የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሠረታዊ ዓላማዋ ከሆነው ስብከተ ወንጌልን የማስፋፋት ተልዕኰዋ በተጨማሪ ለሕዝቡ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ባሕላዊና ኤኮኖሚያዊ ዕድገት ከፍተኛ ሚና ተጫውታለች፡፡ የተጠናከሩ ማኅበራዊ ተቋማት ባልነበሩበት ጊዜ የኅብረተሰቡን ማኅበራዊ ዋስትና ሊያስጠብቁ የሚችሉ ተግባራትን ፈጽማለች፡፡ ከነዚህ ተግባራት መካከል ዕድር፣ ዕቁብ፣ ሰንበቴ፣ የማስታረቅ አገልግሎት፣ የጋብቻ አገልግሎት፣ የትምህርት አገልግሎት ወዘተ. ይጠቀሳሉ፡፡
ከማኅበራዊ አገልግሎቶቿ መካከል አንዱ ፍትሕ እንዳይዛባ፣ በስሜታዊነት ሕግ እንዳይጣስ፣ ደካሞች በኃይለኞች እንዳይጠቁ ለማድረግ ትሰጠው የነበረው የመማፀኛነት /Asylum/ አገልግሎት ነው፡፡
ተማኅፅኖ /Asylum/
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጓሜ- በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ተማኅፅኖ /Asylum/ ከባላጋራው ሸሽቶ ለመጣ ሰው ፍትሕ ርትዕ እስከ ሚያገኝ ድረስ መጠለያ መሸሸጊያ ወይም የደኅንነት ጥበቃ መስጠት ነው፡፡ ይህ ተግባር ከዘመነ ኦሪት ጀምሮ የነበረ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጥልናል፡፡
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ተናገረው- «ለእሥራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፡፡ ወደ ከነዓን ምድር ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ በስሕተት ነፍስ የገደለ ወደዚያ ይሸሽ ዘንድ የመማፀኛ ከተሞች እንዲሆኑላቸው ከተሞችን ለእናንተ ለዩ፡፡ ነፍሰ ገዳዩ በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ እንዳይሞት ከተሞቹ ከደም ተበቃይ የመማፀኛ ከተሞች ይሁንላችሁ፡፡... እነዚህ ከተሞች በመመካከላቸው ለሚቀመጡ እንግዶችና መጻተኞች መማፀኛ ይሆናሉ» /ዘኍ.35÷9-15/፡፡
እነዚህ ስድስት ከተሞች ኬብሮን፣ ሴኬም፣ ቃዴስ፣ ቦስር፣ ራሞት፣ ጎላን ይባላሉ /ኢያ.20÷7-9/፡፡ በነዚህ ከተሞች መሠዊያዎች ነበሩ፡፡ ተማፃኙ ሰው የመሠዊያውን ቀንድ ይይዛል 1ነገሥት 1÷30/፡፡
በዘመነ ብሉይ በእነዚህ የመማፀኛ ከተሞች በመጠቀም ብዙዎች ከደም ተበቃዮቻቸው ተርፈዋል፡፡ ለምሳሌም ያህል ንጉሥ ዳዊት መንግሥቱን ለልጁ ለጠቢቡ ሰሎሞን ባስረከበ ጊዜ ዳዊት ሳያውቅ በራሱ ጊዜ የነገሠው አዶንያስ ፈርቶ የመሠዊያውን ቀንድ ያዘ፡፡ መልእክተኛም ልኰ ንጉሡ ሰሎሞን በሠራው ጥፋት ተበቅሎ እንዳይቀጣው ምሕረትን ለመነ፡፡ ሰሎሞንም «እርሱ አካኼÄ#ን ካሣመረ ከእርሱ አንዲት ጠጉር እንኳን በምድር ላይ አትወድቅም» ብሎ ቃል ስለ ገባለት /1ነገሥት 1÷32/ ከቅጣቱ ሊተርፍ ችሏል፡፡
በሌላም በኩል የመሠዊያውን ቀንድ ይዞ የተማፀነው ኢዮአብ እንደ አዶንያስ ሳይተርፍ በሰሎሞን ትእዛዝ ተገድሏል /1ነገሥት 2÷28-35/፡፡
ተማኅፅኖ በኢትዮጵያ
- ኢትዮጵያ ብሉይ ኪዳንን ተቀብላ የኖረች ሀገር እንደ መሆንዋ ይህ ሥርዓት ወደ ሀገሪቱ ገብቶ የሥርዓቷና የባሕሏ አካል ሆኖ የቀጠለ ይመስላል፡፡ በስድስተኛው መ.ክ.ዘ የዓረቢያ ቆሪሾች የነቢዩ መሐመድን ተከታዮች ባሳደዷቸው ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ጥገኝነት /Asylum/ ጠየቁ፡፡ በወቅቱ ንጉሥ የነበሩት ንጉሥ አርማሕ የሳዑዲ ዐረቢያ ገዥዎች ስደተኞቹን አሳልፈው እንዲሰጧቸው ቢጠይቋቸውም በሀገሪቱ ነባር ሥርዓት መሠረት ተማፃኝን ለባላጋራ መስጠት ክልክል በመሆኑ አሳልፈው አልሰጧቸውም፡፡ ይህም ቤተ ክርስቲያኒቱ ለሀገሪቱ ሥርዓተ መንግሥት ካበረከተቻቸው ደንቦች አንዱ በመሆኑ ነው፡፡
በሌላም በኩል ይህን የኢትዮጵያን ሥርዓት ያወቁ ብዙ ክርስቲያኖች በሀገራቸው የሃይማኖት ስደት በተነሣ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንደ ሀገሪቱ ዜጎች ለመኖር ችለዋል፡፡ በኬልቄዶን ጉባኤ ምክንያት በተዋሕዶዎች ላይ በአውሮፓ፣ በታናሽ እስያና በመካከለኛው ምሥራቅ የተነሣውን ስደት ሸሽተው የመጡት ተሰዓቱ ቅዱሳን ታሪክ ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው፡፡
በየጊዜውም ግብፆች፣ የመናውያን፣ አርመኖች፣ ሕንዶች ወዘተ. ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በዚህ ሥርዓት ኖረዋል፡፡ ለምሳሌ በአጼ ዳዊት ዘመነ መንግሥት የነበረውና ለበልበሊት ኢየሱስ ገዳም መመሥረት አስተዋጽዖ ያደረገው የመናዊው ነጋዴ ፊቅጦር፣ በ10ኛው መክዝ ኢትዮጵያ ውስጥ በጥገኝነት የነበረውና በኋላም ጵጵስና ለእኔ ይገባል እያለ ያስቸግር የነበረው አብዱን የተባለው ግብፃዊ፣ በ10ኛወ መክዘ በቱርኮች ወረራ በተነሣው ስደት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በየገዳማቱ የገቡት አርመኖች፣ በአጼ ምኒሊክ ዘመን የመጡትና በባለሟልነት ደረጃ ባለ ርስት ለመሆን የበቁት ሐጂ ቀዋስ [ ሐጂ ቀዋስ ከሕንድ የመጡ አርክቴክት ናቸው፡፡ ከአጼ ምኒሊክ ጋር የተገናኙት አንኮበር ነው፡፡ እዚያ ብዙ ሕንፃ ገንብተዋል፡፡ ሚስታቸው ሞታባቸው ከሰንዳፋ ሐሊማ የተባለችውን አገቡና ልጅ ወለዱ፡፡ ነገር ግን ሚስታቸውና ልጃቸው በ1910/11 በእንፍሉዌንዛ ሞቱባቸው፡፡ አማርኛ አጣርተው የሚናገሩት ሐጂ ቀዋስ ከምኒልክ ጋር ከመግባባታቸው የተነሣ እንደ ባለሟል ይታዩ ነበር፡፡ ብዙ መሬትም ተሰጥቷቸዋል፡፡ ከሕንድና ከየመን ዕቃ እያስመጡ የሚሸጡበት ትልቅ ሱቅ አዲስ አበባ ውስጥ ነበራቸው፡፡ መጀመርያ ባሻ ወልዴ ሠፈር በኋላም ደጃች ነሲቡ ሠፈር ይኖሩ ነበር ፡፡ከአዲስ አበባ አዲስ ዓለም የሚያመላልስ በበሬ የሚጎተተት ጋሪ ሠርተው ነበር፡፡ በ1905 ዓም አርፈው ጉለሌ ተቀበሩ፡፡] የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንና የተማኅፅኖ አገልግሎት
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለሕዝቡ ትሰጣቸው ከነበሩት አገልግሎቶች አንዱ የመማፀኛ ቦታ በመሆን ማገልገል ነው፡፡ በተለይም ገዳማትና አድባራት በሚደበሩበትና በሚገደሙበት ጊዜ ንጉሡ በአካል ተገኝቶ ወይም ደግሞ እንደ ራሴውን ልኰ
«ይህ ቦታ ዳሩ እሳት መሐሉ ገነት ይሁን፤ ከዛሬ በኋላ ማንኛውም የሀገር ገዥ የዚህን ደብር ክብር እንዳይሽር፡፡ አበሉንም በጉልበት እንዳይቀማ፡፡ በጳጳሳቱ አንደበት የተወገዘ ይሁን፡፡ በስሕተት ለገደለም መማፀኛ ይሁን» በማለት ያውጃል፡፡ ጳጳሱም ዐዋጁን በግዝት ያጸኑታል፡፡ ወዲያውም ጸሐፊ ተመርጦ ቃሉን በደብሩ ወንጌል ዳር ያሠፍረዋል፡፡ ንጉሡም ማኅተሙን ያትምበታል፡፡
ከዚህ በኋላ የደብሩ ክልል ተብሎ የተከለለው አካባቢ ሁሉ የመማፀኛ ቦታ ይሆናል፡፡
የተማኅፅኖ አጠያየቅና አፈጻጸም
1. ወደ ደብሩ/ገዳሙ ክልል የገባው ተማፃኝ ደወል ይመታል፣
2. ጉዳዩን ለካህናቱ ያስረዳል፡፡
3. ካህናቱ/መነኰሳቱም ምግብና መጠለያ ሰጥተው ከጥቃት ያስጠብቁታል፣
4. ጉዳዩን በእርቅ ለመፍታት ከተቻለ ከባለጋራው ያስታርቁታል ካልተቻለ ግን ፍርድ ሊያገኝ ወደሚቻልበት ቦታ ያደርሱታል፡፡ ከዚያ ውጭ ባላጋራው ወይም ደመኛው እጁን ስጡኝ ብሎ ቢጠይቅ ካህናቱ /መነኰሳቱ አሳልፍው ላለመስጠት ዐቅማቸው የፈቀደውን ያህል ተጋድሎ ያደርጋሉ፡፡ ከዐቅማቸው በላይ በሆነ ኃይል ካልተሸነፉ በቀር አሳልፈው አይሰጡም፡፡
የተማኅፅኖ አፈጻጸም በሦስት አድባራት/ገዳማት
ጨለቆት ሥላሴ / ትግራይ/
ጨለቆት ሥላሴን ያስተከሉት ራስ ወልደ ሥላሴ ሐምሌ አራት ቀን 1785 ዓ.ም የደብሩ ቅዳሴ ቤት ሲከበር «እንበለ ቀዳሲ ኢይባእ ነጋሢ» በማለት ዐውጀው ነበር፡፡ በዚህ ዐዋጅ ላይ «በቦታው ገብቶ የደወል ወንጀለኛ ይማራል» የሚል ሥልጣን ለደብሩ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም የተነሣ ዐዋጁ በተነገረበት ሰሞን ነፍስ ገድሎ ሸፍቶ የነበረ ሽፍታ መጥቶ ደወል መታ፡፡ በአካባቢው የነበሩት ራስ ወልደ ሥላሴም ለባለደሞቹ ካሣ ከፍለው አስታርቀውታል፡፡ ለብዙ ዘመናትም የአካባቢው መማፀኛ በመሆን አገልግሏል፡፡
ጨለቆት ሥላሴን ያስተከሉት ራስ ወልደ ሥላሴ ሐምሌ አራት ቀን 1785 ዓ.ም የደብሩ ቅዳሴ ቤት ሲከበር «እንበለ ቀዳሲ ኢይባእ ነጋሢ» በማለት ዐውጀው ነበር፡፡ በዚህ ዐዋጅ ላይ «በቦታው ገብቶ የደወል ወንጀለኛ ይማራል» የሚል ሥልጣን ለደብሩ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም የተነሣ ዐዋጁ በተነገረበት ሰሞን ነፍስ ገድሎ ሸፍቶ የነበረ ሽፍታ መጥቶ ደወል መታ፡፡ በአካባቢው የነበሩት ራስ ወልደ ሥላሴም ለባለደሞቹ ካሣ ከፍለው አስታርቀውታል፡፡ ለብዙ ዘመናትም የአካባቢው መማፀኛ በመሆን አገልግሏል፡፡
ማኅደረ ማርያም /ደቡብ ጎንደር/
በተለይም የደቡብ ጐንደርዋ ማኅደረ ማርያም በዘመነ መሳፍንት ከፍተኛ የመማፀኛነት አገልግሎት ትሰጥ ነበር፡፡ ዐፄ ሠርፀ ድንግልና እቴጌ ማርያም ሥና በ1589 ዓ.ም ሲደብሯት አቡነ ማቴዎስና እጨጌ ዮሐንስ በተገኙበት «መሐሏ ገነት ዳሯ እሳት ይሁን፣ የመማፀኛ ቦታ ትሁን፡፡ ማንም በኃይል አይድፈራት፤ የወደቀ አይነሣባት የተተከለ አይቆረጥባት» ተብሎ ታውጆ ነበር፡፡
በዚህም የተነሣ ብዙ መኳንንትና መሳፍንት በደብርዋ ክልል ቤት ሠርተው አስቀምጠው ነበር፡፡ በመከራ ጊዜ ለመጠለል፡፡ ለምሳሌም ያህል ንጉሥ ወልደ ጊዮርጊስና ራስ ጉግሣ ወሌ በደብሯ የመማፀኛ ቤቶች ነበሯቸው፡፡
በዚህች ደብር ተማኅፅኖ ያቀረቡት የመጀመርያው ባለ ሥልጣን አቤቶ ኃይሉ ናቸው፡፡ አቤቶ ኃይሉ ከንጉሥ ተክለ ጊዮርጊስ ጋር ተጋuተው ጐጃም ቡሬ ታስረው ይኖሩ ነበር፡፡ አቤቶ ኃይሉ ከቡሬ አምልጠው ማኅደረ ማርያም ገብተው ተማፀኑ፡፡ ካህናቱ በደብሩ ካስጠለሏቸው በኋላ ወደ ላስታ ዘመዶቻቸው ዘንድ እንዲሄዱ አደረጉ፡፡ ይሁን እንጂ በዚያም ሊመቻቸው ባለመቻሉ ተመልሰው ወደ ማኅደረ ማርያም መጥተው ለአራት ዓመታት በጥገኝነት ተቀምጠዋል፡፡
ራስ ዓሊ አሊጋዝ ከበጌምድሩ ገዥ ራስ ወልደ ገብርኤል ጋር ተጣልተው ማኅደረ ማርያም ሲገቡ ራስ ወልደ ገብርኤል መጥተው ለመውሰድ ጠየቁ፡፡ የማኅደረ ማርያም ካህናት ግን ፈጽመው ተቃወሙ፡፡ ራስ ወልደ ገብርኤል የደብሩን መብት ተጋፍተው በመግባት ራስ ዓሊን አሥረው በወታደር አስጠበቋቸው፡፡ ራስ ወልደ ገብርኤል መርሐ ቤቴ ዘምተው ከባላምባራስ አሥራት ጋር ባደረጉት ጦርነት ድል ሆኑ፡፡ በዚህ ጊዜ ካህናቱ ራስ ዓሊን ፈትተው ነጻ አወጧቸው፡፡
የትግሬና የሰሜን ገዥ ደጃች ውቤና የጐጃሙ ገዥ ደጃች ጐሹ በራስ ዓሊ ላይ በተነሡ ጊዜ የራስ ዓሊ ባለቤት ወ/ሮ ኂሩት የራስ ውቤ ልጅ በመሆናቸው ፈርተው ማኅደረ ማርያም ገቡ፡፡ ራስ ዓሊ ድል ሲሆኑ ደጃች ውቤ መጥተው ወ/ሮ ኂሩትን ለመውሰድ ጠየቁ፡፡ የማኅደረ ማርያም ካህናት ግን ድርጊቱን ተቃወሙት፡፡ በኋላ ላይ ግን በኃይል ገብተው ወ/ሮ ኂሩትን ወሰዷቸው፡፡
በአይሻል ጦርነት ሰኔ 22 ቀን 1846 ዓ.ም ዐፄ ቴዎድሮስ ራስ ዓሊን ድል ሲያደርጉ ራስ ዓሊ ማኅደረ ማርያም ገብተው ተማፀኑ፡፡ በዚያም ለጥቂት ጊዜ ቆይተው ወደ የጁ ዘመዶቻቸው ዘንድ ሄደዋል፡፡ የማኅደረ ማርያም ካህናት ራስ ዓሊን ከኃይ ለኛው ከዐፄ ቴዎድሮስ በመደበቃቸውና አሳልፈው ባለመስጠታቸው ምክንያት ንጉሡ ካህናቱንና ሊቃውንቱን አርደዋል፡፡
ዋልድባ /ሰሜን ጎንደር/
በመማፀኛ ቦታነት የታወቀው ሌላ ቦታ ደግሞ የዋልድባ ገዳም ነው፡፡ የነገሥታቱ ዘመን አልፎ ዘመነ መሳፍንት ሲተካ ፈጻሜ መንግሥት ተክለ ጊዮርጊስ የተጠለሉት በዋልድባ ስቋር ገዳም ነበር፡፡ በኋላም የገዳሙ መናኒ ሆነው በዚያው ቀሪ ሕይወታቸውን አሳልፈዋል፡፡ መናኔ መንግሥት ተብለው የሚጠሩት ንጉሥ ተክለ ጊዮርጊስም ከዘመነ መሳፍንት የመኳንንቱ መገዳደል የተረፉት በዋልድባ ስቋር ተማIነው ነው፤ በኋላም በ1769 ዓ.ም መንኩሰው በዚያው ዐርፈዋል፡፡
በመማፀኛ ቦታነት የታወቀው ሌላ ቦታ ደግሞ የዋልድባ ገዳም ነው፡፡ የነገሥታቱ ዘመን አልፎ ዘመነ መሳፍንት ሲተካ ፈጻሜ መንግሥት ተክለ ጊዮርጊስ የተጠለሉት በዋልድባ ስቋር ገዳም ነበር፡፡ በኋላም የገዳሙ መናኒ ሆነው በዚያው ቀሪ ሕይወታቸውን አሳልፈዋል፡፡ መናኔ መንግሥት ተብለው የሚጠሩት ንጉሥ ተክለ ጊዮርጊስም ከዘመነ መሳፍንት የመኳንንቱ መገዳደል የተረፉት በዋልድባ ስቋር ተማIነው ነው፤ በኋላም በ1769 ዓ.ም መንኩሰው በዚያው ዐርፈዋል፡፡
ማጠቃለያ
ቤተ ክርስቲያን ትሰጣቸው ከነበሩ ፈርጀ ብዙ ማኅበራዊ አገልግሎቶች አንዱ የሆነው የመማፀኛነት አገልግሎት በአሁኑ ጊዜ እምብዛም ሲተገበር አይታይም፡፡ አንዳንድ ሰዎች ከ1966 ዓ.ም በኋላ የቀረ ይመስላል የሚል አመለካከት አላቸው፡፡
ይህ አገልግሎት ፍትሕ ርትዕ እንዳይጓደልና መበቃቀል በፍርድ ምትክ ቦታውን እንዳይዝ ያደርጋል፡፡ በግርግርና በፀጥታ መታወክ ጊዜ የሰው ሕይወት በቀላሉ እንዳይጠፋ ክፉውን ዘመን ለማለፍ ያገለግላል፡፡ በመሆኑም ኅብረተሰቡ ይህንን በመረሳት ላይ ያለ አገልግሎት እንዲያስታውሰውና እንዲጠቀምበት ቢደረግ መልካም ነው፡፡ ይኽም፡
በተለይ በገጠር የሚገኘውን በመበቃቀል መገዳደል በመቀነስ ሰዎች በሕጋዊና በሕጋዊ ፍርድ ብቻ መብታቸውን እንዲያጡ ያደርጋል፤
በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመቀነስ የተበደሉ ሴቶች ወይም በደል ሊደረስባቸው የታሰቡ ሴቶች ተማጽነው ፍትሕ እንዲያገኙ ያደርጋል፤
በሀገሪቱ ሰላም በሚናጋበት ጊዜ በባለሥልጣናት እና ሕዝቡ መካከል መገዳደል እንዳይኖርና ሰላም ነግሦ ፍትሕ እስኪሰፍን ድረስ ፖለቲካዊ ጥላቻ እንዳይባባስ ያደርጋል፡፡
ዋቤ መጻሕፍት
ተክለ ጻድቅ መኩሪያ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ ከዐፄ ልብነ ድንግል እስከ ዐፄ ቴዎድሮስ፣ 1953፣ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት
ልሳነ ወርቅ ገብረ ጊዮርጊስ /መሪጌታ/፣ ጥንታዊ ሥርዓተ ማኅሌት ዘአቡነ ያሬድ፣
መቕሌ ንዑስ ማዕከል፣ ዝክረ ጽዮን /መጽሔት/፣ 1994 ዓ.ም
መቕሌ ንዑስ ማዕከል፣ ዝክረ ጽዮን /መጽሔት/፣ 1994 ዓ.ም
«መጽሐፈ ታሪክ ዘማኅደረ ማርያም» በደብሩ የሚገኝ
በሪሁን ከበደ፣ የዋልድባ ገዳም ታሪክ፣ 1983 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ
Tareqegn Yibabe, The History of Mahidere Maryam. CA. 1596-1939. AAU. May 1988 (BA Thesis)
H.Welde. Bludeu. Royal Chronicle of Abyssinia 1769-1840 (Cambridge, 1922)
Allen C.Myers. EErdmans Bible Dictionary. (Grand Rapids, Michigan 1987)
ቃለሕይወት ያሰማልን
ReplyDeleteረጅም ዕድሜ ከጤና ጋር ያድልልን
አግዚአብሔር ይባርክህ ዲያቆን ዳንኤል ።
ReplyDeleteድሮማ ነበረ አሁን የት ተኘና መማፀኛ። የደሮዎቹ ሰለ ሕዝቡ ታረዱ ሞቱ የዛሬዎች ረዶቸው ገደሉዋቸው ሆነና ምን ይድረግ ?
THIS STORY REMINDS ME WHAT HAPPENED IN 1993 E.C. WHEN AAU UNIVERSITY STUDENTS ENTERED IN ST. MARY CHURCH(we can consider it as an asylum?), THE POLICE TOOK THEM FORCIBLY. THE CHURCH WAS HIGHLY CRITICIZED. BUT IF THE CHURCH DELIVERS SUCH HOLY SERVICE, I BELIEVE MANY PROBLEMS COULD BE SOLVED. THE MAJOR PROBLEMS ARE THE CHURCH LOST ITS GRACE AND THE SPRITUALITY OF OUR FATHERS BECAME DOUBTFUL. thank u dani very much.
ReplyDeleteራስ ዓሊ አሊጋዝ ከበጌምድሩ ገዥ ራስ ወልደ ገብርኤል ጋር ተጣልተው ማኅደረ ማርያም ሲገቡ ራስ ወልደ ገብርኤል መጥተው ለመውሰድ ጠየቁ፡፡ የማኅደረ ማርያም ካህናት ግን ፈጽመው ተቃወሙ፡፡ ራስ ወልደ ገብርኤል የደብሩን መብት ተጋፍተው በመግባት ራስ ዓሊን አሥረው በወታደር አስጠበቋቸው፡፡ ራስ ወልደ ሥላሴ መርሐ ቤቴ ዘምተው ከባላምባራስ አሥራት ጋር ባደረጉት ጦርነት ድል ሆኑ፡፡ በዚህ ጊዜ ካህናቱ ራስ ዓሊን ፈትተው ነጻ አወጧቸው፡፡
ReplyDeleteDn. Daniel Look at the fourth sentence. The one who was defeated by Balambaras Asrat is Ras Wolde Silasie. But, the one who took Ras Ali from Mahidere MARIAM was Ras Wolde Gebriel. So what is the relation b/n Ras Wolde Silasie and Ras Wolde Gebriel or is that a type error?
Thank u very much God bless you.
ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡
ReplyDeleteሃሳቡ ጥሩ ነበር ፡፡ ግን እኔ እንጃ በዚህ ዘመን ሊገድል የመጣው የሚመለስ አይመስለኝም ካህናቱም ደፍረው ተው የሚሉ አይመስለኝም፡፡
ፈሪሃ እግዚአብሔር የለ ፤
ዘመኑ እኮ እልቅ ሙጥጥ ብላል፡፡
I thought what happened in 1993 EC in St. Mary abbey had never done before. I have now learned that is not the case. All the times the priests were unable to protect the asylum seekers so long as the kings are looking for them.
ReplyDeleteGood to know!
I don't think that even the church administration is aware of this fact. A case in point is when the Patriarch allowed the police to take and imprison university students sheltered in "KIDIST MARIAM" church in Addis Ababa. I am disappointed by the falling trajectory of our church and our loss of trust on our fathers
ReplyDeleteደብረ ቁስቋም
ReplyDeleteወንድማችን በእውነት ይህንን የሚያክል ነገር ስላስታወስከንና ስላስተማርከን በጣም እናመሰግናለን.በርግጥ አሁንም ቢሆን ቤተክርስትያናችን የመማፀኛ ከተማ ናት ነገር እኔ እንደማስበው አባቶች{አሁን ያሉት}ክብሯንና ስርአትዋን አላስጠበቁላትም ይህንም በተለያየ ጊዜና በተለያየ ቦታ አይተንዋል.ህግ ቢወጣም አስፈፃሚ ያስፈልገዋል አሁን ችግሩ ህግ አስፈፃሚ ነው የጠፋው.ለማንኛውም ቃለ ህይቀት ያሰማልን በርታ.
ዳኒዬ በአሁን ሰዓት በተሰጣቸው ጸጋ ከሚጠቀሙ ሰዎች አንዱ አንተ ትመስለኛለህ እግዚአብሔር ይህን ጸጋህን እስከመጨረሻው አይውሰድብህ ጨምሮ እንዲሰጥህ ምኞታችን ነው፡፡ ላንተ ያለኝን አድናቆት እንዴት መግለጽ እንዳለብኝ አላውቅም በህይወቴ ብዙ እንድለወጥ ነገሮችን በበጎ እንዳስተውልና ለሰዎች ጥሩ አመለካከል እንዲኖረኝ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርገህልኛል በዛሬው ጽሁፍህ ደግሞ ስለቤተክርስቲያናችን አስተዋጽኦ አሳይተኸናል እግዚአብሔር ዕድሜና ጤና ሰጥቶህ ከነቤተሰቦችህ ያቆይህ፡፡ አሜን!ፅ
ReplyDeleteአሁንማ ቤ/ያን ምንም ሳያጠፉም የሚማጸኑባት አልሆነች እኮ
ReplyDeleteየሒወትን ቃል ያሰማልን!
ReplyDeleteበጣም ጥሩ ጥናት ነው፡፡ በተጨማሪ ዋቢ መጻህፍቱን ስላስቀመጥክልን የማንበቡ ሁኔታንም ያበረታታል፡፡
ኪዳነማርያም ዘደብረ ይድራስ
kale hiwot yasemalen!!!!
ReplyDeleteአሁን ባለንበት ዘመን ተማኅፅኖ /Asylum/ ለስንቱ ተነፈገ ስንቱስ ተላልፎ ተሰጠ ?
ReplyDeleteጌታ ለቤተክርስቲያናችን የቀደመ ክብሯን ይመልስላት
A very interesting piece! Thank you.
ReplyDeleteWas it deliberate on your side to include only certain historical episodes of refuge in our beloved church and leave out the recent tragic attacks against Mi'imenan who took refuge at Debre Mariyam in Addis, etc. with the full knowledge of the current Patriarch?
የማኅደረ ማርያም ካህናት ራስ ዓሊን ከኃይ ለኛው ከዐፄ ቴዎድሮስ በመደበቃቸውና አሳልፈው ባለመስጠታቸው ምክንያት ንጉሡ ካህናቱንና ሊቃውንቱን አርደዋል፡፡
ReplyDeleteWas King Theowodros a tyrant leader? .When he was crowned ,he obeyed the church rule .however ,During his regime ,he had killed so many inocent citizines and yet historians admire as if he is the only outstanding leader.
+++
ReplyDeleteእኔ ራሴ ቤተ ክርስቲያን ያላትን የመጠለያነት ታሪክ ስለማውቅ ከአሳዶጃችን ሸሽቼ አዲስ አበባ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለመጠለል ከሞከሩት መካከል ነበርኩ፤ የወሬው ጫፍ ጫፉ ስለሰማን ግማሾቻችን ቀድመን ብንወጣም ምን ያደርጋል ወንድሞቻችንን ሰውዬው ለጅብ መንጋጋ አሳልፈው ሰጧቸው! ስለዚ ሕዝቡ ሳይሆን ነገሥታቱና ነገሥታቱን የሚቀቡት ናቸው ታሪኩን የረሱት!
Qale hiwoten yasemalen !!!
ReplyDeletedes yemil tseuf teru meleket new
YEFETERN AMELAK YEMEMATEGA marefiya aysatan Amen
leanetem wendem Dani mastewalun tesgawen yabezaleh endeanetem yale mekari; astemari aysatan Amen!!!!!
+++
ReplyDeleteYetwededk wendmachn huulem endamnelaw QHY abzto yagelglot zemn yadlh. Ye enat Betkirstianen bego sera endh masayet lehulachnem telk temhert new. Bezuwach yemimseln betkrstian tela zegeta meba teyakinewan melkam neger senasaye tiru new. If u are in Ethiopian it could be great if u send for Addis Zemen or other government news papaers. Behuulu Amlak yektlh. +++ Ye toronto akbari betsebochn
kal hiwot yasemaleg
ReplyDeleteመጽሐፈ፡ነገሥት፡ቀዳማዊ፣ምዕ.1 ቁጥር፡32 > ቁጥር፡ 52ተብሎ፡ይታረም።
ReplyDelete«እርሱ አካሄዱን ካሳመረ ከእርሱ አንዲት ጠጉር እንኳን በምድር
ላይ አትወድቅም» ብሎ ቃል ስለ ገባለት /1ነገሥት 1÷52/ ከቅጣቱ ሊተርፍ ችሏል፡፡
ዲን ዳንኤል ቃለህይወት ያሰማልን እለት እለት በምትጽፋቸው ጽሁፎች ብዙ ትምህርቶችን እያገኘሁ ኝ ነው። ዛሬ ደግሞ እንድጽፍልህ ያነሳሳኝ በአሜሪካ የሰይጣን በአል የሚባል አለ ታውቀዋለህ ብየ አምናለሁ እናም ይህ ቀን ከመድረሱ ቀደም ብሎ ሱቆች ሁሉ በሚያስፈራራ ነገር ይሞላሉ በአሉን የሚያከብሩ ሁሉ ያን አሰቃቂ ምስል በመግዛት እንደሀገራቸው ባህል ያከብራሉ። ዋናው እኔየምጠይ ቅህ ኢትዮጵያዊ ሆነው የራሳቸው ሀይማኖት፤ባህል እያላቸው ልጆቻቸውን ለዚህ አይነት ድርጊት ከሚያለቅሱ በሚል ስበብ ለሚያጋልጡ ምን ትመክራለህ ። አንዳንዶች ባለማወቅ ሲሳሳቱ ይታያሉና።
ReplyDeleteዳኒ ይህ መጣጥፍ ባለፈው ካልተሳሳትኩ 1993 ዓ.ም የዩንቨርሲቲ ተማሪዎችን የእኛ ‘’አባት’’ ተብየው በቤተክርስቲን ተማኅፅኖ የጠየቁ ተማሪዎችን አማሌቃውያኑና መሀመድአውያኑ አሳልፈው ሳይሰጡ በቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ተጠልለው የነበሩ ተማሪዎችን አሳልፈው ሰጡ!! ለመሆኑ እሳቸውም ሆኑ ሌሎች ‘’ጳጳሳት’’ ይህንን የውቁት ይሆንን? እጠራጠራለሁ!! የሚያውቁት ስንት ቤት እና ብር እንጂ እንዲህ አይነት ቁምነገሮችን መተግበርማ እንዴት ተብሎ ይሞክሩታል!!
ReplyDeleteዲምፕል
ዳኒ ሀሳቡ ያሥማማናል በእውነት ግን የቤታችን አስተዳደር ይህን ማህበራዊ ስራ ቀርቶ ሀይማኖትን ጠብቆ ማስጠበቅ እኮ አቅቶታል ባይሆን ዳኒ ስለ ዔልዛቤል ፃፍ ምእመኑ በርሳ የቤተ ክርስቲያን አመራር ተቃጥላል(የአዋሳ) እባክህ ዳኒ .....ፃፍ
ReplyDeleteቃለ ህይወት ያሰማልን መምህራችን! በ1993 ዓ.ም ከቅድስት ማራያም ከተጋዙት ውስጥ አንዱ ነኝ። በዕለቱ እንደመጠለያነት የቀረቡ ሌሎች ምርጫዎችም ነበሩ። ከሁሉም ትሻላለች የተባለችው ግን ቤተክርስቲያን ነበረች። ትሻላለች ተብሎ የታመነበትም አንተ በደንብ ያብራራህልን የአሳይለም አስተምህሮ በግቢ ጉባዔ አስተባባሪዎች ስለተነገረ ነበር። በቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን የተሰበሰብነው ሃይማኖት ሳይለየን ነበር። መስሊምናፕሮቴስታንት ጋደኞቻችንም አብረውን ነበሩ። የህዝቡ እንክብካቤ እና የቤተክርስቲያን እጣን መዓዛ አስደሳች እና እንኳንም የዚህች ሃይማኖት ተከታይ ሆንኩ ያሰኘን ነብር። ግና..... ተስፋችን እና በእናት ቤተክርስቲያን ላይ የነበረን ተስፋ ከሰዓታት አልዘለቀም። ቅዱስ ፓትርያርኩ እና አባቶች አሳልፈው ሰጡን!!! እኛም አዘንን። ተሰበርን። የሰበረን እስሩ ሳይሆን የቤተክርስቲያን መደፈር ነበር። በዚህም የተነሳ ጥቂት የማይባሉ የግቢ ጉባዔ አባላት ላይመለሱ ተለዩን። ሌሎችም በቤተክርስቲያን ላይ ምላሳቸውን አስረዘሙ። ህግ ዶግማ ቀኖና... ጠብቆ የሚያስጠብቀው ካልተገኘ ምን ዋጋ አለው።
ReplyDelete"...ትንሣኤሽን ያሳየን..."
ተሰዓቱ ቅዱሳን ወደኢትዮጵያ የመጡት ሸሽተው አይደለም። ገድላቸውም ይህን አይልም። በሽሽት ቢሆንማ ኖሮ ሊመጡ የሚገባቸው ዘጠኝ ብቻ ሳይሆኑ ዘጠኝ መቶ ሊሆን በተገባው ነበር።
ReplyDeleteI think in 1993 St Markos Church of Sidist Killo saved many asylum seeker students and we should be greatful for the church.
ReplyDeleteThanks Dn Daniel for reminding us the role of the church as well.
It was at the outside of the main gate of Miskaye-Hizunan Medihanialem church in Addis. One lady was sobbing at 10:00 evening since she has no area to pass the night. I think she came from the country side. The guard of the church, with his merciless order, insulted her and tried her away from the gate. The guard has no spirituality even during at Sunday when most of us go to church. Imagine how the persons around the church are acting!
ReplyDeleteThe administration of this church collects money from educational, health and recreational services and went their vacation to Debre-Zeit to drink and dance. In the mean time, Dn. Zebene Lema collected money from America and gave to this church. All these secular life styles of the church administrators including the so called “papas” forced them from spiritual acts like you discussed above and under your article entitled “SEWOCH LEMIN BEKUMACHEW HAWULT YASERALU?”.
Keep it up Dn. Daneal. God knows, your effort may lead them to NESEHA.
God Bless You,
Gebre-Georgis
ዛሬ ዘመኑ ጋኖቹ አልቀው ምንቸቶች የተሾሙበት በመሆኑ፤ ቤተክርስቲያኒቱ እንኳንስ ለምእመኖቿ ለጳጳሳቷ መሸሻ መሥጠት ተስኗታል እኮ !! በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚማር ተማሪ ቢያንስ በየ አራት ዓመቱ ከሚወስዳቸው የጋራ ትምህርት (ኮመን ኮርስ) አንዱ የፖሊስ ዱላ ነው፡፡ ለተማሪዎችን ከፖሊስ ዱላ ማምለጫቸው ታዲያ ቤተክርስቲያኒቱ ሳትሆን የእነ ማዘር ሽሮ ቤቶች መሆናቸውን ኮርሱን የወሰድን እናውቀዋለን፡፡
ReplyDeleteባለፈው ዓመት የቅዱስ ሲኖዶስ ተሰብሳቢ ብጹአን ሊቃነጳጳሳት በ አባ ጳውሎስ ጋንግስተሮች (ወሮ በሎች) ሲደበደቡ ከማየት ሌላ ምን ልብ የሚሰብር ታሪክ መጥቀስ ይቻል ይሆን! የተማኅጸኖ አገልገሎት ድሮ ከባለሥልጣናት ዱላ ለማስጣል እና ለማስታረቅ የነበረ አገልገሎት ሲሆን በእኛ ዘመን ግን ከጳጳሳቱ አምልጠን ወደ ቤተመንግስቱ መሸሻችንን ለማረጋገጥ የአባ ፋኑኤልን እና የአዋሳ ምእመናንን ጉዳይ ማየት ብቻ በቂ ይመስለኛል፡፡
መሐረነ ክርስቶስ !!!
kale hiwot yasemalene rejem edemiee yisetelene tsegawen yabzaleh!!!
ReplyDeleteDani,
ReplyDeletePlease elaborate and print out in a small book form. That is just with the size of ''YE NAGRAN SEMAYTAT''
Other wise where can we gate the reference? unless we see on book stores.
Getachew
Great thanks Dn. Daniel. I appreciate your quality of looking things in depth. May God protect your wisdom.
ReplyDeleteI loved your preachings @ Lideta Gondar.
Esdros Ze Gondar
One of the monastries in Lake Tana is very blessed for saving many lives. They have a wooden bell any body who needs their temporary shelter is not denied the shelter, be it women who had extra maritial sex, men who did kill some one with simple quarrel to get some clemancy from victems relative and the government. The monastery sends representative to the government, the victms family and the husband tried to find some forgiveness. The church worked very hard to create a peaceful society. Mengistu was the bigger devil that happen to the church. Then comes gebere medhn with his big horn of lucefer.
ReplyDeleteI think you have a negative attitude towards emperior Teodros, I realized it in many of your writings.How about e. Teodros's contrbution to the church? Teodros is not a killer as you said, try to be fair. he loved his country as anyone else
ReplyDeletehow can you say የማኅደረ ማርያም ካህናት ራስ ዓሊን ከኃይ ለኛው ከዐፄ ቴዎድሮስ በመደበቃቸውና አሳልፈው ባለመስጠታቸው ምክንያት ንጉሡ ካህናቱንና ሊቃውንቱን አርደዋል፡፡
ReplyDeletedue think it is fair to say this?
ወንጌላችን “የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና ማቴ 5፡-9” እንደሚለው ይህ ተግባር የቤተክርስቲያናችንና የተከታዮቿ ምእመናን የዘወትር ተግባር መሆን አንዳለበት የታመነ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ወንጀለኛ ተጠልሎባት ከወንጀል ድርጊቱ የሚታቀብባት፣ በደለኛ በደሉን የሚረሳባት፣ ሰላም የሚሰፍንባት መድረክ መሆኗ፤ በነፍስ በደልን በንሰሓ አጥባ፣ ከእግዚአብሔር አስታርቃ ለመንግሥተ ሰማይ የምታበቃ በሥጋም ከሌላው ህብረተሰብና ከዓለም ገዥዎች ጋር አስማምታና አስታርቃ ሁሉም በሠላም እንዲኖር የምታደርገው ጥረት የሚጠበቅባት ታላቅ ተግባር እንደሆነና ስታደርገውም እንደኖረች የቀደሙት አባቶቻችንና የቤተክርስቲያናችን ታሪክ የሚነግረን ሃቅ ነው፡፡ ይህ ተግባሯን የተረዱ የAAU ተማሪዎች በ1993 በቅድስት ማርያም ቤተክ’ያን ቢጠለሉም ከሰንዳፋው ግርፋት ሊድኑ አልቻሉም፡፡ በወቅቱ ብጹእ አቡነ ኤፍሬም በሬድዮ የሰጡት ቃለመጠይቅና በተማሪዎቹ ላይ የደረሰው ችግር በግቢ ጉባኤው አካባቢ በነበረው እንቅስቃሴ አንገታችንን እንድንደፋ አድርጎ ነበር፡፡ ምክንያቱም ኢአማኒው ብቻ ሳይሆን አማኒው ጭምር በአባቶቻችን ላይ ክፉ ነገር ሲናገር ከመስማት የበለጠ ምን አሳፋሪ ነገር ይኖራል፡፡ ይህ የሚያሳፍር ቢሆንም የፈተና አንዱ አካል መሆኑንና ቅድስት ቤተክ’ያንም በታላቁ የተፈተነችበት መሆኑን አምኖ ማስረዳትና ጸንቶ እምነትን ጠብቆ መኖር ይገባ ነበር፡፡ ምንምእንኳ ፈተና አይቀሬ ቢሆንም በቤተክ’ያን እና በአባቶች ላይ ክፉ ነገር መናገርና ማሰብ ተገቢ አይሆንም ምክንያቱም እግዚአብሔር የሾመው ላይ መጠቋቆም ሌላ በደል ነውና፡፡ ትናንት የተፈተኑ አባቶች ዛሬ ታሪክ እየሠሩ ነው፡፡ ዛሬ ታሪክ የሚሠሩ አባቶች ደግሞ ነገ የነበረውን የቤተክ’ያን ትውፊት ለማምጣት እንደሚተጉ ጥርጣሬ የለኝም፡፡ ስለሆነም እኛም የቤተክ’ያን ልጆች በሩቁ ከማየት ወደ ቤተክርስቲያን ቀርበን ትውፊቷን፣ መንፈሳዊነቷን፣ ክብሯን ለማስጠበቅ መትጋት ይጠበቅብናል፡፡ እንደማንኛውም ሲመቸን የምንሄድባትና የምናገለግልባት ሳይመቸን በሩቁ የምናይበት ጊዜ ላይ አይደለም ያለነው፡፡ ይህ ጊዜ አልፏል፡፡ የዛሬው ግን የቤተክ’ያናችንን ማንኛውንም በጎ እንቅስቃሴ የምንደግፍበት ጥሩ ያልሆነውን እንዲስተካከል የራሳችንን ድርሻ የምንወጣበትና መንፈሳዊነቷ ተጠብቆ እንዲኖር የወሮበሎች መፈንጫ እንዳትሆን ተግተን የምንጠብቅበት ጊዜ ነው፡፡ ስለዚህ የቻለው በጸሎት ያልቻለው በገንዘብ፣ በጉልበት፣ በሀሳብና ባለው ዕውቀት ሁሉ መትጋት የውዴታ ግዴታችን ነው፡፡ ዲ.ዳኒ አስተማሪ ጽሑፎችህን ዘወትር እንድታደርሰን እግዚአብሔር ረጅም ዕድሜ ይስጥህ፡፡
ReplyDelete