Monday, November 8, 2010

ዓይናማው የአዞዞ ሰዓሊ

በዐፄ ሱስንዮስ ዘመነ መንግሥት የተተከለውን የአዞዞ ተክለ ሃይማኖትን ቤተ ክርስቲያን ሲጎበኙ በሦስት ነገሮች ይደነቃሉ፡፡ የመጀመርያው ከጎንደር ዘመን በፊት የነበረውን የሕንፃ ቤተ ክርስቲያን አሠራር የሚያዩበት አጋጣሚ ስለሚፈጠርልዎት ነው፡፡ ምንም እንኳን በየዋሕነት አንደኛው ግድግዳ ቀለም ተቀብቶ የታሪ ልዋጤ ቢደርስበትም በአንድ በኩል ግን ከነ ምልክቱ ያዩታል፡፡ በተለይም ከግድግዳው በላይ የተለጠፉት የነገሥታቱ ምልክቶች ጥንታዊነቱን ያሳያሉ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ለብዙ ዘመናት ተጠብቀው የቆዩት ቅርሶች ናቸው፡፡ ከግራኝ በኋላ እና ከጎንደር በፊት ያለውን ጥበብ የሚያሳዩ መጻሕፍት፣ደወሎች፣ነጋሪቶች፣አልባሳት እና መስቀሎችን ታገኛላችሁ፡፡

ሦስተኛው የዓይናማው የአዞዞ ሰዓሊ ሥዕሎች ናቸው፡፡ ስሙን በሥዕሎቹ ላይ ያላሰፈረው የ1960ው ይህ ዓይናማ ሰዓሊ መጽሐፍ፣ ታሪክ እና ባህልን ልቅም አድርጎ ያውቅ እንደነበር ሥዕሎቹ ይመሰክራሉ፡፡ የኢትዮጵያን ነገሥታት ታሪክ ቅደም ተከተል ከነ ስማቸው ሥሎ አቆይቶናል፡፡ የደብረ ሊባኖስን እጨጌዎች ከቅደም ተከተላቸው እና ከስማቸው ጋር የቤተ መቅደሱን ዙር ግድግዳ ሞልቶ በቅርስነት አቆይቷቸዋል፡፡ በጣና ገዳማት ውስጥ እንደምናየውም በእርሱ ዘመን የነበረውነ ተግባረ እድ የሚያመለክቱ ዘመን ቀረስ ሥዕሎችንም በመቅደሱ በር ግራ እና ቀኝ ስሏቸዋል፡፡

በአዞዞ ከሚገኙት ታሪካዊ ቅርሶች አንዱ በጎንደር የነበረው የፕሮቴስታንት ሚሲዮናዊ የማርቲን ፍላድ ስም የተጻፈበት ደወል ነው፡፡ «የፍቅር መንሻ፣ ከማርቲን ፍላድ» ይላል፡፡ ማርቲን ፍላድ (1831 - 1915 እኤአ) በጎንደር የነበረ ጀርመናዊ ሚሲዮን ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ወደ አማርኛ በመተርጎሙ ይታወቃል፡፡ ማርቲን ፍላድ በተለይም ከዐፄ ቴዎድሮስ ጋር በፍቅርም በጠብም ሠርቷል፡፡ እንደ እኔ ግምት ይህንን ደወል የሰጣቸው ለዐፄ ቴዎድሮስ ሳይሆን አይቀርም፡፡

በደወሉ ላይ «Gegossen von Christian vogt In Stuttgart 1879 » ይላል፡፡ ምናልባት ጀርመንኛ ሳይሆን አይቀርም ብዬ እገምታለሁ፡፡ ታድያ ምናለ ጀርመን አያሌ ወዳጆች አሉን፡፡ አንዱ ተርጉሞ ይነግረን ይሆናል፡፡

ከአዞዞ ሳልወጣ አንድ ሃሳብ ላቅርብ፡፡ «የአዞዞ ታሪካዊ ቦታዎች ወዳጆች ማኅበር» የሚል አቋቁመን እነዚያን በመጥፋት ላይ ያሉትን ቅርሶች ብንጠብቅ ምናለ፡፡ ዐቅሙ እና ፍላጎቱ ያለው በፌስ ቡክ በኩል ያሰባስበን እና አንዳች ሥራ እንሥራ፡፡ ያለ በለዚያ «ጽጌረዳ እና ደመና» የሚለው የከበደ ሚካኤል ትንቢታዊ ግጥም ይደርስብናል፡፡

ከአዞዞ እንውጣና ወደ ዋናው ከተማ ወደ ጎንደር እንግባ፡፡ ለመሆኑ ጎንደር ከተማ ውስጥ ስላሉት «የእጨጌ ቤቶች» ሰምተው ያውቃሉ? በኋላ ላይ እመለስበታለሁ፡፡

19 comments:

 1. በጣም ደስ የሚል ታሪክ ነዉ። Stuttgart በደቡብ ጀርመን የምትገኝ የ Baden-Württemberg ዋና ከተማ እንደሆነች እና በ2008 ወደ 600,038 የሚጠጋ ህዝብ እንደነበራት ያነበብኩት ምንጭ ያሳያል። በ 1879 ይኖሩ ከነበሩ ታዋቂ ሰአሊያንና ፎቶግራፈር Christian vogt አንዱ ሳይሆን አይቀርም። ስለዚህ «Gegossen von Christian vogt In Stuttgart 1879 » ማለት በ 1879 በChristian vogt ሰው Stuttgart በምትባል ከተማ የተሰራ ማለት ይመስለኛል። ጀርመንኛ በደንብ የምትችሉ እንግዲህ አስተካክሉት።
  ለማንኛውም «የአዞዞ ታሪካዊ ቦታዎች ወዳጆች ማኅበር» የሚል ቢመሰረት የምደግፍ እና የምችለውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጙ ነኝ።

  ReplyDelete
 2. Until Germany speaker translates the word at least let's use free online language translator to understand what written on the bell. Based on Google language translation,the script on the bell translate as "Cast Christian Vogt In Stuttgart 1879". Cast = give as "cast a vote".

  ReplyDelete
 3. When I tried it in Google Translate
  'Gegossen von Christian vogt In Stuttgart 1879' means 'Cast by Christian Vogt In Stuttgart 1879'

  ReplyDelete
 4. «Gegossen von Christian vogt In Stuttgart 1879 » -Poured of Christian vogt in Stuttgart 1879. The world lingo traslation(http://www.worldlingo.com)

  ReplyDelete
 5. «Gegossen von Christian vogt In Stuttgart 1879 » ትርጉሙ፡በክርስቲያን፡ፎግት፡ሽቱትጋርት፡ከተማ፡
  ተሠራ፡ነው፡የሚለው፡፡

  ReplyDelete
 6. http://www.heimatkreis.com/glockenbuch/text_umschlag.jpg

  Heimatkreis Isselburg
  Paul Biermann Tel.: 02874 / 2704
  Drengfurter Straße 26

  46419 Isselburg

  ReplyDelete
 7. Christian Voigt bell cast in 1781 for the St. Bartholomew's Church in Isselburg.Gegossen von Christian vogt In Stuttgart 1879(Cast by Christian Vogt In Stuttgart 1879)he is one of a big family vogt.this book is THE FAMILY VOIGT (1729 - 1827),he is ab to 98 ANNUAL BELL CAST IN GERMAN-DUTCH SPACE.

  ReplyDelete
 8. Selam Dn Daniel,

  It is very impressive that you started introducing us to epic monastries and historical religious sites.In fact it would be good if you can creat a seperate label for such articles that cognizance us to such places.And also the ones from your book "Church Encyclopedia" always wished to get those along with pictures.It would be incredible.
  At last the german translation means the following "Cast of Christian vogt In Stuttgart 1879".Mesgana legoogle

  ReplyDelete
 9. «Gegossen von Christian vogt In Stuttgart 1879 »

  በእርግጥም፡ጀርመንኛ፡ነው።
  ትርጓሜውም፦

  "በአንጥረኛው፡ክርስቲያን፡ፎግት፡1879፡የተሠራ" ነው።

  እግዚአብሔር፡ኢትዮጵያንና፡ተዋሕዶን፡
  ይጠብቅልን።አሜን።
  እግዚአብሔር፡በተዋሕዶ፡ለተዋሕዶ፡የሚተጉትን፡ሁሉ፡
  ይባርክልን።አሜን

  ReplyDelete
 10. Dear Daniel,

  Still in Azezo there are many more historical places to learn. Places such as the very old St. Michael church around the meat factory or not far from the new Dashen brewery. Here you can see the destroyed old church building, partly still standing (as I remember it few years ago). It was destroyed by the Derbush (Sudan's mahadists). Also the Azezo Loza Mariyam church. Around the church (1-2 kms surrounding) there are a lot of historical places. There is also another beautiful bath where the Tabot of the St. Mary church (i.e., Loza Mariyam) used to rest for "Timket" feast. Many more....

  Keep up with these kinds of enlightening works.

  Orthodox child.

  ReplyDelete
 11. Selam Dani, I used "Google Translater" until someone from German to translate to Amharic

  «Gegossen von Christian vogt In Stuttgart 1879 » means- "Cast by Christian Vogt In Stuttgart 1879"
  Cast means to form (liquid metal, for example) into a particular shape by pouring into a mold.

  God bless you.
  Kiya from Canada

  ReplyDelete
 12. ዲ/ን ዳኒ ሰላም ላንተ ይሁን! በጣም ደስ የሚል ታሪክ ነው። መቼም ገና ስለጎንደር ብዙ እድምትነግረን ተስፋ አደርጋለሁ።
  እድሜ ይስጠን አሜን።

  ReplyDelete
 13. Use this http://www.freetranslation.com/
  copy the item you wanna translate.
  Select source and destination language
  click translate

  ReplyDelete
 14. ዲ/ን ዳንኤል ታላቅ ነገር ብለሃል < ባለቤት ያቃለለውን ባለዕዳ አይቀበለውም› እንዲሉ የማስተዋወቁን ሥራ ጠንክረህ ሥራልን፡፡ እኔ ደግሞ ተጨማሪ አደራ ልበልህና እስኪ ወደ ምሥራቁ የሀገራችን ክፍልም (በተለይ ሐረር ከተማ ውስጥ) ስላሉት ታላላቅ አድባራት እና ሌሎች ትኩረት የተነፈጋቸውን ታሪካዊ ቅርሶች አስተዋውቀን፡፡ የዛሬን አያድርገውና ታላላቅ የቤ/ክ ሊቃውንት ያለፉባት እንደ አደሬ ጢቆ ቅ/ሥላሴ ደብር--ሊቃውንቱ የሐይማኖተ አበው ትርጓሜ መጻሕፍትን ያሄዱበት፣ የታላቁ የጥበብ ሰው አለቃ መዝሙረ ዳዊት (1892 – 1975 ዓ.ም) የሳሏት ግርምት የእመቤታችን የመንበር ሥዕል ትገኛለች፤ ገና ብዙ ያልተጠኑ አሉ
  (በነገራችን ላይ ስለ ኢትዮጵያ ሠዓሊያን ሳነብ ያገኘሁት እሳቸው የሳሏቸው ተመሳሳይ ሥዕሎች --በሌመን ሥላሴ፣ ሜታ አቦ ቤ/ክ በሸዋ፣ መናገሻ ማርያም፣ የደብረ ቤቴል ሥላሴ በወሎ፣ የደብረ አባይ አቡነ ሳሙኤል በትግራና የሀገረ ሰላም መድኃኔዓለም በሲዳሞ፣የቅድስት ማርያም በአርሲ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ በአዲስ አበባም --ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል፣ በቅድስት ማርያም፣ በዮሐንስ በቀጨኔ መድኃኔዓለም፣ በየካ ሚካኤል፣ በየካ አቦና በጎላ ሚካኤል፣ በልደታ ቤ/ክ ፣ በቀድሞው ፓርላማ፤ እንዲሁም በኢየሩሳሌም ዴር ሱልጣንና ቢታኒያ ተ/ሐይማኖት ወዘተ…ተመሳሳይ ሥዕሎች አሏቸው)፡፡
  የአቦከር ደ/ጸ/ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብርም እንዲሁ ‹ዳግማዊ ዋሸራ› ነበር (ከመንግስቱ ለማ የልጅነት ታሪክ ያነበብኩት) ዛሬ ግን አፀዱ ብቻ ቀርቷል፣ እንደያኔው ቅኔ የሚዘርፍበት የለም፡፡ የአብነት ት/ቤቶቻችን ወደ ሰሜኑ ሸሽተው ሸሽተው ይሄው ባሉበት ቦታ ለጥፋት ተጋልጠዋል፡፡ በቀሩት አድባት ላይም ተጨባጭና ትክክለኛ መረጃ አይገኝም፡፡ ለምሳሌ፡- በደብረ ገነት መድኃኔዓለም ቤ/ክ ዙሪያም የማናውቀው የተደበቀብን ብዙ ታሪክ አለ (ምን አልባት አዲስዓለም ማርያም ፍንጭ አለ የሚባል ሰምቻለሁ) አንተ ለቤ/ክ ታሪክ ቅሩብ ነህና አውነተኛውን ታሪክ ንገረን፡፡
  በሐረር ዙሪያም የደ/ስብሐት ቅ/ድንግል ማርያም አለች፤ ያኔ ከ300 በላይ ካህናትና ሊቃውንት ይርመሰመስባት የነበረችዋ ዛሬ አራት የማይበልጡ ካህናት ብቻ ናቸው ያሏት፡፡ ለማንኛውም አይተህ ታሪካችንን ተርክልን፡፡

  እግዚአብሔር እድሜህን ያርዝምልን

  ReplyDelete
 15. wonderful job and idea Dn.Daniel

  ReplyDelete
 16. ወልደ ዮሐንስNovember 10, 2010 at 11:49 AM

  በሐረር መካነ ሥላሴ ካቴ (አደሬ ጢቆ) አንድ ቅልቅ አስታዋሽ ያጣ ተመሳሳይ ደውል አለ እጅግ በጣም ግዙፍ የሚጠይቀው አጥቶ -- አኩርፎ የተቀመጠ!

  ስለመኖሩም ብዙዎቻችን አናውቅም

  ReplyDelete
 17. +++ Ejeg yetwededk wendmachn QHY awo endh erget yale melket yasfelgenal I think all we are in day dream pls all volunteers let us take some commitment & met face book! Great issue. Medhanealem abate yetabkeh edmehn yarzmlh! Ke Toronto akbari betseboch

  ReplyDelete
 18. ኤልያስ
  መምህር ዳንኤል መልዕክትህ ግሩም በመሆኑ በየወቅቱ እከታተላለሁ ።
  መምህር የጌታችንን የኤየሱስ ክርስቶስን ምስል በተመለከተ ጽሁፍ ብታዘጋጅልን
  አሁን በየቦታው የምናየው ምስል እውን ትክክለኛ የጌታችንን ምስል ነውን? ለምንሰ ከቦታ ቦታ ይለያያል?
  የእኛ ሰዓሊያን የሚስሉት በገበያ ላይ ከሚታየው ለምን ተለየ?

  ReplyDelete
 19. Gegossen is the past form of Giessen.which means Watering.ስለዚህ በዚህ ቦታ ቃሉ
  የሚያገለግለው ማፍሰስ ለሚለው ይሆናል።ስለዚህ ክርስቲያን ፎግት የተባሉት የሽቱትጋርት ነዋሪ
  አቅልጠው እንደሰሩት ያሳያል።

  ከጀርመን

  ReplyDelete