Thursday, October 28, 2010

ጀግና የናፈቀው ሕዝብ

ሰሞኑን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ሦስት ታሪካዊ ሊባሉ የሚችሉ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ ያለ አግባብ የቆመው የአቡነ ጳውሎስ ሐውልት እንዲፈርስ፣ በየቤተ ክርስቲያኑ የተሰቀለው ፖስተር እንዲነሣ እና በቤተ ክህነቱ ሥልጣን ሳይኖራቸው ባለ ሥልጣን የሆኑ መበለቶች እንዲገለሉ፡፡

ውሳኔው እንደ ተሰማ የሕዝቡ ደስታ ወሰን አልነበረውም፡፡ ስለ ጉዳዩ የዘገቡ ዌብ ሳይቶችን፣ ብሎጎችን፣ ፌስ ቡኮችን እና ሌሎችንም አጨናንቋቸው ነበር የዋለው፡፡ ለምን?

የኢትዮጵያ ሕዝብ ጀግና ይወዳል፡፡ በጦር ሜዳውም፣ በግብርናውም፣ በሃይማኖቱም፣ በፖለቲካውም፣ በኪነ ጥበቡም ጀግና ይወዳል፡፡ ሌላው ቀርቶ ከባድ ኃጢአት ቢሠራ እንኳን ጀግናን ይቅር ይላል፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስ ብዙ ሕዝብ በግፍ ገድለዋል፡፡ ብዙ የጭካኔ ሥራም ሠርተዋል፡፡ ነገር ግን ለእንግሊዝ እጄን አልሠጥም ብለው ለትውልድ ምሳሌ በሚሆን መንገድ ጀግንነት ፈጽመው ተሠው፡፡ ሕዝቡ የሠሩትን ክፉ ሥራ ሁሉ በፈጸሙት ገድል አስተሠረየው፡፡

በሃይማኖትም እንዲሁ፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በታሪኳ ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያን ጳጳሳትን ቀብታለች፡፡ እንደ አቡነ ጴጥሮስ ስሙ የገነነ ጳጳስ ግን የለም፡፡ የኢትዮጵያውያንን የጀግና ጥም ያረኩ አባት ናቸውና፡፡

ባለፈው ሰሞን ሲኖዶሱ በአንድ ጳጳስ ቁጥጥር ሥር ከመዋል አልፎ ጉዳዩ በማይመለከታቸው እና ጉዳዩንም በማይመለከቱት ግለሰቦች ሥር ወድቆ ነበር፡፡ ሲኖዶሱ ምን ወሰነ መባሉ ቀርቶ የነማን በር ተሰበረ? እነማንን እነማን አስፈራሯቸው? እነማን ከነማን ጋር ተሰለፉ? ሆኖ ነበር ጨዋታው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ፖለቲካዊ ካልሆኑ ተቋማት መካከል አንዱ እና ጠንካራዋ፣ ቀዳሚዋም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ የዚህች ቤተ ክርስቲያን የሉዓላዊነቷ መገለጫ ደግሞ ቅዱስ ሲኖዶሷ ነው፡፡ ይህ ጉባኤ ጳጳሳት መጀመርያውኑ ከሕዝብ ርቆ፣ ንጽሕ ጠብቆ መኖር ጀመረ፡፡ በኋላ ደግሞ ከቀኖናዊ አሠራር ወደ አምባ ገነናዊ አሠራር ተዛወረ፡፡ በመጨረሻም ከነ መኖሩ መዘንጋት ጀመረ፡፡

ይህ ሁኔታ ሕዝቡን ሲያስጨንቀው ነው የከረመው፡፡ ጭንቀቱ ለእምነቱ ተከታዮች ብቻ አልነበረም፡፡ የዚህችን ሀገር ብርታት፣ ጥንካሬ፣ ዕድገት፣ ዴሞክራሲያዊ ሂደት፣ መልካም ገጽታ እና በጎነት በሚመኙ አካላት ሁሉ ዘንድ ነበር፡፡ ትልቋ ቤተ ክርስቲያን እና ትልቁ ተቋም እንደዚህ ከሆነ የሌሎችስ ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል? የሀገሪቱ ዕድገት ሁለገብ ዕድገት እንጂ የአንድ ወገን መመንደግ አይደለምና ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ዜጋ የምትመራ ተቋም እንዲህ እየሆነች ዕድገት እንዴት ሙሉ ይሆናል? እያለ ያልተጨነቀ አልነበረም፡፡

በተለይ ደግሞ ለብዙዎች የሕይወታቸው መሪ ቤተ ክርስቲያን ለሌሎችም የሀገሪተ የሥነ ምግባር፣ የባህል፣ የርዕዮተ ዓለም፣ የትውፊት፣ የማንነት እና የወጥነት /ውርጂናሊቲ/ ምንጭ የሆነች ተቋም፣ ለሌሎችም የኢትዮጵያውያን ሲቪክ ሃይማኖት /civic religion/ ጠባቂ የሆነች ተቋም ከመንፈስ ልዕልና ይልቅ የምግባር እና የአሠራር ብልሹነቶች መገለጫ እየሆነች መምጣቷ አሳሳቢ ነበር፡፡

የቤተ ክርስቲያኒቱን ነባር አኩሪ ሥራ እና ታሪክ፣ የጠራ አስተምህሮ እና ሀገራዊ አስተዋጽዖ፣ የቅርስ ባለ ቤትነት እና የሕዝብ ባህል እና ሥነ ምግባር ባለአደራነት የሚሸፍኑ እና የሚያስረሱ ዜናዎች ከያቅጣጫው ይሰሙ ነበር፡፡ በተለይም ደግሞ የበላይ ሉዓላዊ አመራር የሆነው ሲኖዶስ ዐቅሙ እየደከመ፣ ክብሩ እየከሰመ፤ ድምጹ እየጠፋ፣ ዜናው እየከፋ መምጣቱ የቤተ ክርስቲያኒቱን ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱን ውድቀት አመላካች ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ጀግና የፈለገው በዚህ ጊዜ ነበር፡፡ እንደ አቡነ ጴጥሮስ ለእምነቱ እና ለአቋሙ የጸና፤ የሚመጣበትን በጸጋ ለመቀበል የተዘጋጀ፣ ታሪክ ሠርቶ ታሪክ የሚያስ ቀምጥ፣ አሁንስ በቃ የሚል የጀግና አባት አባት ጥም የእምነት እና የዜግነት ጉሮሮውን ሰንጎ ይዞት፣ ዋልያ ወደ ውኃ ምንጮች እንደሚናፍቅ እርሱም ጀግና ይናፍቅ ነበር፡፡

ሀገሪቱ የዕድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አውጥታ ራሴን ከድህነት አወጣለሁ እያለች ላይ ከታች ትኳትናለች፡፡ በዚህ ሰዓት ሕዝቡ እንደ አጥቢያ ኮከብ ከሩቅ የምታበራለት አንዲት ሀገራዊ ተቋም ጉዳይ እያሳሰበው እንዴት ልቡን ሰብስቦ ስለ ዕድገት ያስብ፡፡ የነበረውን እያጣ እንዴት አዲስ አገኛለሁ ብሎ ተስፋ ያድርግ፡፡ ይህንን የክፉ ወሬ ምርግ አፍርሶ ደግ ዜና የሚያመጣ ጀግና ነበር ሕዝቡ የፈለገው፡፡

ለዚህ ነበር ቅዱስ ሲኖዶስ እነዚያን ሦስት ታሪካዊ ውሳኔዎች ሲወስን አገር በእልልታ የቀለጠው፡፡ ጥቂትም ቢሆን የጀግንነት ጭላንጭል ለማየት ስለቻለ፡፡

በቤተ ክህነቱ ውስጥ ሥር የሰደዱ በአንድ ጉባኤ የማይፈቱ ችግሮች አሉ፡፡ እነዚህ ችግሮች ዝም ከተባሉ ከቤተ ክህነቱ አልፈው እንደ ወረርሽኝ ወደ ሌሎችም ተቋማት ሊጋቡ የሚችሉ ናቸው፡፡ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የአንድ ሰሞን ጉባኤ አይበቃቸውም፡፡ ወሳኙ ነገር ጀግንነት ነው፡፡ ጀግና ችግሮቹን ሁሉ ላይፈታ ይችላል፡፡ ለችግሮች ሁሉ ግን መፍትሔ እንዳለው ያመላክታል፡፡ ጀግና ያለፉትን ኃጢአቶች ሁሉ ላያስተ ሠርይ ይችላል፡፡ ዳግም ሌላ ኃጢአት እንዳይሠራ ግን በር ይዘጋል፡፡ ጀግና በወቅቱ ያለውን ችግር በፍጹምነት ላያስወግደው ይችላል፡፡ ነገር ግን ችግሮች መቼም ቢሆን ተቀባይነት እንደሌላቸው በመሥዋዕትነትም ቢሆን ያሳያል፡፡ ጀግና ጨለማውን ላይገፍፈው ይችላል፡፡ ነገር ግን ሕዝብ በጨለማ መካከል ጭላንጭል እንዲያይ ያደርጋል፡፡

አንዳንድ ሰዎች ትናንት ያጠፉትን፣ የተሳሳቱትን፣ ምናልባትም በማወቅም ሆነ ባለማ ወቅ ያጠፉትን እያሰቡ እንዲህ ባደርግ እንዲህ ያደርጉኛል፣ ብገልጣቸው ይገልጡኛል፣ ብነግራቸው ይነግሩኛል ብለው ይፈራሉ፡፡ ከጀግኖች ሜዳም ይሸሻሉ፡፡ ይህ ግን የኢት ዮጵያን ሕዝብ ጠባይ ካለማወቅ የሚመነጭ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ የጀግናን ኃጢአት ያስተሠርያል፡፡ ስለ ጀግኖቹ ክፉን ነገር ለመስማት በፍጹም አይፈልግም፡፡ የዚያን ሰው ርእዮተ ዓለም ባይቀበሉትም፡፡ ያ ጀግና እነርሱን ለመውጋት የተሰለፈም እንኳን ቢሆን፤ ጀግና ከሆነ ጀግንነቱን እንጂ ሌላውን አያይም፡፡

አባቶቻችንም እንዲህ እና እንዲያ እንጽፍባችኋለን እያሉ ከጀግንነቱ ሜዳ የሚያስቀሯችሁን አትቀበሏቸው፡፡ ባለፈው ሰሞን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሳሙኤል ላይ ራሱን ቤተ ክህነትን የሚያሳፍር መጽሐፍ ተጻፈ፡፡ ግን ሕዝቡ ተቀበለው? አመነ? በብጹእ አባታችን ላይ ፊቱን አዞረ? ፈጽሞ፡፡ ሕዝቡ ጽሑፉን ሳይሆን ለምን እንደ ተጻፈ ነው ያነበበው፡፡ በጻፉት ላይ አዘነባቸው፤ ኀዘኑም ደርሶ ጸሐፊዎቹን እና አጻፊዎቹን እርስ በርስ አባላቸው እንጂ በእርሳቸው ላይ ምን ቀነሰባቸው፡፡ ከፊት ይልቅ ከበሩ፣ የማያውቃቸው ዐወቃቸው፡፡

ማስፈራሪያ እና ፈንጣጣ አንዴ ከወጣ በኋላ ዳግም አይመጣም፡፡ ጀግና መጀመርያ ማሸነፍ ያለበት ፍርሃትን ነው፡፡ ፍርሃትን ያላሸነፈ ሰው ሊጀግን አይችልም፡፡ እናም አባቶቻችን መጀመርያ ፍርሃትን አርቁት፡፡ እናንተም እንደምታስተምሩን መላእክት እንኳን ወደ ሰዎች ሲመጡ መጀመርያ የሚያርቁት ፍርሃትን ነው፡፡ «አትፍሪ፣ አትፍራ» ነው የሚሉት፡፡

ወሳኔዎቹ መወሰናቸው በራሱ አንድ ገድል ነው፡፡ ከሲኖዶስ የሚጠበቀው ትልቁ ነገር ጠንካራ ውሳኔ ነው፡፡ ቢያንስ የተሠሩት ስሕተቶች የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ አለመሆናቸውን ያሳያል፡፡ ነገ ታሪክ ለሚጽፉ ሰዎች በቂ ማስረጃም ይሆናል፡፡ ዛሬ ስሕተቱን ማረም ባይቻል እንኳን አርጌንስ ከሞተ በኋላ ተወግዞ ስሕተቱ እንደታረመው ሁሉ እንዲያ የሚደረግም ይኖራል፡፡

አባቶች አሁን የጀመሩትን ጀግንነት በሦስት ነገሮች ማጽናት አለባቸው፡፡ በአሠራር፣ በቀጣይነት እና እንዳይደገም በማድረግ፡፡ ስሕተቱ እንዲፈጸም በር የከፈቱትን አሠራሮች ረጋ ብለው መዝጋት እና ማስተካከል አለባቸው፡፡ ጀግንነቱ በአንድ ጉባኤ ታይቶ የሚጠፋ መሆንም የለበትም፡፡ በየጉባኤያቱ፣ በየሀገረ ስብከቱ፣ በየመምሪያው መቀጠልም አለባቸው፡፡ ችግር በሂደት እንጂ በክስተት አይፈታምና፡፡ የመጨረሻው ደግሞ ያለፈውን ለማጥራት እንዲቻል ሌሎች ስሕተቶች እንዳይደገሙ መደረግም አለባቸው፡፡ ለምሳሌ ስለ ቀጣዮቹ ጳጳሳት አሿሿም፣ ስለ መምሪያ ኃላፊዎች ሹመት እና አሿሿም ማሰብ እና መጨነቅ አለባቸው፡፡

ሦስት ነገሮችን ደግሞ ማሰብ አለባቸው፡፡ እግዚአብሔር ከጀግኖች ጋር ነው፡፡ የሰማዕታት ታሪክ ይህንን ይነግረናል፡፡ ሕዝብ ከጀግኖች ጋር ነው፡፡ አቡነ ቄርሎስን በግሪክ እና በጀርመን ለማሳከም ምእመናን ያደረጉት ርብርብ እና የሰሞኑ ዜና ሲነገር ሕዝብ የተሰማው ስሜት ይህንን ያሳየናል፡፡ መንግሥትም ከጀግኖች ጋር ነው፡፡ ሀገርን ማሳደግ፣ ሕዝብን ማሠልጠን፣ የሀገርን ገጽታ መገንባት፣ የሚሻ መንግሥት ጀግኖችን ይፈልጋል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ጀግና ናፍቆታል፡፡


42 comments:

 1. Kele hiywote yasemalin!!!

  ReplyDelete
 2. Kale Hiwot Yasemalin, Mengiste Semayatin Yawrislin D/N Daniel. I think you hit all the spots, Ethiopians need heroes, and heroes want attention so lets mention this great deed to all we know so our father can continue to accomplish such victories over the devil. May god contiue to bless our Home Land and Our Tewahedo. God Bless

  ReplyDelete
 3. Good view.
  How can this message reach our Fathers? Who can read it for them? I really Afraid that the decision will be realized. Cos ...

  ReplyDelete
 4. Thanks a lot Dn. Daniel. Keep on persuading everyone for the sake of spiritual truth and continuation of our apostlic church's grace.

  Esdros Zelideta, Gondar

  ReplyDelete
 5. ዲያቆን መሐሪ ገብረማርቆስOctober 28, 2010 at 11:47 AM

  ብፁዓን አበው ጳጳሳት ሆይ እባካችሁ የምንለውን ስሙን፡፡ ስብሰባውን በአርምሞ ሲከታተል የነበረው ሰይጣን በክፉ ሐሳብ አይከፋፍላችሁ፡፡

  ለቤተክርስቲያን የሚጠቅምን ነገር እንጂ አምባገነኖች ለሹመታቸው መደላደል ሲሉ የሚፈጥሩት መዘበራረቅን አትቀበሉ፡፡ እንደርግብ የዋኀን እንደ እባብ ብልኅ ሁኑ እያላችሁ የምታስተምሩንን አሁን በተግባር አሳዩን፡፡ ክፉዎችን፣ ለራሳቸው እንጂ ለቤተክርስቲያን የማያስቡትን ዕወቁባቸው፡፡ ክፉ ዕቅዶቻቸውንም አትቀበሏቸው፡፡ ቤተክርስቲያንን በመንፈሳዊነት ሳይሆን በማኪያቬሊ የተንኮልና የማበጣበጥ ፍልስፍና ሊቆጣጠሩ የሚሹትን ሰዎች ንቁባቸው፡፡ የዋኅነታችሁን ሊጠቀሙበት ይሻሉና፡፡

  ስለ ጽዮን ዝም አትበሉ፡፡ ተሟቱላት፡፡ ሙቱላት፡፡ ጀግኖች ሁኑልንና እንከተላችሁ፡፡

  እባካችሁ፡፡ እባካችሁ፡፡ እባካችሁ፡፡

  ድንግል ሆይ እባክሽን ስሚን፡፡ ያየነው ጭላንጭል ብርሐን አይወሰድብን፡፡

  ReplyDelete
 6. ''ቁርጥ ቀን ባይመጣ ሁሉም ጀግና ነበር፣
  አስክመጣ ድረስ ቁርጥ ቀን በቶሎ ፣
  ፈርም ያውቅበታል መኖር ተመሳስሎ ''
  አባቶቻችን!! ሃይማኖት አኮ ዛሬ አኛ አልጀመርናትም ሐውልቱን የባረከ ጳጳስን ''አቦ ፣አቦ፣'' ብላችሁ አስቀምጣችሁ ልትሄዱ ነው ?
  ስርዓተ ቤተክርስትያንን ህገ ቤተክርስያንን ያፈረሰ አይወገዝም አይለይም ?
  የ ቅዱሳን አባቶቻችን አጥንት አይወጋንም?

  ReplyDelete
 7. Thank you Dani,

  We need heroes these days more than ever. It has been very difficult for all orthodox Christians. We want to hear news of reformation, forgiveness, admittance of past and current mistakes made.

  GOD you are the almighty, please don't forget your nation who is very sad for the wrong doings of your ministries. They were supposed to be a Shepperd to all of us.

  Amlak gimirun endasamerewu afetsatsemun yasamirew AMEN AMEN AMEN. I am really really really happy at the moment that is what matters, the future can think for itself.

  ReplyDelete
 8. ማስፈራሪያ እና ፈንጣጣ አንዴ ከወጣ በኋላ ዳግም አይመጣም፡፡
  የኢትዮጵያ ሕዝብ ጀግና ናፍቆታል፡፡
  bravo dani!!

  ReplyDelete
 9. ላስተያየት ሰጪዎች አስተያየታችሁን ስትጽፉ እውነታውን እዲሁም አስባችሁ ብትጽፉ እንዲያው ዝም ብላችሁ በስሜታዊነት፣በጥላቻ፣…… ባይሆን ክርስትና የፍቅር(የመተሳሰብ፣የመካባበር፣የይቅር ባይነት…) እምነት ከሥነ-ምግባር አንጻር መሖኗንም አንርሳ፨ ከሀይማኖት(ዶግማ) አንጻር ግን ርትዕት የሆነችውን ተዋሕዶን የነካ ያለምንም ርህራሄ መወገዝ ነው ያለበት!!!!!

  ReplyDelete
 10. ልክ ነህ ዳኒ እውነተኛ ጀግና ናፍቆናል

  ReplyDelete
 11. ወለተማርያምOctober 28, 2010 at 1:50 PM

  እግዚአብሔር ለመፈጸም ያብቃን እላለሁ!

  ReplyDelete
 12. Great,

  I am happy with the decision but do not agree on the way how we get the information.

  we should not be emotional. At least we had to wait until we get the official decision from the meeting.

  this is the big problem, our fathers are having meeting there and the information is leaking before it is finalized.

  The decision should be made official in a formal way not in sush informal way.

  ReplyDelete
 13. እርግጥ ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጀግና ይወዳል - በተልይ መንፈሳዊ ጀግና ።
  ደግሞ በዚህ ወቅት ከመውደድ በላይ እጅግ ይናፍቃል ።
  እግዚአብሔር ጀግና ያስነሳል እንደሚያስነሳ እርግጠኞች ሆነን በፀሎት መትጋት ነው የሚጠበቅብን ።
  " እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመፅ
  ወአምላክነሂ ኢያረምም
  እሳት ይነድድ ቅድሜሁ"

  ReplyDelete
 14. Selam Dani,

  Egziabher ysiteln

  Esti tselyu enen embi belongal, egziabhr endtarken

  ReplyDelete
 15. ወንድም ዳንኤል ቃለ-ህይወት ያሰማልን እያልሁ የሚሰማኝን ላስቀምጥ። በርካታ ፍሬ ሃስቦችን የዳሰስህ ሲሆን ፣ ይህ የሲኖዶሱ ውሳኔ ግን በኔ ላይ አንዳች ያሳደረው ትልቅ ተስፋ እና ተይዠበት ከኖርሁት ጨለምተኝነትም የገላገለኝ ጉዳይ አለ። በስደት እንደኔው የሚንከራተቱ ኢትዮጵያውያንም ይጋሩት ይሆናል። ይኸውም ፣ አገር ቤት ያለውን ሲኖዶስ ፈጽሞ በመንግስት ተጽኖ ስር የወደቀ እና የጳጳሱንም ጉዳይ ብቻ አስፈጻሚ አድርጌ በማሰብ ፣ በውጭ የሚገኙ ጳጳሳትን በሙሉ ልብ የኢትዮጵያ ችግር መፍትሄ አድርጌ ነበር የምመለከተው። ዛሬ ግን የሲኖዶሱን ውሳኔ ስመለከት ፣ ነገ በአገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ አባቶች ፣ መንፈሳዊ ቅርርብ የማድረግ ትስፋ እንዳላቸው እንድጠብቅ ሆኛለሁ። ይህ ደግሞ ተፈጻሚ የሚሆነው “አስታራቂ ሽማግሌ እንሁናችሁ” በሚሉ አለማዊ ፖለቲከኞች ሳይሆን ፣ በራሷ በቤተክርስቲያናችን መንፈሳዊ አባቶች አማክኝነት እና በተለይም በሲኖዶስ ደረጃ እንደሚፈታ በመተማመን ነው።

  ዜናው ተፈጻሚ እንዲሆን እግዚያብሄር አይለየን
  በለው ከካናዳ

  ReplyDelete
 16. Yes indeed "ችግር በሂደት እንጂ በክስተት አየፈታም", So, implementation of those heroic decisions requires the consistent follow up of our fathers and their unity. They should stay in their unity to see the fruits of their glorious decisions.Otherwise they will exposed to the hands of the Patriarch which is ready to take revenge over those who considered as enemies of his superiority and Infallibility.
  Good job Dani

  ReplyDelete
 17. Qale hiwoten yasemalen !!!

  teru eyeta new EGZIABHER lulachenm endezih yemenastewlebetn aemero yadelen

  ፡፡ ለምሳሌ ስለ ቀጣዮቹ ጳጳሳት አሿሿም፣ ስለ መምሪያ ኃላፊዎች ሹመት እና አሿሿም ማሰብ እና መጨነቅ አለባቸው፡፡

  yewsanewen fetame betegebar yasayen ega yemanawekewn gudelet AMELAKACHEN yasekakelelen Amen

  EGZIABHER betekereseteyanachenen ena Ethiopian yebarekelen yetebekelen

  yetelat medesecha ayderegen Amen !!!!

  ReplyDelete
 18. ዳኒ አንተም አንተም የእኛ ጀግና ነህ

  ReplyDelete
 19. ይህንን ሁሉ ላደረገልን ለሉዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይግባው ቅዱስ ሲኖዶሱ የሚመሰገን ሥራ ነው የሠራው አሁንም የበለጠ ሥራዎችን መሥራት ይጠበቅበታል የተወሰኑትን ውሳኔዎች ጊዜ ሳይሰጥ ተከታትሎ ማሥፈጸም አለበት በየአጥቢያው ቤተክርስትያን ያለውን የተበላሽ አሰራር ትኩረት ሰጥቶ መከታተል እግዚአብሔር ከናንተ ጋር ነውና መሰረቱን ማጠናከር በቤተክርስትያናችን ላይ ብዙ ጠላቶች አሉባት ይህንን የምናሸንፈው አንድ ስንሆን ነው ሁላችንም ባለንበት ሐላፊነታችንን በአግባቡ እንወጣ ያገር ቤቱን አስተካክለን ደግሞ በውጪ ቤተክርስትያናችን የሚሰራውን በደል ምዝበራ በብሄር መሰባሰብ አላግባብ ሹመቶችን እንያቸው ብዙ ቤተ ክርስትያን እየጠፉ ነው ባለቤት የሌላችው ያስመስላቸዋልና ሁሉን ትተን ወደፊት እንሂድ የትናንቱ ችግር እንዳይከሰት ቀዳዳዎችን እንድፈን እግዚአብሔር እስከምጨረሻው ድረስ ይርዳን

  ReplyDelete
 20. ++=

  ዲያቆን ዳንኤል ቃለ-ህይወት ያሰማልን እያልሁ እርግጥ ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጀግና ይወዳል እውነተኛ ጀግና ናፍቆናል::ስለ ጽዮን ዝም አትበሉ፡፡ ተሟገቱላት፡፡ ሙቱላት፡፡ ጀግኖች ሁኑልንና እንከተላችሁ፡፡ ለምሳሌ ስለ ቀጣዮቹ ጳጳሳት አሿሿም፣ ስለ መምሪያ ኃላፊዎች ሹመት እና አሿሿም ማሰብ እና መጨነቅ አለባቸው፡፡ ሁሉ ላደረገልን ለሉዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይግባው

  ReplyDelete
 21. +++
  Ahun metahu ayschelm andandu neger ewnathn new jergan enwdalen Abate Eka enkuan sewadk "ANBESAW" yelale yensesoch alekan? awo westachnen yeselabn dekma gonach yewgdeln ena
  "አባቶች አሁን የጀመሩትን ጀግንነት በሦስት ነገሮች ማጽናት አለባቸው፡፡ በአሠራር፣ በቀጣይነት እና እንዳይደገም በማድረግ፡፡ ስሕተቱ እንዲፈጸም በር የከፈቱትን አሠራሮች ረጋ ብለው መዝጋት እና ማስተካከል አለባቸው፡፡ ጀግንነቱ በአንድ ጉባኤ ታይቶ የሚጠፋ መሆንም የለበትም፡፡ በየጉባኤያቱ፣ በየሀገረ ስብከቱ፣ በየመምሪያው መቀጠልም አለባቸው፡፡ ችግር በሂደት እንጂ በክስተት አይፈታምና፡፡ የመጨረሻው ደግሞ ያለፈውን ለማጥራት እንዲቻል ሌሎች ስሕተቶች እንዳይደገሙ መደረግም አለባቸው፡፡ ለምሳሌ ስለ ቀጣዮቹ ጳጳሳት አሿሿም፣ ስለ መምሪያ ኃላፊዎች ሹመት እና አሿሿም ማሰብ እና መጨነቅ አለባቸው፡፡ enberta adera Tselot aykuaret Mesaku yebkan malksem yaseflgenal for our mother church! Ke toronto akbari betseboch

  ReplyDelete
 22. Glory be To God who created us so we can worship his glorified name. I am really happy with what i am hearing. I am an eritrean orthdox tewahedo, growing up in ethiopia this pain that our church was going thru was hurting me and my friends like wise. Because it doesn't matter if you are serian, indian, coptic, armenian, ethiopian or eritrean our belief our dogma makes us one....So how could i not be happy, how could i not shed tears of joy....Tewahedo semayawit Yetesenach emineti hale luya.... I am so happy abune Abrham is staying in DC.... on top of everything else that is. And D/N daniel i really love your teachings of Gedilat, and tarik of kidusan that we dont' hear any more from the new sebakiyans... It really tells us to strive and ye kedemutin le maseb....please continue doing what you are doing... may i suggest that you start recording sibkets in cd so we can have it for generations to come. Every body else is doing it to teach the tehadeo teaching why not you and all the real tewahedos out there. God bless you and God bless our haimanot.

  ReplyDelete
 23. kale hiwote yasemalene Dn.

  ReplyDelete
 24. Amen kale hiwot yasemahe. am so happy dani
  /Tse/

  ReplyDelete
 25. መንግስቴ ያያOctober 29, 2010 at 10:46 AM

  ቃለ ህይወት ያሰማልን ረጅም እድሜ ይስጥልን

  ReplyDelete
 26. የማይበላ እንዳያስበላ ያብላላOctober 29, 2010 at 11:08 AM

  " መንግሥትም ከጀግኖች ጋር ነው፡፡ ሀገርን ማሳደግ፣ ሕዝብን ማሠልጠን፣ የሀገርን ገጽታ መገንባት፣ የሚሻ መንግሥት ጀግኖችን ይፈልጋል፡፡"

  ጆሮ ያለው ይስማ !

  ReplyDelete
 27. simply great happiness

  ReplyDelete
 28. እኔ በበኩሌ በሀውልቱም ሆነ በየቤተክርስቲያኑ የተሰቀለውን የአቡኑን ፎቶ ስላልወደድኩት ይህንነን በመስማቴ እግዚያብሄር የተመሰገነ ይሁን ይፍረስ በየቤተክርስቲያኑ በር ላይ ተሰቅሎ ለመፀለይ የሚያስቸግር

  ReplyDelete
 29. ወልደ ዮሐንስOctober 29, 2010 at 11:45 AM

  የሐይማኖት አርበኛ ማለት አንዱ ይሄ አይደል?
  የቅዱስ ሲኖዶስ በረከቱ ይደርብን መግቦቱም አይለየን አሜን

  ReplyDelete
 30. ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡ ሐውልተ ሥምዕ በሕይወት ሳሉ የሚያሠሪት እነ ናቡከደነፆርን የመሳሰሉ መምለኬያነ ጣዖት እንጂ አንደ የሃይማኖት አባት ይልቁንም ፓትርያርክ እንዲህ ዓይነት ክፉ ሃሳብ እንዴት አሰቡት!!! ጠቅላይ ሚኒስተሩ እንኳን ለጀግኖች ሰማዕታት ሐውልት ሲያሠሩ ለራሳቸው አለማሠራታቸው ምንያህል እኛ ከምድራውያን መሪዎች በታች እንሆናለን!አወይ የኛ ትዕቢት ብቻ እግዚአብሔር ከነ ብዙ ችግራችን ችሎናልና ነው እንጂ መቅሰፍት አለመምጣቱም ንስሐ እንገባ ዘንድ መሆኑን ተገንዝበን በሐውልቱ ሥራ የተበርን ሁሉ እንመለስ እላለሁ ይልቁንም ፓትርያርኩ!
  የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን ግን ሳላመሰግን አላልፍም፡፡

  ReplyDelete
 31. daniel kale hiwot yasemah!thank u. lik bilehal.

  ReplyDelete
 32. Dani, do you know that you are also one of the heroes? Your articles, books, audio-video preachings, firm stand in tewhdo faith, being with us in Ethiopia, etc reveal your practical christianity. I saw you with your family last Meskerem 1 at Entoto Raguel. Not only you but also Dn Zelalem. I was extremely happy. Because many of the old famed preachers are with our brothers and sisters in diaspora. I don't have objection on that.Because christianity is not bound by territory. Any way there are many unseen heroes of our church. I am very glad by the decisions of our Holy synod. This is a glimmer of hope to our apostolic church. Glory to God in the highest heaven.
  Jimmaa biyya Abbaa Jifaarirraa.

  ReplyDelete
 33. ጀግና መሆን የናፈቀው አባት እግዚአብሔር ይስጠን፡፡ እንደ ቀደሙት ሰማእታት ይህ ሰማዕትነት እንዳያመልጠን እያለ የሚጣደፍ አባት እግዚአብሔር ያድለን፡፡ በእውነት ልቤ እጅግ…….. ናፍቋል ቤተክርስቲያን ክብሯ ተመልሶ ለማየት፡፡

  ማሂ

  ReplyDelete
 34. እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገልን ደስም አለን!!!

  ReplyDelete
 35. የማይበላ እንዳያስበላ ያብላላOctober 29, 2010 at 8:53 PM

  "በዚህ ሰዓት ሕዝቡ እንደ አጥቢያ ኮከብ ከሩቅ የምታበራለት አንዲት ሀገራዊ ተቋም ጉዳይ እያሳሰበው እንዴት ልቡን ሰብስቦ ስለ ዕድገት ያስብ፡፡ የነበረውን እያጣ እንዴት አዲስ አገኛለሁ ብሎ ተስፋ ያድርግ"

  እናስተውል !

  ReplyDelete
 36. God bless Ethiopian for ever.

  ReplyDelete
 37. We have such a great spiritual lineage to learn from. Chapter 11 of the book of Hebrews tells us about spiritual heroes, men and women who put their confidence in God, like Abel, Enoch, Noah, Abraham, Sarah, Isaac, Jacob, Joseph, Moses, Rahab, Gideon, Samson, Samuel, David, and Daniel. They were all far from perfect models, but they had the courage to not give up. God offers to each of us a journey of hope. May God bless your journey.
  In the world there are many kind of heroes.In christianity a hero is the one who preach the gospel like Apostle Paul,who is perscuted for the sake of the gospel of Jesus Christ.In christinity being hero is directly related to applying the word of God in our daily life.

  ReplyDelete
 38. Dani, kalehiwot yasemalin
  I am realy happy of the decision. and we all should also be heroes by keeping christanity in our day to day life.

  Abiot from oldenburg,Germany

  ReplyDelete
 39. God is God of impossibility!
  Egzebher yechel yele gena enayalen edme tigest keseten

  ReplyDelete
 40. Don't be glad,however,because you have power over sprits, but because your names are recorded in heaven Lu 10-17.Please let us think over, We are true christian and citzenship of heaven.Now is it relevent to talk about dead things that doesn't give life.

  ReplyDelete