አንድ የቆሎ ተማሪ ነበረ አሉ፡፡ ትምህርት አይወድም፡፡ ትምህርት ያደክማል የሚል ፍልስፍና ነበረው፡፡ «ትምህርት ይቀትል፣ ወምላስ የሐዩ» የሚለው አባባሉ ተይዞለታል፡፡ እግረ ተማሪ የሚሉት ዓይነት ነው፡፡ በየትምህርት ቤቱ ይዞራል እንጂ ቀለም አይዝም፡፡ እርሱ እቴ የሚፈልገው «ከየኔታ እገሌም ይህን ተምሬያለሁ፣ ከየኔታ እገሌም ይህን ቀጽያለሁ» እያለ ማውራት ነው፡፡
ታድያ የመንደሩን ወይዛዝርት እና መኳንንት ለመቅረብ እና ጠባያቸውን ለማወቅ ማንም አይቀድመውም፡፡ እያንዳንዱ ቤት ድግስ የሚደግስበትን ዝክር የሚያዘክርበትን ቀን ከባለቤቶቹ በላይ እርሱ ያውቀዋል፡፡ ክብረ በዓል ሲሆን አምሞ ጠምጥሞ ዋዜማ ይቆማል፡፡ ነገር ግን አንዲት ቀለም ከአፉ አትወጣውም፡፡ ብቻ ወይዛዝርቱ እንዲያዩት ከፊት ከኋላ እያዠረገደ ያሟሙቃል፡፡ አይመራ፣ አይመራ፣ አያዜም፣ አይቀኝ፣ መቋሚያውን ይዞ አንገቱን እንደ በግ እንደደፋ ያመሻል፣ያድራል፡፡
ጠዋት ታድያ የዓመት በዓሉ ድግስ ቤተ ምርፋቅ ሲገባ ከሊቃውንቱ እና ከካህናቱ ቀድሞ የከበሬታውን ሥፍራ የሚይዘው እርሱ ነው፡፡ ሴት ወይዛዝርቱ እና ወንድ መኳንንቱ ሌሊት ሲያዠረግድ ስላዩት ሊቅ የሚመስላቸው እርሱ ነው፡፡ አንዳንዶቹማ እርሱ ባይኖር ማኅሌቱ አይደምቅም ነበር እያሉ የመሪጌታውን ቦታ ይሰጡታል፡፡
«ለእገሌ ጣሉለት ለእገሌ ንሡት» እያለ አጋፋሪ ሆኖ ድግሱን ያሳምረዋል፡፡ ያ ሌሊቱን ጨዋ ሆኖ ተለጉሞ ያደረ አንደበት አሁን ጉሮኖ እንደ ሰበረ የፍየል መንጋ ይለቀቃል፡፡ «ፈቀደ እግዚእ» እንኳን ለማለት የተሣሠረ ምላስ ቤተ ምርፋቁን የዋሸራ ባለቅኔ የገባበት ቅኔ ማኅሌት ያስመስለዋል፡፡ በየዋሕነት አንገታቸውን እየነቀነቁ ለሚሰሙት ምእመናን የባጡን እና የቆጡን ብቻ ሳይሆን የመደቡንም ሳይቀር ይለፈልፍላቸዋል፡፡
ታድያ ይህ ጠባዩ ሊቃውንቱን እና ተማሪውን እያናደደ ቢኖርም አብዛኞቹ ዳዊቱ እንደሚለው «በልባቸው ይረግሙት» ነበር እንጂ ገሥፀውት አያውቁም ነበር፡፡ ምእመናኑም ለደብሩ እጅግ አስፈላጊ ሰው ስለመሰላቸው «መሪጌታ» እያሉ እፍታ እፍታውን የሚጥሉት እርሱ ገበታ ላይ ነው፡፡ ስለ ድግሳቸውም የሚያማክሩት እርሱን ነው፡፡
አንድ ቀን አንድ ኃይለኛ ተማሪ ገጠመው፡፡ ያመቱ ማርያም ዋዜማ ተቁሞ እያለ የሊቁን ቅኔ በዜማ ተመራ አለው፡፡ አጅሬ ዐቅሙን ያውቃልና በብልጠት ትኅትና አንገቱን ደፋ፡፡ ከበሮ ያዝ አለው፤ «ሲይዙት ያደናግር» የሚሉት ይደርስብኛል ብሎ አይሆንም አለ፡፡ «መልክአ ማርያም አድል» አለው፡፡ «ከኔ የሚበልጡ አሉ» እያለ ሸሸ፡፡ እንዲህ ሲያመልጥ ሲያመልጥ ቅዳሴው ደረሰ፡፡
ሠርሖተ ሕዝብ ሆኖ ካህን እና ሕዝብ ወደ ድግስ ሲወርዱ ቀድሞ መደላድሉን ይዞ ያሣምረው ጀመር፡፡ ያወቀ እየሳቀ፣ ያላወቀ እያደነቀ ድግሱን ተቀላቀለ፡፡ እየበሉ እየጠጡ ዝም የጋን ወንድም ይባላል፡፡
ዝ ጠላ ከመ ወይን ጣዕሙ
እስኩ ድግሙ ድግሙ
እስኩ ድግሙ
እያለ በዜማ እያወረደለት የደረቀ ጉሮሮውን ቋሚው ሁሉ አራራሰው፡፡ ሆድ ሲደላደል፣ ጉሮሮ ሲረጥብ ምግቡ ተግ ይልና ጨዋታው ይደራል፡፡ የአጅሬም ሊቅነት አሁን ይጀምራል፡፡ እንደ አራቱ አፍላጋት የርሱ ወሬ አራቱን መዓዝን ያዳርሰዋል፡፡
አንዱ ተናደደ፡፡ አጽፉን አጣፋና ዘሎ ተነሣ፡፡ ወደ አጅሬ እያየም እንዲህ አለ፡፡
ሀገርከ ቆላ ወስምከ ወርቄ
በጊዜ ማኅሌት በግዕ ወበጊዜ መክፈልት አንቄ፡፡
ሊቁ ሁሉ አወካ፡፡ ከዳር እዳር አስገመገመ፡፡ «ወገብረ መብረቀ በጊዜ ዝናም» በዝናም ጊዜ መብረቅን አደረገ ማለት ይኼ ነው አሉ፡፡ አጅሬ ውርጭ እንደ መታው የሞላሌ በግ ነጭ ሆነ፡፡ «ሀገርህ ቆላ ነው ስምህም ወርቄ ነው፤ በማኅሌት ጊዜ እንደ በግ ዝም ትላለህ፣ መክፈልት ሲመጣ ግን እንደ ጭልፊት ትሞጨልፋለህ» ነበር ያለው፡፡
እነሆ ይህ ታሪክ በቆሎ ትምህርት ቤት ምሳሌ እየሆነ ሲነገር ይኖራል፡፡
ወርቄ ብቻውን አይደለም፡፡ ከእርሱም በፊት ሆነ ከእርሱ በኋላ ብዙ ሰዎችን አፍርቷል፡፡ በትግሉ፣ በሥራው፣ በልፋቱ፣ በድካሙ፣ ከውጣ ውረዱ የሉበትም፡፡ በግ ናቸው፡፡ ከድግሱ፣ ከሹመቱ፣ ከሽልማቱ፣ ከመድረኩ፣ ከአደባባዩ፣ ከሙገሳው፣ ከምርቃቱ እንደ ጭልፊት ማንም አይቀድማቸውም፡፡
የአፍ ቅልጥፍና ከአእምሮ ቅልጥፍና፣ የምላስ ርዝመት ከልቡና ስፋት፣ የከንፈር ፍሬ ከሥራ ፍሬ፣ ሥራ ከመቻል ውዳሴ መቻል ይበልጥ በሚወደድበት ማኅበረሰብ ውስጥ ወርቄ ትልቅ ቦታ አለው፡፡
ወርቄ ምን ተሠራ? ለሚለው አይጨነቅም እንዴት ይቀርባል? የሚለው ነው የሚያስጨንቀው፡፡ ወርቄ አሳማኝ ነገር አለ ወይስ የለም? የሚለው አይደለም የሚያስጨንቀው፤ እንዴት ማሳመን ይቻላል የሚለው ነው፡፡ ወርቄ ምን ውጤት መጣ? አያሳስበውም፡፡ ምን ይታይ? የሚለው ግን እንቅልፍ ይነሣዋል፡፡ የወርቄ መመርያ «ሰው የሚጠቅመውን ሳይሆን የሚያየውን ይመርጣል» የሚለው ነው፡፡ ከሰው ልብ ከመግባት ከሰው ዓይን መግባት ይሻላል ይላል ወርቄ፡፡
ሲሠራ አይታይም፤ ሲሸለም ግን ይታያል፤ ሲደክም አይታይም፣ ሲመሰገን ግን ይገኛል፤ ሲለፋ አይታይም፤ ሲደነቅ ግን ይታያል፤ በስብሰባው ሰዓት የለም፤ መግለጫ ግን ይሰጣል፤ ከምርምሩ የለበትም፤ ምርምሩ ሲታተም ግን ስሙ ይጠቀሳል፡፡ የመስክ ሥራው ላይ የለም፤ ሪፖርቱ ውስጥ ግን ይገባል፡፡ የመሥሪያ ቤቱን ሥራ አያውቀውም፣ ስለ መሥሪያ ቤቱ ግን የሚጠየቀው እርሱ ነው፡፡
ወርቄ ብዙ ዕውቀት አያውቅም፤ ብዙ ሰው ግን ያውቀዋል፡፡ ወርቄ ሞያ የለውም፣ ብዙ ባለሞያ ግን ያስተዳድራል፡፡ ወርቄ ስለ ጉዳዩ ባያወቅም፣ ያንኑ የማያውቀውን ጉዳይ እንዲመራ ግን ይመረጣል፡፡ ወርቄ ልብስ አያሰፋም፤ ሌሎች ያሰፉትን ግን አሣምሮ ይለብሰዋል፡፡ ወርቄ መዓድ አይሠራም፡፡ ሌሎች የደገሱትን ግን በሚገባ ያስተናግዳል፡፡ ወርቄ አያበላም፡፡ በሰው ግብዣ ግን ብሉልኝ ጠጡልኝ ይላል፡፡
ጓደኞቹ የማኅሌቱን ቀለም ለማጥናት ሁለት ሦስት ዓመት ይወስድባቸዋል፡፡ ወርቄ ግን በጆሮ ጠገብ ስለ ማኅሌት የሚያውቀውን አሠማምሮ መክፈልቱን ለማግኘት ደቂቃ አይወስድበትም፡፡ ከማኅሌታውያኑ በላይ ማኅሌታዊ ሆኖ ብቅ ይላል፡፡ እንዲያውም ስለማኅሌታውያኑ ሞያ የሚያስተዋውቃቸው እርሱ ይሆናል፡፡
በሹመት አደባባይ፣ በከበሬታ ሥፍራ፣ በመኳንንት ደጅ፣ በወይዛዝርት ሳሎን፣ በድግስ አዳራሽ፣ ወርቄዎች ሞልተዋል፡፡ ወርቄ ለጋዜጠኞች ቅርብ ነው፡፡ ለቴሌቭዥን መስኮትም ይስማማል፡፡
ብዙ ማኅሌታውያን ወርቄን ይፈሩታልም፣ ይፈልጉታልም፡፡ ዕውቀት የማይከፍታቸው፣ ችሎታ የማይሰብራቸው፣ ሞያ የማይደፍራቸው፣ ብቃት የማይሻገራቸው፣ ሊቅነት የማይደርስባቸው፣ ትኅትና የማያልፍ ባቸው፣ አያሌ በሮች አሉ፡፡ እነዚህን በሮች ለማለፍ እንደ ወርቄ ያሉ ያስፈልጋሉ፡፡ የምሁራኑን፣ የሊቃ ውንቱን፣ የባለሞያዎችን ጸሎት ወደ ጽርሐ አርያም ለማሳረግ ያለነ ወርቄ አማላጅነት አይሆንም፡፡ እነ ወርቄ ቅጣልን ብለው ያስቀጣሉ፤ ማርልን ብለው ያስምራሉ፡፡
እንደዚያ የነደደ የቆሎ ተማሪ እነ ወርቄን ደፍሮ የሚናገራቸው የለም፡፡ የሌላቸውን አለን፣ ያላደረጉትን አድርገናል፣ ያልሆኑትን ሆነናል፣ ያልደረሱበትን ደርሰናል ሲሉ ዝም ይባላሉ፡፡ ደግሞ በዚህ ሀገር ትርጉም ዝምታ ቁጥሩ ከመስማማት ነው፡፡ የሰው ድካም ወስደው የራሳቸው አድርገው ሲያቀርቡ፣ ባልተዋጉበት ግዳይ ሲጥሉ፣ ያለ ቃላት ድርሰት፣ ያለተዋናይ ድራማ ሲሠሩ፤ ያለ ዜማ ሙዚቃ፣ ያለ ካሜራ ፊልም ሲሠሩ፤ የሚናገራቸው የለም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ነገሩን ማን ሠራው? የሚለው ይቀርና ማን የኔ ነው አለ? የሚለው ዋና ጉዳይ ይሆናል፡፡
ተማሪው ጎጃም የሚገኙትን የመምህሩን ቅኔ ይዞ ይሄድና አያውቁብኝም ብሎ ትግራይ ውስጥ ቅኔ ማኅሌት ገብቶ ይዘርፈዋል፡፡ የራሱ እንዲመስል ንፋስ እንደ ነካው የወፍ መንጋ ከግራ ወደ ቀኝ ከቀኝ ወደ ግራ እየተመላለሰ ያወርደው ጀመር፡፡ በግራ በቀኝ የነበረው ተመልካች ሰም እና ወርቁን ፈትቶ ምሥጢሩን ባይረዳውም ድምፁን እና እንጉርድጃውን አይቷልና ይበል ይበል ብሎ አጨበጨበለት፤ እልልታውም ደመቀለት፡፡
ስሜቱ በርዶ፣ ፊቱም እንደ ሕፃን ልጅ ተፍለቅልቆ ወደ ማኅሌታውያኑ ሲመለስ አንዱ ሊቅ ዞር አሉና «የኔታ እገሌ ቅኔስ ደረሰን፤ ለመሆኑ የኔታ ደኅና ናቸው» ብለው ጠየቁት፡፡ እንደ ዳታን እና አቤሮን መሬት ተከፍታ የዋጠችው ነው የመሰለው፡፡
ዛሬ ማን እንደዚህ ይላል፡፡ በየምርምር ቦታዎች እነ ወርቄ የሰው ጥናት ሲዘርፉ፣ በየሥነ ጽሑፍ መስኩ እነ ወርቄ የሰው ድርሰት ሲነጥቁ፣ በየሥነ ጥበብ ሜዳው እነ ወርቄ የሰው ዜማ ሲሞጨልፉ፣ ከፈጠራ ጓዳ ገብተው የሰው ሃሳብ እና የፈጠራ ውጤት በስማቸው ሲያወጡ፤ ሳይደክሙ ሲሾሙ፣ ሳይጾሙ ሲፈስኩ፤ ሳይማሩ ሲያስተምሩ፣ ሳይሠሩ ሲከበሩ ማን ይናገራቸዋል፡፡
የሚነግዱት ሌሎች፣ የሚያተርፉት እነ ወርቄ፤ የሚዘሩት ሌሎች፣ የሚያፍሱት እነ ወርቄ፤ የሚያጠኑት ሌሎች፣ ፈተና የሚያልፉት እነ ወርቄ፤ የሚወዳደሩት ሌሎች፣ የሚያሸንፉት እነ ወርቄ፤ የሚጽፉት ሌሎች፣ የሚታተመው በነ ወርቄ ስም፤ የሚያጩት ሌሎች፣ የሚያገቡት እነ ወርቄ፤ የሚሮጡት ሌሎች፣ ሜዳልያ የሚወስዱት እነ ወርቄ፤ ማኅሌታውያኑ እና መክፈልተኞቹ ተላያዩኮ፡፡
የበሬን ምስጋና ወሰደው ፈረሱ
ከኋላ ተነሥቶ ከፊት በመድረሱ
ይባል የለ፡፡ በሬው ከጠዋት እስከ ማታ አርሶ አርሶ ደክሞት ቀስ ብሎ እያዘገመ ሲሄድ፣ ሲግጥ ያረፈደ ፈረስ ገሥግሦ ይደርስና ስለ እርሻው፣ ስለ ማሳው፣ ስንት ትልም እንደታረሰ፣ ምን እንደተዘራ፣ ምን እንደ ቀረ የሚያውቀውንም የማያውቀውንም እየጨማመረ፣ እያሣመረ፣ በል ሲለውምም አሂሂሂሂሂ በሚለው የፈረስ ሳቅ እያጀበ ዜናውን አዳርሶት ይጠብቀዋል፡፡
የዋሑ በሬ እያዘገመ ሲደርስ ፈረሱ ተመስግኖ፣ ወሬውም ቀዝቅዞ ይደርሳል፡፡ ከዚያ በኋላ ለርሱ ትኩረትም የሚሰጠው የለም፡፡ ከዚያ በኋላ የበሬው ድርሻ በረት ተኝቶ ራሱን እየነቀነቀ ማዘን ብቻ ይሆናል፡፡ ለዚህ ነው በሬ ሌሊት በተኛበት ቀንዱን ከግራ ቀኝ እያወዛወዘ አንገቱን ሲነቀንቅ የምናየው ይባላል፡፡ ምስጋናው ተወስዶበት፡፡ አይ በሬ፤ ስንት እንዳንተ ምስጋናው ተወስዶበት አንገቱን ሲነቀንቅ የሚያድር ሰው አለ መሰለህ፡፡
መምህር ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡
ReplyDeleteወርቅ በወርቅ ሆነናል በለኛ!
ጠቅላላ እኮ በቤተመንግስትም በቤተክህነትም ወርቅ ብቻ ነው፡፡
ተወድሶ በምድር ተከብሮ በሰዎች
ReplyDeleteአቦ ተብሎ በብዙዎች
ሲመዘን በፈጣሪ
ሲገመገም ምንም ሰሪ
ነኝና በጣም ምስኪን
የዘነጋሁ የሰማዩን
ከንቱነቱን እንድዘከር
ውዳሴውም እንደሚቀር
እንዳስተውል እንድሰበር
ጸልዩልኝ እንድመከር፡፡
Kale heyote yasemalen! Lebe Yesten!
ReplyDeleteአይ በሬ፤ ስንት እንዳንተ ምስጋናው ተወስዶበት አንገቱን ሲነቀንቅ የሚያድር ሰው አለ መሰለህ፡፡
ReplyDeleteዳኒ በጣም አመሰግናለው።
አንዳንድ ቦታ ከመጀመሪያው ጀምረን ግህዝ አይገባንም ላልን ሰዎች...ግን አሪፍ ነው በአውደ ንባቡ(ሲባል ሰምቼ ነው-contextual meaning) ለመረዳት እንድንሞክር ስላደረከን ለወደፊቱ እንድንሞክር ጭምር።
በድጋሚ አመሰግናለው
ዳኒ እግዚአብሔር ያክብርህ በጣም ጥሩ ምሳሌና እየሆነ ያለ ነገር ነው ከገባንና የምንማርበት ከሆነ
ReplyDeleteያበርታህ
yegermal beyebotaw new enda leka begname senbet temehert bete sente werku ale meselhe
ReplyDeleteEgziabehare lebe yestachew
Esayas
ReplyDeleteejig betam temechitognal.Egziabher yeagelgilot
zemenihin yebarkilih.
What an article!!!
ReplyDeleteIn all aspects, what block the smooth and fast motion of individuals is the presence of the so called "WORKE" just like unwanted friction. I do not know how and when these "WORKES" leave others alone so that they can do to the maximum of their potential and get what corresponds to their effort. In our country the presence and activities of "WORKES" is well known. That is why we have the following,
Ethiopia hagere mogn nesh telala
Yemotelish kerto ye GEDELESH BELA.
"WORKES" are eating and get admired on behalf of the hard working peoples.
Dn. Daniel May God BLESS you.
ማኅሌት እና መክፈልት ነገር ሲነሳ አንድ ቅኔ ትዝ አለኝ ... አባቴ ነው የነገረኝ/የራሱ ቅኔ ናት/።
ReplyDeleteምንት ይብልዑ ክዋክብት ካህናተ ሰማይ ዘደክሙ
ሥጋ ላህም እንተ ተጠብሃ ለስሙ
ለኩናይተ ሐጺን ነግድ ድኅረ ንስቲተ አጣሙ
ቅውማን ዘኮኑ ቅንዋት እስመ ኅቡረ ፈጸሙ።
ትርጉም
የደከሙ የሰማይ ካህናት /ክዋክብት/ ምን ይብሉ
ለስሙ የታረደውን ያንድ ላም ሥጋ
እንግዳ ለኾነ ለጎኑ ጦር ትንሽ ካቀምሱ በኋላ
ቋሚ የሆኑ ችንካሮች ተባብረው ጨርሰውታልና።
ታሪክ
ለደብሩ በዓለ ንግስ ዋዜማ የታረደውን ላም ሥጋ ለእንግዶችና ካህናት ትንሽ ካቀማመሱ በኋላ አለቀ...አለቀ ብለው አስተናጋጆቹ ለብቻቸው መብላታቸውን ሲሰማ በማግስቱ የበዓሉ ዕለት ይህን ቅኔ እንደተቀኘባቸው ነግሮኛል።
ምስጢሩ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ ሲል መሞቱን፥ በመስቀል ሳለም በጦር ጎኑን መወጋቱን እና እጅና እግሩን መቸንከሩን ይናገራል።
ግን እግዚአብሔር አኮ - ዋጋውን ያውቀዋል ።
ReplyDeleteአርሱ ክብር ሳይሆን - ዉርደት ይከፍለዋል ።
ምክንያቱም -----
ወርቄ እንደ ዲያብሎስ ነው ።
ሲፈጥሩ አንኩዋን ሳያይ -አኔ ፈጣሪ ነኝ ብሎ አንደዋሸቸው ።
በሉ ፀልዩለት - እግዚአብሔር ልብ ይስጠው ።
ከፍርድ ቀን በፊት - ተመለስ! ይበለው ።
አሜን
ዳኒ እግዛብሄር አብዝቶ ይባርክህ
ReplyDeleteይህ አስተማሪህ ጽሁፍህ የእያንዳችንን ልብ ሰብሮ በመግባት ማንነታችንንና ዙሪያችንን እንድፈትሽ ይረዳናል። ሁልግዜም ሳትታክት ልምድህንና እውቀትህ ልታካፍለን ቆርጠህ የተነሳህ ምርጥ የኢትዮጵያ ልጅ በመሆንህ እኮራብሃለሁ። በርታ !!!
እንድሪስ
አይ ጋሼ ወርቁ እኔ የሚያሳስበኝ የነፍስዎት ጉዳይ ነው፡፡
ReplyDeleteየት ይሆን መግቢያዋ ?
እኔን የሚገርመኝ ግን በራሳቸው መወሰን የሚችሉትና ሕሊናቸውን ሳይሸጡ መኖር የሚችሉት ትላልቆቹ ምሁራኑ አባቶቸች ከወርቄ ጋር እያወቁ እለት ዕለት አብረው መዋላቸውና ለምክርም እሱን መፈለጋቸው ነው!
ReplyDeleteየበሬን ምስጋና ወሰደው ፈረሱ
ReplyDeleteከኋላ ተነሥቶ ከፊት በመድረሱ
እውነተኛ ክርስቲያን ባልሰራው ስራ ቀርቶ በሰራው ስራ ሊመሰገን አይፈልግም፡፡
እግዚአብሔር ለሁላችንም አስተዋይ ልቦና ያድለን፡፡
የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመንህን ያብዛው፡፡
ካሳሁን
tewahido
ReplyDeletekalehiwot yasemah
የዋሑ በሬ እያዘገመ ሲደርስ ፈረሱ ተመስግኖ፣ ወሬውም ቀዝቅዞ ይደርሳል፡፡ ከዚያ በኋላ ለርሱ ትኩረትም የሚሰጠው የለም፡፡ ከዚያ በኋላ የበሬው ድርሻ በረት ተኝቶ ራሱን እየነቀነቀ ማዘን ብቻ ይሆናል፡፡ ለዚህ ነው በሬ ሌሊት በተኛበት ቀንዱን ከግራ ቀኝ እያወዛወዘ አንገቱን ሲነቀንቅ የምናየው ይባላል፡፡ ምስጋናው ተወስዶበት፡፡ አይ በሬ፤ ስንት እንዳንተ ምስጋናው ተወስዶበት አንገቱን ሲነቀንቅ የሚያድር ሰው አለ መሰለህ፡፡
ReplyDeletegudachinen ngirehenal lbuna Yseten ineji. Yetemaru Yetebaleneme bezuwoch Yaemero leboch hhonenal beye tenate(research paper)
ReplyDelete+++ Selam lehulach yehunena yetwdedk wendmach QHY lehulachn leb yesten enlalaen "Werke" Lematfat yemsemagn yegbrgab temhert lehzbach gena ke cheklantach besetan melkam new betlayem bezh ye technology zemn " ALEM WERKET behonachbet" mister betfaft yebretan endnhon esun tedgfen Werken enata erasachnen enaseda. Hailen yemiset yekidusan AMLAK Leuel E/abher bertatun lehulachn yadlen yesemanewn belbonachn yasadrlen! +++ Bekirstos Akbari betseboch ke toronto
ReplyDelete+++ temlesh metahu "ሳይማሩ ሲያስተምሩ፣ ሳይሠሩ ሲከበሩ ማን ይናገራቸዋል፡፡" ezech laye yesemrelgn ena band wekt bebtachn west bemdark yetselot merha geber laye and mendm yegsets astawegen Kale E/abherun tesch yemgebun negen lemazgajet sew yasamerwn lemakreb seuarat degagmo "MARTA MARTA MArta............." ale gen sem selalhon zem alku esu lekanse gebern new "ebaksh ehte hoye Maryam tenafkech ke Geta eger ser tekmch ena temari" esun yekoyen !!!!!!!!!!!! +++
ReplyDeleteደብረ ቁስቋም
ReplyDeleteወንድማችን ጥሩ እይታ ነው እውነት ነው በጣም ብዙ ወርቅ ቅብ ጌጣጌጦ ች መኖራቸው ይታወቃል ታድያ እነዚህ ነቸው ቤ/ክርስትያንዋን ስምዋን እያስጠፉ ያሉት ለሁሉም ልቡና ይስጣቸው.
OMG! Who would believe that I know few people exactly like WERKE. This is what I love about my Ethiopian Orthodox Religion; every aspect of human life is well documented. Plus, my TEWAHDO always has a great son like Daniel. I love you my brother. You do not know what this article means to me.
ReplyDeleteBelew , Calgary, Canada
+++
ReplyDeleteለካንስ ጽሑፍም እንደ ውኃ ጥም ይቆርጣል?! ጥም የሚቆርጥ ጽሑፍ ነው! ፀጋውን ያብዛልህ!
Geta yibarkih Dn Daniel. Enkuan worku Kesemu belto Gebagn.Bithu worku nachew ahun yalun.
ReplyDeleteWorke lela sew aymeslegnim...keyandandachin wust binfelig yemanataw maninet new...minalbat andand sewoch lay siga nesto eyayenew yihon yihon???
ReplyDeletetihut lib yadlen.
Egziabher yistilign
ውድ ዲያቆን ዳንኤል እጅግ ብዙ ብዙ ወርቄዎች በየመስሪያቤቱ በየቤተክርስቲያኑ በየሃገረስብከቱ በጠቅላይ ቤተክህነት ውስጥ ይኖራሉ አሉም። እባክህ ወርቄዎችን እንዴት አድርጎ ማስወገድ እንደሚቻልና እውነተኛዎቹን የሃይማኖት አባቶችን ባለሙያዎችን በቦታቸው መምደብ የሚቻልበትን መንገድ አመላክተን?
ReplyDeleteፍሬሰንበት
እግዚአብሔር ስራህንና አገልግሎትህን ይባርክ፡፡
ReplyDeleteወርቄዎችን እግዚአብሔር ከቤተ ክርስቲያናችን ያስወግልን፡፡
ወልደ ዮሐንስ
ReplyDeleteመምህር!... ምነው በዕለተ ረቡዕ አንጀቴን ቅቤ ውስጥ ነከርከው? ይህቺ ጦማርህ የልብ አድርስ ልብ መልስ ናትና ለዛሬው ‹ወርቃማ› ትውልድ ሁሉ ትድረስ፡፡
እግዚአብሔር እድሜህን ያርዝምልን
KHY
ReplyDeleteሲሠራ አይታይም፤ ሲሸለም ግን ይታያል፤ ሲደክም አይታይም፣ ሲመሰገን ግን ይገኛል፤ ሲለፋ አይታይም፤ ሲደነቅ ግን ይታያል፤ በስብሰባው ሰዓት የለም፤ መግለጫ ግን ይሰጣል፤ ከምርምሩ የለበትም፤ ምርምሩ ሲታተም ግን ስሙ ይጠቀሳል፡፡ የመስክ ሥራው ላይ የለም፤ ሪፖርቱ ውስጥ ግን ይገባል፡፡ የመሥሪያ ቤቱን ሥራ አያውቀውም፣ ስለ መሥሪያ ቤቱ ግን የሚጠየቀው እርሱ ነው፡፡
ReplyDeleteውድ ዳን
ReplyDelete**ጥሩ ለሰራ የሚያሸልም ላልሰራ ደግሞ የምያስወቅስ አሰራር ከሌለ
**ሚዛናዊ የ መገናኛ ብዙሃን
**ህሊና አና አግዝያብሔርን የሚፈሩ የ ሃይማኖት አና ማህበረሰብ ተቁአማት
ይሄንንም ከ አራሳችን አልፈን ለ ሚመጣው ትውልድ ማስተላለፍ ካልቻልን
ወርቁ አሁንም አለ ወድፊትም ብዙ ወርቁዎች ሆኖ ይመጣል ።
Txs for this interesting article!
ReplyDeleteSelam brother: KHY, Amen. It is very live and heart touching great article. I work with people from many countries and saw the same pattern like "Worke". This one is a modern WORKE - he can lie and also do a lobbying alot. I did the job but Worke told first and when we sit all together I get ashamed to say it again. WORKIE lies a lot, confuses people a lot ... So, how could we handle WORKE apart from challenging infront of people?, ...
ReplyDeleteCould you please add your comments how to manage "Worke"?
God bless you and your family.
የበሬው እና የፈረሱ ምሳሌ ደስ ይላል::
ReplyDeleteምስጋናችን ይድረስህ ወንድም ዲ/ን ዳናኤል
D/NDANE yageleglot zemenehene ybarklehe
ReplyDeletekale hiwot yasemalgne
ReplyDeleteOMG DANY I LIKE IT THIS INTERSTING
ReplyDeleteANY WEY BERTA Z CHICAGO
ATO AND W/RO WERKE ARE TOO MANY AND PEOPLE KNOWINGLY,GIVE THEM ALL THE POSSIBLE SPACE! WHO DARES TO TO SAY NO! TO THE WERKEISM IDEOLOGY?
ReplyDeleteእግዚአብሔር አምላካችን እንደነ ወርቄ ከመሆን ያድነን ከሆንም መውጫውን ያብጅልን
ReplyDeleteአብዛኞቻችሁ ወርቄን በመርገምና በመኮነን ተጠምዳችሁ ወርቄ ያለውን የክፋት ዐቅም መመልከት የቻላችሁ አልመሰለኝም፡፡ በእኔ አመለካከት ወርቄ የሚከተሉት ታላላቅ ዐቅሞች አሉት፡-
ReplyDeleteሀ. ከፊቱ ታቁሮ ያገኘውን ነገር ሁሉ ለራሱ በሚመቸው መንገድ ማፍሰስ ይችላል፡፡
ለ. የሊቃውንቱና የሕዝቡ ደካማ ጎኖች ምን እንደሆኑ ያውቃል፡፡
ሊቃውንቱ ከመኮፈስ ወይም ከፍርኃት የተነሣ አይናገሩም፡፡ ሕዝቡም ከአጉል ትሕትና ወይም ከምንግዴነት የተነሣ አይጠይቅም፡፡ ሁሉም እንደ በሬው በረቱ ውስጥ ራሱን ከመነቅነቅ ውጪ የዝምታ እስረኛ ነው፡፡
ከዚህ በላይ ተቁቶ ታቁሮ መገኘት የት ይገኝ ኖሯል?!
ሐ. ሕዝቡን በዝርግድ ቁመናውና በስም አልባ የታይታ እንቅስቃሴዎቹ መማረክ ይችላል፡፡
መ. እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው ችሎታዎች ስላሉት ደግሞ በብልጣ ብልጥነቱ ሕዝቡን እንደ ሰም አቅልጦ እንደ ገል ቀጥቅጦ መግዛት ይችላል፡፡
አትሳሳቱ! በዚህ ዘመን ያለው ወርቄ ትንሽ የብልጥነት ዕድገት ስላሳየ ተከታዮቹን አሰተባብሮ ሊቃውንቱን ገደል ሊያስወረውራቸውም ይችላል፡፡ ወርቄን መንቀል የሚሻ ሁሉ ሥሮቹ የተተከሉበትን የሕዝቡን አላዋቂነት መዘንጋት የለበትም፡፡ መሬቱን ካሳጣኸው ሥሩም ዛፉም መድረቁ አይቀርም፡፡
Dani 10Q This is a nice post. In my Opinion እነወርቄ በተለይ በሀገራችን እየተሞገሱ እየተመሠከረላቸውና ክብር እያገኙ ያለበት፤ ሌሎች ራሳቸውን በዕውቀት ያበለጸጉትና ታታሪ ሠራተኞች ግን በነወርቄ እየተበደሉ የሚገኙበት ሁኔታ ይታያል፡፡ ለምሳሌ በቤተክርስቲያናችን ስንመለከት የቤተክርስቲያንን ትምህርት ያዳበሩና በሥርዓት ያጠናቀቁት በሙዳየ ምጽዋት፣ በጸበል ቤትና በጥበቃ ሥራ ሲሰማሩና ለብዙ ጊዜያት ደጅ እየጠኑ ከቻሉ ዳጎስ ያለ ገንዘብ ለነወርቄ ሰጥተው አላደርግም ካሉ በነወርቄ እየተረገጡ የሚሰቃዩበት ሁኔታ እየባሰ የመጣ ሲሆን እነወርቄ ግን የክብር ቦታ እያገኙ በየሄዱበት ቦታ በየቆሙበት መድረክ መስለው ምእመናን የሚያሳዝኑ በአስተዳደር ሲገቡ አገልጋዮችን እያጣሉና እያባሉ ራሳቸውን ግን ለክብር የሚያጩ አለቆቻቸውም የነሱ መሳይ ናቸውና በነሱ እየተወደሱና እየተሞገሱ የሚኖሩበት መድረክ መሆኑ አሳዛኝ ክስተት ነው፡፡ እኔ በምሠራበት መ/ቤት አካባቢም ቢሆን ወርቄዎች ሲሠሩ የማይታዩ ግን ዕድገት፣ ሽልማት ሲመጣ ማንም የማይቀድማቸው፣ ስልጣን የሚፈልጋቸውና የTransformation በር ለነሱ ብቻ የተከፈተ እስኪመስል እነሱ ብቻ ተመርጠው ልዩ የደሞዝ ዕርከን ቢሠራላቸውም የተፈለገው transformation መተግበር ባለመቻሉ ይኸው አሁን ማኔጅመንቱን እያኮናተርን እንገኛለን፡፡ ለነገሩ አሁንም በተመረጠው ማኔጅመንት ሥር የወደፊት ተረካቢ ተብለው እየተመረጡ የሚገኙት ራሳቸው መሆኑና ለሀገር ዕድገት፣ ለለውጥ ተቆርቋሪና ለውጥ አምጪ ተብለው በየመድረኩ እየተወደሱ መሆኑ የወደፊት የማደግ ተስፋችንን እያደበዘዙት ይገኛሉ፡፡ ወሬን በማሳበቅ፣ ነገርን በመጎንጎን ክብር እንደሚገኝ ታታሪ ሠራተኛ ግን አስታዋሽ እንደማያገኝ በግልጽ እየመሰከሩልን ይገኛሉ፡፡ እንዲህ ባለ ሁኔታ ሀገር እንዴት ትደግ? ከእነዚህ ጋር መሥራት አይደለም ለጥቂት ጊዜያት አብሮ መኖር ቋቅ ያሰኛል፡፡ እንዲህ ሆኖ የኛ Life expectancy እንዴት ከ40 ይዝለል? እነሱ Confidence ስለሌላቸው ምን ይመጣ ይሆን በማለት ሲጨነቁ ሌላውም ከእነሱ ለመገላገል (ባይቻልም) ሲጥር እነሱም አይኖሩ ሌላውም አንኖርም፡፡
ReplyDeleteእኛ ግን ጸግወኒ ማእጾ አፍ እንተ ይእቲ አርምሞ ለትእግስትከ ከመ አእምር አቅሞ የሚለውን ታላቁን ጸሎት ልንጸልየውና በሥርዓትና በአግባብ ለሌላው መጠቋቆሚያ ላለመሆን በመጠንቀቅ ልንኖር ይገባል፡፡ ከጌታችንና ከአባቶቻችን የተማርነው፤ እንዲሁም ወርቄን በቅኔ የሚዘልፉ አባቶች የሚያስተምሩን ይህንኑ ነውና፡፡ ለሁሉም አምላካችን ልቡና ይስጠን፡፡ እኛ ግን ጸግወኒ ማእጾ አፍ እንተ ይእቲ አርምሞ ለትእግስትከ ከመ አእምር አቅሞ የሚለውን ታላቁን ጸሎት ልንጸልየውና በሥርዓትና በአግባብ ለሌላው መጠቋቆሚያ ላለመሆን በመጠንቀቅ ልንኖር ይገባል፡፡ ከጌታችንና ከአባቶቻችን የተማርነው፤ እንዲሁም ወርቄን በቅኔ የሚዘልፉ አባቶች የሚያስተምሩን ይህንኑ ነውና፡፡ ለሁሉም አምላካችን ልቡና ይስጠን፡፡
I identified my place in this fantastic classification.Thank you DDK!!
ReplyDeleteQale Hiwoten yasemalen !!!!
ReplyDeleteDani bewenet leantem abezeto tegawen yabezaleh ye agelegelot zemenhen yarezemeleh
legam letadamiwoch hulu masetewalun yadelen ye meleketu tetekamiwoch yaderegen !!!!!!!!
enem ende berew rasen enekenekalew
d/n Daniel grum dink timihirt ena agelaleste egiziyabihere ageliglotikin yibark.
ReplyDeleteDani this is our country a commen problem.God Bless you.
ReplyDeleteWhat a touchy story! Dn. Daniel, no words to thank you for this an your overall efforts for the betterment of social and religious life in Ethiopia.
ReplyDeleteWe have a number of 'Workes' in many fields of our life....there are even times when I found some practices of mine (especially as perceived by others)to be similar with that of Worke! Ayiiiii...
God Bless You!
Esdros Zelideta Gondar
God bless you
ReplyDeleteaye werke! werkewoch asteyayet betsifulh degmo tiru neber lemanignawim ene begile 3 awra werkewochin awkaleh kkkkkkk
ReplyDelete