አሁንም አዞዞ ላይ ነው ያለሁት፡፡
ከግራኝ ወረራ በኋላ እና ከጎንደር ዘመን በፊት ከነበሩት የመንግሥት መቀመጫ ከተማዎች አንዷ ናት አዞዞ፡፡ ምናልባትም ከጎንደር በፊት የመጨረሻዋ ከተማ ሳትሆን አትቀርም፡፡ ይህንን ታሪኳን የሚመሰክሩ አያሌ ጥንታውያን ቅርሶች ከመሬት በላይ እና ከመሬት በታች ይታያሉ፡፡ ኢትዮጵያውያን ምን ያህል በራሳችን ላይ እንደምንቀልድ ለማወቅ የፈለገ ሰው አዞዞ የቀበረቻቸውን እና እንደ ዋዛ የጣለቻቸውን ቅርሶች መመልከቱ ብቻ በቂ ነው፡፡
ከጎንደር ዘመን በፊት ከነገሡት ነገሥታት መካከል ኃያል የነበረውና ለሃይማኖት ግጭት መነሻ የሆነው የዐፄ ሱስንዮስ የአዞዞ ቤተ መንግሥት እየፈራረሰ ይገኛል፡፡ ከፊሉን ቤተ መንግሥት መሬት ውጦታል፡፡ ከፊሉን ደግሞ የአካባቢ ከብቶች ይታከኩታል፡፡ ገበሬዎችም ያርሱበታል፡፡ ዙርያውን ዳዋ ውጦት ለቅርሶቻችን ግዴለሽ መሆናችንን ይመሰክርብናል፡፡
እርሱ ብቻ አይደለም፤ የሱስንዮስ ዘመን አልፎ የፋሲል ዘመን ሲተካ ፖርቹጊዞች አዞዞ ላይ የኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ነበር፡፡ እነ እጨጌ በትረ ጊዮርጊስ አዞዞ ትገኝ የነበረችውንና በስደቱ ዘመን ይዘዋት የተሰደዱትን የእመቤታችንን ታቦት «ካቶሊኮች በቀደሱበት አናስገባትም» ብለው ነበር አዞዞ ተክለ ሃይማኖትን ያነፁት፡፡ ያ የኢየሱስ መቅደስ ዛሬ ፈራርሶ፣ በላዩም ላይ እርሻ እየታረሰበት ይታዘበናል፡፡ የመጨረሻዎቹ የግንቡ ፍርስራሾች ሊጠፉ አንድ ሐሙስ ቀርቷቸዋል፡፡ ታሪክን ወደ ተረትነት መቀየር እንደምንችልበትም ይመሰክርብናል፡፡ የአካባቢው ቤተ ክህነት፣ የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ፣ የአካባቢው ተወላጆች እና ለቅርስ እና ለባህል የሚቆረቆሩ አካላት አዞዞን ምን እስከምትሆን እንደሚጠብቋት እንጃ፡፡
ሌላው አሳዛኝ ታሪኳ ደግሞ ከፋሲል መዋኛ በፊት የተገነባው የሱስንዮስ የመዋኛ ገንዳ ጉዳይ ነው፡፡ ከ300 ዓመት በፊት የነበረውን የመዋኛ ገንዳ አሠራር ጥበባችንን ሊመሰክር የሚችለው ይህ ገንዳ በአፈር ተደፍኗል፡፡ ለምን? ብዬ የአካባቢውን ሰዎች ጠየቅኳቸው፡፡ «በክረምት ሕፃናት እየገቡ በመሞታቸው ተደፈነ» ብለው ነገሩኝ፡ እንደው ማን ይሙት ይህንን ችግር ለመቅረፍ በ300 ዓመት ታሪክ ላይ አፈር ሞልቶ ከመድፈን ይልቅ በአሮጌ ቆርቆሮ በሚገባ አጥሮ መከላከል አይቻልም ነበር?
ምን ይሄ ብቻ፤ ግንቦቹ ሲሠሩ በዚያ ዘመን የተመረተው ሲሚንቶ የተዘጋጀበት የመቀመሚያ ገንዳም በአፈር እየተዋጠ ነው፡፡ የገንዳው አሠራር ራሱ ጥበብ ሆኖ፣ ለሌሎች ጥበቦችም መፍለቂያ ነበረ፡፡ ግን ምንያደርጋል ወደ አፈር ለመግባት እየተሰናበተን ይገኛል፡፡የአዞዞ ተወላጆች፣ የቅርስ እና ታሪክ ወዳጆች፣ የአካባቢው ቤተ ክህነት፣ የቅርስ፣ የባህል እና ቱሪዝም አካላት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የጥንቷ አዞዞ ከመሬት ሥር ገብታ ከዓይን ከመጥፋቷ በፊት የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ፡፡ አዞዞ ትጣራለች፡፡
ከአዞዞ ተክለ ሃይማኖት ፣ጎንደር
Habtamu/Awassa
ReplyDeleteHi dan
I was looking for your today's post based on your promise. I was doing it starting from the morning. Now U keep your promise.
10q too much
Wish U all the best
Wish me/us the bright mental to read U
I am craying...Idon't know what to do that is all I have...I heared my home town Voice...what should I do??? You should to find something...I am waiting ur solution.
ReplyDeleteYemisema yistat
ReplyDeleteIt's very disappointing to see such heritage being disappear at our time. I think well organised awareness campaign for local residences may be enough to reserve it. If they reserve the heritage as much as possible, it can attract national and international tourists who help to grow local businesses.
ReplyDeleteከሰላሳ ቀን በፊት ጎነደር ነበርኩ ሃገርና ታሪክ ለመጎበኘት በዬ። የጎነደር ታላለቅ ታሪኮችን እግዚአበሄርና ግዜ የፈቀዱልኝን ያህል ተመለካክቼ ዛሬ የምትጣራው አዞዞ ነበርኩ።አላማዬ ሀገሬንና ታሪካችንን የማየት ስለነበረ አሰተናጋጆቼን አዞዞ ከሃያአምስትና ከሰላሳ ዓመት በላይ የኖሩትን ጠየቅሁ አዞዞ ላይ ማየት የሚገባኝ ታሪክ ንገሩኝ ሳላየው እነዳልሄድ ብዬ፤አንድም ሰው ያዞዞን ታሪክ አሁን የምትነገረኝን ሊነግረኝ የደፈረ የለም።ቀደም ብዬ አውቄው በነበር መጣም ነው የቆጨኝ ዳኒ።ትውልዳችን ላኢ ስለታሪኩ መስራት አለብን በዬ አስባለሁ ቢጠፋም በታሪክነቱ ማስዋወቅ ማሳየት ነበረ ብሎ መናገርን እንዲለምድ ማለቴ ነው።አሁን ሳነበው ምን ተሰማኝ መሰለህ ይህንን ደብዳቤ ማን ባደረሰልኝ አልኩ ለአዞዞ ወገኖቼ።ትንሽ ታሪኩን ዞር ብሎ እነዲያይ እነዲረዳ ማለቴ ነው።እኔን መሰል ወንድሞቼ ዝግጅት አድረጉ ታሪካችሁን ለማወቅ።ለመጎበኘት።አደራ ባለታሪኮቹ ቁጭ ብለን ሳናቀው ሌላው እንዳያስረዳን ።ዳኒ ወንድሜ ከልቤ ላመሰግንህ እወዳለሁ ወደአዞዞ እደመለከት ሆኛለሁ።እግዚአበሄር ይስትልኝ።
ReplyDeleteወገኔ ለታሪክህ ግዜ ስጥ እባክህ
be Ethiopia tesfa yalkorete ande anten ayehu
ReplyDelete+++
ReplyDeleteBe Kirstos ejege yetwededk wendmach QHY! endalamrben yemi yamelkt melkt new? yetelant manntachnen eyzngan yefrenj weraj sensbsb yehw yemanet asharachnen eykabern mehoneun yemiasayew teri eyferdaben new. Er wegen enenqa ebakachun?????????????? +++
Ke toronto akbari betseboch
Wow!If it is not now, when?
ReplyDeleteምን ማለት ያቻላል! ታሪክ የማይወድ ትውልድ? ቅርስ
ReplyDeleteየማይጠብቅ ትውልድ? .............ግራ ገብቶኛል፡፡ ዲ. ዳንኤል እኔ የምመክርህ ጽሁፍህን ለክልሉ መስተዳድር ከቻልክ ብተሰጣቸው፡፡ ወይም ይህንን ብሎግ የሚከታተሉ የአካባቢው ተወላጆች፣ አለመስተዳድሩ ቅርብ የሆናችሁ በሰራ አጋጣሚ መረጃውን ማቅረብ ይቻላል፡፡ እኔ ግን የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን አማራ ፐሮግራም ላይ ለሉ አዘጋጆች ኢ-ሜል እልካለሁ፡፡
ለጊዜው እንደመፍሔ ያሰብኩት ይሄ ነው ሌሎች ወንድሞች እህቶችም የመፍትሄ ጥቆማዎችን እናድርግ፡፡
ይቆየን
Wow what an eagle eye? It is our birth place but I know little about Azezo and its surrounding. There are so many assumptions on where the name "Azezo" it self drives from.Although,it is shame for us,(since we grew around there, we should be at least a source of information for your work. However,...) Dani please tell us the history of our locality (ጉዋሮ) By the way is it possible to call Azezo as a separate entity? b/c you begin your article by "ወደ ጎንደር ከተማ ልትገቡ ጥቂት ሲቀራችሁ...". I think at list for about the last half century, Azezo considered as one kebele of Gondar administratively. So, it is better to change your wording " አዘዞ ከጎንደር 21 ቀበሌዎች ዘንድዋ..." ቂ. ቂ. ቂ... ይች ናት ሂስ
ReplyDeleteእረኛ ነዉ ብዬ ተስፋ ያደረኩት
ReplyDeleteጥጃዋን ሊያደልብ ላሟን አሰዋት
ልጆች ማሳደጊያ እርጞ የለኝ ወተት
እኔስ ምን ቀረልኝ የምቆይበት
እንግዲህ የተክለኃይማኖት አምላክ የማመለከተውን አካል ልቡን ያነሳሳ እኛም የቻልነውን የምንሰጥበት ነገር ቢመቻች
ReplyDeleteየምሥራች ገብርኤል
kalhiwot yaseman!!!tarekachen tefto kamyetachen befet lenasebbet yegebal !hulachenem yerasachenen enweta!
ReplyDeleteDear Dn.Daniel;
ReplyDeleteThank you for your figurative narration about Azezo and its surroundings.May God bless you much.
Egziabher yestelne Q H Y wendmchen ERI BELE GUNDER asetwayune yezezlen engdhe le boutawe
ReplyDeleteThanks Dn. Daniel.
ReplyDeleteI am from Gondar but has never heard of any of the comments you gave....I appreciate your endeavors...How can we be expected to defend something without any knowledge about it? Whose fault is it? I don't know...From now on, I'll at least try to know the history of Azezo.
በጣም ደስ የሚሉ ብዙ ታሪካዊ የሆኑ ነገሮች እያሉን ትኩረታችንን በአክሱም እና በላሊበላ ላይ ብቻ በማድርግ ሊሎቹ እንዲጠፋ እየፈቀድን ነዉ። በሚሊየን የሚቆጠር ብር መኪናና ሃውልት ላይ ከሚፈስ ምን አለበት ለእንደነዚህ ላሉ ከትውልድ ትውልድ ለሚተላለፉ፣ ለሀገር /ለቤተክርስትያን/ ገቢ ለሚያስገጙ (በቱረዝም መልክ) ቁም ነገሮች ቢውል?
ReplyDeleteYante Tsihufoch Eyaguwagu Yalkubinal.
ReplyDeleteBerta eski wendimalem,
Thankyou dani. I never know before.
ReplyDeleteWe will help you by any means. please!!! Dani.
በጣም ደስ የሚል ታሪክ ነው። ለሚጠበቅብጝ ነገር ሁሉ ዝግዱ ነጝ።
ReplyDeletebetam tiru mereja new. Teyakina enbabi tiwled mehon endalebin yisemagnal.
ReplyDeleteLet the blessing of God be with u!
+++
ReplyDeleteደሞዙን ቢጥል አንስተው ጠጡበት
ባርንጣውን ቢጥል ወስደው ደመቁበት
ከዘራውን ቢጥል ተመረኮዙበት
በሂደበት ሁሉ እየተከተሉ
በጣለው ሲያገጡ በጣለው ሲያተርፉ
እራሱን ሲጥል ግን አይተውት አለፉ!!! በበውቀቱ
one person say "You should to find something...I am waiting ur solution"
ReplyDeleteother "it is better to change your wording " አዘዞ ከጎንደር 21 ቀበሌዎች ዘንድዋ..." ቂ. ቂ. ቂ... ይች ናት ሂስ "
ena eskemeche new besew mind yemenasebi were is our mind pius Dn.Daniel mengeduni kasayeni megalebi yalebin be gara new enji eskemeche new ----- lelaw word corection kemseti why dont u give one solution yeminfelgew esuni newena
plus lelechi endaluti le kiresochacheni bot seteni yemitebekibenini endregi
Amelaki lebona yesteni
Amen
...Thank Dn Daniel...it shame for me bcoz i am from Azezo and i never heard such hitory other than Azezo t/haymanot church...anyways i am ready to do whatever i can..in the mean time i living in Europe but i will take full responsibility starting from getting permission from government upto reconstruction hisorically places when i get back after 1 and half yearr..anyways if anyone who want participate please let's discuss..u can reach me via eyobe8@gmail.com
ReplyDeleteI don't expect this kinds of azezo explanation thanks my brother danei its so amusing I was born their and also lived at least 20 years more but not known this history for azezo I tell some body about their based on risk
ReplyDeleteቅርሶቻችንን የመጠበቅ የሁላችን አላፊነት ነው
ReplyDelete