Sunday, October 3, 2010

ምን ዓይነት ሲኖዶስ ያስፈልገናል?

ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያን የመጨረሻው ላዕላይ አካል፣ የትምህርተ ሃይማኖቷ፣ የሥርዓቷ እና የትውፊቷ ጠባቂ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን የመወከል የመጨረሻው ሥልጣን ያለው፣ መናፍቃንን እና ከሀድያንን ለማውገዝ፣ የተመለሱትንም ይቅርታ ለማድረግ ሥልጣን ያለው የቤተ ክርስቲያን አካል ነው፡፡

ከላይ ከተገለጡት ሃይማኖታዊ ተግባራት በተጨማሪ የፋይናንስ፣ የሠራተኛ አስተዳደር፣ የንብረት፣ የይዞታ፣ የማኅበራዊ ጉዳዮች፣ የቅርስ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ግንኙነት በተመለከተ ፖሊሲ እና መመርያ የሚያወጣ፣ አቅጣጫ የሚወስን እና የመጨረሻውን ውሳኔ የሚሰጥ አካልም ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ሃይማኖታዊ፣ ሀገራዊ፣ ማኅበራዊ፣ ዓለም ዐቀፋዊ እና ሰብአዊ ኃላፊነቶች ያሉበት የቤተ ክርስቲያን ሉዓላዊ አካል ነው፡፡

እነዚህን ከባድ ኃላፊነቶቹን መወጣት ይችል ዘንድ ሃይማኖታዊ፣ ኁባሬያዊ እና አስተዳደራዊ ጥንካሬዎች ሊኖሩት ይገባል፡፡

ሃይማኖታዊ

የአንድ ሲኖዶስ ሃይማኖታዊ ጥንካሬ ሲባል አባላቱ በሐግ እና በሥርዓት የተሾሙ፣ እምነታቸውን ጠብቀው የሚያስጠብቁ፣ ለእምነታቸው ታማኝነት ያላቸው፣ ላመኑበት ነገር እስከ መጨረሻው ለመቆም ጥብአት እና ጥንካሬ ያላቸው ማለት ነው፡፡

በቤተ ክርስቲያናችን የቅዱስ ሲኖዶስ ኣባት የሚሆኑት ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው፡፡ ስለዚህም የሲኖዶሱ ጥንካሬ በብጹአን ጳጳሳት ጥንካሬ ላይ የተመሠረተ ነው ማለት ነው፡፡ ይህም ጥንካሬ በሚከተሉት ሁኔታዎች ይገለጣል፡፡

የሃይማኖት ትምህርት ብቃት


የቅዱስ ሲኖዶስ አንዱ ተግባር የቤተ ክርስቲያኒቱን ትምህርተ ሃይማኖት መጠበቅ እና መመስከር ነው፡፡ ይህንን ለመወጣት ደግሞ አባላቱ የቤተ ክርስቲያኒቱን ትምህርተ ሃይማኖት በሚገባ ያወቁ፣ዐውቀውም ለመመስከር የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ አንድ ሲኖዶስ ይህንን የመሰሉ አባቶች ካሉት ሊቃነ ጳጳሳቱ ነገረ ሃይማኖትን ሲያስተምሩ፣ ሲያብራሩ እና ሲተነትኑ ይታያሉ፡፡ ምእመናን ሃይማኖታቸውን እንዲጠብቁም መጻሕፍትን ይጽፋሉ፤ ለመናፍቃን ጥያቄ በየጊዜው መልስ ይሰጣሉ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ የሚያከራክሩ፣ የሃሳብ ልዩነት የተፈጠረባቸው እና ምእመናነን የሚያደናግሩ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ አንድ ውሳኔ ይሰጣሉ፡፡

የቤተ ክርስቲያን ሀብታት ዕውቀት

የአንድ ጠንካራ ሲኖዶስ አባላት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሥሪት በሚገባ ያውቁታል፡፡ ገዳማዊ ሥርዓቷን፣ የቅዳሴ ሕይወቷን፣ የጸሎት ጉዞዋን፣ የቅርስ ሀብቷን፣የንብረት ይዞታዋን፣ ታሪኳን እና ባህልዋን፣ ችግርዋን እና ፈተናዋን በሚገባ ይረዳሉ፡፡ በዚህ ረገድ ለሚጠየቁት ጥያቄ በቂ መልስ ይሰጣሉ፡፡ ችግሮች ተባብሰው አደጋ ከማድረሳቸው በፊትም መፍትሔ ይሰጣሉ፡፡

መንፈሳዊ ብቃት

የአንድ ጠንካራ ሲኖዶስ አባላት በምእመናኑ፣ በሚያገለግሉበት ድርሻ እና በራሱ በሲኖዶሱ የተመሰከረለት ሕይወት ያላቸው ናቸው፡፡ ምእመናነን የሚያሰናክል፣ በፍርድ ቤቶች አደባባይ የሚያውል፣ እነርሱንም በቆራጥነት ከመጋደል የሚያግድ ነውር ነቀፋ አይኖርባቸውም፡፡ ምእመናን አፋቸውን ሞልተው ይመሰክሩላቸዋል፡፡ በሕግ ከሚያስጠይቅ ወንጀልም ነጻ ናቸው፡፡

የጸሎት፣ የስግደት፣ የትምህርት፣ የቅዳሴ፣ የተባሕትዎ፣ የተጋድሎ ሕይወታቸው ለሌሎች አርአያ የሚሆን ነው፡፡ ከምቾት እና ቅንጦት ይልቅ ቀላል እና ጽዱ የሆነ አኗኗርን ይመርጣሉ፡፡ ከሀብት ክምችት ይልቅ የጸጋ ስጦታን በብርቱ ይፈልጋሉ፡፡ ከዘመዶ ቻቸው ይልቅ የመንፈስ ልጆቻቸውን ያሰባስባሉ፡፡ ከምድራዊ ወንዝ ይልቅ ሰማያዊውን የሕይወት ወንዝ ይሻሉ፡፡

በገዳማዊ ሕይወታቸው የተመሰከረላቸው፤ በየጊዜው በገዳማቱ ሱባኤ የሚይዙ፤ ከሥጋዊ መፍትሔ ይልቅ መንፈሳዊ መፍትሔ የሚመርጡ ይሆና፡፡ በከተሞች ከመቀመጥ ይልቅ በገዳማቱ ማሳለፍን፤ የገጠር ምእመናነን መጎብኘትን፣ የሕዝቡን ችግር መፍታትን ይመርጣሉ፡፡ ሕመሙማንን ለመጠየቅ በሐኪም ቤቶች፣ ርሃብተኞችን ለመጎብኘት በረሃብ ቦታዎች፣ ገበሬዎችን ለማበረታታት በገጠሮች፣ ሠራኞችን ለማጽናት በፋብሪካዎች ይገኛሉ፡፡ የሕዝብ አባትም ይሆናሉ፡፡

መኪና ከየት እገዛለሁ፣ ቤስ መቼ እሠራለሁ ብለው አይጨነቁም፡፡ አገልግሎታቸውን ያዩ ምእመናን መኪናውን ያዘጋጃሉ፤ በመንበረ ጵጵስናቸውንም ይሠሩላቸዋል፡፡ አይናገሩም፤ ነገር ግን በፍቅር ያስደርጋሉ፤ አይለምኑም፣ ነገር ግን በሃይማኖት ያስፈጽማሉ፡፡

ሲሆን ሲሆን እግዚአብሔር ትምህርታቸውን በተአምራት ያጸናላቸዋል፡፡ የማስተማር፣ አጥምቆ የመፈወስ፣ ጽፎ የማስረዳት፣ ጸልዮ ግዳጅ የመፈጸም፤ ተክሎ የማፍራት፣ገዳም ተክሎ የማጽናት፣ ጸጋን ያድላቸዋል፡፡ ምእመናኑ እንደ አለቃ ሳይሆን እንደ አባት፣ እንደ ባለ ሥልጣን ሳይሆን እንደ መምህር ያዩዋቸዋል፡፡ እነርሱ እረኞች ናቸው እንጂ ምንደኞች አይደሉምና፡፡

አስተዳደራዊ

አስተዳደራዊ ብቃት ስንል የየአንዳንዱ የሲኖዶስ አባል እና የምልዐተ ጉባኤው አስተዳደራዊ ብቃት ማለታችን ነው፡፡

ግላዊ

እያንዳንዱ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አስተዳደራዊ ብቃት ከሌላቸው የሁሉም ውሑድ የሆነው ምልዐተ ጉባኤ ብቃት አይኖረውም፡፡ ይህንን ብቃት ለማግኘት ደግሞ አመራረጥ፣ ልምድ እና ሥልጠና ወሳኞች ናቸው፡፡

አመራረጥ

የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሚሆኑ ጳጳሳት ሲመረጡ ከሃይማኖታዊ ብቃት እና ዕውቀት በተጨማሪ አስተዳደራዊ ዕውቀት እና ብቃት ወሳኞች ናቸው፡፡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ለምሳሌ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ለኤጲስ ቆጶስነት የምትመርጣቸውን አባቶች አስቀድማ በመምረጥ በልዩ ልዩ የኃላፊነት ቦታዎች ትመድባቸዋለች፣ ትምህርት ቤት እንዲገቡ ታደርጋለች፣ ከአነስተኛ እስከ ከፍተኛ ቦታዎች ገብተው ያያሉ፣ ይፈተና፡፡ ድክመታቸውን ያሻሽላሉ፣ ብርታታቸውን ያጠነክራሉ፡፡

በመካከሉ ነውር ነቀፋ ከተገኘባቸው፤ ሕዝብ የሚያማርራቸው፣ ሀብት እና ገንዘብ የሚያባክኑ፣ አስተዳደራቸው የማይሻሻል እና ለሙስና የተጋለጠ ከሆነ ወደ ቀጣዩ የክህነት መዓርግ አይሸጋገሩም፡፡ ነገር ግን በበጎ ሥራቸው የተመሰከረላቸው፣ አብረዋቸው የሠሩት አካላት ያመሰገኗቸው እና የሥራ ፍሬያቸው የሚታይ ከሆነ ቤተ ክርስቲያኒቱ ትሾማቸዋለች፡፡

ቤተ ክርስቲያን ብጹዐን ጳጳሳትን ከሾመች በኋላ ልታስብበት የሚገባ አንዱ ጉዳይ የሚያስፈልጋቸውን መሣርያ ስለማሟላት ነው፡፡ መጀመርያ ደረጃ ታውጣ፡፡ ተመሳይ ደረጃ ያላቸው መንበረ ጵጵስናዎች፣ የቤት ዕቃዎች፣ አልባሳት፣ ተመሳይ ደረጃ ያላቸው መኪኖች፣ የአገልግሎት መሣርያዎች እንዲኖሯቸው ሕግ ታውጣ፡፡ ግዥው በአንድ መምሪያ ሥር፣ ከአንድ የበጀት ቋት ይሁን፡፡ ሸላሚ ያገኘ ባለሚሊዮን መኪና ያላገኘ ባለ በቅሎ መሆን የለበትም፡፡ ጋምቤላም፣ አሶሳም፣ ጂግጂጋም፣ አዲስ አበባም ተመሳሳይ ደረጃ ይኑራቸው፡፡ አባ እገሌ በዚህን ያህል ብር መኪና ገዙ የሚለው ዜና እንዲቆም ቤተ ክርስቲያኒቱ በዕቅድ ታሟላላቸው፡፡ መኪና ለአባቶቻችን ምናቸው ነው፡፡ እንዲያውም ለአሶሳ፣ ለጋምቤላ፣ ለዑጋዴን፣ ለሐረር፣ ለአፋር አህጉረ ስብከት ጳጳሳት ከአገልግሎታቸው አንፃር ሄሊኮፕተርም ያስፈልጋቸዋል፡፡ የሀገሪቱ ሕግ ከፈቀደ፡፡ ነገር ግን ይህ ሁሉ በሲኖዶሱ ተፈቅዶ በዕቅድ ይገዛ እንጂ በሽልማት እና በስጦታ ስም መሆን የለበትም፡፡ አንዱ ተደሳች ሌላው ተመልካች መደረገም አይገባውም፡፡

ከዚህም በተጨማሪ እንደ ግብጽ እና አርመን ቤተ ክርስቲያን አባቶች የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በበጀት እንጂ በደመወዝ መተዳደር የለባቸውም፡፡ የሚያስፈልጋቸውን ቤተ ክርስቲያን ታሟላ፡፡ ከዚያ ውጭ ለጳጳሳት ደመወዝ መክፈል እረኞችን ቅጥረኞች ማድረግ ነው፡፡ ጳጳሳትም ለዕለት ከሚጠቀሙበት በቀር ቋሚ ሀብት ማፍራት፣ ቤት መሥራት ዘር መዝራት አያስፈልጋቸውም፡፡ ቤተ ክርስቲያን የማን ሆና ነው እነርሱ በየመንደሩ ቤት የሚሠሩት፡፡

በምእመናኑ ድጋፍ እና ፍቅር የተሾሙ፣ ቤተ ክርስቲያን የምትመሰክርላቸው አባቶች ከተሾሙ ነገ ዐረፍተ ዘመናቸው ሲደርስ መቀበር ያለባቸው በሀገረ ስብከታቸው ነው፡፡ ቫቲካንን ያየ ሰው ከሚቀናባቸው ነገሮች አንዱ ለፖፖቹ የተዘጋጀው የቀብር ሥርዓት ነው፡፡ እኛም በየሀገረ ስብከቱ የታወቀ የቀብር ቦታ፣በተለይም በገዳማት መዘጋጀት አለበት፡፡ ይህም ቦታ ምእመናን የሚጸልዩበት፣ሻማ የሚያበሩበት እና የአባቶች ንዋያተ ቅድሳት እና አልባሳት የሚቀመጡበት መሆን ይገባዋል፡፡ አንድ ሊቀ ጳጳስ መቀበር ያለበት ባገለገለበት ሀገረ ስብከት እንጂ ዘመዶቹ ባሉበት ቦታ መሆን የለበትም፡፡ ሲያርፍም ንብረቱ ለአገለገለበት ሀገረ ስብከት መሰጠት አለበት፡፡ ያም ሀገረ ስብከት ለምእመናን በቅርስነት መታየት ያለባቸውን በመቃብራቸው አካባቢ ሊታዩ በሚችሉበት ቦታ ማስቀመጥ፣ሌሎቹን ደግሞ ወደ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይገባዋል፡፡

ሥልጠና

አስተዳደራዊ ክሂሎት በአንድ ጀምበር አይመጣም፣ በአንድ ኮርስም አይገነባም፡፡ ነገር ግን ልዩ ልዩ ዘዴዎችን፣ወቅታዊ አሠራሮችን እና የተለዋወጡ ሕጎችን ለማወቅ እንዲቻል የሥራ ላይ ሥልጠናዎች ወሳኞች ናቸው፡፡ በአንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ለጵጵስና መብቃት ማለት በሁሉም ነገር መመረቅ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ይህ ግን ፈጽሞ ስሕተት ነው፡፡ ሰው ምሉዕ በኩልሄ ሊሆን አይችልም፡፡ ነገር ግን ሁሉን አቀፍ መሆን ይችላል፡፡ በተለይም ዓለማዊ አሠራሮች፣ ሕጎች፣ መዋቅሮች እና ስልቶች በየጊዜው ስለሚለዋወጡ እነርሱን ተከታትሎ ለማወቅ ወቅታዊ ሥልጠናዎች ያስፈልጋሉ፡፡ ይህ ደግሞ ብጹአን አባቶችንም ይመለከታል፡፡

ለምሳሌ በኛ ቤተ ክርስቲያን ለጳጳሳት ሥልጠና ማዘጋጀት እና መስጠት እንደ ድፍረት ይቆጠራል፡፡ ይህ ግን ፈጽሞ ስሕተት ነው፡፡ መሠለጥን ማለት አላዋቂነትን መግለጥ ማለት አይደለም፡፡ ዐዋነትን ማጽናት እንጂ፡፡ ወቅቱን እንድንቀድመው፣ ከምእመናንም የተሻለ እንድናውቅ የሚያደርገን ነው፡፡

ዛሬ ዛሬ በየሀገረ ስብከቱ ጳጳሳት ፋይናንስ ያንቀሳቅሳሉ፣ሀብት ያስተዳድራሉ፣የቦታ ይዞታ ጉዳይን ያያሉ፣ የሠራተኛ አስተዳደር ይመለከታቸዋል፣ የሕግ ክርክሮችን ያያሉ፣ የቤተሰብ ጉዳዮችን ይዳኛሉ፣ በጤና ጉባኤያት ይሳተፋሉ፡፡ እነዚህ ትምህርቶች ደግሞ በአብነት ት/ቤቶቻችን ውስጥ የሉም፡፡ ብጹአን አባቶች እነዚህን ጉዳዮች በሚገባ ተገንዝበው ለመምራት እና ለመወሰን እንዲችሉ ወቅታዊ ሥልጠናዎች ያስፈልጓቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን በመላው ዓለም በተበተኑበት በአሁኑ ዘመን አባቶች በመገናኛ ብዙኃን ተደራሽ መሆን አለባቸው፡፡ ሲሆን ሲሆን እያንዳንዱ ሀገረ ስብከት የየራሱ ዌብ ሳይት ያስፈልገዋል፣ አባቶችም ፌስ ቡክን በመሳሰሉ መሣርያዎች ማስ ተማር አለባቸው፡፡ ትምህርቶቻቸውን በቪሲዲዎች እና በዲቪዲዎች ልናገኛቸው ይገባል፡፡ ለዚህ ለዚህ ደግሞ ዘመኑን የዋጀ ሥልጠና ወሳኝ ነው፡፡ ግብፆች ከ1400 በላይ ዌብ ሳይት ሲኖራቸው የኛ አባቶች እና ቤተ ክህነት አንድም ጠንካራ የመረጃ መረብ የለንም፡፡

በሀገር ዐቀፍ እና በዓለም ዐቀፍ መድረኮች ቤተ ክርስቲያንን ወክለው ጥናታዊ ጽሑፎችን ማቅረብ፣ የቀረቡትን ሰምቶ ሃሳብ መስጠት፣የቤተ ክርስቲያኒቱን ዐቋም ማንፀባረቅ፣ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተገኝተው ማብራርያ መስጠት፣ መንግሥት ሕግ ሲያወጣ ተገኝተው የቤተ ክርስቲያንን መብት ማስከበር ዘመኑ ይጠይ ቃቸዋል፡፡

እስካሁን ድረስ በጥናታዊ መጽሔቶች ውስጥ ጥናታዊ ጥሑፋቸው የታተመላቸው የቤተ ክርስቲያናችን ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ብቻ ናቸው፡፡

ልምድ

የመንግሥትን ልዩ ልዩ ኃላፊዎች እና የፓርላማ አባላት ብንመለከት በየጊዜው ወደ ልዩ ልዩ ሀገሮች እየተጓዙ ልምድ ይቀስማሉ፡፡ ይህ ነገር ለብጹአን አባቶችም ያስፈልጋል፡፡ በተለይም በሃይማኖት ከሚመስሉን አኃት አብያተ ክርስቲያናት ጋር የልምድ ልውውጥ ማድረግ ዕውቀት ያስገበያል፡፡ ከእነርሱ ድክመት እና ጥንካሬም እንድንማር ያደርጋል፡፡ ስለ ችግሮች አፈታት፣ስለ ምእመናን አያያዝ፣ ስለ ሀብት እና ንብረት አስተዳደር፣ ስለ ገዳማት አሠራር፣ ስለ ስብከተ ወንጌል ሥርጭት ልምድ መቅሰም ያስፈልጋል፡፡

በሌላም በኩል በሀገር ውስጥ ከሚገኙ መሥሪያ ቤቶች፣ ተቋማት፣ ድርጅቶች፣ የትምህርት ማዕከላት እና ከመሳሰሉት ልምድ መቅሰሙ፣የሞያ እና የልምድ እገዛ መጠየቁ፣ ብሎም ተባብሮ መሥራቱ የብጹአን አባቶችን አገልግሎት ውጤታማ ያደርገዋል፡፡

ኁባሬያዊ

ቅዱስ ሲኖዶስ እንደ አንድ ተቋም አስተዳደራዊ ብቃት እና ጥንካሬ ያስፈልገዋል፡፡ አሁን ባለው አሠራር የቤተ ክርስቲያናችን ሲኖዶስ ከጊዜያዊ ኮሚቴ ባለፈ መካሪም አማካሪም የለውም፡፡ ራሱ ያረቅቃል፣ ራሱ፣ ይፈትሻል፣ ራሱ ያጸድቃል፡፡ ሌሎች የቤተ ክርስቲያን አካላት እና ምእመናን የሚሳተፉበት ምንም ዓይነት መንገድ የለውም፡፡

ከአኃት አብያ ክርስቲያናት ግብጽን፣ ከሌሎቹ ደግሞ የሮም ካቶሊክን ብንመለከት ግን ይህ ዓይነት አሠራር የላቸውም፡፡ ሲኖዶሳቸው በሥሩ ቋሚ ኮሚቴዎች አሉት፡፡ እነዚህ ቋሚ ኮሚቴዎች በሊቃነ ጳጳሳት፣ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣በባለሞያዎች እና በጽ/ ቤት ሠራተኞች የተደራጁ ናቸው፡፡ አስቀድመው ጉዳዮች የሚታዩት፣ የሚረቅቁት፣ የሚስተካከሉት እና ለውሳኔ የሚቀርቡት በእነዚህ ቋሚ ኮሚቴዎች አማካኝነት ነው፡፡

ሲኖዶሱም አንድን አጀንዳ ተነጋግሮበት ለዝርዝር እይታ ወደ እነዚህ ኮሚቴዎች ነው የሚመራው፡፡ ዕቅድ የሚዘጋጀው፣ የፖሊሲ ረቂቅ የሚቀርበው፣ የጳጳሳት ምርጫ ዕጡ የሚቀርበው፣ የኃላፊዎች ሹመት ዕጩ የሚቀርበው በእነዚህ ኮሚቴዎች ነው፡፡ ይህ አሠራር ነገሮች ጊዜ ተወስዶባቸው በዝርዝር እንዲታዩ ከመርዳቱም በላይ ከስሕተትም ይጠብቃል፡፡ የሚመለከታቸው አካላትም ሃሳብ እንዲሰጡ ዕድል ይሰጣል፡፡

ለምሳሌ አንድ የሕግ ረቂቅ ሲዘጋጅ የሕግ ኮሚቴው ከቅዱስ ሲኖዶስ በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት ያረቅቃል፤ የሚመለከታቸውን አካላት እና ግለሰቦች ጠርቶ ያወያያል፤ ሃሳብ ያሰባስባል፤ ከዚያ በኋላ ደግሞ ጨምቆ እና የሕግ መልክ አስይዞ ለሲኖዶሱ ያቀርባል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስም የቀረበለትን መርምሮ ያጸድቃል፡፡ በዚህ ሂደት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ምእመናን፣ ባለሞያዎች እና ሌሎች መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላት ስለተሳተፉበት የሲኖዶሱ ውሳኔ ተጠቃሽ፣ አግባቢ እና ሁሉም የሚቀበለው ይሆናል ማለት ነው፡፡

ለምሳሌ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ የሚከተሉት ቋሚ ኮሚቴዎች አሉት፡፡

1. የዶግማ እና መንፈሳዊ ትምህርት

2. የሕግ

3. የአህጉረ ስብከት ጉዳዮች

4. የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እና ትውፊት ጉዳዮች

5. መንፈሳዊ ግንኙነት

6. የሕዝብ ግንኙነት

7. የክህነት ጉዳዮች

8. የዕቅድ

እንዲሁም በጽ/ቤቱ ሥር ቃለ ጉባ የሚይዙ እና ውሳኔዎችን የሚከታተሉ ባለሞ ያዎች አሏቸው፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስም

 በብፁአን አበው የሚመሩ፤ ሦስት ጳጳሳት፣ሦስት ሊቃውንት፣ ሦስት ባለሞያ ምእመናን የሚሳተፉባቸው፣ በየራሳቸው የተሟሉ የጽ/ቤት መሣርያዎች፣ በጀት እና ድጋፍ ሰጭ የሰው ኃይል ያላቸው ቋሚ ኮሚቴዎች ቢኖሩት መልካም ነው፡፡ እነርሱም፡

1. የዶግማ እና የቀኖና ጉዳዮች፡ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት እና ሥርዓት የሚያብራራ፣ ለሚነሡ ጥያቄዎች በሲኖዶሱ መወሰን ያለባቸውን የዶግማ እና የሥርዓት ጉዳዮች አርቅቆ የሚያቀርብ፣ ለሚነሡ ክርክሮች ዝርዝር ምላሽ የሚያዘጋጅ፤ ሥርዓት ሊሠራባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን በመለየት ረቂቅ የሚያቀርብ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ የሚታዩ የሃይማኖት መጻሕፍትን የሚመረምር፣ ከልዩ ልዩ አካላት ለሚቀርቡ የቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖታዊ አስተያየት ለሚጠይቁ ጉዳዮች መልስ የሚያዘጋጅ፡፡


2. የካህናት እና የክህነት ጉዳዮች፡  የካህናትን አሿሿም፣ ሥርዓት፣ አለባበስ፣ አቀጣጠር፣ የሥነ ምግባር ሁኔታ፣ ብዛት፣የሚመለከት፤ ክህነትን ለሚመለከቱ ቅሬታዎች እና ጥያቄዎች ዝርዝር መልስ የሚያዘጋጅ፤ በካህናት መካከል ለሚነሡና የሲኖዶሱን ውሳኔ ለሚፈልጉ ጉዳዮች ረቂቅ ውሳኔ የሚያዘጋጅ፡፡ ክህነትን እና ካህናትን በተመለከተ መጽደቅ ያለባቸውን ረቂቅ የሕግ ሃሳቦች የሚያመነጭ፤ ከልዩ ልዩ አካላት ካህናትን በተመለከተ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች መልስ የሚያዘጋጅ፡፡ ስለሚሾሙ ኤጲስ ቆጶሳት መረጃ የሚያሰባስብ፣ሥልጠና የሚያዘጋጅ፣ እጩ የሚያቀርብ፡፡

3. የገዳማት ጉዳዮች፡  የገዳማትን ይዞታ፣ሥሪት፣ የገዳማውያንን አገባብ፣ አኗኗር፣ የገዳማትን ሀብት እና ንብረት፣ የገዳማትን አስተዳደር፣ የምንኩስናን አሰጣጥ፣ የመነኮሳትን አመዘጋገብ፣ በተመለከተ የሚያይ፣ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ የሚያቀርብ፣ሕግ የሚያዘጋጅ፡፡

4. የቤተሰብ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች፡  ክርስቲያናዊ ቤተሰብን በተመለከተ መውጣት ያለባቸውን ፖሊሲዎች እና መመርያዎች የሚያረቅቅ፣ ማኅበራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ሃሳብ የሚያቀርብ ነው፡፡ የቤተሰብ ምጣኔ፣የወሊድ መቆጣጠርያ፣ ኤች አይቪ/ኤድስ፣ የቤተሰብ ሕግ፣የሕፃናት አስተዳደግ፣ የአረጋውያን ሁኔታ፣ ጤና ጉዳዮች፣ የሴቶች መብት ጉዳዮች፣ ወሊድ እና ከወሊድ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣ የዚህ ኮሚቴ ጉዳዮች ናቸው፡፡

5. የቅድስና እና ቅዱሳት መጻሕፍት ጉዳዮች፡ የቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱሳን እነማን እንደሆኑ፣ ታካቸው፣ ገዳማቸው፣ክብረ በዓላቸው ተጠንቶ በሲኖዶሱ እንዲጸድቅ፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱን መጻሕፍት የመለየት፣ በቀኖና ዕውቅና የመስጠት፣ በቅዱስ ሲኖዶስ መዓርገ ቅድስና ሊሰጣቸው የሚገቡ ቅዱሳንን ማጥናት እና ማቅረብ፤ የዚህ ኮሚቴ ተግባራት ናቸው፡፡

6. የፋይናንስ፣ የበጀት እና ኢኮኖሚ ጉዳዮች፡  የቤተ ክርስቲያኒቱን የገቢ ምንጮች ሃሳብ ማቅረብ፣ የፋይናንስ ሕጎችን ማርቀቅ፣ የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማርቀቅ፣ የአብያተ ክርስቲያናትን የፋይናንስ አያያዝ በተመለከተ ሃሳብ ማቅረብ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ በኢኮኖሚ ራስዋን የምትችልበትን ሃሳብ ማቅረብ፡፡ በሀገሪቱ የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ጉዳዮች የቤተ ክርስቲያኒቱ ድምፅ የሚሰማበትን መንገድ መተለም፤ ከልዩ ልዩ ክፍሎች የሚቀርቡትን የቤተ ክርስቲያኒቱን የበጀት ጉዳዮች ተመልክቶ ለቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ሃሳብ ማቅረብ፡፡

7. የንብረት፣ የአስተዳደር እና መረጃ ጉዳዮች፡ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሠራተኞች ሁኔታ፣ የደመወዝ ደረጃ፣ የአስተዳደር ስልት እና መንገድ፣ አዳዲስ የአሠራር መንገዶችን፣ የመረጃ እና የመረጃ ቋትን በተመለከተ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን የመረጃ ግንኙነት በተመለከተ፣የዶክመንት እና አርካይቭን ጉዳይ በተመለከተ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን የንብረት እና ቅርስ አያያዝ በተመለከተ፣ የይዞታ እና ርስት ጉዳዮችን በተመለከተ የሚመለከትና ሀሳብ የሚያቀርብ፣ የፖሊሲ እና የመመርያ ረቂቅ የሚያቀርብ፡፡

8. የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች፡ የቤተ ክርስቲያኒቱን ኢኩሜኒካል ግንኙነት፣ ከአኃት አብያተ ክርስቲያናት፣ ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት፣ ከዓለም ዐቀፍ ድርጅቶች፣ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ስለሚኖራት ግንኙነት የሚያጠና፣ የፖሊሲ እና የሕግ ረቂቅ የሚያቀርብ፣በሚወሰኑ ውሳኔዎች ላይ ሃሳብ የሚያቀርብ፡፡

9. የሕዝብ ግንኙነት እና ሚዲያ ጉዳዮች፡ ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ መረጃ የሚሰጥ፣ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚያዘጋጅ፣ መታወቅ ያለባቸውን የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔዎች ለሕዝብ የሚገለጡበትን መንገድ የሚያመቻች፤ የቅዱስ ሲኖዶስን እንቅስቃሴ የሚገልጡ የመረጃ መረቦችን የሚያደራጅ እና የሚከታተል፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሬዲዮ፣ የቴሌቭዥን፣ እና የኅትመት ሚዲያ እንዲኖሯት፣ ያሏትም እንዲበለጽጉ ለቅዱስ ሲኖዶስ ሃሳብ የሚያቀርብ፣ የፖሊሲ ረቂቅ የሚያዘጋጅ፣ የሚያማክር እና ሃሳብ የሚያመነጭ፡፡

10. የወጣቶች እና ትምህርት ጉዳዮች፡ የሰንበት ት/ቤቶችን፣ የማኅበራትን እና ከወጣቶች ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በተመለከተ የሚያጠና፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ነባር እና ዘመናዊ ት/ቤቶችን በተመለከተ የትምህርት ፖሊሲ የሚያረቅቅ፣ ስለ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ኮሌጆች እና ማሠልጠኛዎች ሃሳብ የሚያቀርብ፣ የሚያማክር፤ ለቤተ ክርስቲያኒቱ የትምህርት ተቋማት የፕሬዚዳንቶችን እና ሴኔቶችን ሹመት የሚያቀርብ፣

11. የሕግ ጉዳዮች፤  በቅዱስ ሲኖዶስ የሚወጡ ሕጎችን አስቀድሞ የሚያይ፣ ከሌሎች ኮሚቴዎች ጋር በመሆን ሕጎች የቤተ ክርስቲያኒቱን አሠራር፣ የሕግን ቅርጽ እና የሀገሪቱን የሕግ አግባብ የጠበቁ መሆናቸውን የሚከታተል፣ ለሲኖዶሱ የሕግ ምክር የሚሰጥ፣የሚሻሻሉ ሕጎችን ለይቶ የሚያቀርብ፣ የአዳዲስ ሕጎች ሃሳብ የሚያመነጭ፡፡

እነዚህ ቋሚ ኮሚቴዎች ከላይ ከተጠቀሱት ተግባሮቻቸው በተጨማሪ ከሥራቸው ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የጠቅላይ ቤተ ክህነት የሥራ ክፍሎች ይከታተላሉ፡፡ ሪፖርቶቻቸውን ይመረምራሉ፤ ዕቅዶቻቸውን ተመልክተው ለቅዱስ ሲኖዶስ ያቀርባሉ፤ በየጊዜው እየጠሩ በጉዳዮች ላይ ማብራርያ ይጠይቃሉ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ቅዱስ ሲኖዶስ ለመምሪያዎች፣ለኮሚሽኖች፣ለድርጅቶች እና ለልዩ ልዩ ተቋማት የሚሾሟቸውን ኃላፊዎች የሚመለከታቸው ኮሚቴዎች አጥንተው፣ መረጃ አዘጋጅተው ያቀርቡለታል፡፡ ይህ አሠራር ሲኖዶሱን ከሐሜት የሚያወጣ እና በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ እንዲሰጥ የሚያደርግ ነው፡፡

በሌላ በኩል በቤተ ክርስቲያናችን ሁሉም ጳጳሳት ተመሳሳይ ስም፣ መዓርግ እና አገልግሎት ነው ያላቸው፡፡ በአኃት አብያተ ክርስቲያናት ግን እንደዚህ አይደለም፡፡ ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚሾሙ ጳጳሳት ስማቸውም ድርሻቸውም የተለያየ ነው፡፡ ለምሳሌ ግብፃውያን የሚከተሉት ዓይነት ጳጳሳት አሏቸው፡፡

ፓትርያርክ፡  የሲኖዶሱ ሰብሳቢ

ሜጥሮጶሊጣን፡ በታላላቅ ከተሞች እና በኢየሩሳሌም የሚሾሙ ጳጳሳት

ሊቃነ ጳጳሳት፡  በሥራቸው ኮሬ ኤጲስ ቆጶሳትን እና ኤጲስ ቆጶሳትን የሚያስተዳድሩ እና ታላላቅ ሀገረ ስብከቶችን የሚመሩ፡፡ ለምሳሌ የአፍሪካ ሊቀ ጳጳስ

አበ ምኔቶች፡ monastic Bishops ገዳማትን የሚያስተዳድሩ

ኮሬ ኤጲስ ቆጶሳት፡  ለገጠሪቱ ቤተ ክርስቲያን የሚሾሙ፣ በሌላም በኩል በአንድ ሊቀ ጳጳስ ሥር ሆነው ሰፊ ሀገረ ስብከቱን ተካፍለው የሚያስተዳድሩ፡፡

አጠቃላይ ጳጳሳት፡ General Bishops በሀገረ ስብከት ደረጃ ሳይሆን ለልዩ ልዩ ጉዳዮች የሚሾሙ፣ ለምሳሌ ለመምሪያዎች፡፡

ጳጳሳት፡ Diocesan Bishops ሀገረ ስብከት ተሰጥቷቸው የሚሾሙ፡፡

ረዳት ጳጳሳት፡ ፓትርያርኩን በልዩ ልዩ ጉዳዮች የሚያማክሩ ጳጳሳት

ሊቀ ካህናት፡ በትዳር የሚኖሩ ካህናትን በመወከል በቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰበሰብ ካህን፡፡ እነርሱ wakil-al batrakiya ይሉታል፡፡ የካህናትን ጉዳይ በሲኖዶሱ የሚያቀርብ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም ሁሉንም ለቃነ ጳጳሳት ከምታደርግ፡

ለታላላቅ ገዳማት አበምኔቶቻቸውን ጳጳሳት ቢያደርግ መልካም ነው፡፡  ገዳማውያን ክህነት ለመቀበል እና ለቡራኬ ከተማ ከሚመጡ፣ የሥርዓት ጉዳዮችን ለማስወሰን ወደ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤቶች ከሚወጡ እዚያው ቢጨርሱ፡፡ በሌላም በኩል ገዳማት የቤተ ክርስቲያኒቱ ዋና ነገሮች ናቸው፡፡ በመሆኑም የቅዱስ ሲኖዶስ የቅርብ ክትትል ያስፈልጋቸዋል፡፡

የቤተ ክርስቲያኒቱን ዋና ዋና ጉዳዮች የሚመሩ አጠቃላይ ጳጳሳት ቢኖሯት፡፡  ስብከተ ወንጌል መምሪያ፣ገዳማት መምሪያ፣ የወጣቶች ጉዳይ መምሪያ፣ የካህናት ጉዳይ መምሪያ፣ ወዘተ በጳጳሳት ቢመሩ፡፡ ሌሎች ድጋፍ ሰጭዎች፣ ማለትም የፋይናንስ፣ የአስተዳደር፣ የበጀት፣ የልማት፣ አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት፣ ወዘተ በባለሞያ ምእመናን ወይንም ካህናት ቢመሩ፡፡

• እንደ አዲስ አበባ ላሉ ታላላቅ ከተሞች ሜጥሮጶሊጣን ቢመደቡ፡፡

ለታላላቅ ሀገረ ስብከቶች ሊቃነ ጳጳሳት ተመድበው በሥራቸው ኤጲስ ቆጶሳት ቢኖሩ፡፡  ለምሳሌ ለአፍሪካ፣ ለአሜሪካ፣ ለአውሮፓ፣ እና በሀገራችንም ብዙ አድባራት እና ገዳማት ላሉባቸው አህጉረ ስብከት በሥራቸው ኤጲስ ቆጶሳት ተመድበው ሊቃነ ጳጰሳት ቢያስተዳድሯቸው፡፡ ይህ አሠራር አዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ከነባሮቹ ልምድ እንዲያገኙ፤ አረጋውያን አባቶችም በኤጲስ ቆጶሳት ታግዘው አገልግሎታቸውን እንዲፈጽሙ ያደርጋቸዋል፡፡

ኤጲስ ቆጶሳት፡  በሊቃነ ጳጳሳት ሥር ከሚመደቡት በተጨማሪ ለታላላቅ እና ታሪካዊ አድባራት ኤጲስ ቆጶሳት ቢመደቡ መልካም ነው፡፡ ለምሳሌ አኩስም ጽዮን፣ ላሊበላ፣ እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት፣ ቁልቢ ገብርኤል፣እና የመሳሰሉት ካላቸው ታሪካዊ ቦታ፣ ከቅርሶቻቸው፣ ከሚያስተዳድሩት አገልጋዮች እና ሀብት ብዛት አንፃር የቅዱስ ሲኖዶስ ትኩረት ያስፈልጋቸዋል፡፡

ረዳት ጳጳሳት፡  ቅዱስ ፓትርያርኩን የሚያማክሩ፣ የቅዱስ ፓትርያርኩን ተልእኮ የሚያፋጥኑ አባቶች፡፡

የሕጋውያን ካህናት ተወካይ ሊቀ ካህናት፡  የቤተ ክርስቲያናችን ቅዱስ ሲኖዶስ ሊያስብባቸው ከሚገቡ ጉዳዮች አንዱ የሕጋውያን ካህናት ጉዳይ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ አብዛኛውን የሹመት ቦታ መነኮሳት ብቻ እየያዙት መምጣታቸው ሕጋዊ ካህናትን እያስከፋና፣ያለ ፍላጎታቸው ለሹመት ሲሉ የሚመነኩሱ እንዲበዙ አድርጓል፡፡ ከዚህም በላይ የሕጋውያኑ ጉዳይ በሌሉበት እንዲታይም አድርጓል፡፡

የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ይህንን ጥያቄ በሦስት ደረጃ ለመመለስ ሞክራለች፡፡ የመጀመርያው የከተሞችን እና የውጭ ሀገርን አገልግሎት ለሕጋውያን ካህናት ብቻ በመስጠት፤ የአድባራት አስተዳዳሪነትን፣ የልዩ ልዩ የአገልግሎት ክፍሎች ኃላፊነትን በመፍቀድ፣ በሲኖዶሱ ቋሚ ኮሚቴዎች ውስጥ ተሳትፎ እንዲኖራቸው በማድረግ፤ ሦስተኛው እና ከፍተኛው ደግሞ በቅዱስ ሲኖዶስ ውስጥ አንድ ወኪል እንዲኖራቸው በማድረግ ነው፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስም እነዚህን ነገሮች ሊያስብባቸው ይገባል፡፡ የካህናት ልጆች የአባቶቻቸውን አስተዳደራዊ በደል እና መገፋት እያዩ «ቤተ ክርስቲያንን አያሳየን» ከማለታቸው በፊት ጉዳዩ መፍትሔ ይሻል፡፡ እንደ እኔ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን የተከተለችው መንገድ የተሻለ ይመስለኛል፡፡ 

እንግዲህ በአጠቃላይ ሲኖዶሳችን ግንቦት እና ጥቅምት በመጣ ቁጥር የሚናጥ፣ ማንም የፈለገ በሩን እየሰበረ የሚያስፈራራው፣ በሌላ ቦታ ቦታ ያጡ ሴት ወይዛዝርት ጉልበት መሞከርያ፣ የአንድ ሰው አምባገነንነት የሚንጸባረቅበት፣ በቤተ ዘመድ አሠራር የተተበተበ፣ በሀገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ምንም ድርሻ የሌለው፣ በብዙ ያልተመለሱ ሃይማኖታዊ እና ሥርዓታዊ ጉዳዮች የተከበበ እንዳይሆን ከምንጊዜውም በላይ ሊታሰብበት የሚገባው ጊዜ አሁን ነው፡፡

ቤተ ክህነታችን የአስተዳደር እና የአሠራር አርአያ እንጂ የብልሹነት፣ የሙስና፣ የዘመድ አሠራር እና ብቃት የሌላቸው ሰዎች መከማቻ መሆን የለበትም፡፡ ለዚህ ደግሞ ጳጳሳት፣ ሊቃውንት፣ካህናት፣ ምእመናን፣መንግሥት፣ ሌሎችም የዚህችን ሀገር ዕድገት የሚመኙ ሁሉ አስተዋጽዖ ማድረግ አለባቸው፡፡ ይህቺ ቤተ ክርስቲያን ሳታድግ ሀገሪቱ ልታድግ በፍጹም አትችልምና፡፡


45 comments:

 1. Kale Hiwot Yasemalen Dn. Daniel
  it was also my best wish if they consider as you wrote or if they prepare there own solution to stregthen our Holy Synod but considering what is going on in our churh it may be a miracle to see such things.
  anyway you are struggling your part.
  if i know any pope i would print and give this article to contribute at least my part but i don't. and i think this is a good chance for those who can find our fathers.
  God Bless you Dear Bro
  Tezekerene Egzioo
  Tezekerene Egzioo
  Tezekerene Egzioo

  ReplyDelete
 2. Wonderful and exceedingly insightful article. Dear Dn. Daniel your article got an eagle eye to observe and figure out some of the burning issues in our Holy Synod. You're absolutely right we're by far lug behind and the worst we're going from the frying pan to the firing in the day to day activities of the Church. The problem seems so huge and untouchable but I personally do believe that the Almighty God will give us the right Fathers to the right place...we don’t have to stand at the gate and suggesting, we should hold our hands together and work hard for progress and above all pray in pure spirit and not passing judges on anybody’s. It seems we’re at the 11th hour God’s judgement is at the gate!!! Our Ethiopian Orthodox Church has got a great hope form the Almighty Jesus Christ! God hears the outcry of our holy Fathers, Mothers and innocent children from His House!
  Much love for our Church. May her healing be swift and long lasting!

  ReplyDelete
 3. ዳኒ እግዚአብሔር ጸጋዉን ያብዛልህ፡ አባቶቻችን ከተጠቀሙበት በሚገባ ዘርዘር አድርገህ አቅርበሃል። ይህንን ብሎግ የምታነቡ ሁሉ የ internet access ለሌላቸዉ ብጹዐን ሊቃነ ጳጳሳት እና ለምታዉቋቸዉ ምዕመናን አባዝታችሁ ብትሰጡአቸዉ መልካም ይመስለኛል።

  ተጉሻ

  ReplyDelete
 4. THIS IS ABSOLUTELY COMMENDABLE IDEA. BUT WHO IS GOING TO LISTEN TO THIS? GOD IS ALWAYS READY TO HELP US OVERCOME OUR CHALLENGES,BUT WE SOMEHOW TRY TO ESCAPE FROM THE TRUTH THAT GOD IS NOT HAPPY ABOUT IT; AND HENCE OUR PEACE AND UNITY IS OVER DUE.YOUR DETAILED SUGGESTIONS ARE MARVELOUS,BUT BEFORE ALL THIS I WANT TO SEE THE HOLY SYNOD PREPARES A COMPREHENSIVE POLICY FOR THE CHURCH IN ABROAD IN ORDER TO RESOLVE THE MESSY SITUATION FOR THE LAST 20 YEARS.

  ReplyDelete
 5. Abysinian Habib GeorgisOctober 4, 2010 at 2:36 AM

  All what you said is right. This is what should be done. But the question is who will understand, accept and implement these things? I can see no one. To me the most of the people who are currently leading our Church are of three types.

  1. Unable ones: These are spiritual fathers who are doing their best. But they have the education and awareness nearly similar to a person some few hundred years ago. So they don't even know what they don't have and what they need. They don't have the intellectual frame work and back ground to take the courses you proposed and upgrade them selves.Generally, they are not fathers for this age. They can almost do nothing even if they want to.

  2. Rent collectors (seekers): These have lived and taken the position for them selves just as a job, not for the Church, as a service. They are doing what they are doing deliberately.

  3. Heretics: These are heretics who have taken the Church positions to attack her from inside.


  Now this is the question. Which group can change? To me none. The first due to lack of potential, the last two deliberately.

  So to whom are you writing? Who are you expecting to implement your ideas? Don't you think it is like speaking to the wind? Even the people who are reading your blog and giving comments are only fans. I have read many comments admiring you, and suggesting what should be done. But I have read few saying they would take their share. What would be benefit from dreams and intellectual discourses? And what can one do to solve the problem even if he wants to do so. We know the system is locked. These people don't even want to hear you. There is no even a way that one can at least formally give comments.


  What should be done?

  I think we need to work on the next generation strategically. Look, what is frighting more is thinking what the next Synod would look like. According to the current trends, it is going to be a group of gangsters from the second and third groups that I noted above.

  And do we really have 50 monks which would qualify to be bishops if we are given the chance to select members of the next Synod, and another 50 to be managers of the Dioceses,and another 500 for the Woredas. I don't think so.


  So we should work on the next generation strategically. We need a new system by which we produce deacons, priests and bishops.


  Church Tradition is a living river, not a dead one. It is not some thing to simply receive and pass. Every generation will receive it, live in it, develop it to make it work for the current time and then pass it. Of course the development has to be 100 percent in line with what has been received.

  Now how much has our world, our country and their people changed in the last 500 years. A great deal. And what has been changed in our Church education in these times? Almost nothing. To me this is the problem.


  So? So, we need a new system.

  I will come back with proposals on this new system if you think my comment is relevant and post it.

  ReplyDelete
 6. +++
  ዲን. ዳንኤል እግዚአብሔር ይሰጥልን። ቃለ ሕይወት ያሰማልን።
  በጥሩ ሁኔታ ዘርዝረሃቸዋል።
  የእኔ ጥያቄ ይህን ሃሳብ ማነው እየሰማው ያለው? በእውነት እኮ ቤተ ክርስቲያን ያለባት የተወሳሰብ ችግር ሰሚ ጠፈቷል ወይንም የተወሰኑ ሰዎች ብቻ የሚያራግቡት ወሬ እየሆነ ነው። እና አቤት ለማን እንበል? የትዉልደ አደራ መወጣት አልቻልንም።
  እኔ ከጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በፊት ማድረግ አለብን የምለውን እነሆ!
  1.እሰከ አሁን በተጨባጪ በቤተ ክርስቲያናቺን እየተፈጸሙያ ያሉ ቸግሮች በዝርዝር ቢዘጋጁ ፥ እና ለብዙሃኑ የኢ.ኦ.ተ.ቤ ልጆ ቢተላለፍ፡ ምክንያቱም የኢንተር ኔት ወሬ ብቻ ሆኖ እንዳይቀር!!!!
  2.ይህ በቤተ ክርስቲያን ላይ እየተፈጸመ ያለ ችግር (ሥርዓትየለሽነት፥ሙስና፥አደርባይነት፥ቸልተኝነት፥የቀኖና ጥሰት፥ አርአያ ክህነት እና ምንኩስና ማጣት፥ ወ.ዘ.ተ) በአስቸኳይ ይስተካከል ዘንድ ለፓትርያረኩ ፥ለጳጳሳቱ እና ለሊቃውንት ጉባኤ በጽሁፍ ቢቀርብ ግላባጩም ለመንግሥት ቢደርስ፥
  3.በሓገር ውስጥ እና በውጭ ያሉ የተዋህዶ ልጆች በራሳቸው አነሳሽነት ከየአድባራቱ ለሶስት ቀን ሳይወጡ ምህላ እና ጾም ቢያደርጉ እና የቤተ ክርሰቲያን አባቶች ራሳቸውን እና ቤተ ክህነቱን ያጽዱ መልእክት በተለያዩ መንገዶች በህብረት ቢያሰሙ፥
  4.ወደፊት ቤተ ክርስቲያን ከአድር ባዮቸ የጸዳች ትሆን ዘንድ
  ከካህናት እና ከምእመናን የተውጣጣ የቤተ ክርስቲያንን ችግሮቸ እየተከታተለ ለቅዱስ ሲኖዶስ ፥ለሊቃውን ጉባኤ እና ለምእመናን ጉባኤ የሚቀርብ ካውንሲል ቢቋቋም፥
  የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይርዳን።

  ReplyDelete
 7. +++

  ብጹዕ አባታችን እባከዎ ባለች በዚህ አጭር ዘመነዎ ያንብቡት እና መመሪያ ሆነዎት ቅዱስ ሲኖደሱን ቅዱስ ሲኖዶስ ያድርጉት በአክሱሚቱ ይዠዎት አለሁ::

  እግዚአብሔር ይርዳን አሜን::

  ReplyDelete
 8. Dear Dn. Daniel,

  Well Said. But, the question is how we are going to deliver this thing to the Holy synod fathers and even the Pateriarch.

  Do they accept it gladly and put it into action.I read from one of the books of HG Antonius Markos of african affairs while he was working in ethiopia as a medical professional he used to give some advice to the HH anba Tawephelos about the observation he saw and HH Anba Tawphelos used to listen to him intently nodding his head. And in few days, the Holy synod adopted those advices.

  First, it needs humility for all this. One of the reposed alexanderian father who is considered a Saint usually gets a lesson even from the little child. So, if there is humblness, what you said is true and the Fathers should adopt it.

  When we present this to the fathers , it should be in the way that we are the teachers and they are the students. First, we have to develop a really loving releationship with them. Then may be tell them in loving way how we think things should be going.

  HG Antonius Markos had a very loving releationship with HH Anba Tawphilos. We should first approach our fathers. Loving them, pray for them,sincerly care for them. Then Our God seeing our sincer love for His clergy, will send His solution to our mother church

  ReplyDelete
 9. የኢትዮጵያውያን የጳጳሳት ዓይነትስ ምን ዓይነት ነው? የግብጻውያንን የጳጳሳት ዓይነት ገልጸህ የኢትዮጵያውያንን ግን አልገለጽክልንምና ነው፡፡ ሌላው ሌላው የሚጠየቁትን ጥያቄዎች ብትመልስልን ምንም ሲመለሱ ያየኋቸው ጥያቄዎች ስለሌሉ ነው::

  ReplyDelete
 10. ከሁሉም ነገር ይልቅ በአሁኑ ሰዓት ውስጤን የሚያብሰለስለውን ነገር ገና አሁን ጻፍክ፨ነገር ግን የኢትዮጵያውያን የጳጳሳት ዓይነት(አሁን እየተሰራበት ያለው የጳጳሳት መዋቅርስ) ምን ዓይነት ነው? የግብጻውያንን የጳጳሳት ዓይነት ገልጸህ የኢትዮጵያውያንን ግን አልገለጽክልንምና ነው፡፡ ሌላው ሌላው የሚጠየቁትን ጥያቄዎች ብትመልስልን ምንም ሲመለሱ ያየኋቸው ጥያቄዎች ስለሌሉ ነው፡፡
  በተረፈ ግን ቅዱስ ሲኖዶሱ አምና ሁለት መምሪያዎችን በሊቃነ ጳጳሳት እንዲመሩ ማድረጉ ይበል የሚያሰኝና ቸር የሰማን የሚያስብል ነው፡፡

  ReplyDelete
 11. What a nice view,problem identification and giving solution to the existing problems. But, Danni do u think that the current and the existed reality allows this solution?. I don't think b\c there is one proverb in Amheric " Awoko yetegna bekisksut Aynekam". My God bless u. Kale hiwot Yasemalen.

  ReplyDelete
 12. መምህር ዳንኤል መቼም እንዲህ ቢሆን ብለህ በቀረብከው ሲኖዶሳዊ አወቃቀርላይ በጣም ተደስቻለሁ ቤተ ክርስቲያን ይህን መከተል ብትችለ የት በደረሰች ነበር ነገር ግን አንተ የጠቀስካቸውነገሮች እንዳይተገበሩ የሚያግዱት የቤተ ሰብ አስተዳደር በፓትርያሪኩ ዙርያ ብቸ በመብዛቱ ሳይሆን በእያንዳንዱ ሀገረስብከትም በመተግበሩ ነው ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት በ1991 ዓም የጸደቀም የመየዳደርያ ደንብ ነው ምክንያቱ ይህ ደንብ አባቶች በየሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ መምረጥ እንደሚችሉና ተጠሪነቱም ለእነርሱ እንዲሆን በመደረጉ ከዚያም ሀብታቸው ለቤተሰባቸው በውርስ እንዲሰጥ በማጽደቃቸው አስተዳደሩን የበለጠ እንዲጠፋ አድርጎታል ሌላው ፓትርያሪኩ ቀኖናው የሰጠው ሀላፊነትም መጠበቅ አለበት እላሁ

  ReplyDelete
 13. ረዳት ጳጳሳት፡ ቅዱስ ፓትርያርኩን የሚያማክሩ፣ የቅዱስ ፓትርያርኩን ተልእኮ የሚያፋጥኑ አባቶች፡፡ ከአንድ ጳጳስ በላይ ለማለት ተፈልጎ ነው? ወይስ እንዱት ነው?

  ReplyDelete
 14. beteru hunata temelkethewal

  ReplyDelete
 15. ዲ/ን ዳንኤል አንተው ጽፈህ አነተው ገዝተህ ( ጋዜጣ ቢሆን ኖሮስ) ስላስነበብከን እግዚአብሔር መንግሰቱን ያውርስህ፡፡ በተረፈ ምክሮችህን የሚመለከተው አካል በቀና አስተሳሰብ ተመልክቶ እና መርምሮ ተግባራዊ ቢያደርጋቸው መልካም ይመስሉኛል፡፡ አማላካችን የቤተ ክህነታችንን ትንሳኤ እንዲያሳየን ምኞቴ የላቀ ነው፡፡

  ReplyDelete
 16. tanash wendemeh haile michael from dallasOctober 4, 2010 at 2:08 PM

  kale hiwot yasemalen yeagelgelot gezeahen yebarkelen dani.

  ReplyDelete
 17. በመጀመሪይ ያንተን የአገልግሎት ድርሻ እየተወጣሕ በመሆንህ ላመሠግንህ ወደድኹ።በመቀጠል ደግሞ የኔን ልበል፣አሁን በአገልግሎት ላይ ያሉት ሊቃነ ጳጳሳት፣ጳጳሳት፣ኤጲስ ቆጶሳት፣ቅዱስ ፓትሪያሪኩን ጨምሮ ለንደዚሕ ያለ ነገር ታዛዥ ለመሆን ፈቃደኛ የሚሆኑ አይመስሉኝም።ምክንያቱም፡መሰረታዊ ችግር አለባቸውና ለምሳልሌ የትምህርት ማነስ፣የተመረጡት በዘር በመሆኑ፣እንደራሴ ሆነው በመቀመጣቸው፣ፍቅረ ንዋይ ያለባቸው በመሆኑ፣ውሳጣዊ ማንነታቸው ኦርቶዶክስ አለመሆኑ፣ልበ ቅንነት ስለሚጎድላቸው ወዘተ እዚህ ላይ ግን ሁሉንም ማለቴ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ።

  ReplyDelete
 18. May God Bless You and your work
  You are doing your best. There are many people who can contribute much but we are not doing except you. We miss these kinds of people who try to contribute to the Church and the country´s development.

  Anyway, I agree with your suggestions!!!
  May God be with you

  ReplyDelete
 19. በጣም ጥሩ እይታ ነው። ይህም ደግሞ ባለፈው ባቀረብከው የመፍትሄ ሀሳቦች ውስጥ መነሳት ከሚለው ስር "መዋቅራዊ ለውጥ" ባልከው የሚወድቅ ይመስለኛል።
  ቤተ ክርስትያናችን ምን ያህል የተተበተበ ችግር ውስጥ እንዳለች የሚያሳይ ነው። መፍትሄው ደግሞ በአርቆ አስተዋዮችና ቀና አባቶች እጅ ነበር ነገር ግን እነሱ ባሁኑ ጊዜ የባህር ውስጥ አሳ እየሆኑ ነው።
  በዳሰሳህ ላይ አንድ ይቀረዋል የምለው ነገር የአሁኑን መዋቅር ድክመ ቶች አለመተንተኑ ነው ለምሳሌ "ለታላላቅ ሀገረ ስብከቶች ሊቃነ ጳጳሳት ተመድበው በሥራቸው ኤጲስ ቆጶሳት ቢኖሩ፡፡ ለምሳሌ ለአፍሪካ፣ ለአሜሪካ፣ ለአውሮፓ፣ እና በሀገራችንም ብዙ አድባራት እና ገዳማት ላሉባቸው አህጉረ ስብከት በሥራቸው ኤጲስ ቆጶሳት ተመድበው ሊቃነ ጳጰሳት ቢያስተዳድሯቸው፡፡" ላልከው የአሁኑ አሰራርና ድክመቱ አልተገለጸም። ቢሆንም እጥር ምጥን ያለ ሁሉንም የዳሰሰ ነው።
  እግዚአብሔር ይስጥልኝ

  ReplyDelete
 20. ዉድ ወንድማችን በአሁኑ ሰዓት የቤ/ንን መብት የሜደፋፈሩና የሚጥሱ ብሎም ያሉአትን መብት እዳትጠቀም እያደረገ ይለዉ የቤ/ኒቱ ቁንጮ የሆነዉ ሲኖዲወስ አስተዳድራዊ ብቃት ኖሮት ቤተክርስቲያኗን መምራትና ማሰተዳደር አለመቻሉ ይመስለኛለ፡፡ የማስተዳደር ብቃት አለዉ ተብሎ ቢታመን እንኳ በአንዳንድ የተወሰኑ ሰወቸ የታፈነ በመሆኑ ሰልጣናቸዉን በአድባቡ መጠቀም አልቻሉም፡በመሆኑ በዚህ ርዕሰ ላይ ሰፋ ያለ ነገር መስራት ከሁላችንመ የሚጠበቅ መስሎ ይታየኛል፡፡ በተለይም በአሁኑ ጊዜ የተፈጠረዉ ክፍ ተት እንደመልካመም አጋጣሚ ተጠቀመዉ ብዙ ስራን እየሰሩ ባለበት ወቅት ላይ በመሆናችን ከመቸዉም በላይ ጠንክረን መስራት ይኖርብናል፡፡ስለዚህም ዳኒ በዚህ አርዕስት ብዙ እድትሰራበትና እንዲሁም ያሉህን መረጃወች እንድታደርሰን አሳስባለሁ፡፡
  ገ/ስላሴ አ.አ

  ReplyDelete
 21. This is the proposal I have been waiting for long; after the long critical analysis and counter analysis that have been posted on this blog, by different brothers and sisters who have concern about our church.

  I can only say that establishment of such types of administrative and religious structure with full responsibility and accountability is the way forward. This proposal may not be the best one; but I think those who have been involved in matters of church discussion on this blog would agree that we need one or another type of administrative and religious structure, which could relieve our church of many problems it confronted today.

  As a person with little religious knowledge; but have enormous concern about Christ's Church, I fully support Dn. Daniel's proposal and call upon, as member of Orthodox Christian, the Holly Synod and all concerned organs of the church to work hand in hand towards the fulfillment of such or, essentially similar proposals that may be forwarded.

  May God keep our church's and servants' unity Amen! May God bless you Dani!

  ReplyDelete
 22. dani wonderful idea!!!

  ReplyDelete
 23. ቀብረ ቁስቋም
  በእውነት ጥሩ እይታ ነው ዲ.ዳንኤል ይህንን አባቶች ሊያስቡበት ይገባል አባቶች ከምእመኑ መቅደም አለባቸው እንጂ ምእመኑ ካባቶች መቅደም የለበትም አሁን አንተ ባልከው መሰረት ላባቶች በተለያየ ጊዜ ከዘመኑ ጋር የሚሄድ ስልጠና ሊጣቸው ይገባል.ለምሳሌ ወደ ውጪ ሃገር የሚላኩ አባቶች መጀመሪያ ስለሚሄዱበት ሃገር መጠነኛም ቢሆን የቋንቋ፤የባህል፡የምግቡ ሁኔታ እንኩዋን ሳይቀር እና የህዝቡ ባህሪያት እነዚህንና የመሳሰሉትን ስልጠናዎች ሊሰጣቸው ይገባል ምክንያቱም እዛ ሃገር የሚሄዱት ኢትዮጵያውያን ምእመናንን ብቻ አይደለም ማስተማር ያለባቸው ልላው ችግር እንኩዋን ቢፈጠር ቢያንስ በሀገሩ ቋንቋ ተናግረው ማሳመን አለባቸው.
  አምላከ ቅዱሳን ሃገራችንን ይጠብቅ.

  ReplyDelete
 24. Dn, Daniel
  what you have said is 200% true the coming sendoce meating should be about this topic.

  ቤተ ክህነታችን የአስተዳደር እና የአሠራር አርአያ እንጂ የብልሹነት፣ የሙስና፣ የዘመድ አሠራር እና ብቃት የሌላቸው ሰዎች መከማቻ መሆን የለበትም፡፡ ለዚህ ደግሞ ጳጳሳት፣ ሊቃውንት፣ካህናት፣ ምእመናን፣መንግሥት፣ ሌሎችም የዚህችን ሀገር ዕድገት የሚመኙ ሁሉ አስተዋጽዖ ማድረግ አለባቸው፡፡ ይህቺ ቤተ ክርስቲያን ሳታድግ ሀገሪቱ ልታድግ በፍጹም አትችልምና፡፡
  My God bless you and your family. Our God protecte tewhedo Church form evils

  Thank you

  ReplyDelete
 25. በስመ ሥላሴ አሜን።

  ጤና ይስጥልኝ ወገኖቼ እንደምን ከረማችሁ? ... መምህር ቃለ-ሕይወትን ያሰማልን። ... እየሰራኸው ስላለው መልካም ነገርም እግዜር ዋጋ አያሳጣህ ...

  ምንም እንኳ ይህ አስተያየቴን ላንተ ለራስህ ብልከው በተሻለ የነበረ ቢሆንም ምናልባት አንባብያንም ቢያነቧት ምንም አትልም ብዬ በአደባባይ ጻፍኳት ... እንደኔ መረዳት ይህ ጥናታዊ ጽሁፍ ጥሩ የተዋቀረና ትክክልም ነው ፤ ... ግና ... እንደኔ እንደኔ ... እኔ ጽሑፉ ተጽፎበታል ብዬ ከማስበው ፤ ምናልባትም እኔ ካልተረዳሁት በጎ ዓላማና ምክንያት ባሻገር ፤ ሊጤኑ የሚገባቸው ሌሎች ጉዳዮችም አሉ ብዬ አምናለሁ። ... ይኼውም ጥናቱን በመስራት ሂደት ትኩረት ተሰጥቶባቸው የተዳሰሱት ነጥቦችና ቦታዎች ከጥናቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ብቻ መሆናቸውን ሳስብ ፤ ጥናቱም ሊቀርብ የሚገባው ለሚመለከታቸው ቢሆን ብዬ አስባለሁ ፤ እርግጥ ቤተክርስቲያን የሁላችንም ናት ፤ በመሆኑም የሚመለከታቸው ማለቴ የቤተክርስቲያንን ጉዳይ ፤ የተወሰኑ አካላት ጉዳይ ብቻ አድርጌ ማቅረቤ ሳይሆን እያንዳንዱ ምዕመን በቤተክርስቲያን አስተዳደር ያለውን ድርሻ መለያየት ለማመልከት ነው። ...

  እንዲህም ስለሆነ ከመንፈሳዊ የእድገት ደረጃና ነገሮችን ከመረዳት ችሎታ አንጻር አንዳችን ከሌላችን ባለን ልዩነት ምክንያት ይህ ጥናታዊ ጽሑፍ እንዲህ ባለ ሁኔታ ይህንን የጡመራ መድረክ ለሚያነብ ሰው ሁሉ መቅረቡ ፤ እንደኔ እንደኔ ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚያመዝን ይመስለኛል። ... እርግጥ ነው በጥናቱ የተነሱት ነጥቦች ለቤተ-ክህነት ሰዎች በተለይም ለአባቶች ቢደርሱና ሰፋ ያለ ውይይቶች ቢደረግባቸው መልካም ውጤት ሊመጡ ይችላል ፤ ነገር ግን በተለያዩ እንቅፋቶች ምክንያት ከነዚህ አካላት ጋር ለመገናኘት ስላልተቻለ እንዲህ ባለ መልኩ ፤ ይህንን የመሰለውን ታላቅ ነጥብ ዝርው ማድረግ ግን ' አህያውን ፈርቶ ዳውላውን ' አይነት ይሆናል። ( ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ለመገናኘት አለመቻል የፈጠረው ክፍተት ከሆነ ማለቴ ነው ) ... እንዲህም እንኳ ቢሆን ... ሲኖዶሳችንን በተመለከተ ከመረዳታችን ውጭ የነበሩ እውነቶችን መረዳታችን ፤ ብሎም ሲኖዶሳችን ቢሆን ፣ ቢኖሩት ብለን የምናስባቸውን መልካም እሴቶች መመኘታችንና ከዚሁ ምኞታችንም የተነሳ መቆጨታችን በራሱ መልካም ነው። ... ቢሆንም ከዚህ ባሻገር ደግሞ ስንቶቻችን ማወቃችን መቆጨታችንን ወልዶ ፤ ከመቆጨታችን የተነሳም ደግሞ ባቅማችን ሁሉን ሊያደርግ ወደሚችል ጌታ እናለቅሳለን? ... ስንቶቻችንስ ከመቆጨታችን የተነሳ በአባቶቻችን ላይ የማይገባን ነገር እንናገራለን? ... ስንቶቻችንስ ከመቆጨታችን የተነሳ ወደማይረባ አሉባልታ እናመራለን? ... ስንቶቻችንስ ባለማወቅ ለሲኖዶሱ ያለን ክብር የወረደ ይሆናል? ... ቤት ይቁተረን ... እዚህ ላይ ታዲያ ሊነሳ የሚገባው ዋና ነገር ፤ ይህን ጽሁፍ ካነበቡም ሆነ ካነበቡ ከሰሙት መካከል ፤ በማንበባቸው ( በመስማታቸው ) የሚጠቀሙት ፤ ተጠቅመውም ከሚጠቅሙት እና በማንበባቸው ከሚጎዱት ( ተጎድተውም ከሚጎዱት ) ውስጥ አብላጫውን ቁጥር የሚዙት የትኞቹ ይሆናሉ የሚለው ነው? ... ስለዚህም ይህን ከግምት በማስገባት ሁላችንም እንድናነበው ባልተደረገ ነበር እላለሁ። ... ለሁሉም ጊዜ ብቻ ሳይሆን ቦታም አለውና! ...

  ይህን ከመሰለው ሀሳቤ ሌላ በጥናቱ የተነሱትን ነጥቦች በተመለከተ ፤ ከላይ እንዳልኩት የነጥቦቹ አንኳርነትና ቅደምተከተል ይበል የሚያሰኝ ሆኖ የግብፆቹ ተሞክሮ የቀረበበት ሁኔታ ትንሽ ግር አሰኝቶኛል። ... ይኼውም አብዛኃኛዎቻችን በስሚ ስሚ የምናውቀው ጥንካሬያቸው የምናስበውን ያህል ስኬት እንኳ አምጥቶላቸው ቢሆን ፤ በነርሱ ዘንድ ያለው የምዕመናን የአኗኗር ባህል ፣ የምዕመናኖቻቸው ለአስተዳደር ያላቸው አመለካከት ፣ ብሎም ወደምንለው ጥንካሬ የደረሱበት ጉዞ ሁሉ ከእኛ ነባራዊ ሁኔታ ጋራ ይለያያልና ዋና ነጥብ መሆን ያለበት እግዜር የሚወደው ፣ ከእኛነታችን ጋራ የሚዋደድና የእኛ የሆነ የቤተክርስቲያን አስተዳደር መፍጠሩ ላይ እንጅ እኛ መልካም አስተዳደር አላቸው ብለን ከምናሞካሻቸው ግብጻውያን አስተዳደር ጋራ መመሳሰሉ ላይ መሆን አይገባውም። ... ይህንንም ፦ ምዕራባውያኑን ስለጠቀማቸው ምክንያት እኛንም ይጠቅሙናል በሚል ምኞት እየሞከርናቸው ነገር ግን ከእኛ ሀገር ነባራዊ ሁኔታ ጋር ባለመስማማታቸው የምንፈልገውን አይነት ጥቅም ያጣንባቸውን የትምህርት ፖሊሲዎችን በማየት መረዳት ይቻላል።( ነጥቡን ተረድቼው ከሆነ )

  በመጨረሻም መጭው የሲኖዶስ ምልዓተ-ጉባዔ የጠፋው የሚገኝበት ፤ የጎበጠው የሚቃናበት እንዲሆን የፈጣሪ ፈቃድ ይሁንልን ፤ ይህን ከመሰለው የእኛ መውጣትና መውረድ በላይ የእግዜር የቸርነት ስራ ያስፈልገናልና ፊቱን ይመልስልን ፤ እንዲያም እንዲሆን ፊቱን የሚያስመልስ ሥራ በመስራት እንትጋ። ... መምህርም ይህን የመሰሉ ጥናቶችን በመስራት ሂደት ስላገኘህ ድካም ሁሉ መድኃኔ ዓለም ብርታት ይሁንህ ፤ ዋጋንም የምታገኝበት ያድርግህ። ...

  ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

  ReplyDelete
 26. Dear all, Would you please try to print this article and fax/email/distribute it as much as you can to all Mhimenans and Papasat?

  thanks,
  Aklil

  ReplyDelete
 27. Dn.Daniel,

  Wonderful!
  As some of us said,it is better to copy and give it to our holy fathers.

  But my worry is, we all may criticize them now however if most of us happen to be on their shoe we may be much worse.Lets pray not to be bad for our church! That is the solution.

  May God bless the writer again and again!

  ReplyDelete
 28. አሜን ወአሜን!October 5, 2010 at 7:57 AM

  ወንድም ዳንኤል፤ በእውነቱ በጣም የበሰልክ፤ ታታሪና አስተዋይ ሰው ነህ። እግዚአብሔርም በውስጥህ ብዙ የከበረ መዝገብ እንዳስቀመጠ እገነዘባለሁ።ነገር ግን እንደዚህ ዘርፈ-ብዙ ለሆነው ውስብስብ ችግር መሰረቱ፤ የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን እውነተኛና ፍጹም ከሆነው መጽሀፍ ቅዱስ ቃል ውጪ ማፈንገጧ አይመስልህም? የተሐድሶዎችና ወደሌላ እምነት የሚኮበልሉ ወገኖች መበርከታቸው ምክንያቱስ ዋናው ይሔ አይመስልህም? አደራ!! ካንተ ብዙ ይጠበቃል:: ሳትፈራ በውስጥህ እግዚአብሔር ያስቀመጠውን ከማስተላለፍ ወደኋላ እንዳትል።
  እግዚአብሄር ይጠብቅህ።

  ReplyDelete
 29. Can't wait to read Abyssinian's proposal.While it is good to think strategically, we should not wait handcuffed until the second and the third type of people hold the posts and take whatever actions deemed necessary to destroy the church.

  As to the modalities of the implementation, I believe we all can petition to the Holy Synod members to take actions and bring the issue forward and deliberate. If we keep on the momentum, I believe they would hear us sooner or later; besides not all members of the Synod are of the second or the third type nor the first. There are fathers with the necessary intellectual as well as religious capacity to deal with such critical issues.

  one thing that concern me is the uncalled for interference by Government officials, which may deter the implementability of the proposed changes, the case in point is the beating and intimidation of fathers about a year ago. May Amlake Kidusan end this mess, Amen!

  ReplyDelete
 30. God bless U!
  This message is timely.

  ReplyDelete
 31. የቀረበው የመፈተሄ ሀሳብ መልካመ ነው ሁለት ጥያቄ ግን አለኝ
  ፪)የመዋቅር ቸግር ነው ወይ ዋናው ቸገራአ?
  ፩)ቤተ-ክርስትያን አሁን ይህን ለማስተናገድ ዝግጁ ናት ወይ?
  ማለቴ ይሀን ለመተገባር መቅደም ያለበት ነግረ የለም ወይ ?አሁን ያለው በትክክል ቢሰራ ከተጠቀሱት ስረውቸ ብዙወች በተሰሩ ነበረ ለዚህ ማሳያ አንድሆን ከተባሉት መዋቅሮች ውስጥ ለምስሌ የሊቃውንት ጉባዓ ዛር ባለው መዋቅርም አለ
  ‘ የዶግማ እና የቀኖና ጉዳዮች
  የቅድስና እና ቅዱሳት መጻሕፍት ጉዳዮች
  የካህናት እና የክህነት ጉዳዮች ‘
  እነዚህን አሁን የሊቃውንት ጉባዓ ስልጣን ያለው ይመስለኛል ነገር ግን አሁንም አንዳድ ቸግሮቸ አሉ ለምን መፈተሃ መስጠት አልቻለም ?ስለዚህ ከመዋቀር በፈት መሰረት ያለባት ነግረ አለ ማለት ነው፡፡
  ሌላው ደግሞ የቀረበውን የመፈተሃ ሀሳብ እዘህ ከማቅረብ ባለፋ ለሜመለከተው አካል ማቅረብ ትልቅ ስራ ስለሆነ መታሰብ አለባት ሁላችንንም የድረሻችንነ መወጣት አንድንችል ፡፡

  ReplyDelete
 32. ዘጋስጫ
  ሁሉም አስተያቶች፣ሃሳቦች፣…..ምክሮችም፤በተለይም ደግሞ የዲ.ን ዳንኤል ክብረት መወያያ እይታዎች እጅግ በጣም ግሩም ናቸው፡፡ ግን ይህንን ሁሉ የተጻፈውን ሆኖ የሚገኝ (የማያስመስል) ምዕመን፣አባት፣ዲያቆን፣ካህን፣ተራ ወይም ጨዋ ሰው፣… ስለሆነ የጠፋው አምላካችን እደ ኃጢአታችን ብዛት፤እንደ በደላችን ክፋት፣…ሳይቆጥር ስለ እመቤታችን ወላዲተ አምላክና ስለ ሊቀ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ብሎ አስራት የገባላትን ሃገራችንን ኢትዮጵያን መልካም ሰው፣መልካም አባት፣ መልካም ልጆች…፤…፣…. ይስጣት፡፡

  ReplyDelete
 33. ወንድሜ ዲን ዳንኤል ሰላም ላነተ ይሁን፡፡ ስላካፈልከን ሃሳብም በበረከቱ ያትረፍርፍህ!
  በመሠረተ ሃሳብ ደረጃ ቤተክርስቲያኒቱ ያለችበት የችግር ክምር እንዲህ በቀላሉ ተዘርዝሮ የሚያልቅ ባይሆንም ለመወያያ ያህል በቂ ጉዳይ ተነስቷል፡፡ የመፍትሄ ሃሳቦችህን ግን መሬት ለማውረድ መቅደም ያለባቸው ጉዳዮች ያሉ ይመስለኛል፡፡
  1) ችግሮቹ ምንድናቸው ( መዋቅራዊ፣ የአሠራር፣…)
  2) የችግሮቹ ምንጮች የትኞቹ ናቸው (ውስጣዊ፣ ውጫዊ፣ ግለሰባዊ፣ የቡድን ወዘተ)
  3) የመፈትሔ ሃሳቦች ከየት ሊገኙ ይችላሉ (ከተለያዩ ወገኖች የተወከሉ የመማክርት ጉባኤ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል)
  4) ምን የመፍትሔ ሃሳብ አለ (ሪኮመንዴሽንስ)
  5) የመፍትሔ ሃሳቦቹን እንዴት በሥራ ላይ ማዋል ይቻላል (ማኑዋል)
  እነኚህን መሠረታዊ ጥያቄዎች መመለስ ስንችል የቤተክርስቲያኒቱም ችግር በሂደት ይቃለላል፡፡ ከዚህ በፊት እድሉን አግኝቼ ለመጠቆም እንደሞከርኩት፤ ለችግሮቻችን የምር መፍትሔ ለማምጣት ምናስብ ከሆነ ከግለሰባዊ አስተያየቶች እና ምክር በኋላ ተቋማዊ በሆነ መልኩ በትናት ላይ የተመሰረተ ዬሁንታ ሃሳብ (ፐሮፖዛል) ማምጣት አለብን፡፡ ያለበለዚያ እኔ ባይ ተጠያቂ በሌለበት እና የሥራው መነሣ እና መድረሻ ሳናውቀው ወሃ ስንወቅጥ መኖራችን ይቀጥላል! መሐረነ ክርስቶስ !!!

  ReplyDelete
 34. D.Dani baayee yaadafudhatama waan ta'eef waaqayyo eebba isaa siif haaba'isu. Garuu "Adaamiin ollaa hagamsaa jirtu himimaan ishee hin qooru jedhama mitiiree" akkas ta'e waldaan A.O.ETH.

  ReplyDelete
 35. አሁን አሁን እኮ በዚህ በውጭ አገርና በተለያዩ ቦታዎች ያሉ መነኮሳት አባቶች ሁሉም
  ራሳቸውን ቆሞስ አድርገው ቀርበዋል። በቅዳሴ ላይ እንኮን በእደ ከብሩ ካህን ከመ ይባርከነ
  ሲባል ደስ አይላቸውም። ነገ እነዚህ መነኮሳት ሃይ የሚላቸው ከአ ሁኑ ከጠፋ ራሳቸውን ጳጳስ አድርጓ ከዚያም በላይ ለመውጣት ምን ያቅታቸዋል። ዳኒ ይህ ጽሁፍህ በቤተ ክርስቲያናችን ላለው ችግር መፍትሔ አመላከች ነው ግን ምን ያህል አባቶች ያዩታል።

  ReplyDelete
 36. Completely agree. The Synod needs better structure to get things done and to strengthen our church.

  Have you presented this to the holy Synod? What is the purpose of this article? ሰላማዊ ሰልፍ እንውጣ ይህ ነገር እንዲታሰብበት እና ትክክለኛ ስራ የሚስራ ሲኖዶስ እንዲፈጠር? ሆዳችን ከማረሩ በቀር እኛ ምን እናደርጋለን? ምን እናርግ? ሲኖዶሱን እንጠራጠረው? ሲኖዶሱን መክተል እናቁም? ወይስ እንድንጸልይ ነው? Or do you just want us to know that you got great ideas? What is the solution.....

  ReplyDelete
 37. Dear Eyob. G

  በጣም የምታሳዝን ሰው ነህ። ተቃዋሚ ብቻ ለመሆን የተፈጠርክ ትመስለኛለህ (የሰው ሃሳብ በጭራሽ የማይጥምህ)። መልካሙ ሀሳብና መፍትሄ እፊትህ እያለ ሁልጊዜ ጸጉር እየሰነጠክ ነጩን የምታጠቁረው ለምንድነው "አያ ጅቦ ሳታማሃኝ ብላኝ" ያለችው አህያዋ ትዝ አለችኝ።

  ReplyDelete
 38. THE SOLUTION IS WITH IN THE HAND OF GOD.SO LET US ASK HIM WITH HIS MOTHER.GOD BLESS NOT ONLY OUR CHURCH BUT ALSO ETHIOPIA.

  ReplyDelete
 39. Dani Berta if they are able to listen.Thank u.

  ReplyDelete
 40. Dear Eyob.G

  you think that Dn.Daniel reveled the churches father sin to all people.

  But our sin is in-front of the world.now a days our spiritual fathers has committed their sin in the eyes of all the people.what is the need to cover them ? mabedehin mekeble alifeligim kalalek besteker.

  ReplyDelete
 41. እግዚአብሔር የበጎ ሃሳብህን ፍሬ ለማየት ያብቃን፡፡ አንተንም ለቅድስት ቤተክርስቲያን እውነተኛ ሰው አድርጎ ያጽናህ፡፡ ፍፃሜህን ያሳምርልህ፡፡

  ReplyDelete
 42. The analysis and recommendations presented by Memher Daniel deserve our fullest appreciation. In general, EOTC desperately needs a comprehensive overhaul of its institutional arrangement to suit the urgent needs of the 21st century.

  The ideas presented in the paper are worthy of a careful consideration. However, I suggest that the following important items have been lest out:

  (a) Need for a capacity to enable EOTC to perform its main task of evangelization in a much more effective manner (yesebkete-wongael wanna kefel);
  (b) Establishment of a much stronger Planning & Programming Division in order to formulate EOTC's vision, objectives as well as its long-, mediu-, and short-term plans and programs (ye-eqqidenna yeprogram wanna kefel);
  (c) An effective capacity to perform an internal and external auditing system and capacity to ensure the fullest accountability and transparency.

  In addition, what I wish Mem. Daniel included in his piece was the actual qualification demanded from bishops in sister churches such as the Copts, Armenians, and Indians.

  I suggest that a follow-up article be produced by Mem. Daniel taking into account the various observations and ideas presented in response to his paper.

  ReplyDelete
 43. I wonder if you have seen a document if Dn. Daniel has seen EOTC's bylaw re the Synod, entitled:
  "....YeEthiopia Orthodox Tewahedo Bete Kr'stiyan Q'ddus Sinodos ye1991 A/M H'ggae Bete Kristiyan..."

  Your article has no reference to the important document without which the subject would not have a comprehensive coverage.

  Secondly, you may wish to see an open letter to the Holy Synod on various issues including the items you raised by checking the following website:

  www.eotcipc.org

  Best wishes.

  ReplyDelete
 44. I have something to say.

  My brother who ask for a solution and challenge Dani, if you forwarded this idea positively it is good; but it doesn't seem.

  I want to forward some of my personal opinions:

  1. You have said that "hodachin kemareru beker ..." - waht if you get burn for your mother church, are you not her son? and do you know that frequent discussion and information exchange have the power to change your behavior and push you to involve and act?

  2. again You have said that "Have you presented this to the holy Synod? ..." - do you think that the holly senod is the only body for being part of the solution? what is your share? have you realized the importance of information in this article to make active and respondent?

  3. You have Asked for "the purpose of this article" - my brother do you have any idea about communication? this is one way of advocating and mobilizing the christian community and those who are responsible and concerned ... in addition, you need to have an information that many senod members, church fathers, many christians have direct or indirect access to these articles.

  "BE PART OF THE SOLUTION, NOT PART OF THE PROBLEM; BECAUSE WE HAVE IT ENOUGH."

  Thank you for understanding my opinion positively.

  ReplyDelete