Sunday, October 31, 2010

እንማር ወይስ እንማረር

ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤን በመላው ዓለም የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን እና የበጎ ነገር ወዳጆች ሁሉ ሲከታተሉት ነበረ፡፡ ጉባኤው በሦስት ነገሮች የተሻለ ገጽታ ነበበረው፡፡

1/ የብጹአን አባቶች አንድነት በተሻለ ጎልቶ የወጣበት በመሆኑ

2/  የቤተ ክርስቲያንን ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉ ውሳኔዎች የተላለፉበት በመሆኑ

3/  የሃሳብ ክርክር እንጂ የጡንቻ ክርክር ያልታየበት በመሆኑ ናቸው፡፡

ጉባኤው ይህንን የመሰለ መልክ እንዲኖረው ያደረጉ ምክንያችም ነበሩ፡፡ የመጀመርያው እግዚአብሔር ከቤተ ክርስቲያን ጋር መሆኑ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር የተለያት ብትሆን ኖሮ መንፈሳችን በተስፋ መቁረጥ እንደተሞላ ይቀር ነበር፡፡ አንድ ስሙ ያልተገለጠ የኢየሩሳሌም ተሳላሚ ተናገረው ብሎ ጄምስ ብስ እንደገለጠው «ብንወድቅም እዚአብሔር ግን ከወደቅነው ከኛ ጋር ነበር»፡፡ በሌላም በኩል ደግሞ እኛ የማናውቃቸው፣ እግዚአብሔር ግን የሚያውቃቸው ቅዱሳን የጸለዩት ጸሎት መልስም ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በተለያየ መልኩ በጉዳዩ ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ያበረከቱ ምእመናን፣ ባለሞያዎች፣ ሽማግሌዎች ወዘተ ውጤትም ነው፡፡ እንደ ገናም አያሌ ሚዲያዎች ከወትሮው በተለየ መልኩ ችግሩን ሊፈታ በሚችል መልኩ መንቀሳቀሳቸው ያመጣው የቤተ ክርስቲያን ድል ነው፡፡

ይህ ሁሉ ተደርጎ በመጨረሻ የሰማነው ዓይነት ውጤት ተገኝቷል፡፡

አንዳንዶቻችን ፓትርያርኩ ሲወርዱ ወይንም ሥልጣናቸው ሲገደብ፣ ሐውልቱ ሲፈርስ፣ ሙስና ይፈጽማሉ የተባሉት አካላት በሕግ ሲጠየቁ፣ የተበላሸው አስተዳደር በሥር ነቀል ለውጥ ሲሻሻል ለማየት ባለመ ቻላችን ውጤቱን መጨበጥ ተስኖናል፡፡ በተለይም በስተ መጨረሻ ቃለ ጉባኤ በመፈረም እና ባለመፈረም፣ ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት እና ባለመስጠት በተፈጠረ ውዝግብ የጉባኤው ድምቀት መደብዘዙ አንዳንዶቻችንን ተስፋ አስቆርጦናል፡፡

በርግጥ ቤተ ክህነት መሠረታዊ ለውጥ ከሚያስፈልገው ጊዜ እጅግ ዘግይቷል፡፡ የቤተ ክህነቱ አሠራርም expiry date አልፏል፡፡ በውስጡ ከሚሠሩት ሠራተኞች ጀምሮ የማይማረርበት የለም፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱን ዋና ተልዕኮ ለማስፈጸም ባለመቻል፣ በሠራተኛ አቀጣጠር፣ በመዋቅራዊ ተገቢነት፣ በፋይናንስ አያያዝ፣ በአምባገነናዊ አሠራር፣ በማስፈጸም ዐቅም ማነስ፣ ወዘተ የተወሳሰበ ችግር ላይ ይገኛል፡፡ ታድያ እነዚህን የተወሳሰቡ የዘመናት ችግሮች በአንድ የሲኖዶስ ጉባኤ መፍታት ይቻላልን? አሁን ያሉት ብጹአን አባቶችስ ብቻቸውን እነዚህን ችግሮች መፍታት ይችላሉ? እኛስ በጉባኤውና በሂደቱ መማር ነው ወይስ መማረር ያለብን?

የአሁኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ውሳኔ ያላረካቸው፣ «ድሮም ብለን ነበር» ያሉ፣ «ምን ዋጋ አለው» ብለው ተስፋ የቆረጡ፣ «ከዛሬ ጀምሮ» ብለው የተማረሩ ወገኖቼ ንዴት እና ብስጭት የሚመነጨው ራሱን ቤተ ክህነቱን ካለማወቅ ጭምር ነው፡፡ ለመሆኑ አንዳንዶቻችን ወደ ቤተ ክህነት ግቢ ገብተን እናውቃለን? ከቤተ ክህነት ሰዎች ጋር ሠርተንስ እናውቃለን? የቤተ ክህነቱን የአሠራር መዋቅር አናው ቀውም፣ ሌሎቻችንም የቤተ ክህነት ሰዎችን የአሠራር ዐቅም እና ጠባያት አልተረዳንላቸውም፡፡ በዚህም የተነሣ ስለ ቤተ ክህነቱ የምናስበው የሆነውን ራሱን ሳይሆን እንዲሆን የምንፈልገውን ነው፡፡ ስለ ቤተ ክህነት መዋቅር እና አሠራር ስናስብም በትምህርት ቤት ከተማርናቸው አሠራሮች ወይንም በየመሥሪያ ቤቱ ከለመድናቸው አሠራሮች በመነሣት እንጂ ራሱን ቤተ ክህነቱን ከማወቅ አይደለም፡፡

የቤተ ክህነት አሠራርኮ በሀገሪቱ ብቸኛው አሠራር ነው፡፡ ገንዘብ ሚኒስቴር በሰባዎቹ በተዋቸው አሠራሮች ገንዘብ የሚሰበሰበው በቤተ ክህነት ነው፡፡ ያለ አካውንታንት ሂሳብ የሚሠራው በቤተ ክህነት ነው፡፡ የሰው ኃይል አስተዳደር ሥልጠና ያልወሰዱ ሰዎች የሰው ኃይል የሚያስተዳድሩት በቤተ ክህነት ነው፡፡ ላለፉት ሃምሳ ዓመታት ምንም ዓይነት የመዋቅር ማሻሻያ ያላደረጉ ሁለት ተቋማት በኢትዮጵያ አሉ፡፡ ዕድር እና ቤተ ክህነት፡፡ ከመላዋ ኢትዮጵያ የጠፉ ዋልያዎች በስሜን ተራራ እንደሚገኙ ሁሉ በመላ ኢትዮጵያ እየጠፉ ያሉት ታይፕ ራይተሮች የሚገኙት በቤተ ክህነት ነው፡፡

በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እያንቀሳቀሰ፣ ከ45 ሚሊዮን በላይ ምእመን እየመራ፣ ከ35 ሺ አብያተ ክርስቲያናት ከ1100 በላይ ገዳማት እየመራ፣ ዕቅድ የሌለው ብቸኛ የሀገሪቱ ተቋም ቤተ ክህነት ነው፡፡ ምን ያህል ሠራተኞች እንደሚያስፈልጉት ልኩ የማይታወቅ ብቸኛ መሥሪያ ቤት ቤተ ክህነት ነው፡፡

አብዛኞቹ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ዓለምን ባጨናነቁት ልዩ ልዩ ዓይነት ስብሰባዎች የመካፈል እና ልምድ የማግኘት ዕድል የላቸውም፡፡ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው አያውቁም፡፡ በባለሞያዎች ከሚመሩ ኮሚቴዎች ጋር የመሥራት ልምድ አላገኙም፡፡ በየሀገረ ስብከቱ የመንበረ ጵጵስና የሰበካ አጠቃላይ ጉባኤያት አይደረጉም፡፡ በመንበረ ጵጵስና ደረጃ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎች እየሠሩ አይደሉም፡፡

ዓለም በየጊዜው በአሠራር ለውጥ ላይ በመሆንዋ ለኃላፊዎች እና ለበታች ሠራተኞች ሥልጠና፣ ሴሚናር፣ ዐውደ ጥናት እና የሞያ ማሻሻያ ኮርሶችን ይሰጣል፡፡ በአንድ ወቅት ዋና ዋና የሀገራችን የፖለቲካ አመራሮች በተልዕኮ ትምህርት በከፍተኛ ዲግሪ መመረቃቸው ተዘግቦ ነበር፡፡ በቤተ ክህነት ለብፁአን አባቶችም ሆነ ለሌሎች ኃላፊዎች ሴሚናሮች፣ የሞያ ማሻሻያዎች፣ የአዳዲስ አሠራች ማስተዋወቂያዎች፣ ዐውደ ጥናቶች እና ሥልጠናዎች አይሰጡም፡፡ እንዲያውም አንዳንዴ እነዚህን ማድረግ ቀርቶ ማሰብ እንደ ድፍረት የተቆጠረበት ጊዜም አለ፡፡

በቤተ ክህነቱ ሁለት ዓይነት አገልግሎቶች እየተሰጡ ነው፡፡ መንፈሳዊ እና ዓለማዊ አገልግሎቶች፡፡ ዓለማዊ ሲባል በቀጥታ መንፈሳዊ ይዘት የሌላቸው ለማለት ነው፡፡ ቀደምት አባቶች በዘመኑ ለነበሩት ዓለማዊ አሠራሮች ምን ያህል ቅርብ እንደነበሩ የሚያሳየን የጻፏቸው እና የተረጎሟቸው ጽሑፎች ናቸው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከመንፈሳዊው ነገር በተጨማሪ የሕግ ለምሳሌ ፍትሕ ሥጋዊ፣ የታሪክ ለምሳሌ የዓለም ታሪክ፣ የሕንፃ አሠራር፣ የፍልስፍና ለምሳሌ አንጋረ ፈላስፋ፣ ጽፈው እና ተርጉመው አንበዋቸዋል፣ ተጠቅመውባቸዋልም፡፡

በየገዳማቱ ያለውን መንፈሳዊውን አሠራር ከዴሞክራሲያዊው አሠራር ጋር ያጣመረውን አሠራር ስናይ ብቃታቸውን እናደንቃለን፡፡ የገዳሙን መናንያን የገዳሙን ምርፋቆች/ ሥራ አስፈጻሚዎች ይመርጣሉ/፤ ምርፋቆቹ ደግሞ አበ ምኔቱን ይመርጣሉ፡፡ የገዳሙን አጠቃላይ ሁኔታዎች በተመለከተ እነዚህ ሥራ አሥፈጻሚዎች በጋራ እየተወያዩ ነበር የሚወስኑት፡፡

ቤተ ክርስቲያኒቱ ዘመናዊውን ቤተ ክህነት ስትጀምረው ግን ዘመናዊውን አሠራር ከመንፈሳዊ አሠራር ጋር በተጣጣመ መልኩ ከመከተል ይልቅ ፊውዳላዊውን አሠራር ወሰደች፡፡ ሀገሪቱ ከፊውዳሊዝም ወደ ካፒታሊዝም፣ ከካፒታሊዝም ወደ ሶሻሊዝም፣ ከሶሻሊዝም ተመልሳ ወደ ካፒታሊዝም ስትገለባበጥ ቤተ ክህነቱ ግን እስካሁን ያንኑ ፊውዳላዊ አሠራር እንደያዘ ነው፡፡

አሁንም «ከመስቀልዎ እግር ሥር ተንበርክኬ እለምናለሁ» እያሉ የሚለምኑ የሥራ ደብዳቤዎች አሉን፡፡ «ደጅ መጥናት» እንደ አንድ የሥራ መለኪያ ነው፡፡ አሠራሩ ወይንም ሕጉ ምን ይላል? ከማለት ይልቅ ኃላፊው ምን ይላሉ? የሚለው ዋናው የሥራ ማስኬጃ ነው፡፡ በአንድ ጉዳይ ላይ ከመነጋገር ይልቅ ሽንገላ እና ውዳሴ ማዥጎድጎድ ሞያ የሆነበት ቤት ነው፡፡ በጥንቱ የሀገራችን አሠራር ጉዳይ ለማስፈጸም ባልደረባ ይሰጥ እንደነበረው ሁሉ ጉዳይን በመሥመሩ ሳይሆን በሰው በኩል ማስፈጸም እንደ ዋና አሠራር የሚካሄድበት ቤት ነው፡፡

ንጉሡ ወይንም መሳፍንቱ የሁሉ ነገር ባለቤት እና ከላይ እስከ ታች አዛዥ ናዛዥ እንደሚሆኑት ሁሉ ፓትርያርኩ ከጥበቃ እስከ ጳጳሳት የሚመድቡበት ቤት ነው፡፡ በዐፄ ምኒሊክ ዘመን እንደነበረው ሁሉ «ጸሐፊ» /ጽሑፍ የሚጽፍ ወይንም executive secretary ማለት አይደለም/ የሚባል የኃላፊነት ቦታ ያለው በቤተ ክህነት ብቻ ነው፡፡ በርግጠኛነት በየስንት ጊዜው እንደሚታተም የማይታወቅ ጋዜጣ ያለው በቤተ ክህነት ነው፡፡

እንግዲህ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ነው በአንድ ጉባኤ እንዲፈቱ የምንፈልገው፡፡

አሁን ያለው ቤተ ክህነት ለቤተ ክርስቲያናችን የሚመጥናት አይደለም፡፡ ያንስባታል፡፡ ሥርዓትዋ፣ ትውፊቷ፣ ዶግማዋ፣ ጥርት ብሎ የሚታየውን ያህል የቤተ ክህነቱ አሠራር ገና አልጠራም፡፡ የመልከ መልካም ልጅን ገጽታ የማይገባ አለባበስ እንደሚያጠፋው ሁሉ የቤተ ክርስቲያኒቱን መልካም ገጽታ የቤተ ክህነቱ ዝርክርክነት፣ ደረጃው አለመጠበቅ እና ብቁ አለመሆን ከልሎታል፡፡

ስለሆነም ካሁኑ ጉባኤ መማር እንጂ በጉባኤው ፍጹም ነገር በመጠበቅ መማረሩ ውጤት አያመጣልንም፡፡ ተጀመረ እንጂ አላበቃም፡፡ በመልካም ጎዳና ላይ ቆምን እንጂ መልካም ነገሮችን ሁሉ ሠርተን አልፈጸ ምንም፡፡ ድል ብቻ ሳይሆን ሂደትም ውጤት ነው፡፡ ሐዋርያት ዓለምን ሁሉ እንዲያስተምሩ ታዝዘው ነበር፡፡ ከመካከላቸው ግን ዓለምን ሙሉ የዞረ የለም፡፡ ነገር ግን ወንጌል በዓለም ዙርያ የሚሰበክበትን መንገድ ተልመው፣ ጀምረው እና ለዚያም መሥዋዕትነት ከፍለው አለፉ፡፡ ሂደቱ ነበር ውጤታቸው፡፡ እኛም ችግሩን ሁሉ በዘመናችን ላንፈታው እንችል ይሆናል፡፡ ግን በመንገዱ ላይ ነን ወይ? ነው ጥያቄው፡፡

አሁን ልናስብበት የሚገባን ዋናው ነገር ምን ልንማር ምንስ ልናደርግ እንችላለን? የሚለው ነው፡፡ እንደ እኔ ግምት የአሁኑ ጉባኤ አምስት ነገሮች ያስተምረናል፡፡

የመጀመርያው አባቶች ቤተ ክህነቱ አሁን ባለበት ችግር ላይ ከተስማሙ እና መፈታት እንዳለበት የጋራ ግንዛቤ ካላቸው ችግሮቹን መፍታት በአንድነት እንደሚቻል ትምህርት ያገኙበት ነው፡፡ ስለሆነም በየአካባቢው ቤተ ክህነቱ ያለበትን ደረጃ፣ ምን መሆን እንዳለበት? ምን አደጋ ከፊቱ እንደተጋረጠ? የተጠኑ ጥናቶች ለየብጹአን አበው በማቅረብ፣ በማወያየት፣ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በመጠቆም ብንሠራ በቀጣይ ጉባኤያት ከዚህ የተሻሉ ውጤቶች ይገኛሉ፡፡

እስካሁን ድረስ ችግሮቻችንን በማመልከት፣ ንዴታችንን በማሳየት እና ድጋፋችንን በመግለጥ ካልሆነ በቀር የተጠኑ፣ ችግሮችን በግልጥ የሚያሳዩ፣ ለጉባኤው ግብዐት የሚሆኑ እና የብጹአን አባቶችን ግንዛቤ ሊያሳድጉ የሚችሉ የጥናት ውጤቶችን አናቀርብላቸውም፡፡ በዚህም ምክንያት ችግሮቹን የተረዱ እና ለማስወገድ ቆራጥነት ያላቸው አባቶች እንኳን አማራጮችን ለማግኘት አልቻሉም፡፡

ሁለተኛው ደግሞ ሁለገብ ጥረቶች ከተደረጉ መፍትሔዎቹ ቅርብ መሆናቸውን ማየት መቻላችን ነው፡፡ ከአሁኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በፊት እና በተጓዳኝ ግለሰቦች፣ አባቶች፣ ኮሚቴዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ባለሞያዎች በማማከር፣ ሃሳብ በመስጠት፣ ግፊት በማድረግ እና አዎንታዊ ተጽዕኖ ያለማሳደር ባለማሰለስ ሠርተዋል፡፡ በየገዳማቱ እና በየአካባቢው የጸሎት ጸጋ የተሰጣቸው አባቶች እና እናቶችም በብርቱ ተጋድለዋል፡፡

እስከዛሬ ድረስ ብዙ አካላት ለቤተ ክርስቲያን ቅርብ ለቤተ ክህነቱ ግን ሩቅ ነበርን፡፡ አሁን የተከሰተው የቤተ ክህነት ፈተና ካመጣቸው በጎ ውጤቶች አንዱ ሕዝቡ ለቤተ ክህነቱ ጉዳዮች ቅርብ እንዲሆን ማድረጉ ነው፡፡ ጥንት ሲኖዶሱ ይሰብሰብ አይሰብሰብ፣ ጳጳሳት ይሾሙ አይሾሙ፣ ውሳኔ ይወሰን አይወሰን ከቤተ ክህነቱ ሠራተኞች ውጭ የሚያውቅ አልነበረም፡፡ ሌላው ቀርቶ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ማን እንደሆኑ ብዙ ምእመን አይለይም ነበር፡፡ አሁን ግን የቤተ ክህነት ጉዳይ ምእመናን እና ልዩ ልዩ አካላት እንደ ቆቅ ጆሯቸውን ሰትረው የሚከታተሉት ነገር ሆኗል፡፡

ይህ ሁኔታ ይበልጥ መቀጠል አለበት፡፡ የአዋሳ ምእመናን ችግሩን እህህ ብለው ከመጓዝ ይልቅ ሕግ እና ሕጋዊነትን ብቻ ተከትለው በመሄድ ችግሮችን ለመፍታት የተጓዙበት መንገድ ታላቅ አርአያነት ያለው ነው፡፡ በሌሎች ቦታዎችም ምእመናን የቤተ ክርስቲያኒቱን ተልዕኮ የሚያደናቅፉ፣ የሀገርን ገጽታ የሚያበላሹ፣ ዕድገታችንን የሚያቀጭጩ፣ ዝርክርክ እና የተበላሸ አስተዳደርን የሚያበረታቱ አሠራሮችን መንፈሳዊ እና ሕጋዊ በሆነ መንገድ ለማስተካከል መነሣት አለባቸው፡፡ በየአጥቢያው፣ በየወረዳው፣ በየሀገረ ስበከቱ ችግሮች እንዲስተካከሉ አዎንታዊ ግፊት ለማድረግ ወገባችንን አሥረን መነሣት ይገባናል፡፡

ሦስተኛው ትምህርት ብጹአን አባቶች በየግላቸው ያሳዩት ቆራጥነት ነው፡፡ ይህ ግላዊ ቆራጥነት ከጉባኤው ባሻገርም መቀጠል መቻል አለበት፡፡ ጀግንነት የሚጠቅመው ቀጣይነት ሲኖረው ነው፡፡ የእናንተን ጀግንነት የሚፈልጉ አህጉረ ስብከት፣ አጥቢያዎች እና ገዳማት አሉ፡፡ በአባ ወርቅነህ ቋንቋ ለመግለጥ ጋሪው ፈረሱን እየቀደመው ነው፡፡ ይህንን ሁኔታ በአዋሳው ሂደት አይተነዋል፡፡ እናም ብጹአን አባቶች በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ እንዲኖሩ የሚፈልጓቸውን መልካም አሠራሮች በየሀገረ ስብከታቸው መጀመር አለባ ቸው፡፡ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ደረጃ ለሚደረጉ ስሕተቶች ሌላውን ተጠያቂ እያደረግን አመካኘን፤ በየሀገረ ስብከታችንስ በማን ልናመካኝ ነው?

ምእመናን የሚያማርሩት አባት አይተን አንገታችንን እንደደፋነው ሁሉ እስኪ ምእመናኑ የሚሸልሙት አባትም እንይ፡፡ የምእመናን ክብካቤው፣ መንፈሳዊ ብስለቱ፣ አስተዳደሩ፣ የገንዘብ አያያዙ፣ የንብረት አጠባባቁ፣ በምእመናን ብቻ ሳይሆን በአካባቢው የመንግሥት አካላት፣ በሌሎች የእምነት ተቋማት፣ መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች፣ በሚዲያዎች የሚመሰገን ሀገረ ስብከት እስኪ ፍጠሩ፡፡

ጽዳት ከራስ፣ ምሕረት ከመቅደስ ይጀምራል እንዲሉ እስኪ መዋቅራዊውን ማሻሻ ከራሳችሁ ጀምሩት፤ ጵጵስናውን አክብራችሁ አስከብሩት፣ የክህነት አሰጣጡን አስተካክሉ፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች መመዘኛ አውጡ፣ ለሀገረ ስብከታችሁ ዕቅድ ይኑራችሁ፣ የሂሳብ አሠራራችሁን ዘመናዊ አድርጉት፣ ምእመናን በሀገረ ስብከቱ አገልግሎት እንዲሳተፉ አድርጉ፣ ከባለሞያዎች ጋር ሥሩ፣ ከአካባቢው የመንግሥት ተቋማት፣ በጎ አድራጊ ድርጅቶች እና ባለሞያዎች ጋር በመነጋገር የሞያ ማሻሻያ ሥልጠናዎችን እና ሴሚናሮችን ጀምሩ፡፡ መዋቅሩን አስጠኑት፣ የሀገረ ስብከታችሁን ገንዘብ በውጭ ኦዲተርራችሁ አስመርምሩ፡፡ ሀገረ ስብከቱ የእናንተ ነው ማን ይከለክላችኋል፡፡ በጥቂቱ ያልታመነ በብዙ አይሾምም ብላችሁ ታስተምሩን የለ፡፡

አራተኛው የሚዲያዎች ሚና ነው፡፡ ዘመኑ የመረጃ ዘመን መሆኑን አይተናል፡፡ በተለይ ደግሞ ሚዲያዎች በአቋም፣ በዘገባ ትንታኔ፣ በመረጡት መዓዝን እና በሰጡን መረጃ ቢለያዩም አብዛኞቹ ከመሠረታዊ ችግሮች የጸዳ ቤተ ክህነትን ለማየት ሕልም እንዳላቸው ያሳዩ ነበር፡፡ መረጃዎችን ለሕዝቡም ለአባቶችም በማድረስ ታላቅ ሚና ተጫውተዋል፡፡ ሚዲያዎችን ለማግኘት ለማይችሉ አባቶች ኢንተርኔት ከፍተው በማስነበብ፣ አትመው በመስጠት፣ጋዜጦቹን እና መጽሔቶችን በነጻ በማደል፣ መረጃዎችን ጨምቀው በማቅረብ አያሌ ምእመናን ተግተው ሰንብተዋል፡፡ የአብዛኞቹ ሚዲያዎች ዘገባ እና ትንታኔ ከስሜታዊነት፣ ከጥላቻ፣ ከስድብ፣ ከግለሰባዊ መስተጻምር እና ከጩኸት ይልቅ በመረጃ እና በዕውቀት ላይ የተመሠረቱ መሆናቸው አስደናቂ ነበር፡፡

ይህ የሚዲያዎች ሚና እንዲቀጥል እና «ዕውቀት ተኮር፣ መረጃ ደገፍ፣ ሃሳብ ሰጭ፣ መንገድ አመልካች» እንዲሆኑ ባለቤቶቹ፣ ጋዜጠኞቹ፣ አንባቢዎቹ እና ጸሐፍቱ መጣር አለባቸው፡፡ በአሥራ ዘጠኝ ሰማንያዎቹ እናየው ከነበረው የሚዲያዎች ገጽታ በተሻለ መልኩ ሚዲያዎቹ ሰከን ብለው ውኃ ያዘለ መልእክት እና መረጃ ይዘው ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ይህ ደግሞ ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ አድርጓቸዋል፡፡

አባቶች፣ የሃይማኖት ሊቃውንት፣ ባለሞያዎች እና ሃሳብ ያላቸው ሰዎች ትንታኔዎችን፣ አማራጮችን እና ሃሳቦችን የሚሰጡበት መንገድ መዘጋጀት አለበት፡፡ የቤተ ክህነቱን አደራ የበሉ ሰዎች እየሠሯቸው ያሉ ሙስና፣ የዝምድና አሠራር፣ብኩንነት እና ኢሞራላዊ ተግባራት ፀሐይ እንዲመታቸው መደረግ አለባቸው፡፡ እየተወሰዱ ያሉ መፍትሔዎች፣ እየተከናወኑ ያሉ በጎ ሥራዎች ደግሞ መበረታታት ይገባቸዋል፡፡

አምስተኛው ትምህርት መቀስቀስ እና መንቀሳቀስ ያለባቸው አካላት ገና እንደሚቀሩ መገንዘብ መቻል ነው፡፡ ዕድገት የሁሉንም ሱታፌ ይጠይቃል፡፡ የተኛውን መቀስቀስ፣ የደከመውን ማበርታት፣ የሳተውንም ማረም ይገባል፡፡ ሰሞኑን እንደታየው ዕድገት እንዲመጣ የሚፈልጉ ለዕድገቱ ግን ምንም አስተዋጽዖ የማያደርጉ አካላት ገና አሉ፡፡ አንዳንዶቹም ዕድገቱን ወይንም ለውጡን ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጥቅም አንፃር ከመመዘን ይልቅ ለእነርሱ ከሚያመጣው ትርፍ እና ኪሳራ አንፃር ይመዝኑታል፡፡

በተለይም አንዳንድ የቤተ ክህነቱ ባለ ሥልጣናት እና ሊቃውንት እንደ እግር ኳስ ማን አሸነፈ? የሚለውን እንጂ ለቤተ ክርስቲያን ምን ተረፋት? የሚለውን ለመመዘን ፈቃደኞች አይደሉም፡፡ አሸናፊውን ለይተው ካሸናፊው ጋር በመቆም የጥቅም ተቋዳሽ መሆን እንጂ ቤተ ክርስቲያኒቱ እና ሀገሪቱ እንድታሸንፍ አይሠሩም፡፡ ብጹእ አቡነ ቀውስጦስ ለአዲስ አበባ ከተመደቡ ጀምሮ «እንኳን ደስ ያለዎ» ለማለት የሚጎርፈው ሰው «አትርሱኝ» እያለ መሆኑን ማንም ያውቀዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ዐቅሙ እና ዕድሉ እያላቸው ድምፃቸውን ለማሰማት ያልመረጡ ማኅበራትም ነበሩ፡፡ እነርሱ ራሳቸው ሲነኩ አገሩን የሚያናውጡት ማኅበራት ቤተ ክርስቲያኒቱ ስትነካ ግን ዝምታን መርጠው ሰንብተዋል፡፡ በታላላቅ የአዲስ አበባ አዳራሾች ኃይላቸውን ሲያሳዩን የከረሙት ማኅበራት ሰው በሚያስፈልግበት ሰዓት አድፍጠው ሰንብተዋል፡፡ አንዳንዶቹም የሚዲያዎቻቸውን ድምጽ አጥፍተው ከርመው «የበሬን ምስጋና ወሰደው ፈረሱ» እንደ ተባለው ነገሩ ካለቀ በኋላ «በኛ ጥረት ነው» ማለት ጀምረዋል፡፡ እነዚህ ሁሉ ካለፈው ትምህርት መውሰድ አለባቸው፡፡ አሁን ዘመኑ እነ «ወርቄ» መክፈልት የሚቆርሱበት ሳይሆን እነ «መንክር» ማኅሌት የሚቆሙበት ነውና፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ «የኋላዬን ትቼ በፊቴ ወዳለው እዘረጋለሁ» እንዳለው ያለፈውን ገምግመን እና ተምረን ከፊታችን ወዳለው የተከፈተ በር የምናመራበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡ ሀገራችንም ሆነች ቤተ ክርስቲያናችን እመርታ ማስመዝገብ ባለባቸው ዘመን ላይ ነው ያለነው፡፡ ማማረሩን እና ተስፋ መቁረጡን ትተን፣ ካፈውም ትምህርት ወስደን፣ ለበለጠ ሥራ እንነሣ፡፡ እርሱ የሰማይ አምላክ ያከናውነዋል፡፡53 comments:

 1. Kale Hiwot Yasemalin

  ReplyDelete
 2. ዳን ያንተ ይሻላል ።
  ግን አሁን የ ፓትርአርኩ አካህያድ ያለ አንዳች አስተምሮ መታለፍ የለበትም ብዬ አስባለሁ ።
  ይህን ያህል በ ቅዱስ መንፈስ የሚመራን ቅዱስ ሲኖዶስ በ ተራ ማጭበርበር መፈፀሙ ወንጀል ነው ። ይህ ወንጀል በምንኖርበት ምድርን በሚመጥን መልኩ አና አሳፋርነቱን በ ግልፅ በምአመላክት ደረጃ
  ተገቢ ቅጣት አስፈላጊ ይመስለኛል ። አለበለዝያ በ አንድ አጥብያ ያለ ድያቆን አንኩዓን የ አሳቸውን ተሞክሮ አያየ አንዴት ቤተክርስትያንን አንደምደፍር ይታየኛል ። የ አሕዛብ አና መናፍቃንን መገዳደርማ ተወው ።
  ይሄ ሁሉ ያለው አንደምታ አና የ አጭርም ሆነ የረጅም ጊዜ ተፅኖ ይህ ነው አይባልም ።

  ReplyDelete
 3. IT IS A NICE VIEW
  MAY GOD BE WITH US

  ReplyDelete
 4. Well said D Daniel, I think even though you don't like Abune Melketsadik (he is 86 now), we can't deny that he is a hard worker and visionary father who want to advance the church. I hope you post this.

  ReplyDelete
 5. Dani as much as a like your writings, I don't like your stand about Abune Melketsadik and Aba woldetensae. Be open your mind and think, do you have any thing +ve to say about these fathers?

  Abune Melkestadik served the church for about 70 years, can you mention atleast one good think he did?

  Aba Woldetensae preached about all kidusan and our mother Mary and about church kenonas and dogmas, do you any thing good to say?

  ReplyDelete
 6. እግዚአብሔር ይስጥልን ቃለ ህይወት ያሰማልን

  ReplyDelete
 7. ዘ ሐመረ ኖህNovember 1, 2010 at 1:06 AM

  ዲ/ን ዳኒ በርታ ቤተክርስቲያናችንና ቤተክህነታችን ብዙ ዲ/ን ዳንኤሎች ብዙ ደጀሰላማውያን ያስፈልጓታል፡፡ከምእመን እስከ ብፁአን አባቶች ድረስ አንድ ሆነን ለስልጣንም ለሆድም ለኑፋቄም የዘመቱብንን በእግዚአብሔር ኃይል ታግለን እናሸንፋቸዋለን፡፡ ለዚህም ምእመኑን እስከ ብፁአን አባቶች ድረስ የሚያስተተባብር መንገድ እንፈልግ፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዳይከበር ሲሞከር ሌላው ሕዝብ ዝም ማለት የለብንም በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምንገኝ ሁሉ እንደ አዋሳ ሕዝብ ወደሚመለከተው ሁሉ መጮህ አለበት ለዚህም ኦርጋናይዝድ እንሁን፡፡ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

  ReplyDelete
 8. Well in my view what is happening now had been happening for the last 20 years. Many Christians are aware of it. Yet a few people think something new is beginning to happen. Just now. Just this year. If we notice the results of the synod 40 and so meetings, it is the same old. Pops will talk the talk the big pope walk the walk. What has happened after this year's meeting? The same old. Pops denounce and bow to destroy the statue of their leader and other people. The big pope continues to do what he is supposed to do by his masters. One of the brilliant ye tewahedo scholar, Aleqa Ayalew, detected the evil act of this person very early. Even tried to teach the evil acts of this person to others. No body paid attention. No body listened to him including the present pops. He died with dignity with so many of us waiting to erect his statue like Martyr Abune Petros. When we look back, what happened last year? If we don’t learn from the past how can we learn from the present? Let’s face the reality. The church is right now under the fist of Devil. If we think it is not let’s throw the trashes in the garbage bin.

  ReplyDelete
 9. እግዚአብሄር ይስጥልን ዲ/ን ዳንኤል: በዚ ሰአት እንደዚ የሚያጽናና እና የሚያበረታ ጽሁፍ ስላስነበብከን:: በተስፋመቁረጥ ውስጥ ላለን እንድናገግም ይረዳናልና::
  እንዳልከውም “ማማረሩን እና ተስፋ መቁረጡን ትተን፣ ካፈውም ትምህርት ወስደን፣ ለበለጠ ሥራ እንነሣ፡፡ እርሱ የሰማይ አምላክ ያከናውነዋል:: ”

  ReplyDelete
 10. +++
  Yetwdedk wendmach melkamun yesenbet mekfelt selaquadsken QHY. Zare yemneshaw medgagef enji mewenjajele aydelm. Abatochachenen ejeg merdat yasfelgale. Ke zare 5 amet gabcha fetsemen merjajchnen kebetknet (certify) lemadreg yekfalnew ye birokrasi merb zare lenayew ansham. Selazih hulem tefat senay metchtu hasab mestetu melkam new.
  chegeru beand jember ayfetam yehonale gen, let us be volunteer to stand with others to solve our mother church problems. Selahulum ye tselot yenba hale kebad newna enberta genzbachnen lemlkam mawalen anzenga. Ketoronto akbari betseboch

  ReplyDelete
 11. ጆሮ ያለዉ ይስማ/በተቻለን መልክቱን ለማዳረስ እንሞክር::

  ReplyDelete
 12. Dani dinek analysis and timehert new kale hiwot yasemalen

  ReplyDelete
 13. egzyabeher yagelgelot zemenehene ybarekleh

  ReplyDelete
 14. ዲ/ዲኒ እግዚአብሔርን እውቀትህንና ማስተዋልህን ያብዛልህ መልካም ነው እይታዎችህ ቀጥልልን በርታልን!

  1.ለመልካም የምስራች ተናጋሪዎች በሙሉ ፦ (ለእውነተኛ ጋዜጠኞች)

  “እንግዲህ አትፍሩአቸው፤ የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለምና። በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ።” ማቴ 10፦26-27

  2.ሕግንና ስርዓትን ጠብቀው ላስጠብቁ ፦ (በሕይወታቹቸው ለክርስቶስ መስዋት የሆኑ)

  “መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል።መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።” ማቴ 5፦15-16

  3.ለህዝበ ክርስቲያን፦

  “ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል።” ማቴ 7፦7

  4.ምንም ቢሆን ይህን አንዘነጋ ፦
  “አዎን፥ አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።” ማቴ 10፦26

  5.ለብፁዓን አበዊነ ሊቃነ ጳጳሳት፦ (ለእረኞች)

  “መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።” ዮሐ 10፦11

  6.እግዚአብሔርን የሚፈራ ሁሉ እንዲ ይባላል፦

  “እግዚአብሔር ይባርክህ፥ ይጠብቅህም፤እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ፥ ይራራልህም፤ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሣ፥ ሰላምንም ይስጥህ።” ዘኁላቁ 6፦24-26

  እግዚአብሔርን ለሃገራችንና ለቤ/ክርስቲያናችን ሰላሙን ይስጠን ። ወ ስብሐት ለእግዚአብሔርን
  ቸር ወሬ ያሰማን!!!

  ReplyDelete
 15. tanks dany tanks agen lela men elalew

  ReplyDelete
 16. well good points.
  by the way where is Mahibre Kidusan? I Know folks at Mk will say its is a matter of church politics; But I think it is a matter of church dogma and "Kenona" come on MK use your power and stand besides church fathers.

  one of MK members

  ReplyDelete
 17. ye ene """ werekiee """ zemene yaketemelate yimeselale... dani tsegawene yabezaleh .

  ReplyDelete
 18. ዲ/ዳንኤል የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክልህ አምላከ ቅዱሳን ጥበቃውን ያብዛልህ ይህን የምለው ለአንተ ብቻ ብዬ አይደለም እኛም ሰው እንዳናጣ ከአሉ ነበሩ እንዳይመጣ በማሰብ ነው እንጂ
  ዳኒ አባቶቻችን በሚሄዱበት ሰፍራ ሁሉ የእግዚአብሄርን መሪነት አስቀድመው ጉባዔው ላይ እንዳሉ አንድነታቸው ቀጥሎ መንፈሳዊነታቸው ጠንክሮ በጸሎታቸው በርትተው በተሰነጠቀው በር ወደ ውስጥ መታየቱ ባይጕዳንም ውሰጥ የሚታየው በር ከልሎት የቆየው ጉድ ሲታይ ግን ይጐዳናልና ለችግሩም ከእኛ እነሱ ቅርብ ናቸውና ጉዞቸውን ቀጥለው ከዳር ይደርሱ ዘንድ እንዲበረቱ እኛም ሁላችንም እንደ አቅማችን እንደ ተሰጠን ጸጋ ከጎናቸው በመሆን የቀደሙ አባቶቻችን ልጆች ሆነን ቤ/ክ በምትፈልገን ቦታ ሁሉ እንገኝ
  አሁን ዘመኑ እነ ወርቄ መክፈልት የሚቆርሱበት ሣይሆን እነ መንክር ማኅሌት የሚቆሙበት ነው አልክ እውነት ያድርገው
  ከአቡዳቢ

  ReplyDelete
 19. GOD blessed our country, Our church and you

  ጆሮ ያለዉ ይስማ በተቻለን መልክቱን ለማዳረስ እንሞክር::

  ReplyDelete
 20. This is a genuine reflection of a true Christian. We all are expected to have such a fruitful stand. The writing has shown the general context of our church and its spiritual, structural and educational aspects of the human and material resources. We can learn a lot from this if we are open and free minded.

  ReplyDelete
 21. ሁሌም ከስህተት መማር ብቻ?? መቼ ነው እርምጃ እንዲወሰድ የምናበረታታቸው??? መቼ ነው ምእመናንስ የሲኖዶሱን ውሳኔ ለማስከበር ድምጻችንን የምናሰማው??

  ReplyDelete
 22. Kale hiwot Yasemalin. Dn Dni gin eskemech entages? The patriarch do not have any +ve mentality b/c of his mision, guys like sereke and Ejigayehu. If we keep him going he will totaly distroy the church. You said the our fathers correct things in your locality and be an example for others but there are members of the mafiya group in all the hageresbikets so that if good is done there it will touch them and they will come to their leader(patriarich)tell him and then he will interfear as usual. This was practical seen in North Gondar and North Shoa(Debire-Birhan). So the dawon of the Patriarich is realy mandatory and could be immidaite but how? benegerachin lay the patriarich has 100% fulfill the criterea to be dawon. So our fathers could meet immidiately now and made him dawon, then we will get relived and every impruvement is possible. Mengistim benekahew yemetekakat merih ebakih egnihin sew asiwogidilin. Amilake Kidusan Yitebiken Amen

  ReplyDelete
 23. በሌላ በኩል ደግሞ ዐቅሙ እና ዕድሉ እያላቸው ድምፃቸውን ለማሰማት ያልመረጡ ማኅበራትም ነበሩ፡፡ እነርሱ ራሳቸው ሲነኩ አገሩን የሚያናውጡት ማኅበራት ቤተ ክርስቲያኒቱ ስትነካ ግን ዝምታን መርጠው ሰንብተዋል፡፡ በታላላቅ የአዲስ አበባ አዳራሾች ኃይላቸውን ሲያሳዩን የከረሙት ማኅበራት ሰው በሚያስፈልግበት ሰዓት አድፍጠው ሰንብተዋል፡፡

  ReplyDelete
 24. diakon danieal it is a good idea but it is a starting not the end please God help Orthodox tewahedo

  ReplyDelete
 25. ዳኒ ቤተ ክህነቱ እስካሁን ያንኑ ፊውዳላዊ አሰራር እንደሚከተል እንዳንተ ጠልቄ ባላውቅም መጀመሪያውኑ በስብሰባው የፀደቁት ቃለጉባኤዎች ቢፈረሙ እንኳን ስብሰባው ሲያልቅ ፓትሪያርኩና መሰሎቻቸው ይሽሩታል ብዬ ስላሰብኩ ብዙም አልደነቀኝ፡፡ እነሱ ማንን ፈርተው፡፡ ነገሩ እኮ ‹‹ብዙ ሀጥያት ባለችበት የእግዚአብሔር ጸጋ ትበዛለች ሆኖ ነው››፡፡ ብቻ መድሐኒአለም ይርዳን፡፡

  ማሂ

  ReplyDelete
 26. ዲያቆን መሐሪ ገብረማርቆስNovember 1, 2010 at 3:08 PM

  ለማኅበራታችን፡-

  በቅርቡ በቤተክርስቲያናችን እየተካኼዱ ያሉትን ጉዳዮችም ሆነ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔዎች በተመለከተ ምንም ስትናገሩ ላልተሰማችሁትና እያደመጣችሁ መሆኑም ለሚያጠራጥረው ማኅበራታችን በሙሉ፡-

  ቤተክርስቲያናችን በአሁኑ ወቅት ከፊውዳሊዝምና ከአምባገነናዊነት እንዲሁም እነርሱ ከወለዷቸውና ካዋለዷቸው ችግሮች ለመላቀቅ ወሳኝ ጊዜ ላይ ትገኛለች፡፡ ለእግዚአብሔር ክብር ይግባውና እርምጃው በቅዱስ ሲኖዶስ ታሪካዊ ውሳኔዎች ተጀምሯል፡፡ ከዚህ በኋላ የተጀመረውን እንቅስቃሴ ወደፊት እንዲገፋም ሆነ ባለበት ተገትሮ ጊዜ እንዲያሻግተው ማድረግ በቤተክርስቲያኗ ልጆች እጅ ያለ ጉዳይ ይመስለኛል፡፡

  ምእመናን ደግሞ አንድን ሥራ ለመሥራት ሁሌም ቢሆን የሚያስተባብራቸው የሚያነቃቃቸው በእጅጉ ይፈልጋሉ፡፡ የእናንተ ታሪካዊ ድርሻም ይህ ነው- ምእመኑን በጥበብና በትዕግስት ለሥራ ማነቃቃት፤ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ከዕለት አጀንዳው ውስጥ እንዲካተት ማድረግ፤ ሠርቶ እያሳዩ የሥራው ለተሳታፊነት ማነሣሣት፡፡ እናንተ ግን በዚህ ወሳኝ ጊዜ ዝምታን የመረጣችሁ ይመስላል፡፡ ምእመኑን ለማንቃት ይቅርና ራሳችሁም የነቃችሁ አትመስሉም፡፡ እርግጥ ነው ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ቤተክርስቲያናችን እያለፈችበት የምትገኘው ችግር ብዛቱና ዓይነቱ ባይገድል እንኳ መንፈስን በተስፋ መቁረጥ የማደንዘዝ፣ ወኔን የማንጠፍ ዐቅሙ ትልቅ ነው፡፡ ግን እስከ መቼ ተስፋ ቆርጠን እንዘልቀዋለን? ተስፋ ያስቆረጠን ችግር እነሆ ይፈታ ዘንድ በእግዚአብሔር ፈቃድ ውሉ ተይዟል፡፡ አሁን ተነቃቅቶ ሥራ የመሥራት ጊዜ ነው፡፡

  ትልቁ ሥራ ያለውም ከዚህ በኋላ ነው፡፡ ጨለማው ህልውናው የግድግዳው ቀዳዳ እስኪሸነቆር ነበር፡፡ አሁን ተሸንቁሯል፡፡ ከዚህ በኋላ ያለው ሥራ የጨለማውን ግድግዳ መደርመስ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ረጅም ጊዜ፣ ብዙ ገንዘብ፣ ብዙ ጉልበት፣ ብዙ ጩኸት ይጠይቀናል፡፡ ከሁሉም በላይ እንደሙሴ ጠንካራና ብልኅ አስተባባሪ ይፈልጋል፡፡ ማኅበራታችን ልትሆኑ የሚገባችሁም ይህንን ነው፡፡ “እንዴት?” የሚል ጥያቄ ሊነሣ ይችላል፡፡ ይህ ጥያቄ መልስ የሚያገኘው ግን እናንተ በውስጣችሁ መወያየት ስትጀምሩ ነው- ወደ አንዱ መንገድ የሚያደርሱ ብዙ መንገዶች አሉና፡፡

  በመዝሙር አገልግሎታችሁ፣ በስብከት ተፋጥኗችሁ፣ በእርዳታ ልገሳችሁ ያየነውን ቀናነትና ቀናዒነት የችግሮቻችንን መሠረት በመፍታት ልታሳዩን ግድ ይላችኋል፡፡

  እየሰማችሁን ነው?

  ReplyDelete
 27. Deacon Mehari GebremarqosNovember 1, 2010 at 3:16 PM

  To Mahiberats,

  Don't you have anything to say the recent decisions by the Holy Synod of our church? Where is your stand? Are you with our fathers or with those who would always like to pursue their worldly aspirations? Where do you think should be your position in the current situation?

  Here, I think, there is no ground to stay indifferent on the burning issues. You have to say something to let us know where your stand is. I think this time is where our church badly needs the unity and organization of her children. Do you think the solution for the rank and file problems of our church can be solved by just investigating the reformists?

  The heart of our church problems lies beneath the structural decadence, which is the result of autocracy and feudalism. That is where every one of us should be working diligently at. That is where our fathers have started to give corrections. Shouldn't we be helping them? I think, anyone who avers that he/she is concerned about the church can not be indifferent at this turning point of our history. How can be you be indifferent? How?!

  What I aspire your (Our) Organization to do at this time is to organize the movement of the structural reformation of our church, the only redeeming way from the decadence and its anomalies. You should be the one, I think, to organize and lead the situation as you claim much of the intelligentsia.

  The decisions by our fathers should come in to effect. You should take the great role in organizing that. Your organization should be leading the people. Your media should talk about the problems and their immediate as well as long run solutions without fear. Otherwise, tomorrow will not be comfortable either to you or to our mother church.

  It is basically the structural decadence and impotence which is serving a fertile ground to the proliferation of the reformist groups in our church. The major cause for our church's structural weakness is the dictatorship and feudalism the church has been in for decades. This problem is, as you all know, deterring the church's structure as well as the faith among believers'. Hence, anyone who aspires to see our church glowing he/she should be working assiduously to uproot these problems of dictatorship and feudalism which led us to all the corruption and nepotism.

  At this critical time of history there is no grey middle to anyone to play on the edge. History will never forgive you leave aside God, who commenced you to serve His church.

  God Bless Dn. Dani's Ethiopia!

  ReplyDelete
 28. hello danie, it is a nice advice that all son of orthodox towahdo church should take it. thankyou
  God bless you!

  ReplyDelete
 29. Qale hiwoten yasemalen !!!!!!!!

  mekari atenag yalasatan AMELAKACHEN YEKEBER YEMESEGEN Amen !!!!

  semonun betwesenew wesane sendeset endeteferawe degmo destachenen sanecheres ytesemawe eytesema yalew neger anget yemiasdefa new . Dani endeante aynetu asteway sew degmo betesetew tega banteyayem enkuan wegenek men eytesemaw endale terdeteh ayzachew yemilew atenag tehufhn asdemateken EGZIABHER antenem yaberetah elalew

  abet ye ahezab ena yemenafekan mesalekiya mehonachenen saseb gen lebe behazen ayne be eneba yemolal
  ABETU YEGA YEDAKAMOCHE legochehn mekara bedmeh yemeseretekaten ye betekereseteyanehen cheger temeleket Amen !!!

  ReplyDelete
 30. Dn Daniel Well said!!! I have nothing to add on what you said.
  As to me ENIMAR!!!
  Egziabher amlak tsegawun yabzalih rejim edime ke mulu tena gar yistilin.

  ReplyDelete
 31. "ድል ብቻ ሳይሆን ሂደትም ውጤት ነው፡፡"

  ዳኒ እባክህን ይህችን ዓ.ነገር በትልቁ ጡማርህ ላይ ጻፋት: ሁሌም እንድናነባት:: ኦባማ የምርጫ ቅስቅሳ በሚያካሂድበት ጊዜ በአዲስ ነገር የጻፍከው ጽሑፍ ሁሌም ከኅሊናየ አይጠፋም:: "ሉተር በቀደደው ኦባማ ገሰገሰ" ካልተሳሳትኩ:: የትኛውም የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ሊማር የሚገባው ድል ዛሬውኑ ተጀምሮ ዛሬውኑ እንደማይመጣ:: በእግር ኳስም: በፖለቲካውም: ባጠቃላይ በእድገታችን: ዛሬውኑ ጀምረን ዛሬውኑ ውጤታማ መሆን እንፈልጋለን:: ታሪክም ሆነ ሳይንስ የሚያስተምረን ለውጥ በውስን ጊዜ ውስጥ እንደማይመጣ ነው:: እንቁላል ቀስ በቀስ በእግሩ ይሄዳል ይል አይደል ብሂላችን : እስኪ በመጀመሪያ ሂደታችን ይመርበት: ከዛ ለውጡ: ማሸነፉ በራሱ ጊዜ ይመጣል::

  ReplyDelete
 32. በስመ ሥላሴ አሜን።
  በእውነት ለመናገር የሆነው ሁሉ የሆነው ከጌታ ነው ብዬ ለመቀበል በእጅጉ እቸገራለሁ ... ምክንያቱም “ የቤተክርስቲያን ድል” የተባለለት ውሳኔ የመጣበትን መንገድ ( “ ከፍተኛ ተሳትፎ ያበረከቱ ምእመናን፣ ባለሞያዎች፣ ሽማግሌዎች ፣ አያሌ ሚዲያዎች ” ሰጡት የሚባለውን ድጋፍ ... እረ እንዲያውም “ ግፊት ” ነው የሚባለው ) ... ሳጤነው ራሳቸውን አዋቂ አድርገው የተቀመጡ ( ጋሪው ፈረሱን ቀድሞታል ) እያሉ አባቶቻቸውን መብለጣቸውን ባደባባይ የሚያውጁ ) ፤ ጊዜ የሰጣቸው ሰዎች ግፊት ውጤት መሆኑ ይጎላብኛልና።

  ከዛሬ ጽሑፉዎት ከታዘብኩት ፦

  1.ላለፉት ሃምሳ ዓመታት ምንም ዓይነት የመዋቅር ማሻሻያ ያላደረጉ ሁለት ተቋማት በኢትዮጵያ አሉ፡፡ ዕድር እና ቤተ ክህነት፡፡

  ምነው መምህር? ... እርስዎ ነፍስ ካወቁ በኋላ ያዩዋቸው ፣ የመረመሩዋቸው ፤ ፍርድ ሊሰጡባቸው የሚችሉ አያሌ ተቋማት እያሉለዎት የሚጠይቀኝ የለም ብለው ከመወለድዎ በፊትም ስላለው ነገር ፤ እንዲህ በርግጠኝነት ፤ ... ዕድርንና ቤተ-ክህነትን ብቻ ለምን? ... አዎ ርዕሰ ጉዳይ ስለሆኑ ይሆናል ... ታዲያ ለምን ማጋነን አስፈለገ? ... ያለማጋነን ችግሩን ጥርት አድርጎ ማቅረብ አይቻልም ማለት ነው? ...

  2.ዕቅድ የሌለው ብቸኛ የሀገሪቱ ተቋም ቤተ ክህነት ነው፡፡

  እርስዎ ምን ያህል ዕቅድ ያላቸው ተቋማት ያውቃሉ? ... የቤተ-ክህነት ችግር ሰው እንዲገባው ቤተ-ክህነት ዕቅድ የሌለው ብቸኛው ተቋም መሆን አለበት? ...

  3.በአንድ ወቅት ዋና ዋና የሀገራችን የፖለቲካ አመራሮች በተልዕኮ ትምህርት በከፍተኛ ዲግሪ መመረቃቸው ተዘግቦ ነበር፡፡ በቤተ ክህነት ለብፁአን አባቶችም ሆነ ለሌሎች ኃላፊዎች ሴሚናሮች፣ የሞያ ማሻሻያዎች፣ የአዳዲስ አሠራች ማስተዋወቂያዎች፣ ዐውደ ጥናቶች እና ሥልጠናዎች አይሰጡም፡፡

  በከፍተኛ ድግሪ ተመርቀው ምን ፈጠሩ? ... ስለተማሩ ፣ ስለሰለጠኑ ፣ ስላወቁ የመጣው መልካሙ ነገር ምንድን ነው? ... በእውነት ነው የምልዎት እኔ ከርስዎ ባላውቅ እንዲህ የቤተ-ክህነትን ነገር አኩሱሶ ለማሳየት ከመንግስት አመራር ጋር የሚያጣቅሱት ነገር ባዶ ነው ... ዋናው ነገር ስልጠናዎች አይሰጡም ለማለት ከሆነ ፤ ... ጥሩ ሀሳብ እኮ ነው ... እርግጠኛ ይሁኑበትና አይሰጡም መሰጠት አለባቸው ይበሉ ... እርሱ በቂ ነው ... ነው አንድ ጥግ ሲያስይዙት የበለጠ ተነባቢ ይሆንለዎታል? ...

  4.ችግሮችን በግልጥ የሚያሳዩ፣ ለጉባኤው ግብዐት የሚሆኑ እና የብጹአን አባቶችን ግንዛቤ ሊያሳድጉ የሚችሉ የጥናት ውጤቶችን አናቀርብላቸውም፡፡ በዚህም ምክንያት ችግሮቹን የተረዱ እና ለማስወገድ ቆራጥነት ያላቸው አባቶች እንኳን አማራጮችን ለማግኘት አልቻሉም፡፡

  እኔ እምለው ... የብጹአን አባቶችን ግንዛቤ ሊያሳድጉ የሚችሉ የጥናት ውጤቶችን የሚያቀርቡት እነማን ናቸው? ... እኛ ይበሉንና አባቶችን ትተን እነርሱን ብጹአን እንበላቸው ... ... ወይ ጉድ እንደው ማፈር ቀረ እንዴ? ... ወዲህ ችግሮቹን የተረዱ እና ለማስወገድ ቆራጥነት ያላቸው አባቶች እንዳሉ እየነገራችሁን ... ወዲህ ደግሞ ግንዛቤያቸውን እንደምታሳድጉት ትነግሩናላችሁ .... ምነው ዙሪያ ገባውን ከመሄድ ቀጥታው አይሻልም እንዴ?

  5.በየገዳማቱ እና በየአካባቢው የጸሎት ጸጋ የተሰጣቸው አባቶች እና እናቶችም በብርቱ ተጋድለዋል፡፡

  የጸሎት ጸጋ የተሰጣቸው ብቻ? ... ከፍተኛ ተሳትፎ አደረጉ የተባሉት ምዕመናንስ? ... ባለሙያዎቹስ? ... ምን ያደርጉ ነበር? ... አዎ ነገር ወዲህ ወዲያ ያራግቡ ነበር? ... ለእነርሱ፦ እንደነሱ ያልሆነው ለቤተክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጅ አይደለም ... ግን መምህር ፤ ክርስትናን እንደ እውቀት ማወቅ እና መኖር ይለያያሉ ያሉን እኮ እርስዎ ነበሩ ... ጥፋቱን ያንድ ወገን አድርጎ እንዲህ ሰውን ሁሉ ዘመቻ እንዲወጣ “መቀስቀስ እና ማንቀሳቀስ ”ምናምን ማለት ምንድን ነው? ... እንዲህስ ባለው ዘመቻ ምን ጠቃሚ ውጤት ይመጣል? ... በሀዘን በመንገብገብ ፣ የሽብር ወሬ ወዲህ ወዲያ በማድረግ ፣ ሚዛናዊ ባልሆነ ጥላቻ ( ፍቅር ) ፤ እኒህን እና እኒህን በመሳሰሉት ዘመቻዎች ቢሆን እኮ የሀገራችን ፖለቲካ በመጠኑም ቢሆን ፤ ሁሉንም ባይሆን ዘመቻ የወጣውን እንኳን ባስደሰተ ነበር ... እና በቴክኒክ ና በታክቲክ ውጤት ይመጣበታል ተብሎ የሚታሰበው ፖለቲካ ከዘመናትም በኋላ ውጤት ሳይኖረው ፤ መልካም ምግባርንናና ጽኑ እምነትን እንደ ቅድመ ሁኔታ የሚጠይቀው የክርስቲያኖች ቤት ችግር፤ እንዴት ተብሎ ነው ባንድ ሰሞን ሆ ባይ “ ድል ” ሊመዘገብበት የሚችለው? ... ነው ወይስ ይህ ሕዝብ አንዳች ተዓምር እግዜር እንዲሰራ የፈጣሪን ልብ መግዛት ችሏል? ... እረ በእግዜር መምህር ምነው ሆ ባዩ ቀድሞ ሊኖረው ፣ ሊያሟላው ስለሚገባ አብይ ነገር አይነግሩትም? ... ለምን ስለሚወደው ፤ ስለሌሎች ብቻ ይነግሩታል? ... እርስዎ አባቶችዎን እንዲህና እንዲያ ብላችሁ አስተምራችሁን የለምን ብለው ይጠይቃሉ? ... እኔ ደሞ እርስዎን ልጠይቅዎት ... “ብዙ ሰው ሀገራችንን እግዜር ለእመብርሃን አስራት አድርጎ ስለሰጣት ምንም አትሆንም ይላል ... ግን እግዜር ቃልኪዳኑን የሚጠብቀው ቃልኪዳን ከሚጠብቅ ሕዝብ ጋር ብቻ ነው ” ብለውን ነበር ... ታዲያ ምነው አሁንም ፈተናው ከእግዜር መንገድ ፈቀቅ የማለት ውጤት ነው አይሉንም? ... ለምን የተከፋፈለች መንግስት እንደማትጸና አይነግሩንም? ... ለምን ስለሌሎች በማውራት ፣ ሌሎች ላይ በመፍረድና ሌሎች እንዲህና እንዲያ ማድረግ አለባቸው በማለት ከሚመጣው ውጤት የበለጠ ራስን ለእግዜር በማስገዛት በሚመጣ የእግዜር ምህረት የሚሆነው ይበልጣል አይሉንም? ... “ ጀግና የናፈቀው ሕዝብ ”... ሳይሆን ጀግንነት መስራት ስላለበት ሕዝብ አይነግሩንም? ...

  ReplyDelete
 33. 6.አሥራ ዘጠኝ ሰማንያዎቹ እናየው ከነበረው የሚዲያዎች ገጽታ በተሻለ መልኩ ሚዲያዎቹ ሰከን ብለው ውኃ ያዘለ መልእክት እና መረጃ ይዘው ተንቀሳቅሰዋል፡፡

  እንዴት መምህር? ... የዛን ጊዜም እኮ ሚዲያዎቹን እንደርስዎ ሰከን ያሉ የሚሏቸው ሰዎች ነበሩ ... ምናልባት ያኔ እርስዎ የሚዲያውን እንዲያ የመሆን ምክንያት ( cause ) አይደግፉት እንደሆነ ነው እንጅ ... ማለቴ አሁን ከእርስዎ ምክንያት ጋር ስለገጠሙ ይሆናል ሰከን አሉ ያሏቸው ... የቀድሞዎቹ ጯሂዎች ... የአሁኖቹ ደሞ ሰላም ዘማሪዎች ... እንዴ ተብሎ መምህር?

  7.ዐቅሙ እና ዕድሉ እያላቸው ድምፃቸውን ለማሰማት ያልመረጡ ማኅበራትም ነበሩ፡፡ እነርሱ ራሳቸው ሲነኩ አገሩን የሚያናውጡት ማኅበራት ቤተ ክርስቲያኒቱ ስትነካ ግን ዝምታን መርጠው ሰንብተዋል፡፡

  የትኞቹ ናቸው መምህር? ... መቸም ይህቺ አትከብድዎትም ... ምክንያቱም ከዛሬ ወደ ኋላ 50 ዓመት ተመልሰውና አጥንተው የመዋቅር ማሻሻያ ያላደረጉትን በጥቁርና ነጭ ለማስቀመጥ ስላልከበደዎት ማለቴ ነው ... ነው አንባቢዎችዎ በአቦ ሰጤ እንድንሞላልዎት የቀረበ በጎደለ ሙላ ነው ... ግን ግን ማኅበራቱም ምላሽ መስጠት ያለባቸው እንደርስዎ ብቻ መሆን አለበት? ... በቃ እርስዎ ከሚከተሉት መንገድ ሌላ መንገድ የለም? ... የቤተክርስቲያን ችግር የሚያንገበግባቸውንማ እኮ አየን ... ያ ሁሉ ወዲህ ወዲያ ( በነገር መሽኮርመም ) የሚፈልጉትን ስላላመጣ በፈጣጣ በበኩላችን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ “ረግረጉና እቋሪው ውኃ ግን ጨው እንደሆነ ይኖራል እንጂ አይፈወስም” እንደተባለው (ሕዝ.47፤11) ከእንግዲህ ወዲህ የማይፈወሱ ድውይ ናቸውና ቅዱስ ሲኖዶስ ከመንበሩ ሊያስወግዳቸው ይገባል፡፡ ብለው አርፈዋል። ... ሌላ ሌላውን ትተው መጀመሪያውኑ ይህንኑ ቢሉ ... ምናልባት ... ደግሞ እኮ የጠባያቸው ክፋት ... አስተያየት እንኳ ሲሰጣቸው “ ዘጸሐፍኩ ጸሐፍኩ ” የሚሉ ... አይ የነሱ ነገር!

  ግን ግን ... ሁሉም ይቅር መምህር ... በቃ የምትሰብኩን ክርስትና ፣ አባቶች የኖሩበት አስተምህሮ እንዲህ ላለው የችግር ጊዜ አይሰራም እንዴ? ... በሕዝብ ( በቤተክርስቲያን ) ላይ ፈተና ፣ መከራ ሲመጣ እግዜር በጸሎት ፣ በለቅሶ ፣ በዋይታ ይጠየቅ የነበረው ጥንት ነው? ... ዛሬ እንደዛ አይሰራም? ...

  ምንም እንኳ ቁጥሩ የበዛ ሕዝብ ሆ ቢል ፣ በግል እና በቡድን ቴክኒክና ታክቲክ እየተጠቀመ ጠቃሚ መሰል አሳቦች ቢያመጣ አካሄዱ እግዜርን የያዘ ካልሆነ ቢቀርብን ይሻለናል ... ሆ ባዮች ለቤተክርስቲያን ባዳ ቢሉን እኛ ደግሞ የሚጠይቁትን በውል የማያውቁ በቤት ውስጥ ያሉ በጥባጭ ልጆች እንላቸዋለን ... መበጥበጣቸው ልኩን ሲያልፍና የልጅ አልመስል ሲል ደግሞ ....

  " እግዚአብሔር የሚወደውን መልካሙንና እውነቱን ፍፁሙንም መርምሩ " ሮሜ 12 ፦ 2

  ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

  ReplyDelete
 34. +++

  እግዚአብሄር ይስጥልን ዲ/ን ዳንኤል::ዘመንህን ይባርክልህ አምላከ ቅዱሳን ጥበቃውን ያብዛልህ :: ልቦና ላለው አስተማሪ ነው :: ትልቁ ሥራም ያለውም ከዚህ በኋላ ነው::

  አምላከ ቅዱሳን ከሁላችን ጋር ይሁን::

  ReplyDelete
 35. እስከዛሬ ድረስ ብዙ አካላት ለቤተ ክርስቲያን ቅርብ ለቤተ ክህነቱ ግን ሩቅ ነበርን፡፡ አሁን የተከሰተው የቤተ ክህነት ፈተና ካመጣቸው በጎ ውጤቶች አንዱ ሕዝቡ ለቤተ ክህነቱ ጉዳዮች ቅርብ እንዲሆን ማድረጉ ነው፡፡ ጥንት ሲኖዶሱ ይሰብሰብ አይሰብሰብ፣ ጳጳሳት ይሾሙ አይሾሙ፣ ውሳኔ ይወሰን አይወሰን ከቤተ ክህነቱ ሠራተኞች ውጭ የሚያውቅ አልነበረም፡፡ ሌላው ቀርቶ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ማን እንደሆኑ ብዙ ምእመን አይለይም ነበር፡፡ አሁን ግን የቤተ ክህነት ጉዳይ ምእመናን እና ልዩ ልዩ አካላት እንደ ቆቅ ጆሯቸውን ሰትረው የሚከታተሉት ነገር ሆኗል፡፡


  ይህ ሁኔታ ይበልጥ መቀጠል አለበት፡፡

  ReplyDelete
 36. Egziabher kesemay eskimeleketgn ena eskigobegnegn deress ayne satakuart ena zim satel enban tafesalech.''seqokaw ermiyas 3:50''

  ReplyDelete
 37. Girum tsihuf new. Hulet ababaloch golden honew tayitewugnal.
  1. "በዚህም የተነሣ ስለ ቤተ ክህነቱ የምናስበው የሆነውን ራሱን ሳይሆን እንዲሆን የምንፈልገውን ነው፡፡" ende ene ende ene besemonu ye sinodos sibseba beye mediaw yetezegebew hulu be ergit be synodos yetenegerewuna yetefetsemew sayhon egna endinegerina endifetsem yetemegnenew neger new. be achiru zegebawochachin chuhewal. sile chohum mecheresha lay yetayew neger chiwww endilibin adrigoal.

  2. "እስካሁን ድረስ ችግሮቻችንን በማመልከት፣ ንዴታችንን በማሳየት እና ድጋፋችንን በመግለጥ ካልሆነ በቀር የተጠኑ፣ ችግሮችን በግልጥ የሚያሳዩ፣ ለጉባኤው ግብዐት የሚሆኑ እና የብጹአን አባቶችን ግንዛቤ ሊያሳድጉ የሚችሉ የጥናት ውጤቶችን አናቀርብላቸውም፡፡" wanaw qum neger eza lay neber. be gudayu lay eniseralen bilen yetesemaran sewoch yatekornew yehonewun woyim yehone yemeselenin neger report madreg lay new. Tsehafiw endalut le gubaew gebeat yemihonu hasabochin maqreb alchalnim woyim alfelegnim. Lemanignawum yezih website azegaj yemiyaqerbuachew tsihufoch kelay ke qerebew woqesa netsa nachewuna atenakirew yiqetilubet elalehu. egziagher yabertawo.

  ReplyDelete
 38. Thanks to God.

  Hi Dani, Well communicated article. I am learning a lot of good staff from this blog. I hope others do the same.

  Dani, I never forget what you told us almost 12 years ago in one meeting. You said " ... you (We) have too use properly (efficiently)each pen and paper because the money came from members who deduct from their living( food & cloth )..." I hope some one will tell to those corrupted, including those who waste our church resources. How, specially the poor church members are giving their (God's) money by sacrifice their living.

  ReplyDelete
 39. qale hiwote yasemalen.

  i was so like crazi when i hered that happened. i don't no noting well but i know i falow the true religion(ortodox)so so money peopel got this religion let's go be ready for any happen to fix we gonne win!!!!!!!!!!!!!! .I am THE FIRST WITH GOD.egziabher yabertahe for more.............

  ReplyDelete
 40. Kale yewot yasemalen.

  Even though I admire what they did, I still am not satisfied at all. Again even though some of us were not present at the past slow movement of the church, and we show up at the eleventh hour, we still were expecting the removal of the partirarc from his post. Not because of his trib or any thing else, but of his disobedience to the Sinodose and repeated violations of our church rules and regulations. D.Daniel you have said it all correct, but I feel as if it is like aheyawen ferto dawelawen. This is with due respect to you and the fathers. Instead of removing the patriarc, they did some thing else. Even though they let go easy, the donkey is still kicking back. How are we going to contineu calling his name during Kidase knowing all his past and current arogance. What would Misak, Abdinago and Midrak say about us? Pardon me about their names. I remeber their story. St. Gabriel saved them from that furnes of fire. The Sinodose, if possible must call back immediet ( emergency meeting ) and remove him out of there. How long are we going to contineu to learn? another 2000 years? or an other Bible must be written for us? or Eyesus Kiristos endegena yesekelelen? Ye Egziabher Kale keweta sayefetsem ayemelesim. Both the stachu and the patriarck must be removed. Personally, I lost all my respect after his refusal to sign the Sinodose final decision. On the other hand, I felt very happy about almost every body coming together and be concerned about EOTC. Even the other once who left the church looks like calm down and express their ideas with out throwing bad words for the first time. Churu Fetariachin yerdan. Balachihubet tsenu endetebalew yatsenan. Any way keep up the good job and don't forget God is always with His true followers. Egziabeher yestilign.

  ReplyDelete
 41. Amen kale Hiwot yasemalin.

  ReplyDelete
 42. ለዲ.ዳንኤል
  መጀመሪያ ቃለ ህይወት ያሰማልን እያልኩ የሚከተሉትን ልጠይቅህ ፈለግሁ።አንደኛ ሠላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ምን ማድረግ አለብን? መንግስትስ እነዴት ነው የሚፈቅደው? ማስተባበር የሚችልስ ሠው ምነው ጠፋ? አቤቱታችንንስ እንዴት ማሰማት አለብን? መልስህን እጠብቃለሁ።

  ReplyDelete
 43. Dani well said, I support your view in this issue...Let's pray more and more...Stay safe and blessed!

  ReplyDelete
 44. Eyob G:

  አስተያየትህ: ትንሽ ስሜታዊነት የሞላበትና:ጸሓፊውን ለመቃወም ብቻ የጻፍከው ሆኖ ታይቶኛል:: ቤተክርስቲያን ባሁኑ ጊዜ የገጠማት ትልቁ ፈተና:ከዘመናዊው ዓለም ጋር በሞያው ትውውቅ ያለው ወገን መስራት ያለበትን የቤት ስራ ስላልተወጣ መሆኑ ግልጽ ነው:: አገር ጸሎተኛ ያስፈልጋታል፤ ዘመኑን ደግሞ እየተረጎመ አቅጣጫ የሚያስይዝላት እንዲሁ ያስፈልጋታል:: ዲያቆን ዳንኤል የቤተክህነትን ቀልጣፋ አሠራር አለመኖር ሲጠቁም (ወደድክም ጠላህም እውነታው ያ ነው፤ እንደቤተክህነት የተዝረከረከ አሠራር ያለው ተቋም ፈልጎ ማግኘት አይቻልም:: ጥሩ አሠራር አለመኖሩም ደግሞ በጣም ትልቅ ችግር ነው)በሌላ በኩል የመንፈሳዊነት አለመኖር ችግር አልፈጠረም እያለ አይደለም:: ስለዚያማ ያለውን አቋም: በስብከቶቹም በሌሎች ጽሑፎቹም ውስጥ በግልጽ እናያቸዋለን:: በዓለም ውስጥ ግን ቦታ ይዞ ያለውና: በዓለማዊነት ሳቢያ ቤተክርስቲያን ላይ የሚመጣውን ፈተና ማየት የሚችለው የተማረው ወገን: እንዲሁ ዝም ብሎ ከመማረር ይልቅ: በዕቅድና በጥናት ወይም በታክቲካዊና ቴክኒካዊ ሥራ ጭምር አባቶቹን ሊያግዝ እንደሚገባ የሚያመላክት ነው:: ደግሞስ ካላገዘ: ምን ሠርቶ ሊጸድቅስ ኖሯል?! አባቶችስ: ሰው እንደመሆናቸው መጠን: ከመንፈሳዊነት ማጣት በተጓዳኝ: አንዳንዴም የኅብረተሰቡን አኗኗር ለመረዳትም ሆነ ውሳኔ ለመስጠት የግንዛቤ እጥረትና ብልሃትና ዘዴው እንደሚጠፋቸውም ጭምር ልንዘነጋ ይገባል ወይ? ይህንን ገጽም ልናየው እንደሚገባ መጠቆሙ ጸሓፊውን ያስመሰግነዋል እንጂ ያስወቅሰዋል ወይ?

  ስለዚህ: በደፈናው የተማረው ወገን እንዴት የመፍትሄው አካል ልሁን ብሎ ተገቢውን ጥያቄ በሚጠይቅበት ወቅት: በጭፍን ብጹዓን አባቶችን ለመተካት የታሰበ ተንኮለኛ ጥያቄ አድርጎ ማየት አይገባም:: ድሮ: ጥያቄው: የተማረው ወገን ለምን ቤተክርስቲያንን ጠልቶ ኮበለለ የሚል ነበር:: አሁን ደግሞ ለምን መጣ ብሎ መናደድና ጭራሽ አባቶችን አፈናቅሎ ለመተካት ግፊት እያደረገ ነው ብሎ መተርጎም ከቀና መንፈስ የመነጨ ሊሆን አይችልም:: በአባቶቹ ላይ ግፊት ማሳደር የማይችል ምዕመን: ቸልተኛ ወይም አላዋቂ መኃይም እንጂ ምዕመን አይደለም:: ይልቅ ትልቁ ጥያቄ ግፊት እያሳደረ ያለው ወደመጥፎ ነው ወይስ ወደመልካም ነው ብሎ መጠየቅ ነው:: የተቀላጠፈ አሠራር፣ ዕቅድ፣ ዐውደ ጥናት፣ ሴሚናር፣ ወዘተ ይኑረን ማለት ደግሞ በየትኛውም መለኪያ መጥፎ ግፊት ሊሆን አይችልም:: ይህን የመሣሰለው አሠራር: መንፈሳዊነትን የሚጻረር ክፉ ነገር ነው ካልን ደግሞ: በመጀመርያ ራሳችንን ቢያንስ ኮምፒዩተር ታይፒንግ ለመሠልጠን ብለን ያጣነው መንፈሳዊነት ካለ: በቅድሚያ ለርሱ ንስኃ መግባት ይኖርብናል::

  ለአንድ የተወሰነ ቡድን ያለንን ጥላቻ: እይታችንን እንዲጋርድብን ዕድል አንስጠው::

  ኢትዮጵያዊው

  ReplyDelete
 45. Dn Daniel, I do not have courage to advise you. You know what you are doing. You write just not to fill your blog. You write what you believe with it. Don't be discouraged by irrational comments. As you write with purpose, they too have objectives. They are those who play under the statue for earthly matters. True christian, particularly a preacher, should play a constructive role like John the Baptist, Prophet Eliah, or as one of our righteous forefathers and mothers.God had been working with the apostles; today he is also working!! This is WOLDESENBET from JBAJ.

  ReplyDelete
 46. ዲ/ን ዳንኤል
  መጀመሪያ ቃለ ህይወት ያሰማልን እያልኩ «እነርሱ ራሳቸው ሲነኩ አገሩን የሚያናውጡት ማኅበራት ቤተ ክርስቲያኒቱ ስትነካ ግን ዝምታን መርጠው ሰንብተዋል፡፡ በታላላቅ የአዲስ አበባ አዳራሾች ኃይላቸውን ሲያሳዩን የከረሙት ማኅበራት ሰው በሚያስፈልግበት ሰዓት አድፍጠው ሰንብተዋል፡፡ አንዳንዶቹም የሚዲያዎቻቸውን ድምጽ አጥፍተው ከርመው «የበሬን ምስጋና ወሰደው ፈረሱ» እንደ ተባለው ነገሩ ካለቀ በኋላ «በኛ ጥረት ነው» ማለት ጀምረዋል፡፡» የተባሉት እነርሱ እነማን ናቸው?

  ReplyDelete
 47. ዲ/ን ዳንኤል
  ሐሳብህን እጋራዋለሁ። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

  ReplyDelete
 48. አዳም ባይሳሳት

  አዳም ተሳስቶ - በሄዋን ቢያመካኝ
  እሷም በተራዋ - በባብ ብታመካኝ
  መች ሆነና ምህረት
  ባልባሌ ምክንያት
  ግን ግን - መወቃቀስ ቀርቶ
  በበጎ ብንወስደው - እንደ አባ ጋቶ
  ድንጋዩን ባፋችን - ክፉ እንዳይወጣ
  መልካም ይሆን ነበር ድርሻችንን ብንወጣ
  እስኪ እናስተውል…………
  አዳም ባይሳሳት ማን ያውቀው ነበረ
  የሔኖክን ፀሎት
  የሙሴንስ ፀላት
  ያሮንን ክህነት
  ማንስ ያውቀው ነበረ የአብርሀም ቸርነት
  የኖህን ቅንነት
  እረ ማን ይማራል ከዳዊት ገርነት
  ከእዮብ ትዕግስት
  ማንስ ያገኘ ነበር የኢሳያስን ትንቢት
  ከጳውሎስ መልክታት
  ማንስ ያገኝ ነበር የአምላክን እናት
  የልጇን ቸርነት
  እረ ማን ይድናል በጌታችን መሞት
  ………. አዳም ባይሳሳት
  ዳሩ በጌታ ዘንድ - ሁሉ ይታወቃል
  ሁሉ ሊድን ሲሻ - አዳም ተፈትኗል
  ፍቅሩን ሊያሳይ ሲል - ከሰማያት ወርዷል
  እኛን አስተምሮ - ወደ ሰማይ ወቷል
  ዳግም ሲመጣ ግን - ይህን ሁሉ ተምረን
  ይህን ሁሉ አውቀን
  እንዳዘናጋ በንስሀ መኖርን!

  ኪዳነማርያም ዘደብረ ይድራስ

  ReplyDelete
 49. Thank you very much for your views .They are nice . keep it up.
  From your readers

  ReplyDelete
 50. እንማር ወይስ እንማረር? እንማረር

  ReplyDelete
 51. Hi Ato Daniel

  As far as I know a Christian is not deplomat or cowardice (Ferri). He tells it as it is. Your writings tell me that you are Mehal Sefari. As any Cowardice you black mail the exile Synodos and support the current one. You do these because the former has no power and the latter does have all the power and the money.

  Be wodeq gind misar yibezabetal. Who should speak for the weak, the hungery, the diseased, and the dying?

  Yih hulu yalfal! Your writings of supporting the unholly "popes" will never.

  Thank you!

  ReplyDelete
 52. Amlakachen mastewalen lebonan lehulachenem yest! letederegew eyetederegem lalew amlakachen meftehe yamtalen ! askefi geze lay nun betselot entga ! Memeher Daniel "eyetah" melkam nuw le ewnet le'emnet eskekomk deres EGZEYABHER kante gar nuw berta mastewalun yabzaleh ! lehulachenem cher neger yaseman !
  Kale hiwot yasemalen ! peace from 403.....

  ReplyDelete