Saturday, November 6, 2010

ከአዞዞ እስከ ጃናሞራ

ሼህ አብደላስጥ አባ ከርቤ

ወደ ጎንደር ከተማ ልትገቡ ጥቂት ሲቀራችሁ አዞዞ የተባለውን ጥንታዊ ከተማ ታገኙ ታላችሁ፡፡ ጎንደር ከመቆረቆሯ በፊት የተከተመው ይህ አካባቢ ይበልጥ የሚታ ወቀው በአዞዞ ተክለ ሃይማኖት ነው፡፡ ከ300 ዓመታት በፊት የተተከለው ይህ ታላቅ ደብር ከደብረ ሊባኖስ ገዳም ጋር የቆየ ግንኙነት አለው፡፡ ታሪኩን በነገው ዕለት እተርክላቸኋለሁ፡፡ ለዛሬ ወደ ሼህ አብደላ ሰጥ አባ ከርቤ ልውሰዳችሁ፡፡

የአካባቢው አፈ ታሪክ እንደሚናገረው እኒህ ሰው በዐፄ ሱስንዮስ ዘመን የነበሩ ናቸው፡፡ በዚያ ዘመን አዞዞ ላይ የሱስንዮስን እምነት አልቀበል ያሉ 500 የአዞዞ እና የአካባቢው መነኮሳት ታርደዋል፡፡ እነርሱ የታረዱበት ቦታ ላይ ቀስተ ደመና ተተክሎ ነበር፡፡ እኒህ ሰው ከሩቅ ሀገር ወደ ጎንደር ሲመጡ በቦታው የተተከለው ቀስተ ደመና ይታያቸዋል፡፡ በነገሩ ተገርመው ወደ ቦታው ሲመጡ መነኮሳቱ ሃይማታችንን አንለውጥም ብለው እየታረዱ ነው፡፡ ሼህ አብደላም ይህ በረከት አያምልጠኝ ብለው ቀረቡ፡፡ አንገታቸውንም ለሰይፍ ሰጡ፡፡ ወዲያውም ከሰማዕታት ጋር ተቆጠሩ፡፡ የተቀበሩበት ቦታ ከአዞዞ ፊት ለፊት ተራራው ላይ ይታያል፡፡ መታሰቢያቸው በየዓመቱ ትንሣኤ በዋለ በሦስተኛው ቀን ይደረጋል፤ እስላሞቹም ክርስቲያኖቹም በቦታው ይገኛሉ፣ ብለው የአካባቢው ነዋሪዎች ነግረውኛል፡፡

አስደናቂው የሼህ አብደላስጥ አባ ከርቤ ታሪክ ይበልጥ ሊጠና የሚገባው ይመስለኛል፡፡

አዞዞ ተክለ ሃይማኖት

14 comments:

 1. +++

  ምን ያህል የታደሉ ናቸው ከአኛ ያልሆኑ ከሌላ በረት የሆኑ ስንት አሉ አርሱ የሚመርጣቸው
  አህዛብ አንዳይናጠቁን ከተመረጡት ያድርገን በቸርነቱ መድሃኔዓለም ጸጋውን ያብዛልህ አሁንም ዳኒ

  ReplyDelete
 2. Hi Dani, we all long for your thoughts about Azezo.

  Esdros, Zelideta

  ReplyDelete
 3. በጣም ደስ የሚል ታሪክ ነው። በአሁን ግዚ እንደ ሼህ አብደላስጥ አባ ከርቤ ያለ አይደለም ከአኛ ካልሆኑት ከአኛ ከሆኑት ይገኛል? ምናልባት በገዳም እና በበረሀ በጸሎት ተወስነው ካሉት ሊኖር ይችላል። በከተማ ያሉት ግን (ሰባኪው፣ ዲ/ኑ፤....) አቆሰሉን።

  ReplyDelete
 4. Dani eski wede Gonder gora bleh ye Atse Fasil tarik asnebben ahun betemengstu yeteserabet bota Tana gedamat koytew be subae yetemerut bota endehone and abat achawtewgnal. Ke susnyos behuala atse Fasil keleloch gar subae gebtew wefcho lemtfechew raeyu tegeltso FASIL YINGES HAYMANOT YMELES bla menageruan yangize atse fasil eziaw gedam subae lay endeneberu behuala be raey betemengsthn yemtseraw ----yetebale bota new bluachew botawn sifelgu and gebere sile botaw siawera semtew eski dgemna traw? blewt botawn tertolachew behuala asayegn blewt ahun betemengstu yeteserabet bota lay yegeberew bere tegnto alnesam maletu behuala le Atse Fasil tenesto endesegede....awrtewgnal eski bedenb ayteh asnebben merejaw ynorhal bye new. Ene Tana gedamat Daga estifanos yalu abat nachew yawerugn gn masrejawn atenakreh eski asnebben.

  ReplyDelete
 5. Dear Dn.Daniel,

  It is really a very nice story. Short and precious and to the point.

  You are always our source, I do expect more and more information/knowledge from you.

  KK
  USA

  ReplyDelete
 6. Bless u Daniel

  I hope we will read more about Azezo and the story in the very soon

  ReplyDelete
 7. በኔ እይታ ከሸህ አብደላ ይልቅ የባእድ እምነት አንቀበልም፡፡የኛው ምን ጎደለውና? ሰብአዊነት፤ስርአተ አምልኮ፤የተዋጣለት ቀኖና ምን ቀረን? ምን ጎደለን? ብለን ነው ኢተዮጵያዊ መሰረት ያለው እምነታችን የምን ቀይረው በማለት መስዋእት የሆኑት መነኮሳት ታሪክ የጥንቱ መለያ ታሪካችን አካል ሆኖ አግንቸዋለሁ፡፡
  ዛሬ በእምነታችን ዙሪያ ያጣነው እንዲህ አይነት ቀናኢነት ነው፡፡ኢትዮጵያዊ እምነት ምንም የሚጎድለው ነገር የለም፡እንዲያውም ከመካከለኛው ዘመን ከአውሮፓ እምነት ጋር ሲነጻጸር ኢትየጲያዊ እምነት በእጅጉ ወደር የሌለውና አኩሪም ነው፡
  ለምሳሌ በአውሮፓ በመካከለኛው ዘመን ስለሳይንስ በይፋ መናገር የሚያሰቀትል፤የሚያሰገርፍ የሚያስግዝ ነበር፡፡የነጋሊሎን ታሪክ ልብ የሏል፡፡በዚህ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ ግን የተለየ ነበር፡፡አይደለምና ስለሳይንስ፤ ስለቀኖናችን አንዳንድ ነገር ያሎ እንከዋን ለምሳሌ እንደ ዘራይቆብ አባስጢፋኖስ ምንም አልሆኑም፡፡ግፋ ቢል ከገዳም ዉጪ ከቤተክርሰቲያን ክጥር ግቢ ገለል ሊደረጉ ይችላሉ፡፡ከዚህ ያለፈ ግን እርምጃ አይወሰድባቸውም፡፡
  ለዚህም ነው ዐጼ ትወድሮስ እንግሊዞች የሃይማኖት አስተማሪ እንላክልህ ሲሏቸው ከናንተ ቴክኖሎጃችሁን እንጅ ሌላ ነገራችሁን አልፈልግም ማለታቸው፡፡ለነገሩ ከፈረንጅ ትክኖሎግ እንጅ ሌላ ምንስ ይማሯል;
  በመካከለኛው ዘመን ያውሮፓ ሃይማኖቶች ተቻችሎ መኖርን አያውቁም ነበር፡፡የኛ ግን አይደለም ከሳይንሰ ጋር መጠጊያ ላጡ ባገራቸው ሳይቀር እምነታቸውን ማስፋፋት መስበክ ለተከለከሉ ሁሉ መጠጊያ ዋሻ ነበሩ፡፡ሸህ አብደላም ከመነኮሳቱ ጋር ሰማእት መሆንን ያስመረጣቸውም ምክኒያት ይህ ሊሆን ይችላል፡

  ReplyDelete
 8. አሜን ወአሜን!November 7, 2010 at 11:09 PM

  ጸጋና ሰላም ለእናንተይሁን !
  ወንድም ዳንኤልም ስለጥረትህና ትጋትህ እግዚአብሔር ይባርክህ!
  ምንም እንኳን አገርን መውደድና ሕዝብንም ማፍቀር እጅጉን የሚያስፈልግ ነገር ቢሆንም ከክርስትና እምነት ጋር ግን በጭራሽ ልናቆራኘው አይገባም። ክርስትና በድንበር የተከለለ ምድራዊ አገር የለውም። ባጭሩ ክርስትና ሰማያዊ እንጂ ምድራዊ ዜግነትም የለውም። በመሆኑም ኢትዮጵያዊ፤ እስራኤላዊ፤ ግብጻዊ...የሚባል ክርስትና የለም።ባጭሩ ኢትዮጵያዊ ክርስትና የለም። የሚያጸድቅ ወይም የሚያስኮንን ኢትዮጵያዊነትም የለም። መጤስ ማለት ማንንና ምንን ነው? ኢየሱስ ክርስቶስስ በስጋ የተወለደው ጎንደር ነው ወይስ ጎጃም...? የትኛው ሐዋርያ ነው የቡልጋ ወይም የጭልጋ? ወገኖች አትሳቱ! ክርስትና በኢየሱስ ክርስቶስና በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ የሚገኝ የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስን አምላኩ፤ንጉሱና ጌታው አድርጎ ያልተቀበለ ሰው እስራኤላዊ ቢሆን ኢትዮጵያዊ... የሚጠብቀው የዘለአለም ፍርድ ብቻ ነው። አንድ ሰው ጌታን አምኖ ካልተቀበለ በቀን እጁ መስቀል ይዞ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ካባ ለብሶ ሲኦል ሊወርድ ይችላል።
  ክርስትና ከአገር በላይ ነው።
  ኢየሱስ ክርስቶስ በሁሉም ነገር ላይ ጌታ ነው።
  እግዚአብሔር ይባርካችሁ!

  ReplyDelete
 9. "ዛሬ በእምነታችን ዙሪያ ያጣነው እንዲህ አይነት ቀናኢነት ነው፡፡ኢትዮጵያዊ እምነት ምንም የሚጎድለው ነገር የለም" ምን ማለት ነው???!አልገባኝም!!

  ReplyDelete
 10. ዺያቆን ዳንኤል፡
  በጣም የሚገርም ታሪክ ነው የነገርከን እግዚአብሔር ይስጥህ። የድሮ ኢትዮጵያዊያን አስተሳሰብ በጣም የሚገርም ነው!!!

  ReplyDelete
 11. “ኢየሱስ ክርስቶስስ በስጋ የተወለደው ጎንደር ነው ወይስ ጎጃም...? የትኛው ሐዋርያ ነው የቡልጋ ወይም የጭልጋ? ወገኖች አትሳቱ! ክርስትና በኢየሱስ ክርስቶስና በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን”
  ከዚህ በላይ ቃል በቃል ያስቀመጥሁት አሜን ወአሜን የተባሉ ሃሳብ ሰጭ የሰነዘሩት አስተያየት ነው፡፡
  ወገኖቸ
  የመጀመሪያወ ጥያቄየ ይህ ጽሃፊ ማ ነው?ይታያችሁ እያሉን ያሉት ከፈረንጅ ዉጭ የበቃ የነቃ የሃይማኖት ሃዋሪያና አርአያ ኢትጵያ ውስጥ አልተፈጠረም ነው የሚሉን፡፡መቸም ይህ አባባል ትልቅ ድፍረትና ንቀት ነው፡፡ስድብም ነው፡፡
  የኛን ጾመ ድጓ ዝማሬ ቅኔ ዜማ የደረሱ የአክሱም፤የጎንደርና የጎጃም ሊቃውንት የነጭ ሃዋሪያትን የሚያከነዱ እንጅ የሚያንሱ አይደሉም፡፡ለነገሩ እንደ አሜን ወአሜን አይነቶቹ በእንግሊዝኛ የተጻፈ ካልሆነ ግዕዙን ከመጤፍ የሚቆጥት አይመስለኝም፡፡ይህ አባባሌ ከስሜት የመነጨ እንዳይመስላችሁ፡፡በኢትዮጵያ የቤተክህነት ስርአት ያለፈ እንዲህ አይነት አመለካከት ከቶ ሊኖረው እንደማይችል እርግጠኛ ስለሆንኩ ነው፡፡
  እግዚአብሄር ጥንታዊ ሃይማኖታችን ከሚያኮስሱ ይሰውረን

  ReplyDelete
 12. መጤስ ማለት ማንንና ምንን ነው?
  Let me brief you Amen WoAmen what it means and for whom it concerns for your question cited in the above.
  During the direct and neo colonialism the main tool to manipulate the subject of the colonialist force were their religions.
  The first weapon served to paralyze, demonized and destroy at large the identity of the black people were the religion of the white people.
  It was their religion and the leader of it preached not to say no more subjugation by paraphrasing their book that say it is on his will the white force comes here to suffer you. So that what is expected to do on your behalf is nothing but to say AMEN WoAmen.
  Amen woAmen, mind you, in all ethnic conflict, genocide happened in Africa, there always was and is the invisible and visible hand of the white religion that served as a tool to destroy the black world and instead installed their own white world. There was not an ideologue for that matter the white rulers invading forces other than the white pastors.
  Refer the colonial history of Keniya,Rwanda and congo.in thse countries, all miscarries,genocide,mind boggling crime against humanity had been spearheaded by the white religion leaders.
  Why they massacred the nun of Azezo Teklehaymanot written on this blog a day ago?
  Because it is caused from their fundamental character they had done it in elsewhere African countries.
  You may collect some data’s here in our land in relation to this fact. There are some NGos financed to serve this end. In these NGO nobody will not be hired whatever he/she has a desired qualification if both are indigenous religion follower. Go to and ask world vision.
  To sum up, መጤ refers for the agents of neo colonialism organized in name of religion to destroy our identity and planet their own in order to make us an everlasting slave of them. Is it clear now?

  ReplyDelete
 13. Dear Dani:

  I like you YAZEZO LIJ as some one said please try to visit other places of Ethiopia i would love if could travel to Wolkait, Tegede and Telemt and Waldiba and give us some inside report may God be with you
  sincerely
  Hyley/g

  ReplyDelete