Tuesday, September 7, 2010

የሴቶች አገልግሎት በቤተ ክርስቲያን


የሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መጀመርያ በፖርቹጋሎች፣ በኋላም በእንግሊዝ ቅኝ ገዥዎች በደረሰባት መከራ ዐቅሟ ተዳከመ፡፡ መንበረ ­ፓትርያርኩ የነበረበት ሶርያም በደረሰበት ጫና ምክንያት ሕንድን ለመርዳት አልቻለም፡፡
1806 እኤአ ወደ ፕሮቴስታንቶች ማሠልጠኛ እየገቡ በተማሩ አገልጋዮች ምክንያት «ቤተ ክርስቲያን በወንጌል አልተመራችም´ የሚል ንቅናቄ ተጀመረ፡፡ ቀጥሎም «ለቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ ያስፈልጋል´ የሚል እንቅስቃሴ ተቀጣጠለ፡፡ የተሐድሶ ኮሚቴ የሚባልም ተቋቁሞ ምልጃ ቅዱሳን፣ በዓለ ቅዱሳን፣ ነገረ ማርያም፣ ክብረ ሥዕል፣ ቅዳሴ፣ ጾም እና መጻሕፍተ ቅዱሳን እንዲቀሩ ወሰነ፡፡

ይህንን ውሳኔ አብዛኞቹ ጳጳሳት እና ካህናት ተቃወሙት፡፡ ምእመናንም ለሁለት ተከ ፈለ፡፡ ነገር ግን በፕሮቴስታንት እምነት የተለከፉ አገልጋዮች የራሳቸውን ጳጳስ ሾመው ተሐድሶውን ገፉበት፡፡
ተሐድሶዎቹ ቤተ ክርስቲያኒቱን በፍርድ ቤት ከሰሱ፡፡ 1879 ዓም የተጀመረውም ክስ በጁላይ 12 1889 ዓም እኤአ ተጠናቀቀ፡፡ ፍርድ ቤቱም የቤተ ክርስቲያኒቱ ሀብት እና አጥቢያዎች ለሁለት እንዲከፈሉ ወሰነ፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱም በሕግ ለሁለት ተከፈለች፡፡ ተሐድሶዎችም «ማር ቶማ ቤተክርስቲያን´ የሚባል መሠረቱ፡፡
ቤተ ክርስቲያኒቱ ሀብቷን፣ አጥቢያዎቿን እና ገዳማቷን በማጣቷ ተዳከመች፡፡ ሕዝቡም ተስፋ ቆረጠ፡፡ ካህናቱ ደመወዝ አጡ፡፡ አገልግሎቱንም መስጠት ተቸገሩ፡፡ ምእመኑንም ተሐድሶዎቹ እና ፕሮቴስታንቶቹ ይወስዱት ጀመር፡፡
በዚህ ሁኔታ ያዘኑት የሕንድ እናቶች ተሰብስበው «አንድ ሆነን ቤተ ክርስቲያናችንን እንታደግ» ብለው ወሰኑ፡፡ በሳምነቱ ቀናት ሩዝ ሲቀቅሉ አንድ እፍኝ ሩዝ በማስቀመጥ በሰንበት ይዘው ለመምጣት ተስማሙ፡፡ ያንን አጠራቅመውም አብያተ ክርስቲያናቱን አስጠገኑ፡፡ ገዳማቱን አሠሩ፡፡ ለካህናቱ ደመወዝ ከፈሉ፡፡ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከፈቱ፡፡ መም ህራንን አሠለጠኑ፡፡ እንዳሉትም ቤተ ክርስቲያናቸውን ታደጉ፡፡ ዛሬ የሕንድ ሴቶች በቤተ ክርስቲያናቸው ክህነታዊ ባልሆነው አገልግሎት ሁሉ በመሳተፍ ዕድገት እያስመ ዘገቡ ነው፡፡ እኛስ ?
በቤተ ክርስቲያን የሴቶችን ተሳትፎ በተመለከተ ሁለት ዓይነት ጽንፈኛ አስተሳሰቦች አሉ፡፡ የመጀመርያው ሴቶች እስከ ክህነት ድረስ በሚደርስ አገልግሎት መሳተፍ አለባቸው የሚለውና ከቤተ ክርስቲያን አመሠራረት፣ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን እና ከተፈጥሮ ጋር የሚጣረስ አመለካከት ነው፡፡
ሐዋርያት ሁሉም ወንዶች ናቸው፡፡ በጥንቷ የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን የሴቶች ተሳትፎ ክህነታዊ ባልሆነው አገልግሎት ነበር፡፡ ለሴቶች ክህነት የሚሰጥ ቢሆን ኖሮ ከድንግል ማርያም በተሻለ የቀረበ እና የተገባው ባልኖረ ነበር፡፡
ሁለተኛው ደግሞ እናቶች እና እኅቶች ምግብ ከማብሰል ቢበዛም ቆሞ ከማስቀደስ ያለፈ አገልግሎት አይገባቸውም የሚለው እና ሴቶችን ፈጽሞ «የሚያገልለው´ አመለካከት ነው፡፡ ይኼኛውም አመለካከት ቢሆን ድንግል ማርያም በሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን የነበራትን ቦታ የዘነጋ፣ ጌታችንም ሠላሳ ስድስት ቅዱሳት አንስት መምረጡን የማያስ ታውስ አስተሳሰብ ነው፡፡
ትክክለኛው መንገድ ከሁለቱም መካከለኛው ነው፡፡ ለእናቶች እና ለእኅቶች ጾታቸውን ያልረሳ፣ደረጃቸውን የጠበቀ፣በበቂ ሁኔታ ዕውቀታቸውን እና ጊዜያቸውን ሠውተው ሊያገለግሉበት የሚችሉት ተገቢ ቦታ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያስፈልጋቸዋል፡፡
እናቶች እና እኅቶች በብዛት የሚሳተፉባት በቤተ ክርስቲያን የታደለች ናት፡፡ ቤተ ክርስቲያናች ለሁለት ዓመታት ከውጭ ሀገር ምንም ዓይነት ንዋያተ ቅድሳትን ሳታስገባ አገልግሎቷን እንድትቀጥል ያደረጓት እናቶች ናቸው፡፡ አልባሳቱን ፈትለው፣ መጎናጸፊያውን አዘጋጅተው፣ ሞሰበ ወርቁን ፈትለው፣ መገበርያውን መርጠው አዘጋጅተው፣ ተማሪውን አብልተው አስተምረው፣ ቤተ ክርስቲያኑን ጠርገው፣ ምንጣፉን አራግፈው፣ ካህናቱን አብልተው ለዚህ ያደረሱን እናቶቻችን ናቸው፡፡ የግሪክ አልባሳት ቦታውን የያዙት ከሠላሳ ዓመታት ወዲህ ነው፡፡
ሌላው ቀርቶ እንደ እነ እሙሐይ ሐይመት፣ እሙሐይ ገላነሽ የመሳሰሉት አንስት ቅኔውን ተምረው፣ በቅኔውም ተመርቀው፣ የቅኔ መምህራን በመሆን አያሌ ደቀ መዛሙርትን አፍርተዋል፡፡ እንደነ እቴጌ እሌኒ ያሉት ደግሞ የሃይማኖት መጻሕፍትን አበርክተዋል፡፡ እንደ እነ ወለተ ጴጥሮስ ያሉት በሱስንዮስ ዘመን ሃይማኖታቸውን እየዞሩ አስተምረዋል፣ ገዳም መሥርተዋል፡፡ እንደ እነ ክርስቶስ ሠምራ ያሉት በሃይማኖት ተጋድለዋል፣ እንድ እነ መስቀል ክብራ ያሉት ከላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዱን አንጸዋል፡፡
በቤተ ክርስቲያናችን በቂ እና ውጤታማ ዕድገት ሊመጡ ካልቻሉባቸው ምክንያቶች አንዱ የእናቶቻችን እና እኅቶቻችን ምግብ ከማብሰል ያለፈ አገልግሎት ባለመስጠታቸው ነው፡፡ እነርሱም ያንኑ እንደ በቂ ተቀብለውታል እኛም አናበረታታቸውም፡፡ በቤተ ክህነቱም ከተላላኪነት፣ ከገንዘብ ያዥነት፣ ከታይፒስትነት እና መዝገብ ቤትነት ያለፈ ድርሻ ያላቸው እኅቶችን አይቼ አላውቅም፡፡
እናቶቻችን እና እኅቶቻችን ግን ከዚህም የበለጠ ኃላፊነት በቤተ ክርስቲያን ሊኖራቸው ይገባል፡፡ እንደምናውቀው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁለት ዓይነት አገልግሎቶች አሉ፡፡ የክህነት እና የክህነት ያልሆኑ፡፡ 
እናቶቻችን እና እኅቶቻችን ክህነታዊ ባልሆኑት አገልግሎቶች ከወንዶች የተሻለ ውጤታማ ናቸው ብዬ አስባለሁ፡፡ ክህነታዊ ያልሆኑ አገልግሎቶች የምንላቸው በአስተዳደር፣ በፋይናንስ፣ በትምህርት፣ በማኅበራዊ አገልግሎት፣ በማስታረቅ አገልግሎት፣ በኅትመት፣ በንዋያተ ቅድሳት ዝግጅት፣ እና በመሳሰሉት ነው፡፡
በእነዚህ አገልግሎቶች ክርስትናው የገባቸው፣ ደረጃቸውን የሚያውቁ፣ በሃይማኖት ትምህርት የበሰሉ እናቶችን እና እኅቶችን ክህነታዊ ባልሆነው አገልግሎት ማሳተፉ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎቶች ቀልጣፋ እና ውጤታማ ያደርጋቸዋል፡፡
ለምን?
·        እናቶች እና እኅቶች ከወንዶች ይልቅ በአንድ ነገር ላይ ተረጋግተው መሥራት ይችላሉ፡፡ በየጊዜው ስሜታቸውን እና መንገዳቸውን በመቀያየር ሥራዎችን አያባክኑም፡፡
·        በፖለቲካዊ እና ጎሳዊ እንቅስቃሴዎች ላይ የወንዶችን ያህል ጥልቅ ስለማይሉ ዘር እና ፖለቲካን ከእምነት ጋር የመቀላቀሉ በሽታ እምብዛም አይታይባቸውም፡፡
·        በቤተ ክርስቲያን ሰው ለሚያጫርሰው የደብር አስተዳዳሪነት፣ ወረዳ ሊቀ ካህንነት፣ የጳጳስነት እና ሌላውም ዓይነት ሹመት ስለማይመለከታቸው ከሥልጣን ፆር የራቀ አገልግሎት መስጠት ይችላሉ፡፡
·        እነርሱ የቤተ ክርስቲያንን ነገር በሚገባ ካወቁ ልጆቻቸውን ለቤተ ክርስቲያን የሚመቹ አድርገው ማሳደግ ይችላሉ፡፡
·        «ሴት የላከው ጅብ አይፈራም´ ይባላልና ወንዶቹን በትክክለኛው መንገድ እንዲጓዙ መንገዱን ማመላከት እና መግፋትም ይችላሉ፡፡
·        የርኅራኄ እና የኀዘኔታ ልብ ስላላቸው ባለጉዳዮችን በሚገባ ለማስተናገድ፣ ገዳማት እና ለአድባራት፣ ገጠርም አብያተ ክርስቲያናት፣ ተጎዱ ምእመናንም ያዝናሉ፡፡
·        ሕፃናትን በሰንበት /ቤቶች ለማስተማር እኅቶች የተሻለ ትእግሥት እና ችሎታ አላቸው
·        በሕክምና አገልግሎት፣ ድኾችን በመርዳት፣ ማኅበረሰብ ተኮር አገልግልት በመስጠት ሴቶች የተሻለ ውጤታማ ናቸው
በእነዚህ እና በሌሎችም ምክንያቶች እናቶቻችን እና እኅቶቻችን በቤተ ክርስቲያን ተገቢያቸው የሆነውን አገልግሎት እንዲያገለግሉ መበረታታት አለባቸው፡፡ ሌላው ቀርቶ በአበው መካከል ልዩነት እና ግጭት ሲፈጠር ከወንዶቹ ይልቅ አልቅሰውም ይሁን ብልሃት ፈጥረው እንዲታረቁ እና እንዲስማሙ ለማድረግ እናቶቻችን እና እኅቶቻችን ይሻላሉ፡፡

በዚህ አገልግሎት የሚሳተፉት እኅቶች እና እናቶች ግን ለራሳቸውም ሆነ ለቤተ ክርስቲያን የመከራ ምንጭ እንዳይሆኑ መመዘኛዎች ያስፈልጋሉ፡፡ እነዚህ መመዘ ኛዎች ታድያ ወንዶቹንም የሚመለከቱ ናቸው፡፡
 1. የሃይማኖት ትምህርት በሚገባ የተማሩ
 2. የንስሐ አባት ያላቸው እና በሥጋ ወደሙ የጸኑ
 3. በአንድ ባል የጸኑ ወይንም መነኮሳዪያት የሆኑ
 4. በማኅበረሰቡ ዘንድ በሥነ ምግባር የተመሰከረላቸው
 5. ፈሪሃ እግዚአብሔርን እና ትኅትናን ገንዘብ ያደረጉ
መሆን አለባቸው፡፡
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገባቸው እናቶች አና እኅቶች በተገቢው ቦታ እንዲያገለግሉ ካላደረግን በገንዘባቸው የሚመኩ፣ ሥነ ምግባር የሌላቸው፣ ሴትነ ታቸውን ለክፉ ሥራ የሚጠቀሙበት፣ ደረጃቸውን የማያውቁ፣ እነርሱ ተሰድበው ቤተ ክርስቲያንን የሚያሰድቡ፣ ለአባቶች የስሕተት ምንጭ የሚሆኑ ሴቶች ቦታውን ይዘው መከራ ያመጡብናል፡፡


36 comments:

 1. ዳኒ ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡
  መልካም እይታ ነው ሴት እናቶቻችን እና እህቶቻችን ሊሰሩት የሚገባውን አሳይቶናል

  ReplyDelete
 2. ወቅታዊ ጉዳይ በማንሳትህ በጣም አመሰግንሃለሁ ዲ.ዳኒ፡፡ ሴቶቻችን ከእልልታ ባለፈ የጎላተሳትፎ በቤተክርስቲያን ዉስጥ ሲያደርጉ አይታዩምና መልካም ብለሃል፡፡ እንደ እኔ ግን የችግሩ መንስኤዎች እኛዉ ወንዶች ሳንሆን አንቀርም ባይ ነኝ፡፡ ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን ለሴቶች የምትፈቅደዉን አገልግሎት በደንብ ስለ ማናዉቅ ሴት ይህ አልተፈቀደላትም እያልን ክልከላዉን እናበዛለን ይመስለኛል፡፡ አፍ አዉጥተን ባንከለክል እንኳ በአይናችን እናስደነግጣቸዋለን፡፡
  እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመንህን ያርዝምልህ፡፡

  ReplyDelete
 3. Dani yes you write womens they now how to do this.
  MAMO

  ReplyDelete
 4. ዘመካነ ህያዋንSeptember 7, 2010 at 6:41 PM

  dani i do agree with all ur idea.ሴቶች የቤተክርስቲያን ትልቅ ፈተናዎች እየሆኑ ነው በተለይ አባቶች ከሴቶች ምክር ለመቀበል በጣም ጥንቁቅ መሆን አለባቸው። ነኮሳት አባቶቻችን በሁሉም ነገር የሚረዳቸው አስተዋይ ረድእ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን ቢችሉ ምግብ እንኳን በወንዶች እንዲሰራላቸው ማድረግ ቢችሉ ፡ ባይቻል ግን የቀረቧቸውን ሴቶች በአስተዳደር ጉዳይ እንዳይገቡ ማድረግ (ሃላፊነት ተሰጥቷቸው ካልሆነ) ግድ ነው። አሁን አሁን ግን እንደምንሰማው ሁሉም አባት ምንአልባት ሁሉም ጳጳስ አንድ አንድ ዔልዛቤል አለው። በወሬ ፡ በአስተሳሰብ ፡ በስራ ተጽእኖ የምታሳድር። አባቶች ምን አለ ስለሁሉም ነገር አመዛዝነው ማድረግ ቢችሉ ፡ የሰው ወሬ ባይሰሙ ፡ በራሳቸው አይን ያዩትን ለቤተክርስቲያን የሚጠቅመውን ብቻ ቢያደርጉ ብሎ በሚያስቆጭ ሁኔታ። አቤቱ አባቶቻችንን ጠብቅ እባክህ

  ReplyDelete
 5. I do agreee what ever you raised here. I wanna to draw your attention , especially,to two points

  1. እነርሱ የቤተ ክርስቲያንን ነገር በሚገባ ካወቁ ልጆቻቸውን ለቤተ ክርስቲያን የሚመቹ አድርገው ማሳደግ ይችላሉ፡፡

  This reminded me what HH Pope Shenuada III said for an interview he had with a westoxicated journalist; "Why you (Orthodox)are not allowing priesthood of women", HH was asked. They (women)have had more than this, "they are the one who give us bishops, evanglists, priests, deacons.....", HH Pope Shenuada replied.So, having ritually coached women is the timely necessity for our church.

  2. «ሴት የላከው ጅብ አይፈራም´ ይባላልና ወንዶቹን በትክክለኛው መንገድ እንዲጓዙ መንገዱን ማመላከት እና መግፋትም ይችላሉ፡፡

  This is the one of the nicest observations of you. Dani, we have lost so many brothers to the Protestant churches as they have used this principle effectively. I have lost one of my friend who joined them due to love a girl there.

  3. Your views are supported by economic philosophies too. Let me quote one of the bests, "It must be remembered that aesthetic tastes and prefernces are usually guided by the women in the family". We ususally heard of the fact that "missing women in an economy means missing half of labour force;above and more, missing the positive external effects due to elited women". It is not surprise, given this, to set empowering women at the top of the Millenium Development Goals (MDGs)

  4.At last, but not least, the trend of Indian Orthodox Church women is still visible. This trend can easily seen from the fact that most of church business groups (they have so many colleges and schools inspite of thier faithful number, by the way)have in women in thier top positions. I was speechless, while I saw a women (who is PhD actually)adresses a speech for the crowd that get together for special Christmas festival. I wondered to happen in out church, many thanks to you to whom you raised the isssue timely.

  I hope many thoughts will be exchanged over this issue.Thus, waiting them as usual eagerly!

  Peace and blessings to you Daniel
  Wish you a very prosperous New Year.

  ReplyDelete
 6. Ewnet new Dani,man yejemir new teyakew.

  Egziabher biredan ende hind setoch yebekulachinin beneweta destegnoch nen.

  Esi menesha hasab lay asebebetena .......

  yehen yasasebeh Amlak yemesgen.

  ReplyDelete
 7. አንድ ወንድም ምን አለ እስራኤል በጣም የሚሰሩት ለሴቶች ያላቸው ቦታ ነው
  ምክንያቱም ሴቶች በደንብ ከተማሩ
  1 ባሎቻቸውን መግራት ይችላሉ
  2 ልጆቻቸውን ያስተምራሉ ስለዚህ ህጣናት አወኩ ማለት ደግሞ ታሪክ ተቀየረ

  ReplyDelete
 8. Geta hulem serahen yibarekeleh Dani

  ReplyDelete
 9. +++
  ድንቅ የ21ኛው ክ/ዘመን አመለካከት ይህ ነው። ቤ/ክ ከተዘፈቀችብት ችግር ትወጣ ዘንድ የመንፈሳውያት እህቶቻችንና እናቶቻችን አስትዋጾ ቀላል አይደለምና ከሰ/ት/ቤት ጀምሮ በየደረጃው ተግባራዊ ልናደርገው ይገባል። ይህን ቀድመን ጀምረነው ቢሆን ኖሮ ዛሬ እንደ እጅጋየሁ ያሉ በጥባጮች በቤተ ክርስቲያናችን አይፈነጩባትም ነበር።
  እግዚአብሔር ይስጥህ ዲ/ን ዳኒ
  ፍስሓ

  ReplyDelete
 10. Very good point! We need to encourage women's participation in our church. They will be specially fruitful in charity work which our church is lacking.

  ReplyDelete
 11. Daniel you are trying to teach people the role of women in the church. While you are talking about the church you never mention what the holy bible teachs about the role of women in church.What kind of christianity is this (that you are teaching) that doesn't base its thinking and practice on the bible teaching but on self-annointed (self-ordianed to teach) indivduals' opinions (view) or some church practice like you mention (in India).This is deceptive way of devil to pervert orthodox christians from Gospel(Holy bible). Please in the name of Our Lord and Saviour Jesus Chrsit name ,come to your sense and stop misleading people in pretext of "orthodoxawi theaching"

  ReplyDelete
 12. hello my friend! warm greeting ^^!
  your blog looks nice 0_0

  by the way,
  if you need to find unique typography, you can go to our website.

  best regards;

  ReplyDelete
 13. Dear Dn Daniel,

  I loved all of your issues, but this one is the best one. I thanks God for giving you all rounded knowlege. Do you know most of the points which you raised why woman are better than men, are scientifically approved, so many article wrote on it.

  The wise manegement ablity of woman can be seen from your mum, sister and wife. You know if woman are in working team that team is very peacful and joyful. But the number of the woman should be below half of the team, unless the opposite might happen.
  I wish a happy new year for your family

  ReplyDelete
 14. ኃ/ገብርኤል ከአራት ኪሎSeptember 8, 2010 at 4:20 PM

  ለዲ/ን ዳንኤል ክብረት ከነ ሙሉ ቤተሰቡ እና ለዚህ የጡመራ መድረክ እድምተኞች በሙሉ
  ቅዱስ እግዚአብሔር እንደ በደላችንና እርሱን እንደማሳዘናችን ሳይመለከት ስለ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ፣ ለለ ቅዱሳኑ ሀሉ ልመናና ፀሎት እንዲሁም የቀና ሃይማኖታቸውንና ምግባራቸውን ተመልክቶ የገባላቸውን ቃል ኪዳን አስቦ መጪውን አዲስ ዓመት(2003 ዓ.ም) የሰላም፣ የጤና፣ የብልፅግና፣ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ሰላምና አንድነት የምናይበት፣ ምእመናንና ምእመናት በፍቅርና በመተሳሰብ ሆነን ልዑል እግዚአብሔርን የምናመልክበት፣ በሃይማኖትና በምግባር የምንጎለብትበት፣ አውቀን በድፍረት ሳናውቅ በስህተት በተለያየ መልኩ ያቆሸሽነውን የቅዱስ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ (ሰውነታችንን) የምናፀዳበት፣ ከመቼውም ይበልጥ እንደየ አቅማችንና እንደየ ስጦታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል የምንተጋበት፣ ሀገራችንና ህዝቦቿ በአምላካችን የበረከት እጅ የሚዳሰሱበት ዓመት ያድርግልን።
  ወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት ውስጥ ይህንን የጡመራ-መድረክ ከፍቶ ጊዜውን፣ ገንዘቡን፣ ጉልበቱን ጭምር መስዋዕት አድርጎ ስለ ሃገራችንና ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ፣ በወቅቱ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ስላጋጠሟት የውስጥና የውጭ ችግሮች መንስኤያቸው፣ አካሔዳቸው፣ ሊያስከትሉ ስለሚችሉት ጉዳት እንዲሁም ማስታገሻ ብሎም ማሰወገጃ ብሎ ያመነባቸውን የመፍትሔ ሃሳቦች፣ በሃገራችንና በወጪ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን በዕለት ተዕለት ማኅበራዊ ኑሯችን የሚስተዋሉትን ክስተቶች በጎና መጥፎ ጎናቸውን በግልፅና ኅሊናን ሰብስቦ እኔ ማነኝ ምንስ እያደረኩ ነው? ምንስ ማድረግ ይጠበቅብኛል የሚሉትን ጥያቄዎች በውስጣችን እንድንፈጥርና ራሳችንን እንድንፈትሽ በሚያመላክት ደስ በሚል የአቀራረብ ስልት ምግበ ነፍስና ምግበ ስጋን ሲመግበን ነበር።
  ዲ/ን ዳንኤል ይህንን የምታደርገው ማንም ሳያስገድድህና ምንም አይነት ስጋዊ ጥቅም ለማግኘት ብለህ እንዳልሆነና ባሳለፍካት ትንሽ እድሜ ከአባቶች እግር ስር ቁጭ ብለህ የተማርከውንና ድካምና ስንፍና ሳያሸንፍህ በማንበብ እንዲሁም የተለያዩ ጥናቶችን በማድረግ ያካበትከው ዕውቀት የጋን ውስጥ መብራት እንዳይሆን በአንፃሩ ሌሎችን እንዲያስተምር፣ እንዲመክር እና እንዲገስፅ ብለህ መሆኑ ከእኛ ከእድምተኞችህ የተሰወረ አይደለም። በመሆኑም የዚህ አገልግሎትህን ዋጋ ልዑል እግዚአብሄር ይክፈልህ ረዥም ዕድሜን ከሙሉ ጤና ጋር ከመላው ቤተሰብህ ጋር ይስጥልን፣ ዓይነ ልቡናህን ጨምሮ፣ ጨምሮ፣ ጨምሮ ያብራልህ፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በምልጃዋ ትጠብቅህ፣ የቅዱሳን መላእክት ጥበቃቸው አይለይህ።
  በመጪው ዓዲስ ዓመትም ይህንን የተቀደሰ አገልግሎትህን እንደምትቀጥልና ብዙ ቁምነገሮችን እንደምታሰጨብጠን፣ እንደምታስተምረንና እንደምትመክረን ባለ ሙሉ ተስፋ ነን።
  መልካም ዓዲስ ዓመት
  ቸር ያሰማን።

  ReplyDelete
 15. ከደብረ ቁሰቋም
  ይእግዚአብሔር ሰላምና ፍቅር ለናንተ ይሁንና ወንድማችን የጻፈው ጽሁፍ ለሁላችንም አስተማሪ ከመሆኑም በላይ ለወደፊቱ ምን ብናደረገ ወይም ምን ማድረግ አለብን የሚለውን የሚለውን ጭምር የሚያሳስብ መላእክት ያለው ነው።በቤተክርስትያን የእናቶችና የእህቶች አገልግሎት ቀላል እንዳልሆነ ሁላችንም ልንገነዘበ ይገባል.
  እንኩዋን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ

  ReplyDelete
 16. it is current issue to see in our church.Because it occur many divorse.

  ReplyDelete
 17. My message is to the guy above, who tried to criticize Daniel's article for not being "Orthodoxawi".

  What did you get unorthodox in the article?
  I wonder what being orthodox Christian means for you, brother?
  What sentence from the article was against the teachings of the Holy Bible? (I didn't say your commentary or interpretation of the Bible).

  Please, try to see positively where the deacon is trying to point at for the emancipation of our church from the shackles of sin and indolence.

  Stay blessed,

  Deacon Mehari Gebremarqos
  Addis Ababa

  ReplyDelete
 18. ጥበበ ስላሴ ዘቋራ
  ቃለ ሕይወትን ያሰማልን፡፡ መልካም እይታ ነው!

  ReplyDelete
 19. yes it is a very great idea. our sisters also should get closer to the church services other than the ordinary activities they have been thru

  ReplyDelete
 20. ቃለ ሕይወት ያሰማልን !ትክክል ነው ! የቀደሙ እናቶቻችን ለቤተ ክርስቲናችን ለሀገሪቱም ትልቅ አስተዋዸ አድረገዋል ለትውልዱም የሚተርፍ ስራ ሰርተው አልፈዋል ፡፡ በዚሀ ዘመን ያለን እናቶቸ ሆንን እህቶቸ ከማጀት ወይም ከቤታቸን ባለፈ ዲ.ዳንኤል እንዳልከው በቢሮ ስራ ላይ ተሰማርተን ልንገጘኝ እንችል ይሆናል እንጂ ለትውልድ የሚተላለፍ ሀገርን የሚያኮራ ለቤተ ከርስቲያናችን የሚበጅ ተግባሮችን አልተገበርንም እየተገበርንም አንገጘም፡፡ በእውነቱ በሚገባ ልናጤነው ይገባል በትውልዱም እንወቀሳልን እንደ እናቶቻችን ያለ ጀግንነት ይጠበቅብናል በከፉ ስራም የምንጠራ መሆን የለብንም እናቶቻችን ያለፉበትን ዘመን እኛ ዛሬ እንድገመው በአዲሰ ዘመን አዲሰ ስራ አዲስ መንፈስ ይዘን መነሳት ይኖርብናል፡፡

  ዘ አርሴማ

  ReplyDelete
 21. Dear Dn. Daniel, kale hiwot yasemalen.

  As my point of vision you 'Dn. Mehari Gebremarkos'critisized dn. Daniel's article anonimously and then sle dani article tekorkoari, but not truely because u reached me as a misterious person like 'a missionary of tehadiso'. I am so sorry to say that,but i feel that for the second time. If it is wrong, please forgive me.

  Melkam Addis Amet.

  ReplyDelete
 22. Dn Daniel as u explain our sisters doing in our orthodox church is infinite till now. even now they are working in sebeka gubae as the member of church administration is apriciable. to be enhanced such kind of usable service first we all orthodox church members seport them, second u yourself write such kind of supportive education write on easily availabeld ours' news papers, because u now the access of internet very limitted to us.
  Egeziabehere Yesetelgne!
  mulugeta negn from jimma.

  ReplyDelete
 23. ነገሩ ጥሩ ነው ግን በአብዛኛው ሴቶች ቤተክርስቲያነ አካባቢ ለሚነሱ ስህተቶች እንደ ምክንያት እሆኑ ነው የሚታየው ለምሳሌ ለአባቶች እና ወንድሞች መሳሳት ዋነኛዎቹ ናቸው
  የጥንት አባቶቻችን እኮ በጣም አርቆ አሳቢዎች ናቸው ደግሞም ጸጋ መንፈስ ቅዱስ አልተለያቸውም ነበር በዚህ ሁኔታ ውስትጥ ሆነው ሴቶች ጥሩ ችንደሆኑ በያውቁም የመመጣውን ችግር አስቀድመው በማየት ብዙም ወደ ቤ/ክ አገልግሎት እንዲቀርቡ አያበረታቱም ቤተክርስቲያን ፈተና ያለባት ቦታ ስለሆነች እነርሱን ወደዚ እንዲቀርቡ ማድረግ ፈተናውን ማብዛት ይመስለኛል ብርግጥ በጥንቃቄ ከሆነ ያነሳሀው ሃሳብ ጥሩ ነው ዐንድ ቦታ የገጠመኝ ችግር ስለነበረ ነው ፡፡
  ሊ/ስ አዩ

  ReplyDelete
 24. I totally disagree with the above comment. I don't think the women are to blame for most of the problems facing our church. After-all, it is the men who are in position of power and they are the one running havoc in the church.

  I also reject the idea that having a greater involvement of women will somehow exacerbate the situation. What is the evidence for that? You may point to a few women who have become a bad influence on church leaders but they are not representative of the majority the women in our church.

  I am proud to say that Ethiopian women are for the most part well-behaved, hardworking, and devout Christians. They need to be encouraged and empowered to broaden their service to the church.

  ReplyDelete
 25. I agree with kaleab. Men usually acuse women for their wrong doings. the basic thing is trying to find a reason for your failures can not cure from your sins. Please, think twice before you write. As dn. Daniel pointed out above, the church needs to have mechanisms to evaluate the overall personality and "menfesawi tinkare" of a woman before giving key role. This should of course be done for men as well. Haimanotawi meseret yelelachew wendoch meselugn betechristianachinin eyanawetsuat yalut. So dear annonymous, don't make hesty generalizations.
  There are very strong women who are doing great for the church. Don't try to break their heart.

  Beaddisu amet Egziabher Amlak le Betechrstianachin selamin yisitilin, legna degimo menfesawi tinkare yadilen

  ReplyDelete
 26. +++
  D/n Daniel Happy new year.
  I wish for you & your family zemene lukas be promises of good health, peace and stability,new more dreams to fulfill,
  new goals to achieves and new joys to discover.

  ReplyDelete
 27. Selam le Betechristanachen, Selam le hezebachen Kedus Egezeabeher Yaderglen, Thank you for bringing this topick, yes women have been doing great work and are still doing their share and will continue to do so. I am one of them. I will do my part till the day I dye. all women should know AND RESPECT YEEGEZABEHEREN tezaze. the ademenstreathion and KEHENT is not our for us women but that does not mean we have no part in inriching and giving our services to our BETCHIRSTIAN, she needs all hear children to give service. Yekeksochun sera lenesu enetewewe. ABATOCHENEN BEEWENT ENKEBERE ESU TALAKU GETA KEBETO LEMENKUSENA YETERCHWEN, YEKEBCHEWEN, BE EWENT BEMEGEBA MAKEBER YEGEBANAL BETECHRISTIAN AND NECH. ALL OF OUR FATHERS out side of our country or those who are all in the country beesu yetetru nachew. hulunem betalake tehetene beneyezachew yeshalane, yesu tezaze newena yehe ye BORTODOXAWEAN ethiopian gedeta new. Benesu sera gebeto mezebarek yekere ensun MAWARED EN ENNETE ATAWEKUM MALET YEKER, AS ABOUT THIS WOMEN WHO IS DESTROING AND DESRESPICTHING THE CHURCH she is a well knowen trable maker and vicoushouly cruel person yemeyakat yakatal {thous who know her know her} this women never knew BETECHIRISTAINEN ESWA BELO HAIMANOTGNA BALE WEKEBE OR ZAR ALEBEGNE EYLECH YEMETAGURA NEBERCH. EWENT TEDEBEKO IKEREM TARIQUAEN AGER MAWEKU IKEREM. BEBETEKEHENT AKABABE YALUT BEDENBE MANENETWAN BEYAWEKU NORO AYSETGUATEM NEBER. there are people who know her that how meny men she destroyed. naw wed betechirsten zorech. she is ye DABELOS MESAREYA NECH. kefu sew selehonch bezu setoch yeferuwatal wondochunem end ashangulet tchawetebachwalch yemategebabet yelem. Women like here yebetchirstianE TENKE NACHWE egegayehu beyne malet be Americka benorech geze yesarachewn bezu sew yakeal. she is egzeabehere yeregemat nech bederuwan amelake yekefelatal. pepole like here will pay in this life and in the other for the crime they are inflicthing to what CHRESTOSE BEDEBU YEMESERETATEN BETUN YAKOSHESU. este ebakacheu hulachenm le abatochechachen selam betam betam enalekes teslote enaderege Yetebelashew endecetekakele
  Abtoche beandent BETECHIRESTYENEN TAKE BACK THE WAY SHE WAS BEFORE. LET US HELP THEM TO RE UNITE AND BE STRONG AGAIN. WHEN THEY ARE ON AND STRONG, OUR BELOVD BETECHIRSTIAN WILL BE COME MORE STRONGER AND WILL BECOME IMPOSIBLE FOR PEOPLE LIKE THIS WOMEN AND OTHER ENEMY OF OUR CHURCH TO DESTABLIZE ITS PLIARS. I hope ever one would understand my writhing. I am not good in writhing. but i am crying every day for my Betechirstain, LEAGERE and LE ABATOCHE. BETECHIRSTIAN KELELECH AGER YELM. TALEKE ADERA ALEBEN KE EYESUS KERESTOS YETEKEBELENW. ADERA BELETA AYADERGEN.
  THANK YOU

  ReplyDelete
 28. ዳኒ ብዙስለተባልክ ብዙመባሉባያንስህም ነገርግን ዓንድነገር ሁሌም ሊጨመርልህ
  ይገባል እላለሁ እግዚሐብሄር ጸጋህን ያብዛልህ እድሜና ጤና ይስጥህ
  ቃለ ህይወት ያሰማህ ባራኪው ጌታ እግዚሐብሄር ይባርክህ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 29. kale hiwoten yasemalen abete ena be sedete yemnenure setuoche bebelte kale hiwote yasemalen enlalen betecherstyen seratua temskakel senel semeye yatanbete seate wendmachen egziabher angerhe yehene mekre sethacheu ewnete sentu yanbeuo yeuone abesuo abatuoch melequsate ena bezhe ketel wendmachen d.d

  ReplyDelete
 30. ከአንጎላ
  ቃለ ህይወት ያሰማልን!!!
  በጣም አስደሳች እይታ ነው

  ReplyDelete
 31. Qale Hwiot Yasmalne , its seems nice page but i want to gave a comment , why u post the sebket link if u post it its more intrested page

  Egezabher Yebarke Yembetmaryame Brekete Aylyeke

  ReplyDelete
 32. KALE HIWOT YASEMALIN Dn.DANI
  Ahunim bihon setoch bebetekiristian yalachewun dirsha betemelekete yemifeterubinin tiyakewoch ena amelekaketoch atirten mawek ena meleyet yitebekibinal....
  Dn.Dani BE ADDISU AMET wustawi ayinih kaminaw bedenib berto yetelemede eyitahin enditaderisen Amlakachin yirdahi!!!!!!

  ReplyDelete
 33. Dani, I do not know what to say!!!

  ReplyDelete
 34. kalehiwot yasemalin.

  ReplyDelete
 35. Deacon Haileslassie G.


  Deacon kale hiymot yasemaln, yeagelglot zemenh ybarklk

  ReplyDelete