጋ ተርፈው ለሙዝየም መብቃታቸው አስደናቂ ነው፡፡ ታሪኩን እና ቅርሱን ጠብቀው ለዚህ ወግ መዓርግ ያበቁትን አባ ሙሉንም ያስመሰግናቸዋል፡፡ በገንዘብ እንግዛዎት ተብለው እምቢ አሉ፡፡ በባለ ሥልጣናት ትእዛዝ ከደመወዝ እና ከሥራ ቢከለከሉም ቅርሱን ያለ ተረካቢ አልሰጥም አሉ፡፡ በመጨረሻ ግን ሕዝብ እና መንግሥት ባለበት ለትውልድ አስረከቡ፡፡ ምናለ እንደ አባ ሙሉ ያለ አሥር ቢሰጠን፡፡

የጎንደር አብያተ ክርስቲያናት እያንዳንዳቸው ሙዝየም ሊኖራቸው በተገባ ነበር፡፡ በውስጣቸው ገና ትውልድ ያላያቸው ብዙ ቅርሶች ይዘዋልና፡፡ መካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም የተተከለችበትን ሦስት መቶኛ ዓመት በቅርቡ ልታከበር በዝግጅት ላይ ናት፡፡ ከዚህ በዓል በተያያዘም ሙዝየም ለመገንባት አስበዋል፡፡

ጎንደር ላይ ሁለት አሳዛኝ ቅርሶች አሉን፡፡

ከሸዋ መጥተው ጎንደር ወንበር ዘርግተው ያስተምሩ የነበሩ አለቃ ወልደ አብ የተባሉ መምህር ነበሩ፡፡ መቼም በጥንቱ ባህላችን ሰው ሞያው እንጂ ሀገሩ አይጠየቅም፡፡ እር ሳቸው ደግሞ ደረስጌ ሄዱና መምህር ወልደ ሚካኤል የተባሉትን አምጥተው በትምህርት አሳደጓቸው፡፡ አለቃ ወልደ አብ ሲያርፉ መምህር ወልደ ሚካኤልየ ግምጃ ቤት ማርያምን ትምህርት ቤት ተረክበው ማስተማር ቀጠሉ፡፡

መምህር ወልደ ሚካኤል እያስተማሩ እያሉ ደርቡሽ ጎንደርን ሊያቃጥል መጣ፡፡ ብዙዎቹ ሲሸሹ እርሳቸው ግን «መከራ ታዝዞብናልና እናንተ ሽሹ፤ እኔ ግን ጉባኤ አላጥፍም» ብለው እያስተማሩ እያሉ ከዘጠኝ ተማሪዎቻቸው ጋር በደርቡሽ ሰይፍ ተሰይፈው ዐረፉ፡፡

እኒህ ለትውልድ አርአያ የሚሆኑ መምህር የተቀበሩት
 እዚያው ግምጃ ቤት ማርያም ከግቢው በር በስተ ቀኝ በኩል ነው
እኒህ ለትውልድ አርአያ የሚሆኑ መምህር የተቀበሩት እዚያው ግምጃ ቤት ማርያም ከግቢው በር በስተ ቀኝ በኩል ነው፡፡ የሚያሳዝነው ግን ምንም ዓይነት ምልክት የለውም፡፡ እንዲህ ዋኖቻችንን እየረሳን ነገ ሌላ «ዋና» ከየት እናገኛለን፡፡ የደብሩም ሰዎች ሆኑ ሌሎቻቸን ቢያንስ መምህር ወልደ ሚካኤል ለሃይማኖታቸው እና ለጉባኤያቸው ሲሉ ተሰውተው እዚህ ቦታ ላይ መቀበራቸውን ምልክት ልናደርግላቸው ይገባል፡፡

እዚያው ግምጃ ቤት ማርያም በጀርባ በኩል ደግሞ እንደዚሁ በመረሳት ላይ ያለ ታሪክ አለ፡፡ የዐፄ ቴዎድሮስ አማካሪ የነበረው ፕላውዴን የተቀበረው ግምጃ ቤት ማርያም ነው፡፡ ፕላውዴን በምጥዋ የእንግሊዝ ቆንስል ሆኖ ነበር የተሾመው፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስ ሲነግሡ ወደ ጎንደር መጣና ከንጉሡ ጋር ተገናኘ፡፡ ንጉሥ ቴዎድሮስም በመልካም ሁኔታ ተቀበሉት፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ከእርሳቸው አልተለየም ነበር፡፡


ፕላውዴን የተቀበረበት ቦታ
በብረት አጥር ታጥሮ ተቀምጧል፡፡
ነገር ግን የሰርዶ ዓይነት በቅሎበት
 ሙጃው እንጂ መቃብሩ አይታይም

በመካከል ታመመና ለሕክምና ወደ ሀገሩ ሲሄድ የልጅ ጋረድ ሽፍቶች አገኙትና በደፈጣ ጦር ክፉኛ አቆሰሉት፡፡ ጥቂት ቀናትም ቆይቶ በጥር ወር 1853 ዓም ዐረፈ፡፡ ግምጃ ቤት ማርያምም ተቀበረ፡፡

ፕላውዴን የተቀበረበት ቦታ በብረት አጥር ታጥሮ ተቀምጧል፡፡ ነገር ግን የሰርዶ ዓይነት በቅሎበት ሙጃው እንጂ መቃብሩ አይታይም፡፡ በላዩ ላይ የነበረው ጽሑፍም ጠፍቷል፡፡ ይህ ቦታ የኢትዮጵያን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከሚያሳዩት ቦታዎች አንዱ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ ለወዳጆቿ የምትሰጠውን ቦታም ያሳያል፡፡ ፕላውዴን እንግሊዛዊ ሆኖ እንደ ኢትዮጵያውያን የኖረ ነው፡፡ ታድያ ምነው ዝክረ ታሪኩን ዘነጋንበት?

ጎንደር ላይ እንቆይ፤ ሌላም እናያለን፡፡ ለመሆኑ በጎንደሩ ዐፄ ዮሐንስ ዘመን በዕንባ ስለ ተሳለችው ሥዕል ሰምተው ያውቃሉ?


12 comments:

 1. ዉድ ዳኒ ብዙ ነገር አሳወቅክን እናመሰግናለን
  ስለ ሰማዕቱ መምህር ወልደ ሚካኤል መቃብርስ ምን ምልክት ይደረግ ትላለህ?
  የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደሯ ጠንካራ ቢሆንማ ኖሮ ቅድስና አይገባቸዉም ኖሯልን?

  ምልክት ስትል ግን ሰዎች እንዳይሰሙህ - ሐዉልት እናቁምላቸዉ እንዳይሉን...

  ReplyDelete
 2. what can i say God bless u Dani.

  ReplyDelete
 3. ደብረ ቁስቋም
  በእውነት ታሪካችንን ስላሳውከን እጅግ በጣም እናመሰግናለን.ስለ ስእልዋ እስክሰማ ግን በጣም ቸኩያለሁ መምህር በጣም ትልቅ ስራ ነው ቃለ ህይወት ያሰማልን ድንግል ካንተ ጋር ትሁን.

  ReplyDelete
 4. ዘ ሐመረ ኖህNovember 13, 2010 at 7:34 PM

  ዳኒ ቃለ ሕይወት ያሰማልን በጣም እናመሰግናለን በርታ ወ ዘ ተ ማለታችን ጥሩ ነው ተገቢም ነው ነገር ግን ወገኖቼ ይህን ሁሉ ሥራውን የሚያከናውንበት ወጪ ቢያንስ ቢያንስ ማገዝ የለብንምወይ ?የኛ ነገር መመረቅ ብቻ ሆነ የኢንተርኔት ወጪ አለ ጎንደር ድረስ ተጉዞ ይህን ሁሉ አጥንቶ መዘገብ ብዙ ድካም ብዙ ገንዘብ ይጠይቃል ሻማ እራሱ እየነደደ ለሌላው ብርሃን ይሰጣል ሁሉ ቢቀር የሻማውን ወጪ መሸፈን አያስፈለገንም? ለምሳሌ የስእልዋን ታሪክ ለመስማት ሁላችንም ቸኩለናል የምትጠይቀውን መስዋእትነት ለመክፈልስ ምን ያህል ተዘጋጅተናል?በመንግስት ደረጃ ሊሰራ የሚገባ ሥራ በአንድ ሰው ሲሰራ በነገር ሁሉ ምን ያህል ከባድ እነደሆነ መገመት ያስቸግራል?አንድ የመንግስት ሠራተኛ ይህንን ሥራ አጥንቶ ለሚድያ እንዲያበቃ ቢታዘዝ የሚያዝለትን ወጪ አስቡት ቢያንስ የምንመኘውን ወይም የምንፈልገውን ነገር ለማግኘት ያ ነገር የሚጠይቀውን መስዋእትነት መክፈል አይኖርብንም?የሚቀርብልንን ዝም ብለን መመገብ ብቻ ነው ወይስ ቢያንስ በወጪው መሳተፈ አለብን? ክርስትና በሃሳብና በምርቃት ብቻ ሳይሆን በነገር ሁሉ ሱታፌን ይጠይቃል ማለትም መሳተፍን ይጠይቃል እና ወገኖቼ ለራሳችን ጥቅም ዲያቆን ዳንኤልን እንዴት እናግዘው ?ከበረከቱ እንዴት እንሳተፍ?በሃገር ውስጥም በውጭም ላለነው እቤታችን ድረስ ለሚቀርበልን መንፈሳዊ ምግብና ተስፋ ምን እናድርግ?

  ReplyDelete
 5. ዲ/ዳንኤል የቅዱሳን አምላክ ዋጋህን ይክፈልህ በጉልበትህ በገንዘብህ በሃሣብህ እንዲሁም የትዳርህንና የልጆችህን ግዜ ሳይቀር መስዋእት በማድረግ ለሁሉም የሚመጥን ማንም ያላየውን ያላስተዋለውን እንደውም የረሳውን ነገር ግን ለዚች ቤ/ክ ሞገሶ የሆኑ ቅርሶቾ እንዲታወቁ እንዲታሰቡ እንድታደርግ እድሉን የሰጠህ አምላክ ይክበር ይመስገን ፈቃዱም ሆኖ የአገልግሎት ዘመንህን ያርዝምልን ያፅናህ ያበርታህ

  ከአቡዳቢ

  ReplyDelete
 6. +++ Ejeg lemnwedh wendmach bekdmya QHY! Berta esti yedkmen yemiyaberta hyal kend yalew Amlakach behulu yerdah! wedhuala melse belen ersachnen endnaye ena kebatochachn berket eredet endnagen eyaderk new abernh honeon yedershachnen endnweta betselot asben ! Melkam yesera ena yeagelglo zemn yehunleh Ke toronto akbari betseboch

  ReplyDelete
 7. እናመስግናለን ዲ/ን ዳንኤል::

  በአሜሪካ የምትገኙ የዚህ ብሎግ ተከታታዮች:- ከዚህ በታች ባለው ስልክ ቁጥር በየሁለት ሳምንቱ የሚሰጥውን ትምህርተ ወንጌል በጣም ጠቃሚ ሆኖ አግኚቸዋለሁ:: እናንተም እንድትጠቀሙ እጋብዛለሁ::

  ስልክ ቁጥር:-(712) 451-6000
  መግቢያ ኮድ:- 145670#

  በየሁለት ሳምንት እሑድ
  ከ8:00PM - 9:00PM CST

  ቀኖች:-
  Nov 14, 2010
  Nov 28, 2010
  Dec 12, 2010
  Dec 26, 2010
  Jan 9, 2011
  Jan 23, 2011
  Feb 6, 2011

  ReplyDelete
 8. ዳንኤል እግዚአብሄር ፀጋውን ያብዛልህ ብቻ ኔው:: ሀገርህን እና ቤተክርስቲያንን የምታገለግልበትን ረጅም እድሜ ይስጥህ::

  ReplyDelete
 9. ሰላም ለኪ ኢትዮጵያ ምድረ ገነት
  የቅዱሳን መናኸሪያ የቅዱሳት እናት

  ምስጋና ይገባሻል ከእስራኤልም በመመረጥሽ
  ማረፊያ ስለሆንሽ ለፈጣሪ ለእመቤትሽ፡፡

  ኢትዮጵያ ሃገር ሰው ከመሆን
  ለምንመኝ አሜሪካ ሳር ለመሆን

  ውስጧ የያዘችውን ግለጥልን

  እግዚኦ ልብ ስጠን፡፡

  ላንተም ክብሯን ላስተዋወከን /ለመምህራችን/
  ቃለ ህይወት ያሰማልን፡፡

  ReplyDelete
 10. Dn Daniel, I like you write history and real politics.
  Get out of this retarded EOC political debate, like patriarch, synod, bishops, tehadsso, MK..., then you will transform yourself to the national public figure status. Otherwise you will be remain controversial.

  ReplyDelete
 11. Egziabhair Hailun Yisteh.

  ReplyDelete
 12. Kale Hiwot Yasemalin

  ReplyDelete