ዓርብ ለቅዳሜ ምሽት፣ ጳጉሜን አምስት 2002 ዓም ማታ በኢትየጵያ ቴሌቭዥን ይተላለፍ የነበረውን የአዲስ ዓመት ዋዜማ እያየሁ ነበር፡፡ ከአሜሪካ የገባሁት በዚያው ቀን ነበርና ዕንቅልፌ ሊስተካከልልኝ ስላልቻለ በደንብ ነበር የተከታተልኩት፡፡ እኩለ ሌሊት ሊደርስ ሲል ግን አንድ አሳዛኝ ነገር ተከሰተ፡፡
የማከብራቸው አርቲስቶች ወደ መድረኩ ተሰባስበው ወጡና በዚያች ታሪካዊት ቀን ታሪካዊ ቀን ታሪካዊውን ስሕተት ሠሩት፡፡ እኩለ ሌሊት ስድስት ሰዓት ሊሆን ሽርፍራፊ ሰኮንዶች ሲቀሩ «አዲሱ ዓመት ሊገባ ስለሆነ እንቁጠር» አሉና ወደ ኋላ አሥር፣ዘጠኝ፣ ስምንት፣ እያሉ እስከ ዜሮ ቆጠሩ፡፡ ከዚያም ከምሽቱ ስድስት ሰዓት ላይ አዲሱ ዓመት ገባ ብለው ዐወጁ፡፡
«ሊቃውንቱ ስሕተት እድሜ ሲያገኝ ሕግ ይሆናል» ይላሉ፡፡ በጥንት ጊዜ አውስትራልያ የገባ አውሮፓዊ አይቷት የማያውቅ አዲስ ፍጡር ያይና የሀገሬውን ነዋሪ «ይህቺ እንስሳ ማን ትባላለች?» ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ ያም የሀገሩ ነዋሪ «ካንጋሮ» ብሎ መለሰለት፡፡ ያም ሰው «ካንጋሮ» የምትባል እንስሳ አገኘሁ ብሎ ለዓለም ተናገረ፡፡ በሀገሬው ቋንቋ ግን «ካንጋሮ» ማለት «አላውቅም» ማለት ነበር፡፡ አንድ ሞኝ የተከለውን አምሳ ሊቃውንት አይነቅሉትም እንዲሉ ይሄው ስሟ ሆኖ ቀረ፡፡
ይህ የአዲስ ዓመት መግቢያ ሰዓትም በየሚዲያው እና በየአዳራሹ ብቅ ጥልቅ እያለ ሰነበተና ስሕተት «ሕግ» ሆኖ በአደባባይ ታወጀ፡፡ ለመሆኑ ግን የስሕተቱ መነሻው ምንድን ነው?
የመጀመርያው ቁርጥ ያለ ሕግ ካለመኖሩ የተነሣ ይመስለኛል፡፡ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 51/20 ላይ አንድ ወጥ ካላንደርን ማወጅ የፌዴራል መንግሥቱ ሥልጣን መሆኑን ይገልጻል፡፡ ሳላውቀው ታውጆ ካልሆነ በቀር እስካሁን የተወካዮች ምክር ቤት ካላንደርን በተመለከተ ያወጣው ሕግ የለም፡፡ ስለዚህም እንደ ዘመነ መሳፍንት «ሰው ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ያደርግ ጀመር»፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የሚመለከታቸውን ባለሞያዎች በሚመለከታቸው ቦታ ያለማሳተፍ ልማዳችን የፈጠረው ሊሆንም ይችላል፡፡ አንድ ሰው እድሉን እና መድረኩን ካገኘ፤ ታውቃለህ ከተባለ፤ አጋጣሚውም ከተፈጠረለት ሁሉንም ይሆናል፡፡ ደራሲም፣ አዘጋጅም፣ ዳይሬክተርም፣ ተዋናይም፣ ይሆናል፡፡ ዘፋኝም፣ ኮምፖዘርም፣ ደራሲም፣ የድምፅ ባለሞያም ይሆናል፡፡ ይኼ ልማዳችን የዘመን አቆጣጠራችንን በተመለከተም በሞያው የደከሙ፣ ከልክ በላይ የሠለጠኑ፤ ነገሩን ከነምክንያቱ ሊያስረዱ የሚችሉ ሊቃውንት እያሉ ሞያውን የማያውቁት እና ለሞያውም ትኩረት የማይሰጡ አካላት ገቡበትና ሁሉም የየራሱን መንገድ ፈጠረ፡፡
እንደገናም ደግሞ ፈረንጅ ያደረገው ሁሉ ትክክል ነው የሚለው ክፉ ልማዳችንም ለዚህ ሳያጋልጠን አልቀረም፡፡ ፈረንጆቹ አዲሱን ዘመናቸውን የሚቀይሩት በእኩለ ሌሊት ነው፡፡ ያም እንኳ ቢሆን ትክክል ሆኖ አይደለም፡፡ የዘመን መለወጫ በሽርፍራፊ ሴኮንዶቹ የተነሣ በየጊዜው ይለዋወጣልና፡፡ ነገር ግን በልማድ ሕግ /customary law/ መሠረት በእኩለ ሌሊት ሰዓታቸውን በመጀመራቸው ከሰዓታቸው ጋር እንዲገጥም አድርገው ተጠቀሙበትና በዚያው ጸና፡፡ ታድያ እኛም ለመሠልጠን እንደ እነርሱ በእኩለ ሌሊት አዲሱን ዓመት መቀበል አለብን ተብሎ ሳይታሰብ አልቀረም፡፡
ፈረንጆቹ በእኩለ ሌሊት አዲስ ዓመታቸውን ቢቀበሉ እውነታቸውን ነው፡፡ ምክንያቱም የእነርሱ የቀን አቆጣጠር ከእኩለ ሌሊት አንድ ሰዓት አልፎ ይጀምርና በእኩለ ሌሊት ያልቃል፡፡ አዲሱ ዓመታቸውም 00 ብሎ የሚጀምረው በእኩለ ሌሊት ነው፡፡ ኮፒ በሚጠቅም መንገድ ከተደረገ አንዳንድ ጊዜ መልካም ነው፡፡ ነገር ግን ኮፒ ሲደረግ ለገልባጩ እንዲያመቸው አድርጎ ካልሆነ ከመኮረጅ የባሰ ስሕተት ይሠራል፡፡
ትምህርት ቤት እያለን የሚቀለድ አንድ ቀልድ ነበረ፡፡ አንድ ሰነፍ ተማሪ ነበረ ይባላል፡፡ ይኼ ተማሪ አራተኛ ክፍል ይደርስና እንዴት እንደሚያደርግ ግራ ይገባዋል፡፡ በመጨረሻም በፈተና ሰዓት አነጣጥሮ ተኳሽ መሆን እንደሚያዋጣው ራሱን አሳምኖ ፈተና ክፍል ይገባል፡፡ ከዚያም እያነጣጠረ ከጎበዙ ተማሪ መኮረጅ ይጀምራል፡፡ አንዲትም ጥያቄ ሳታመልጠው ይኮርጃል፡፡ በመጨረሻም ፈተና በሚመለስበት ቀን ግቢው ሁሉ በሳቅ አወካ፡፡
ለካስ ያ ሰነፍ ተማሪ ከጎበዙ ተማሪ ሲኮርጅ ከነ ስሙ እና ከነ ቁጥሩ ኑሯል የኮረጀው፡፡
የኛም አኮራረጅ የዚህን ሰነፍ ተማሪ ዓይነት ሆነ፡፡ ቢያንስ ቢያንስ የአዲስ ዓመት በዓል አከባበራቸውን ወስደን የኛ አዲስ ዓመት በሚከበርበት ሰዓት ብናደርገው ከሰነፉ ተማሪ አኮራረጅ የተሻለ በኮረጅን ነበር፡፡
ምናልባትም ደግሞ ነገሮችን በአራቱም አቅጣጫ ካለማየት የመጣም ይሆናል፡፡ ዕውቀት ማለት ነገሮችን ከአራት አቅጣጫ ማየት መቻል ነው፡፡ ማንበብ፣ መጠየቅ፣ መመራመር፣ ማነፃፀር፣ ማወዳደር፣ መተንተን የሚባሉት ነገሮች የሚመጡት ነገሮችን ከአራቱም አቅጣጫዎች ለማየት ሲሞከር ነው፡፡
በእኩለ ሌሊት ተነሥተው አዲስ ዓመት ገብቷል ብለው የሚያውጁ አካላት ሌላው ቀርቶ የእጅ ሰዓታቸውን እንኳን ቢያዩት በታረሙ ነበር፡፡ «ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት» ነበር የሚለው፡፡ በዚያ ሰዓት ስድስት ሰዓት ካለ ደግሞ ሌሎች አምስት ሰዓታት ከፊቱ ሄደዋል፤ ወይንም ደግሞ ሌሎች ስድስት ሰዓታት ከኋላው ይቀሩታል ማለት ነው፡፡ በዚያ ሰዓት ስድስት ሰዓት ከተባለ ደግሞ ያ ሰዓት ያለፈው ቀን ቅጣይ እንጂ የአዲስ ቀን መጀመርያ አለመሆኑን መረዳት ይገባ ነበር፡፡
አንዳንዶች ይህንን የአዲስ ዓመት ጉዳይ ከገና እና ፋሲካ በዓላት ጋርም ያያይዙታል፡፡ በገና እና ፋሲካ በዓላት ጊዜ በዓሉ የሚበሰረው በእኩለ ሌሊት ነው፡፡ ከዚህ አያይዘውም አዲስ ዓመትም በእኩለ ሌሊት ይበሠራል ይላሉ፡፡ ገና እና ፋሲካ በእኩለ ሌሊት የሚበሠሩት በበዓላቱ ታሪካዊ ምክንያት የተነሣ እንጂ የበዓሉ ቀን በእኩለ ሌሊት ስለ ገባ አይደለም፡፡ ክርስቶስ የተወለደውም ሆነ ከሙታን የተነሣው በእኩለ ሌሊት ነው ተብሎ በቤተ ክርስቲያን ስለሚታመን በዓሉ በእኩለ ሌሊት ተከበረ እንጂ ዕለታቱ በስድስት ሰዓት ስለሚገቡ አይደለም፡፡
በቤተ ክርስቲያን ሁለት ዓይነት አቆጣጠሮች አሉ፡፡ የፀሐይ አቆጣጠር እና የጨረቃ አቆጣጠር፡፡ የፀሐይ አቆጣጠር ከጠዋቱ አሥራ ሁለት በኋላ ጀምሮ እስከ ሌሊቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ይደርሳል፡፡ አብዛኛውን የሕዝቡ በዓላት እና አቆጣጠር /civil calendar/ የተመሠረተው በዚህ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የጨረቃ አቆጣጠር ነው፡፡ ይህም በምሽቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ጀምሮ በማለዳው አሥራ ሁለት ሰዓት ያልቃል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የቤተ ክርስቲያኒቱ በዓላት፣ በተለይም ዐበይት በዓላት የሚወጡት ይህንን አቆጣጠር ከፀሐይ አቆጣጠር ጋር በማጣመር ስለሆነ /Liturgical calendar/ ተብሎ ይጠራል፡፡ በሥርዓተ ጸሎት ምሽት ሲገባ የቀጣዩን ቀን ጸሎት የምናደርሰው የጸሎት አቆጣጠራችን የጨረቃን አቆጣጠር ጭምር ስለሚከተል ነው፡፡
በተለይም የነነዌ ጾም፣ የዐቢይ ጾም መጀመርያ፣ ደብረ ዘይት፣ ስቅለት፣ ትንሣኤ፣ ዕርገት እና ጰራቅሊጦስ በዚህ መሠረት የሚወጡ ናቸው፡፡ መሠረቱ ደግሞ የትንሣኤ በዓል ነው፡፡ የትንሣኤ በዓል ሦስት ነገሮችን መሠረት አድርጎ መውጣት አለበት፡፡ ከእሑድ መልቀቅ የለበትም፤ ከአይሁድ ፋሲካ በኋላ መሆን አለበት፣ ከእርሱ ጋር የተያያዙ በዓላትን ጥንት ማስለቀቅ የለበትም፡፡ እነዚህም ደብረ ዘይት እሑድ፣ስቅለት ዓርብ፣ ዕርገት ኀሙስ፣ ጰራቅሊጦስ እሑድ እንዲውሉ ማድረግ ነው፡፡
የትንሣኤ በዓል የሚወጣው በጨረቃ/ፀሐይ አቆጣጠር ነው፡፡ ምክንያቱም አይሁድ በዓለ ፋሲካቸውን የሚያወጡት በጨረቃ አቆጣጠር በመሆኑ ነው፡፡ አይሁድ በጨረቃ አቆጣጠር ተጠቅመው ያወጡትን የአይሁድ ፋሲካ በዓል አልፎ አማናዊውን ትንሣኤ ለማክበር በጨረቃ/ፀሐይ ቆጥሮ ማውጣትን ይጠይቃል፡፡ የሚገርመው ግን በዚሁ በጨረቃ ብንቆጥረው እንኳን አዲሱ ዓመት የሚገባው ከምሽቱ አሥራ ሁለት ሰዓት እንጂ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ሊሆን አይችልም፡፡
ቤተ ክርስቲያን ሁለቱንም አቆጣጠሮች እንደየ አስፈላጊነታቸው ትጠቀምባቸዋለች፡፡
አንዳንድ መፍቀርያነ በዓል ደግሞ በዓሉ የሚያምረው እና የሚደምቀው በእኩለ ሌሊት ሲሆን ነውና በእኩለ ሌሊት ብናከብረው ምናለ ይላሉ፡፡ በዓሉን በእኩለ ሌሊት ማክበርና አዲሱ ዓመት በእኩለ ሌሊት ገባ ብሎ ማወጅ ይለያያሉ፡፡ የበዓሉን ዋዜማ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ እስከ ንጋት ድረስ ማክበር ይቻላል፡፡ የሺ ዘመናትን ሥርዓት እና አቆጣጠር በአንድ ሌሊት በማወቅ እና ባለማወቅ መናድ ግን በታሪክ እና በትውልድ የሚያስጠይቅ ነው፡፡
ሠለጠን የምንል ሰዎች ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነን በጎርጎርዮሳዊው ቀመር ሰዓታችንን እንሞላዋለን፡፡ በኛ የሰዓት አቆጣጠርም ዕለቱ የሚጀምረው በኛ ከሌሊቱ ስድስት በእናንተ ደግሞ ከሌሊቱ 00 ሰዓት ነው፡፡ የኢትዮጵያን የዘመን አቆጣጠር እያከበሩ በአውሮፓ ሰዓት መጠቀም ግን በዶሮ ወጥ ላይ ማርማላታ እንደ መጨመር ነው፡፡ ሁለቱንም አያይዞ ማጥፋት፡፡
ታድያ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት የሚብተው ስንት ሰዓት ነው?
ይህንን ጥያቄ ለመመለስ እንችል ዘንድ አራት ነገሮችን እናንሣ፡፡ የመጀመርያው በኛ አቆጣጠር ዕለት የሚባለው ምንድን ነው? የሚለው ነው፡፡ ዕለት ሁለት ነገሮችን ይይዛል፡፡ ቀን እና ሌሊት፡፡ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ዕለት የሚባለው ከመንፈቀ ሌሊት እስከ ማለዳ ያለውን ግማሽ ሌሊት፣ ከዚያም ከማለዳ እስከ ማታ ያለውን ቀን እና ከማታ እስከ እከየለ ሌሊት ያለውን ግማሽ ሌሊት የያዘው ክፍል ነው፡፡ በኛ ግን አንድ ቀን እና አንድ ሌሊትን ብቻ የያዘ አቆጣጠር ነው፡፡
ስንክሳሩ መስከረም አንድን ሲጀምር «ይህ የመስከረም ወር የተባረከ ነው፤ እሱውም የግብጽ እና የኢትዮጵያ ዓመቶች መጀመርያ ነው፡፡ የዚህ ወር ቀኑ እና ሌሊቱ እኩል 12 ሰዓት ነው» ይላል፡፡ ይህ የሚያመለክተን በመስከረም አንድ ቀኑ እና ሌሊቱ እኩል የሆነ አንድ ቀን እንጂ በግማሽ ሌሊት እና በሙሉ ቀን የሚቆጠር አይደለም ማለት ነው፡፡
ምንም እንኳን በየወራቱ የቀኑ እና የሌሊቱ ርዝመት ልዩነት ቢኖረውም ሰዓቱ ግን እኩል አሥራ ሁለት ሰዓት ቀን እና ሌሊት ነው፡፡ ለምሳሌ አሜሪካውያን በዓመት ሁለት ጊዜ የሰዓት ማስተካከያ ወደፊት እና ወደ ኋላ ያደርጋሉ፡፡ አውሮፓውያን፣ በተለይም ሰሜኖቹ ደግሞ ከአንድ ሰዓት ሌሊት እስከ ሁለት ሰዓት ቀን የሚደርሱበት ጊዜ አለ፡፡ በኛ ግን የቀኑ እና የሌሊቱ ርዝመት ብዙም ልዩነት የለውም፡፡
ቀኑ ሌሊቱ
መስከረም 12 ሰዐት 12
ጥቅምት 11 13
ኅዳር 10 14
ታኅሣሥ 9 15
ጥር 10 14
የካቲት 11 13
መጋቢት 12 12
ሚያዝያ 13 11
ግንቦት 14 10
ሰኔ 15 9
ሐምሌ 14 10
ነሐሴ 13 11
ይሆናሉ፡፡ ይህም የሚያሳየን ቀኑም ሆነ ሌሊቱ ከአሥራ አምስት እንደማይረዝም፤ ከዘጠኝ እንደማያንስ ነው፡፡
እንግዲህ አዲስ ዓመት በመስከረም ወር እንዲብት የተደረገበት አንዱ ምክንያት ቀኑ እና ሌሊቱ እኩል የሚሆንበት ጊዜ ስለሆነም ነው፡፡
ሁለተኛው ነገር ደግሞ የዓመቱን ወራት የምናወጣው በምን አቆጣጠር ነው የሚለው ነው፡፡ ቀደም ብለን እንዳየነው የዓመቱን ወራት የምንቆጥረው በፀሐይ አቆጣጠር ነው፡፡ በፀሐይ አቆጣጠር ደግሞ መዓልቱ ሌሊቱ ይስበዋል፡፡ ምክንያቱም ፀሐይ የሚሠለጥነው በቀን ነውና /ዘፍ 1፤14፣16/፡፡ ያ ከሆነ ደግሞ በአቆጣጠራችን ቀኑ ቀድሞ ይጀምራል ማለት ነው፡፡ በመሆኑም የኛ አንድ ሰዓት ማለዳ ላይ እንጂ እኩለ ሌሊት ላይ ሊጀምር አይችልም፡፡
ሦስተኛው ደግሞ የሰዓት አቆጣጠራችን ነው፡፡ በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር አንድ ብሎ የሚጀምረው መቼ ነው? አዲሱን ዓመት በእኩለ ሌሊት የሚያውጁት ሚዲያዎች እንኳን መልሰው ጠዋት ይነሡና «መስከረም አንድ ቀን ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ነው» ይሉናል፡፡ የፈረንጆቹ ሰዓት ግን በዚያ ሰዓት 7 ሰዓት ነው የሚለው፡፡ ምክንያቱም እኩለ ሌሊት ላይ አንድ ብሎ ጀምሯልና፡፡ አንድ ሰዓት ደግሞ ስድሳ ደቂቃዎች እና 3600 ሰኮንዶች ነው፡፡ ስለዚህም አንድ ሰዓት ለማለት እነዚህ ተቆጥረው ማለቅ አለባቸው፡፡ እነዚህ መቆጠር የሚጀምሩት ደግሞ ከጠዋቱ አሥራ ሁለት ሰዓት ላይ ነው፡፡ አሥራ ሁለት ሰዓት የሌሊቱ ማጠናቀቂያ ነውና፡፡
በአራቱ ወንጌላውያን ምግብና እናክብር ካልን ደግሞ በየአራት ዓመቱ አዲሱ ዓመት የሚገባ እና የሚወጣበት ይለያያል ማለት ነው፡፡ ማቴዎስ ምግብናውን ማታ በሠርክ 12 ሰዓት ጀምሮ በመንፈቀ ሌሊት በስድስት ይፈጽማል፤ ማርቆስ ምግብናውን በመንፈቀ ሌሊት ይጀምራል፣ በነግህ 12 ሰዓት ይፈጽማል፤ ሉቃስ ምግብናውን በነግህ 12 ሰዓት ይጀምራል፣ በእኩለ ቀን 6 ሰዓት ይፈጽማል፤ ዮሐንስ ምግብናውን በቀትር 6 ሰዓት ይጀምራል፣ በሠርክ 12 ሰዓት ያልቃል፡፡ እናም በምግብናቸው መሠረት ከሄድን ደግሞ በየዓመቱ የአዲሱ ዓመት መግቢያ ይለያያል ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለሕዝቡ መምታታትን ይፈጥራል፡፡
አውሮፓውያንም ቢሆኑ ይህ በየዓመቱ ያለውን የወንጌላውያን መለያየት ያውቁታል፡፡ ነገር ግን የአዲስ ዓመት መግቢያቸውን በእኩለ ሌሊት ያደረጉት አንድ ወጥ ለማድረግ ነው፡፡ እኛም በዚያው በእኩለ ሌሊቱ ብንቀጥለው ምናለ? የሚሉ ሃሳብ አቅራቢዎች አሉ፡፡ ቀደም ብለን እንዳየነው የእነርሱ የዘመን መለወጫቸው ከሰዓት አቆጣጠራቸው ጋር አብሮ ይሄዳል፡፡ የኛ ግን ዘመን ለወጥን ብለን መልሰን ሰባት፣ ስምንት እያልን መቁጠሩ መምታታት ነው፡፡
እንግዲህ እነዚህን ነጥቦች ስናያቸው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በእኩለ ሌሊት ሊጅምር የሚችለው የወንጌላውያንን መግቦት ከተከተልን በዘመነ ማርቆስ ብቻ ነው፡፡ ያም ቢሆን ከሰዓት አቆጣጠራችን ጋር ይጋጫል፡፡ ከሰዓት አቆጣጠራችንም ሆነ ከባህላችን ጋር፣ ብሎም ከመስከረም የቀን እና ሌሊት እኩል መሆን ጋር የሚገጥመው አዲሱን ዓመት በማለዳ አሥራ ሁለት ሰዓት ላይ መቀበሉ ነው፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ ጋዜጠኞች እና አርቲስቶች ጳጉሜ አምስት እና ስድስት ሌሊት ተነሥተው መከራ ከሚያሳዩን ሰነድ ማገላበጥ እና ምሁራኑን መጠየቅ አለባቸው፡፡ ሊቃውንቱም ቢሆኑ ደፍረው ወጥተው ማስረዳት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የውይይት መድረክ የሚያዘጋጁ አካላትም አንዱ የመወያያ ጉዳይ አድርገው ፈር እንድንይዝ ቢያደርጉ ይመሰገኑበታል፡፡
ይበልጥ ደግሞ ያለ ምርምር በዘፈቀደ እየተፈጸመ ያለው ስሕተት ሕግ ሆኖ እንዳይቀጥል በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 51/20 መሠረት ፓርላማው አንዳች ነገር ማድረግ አለበት፡፡ በሀገሪቱ ወጥ የሆነ የዘመን አቆጣጠር የመወሰን ሥልጣን የተሰጠው የፌዴራሉ መንግሥት ሊቃውንቱን፣ ባለሞያዎችን እና ሕዝቡን አማክሮ፤ ሰነድ አገላብጦ እና ታሪክ መርምሮ ይህንን ዝብርቅርቁ የወጣውን የአዲስ ዓመት የመባቻ ሰዓት ጉዳይ አንዳች እልባት የሚሰጥ ዐዋጅ ማወጅ ይጠበቅበታል፡፡
መልካም ዘመን
ናይሮቢ፣ ኬንያ
QALE HIWOT YASEMALEGN! JORO YALEM YESMA LEB YALEW LEB YEBEL EWNET EBAKACHUN ERASACHENEN MESLEN ENENUR MEN GODELEN ENA NEW KEAWROPAWYAN BAHIL YEMNWERSEW LEMN YERASACHNEN BAHEL LELOCH ANASTEWAWQM KETELEYAYE BOTA YALEHONE NEGER YEZEN EYHADEN YEHEBRETESBUN AMELEKAKET ANBEKLEW.
ReplyDeleteበመጻፍ ቅዱስ ደግሞ ማታም ሆነ ጠዋትም ሆን አንድ ቀን ይላል ይህስ እንዴት ነው ዘፍ=1-5 በዚህ ከሄድን 1 ቀን የሚጀምረው ማታ ነው ማለት ነው::
ReplyDeleteልክ ብለሃል ዲ/ን ዳንኤል በኔም ልብ ውስጥ ሲመላለስ የነበረ ጥያቄ ነው:: ሊቃውንቱ ይህንን ቢያርሙት መልካም ነው::
ReplyDeleteስለ እለት አቆጣጠራችን በስነ ፍጥረት መሰረት ሌቱ ይቀድማል ስለዚ ከምሽቱ 12 ሰአት ጀምሮ ነው እለቱን ምንቆጥረው የሚል ነገር ያነበብኩ ይመስለኛል
Interesting!
ReplyDeleteእግዚአብሔር ይባርክህ! ይህ የ ዉጪ ነገር መናፈቃችን ነዉ የ ጌታችንን ልደት ከ መስከረም 1 ወደ ታህሳስ ያስወሰደን! በዚህ ዙርያ ወደፊት ሰፋ ያለ ነገር እንደምስታነብበን ተስፋ እለኝ!
ReplyDeleteDear Dn Daniel,
ReplyDeleteVery nice overview,May God bless you in your all ways and efforts.
Happy Ethiopian New Year!!!
ጥሩ አስተውለህል ዲ/ን ዳኒ፡ ከተጀመረ ግን ቆይቷል፡፡
ReplyDeleteልክ ብለሃል ዲ/ን ዳንኤል በኔም ልብ ውስጥ ሲመላለስ የነበረ ጥያቄ ነው:: ሊቃውንቱ ይህንን ቢያርሙት መልካም ነው::
ReplyDeleteስለ እለት አቆጣጠራችን በስነ ፍጥረት መሰረት ሌቱ ይቀድማል ስለዚ ከምሽቱ 12 ሰአት ጀምሮ ነው እለቱን ምንቆጥረው
በመጻፍ ቅዱስ ደግሞ ማታም ሆነ ጠዋትም ሆን አንድ ቀን ይላል የሚል ነገር ያነበብኩ ይመስለኛል
endante ayinet sewoch yasifelgalu yeminilew leziya new yemiyawuku bicha sayhonu memoget yemichilu tsegaw yesu newuna yabizakih.
ReplyDeleteዲ/ን ዳኒ በእዉነቱ ሁሉንም ነገሮች በማስተዋል ማየት ምነኛ ጠቃሚነዉ፡፡ እኔ ሁል ጊዜ ሰዉ ፊልም ሲያይ አንዳች ቁም ነገር ለመገብየት ከመሳቁ ባሻገር ትኩረት ይኖረዉይሆን ? ይህንን ያነሳሁልህ ታዲያ ያለነገር አይደለም ምድንነዉ አንተ በቤትህ ሁነህ እይተህ ምን እደተፈጠረ ተረድተሀል ሰዉ ግን ከራሴ ጀምሮ በቦታ ላይ ማለትም በሚሊኒየም አዳራሽ ነበርሂኝ ነገር ግን ከእዉቀት ማነስ ይሁን ከሌላ ማስተዋል ግን አልቻልን፡፡ እናም ዳኒ በጣም ድቅ እይታ ነዉ እግዚአብሔር የበለጠዉን ጸጋ ያድልህ፡፡ ገ/ሥላሴ አራት ኪሎ
ReplyDelete‘’ዕውቀት ማለት ነገሮችን ከአራት አቅጣጫ ማየት መቻል ነው፡፡’’ ዳኒ እኔ ግን ነገሮችን ከአራቱ አቅጣጫ ማዬት ትንሹ መስፈርት ነው ብዬ አምናለሁ ምክኒየቱም ሙሉና ዘላቂ እውቀት የነገሮችን ክበብ (360 ዲግሪ) ማየትና መመርመር ይጠይቃልና ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ከመጠምጠም ትምህርት ይቅደም ነውና እነዚህ በየመድረኩ የምናያቸው አዋቂ ነን የሚሉ ግን አላዋቂዎች ምን አለ ሊቃውንቱን ቢጠይቁ፤ መጠየቅም እኮ እውቀት ያስገኛል፡፡ባህረ ሃሳቡን
ReplyDelete( አቡሻክሩን) አምልተው ባስተማሩን ነበር፡፡ ግና ሊቃውንቱን ማን ወደመድረክ ያቅርብ!! በተረፈ ዳኒ እግዚአብሔር ይስጥልን እንተ በርታ! የድንግል ጥበቃ ዘወትር አይለይህ! ወቅታዊና ጥሩ ትምህርት ሰጥተኸናልና፡፡
ዲምፕል
Dear Dn Daniel, I do agree and appreciate your concern. However, the Artists/Journalists duplicated what they saw in the past, i do not see any problem on them. no need of telling you, for how long we have been doing the same. so all of us who sense the ownership of our country, should put our hands, especially as you said the parliament who should take the initiative.
ReplyDeleteThanks
GOD BLESS ETHIOPIA
ዲን ዳንኤል እግዚአብሔር ይባርክህ
ReplyDeleteበጣም ቀላል እና ግልፅ የሆነን ነገር ማስተዋል ስለሌለን ብቻ የተሳሳትነውን ነገር አንተ በማስተዋያ አይምሮህ አይተኸው ይህን መልካም ነገር ስለአስተማርከን አምላክ ይባርክህ፡፡ አሜን
በተረፈ ሁሉም ሰው ከስህተቱ ታርሞ የሚመለከታቸው አካላትም ለነገሩ ትኩረት ሰጥተው ስህተት እውነት ሆኖ እንዳይቀጥሉ ሊያስቆሙት ይገባል እላለሁ፡፡
የኢትዮጵያን ትንሳኤ ያሳየን
የምሥራች ገብርኤል
ጥሩ እዪታ ነዉ! ነገር ግን የጾም ጉዳይስ ከሓሙስ ማታ እስከ ዓርብ ስንት ሰዓት ላይ ከምግብ ክልከላ ይጀምራል? ብዙ ጊዜ ከምሽቱ 6 ሰዓት የሚሉ ኣሉ እና ትክክለኛዉ የትኛዉ ነዉ? ከዚህ ፅሑፍስ እንዴት ይስማማል?
ReplyDeleteእግዚኣብሔር ይስጥልኝ
ከትግራይ
ቃለ ሕይወት ያሰማልን! እኔንም እንዲሁ ሲያብሰለስለኝ የነበረ ጉዳይ ነው:: "አውሮጳ እየኖርክ የማትቀየር" የሚል ስም ካሰጡኝ ነገሮች አንዱ ነው:: ልክ አንተ እንዳልከው ሌሊት አዲሱ ዓመት ገባ ብለው ይደዋወሉና ጧት ሲነጋ ቀኑን አንድ ብለው ይቆጥራሉ:: ይቺ ደግሞ ትንሽ ትንሽም ብትሆን ዛሬ የቀን አቆጣጠራቸውን በአውሮፓውያን ያደረጉት ወገኖች እጅ ይኖርባታል:: እኛ መቸም ሞኞችና ተታላዮች ነንና እንዳይከፋቸው ከእነሱ ላለመለይት ብለንም ሊሆን ይችላል:: ጨዋታን ጨዋታ የነሳዋልና የካንጋሮዋን ታሪክ ካነሳህ አይቀር በእኛም አገር የሚነገር አንድ ነገር ሰምቻለሁ:: እነ ጀምስ ብሩስ ናቸው መሰለኝ ከላይ ተነስተው ወደ ደቡቡ የሃገራችን ክፍል ሲወርዱ አካባቢውን እያማተሩ ስም ጠይቀው እየመዘገቡ ነበርና አንድ ያገራችን ሰው ቁጭ ብሎ ሞያሌውን ሲያወጣ ያገኙትና በማያውቀው ቋንቋ (እንግሊዝኛ)የአካባቢውን ስም እንዲነግራቸው ይጠይቁታል:: ምን ታደርጋለህ ያሉት የመሰለው ሰው "ሞያሌ እያወጣሁ ነው" ይላቸዋል:: ምን? ሞያሌ . ሲላቸው So they call this place MOYALE ብለው ሞያሌ ተብሎ እንዲያውም የ ኢትዮጵያ ሞያሌ - የኬንያ ሞያሌ ተብሎ ሊጠራ በቃ የሚል ነገር ሰምቻለሁ:: ፈረንጅ ካለው ደግሞ አንድም ነገር መሬት ጠብ የሚል የለውም የሚል አመለካከት ላለው ህብረተሰብ አፈፍ አድርጎ ይዞ ያስተጋባል:: የራሳችንን ስም እንኳን በቅጡ መጥራት ባለመቻላቸው (ፈረንጆቹ)እነሱን እንደማረም የእነሱን ፈሊጥ ይዘን እኛው እራሳችን ስናበላሽ እንገኛለን:: ለምሳሌ የምስራች የሚ - ደረጀ - ዴር ወዘተ እንደማለት ነው:: ዲ. ዳንኤል እንደዚህ እንዳንተ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የሚበሩ አንዳንድ ጧፎች አምላክ አያሳጣን:: የውሃ ነጠብጣብ ሲደጋገም ድንጋይ እንደሚበሳው ሁሉ ማስተማሩን ቀጥል:: አምላክ እድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን! ምንተስኖት ዘአውሮጳ
ReplyDeleteግሩም እይታ ነው!!!ነገር ግን ከላይ የተወሰኑ አንባብያን ለመጥቀስ እንደሞከሩት እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ዘመን አቆጣጠር ከቀኑ ሌሊቱ ይቀድማል::ስለዚህ አንድ ቀን የሚባለው ከምሽቱ 12:00 እስከ ንጋት 12:00 (ማለትም ሙሉ 12 ሰዓት ሌሊት)ሲደመር ከንጋቱ 12:00 እስከ ምሽት 12:00 (ማለትም ሙሉ 12 ሰዓት ቀን)የያዘውን ነው::
ReplyDeleteሊቃውንቱ "ስሕተት እድሜ ሲያገኝ ሕግ ይሆናል"
ReplyDeleteምናልባትም ደግሞ ነገሮችን በአራቱም አቅጣጫ ካለማየት የመጣም ይሆናል፡፡ ዕውቀት ማለት ነገሮችን ከአራት አቅጣጫ ማየት መቻል ነው፡፡ ማንበብ፣ መጠየቅ፣ መመራመር፣ ማነፃፀር፣ ማወዳደር፣ መተንተን የሚባሉት ነገሮች የሚመጡት ነገሮችን ከአራቱም አቅጣጫዎች ለማየት ሲሞከር ነው፡፡
በዓሉን በእኩለ ሌሊት ማክበርና አዲሱ ዓመት በእኩለ ሌሊት ገባ ብሎ ማወጅ ይለያያሉ፡፡
አቤት እንዴት ደስ እንዳለኝ እግዚያብሔር የተመኘውን ነገር ያሰማ አሁንም በጥበብ ላይ ጥበብ በእውቀት ላይ እውቀት ጨምሮል ብዙ ነገር ለመባባል ያብቃን።አሜን
አንዳንድ አንባብያን ከቀኑ ሌሊቱ ይቀድማልና አቆጣጠራችን በዚያ መሠረት መሆን አለበት ብላችኋል፡፡ በሀገራችን ሁለት ዓይነት አቆጣጠር አለ ቤተ ክርስቲያናዊ /ሊተርጂካል ካላንደር/ እና ሕዝባዊ /ሲቪል ካላንደር/፡፡ ቤተ ክርስቲያናዊው አቆጣጠር በዋናነት የጨረቃ አቆጣጠርን ይከተላል፡፡ ስለዚሀም ከቀኑ ሌሊቱ ይቀድማል፡፡ በዓል ስናከብር፣ ዋዜማ ስንቆም፣ ምንባብ ስናነብ ይህንን እንከተላለን፡፡ ሀገሪቱ የምትቆጥረው ግን በሕዝባዊ ካላንደር ነው፡፡ እርሱም በፀሐይ አቆጣጠር የሚመራ ነው፡፡ ቀኑን ከሌሊቱ ያስቀድማል፡፡ በዚህ ምክንያት ሰኞ ማታ የተወለደ ልጅ ሰኞ ማታ ተወለደ ይባላል እንጂ ማክሰኞ ማታ ተወለደ አይባልም፡፡
ReplyDeleteQHY Wendmachn betam yegermale enema good new ethiopian zemdochen dewaye Equla lelit Melkam Addis Amet salele bey toqoch neber yiker yebalesh malet enane new awaye erasen alemhon weraj mesabsab tawkubtalach yelu neber liktguhan ewntachew new yeanen betwan kentu! Edm yesteln yemtnagren Kumneger esu yeglatlh!
ReplyDeleteMelkam Zemn
Akbarh betseb Ke Canada
"በዚህ ምክንያት ሰኞ ማታ የተወለደ ልጅ ሰኞ ማታ ተወለደ ይባላል እንጂ ማክሰኞ ማታ ተወለደ አይባልም፡፡"
ReplyDeleteሰኞ ማታ ያልነው አኮ እኛ ነን ምክንያቱም እንደዛ እየተባልን ስላደግን(ለሰኞ ማታው የቱ ነው ቀድሞ የመጣው ወይስ ከቀኑ በኃላ የመጣው)እንደአቆጣጠሩ ይለያያል?(በጨረቃ ወይስ በፀሐይ)
ማታ የተወለዳቹ ምረጡ በፀሐይ ነው ወይስ በጨረቃ? እኔ ግን ቀን ላይ ስለተወለድኩ ችግር የለብኝም፡፡
በጣም አመሰግናለው ዳኒ እንደማረፊያ ቁጠረው
civilisation is not acting like "ferenj" TILIK NEBERN TILIKM ENHONALEN! GOD BLEES YOU
ReplyDeletethank u very much daniel. this was what we need to know and tell people.
ReplyDeletethank you for reminding us who we are!
ReplyDeleteReally a wonderful view! May God bless you Dn. Daniel!
ReplyDeleteGood job Dani.
ReplyDeleteThis is what I got from google about Kangaroo's name.
The word kangaroo derives from the Guugu Yimithirr word gangurru, referring to a grey kangaroo.[7] The name was first recorded as "Kangooroo or Kanguru" on 4 August 1770, by Lieutenant (later Captain) James Cook on the banks of the Endeavour River at the site of modern Cooktown, when HM Bark Endeavour was beached for almost seven weeks to repair damage sustained on the Great Barrier Reef.[8] Guugu Yimithirr is the language of the people of the area.
A common myth about the kangaroo's English name is that "kangaroo" was a Guugu Yimithirr phrase for "I don't understand you."[9] According to this legend, Lieutenant Cook and naturalist Sir Joseph Banks were exploring the area when they happened upon the animal. They asked a nearby local what the creatures were called. The local responded "Kangaroo", meaning "I don't understand you", which Cook took to be the name of the creature. The Kangaroo myth was debunked in the 1970s by linguist John B. Haviland in his research with the Guugu Yimithirr people.[10]
Male kangaroos are called bucks, boomers, jacks, or old men; females are does, flyers, or jills, and the young ones are joeys.[11] The collective noun for kangaroos is a mob, troop, or court. Kangaroos are often colloquially referred to as roos.[12]
Igziabeher Yisteligne!Dn Daniel!
ReplyDeleteI totally agree with your complement.
there are some church scholars who claim our lord Jesus Christ birth to be on September one.
what would you say about this?have you done any research? If you did please share us.
I thank you and appreciate your effort.
Semone k
I do not think this is a big deal that seeks all these explanation. My understanding is that artists or people countdown at midnight because it is usually convenient for partying and celebrating. Imagine when we wait till 6am in the morning to countdown and celebrate new year. We can do that at church. But for the majority of city boys and girls who go on partying all night, starting the new year at 6pm won't work.
ReplyDeleteአቦ ገላገልከኝ
ReplyDeleteሰሞኑን መስከረም 20 ማታ የተወለደችው ልጄ ልደት መከበር ያለበት መቼ ነው እያልን ከባለቤቴ ጋር ሙግት ገጥመን ነበር.. የቤተ ክርስቲያናዊ /ሊተርጂካል ካላንደር/ ወይስ ሕዝባዊ /ሲቪል ካላንደር/ እንጠቀም ብለን። ያስማማን ነገር በእለቱ በተመሳሳይ ሰዐት ማክበሩ ነው።
እሷ ግን ወደ መስከረም 21 ቀን አስጠግታ አብራ የቅ/ ማርያምን በዓል ልታከብር ፈልጋ ነበር። ጠጋ ጠጋ ይሉቹኋል ይቺ ናት...
Qale hiwoten yasemalen wendemalem Amen
ReplyDeleteahuenm tsegawen yabezalek teru meleket new yasetalalfekew !!!
yerasachen kalander endealen hulu yseat akotaterunem berasachen endegeletekeln endenetekem be ande hasb yale maguremerem hulum ameno endikebelew EGZIABHER YEREDAN Amen
ene gen and teyake leteyk Dani ? yehewm lemendenew ega addis ametachen MESKEREM lay yemihonew yeferenegochus TER lay yemikeyerew ?
leyunetun lemawek new ena ebakeh betegeleteleg
Birtuna Asifelagi sew neh bertalin
ReplyDeleteDear Daniel,
ReplyDeleteThat was what a question I had when in 2007 I was celebrating the Ethiopian Millenium in Korea. It was a perfect time there - the sun was rising by that time - as they have a six hours lead that Ethiopia. Then I was surprised why people in our oountry have to celebrate when the day is still not there - six hours back.
As you referred, the new parliament should something in its life about this and should be taken part of the ¨TRANSFORMATION AND ...PLAN¨. It is serious as that. It is all about our identity - reducing poverty is for a good image and syncronizing the calender serves also the same purpose.
Thank you for your critical views including the ones on your published volume.
God bless you.
Hagos M
Madrid
አቆጣጠረችን ከጥዋት ነው የሚጀምር ካልንማ ታድያ ቤተ ክርስቲያን እና ሀገረቸን አቆጣጠረቸው ይለያያል ማለት ነው…ደገሞ ለሀገረቱ አቆጣጠር ቤተ ክርስቲያን ምንጭ አንደሆነች ይታመናል ታድያ ለምን ሊለያይ ቻለ ?
ReplyDeleted dany yeny teyaki hulu tebale ebakhe yetyakewechen mels betam etbekalehu
ReplyDeletekesew ayen yetbekehe z chicago
ስለምትጽፋቸው ጽሑፎች ሁሉ ማመስገን ምንም የማያጠያይቅ ጉዳይ ነው፡፡ እዚህ ላይ ግን አንድ ሀሳብ አለኝ፡፡ አንተ እንዳልከው ጸሎት ሲሆን ከ12ሰዓት በኋላ ሲሆን የቀጣዩ ቀን ይደርሳል፤ በዚህ በተቃራኒው ደግሞ ለረቡዕ ጾም እስከ ለሊቱ 6ሰዓት ድረስ መብላት ይፈቀዳል፤ ይህ ማለት በተዘዋዋሪ ከ6ሰዓት በኋላ እንደ ነገ እንዲታሰብ እያደረገው ነው፡፡ ይህንን እንዴት ታየዋለህ? በጨረቃና በጸሐይ አቆጣጠር እየተባለስ ለምን ቤተክርስቲያን ትጠቀማለች፤ ወጥ ማድረግ አይቻልም?
ReplyDeletebetam tiru asteyayet new dani egzabhair edmahen yarzemlen.
ReplyDeleteDani Egiziabiher yebarik
ReplyDeletedani aimeslegnim !elet yemikoterew ke mata 12:00 kehone yemaksegno rat(dinner)sint se,at new?
ReplyDeleteDani teyke teyekek neber menew zem alekeg pls kechalek kelay ke aseteyayete betecemare teyake tyekek neber .
ReplyDeleteቃለ ሕይወት ያሰማልን!እግዚአብሔር ይባርክህ ዲ/ን ዳንኤል አእነነኔ ገግነን ሁሌም የሚቆጨኝ ነገር ቢኖር የኢትየጵያ ቤተ ክርስቲያን እንኩዋን ለሀገራችን ለአለም የሚበቃ የታመቀ እዉቀት እያላት ሁሌም ፈረንጅ የተናገረዉ ትከክል ነዉ ብሎ በመቀበል የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ስንገዛ እንኖራለን የኢትየጵያ ቤተ ክርስቲያን ለአለም ያበረከተችዉ አሰስተዋጸኦ ባለማወቅ አዋቂ ነን ባዮች ታሪካዊውን ስሕተት ሲሠሩት ይኖራሉ ፤በቃ አቡሻክሩን ከምሁራን ሳንጠይቅ ምሁራን እያለፉ ነዉ.ፈረንጅ ያደረገው ሁሉ ትክክል ነው የሚለው ክፉ ልማዳችንም አእየቀጠለ ነዉ አዋቂ ነን ባዮች ደግሞ እንኩዋን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ለማወቅ ይህን መልዕክት የማግኘት ዕድል የላቸዉም ...
ReplyDeleteእግዚኣብሔር ይስጥልኝ
ሁሉም በጊዜው !!!
ReplyDeleteውድ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የዘመን መለወጫ በአዓልን አስመልክተህ ያወጣኸው ጽሁፍ በጣም አስፈላጊ እና ጊዜውን ጠብቆ የወጣ ነው ፡፡ በተለይ እንደዚህ ከማንነታችን የወጡ ስርአቶችን ለማስተካከል በጣም ጠቃሚ ነው ፡፡ እግዚአብሄር በአገልግሎትህ ያበርታህ !!!
Dn Dani GBU!!! beewenetu talak eyta new.ahunem degmi emlew endneseryehonu ayenochen yeseteh,tisgawen yabezaleh egziabher yimesgen!!!!
ReplyDeletebezih agatami ke layi andand anbabeyan kelayi leyetyekut tiyake Dn Danie ke tihufu betach ke astayet meschaw bota melsotal!!!!
Dani kensu mene titbikalehe mane astemarachewena hulume ande new
ReplyDeleteI like the way u write,
ReplyDeleteI like the way u think as well present
This is Gods Gift that shouldn't be killed
I hope u will work on it for the future in all ur Capacity እመቤቴ ከአንተ ጋር ትሁን!!
ሄኖክ አዱኛ ከ አዲስ አበባ INSA
Ayalew Talema,
ReplyDeleteDear Daniel I share all of your concerns. Some influential people should raise the issue to the responsible bodies to give a solution. We should be reasonable for what we are doing. Our elderlies were very carefull for what they did. The new generation shouldn't be careless for such type of issues. It may seem simple for some people. But, small changes can bring great difference in life!!. God bless you for your effort. Make sure that lots of people are sharing your ideas positively and you have great supporters.
it is good Dani, it is a nice felling in you heart in addittion i have no word to say rather than may God bless you
ReplyDeleteThank u Dani. God Bless U.
ReplyDeleteThank you Deacon Daniel
ReplyDeletemay god bless you
ሰላም ላንተ ይሁን ዲ/ን ዳንኤል ከዚህ ከቀን አቆጣጠር ጋር ያተያያዘ በአይምሮዬ የሚመላለስ ጥያቄ አለኝ " የቤተ ክርስቲያን የቀን አቆጣጠር የሚከተለው የጨረቃን ከሆነ ሰንበትን ማክበር ያለብን ከምሽቱ 12 እስከ ቀኑ 12 ይሆናል እንዲሁም አርብ እና እሮብ በምንፆምበት ጊዜ ሐሙስ ከቀኑ12 በኋላ የፍስግ ምግብ መመገብ የለብንም" በዚህ ጉዳይ ላይ ያለውን የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት አቅም እባክህ አሳውቀን፡፡
ReplyDeleteየጌታችን የመዳኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና በረከት ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር አይለየን!!!
ሰላም ላንተ ይሁን ዲ/ን ዳንኤል ከዚህ ከቀን አቆጣጠር ጋር ያተያያዘ በአይምሮዬ የሚመላለስ ጥያቄ አለኝ " የቤተ ክርስቲያን የቀን አቆጣጠር የሚከተለው የጨረቃን ከሆነ ሰንበትን ማክበር ያለብን ከምሽቱ 12 እስከ ቀኑ 12 ይሆናል እንዲሁም አርብ እና እሮብ በምንፆምበት ጊዜ ሐሙስ ከቀኑ12 በኋላ የፍስግ ምግብ መመገብ የለብንም" በዚህ ጉዳይ ላይ ያለውን የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት አቅም እባክህ አሳውቀን፡፡
ReplyDeleteየጌታችን የመዳኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና በረከት ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር አይለየን!!!