Monday, October 11, 2010

አንድነት ይቅርብን

ብዙ ጊዜ ለኢትዮጵያውያን ችግራችን አንድ ያለመሆን ነው፤ ልዩነቶቻችንን ትተን አንድ እንሁን፤ አንድነት ኃይል ነው ወዘተ እያልን ጩኸናል፤ አስተምረናል፤ ጽፈናል፤ አንብበናል፤ አዚመናል፤ ሰብከናል፡፡ አሁን አሁን ግን ሳስበው እንዲያውም ችግራችን አንድ ከመሆን የመጣ ነው የሚመስለኝ፡፡ እንዲያውም ሀገራችንን አሁን ለደረሰችበት ውድቀት የዳረጋት አንድ መሆናችን ነው፡፡ ደግሞ መች ተለያይተን እናውቃለን? መች ልዩነት አለ በመካከላችን? ሁላችንም እንደ አህያ ጆሮ እንደ ጦር ጉሮሮ አንድ አይደለን እንዴ፡፡

ለመሆኑ እኛ ኢትዮጵያውያን የተለያየነው በምን በምንድን ነው? በዘር? በሃይማኖት? በፖለቲካ? በአመለካከት? በምንም፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ከጥንት ጀምሮ የሚሠራው ፊልም አንድ ዓይነት ነው፡፡ ተዋንያኑ ግን በየጊዜው ይለያያሉ፡፡ ፊልሙ የሚሠራበት ቦታ እና ቋንቋ ግን ይለያያል፡፡ አንዳንዶቹ ያንኑ ፊልም በሚገባ ይሠሩታል፤ ይዋጣላቸዋል፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ፊልሙን በበቂ ሁኔታ አይተውኑትም፡፡ በዚያም ተባለ በዚህ ግን በፊልሙ አንድ ነን፡፡ በፊልሙ ውስጥ መገዳደል፤ መጨራረስ፣ አምባገነንነት፣ እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን፣ጠባብነት፣ ጎጠኛነት ወዘተ አሉበት፡፡

ፊልሙ በአማርኛም ተሠራ በኦሮምኛ፤ በትግርኛም ተሠራ በሶማልኛ፤ በአፋርኛም ተሠራ በወላይትኛ፣ በሐረሪኛም ተሠራ በሲዳምኛ የፊልሙ ስክሪፕት ያው ነው፡፡ የማጀቢያ ዜማውም «ኧረ ጎራው ኧረ ደኑ፤ ግደል ግደል አለኝ፤ የሚቃወምህን አጥፋው አጥፋው አለኝ፤ ካንተ ሌላ ሃሳብ አትስማ አትስማ አለኝ´፤ የሚለው የጥንቱ ዘፈን ነው፡፡

ታድያ ኢትዮጵያውያን አንድ ዓይነት ፊልም እየሠሩ እንዴት ነው የሚለያዩት? ኧረ አንድ ናቸው፡፡

ለመሆኑ የዘር ልዩነት አለን እንዴ? ሁላችንም ከምናውቃት ቋንቋ በላይ መስማት አንፈልግም፤ ስለሌላው ዘር የሚያንቋሽሹ ቃላት በሁላችንም መዝገበ ቃላት ውስጥ አሉ፤ የተናቁ እና የተዋረዱ ማኅበረሰቦች በየዘራችን አሉ፤ ገድለን ጀግና የምንሆንባቸው ማኅበረሰቦች በየጎሳችን አሉ፤ ሁላችንም ጎሳዎቻችንን ብቻ የሚወክሉ ፓርቲዎች አሉን፤ ሁላችንም ጎሳዎቻችንን ነጻ ለማውጣት እንታገላለን፤ ሁላችንም ተጨቁነናል፤ ታድያ አሁን እኛ በዘር ተለያይተናል? ምኑ ላይ ነው ልዩነታችን? አንድ ዘር እኮ ነን፡፡

አሁን እኛ በፖለቲካ ተለያይተናል? ለመሆኑ ምንድን ነው የለያየን? ሁላችንም «ሌላ ድምፅ አልሰማም ከንግዲህ በኋላ´ አይደል እንዴ የምንለው፡፡ የገዥ ፓርቲ መሪዎችም አይለወጡም፤ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችም አይቀየሩም፤ ፖሊት ቢሮ፤ ማዕከላዊ ኮሚቴ፤ ጠቅላላ ጉባኤ፤ በሁሉም ዘንድ አሉ፤ ለምሳሌ በቅርቡ በአምስተርዳም የአቶ መለስ ዜናዊ ምስል ያለበትን ቲሸርት የለበሰ ሰው በኢትዮጵያውያን መደብ ደቡ እንደ ትልቅ የድል ዜና ሲነገር ነበር፡፡ ታድያ ገዥው ፓርቲ እኛን ከዚህ እና ከዚያ ከለከለን ብሎ መናገር እንዴት ይቻላል? ልዩነታችንስ ከምኑ ላይ ነው? እኔ ልሙት አንድ ነን፡፡

እዚያ ኢሳት ተከለከለ ብለን ሰልፍ እንወጣለን፤ እዚህ የእነ እገሌን ሬዲዮ አትስማ፤ ቴሌቭዥናቸውን አትይ፣ እንጀራቸውን አትግዛ እንላለን፤ እዚያ 99 በመቶ የሚያሸንፍ አለ፤ እዚህም 99 በመቶ የሚያሸንፍ አለ፡፡ ሁሉም ተቃራኒ ሳይሆን ጠላት አለው፡፡ ሁሉም ጠላቱን ለማውደም ተነሥቷል፡፡ አሁንም «እገሌ ያሸንፋል´ ብለን እንፎክራለን፡፡ ታድያ በምንድን ነው ልዩነታችን? ኧረ አንድ ነን፡፡

ማነው ለመሆኑ ይኼ ኢትዮጵያውያን ተለያይተዋል እያለ የሚያሟርትብን፡፡ ባያውቀን ነው እንጂ እኛስ ተለያይተን አናውቅም፡፡ አሁን እኛ ተለያይተናል? ስንት ሰው አለ እባካችሁ ያላየውን የሚያወራ፡፡

በውጭ ያሉት አብያተ ክርስቲያናት ገለልተኛ፣ ስደተኛ፣ የሀገር ቤት እያሉ ተለያይተዋል ብሎ የሚያማን ሰው ምን የተረገመ ነው፡፡ አሁን በኛ መካከል እንዲህ ያለ ልዩነት አለ? ሁሉም ጳጳስ ይፈልጋሉ፤ ሁሉም ግን በጳጳስ መታዘዝ አይፈልጉም፡፡ ሁሉም በስም የተለያዩ መስለው ለመንግሥት ባስገቡት ደንብ ግን አንድ ናቸው፡፡ ሁሉም የተለያየ ስም ነገር ግን አንድ ዓይነት ግብር ያለው ቦርድ አላቸው፡፡ ሁሉም ዋናው ገቢው ነው ብለው ያምናሉ፡፡ ሁሉም ጋ የሚፈልጡ የሚቆርጡ ወይዛዝርት፤ የሚያዝዙ የሚናዝዙ መኳንንት፤ የሚከታተሉ የሚቆጣጠሩ ፖለቲከኞች፤ የሚፈሩ፣ ለሥጋ የሚያድሩ አገልጋዮች፤ አሉ፡፡ ታድያ በምን ተለያይተን ነው ተለያዩ እያሉ የሚያሟርቱብን፡፡

ለእነዚህ ገብርኤል የጎንደር ነው፤ ለእነዚያ አቡነ አረጋዊ የትግሬ ናቸው፤ ለእነዚህ ማርያም የሸዋ ናት፤ ለእነዚያ ደግሞ ሥላሴ የጎጃም ናቸው፤ ለወዲህኞቹ ሚካኤል የደቡብ ነው፤ ታቦቶቻችን ሁሉ ዘር እና ጎጥ አላቸው፡፡ ታድያ በዚህ ሁሉ አንድ ሆነን ሳለን እንዴት ተለያይተዋል እንባላለን፡፡ ይህንን የሚሉን የኛን ክፉ የሚመኙ ብቻ ናቸው፡፡

ፕሮቴስታንቶቹስ ቢሆኑ እዚህ ጌታ የወለጋ ነው፤ እዚያ የአማራ ነው፤ ወዲያ የትግራይ ነው፤ እልፍ ሲል የወላይታ ነው፤ ሲመለስ የሲዳማ ነው፤ ታድያ ሁላችንም ቢሆን ጌታን እንደ የብሔረሰባችን ተቀብለነዋል፤ ደግሞም ሁላችንም በብሔረሰባችን ቋንቋ ብቻ በመዘመር እና በመስበክ እናምናለን፤ ሁላችንም ጌታ ከኛ ቋንቋ ውጭ አይሰማም ብለን እናምናለን፤ ሁላችንም ፓስተሮቻችን ሲጣሉ ለሁለት ተከፍሎ የየራሳቸው ቸርች በመመሥረት እናምናለን፤ ሁላችንም ሌላውን ወንጌል ያልገባው መሆኑን አጥብቀን እንመሰክራለን፤ ታድያ ይህንን የመሰለ አንድነት እያለን እንዴት ተለያይተዋል እንባላለን፡፡

ሙስሊሞችና ክርስቲያኖችስ ቢሆኑ መች ተለያዩ፡፡ ይኼ የጠላት ወሬ ነው፡፡ እነዚያ ሀገሪቱን በመስጊድ በማጥለቅለቅ፤ እነዚህም በቤተ ክርስቲያን በማጥለቅለቅ ያምናሉ፡፡ እነዚያም በኃይለኛ ማይክራፎን አዛኑን በመልቀቅ፣ እነዚህም ቅዳሴውን በኃይለኛ ማይክራፎን በማሰማት ያምናሉ፡፡ ሁለቱም ከመወያየት ይልቅ መፋጠጥን፣ መልስ መሰጣጣትን ይመርጣሉ፡፡ ሁለቱም ከጥራት ይልቅ ለቁጥር ይጨነቃሉ፡፡ ሁለቱም ለአምላካቸው በመታየት ሳይሆን ለሕዝብ በመታየት ይስማማሉ፡፡ ታድያ ይህንን የመሰለ አንድነት እያለ ምኑን ተለያየነው፡፡

ምሁሮቻችን ያላቸው አንድነት የሚገርም ነው፡፡ ሕዝብ በሚያውቀው ቋንቋ ባለመጻፍ፤ በውጭ ሀገር እንጂ በሀገር ውስጥ የጥናት ወረቀት ባለማሳተም፤ በአካዳሚያዊ ክበቡ ውስጥ እንጂ በሕዝቡ ዘንድ ባለመታወቅ፤ በወረቀት እንጂ በሥራ ባለማመን፤ ከአባትነት ይልቅ በገዥነት መንፈስ በመመራት፤ ከመመሰጋገን ይልቅ በመተቻቸት በማመን፤ ምሁራዊ ዘረኛነትን በማስፋፋት፤ ምሁሮቻችን አንድ አይደሉ እንዴ፡፡ ማን ነው በመካከላቸው መለያየት አለ እያለ ያላየውን የሚያወራ፡፡ ወሬኛ፡፡

አንድነት ሰለቸን፡፡ እስኪ ደግሞ እንለያይ፡፡ የተለያየ አመለካከት፣ የዕውቀት ደረጃ፤ የአሠራር መንገድ፤ የችግር አፈታት መንገድ፤ የዕድገት መንገድ፤ የመረጃ መንገድ እስኪ ይኑረን፡፡ በቋንቋ፣ በባህል፣ በአመጋገብ ብቻ ሳይሆን በሌላውም እስኪ እንለያይ፡፡ የተለያየ የፊልም ስክሪፕት፣ የተለያዩ ተዋንያን፣ የተለየ የፊልም ጭብጥ፣ የተለየ እመርታ ያለው ፊልም እስኪ ይኑረን፡፡ አንድ ዓይነት ፊልም ሰለቸን፡፡

እስኪ የተለየ ልቦለድ እንጻፍ፡፡ መቼት፣ ትረካ፣ ግጭት፣ ዐጽመ ታሪክ፣ አላባውያን፣ ገጸ ባሕርያት ከሚለው የተለየ የለም እንዴ? እስኪ እንለያይ እነዚህ የሌሉት ወይንም ደግሞ ሌሎች ነገሮች ያሉት ልቦለድ መጻፍ አይቻልም እንዴ?

አንድነት አልጠቀመንም፡፡ ዓለም የተጠቀመው ተለያይቶ ነው፡፡ ፓርላማው ይለያይ፤ ካቢኔው ይለያይ፤ሲኖዶሶ ይለያይ፤ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቱ ይለያይ፤ የወጣት፣ የሴት ማኅበራቱ ይለያዩ፡፡ የሞያ ማኅበራቱ ይለያዩ፡፡ በውስጣቸው ያሉ አባላቱ የተለያየ ሃሳብ፣ አመለካከት፣ አቅጣጫ፣ የዕውቀት ስብጥር፣ ዳራ፣ ይኑራቸው፡፡ይፋጩ፡፡ ተፋጭተው ተፋጭተው እንደ ብረት ተስለው የሰላ ሃሳብ ያውጡ፡፡ ምሁራኑም ይለያዩ ስለ አንድ ጉዳይ ከተለያየ አቅጣጫ ይናገሩ፣ ይጻፉ፣ ይተቹ፣ ያበጥሩ፣ ያንጠርጥሩ፡፡ አዳዲስ አካሄድ ያሳዩ፡፡ አይስማሙ፤ መስማማት የግድ አይጠበቅባቸውም፡፡ እንዲያውም ይለያዩ፡፡ የተለያየ መረጃ፣ የተለያየ ዘዴ፣ የተለያየ ግኝት ነው የምንፈልገው፡፡

የእምነት ተቋማቱም ይለያዩ፡፡ በአሠራር፣ በችግር አፈታት፣ በማስተማርያ መንገድ፣ በምእመናን አያያዝ፣ ለሀገር በሚያበረክቱት አስተዋጽዖ፤ በአሠራር ማሻሻያ፣ በመሪዎች አመራረጥ፣ ሙስናን እና ብኩንነትን በመዋጊያ መንገድ፣ በግልጽነት እና ተጠያቂነት ማስፈኛ መንገዶች ይለያዩ፡፡ ይበላለጡ፤ ይቀዳደሙ፡፡ ያን ጊዜ አንዱ ከሌላው ሃይማኖት ባይማርም አሠራር ይማራል፤ ጥበብ ይማራል፡፡ እንደ ኮካ ኮላ ጠርሙስ አንድ ከመሆን አምላክ ይታደጋቸው፡፡

እስካሁን አንድ ሆነን አይተነዋል፡፡ እስኪ ደግሞ ተለያይተን እንሞክረው፡፡ አንድነት ኃይል ነው የሚለው ይቀየርና ልዩነት ኃይል ነው ብለን እንነሣ፡፡

ሎስ አንጀለስ፣ ዩ ኤስ ኤ


50 comments:

 1. የእግዚአብሔርን አንድነት ለተቀበለ፣ አንድ አባት አዳም፣ አንድ እናት እንዳስገኙን የሚያምን፣ ከሆድ በላይ የመኖር ትርጓሜ፣ ከምድር በላይ ሀገር፣ ከገንዘብ በላይ ፀጋ መኖሩን በእምነት የሚመለከት ሁሉ የአንድነት ትርጉሙ ይገባዋል፡፡ የመለያየት መሠረቱ ሆድና ሽሚያ ሲሆን ይህም የሚመራው ሕሊናቸውን በሆድ የተኩ በክፋት ብልጥ የሆኑ ጥቂቶችና ከጥቂትነታቸው በተቃራኒ የጠመንጃ፣ የመደራጀት፣ የሚዲያ ባለቤትነት፣ የልብ ጭካኔ ባለቤት የሆኑ ሰዎች ናቸው፡፡ ብዙሀኑ 'ጎጋ' ነው፡፡ ልባስ ነው፡፡

  ReplyDelete
 2. hi Dn Daniel. it good how ever hard to understand easly what the central point of your article is. before years I read a quate like "discover what makes a difference".This is a quate that lets us to think that what is the difference that makes us to object others.And also lets us to think to support, to follow and to make others follow us and convince. u know very well that unity is power. it is good to fight our common enemy. but understanding why others struggle for and to achieve what goal should be our start to object their stand. after knowing what others want to do we can follow or make them follow us. people should have an opportunity to come with their contribution to the society and show their result practically. Individuals will able to create more when they are together and develop discussion,but shall not progress in hte same line parallel at the same level. Think and do new thing from time to time, develop their respective work and profession is required as time and exprience goes. thank u Danny.

  ReplyDelete
 3. +++
  በወለላይቱ ደግሜ ደግሜ ባነበዉ አልገባኝም:: የሚያስረዳኝም ባለሙያ አጣሁ የሳይንስ ባለሙያ በመሆኔ ነው መሰል:: አንድ በሉኝ? ዲ/ን ዳንኤል ልዑል እግዚአብሔር ከነቤተሰቦችህ ይጠብቅህ::

  ReplyDelete
 4. yice neger alamarechignme,mecereshawa min yihon?

  ReplyDelete
 5. እኔ እና ወንድሜ


  የአባቴ እና የአባቱ
  የጥንስሳቸው መሰረቱ
  ሐረጋቸው ሲመነዘር
  አንድ ተብሎ ሲቆጠር
  ሀሳባቸውና ፈቃዳቸው
  የአኗኗር ቅኝታቸው
  ለየቅል የተገነባ
  ላይገናኝ ቃል የተጋባ

  ነበሩ...አሉ ሁለቱም
  የተራራቁ በጣሙን

  ወንዘኞችና ጎጠኞች
  ለብቻየ የሚሉ ምቀኞች
  ልዩነትን እንደ ልዩነት
  ያልታደሉ ለመመልከት
  ያልነበረውን አንድነት
  ያልነበረውን ሕብረት
  እንደነበረ የሰበኩ

  ነበሩ...ይላሉ የታዘቡ
  የትዝብት መጽሐፋቸውን ሲያነቡ


  ታዲያ...የአያቴ እና አያቱ
  ሆኖ ውርስ ለአባቴ እና ለአባቱ
  ሀሳብ ለበላት እማማችን
  ኑሮ ላደከማት እናታችን
  ሌላ ሰቀቀን ሆነባት
  የማይሽር የጎን ውጋት

  የኔ እና የወንድሜ እማማ
  የማይቻለውን ችላ ተቀምጣ
  ውጋቷን እያስታመመች አዘዘችን
  የአባቶቻችሁን ቁርሾ እርሱት አለችን።

  እኔ እና ወንድሜ በፋንታችን
  የእምዬን መልዕክት አሽቀንጥረን
  ላንተማመን ቃል ገባንላት
  የአባቴን እና የአባቱን ጎጠኝነት
  በዘመነ ስልት አዜምንላት

  አሁንም እናታቸችን ትጮሃለች
  በደከመ ድምፅ ታቃትታለች
  ባባቶቻችሁ ደም መቃባት
  አንድ ላትሆኑ መለያየት
  አቁሙ!!! በቃችሁ ትለናለች።

  አሁንም ደግማ ደጋግማ
  እራሷን ደጋግፋ ቆማ

  " አባቶቻችን ለራሳቸው
  በራሳቸው መንገድ ሄደው
  ይሆናል...የማይሆነውን አድርገው።
  እኛ በ'ነርሱ ቅዠት
  ዳግም ላንጓዝ ወደ ጥፋት
  በ'ናታችን ፊት ቃል ገባን
  ብላችሁ በይፋ ተማማልን
  ህመሜን ውጋቴን ተረዱልኝ
  መሳቀቅሽ ይብቃ በሉኝ
  ያኔ...
  ያኔ ውጋቴን እረሳለሁ
  ስለፍቅር እና ሰላማችሁ
  አብሬያችሁ እዘምራለሁ "

  እያለች...
  አምርራ ትነግረናለች።

  ታዲያ...እኔ እና ወንድሜ አሁን
  በራስ ፈቃድ መጓዝን
  መደማማቱን ትተን
  ብንሰማት እናታችንን
  የቀደመውን የኃጢአት ውል
  ጃ...ይሰርያል።

  በመጨረሻው እኔ ገባኝ
  የእናቴ ጥሪ ተሰማኝ
  ወንድሜስ? ይሰማው ይሆን? ? ?
  በተሰማው...


  እኔና አቤሎ እንዳሰብነው
  እኔ እንደጻፍኩት

  ReplyDelete
 6. Please Dn

  The Time is for "Drama life "

  One of

  ReplyDelete
 7. እውነት ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ሁል ጊዜ አንዱ ሲደገፍ ስንደግፍ፡ አንዱ ሲቃወም ስንቃወም ነው ዘመናት ያለፉት፡፡ ሁሉም የየራሱን ሃሳብ ቢያፈልቅና የሌላውንም በመልካም ቢቀበል የተሻለ ውጤት ማግኘት በተቻለ ነበር፡፡ ለሁሉም አምላክ ይርዳን፡፡
  ላንተም ረጅም እድሜ ያድልልን፡፡

  ReplyDelete
 8. 4me its complicated more or less i didn`t understand the content

  ReplyDelete
 9. Dear Dn Daniel,

  When ever you write about politicians you just squeeze all the opposition camp as one and equate that with the ruling party. In my opinion that is not a right understanding. There are few political parties that are trying things differently and to the best of their potential and have a clear objective and direction. The first mistake is to just consider all the opposition parties as one. Secondly you equate them with the ruling party which is really a murderer and enemy of the country.

  ReplyDelete
 10. የማይበላ እንዳያስበላ ያብላላOctober 12, 2010 at 9:59 AM

  የኔ ቢጤ ሞኞች ሲያዋቅጧቸው
  ድብልቁ ሁሉ ጠጅ ይሆን መስልዋቸው
  ሁሉን ሲበርዙት ለዚያ ድግሳቸው
  ከድፍርሱ እንለይ ይቅር አምቡላቸው

  ReplyDelete
 11. Dear Dn Daniel,

  This article is not smell good. The idea looks here and there. What you really want to say? Any way you waste some time for it...

  ReplyDelete
 12. Thank you Dani, I understand ur thought. It is to teach not to repeat once mistake or don't be victim for guilties you claim some body for, rather do it differently. it is known that what we oppose is some thing that we think is not good in direction, management,... still we practice the same thing. We don't give love and respect and try to win whom we oppose, we oppose the person but not his idea and hence go to kill him. Had we oppose the negative thinking of a person we would try to lead him to think in a positively by being example for him thinking positively about him and else one. If we are a negative thinker like him what is the difference. The Holy Bible says ክፉን በበጎ ተቃወመው እንጂ በክፉ አትቃወም :: I think this is the central idea of Dani.

  Thank you Dani

  ReplyDelete
 13. Wow!!! very interesting article presented in an interesting way.Even though,I myself read it for myself, it seems as if Dn. Daniel was reading it for me (like live transmission). Besides, the theme of the article is clear and easily understandable (for me). It has addressed what is actually there in our country.
  May God bless u Dani.

  ReplyDelete
 14. Dani lehulum asetewaye lebona yesetene amen!

  ReplyDelete
 15. በየትኛው ዘይቤ ነው የተጻፈው? 'በአያዋ' ነው?
  እንደተረዳሁት፡-
  .ሲገለበጥ፡"ለምን ለዩነታችን አራንባ እና ቆቦ ሆነ?"የሚል ይመስላል
  ."የሓሳብ ልዩነትን እናክብር፣እናድንቅ" ለማለትም ይመስላል

  ."ሁላችንም ለውጥ እነፈልጋለን ግን በተለያየ አስተሳሰብ ሆኖም የልዩነት መቻቻል አለመኖሩን" ያስረዳል።

  ልክ ነኝ ዳኒ?
  ወተት ለምጄ ይህ ግን አጥንት ሆነብኝ።

  ReplyDelete
 16. ትክክለኛ ዕይታ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ በየስብሰባው ላይ ሳይቀር ስንቶቻችን ‹‹ እርሱ እንዳለው ››እያልን የሰውን ሃሳብ በመደጋገም አንድ መሆናችንን የምንገልጽ ስንቶቻችን ነን፡፡ መቼም ዳኒ አንድነት ይቅርብን ሲል በምን ሁኔታ እንደሆነ ስለገለጸው ለማብራራት ብሞክር በኮት ላይ ቲሸርት እንደመደረብ እንዳይቆጠርብኝ ስለፈራው ትቼዋለው፡፡
  ዳኒ እግዚአብሔር ጥበቡን ያብዛልህ፡፡

  ReplyDelete
 17. እግዚአብሄንር ይስጥህ ዲ/ን ዳንኤል:: በዚህ ጽሁፍህ ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ በተልይ ጭፍን ጥላቻ ዘረኝነትና ጥቅመኝነት በሁላችም ስር ውስጥ ያለ ነገር ነው:: በተለይ እዚ ሰሜን አሜሪካ የምንኖር ሰዎች እንኩዋን ከሃገሩ ህዝቦች መልካም ነገርን መማር አልቻልንም:: እኔ በምኖርበት ከተማ ብዙ ኢትዮጵያዊ የለም ያለነውም ግን ተከፋፍለናል አንድ የሚያደርገን ነገር ደግሞ ማንም ክፉም ቢሰራ ደግ በዘር ወይንም በጥቅም የሚያገናኘንን እንደግፋለን ሌላውን እንደጠላት አናያልን ይህ ነገር ደግሞ የሚለቀን እይነትም አይደለም::

  ReplyDelete
 18. Dear Dn Daniel,Thanks for your insightful article on our 'unity'. I think I understood what you want to say, the Gold and Wax of the article. Accordingly I beg to differ from you on one or two point(S) you raised. The first is as my brother Tesfa said it well, the dicothomy between the opposition and the rulling party. In my personal opinion it seems you always prefer the safest ground by equating everybody with everybody else. Some people might think this is a balanced approach, but it is indeed unanbalanced approach. I strongly believe that every body has to be judged by his/her merit.

  The other is about generalization, generalizesd idea about the diaspora (even more generalization about the Church in diaspora).As the saying has it " every generalization is dangerous, even this one".

  ReplyDelete
 19. Ante gudena Dani mehon yemitfelgewen honhe kemisteratu kenchebehe eyelgeski new tekebaye kale.yebel new!
  leul egzabher yetebkehe.

  ReplyDelete
 20. ዲያቆን መሐሪ ገብረ ማርቆስOctober 12, 2010 at 7:04 PM

  All truth passes through three stages. First it is ridiculed. Second, it is violently opposed. Third, it is accepted as being self evident.
  Arthur Schopenhauer

  አንዳንድ ሰዎች ጠንከር አድርጋችሁ ጽሑፉን እንዳልተረዳችሁት ገልጻችኋል፡፡ ፍሬ ሐሳቡ ግራ እንደሆነባችሁም አመልክታችኋል፡፡ ምናልባት የተጻፈበት ድምጸት ስላቅ ስለሆነ ይመስለኛል፡፡

  አማን! አማን!
  ከተባለው ነገር ሁሉ ይልቅ ያጠፋን፣ ያወደመን የሐሳብ ልዩነቶችን ከመቀበል ይልቅ በምንታዌ (dualism) አስተሳሰብ ተወጥረን “ይህኛው ካልሆነ ያኛው ነው፡፡” ብለን ሙጥኝ የምንል፤ የተለያዩ አመለካከቶችን አቻችለን ከምናይ ጽንፍ አስይዘን ብንፋጅ የምንመርጥ መሆናችን እንደሆነ አምናለሁ፡፡

  ፖለቲካን ካነሣን አንድ ሰው ወይ የገዢው ፓርቲ አልያም ደግሞ የተቃዋሚው ደጋፊ መሆን አለበት፡፡ የራሱን አስተሳሰብ መከተል፣ ማመዛዘን አይፈቀድለትም፡፡ ስላለው ነባራዊ ሁኔታ መልካም መልካሙን እያነሣ ሲናገር የሰማነውን ሰው “እርሱማ የለየለት የኢሕአዴግ ካድሬ አይደለም እንዴ!” ብለን ታርጋ እንሰጠዋለን፡፡ የፓርቲ አባልነት ካርድ እናስታጥቀዋለን፡፡ ምናልባት ይህንኑ ሰውዬ በአንድ መሥሪያቤት አሠራር ተበሳጭቶ ሲማረር ወይም ስለኑሮ ዙር መክረር ሲተክዝ ከሰማን የተቃዋሚ ፓርቲዎች ደጋፊ አድርገን እንቀባዋለን፡፡

  ይህ አመለካከት በሕዝቡ ዘንድ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ፓርቲዎቹም ውስጥ ገዢ አስተሳሰብ እንደሆነ አንዳፍታ የየፖለቲካ ፓርቲዎቻችንን ቃና ለማስታወስ መሞከር ነው- ሁሉንም፡፡ የተለየ ሐሳብን መግለጽ በአንዳንዶቹ ፓርቲዎች ዘንድ “የአመለካከት ችግር ያለበት!” የሚል ስም ያሰጣል፡፡ በሌሎች ዘንድ ደግሞ “ባንዳ! ወላዋይ!” ያሰኛል፡፡

  ቤተክርስቲያናችንን ውስጥ ያለው ጉድም ለሰሚው ግራ ነው፡፡ አሁን ያለው ሁኔታዋን ያየ ሰው በእውነት የአርዮስን ትምህርት በትእግስት አድምጠው፣ ጥያቄዎቹን መልሰው፣ ስሕተቶቹን አርመው ሃይማኖትን ያቀኑት ሠለስቱ ምዕት የነበሩባት ቤተክርስቲያን መሆኗ ቢጠራጠር አይገርምም፡፡ አንዳንድ ጊዜ “በዘመናችን መደማመጥ የጠፋው ጣልያን እንደ ብራና መጻሕፍታችን ይዞት ወጥቶ ነው? ወይስ የአባቶቻችን እርግማን ይኖርብን ይሆን?” እያልሁ እጠይቃለሁ፡፡ መልሱን እንጃ?! እስኪ ራሳችንን እንመልከት በቀን ውስጥ የምንናገረውን የምንናገረው መናገር ስለቻልን ነው ወይስ መናገር ስላለብን?

  መጽሐፍ "ዘቦ እዝን ለሰሚዕ ይስማዕ!" እንጂ "ዘቦ አፍ ለነቢብ ይንብብ!" አላለም፡፡

  አቦ የሚያዳምጥ ጆሮ ይስጠን!

  ReplyDelete
 21. Thanks Daniel it is a great message for those who understand it.Yemeles photo yalebet t-shirt yelebese sewuye be Amsterdam debedebut tebale. wey gud min ayinet diaspora new Ethiopia yalebat. Sewoch yefelegut hasab, political, gileseb bemidegufubet Amsterdam hager lemin ye melese photo adereg tebilo yidebedebal set lij enquan endezih atadergim yemebit chigir alebin ketebale bereha tekido litagelu sichilu gileseb medebdeb asafari bicha sayihon lemenagerum ayamechim. be ewunet gin jegininet kemeselachihut tesasitachuhal, jegininet sayihone tesfa mekuret ena confidence matat new. Eski egziabher amlak libona yistenina techachilen yemininorbet gize yisten. Ethiopiawi endezih huno mekiretu gin betam betam yasazinal beteley ferenji min endemilen ene enja.

  ReplyDelete
 22. ለምሳሌ በቅርቡ በአምስተርዳም የአቶ መለስ ዜናዊ ምስል ያለበትን ቲሸርት የለበሰ ሰው በኢትዮጵያውያን መደብ ደቡ እንደ ትልቅ የድል ዜና ሲነገር ነበር፡፡ ታድያ ገዥው ፓርቲ እኛን ከዚህ እና ከዚያ ከለከለን ብሎ መናገር እንዴት ይቻላል? ልዩነታችንስ ከምኑ ላይ ነው? እኔ ልሙት አንድ ነን፡፡ ere sewu abede meselegn. Dile min malet endehone yezenega tiwulid. dile malet ye Adwa torinet ayinet dile bemetebaber yetgegne dil enji yihinen dile kalachihut sewu sew mehone kerto ensisa hone malet new. Lemin ye Meles photo lebese tebilo siletedebedebe tilik dile zena hone weche gud. yawum sewuyew minim yeteneka ayimeslim yeferi aynet dula negeru min yametal. Ebakih Daniel endezih yewerede neger batasnebibeb tiru new sewu endehone ayikeyer bechifin yemihed sew endet tebilo yikeyeral lantem poleticegna hone endayiluh yebetekiristiyan kale egziabher bitasnebiben yishalal.

  ReplyDelete
 23. Qale hiwoten yasemalen bro !!!!!!!!!!!!!!!

  aynen ena leben kefeche bezu endeawkena enadsetewl eyderekeg new wendemalem Dani

  teufochek hulu temehert sechina mastewalen ysetalu men elalew ...

  ye agelegelot gizehn AMELAKE KEDUSAN yarezemeleh ahuenm tegawen ewketun yabezalek Amen !!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 24. SELAM
  des yemil eyita new ,endegebagn beteleyayu mengedoch temesasay tifat yeminiserana ,chigirochin yeminfetr nen

  ReplyDelete
 25. Dn. Daniel
  Let me ask you one question. Are you still a member of Mahebere Kidusan? Your critics is so strong and good but it is unacceptable in Mahebre Kidusan. Rather you must be the brain of MK as Melese is the brain of TPLF. I wond how they accept this idea since they are blindspot.
  Great job!!!

  ReplyDelete
 26. what i understand is ..we Ethiopian believe if we are the same party we think we should be the same,when we talk or dialog...

  same now in out country...like EPRDF think what meles say is always right ..against his word is like our enemy will be happy...Derg ..weyane..the same persons the same starategy every thing is same..merder torture..all the same trend..we can stand by our selfs and speek what our inside tells us...

  it is new generation thinking but we can't go with this thinking unless our country is given to yound generation and rebuild it again..i don't think we can go this way.

  all this happen due to bad gevernance...evel thinking of that generation we can't understand what is inside thier mind..just prey "Yageresew"

  ReplyDelete
 27. Guys, the theme is clearly put in black and white. To understand it more, we need to detach ourselves from the group we belong, at least virtually. We are not going to get the gist of the article as long as we kept attached to our "groups".
  Dani, you are right "ANDNET" SELECHEN.
  Hagos M
  MADRID

  ReplyDelete
 28. በአጻጻፍ ስልት ምክንያት አንዳንድ ሰዎች ውጅምብር ውስጥ ስለገቡ ይህ ጽሑፍ ማብራሪያ ቢሰጥበት መልካም ነው።
  የአንባቢያን የግንዛቤና ያጻጻፍ ስልትን የማወቅ እውቀት ደረጃ ስለሚለያይ ባጭሩ ምን ለማለት እንደተፈለገ ቢገለጽ የተሻለ ይመስለኛል።
  ጽሑፉ አንድነትን የሚሰብክ ሆኖ ሳለ ለአንዳነዶች መለያየትን የሰበክ ስለመሰላቸው። መለያየትን የሚያመጣውን ነገር እንደሚያደርጉት እኛም በአጸፋው ያንኑ እያደረግን እንዴት የተለየን እንባለለን? አንድነትን የምንፈልግ ከሆነ ከዚህ የተለየውን (በጎውን) በመስራት አንድ እንሁን የሚል አንድምታ ያለው ምጸታዊ የአጻጻፍ ስልትን የተከተለ ጽሑፍ ነው ባይ ነኝ።

  ReplyDelete
 29. የማይበላ እንዳያስበላ ያብላላOctober 13, 2010 at 8:59 AM

  Right now our "unity" (in particular in EOTC) is not functional, and more importantly it is just a manipulation by the evil doers. So what we need as individual and a group is not a fake "unity" but a self searching, to clearly defined our own pure identity. Then we will see if it is possible to build a real "unity" in the future.

  God bless you Dn Daniel

  ReplyDelete
 30. I share the Idea of "Mistire Tewahedo". AND HONEN SALE LELOCH ANDINETACHINEN YEMAYIFELIGU AND HUNU YILUNAL. WUSHET SIDEGAGEM EWINET YIHONAL ENDILU!
  God Bless Ethiopia!

  ReplyDelete
 31. Dear Dn Daniel,

  Just to confess, I saw this article on Rose Megazine and I refused to read through because of the title. But now when I read through, lekas kine new. Thank you so much.

  In addition I really appreciate those brothers and sisters commenting here which shows that we have so many potential writers. For eg. @Eyob G. the poem is really a wonderful complement to this article.

  I wish to have as many as possible blogs of this kind so that we have different articles. I think the aim of this article is also the same.

  What do you think Dn Daniel.

  God bless you.

  ReplyDelete
 32. ዲያቆን መሐሪ ገብረማርቆስOctober 13, 2010 at 1:17 PM

  ብዙዎቻችሁ “አልገባንም!” ያላችሁና “አንድነት እንዴት ይጠላል?” ብላችሁ ተቃውሞዎቻችሁን ያሰማችሁ ሰዎች ምናልባት የችግራችሁ መነሻው አንድ ጊዜ ብቻ ከማንበብ የመጣ ይሆናልና ደግማችሁ በርጋታ አንብቡት፡፡ እጅግ በጣም ግልጽ የሚሆንላችሁ ይመስለኛል፡፡

  ReplyDelete
 33. Iether me or Daniel is in the wrong direction. I don't know the right one for the time being.But am very sure one of us in the way of destruction!!

  ReplyDelete
 34. GIN ADDIS NEGER SILAYEHUT TEMECHITOGNAL! I will visit you again Dani!

  ReplyDelete
 35. አንድነት እንዴት ሊጎዳን እንደቻለ እኔንም ሊገባኝ አልቻለም! ጽሑፉን ሁለቴ ሳይሆን ሦስቴ አንብቤዋለሁ፡፡ ለአንዳንዶቻችሁ የተገለጠው ምሥጢር ለምን እንደተሰወረብኝ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ አስረጅ ሆናችሁ የቀረባችሁት አንዳንዶቻችሁም እንዲያውም ጉዳዩን አወሳሰባችሁብኝ እንጂ አላብራራችሁልኝም፡፡ ጸሐፊው በህይወት ስላለ ማለት የፈለገውን እራሱ ይግለጥልን እንጂ ‹‹ ሳይሆን አይቀርም›› በሚል ግምታችሁ እንዴት ልስማማ እችላለሁ !

  ReplyDelete
 36. የጽድቅ መንገድ አለ፤ የኃጢአት መንገድ ደግሞ አለ። እንግዲህ የጽድቅ መንገድ ነው የሚለያየው? ይልቁንም ሁሉም ባንድነት በጽድቅ መንገድ ይጓዝ። መለያየት ከጥላቻ ነው፤ አንድነትም በፍቅር ነው። መልካም መስላ መጨረሻዋ ሞት ከሆነ መንገድ እግዚአብሔር ይጠብቀን።

  ReplyDelete
 37. "መለያየትን የሚያመጣውን ነገር እንደሚያደርጉት እኛም በአጸፋው ያንኑ እያደረግን እንዴት የተለየን እንባለለን? አንድነትን የምንፈልግ ከሆነ ከዚህ የተለየውን (በጎውን) በመስራት አንድ እንሁን የሚል አንድምታ ያለው ምጸታዊ የአጻጻፍ ስልትን የተከተለ ጽሑፍ ነው ባይ ነኝ።" እኔም በዚህ ሐሳ ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ። በአጭሩ 'ያልተሄደበትን መንገድ' እንምረጥ ምክንያቱም ብዙዎች የሄዱበት መንገድ ለአገራችን ፖለቲካዊ ፡ ኢኮኖሚያዊ ፡ ማህበራዊና ሃይማኖታዊ እድገት እንቅፋት የሆነና እንዲያውም ወደኋላ የጎተተን ስለሆነ ነው ። 'ውሃ ቢወቅጡት እምቦጭ' እንደሚባለው እየሆነብን ተቸግረናል። ሁሉም የሌላውን ስህተት እየደጋገመ ስለሚሰራው ነው ጸሃፊው "በመጥፎ ጎኖቻችን አንድ ነን ፡ አልተለያየንም፡ እስቲ የዚህ አንድነት ይቅርብን " ያለው። በጣም ጥሩ እይታ ነው ዲ.ዳንኤል ፡ ቃለ ሕይወት ያሰማልን።

  ReplyDelete
 38. There is one thing current king of Jordan said-"DEMOCRACY WILL MEAN DIFFERENT FOR DIFFERENT PEOPLE".So guys in Ethiopia or Ethiopians around the world can understand living together/democracy only their own way- just the way it has been till now. Western and Eastern cultures do really differ. Just look at our Arab neighbors they are just as hypocrites and naively judging as we r!

  ReplyDelete
 39. ግራ የተጋባው ግራ በገባው ሃሳብ ነው፡፡
  ግራ ያልገባው ጸሐፊ ግራ የገባውን ግራ እንዳይገባው ለማድረግ
  ግራ የገባውን ሃሳብ ግራ ባልገባው መልኩ ቢገልፅለት መልካም ይመስለኛል፡፡

  ReplyDelete
 40. meleyayet enienet besew wust menorun amelakach finch new

  ReplyDelete
 41. AS I understood it, the essence of the essay reads: let's stop herd thinking and forward as many different ideas as possible. It is this unity of idea and lack of alternative way of seeing things that is dangerous for our improvement in all walks of life.

  ReplyDelete
 42. አልግባንም ነው ያላችሁት? አያችሁ አሁንም አንድ ነን:--አንዲት ኢትዮጵያ ወይም ሞት ስንል ከርመን..በኤርትራ መገንጠል ተመዘንን;..አሁንም ለምዶብን ያንኑ መፈክር እንለው የለ.. ወቸ ጉድ ያው እኮ አንድ አይነት ነን... እኛንስ እንደቦንብ ፍንጥርጣሪ ይበታትነን

  ReplyDelete
 43. በእርግጥም ልክ ብለሃል ።
  አሁን ነው የገባኝ ሃሳቡ ። ከዚህ የጥፋት አንድነት ወጣ ብለን ብናስብ ኖሮ አንቀየር ነበር ።
  ግን ምን ያረጋል ሁላችንም አንድ ሆንን ። መፅሃፉም 'ተለዩ' ይል ነበር ።
  ቢያንስ አንኩዓ ቤተ ክርስቲያን ከዓለም መለየት ነበረባት ።
  አግዚአብሔር የምንለይበትን ቀን ያምጣልኝ

  ReplyDelete
 44. አዉነት ብለሃል መች ተለያየን አንድ ሆንን አንጂ ።
  አይ መለያየት አቴ!! ብንለያይማ ጥሩ ነበር ፣ መፅሐፉስ "ተለዩ" አልነበር ያለ ?
  ግን ማን ተለየ ሁሉም ለክፋት አና ለጥፋት አንድ ሆነ አንጂ ።
  አዉነትን ማን ዎዶት ?
  አኔ አሚገርመኝ ቤተ ክርስቲያን አንኩአን ከዓለም አለመለየቷ ነው ።
  ብቻ አግዚአብሔር የተለየን የምንሆንበትን ቀን ያምጣልን።
  አሜን

  ReplyDelete
 45. ዲ/ን ዳንኤል፤

  እግዚአብሔር ይስጥልን፤ ፀጋዉን ያብዛልን። እኔን የሚገርመኝ ሁሌም ብትጽፍ አዳዲስ ሃሳቦችንና የአጻጻፍ ዘይቤዎችን ስለምትጠቀም ጽሑፎችህን በጉጉት ነዉ የምንጠብቀዉ። በዚህም የ'ልዩነት'ን ጥቅም አሳይተሃል ባይ ነኝ፤ አዳዲስ ሓሳቦች፣ አዳዲስ የአጻጻፍ ዘዴዎች፣ አዳዲስ እይታዎች፣ ወዘተ...

  እንደተባለዉም የዚህ አንድ የመሆን (ጥሩ ባልሆኑ ምግባራት) አባዜ ሁሉንም ፓርቲዎች ስለሚያጠቃ በተለይ 'ተቃዋሚ' የሚባሉ ፓርቲዎች ምንም የተለየና የሚያስተማምን ሐሳብ ስለሌላቸዉ ስልጣን ብይዙ አሁን የሚታዩትን የሀገሪቱን ችግሮች ይፈታሉ ብሎ ማሰብ ከባድ ነዉ። ምክንያቱም (ዲ/ን ዳንኤል እንዳለዉ) ፊልሙን አይቀይሩትም፤ አንዱ ተዋናይ በሌላዉ ተዋናይ ከመተካትና ፊልሙን ከመድገም በስተቀር። የተለየ ሐሳብ ቢኖራቸዉማ ብዙ ነገር በተሰራ ነበር። ጉልቻ ቢለዋወጥ ...

  ቤተክርስቲያናችንም የምትፈልገዉ የተለየ ዶግማና ቀኖና ሳይሆን የተለየና የተሻለ አስተዳደር ነዉ። አሁን ያለዉ ከሚቀጥለዉ የተሻለና የተለየ እንዲሆን መጣር ይገባናል። አንድነታችን በዓለማዊ ጥቅም ሳይሆን በሰማያዊ ምግባር ይሁን። እግዚአብሔር ይርዳን።

  ReplyDelete
 46. Wow Dani, thank you so much. May God bless you abundantly. But this paper needs deep and analytical thinking to understand it well otherwise it will be misleading as has been seen by some people comment.

  You raised what I usually argue with my friends... especially about the Diaspora. They say there is no democracy in Ethiopia but they even don't allow people to have different idea. Even we can see the websites…. Then on what mentality are they going to condemn what is going on in Ethiopia. I am not saying that things in Ethiopia as fine.

  Peace,

  ReplyDelete
 47. Wow Dani, thank you so much. May God bless you abundantly. But this paper needs deep and analytical thinking to understand it well otherwise it will be misleading as has been seen by some people comment.

  You raised what I usually argue with my friends... especially about the Diaspora. They say there is no democracy in Ethiopia but they even don't allow people to have different idea. Even we can see the websites…. Then on what mentality are they going to condemn what is going on in Ethiopia. I am not saying that things in Ethiopia as fine.

  Peace,

  ReplyDelete
 48. Wow Dani, thank you so much. May God bless you abundantly. But this paper needs deep and analytical thinking to understand it well otherwise it will be misleading as has been seen by some people comment.

  You raised what I usually argue with my friends... especially about the Diaspora. They say there is no democracy in Ethiopia but they even don't allow people to have different idea. Even we can see the websites…. Then on what mentality are they going to condemn what is going on in Ethiopia. I am not saying that things in Ethiopia as fine.

  Peace,

  ReplyDelete
 49. Good perspective. Do different!

  Esdros ZeLideta, Gondar

  ReplyDelete