ሟቹ የ «እንደ ቸርነትህ´ መዝሙር ደራሲ ዶክተር ኢሳይያስ ዓለሜ እንዲህ ይላሉ፡-
አንድ አባት አህያውን እየነዳ ከልጁ ጋር መንገድ ጀመረ፡፡ እልፍ እንዳለ ሰዎች ተመለከቱትና «ምን ዓይነት ሞኞች ናቸው፤ እንዴት አህያ እያለ በእግራቸው ይሄዳሉ´ በማለት ተቿቸው፡፡ አባትም ትችቱን ሲሰማ ሀሳቡን ቀየረ፡፡ ሁለቱም አህያዋ ላይ ወጡና መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡ ጥቂት እንደሄዱ ሌሎች ሰዎች አዩዋቸውና «እንዴት ያሉ ጨካኞች ናቸው፤ እንዴት አንድ አህያ ለሁለት ይጋልባሉ´ ብለው ራሳቸውን ነቅንቀውባቸው ጥለዋቸው ሄዱ፡፡
አባትዬውም ከአህያዋ ላይ ወረደ፡፡ እርሱ ከኋላ አህያዋን እየነዳ ልጁን በአህያዋ ጭኖ ጉዞውን ተያያዘው፡፡ የተወሰነ መንገድ ከተጓዘ በኋላም ሌሎች መንገደኞችን አገኘ፡፡ እነዚያም መንገደኞች አባት እና ልጁን አዩና «አይ ስምንተኛው ሺ፤ አያሳየን የለ፤ ልጁ በአህያ ተቀምጦ ሽማግሌ አባቱን በእግሩ ያስኬደዋል፡፡ አበስኩ ገበርኩ´ ሲሉ ሰማ፡፡
ወዲያው ልጁን ከአህያዋ አውርዶ እርሱ ተጫነና ጉዞው ተጀመረ፡፡ መንገዳቸውን እንዳጋመሱም ከገበያ የመጡ ሰዎችን አገኟቸው፡፡ እነዚያም መንገደኞች ጉዟቸውን ገትተው «እንዴት ምኑንም የማያውቅ ልጁን በእግሩ እያስደገደገ እርሱ በአህያ ይሄዳል፤ ወይ ጭካኔ፣ወይ ጭካኔ´ ብለው ደረታቸውን ደቅተው ሄዱ፡፡
በዚህ ጊዜ አባትዬው ከአህያዋ ወረደና ለልጁ እንዲህ አለው፡፡ «አየህ ልጄ በዚህ ዓለም ምንም ነገር ብትሠራ ሰውን ሁሉ ማስደሰት አይችልም፡፡ ሰዎች እንዲህ ይሉኛል እያልክ የምትፈራ ከሆነ ምንም ነገር ማድረግ አትችልም፡፡ ሰዎች ምንም ብታደርግ የሚሉት አያጡምና፡፡ አንተ ሰውን ሳይሆን ስሕተትን ፍራ፡፡ ትችትን ሳይሆን ኃጢአትን ፍራ፡፡ ሰዎች ስላሉት ብቻ የምትቀበል ከሆነ ሃሳብህን መቶ ጊዜ ትቀያይራለህ፡፡ መቀበል ያለብህ የሚሉት ነገር ትክክል ከሆነ ብቻ ነው፡፡´ አለው፡፡ ከዚያም አባት እና ልጅ እየተጨዋወቱ መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡
ሰዎች ቢያመሰግኑን አይጠላም፡፡ እንዲያመሰግኑን ብለን መሥራት ግን የለብንም፡፡ ለምዶብን አንዳንዶቻችን የብርጭቆውን ውኃ ስናይ ግማሽ ጎዶሎ መሆኑን እንጂ ግማሽ ሙሉ መሆኑን አናይም፡፡
የሰዎችን ሃሳብ ስንሰማ ቢያንስ ሦስት ነገሮችን መመዘን አለብን፡፡
ይህ ሰው ይህንን አስተያየት ለመስጠት ብቁ ነውን? በሞያው፣ በዕድሜው፣ በውሎው፣ በትምህርቱ፣ በልምዱ፣ ይህንን አስተያየት ለመስጠት ሚዛን የሚደፋ ከሆነ ግምት ውስጥ አስገብተን እንመርምረው፡፡
ይህ ሰው ይህንን አስተያየት አስተያየት ሲሰጥ ከልቡ ነውን? አስቦበት፣ አመዛዝኖ፣ በመሠረተ ሃሳብ አስደግፎ ነው ወይስ እንዲሁ ስለመጣለት በስሜት ተነሣሥቶ?
ይህ ሰው ከሚያነሣው ነገር ጋር የጥቅም ግጭት የለውምን? ክብሩን፣ ሥልጣኑን፣ ገንዘቡን ስለሚነካበት ያንን ለማስጠበቅ ነውን? ተመቅኝቶ፣ ቀንቶ ወይንም ግላዊነት አጥቅቶት ነውን?
ጉዳዩን ያለዚያ ቀን ሰምቶት የማያውቅ፣ በዚያ ነገር በትምህርት፣ በዕድሜ፣ በንባብ ወይንም በልምድ የተገኘ ዕውቀት የሌለው፤ እንዴው አፌ ተባልኝ፣ ንግግሬ ተደመጠልኝ፣ ጨዋታዬ ደራልኝ ያለ ሁሉ የሚናገረውን ሰምተን ሃሳባችን መቀየር፣ መጠራጠር ወይንም ደግሞ ራሳችንን እንደ ስሕተተኛ መቁጠር የለብንም፡፡ አንዳንዱኮ «ይህ ነገር አላማረብህም´ ሲል የሠራውን አርፍተ ነገር ትርጉም እንኳን በቅጡ አያውቀውም፡፡ አንዳንዱም ሰው ሁሉ ሲናገር ከሚቀርብኝ ብሎ ሃሳብ የሚሰጥም አለ፡፡
እንደመጣለት የሚናገረውስ ቢሆን፡፡ ሊቃውንት «አንድ ጊዜ ከመናገር በፊት ሁለት ጊዜ ማሰብ ይገባል´ ይላሉ፡፡ እንኳን ሁለት ጊዜ አንድ ጊዜ እንኳን ሳያስብበት እንደመጣለት የሚናገረውን ሰው እየሰማን እኛ ለምን እንዳደዳለን? ለምንስ መንገዳችንን እንስታለን፡፡ ምናልባትኮ አንዳንዱ የተናገረው ለርሱ ቀልድ ይሆናል? በጆሮው የሰማውን በአንደበቱ ለማውጣት ምንም ዓይነት ሂደት በአእምሮው የማያከናውን ሰው ሞልቷል፡፡ የመንገድ ላይ ቱቦ ያስገባውን ሁሉ እንደሚያወጣ ያየውን እና የሰማውን ሁሉ ሳያጣራ፣ ሳያበጥር፣ ሳይመረምር፣ ይዋል ይደር ሳይል እንዳለ የሚለቅም አለኮ፡፡
«ይህን ነገር ማድረግሽ ስሕተት ነው´ ሲል «ማድረግ የነበረብኝ እኔ ነበርኩ´ እያለ መሆኑን ልንረዳለት የሚገባን ሰውኮ አለ፡፡ «ሰዎች እንዲህ ይላሉ´ ከሚለው ወገናችን በዛ ያለው ራሱ የሚለውን «ሰዎች´ በሚል ባለቤት አልባ ባለቤት በኩል እየነገረን መሆኑንም መጠርጠር ይገባል፡፡
ታድያ የሚያዋጣው ምንድን ነው? መሥራት፡፡ መጀመርያ ነገር ለምናደርገው ሁሉ ለራሳችን አሳማኝ ምክንያት ይኑረን፡፡ ርግጠኞች እንሁን፡፡ ከምንመራበት መሠረተ ሃሳብ፣ ከእውነት እና ከታወቁ እውነታዎች ጋር መዝነንው ትክክል መሆኑን እንመንበት፡፡ ሰዎች በማስረጃ ወይንም በመረጃ የሚያቀርቡልንን ሃሳብ ሁሉ ለመቀበል ለራሳችን ዝግጁ እንሁን፡፡
ከዚያ በኋላ ያለ የሌለ ጉልበታችንን ሥራችን ላይ እናውል፡፡ ምን ተባለ ም?ን አሉ? ምን መልስ ልስጥ? በምን ላሳምናቸው? እያልን ስንብሰከሰክ ወርቃማውን የሥራ ጊዜ አናሳልፈው፡፡ «ወፎች ከጭንቅላታችን በላይ እንዳይበርሩ ማድረግ አይቻልም፤ በጭንቅላታችን ላይ ጎጆ እንዳይሠሩ ማድረግ ግን ይቻላል» የሚል አባባል አለ፡፡ ሰዎች ስለ እኛ ሥራ አንሥተው እንዳያሙ፤ እንዳይተቹ፣ እንዳያጣጥሉ፣ እንዳያንቋሽሹ ማድረግ አንችልም፡፡ የእነርሱ ትችት እና ሐሜት በጆሯችን ገብቶ ኅሊናችንን እንዳይረበሸን ማድረግ ግን እንችላለን፡፡ የተነገረውን ሁሉ ማስማት የተጮኸውን ሁሉ ማዳመጥ የለብንምና፡፡
ደግሞም ሁሉንም ሰዎች ማስደሰት አይቻልም፡፡ እኛ ሃሳብ እና አእምሮ ያላቸውን፣ በምላሳቸው ሳይሆን በጭንቅላታቸው የሚያስቡትን፡፡ አንደበታቸው ከልባቸው፣ ስሜታቸው ከኅሊናቸው ያልቀደመባቸውን ሰዎች፣ ያውም ከእነርሱም መካከል ነገራችን ሊገባቸው የሚችሉትን ካረካን እድለኞች ነን፡፡
ብዙ የሚለፈልፉ ሰዎችን አንፍረድባቸው፡፡ ሠርተው የሚያሳዩት ነገር የላቸውምና፡፡ ብዙ የሚሠሩ ሰዎች ግን ምንም መናገር አያስፈልጋቸውም፡፡ ከንግግር በላይ ተግባር መልስ ነውና፡፡ ሰዎች ለምን እንዲህ ይሉኛል? ለምን የኔ ሥራ አይገባቸውም? ለምን አይረዱኝም? እያሉ በመጨነቅ አእምሮን በማይጠቅሙ ቫይረሶች ከመሙላት የሚችሉትን ሠርቶ ሰዎች በራሳቸው ጊዜ እንዲረዱት መተው ነው፡፡
በዓለም ላይኮ መሬት ክብ ናት በማለታቸው ሞት የተፈረደባቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን ሰዎች ስለተቿቸውና በዘመኑ ስላልተቀበሉት ብለው አልተውትም፡፡ በመጨረሻ ያሸነፉት እነርሱ ናቸው፡፡ በወቅቱ ዓለም ያላየውን እነርሱ አዩ፡፡ ዓለም ግን ዘግይቶ እነርሱ ያዩትን አየ፡፡ ያን ጊዜ ዓለም ይቅርታ ጠየቀ፡፡
የምንሠራው ሥራ ዛሬ ሰዎች ላይገባቸው ይችላል፤ ላይፈልጉትም ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ቀን አለው፡፡ ሰው ሁሉ በአንድ ቀን አልተፈጠረምና በአንድ ቀን እኩል አይረዳም፡፡ ቀልድ ተነግሮት እንኳን ሲጀመር የሚስቅ አለ፤ በመካከል መሳቅ የሚጀምር አለ፤ ሲያልቅ ገብቶት የሚስቅ አለ፤ አድሮ የሚያስቀው አለ፤ ከርሞ የሚያስቀው አለ፤ ጭራሽ የማያስቀውም አለ፡፡ አሁን ቀልዱ ቀልድ መሆኑን በምንድን ነው ማወቅ የሚቻለው?
ደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ ስልብ ነበሩ ይባላል፡፡ ታድያ ዐፄ ምኒሊክ ጎራ ሸለሟቸውና ሰው ሁሉ አደነቀላቸው፡፡ ወዳጆቻቸውም «ይህንን ነገር የማያደንቅ ገብረ ሐና ብቻ ነው» ይሏቸዋል፡፡ ያስጠሯቸውና ለአለቃ ገብረ ሐና ያሳዩዋቸዋል፡፡ አለቃም ጎራዴውን እያገላበጡ «አይ ጎራዴ፣ አይ ጎራዴ፣ ጎራዴ፣ ጥሩ ጎራዴ» ብለው ያደንቁላቸዋል፡፡ ባልቻም ደስ ብሏቸው ይለያያሉ፡፡
ወዳጆቻቸውም «ገብረ ሐና ምናለ?» ብለው ይጠይቋቸዋል፡፡ ደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶም «በደንብ ነው ያደነቀው» ብለው ይመልሳሉ፡፡ «እስኪ ምናለ?» ይላሉ ወግ ፈላጊዎቹ፡፡ «አይ ጎራዴ፣ አይ ጎራዴ ብሎ አደነቀ» ይሏቸዋል፡፡ ያ ሁሉ ሰው በሳቅ ያወካና «እንዴ ደጃዝማች ባልቻ ከዚህ በላይ ገብረ ሐና ምን ሊልዎት ነው» ብለው ያስረዷቸዋል፡፡ ያን ጊዜ ጀግናው ባልቻ እገላለሁ ብለው ያዙኝ ልቀቁኝ አሉ ይባላል፡፡
ዐረቦች «ግመሎችም ይሄዳሉ፣ ውሾቹም ይጮኻሉ» የሚል አባባል አላቸው፡፡ የዐረብ ነጋዴዎች ግመሎቻቸውን ጭነው በመንደሮቹ መካከል ሲያልፉ ውሾቹ እየጮኹ አያሳልፏቸውም፡፡ ነገር ግን በእነርሱ ምክንያት መንገዳቸውን አያቆሙም፡፡ ግመሎቹም መሄዳቸው፣ ውኾቹም መጮኻቸው የማይቀር ነገር ነውና፡፡
ሰው በሚያገባውም በማያገባውም መተቸቱ የማይቀር ነው፡፡ ዋናው መርጦ መውሰዱ ላይ ነው፡፡ ነጭ ሲደረግ ለምን ጥቁር አልሆነም፣ ጥቁር ሲደረግ ለምን ሰማያዊ? ሰማያዊ ሲሆን ለምን ግራጫ? ግራጫ ሲሆን ለምን ቢጫ? ይቀጥላል፡፡ ሰው ይህንን ሁሉ እየሰማ ቀለም ሲቀያይር የሚኖር ከሆነ የሚሠራው ቤት ቀለም ማስተማርያ መሆኑ ነው፡፡
እኛም የምንናገር ሰዎችም ብንሆን የምንናገረው ነገር የዕውቀታችን ማስመስከርያ ሞን የለበትም፡፡ ሊሆን ሊደረግ የሚችል መሆኑን እና አለመሆኑን መለየት አለብንኮ፡፡ ሴትዮዋ ወንበር ገዝታ ከመጣች በኋላ «አይ እዚህ ሱቅኮ በርካሽ የሚሸጥ ነበረልሽ´ ብሎ ማስፀፀት ጥቅሙ ምንድን ነው? እየደጋገመ ሴት የወለደን ሰው «የአሁኗ እንኳን ወንድ ብትሆን ጥሩ ነበር» እያሉ መመጻደቅ ምንድን ነው? ሰውዬው ወስኖ አልወለዳት፡፡ ሰውዬው ከሞተ በኋላ ቋሚውን «እንዲህ ቢያደርግ ኖሮኮ አይሞትም ነበር» እያሉ ለማይመለስ ነገር ቆሽት ማሳረር ምን የሚሉት ሞያ ነው?
ሰው የሚለውን ሁሉ አልቀበልም ማለትም በሽታ ነው፡፡ ሰው የሚለውን ሁሉ መቀበልም ጦስ ነው፡፡ ሰው ለሚለው ሁሉ ዝም ማለትም በሽታ ነው፡፡ ሰው ለሚለው ሁሉ መልስ መስጠትም ጦስ ነው፡፡ ሰው በተቸ ቁጥር ሃሳብን መቀየር ጅልነት ነው፡፡ ሰው የፈለገውን ቢል ሃሳቤን አልቀይርም ማለትም ግትርነት ነው፡፡ ሰው በተናገረ ቁጥር መናደድ እና ማረርም ቂልነት ነው፡፡ በሰው ንግግር ሁሉ መቀለድም ቂላቂልነት ነው፡፡
ልብ ያለው የሚባለውን ነገር ጆሮው በር ላይ አስቀምጦ ይመዝነዋል፡፡ የሚረባ ከሆነ ያስገባዋል፤ የማይረባ ከሆነ ተቀባይ እንዳጣ ፖስታ ይመልሰዋል፡፡ እንዲህ ያለው ሰው በልቡናው ውስጥ የማይጠቅሙ ሃሳቦች ማጠራቀሚያ ቅርጫት የለውም፡፡
Thanks decon daniel
ReplyDeletegad bless you
đồng tâm
Deletegame mu
cho thuê phòng trọ
cho thuê phòng trọ
nhac san cuc manh
tư vấn pháp luật qua điện thoại
văn phòng luật
số điện thoại tư vấn luật
thành lập công ty
Wededikut, Temarkubet...Endnorbet Egiziabher Yirdagn.
ReplyDeleteEgiziabher Yitebikilin.
Wow, Itis happening every event and it is important for all of us who needs change!!!!!!!!!
ReplyDeletewhere is Dr esayas aleme now?
ReplyDeletethank you so much anjeten arasikegn i was reading one comment on your article the person was trying to criticized you {d daniel kibret} infact he was insulting our intellegince by talling us that we are radical and blind follwers of you it's like we don't know the difference b|n dark and light we don't have the stage to expres our view just does't mean we don't know about our church and the other brother who commented about radicalism please rechuck ur dictionary no hard filling though
ReplyDeleteዶክተር ኢሳይያስ ዓለሜ አሁን በሕይወት የሉም፡፡ እኛ በሚገባ ያላወቅናቸው ፣ ብዙ ሥራ ለትውልድ የሠሩ ሰው ናቸው፡፡ «ምክር በኪስ» የምትል መጽሐፋቸውን ያገኘ ሰው ፈልጎ ያንብባት፤ ከኪሱ አይለያትም፡፡ በነገራችን ላይ ግብጽ ውስጥ ከአርባ ዓመት በላይ የተጋደሉትን፣ እነ አቡነ ቄርሎስን እና አቡነ ሺኖዳን ያፈሩትን፣ታላቁን ኢትዮጵያዊ የዘመናችን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስን ከግብጽ ወደ ተሠወሩበት ኢየሩሳሌም የሸኟቸው እርሳቸው ናቸው፡፡ ዲያቆን ኤፍሬም እሸቴን የሚጨቀጭቀው ሰው ካገኘ የኒህን አባት ታሪክ ማሰባሰብ ጀምሮ ነበር፡፡
ReplyDeleteWEY Dn. Daniel,
ReplyDeleteI like this mikir.
Bicha Bertalign.
ውስጤን እንድፈትሽ በቀላሉ እያደረከኝ ነው
ReplyDeleteሊ/ስ/አዩ
Dani u r realy fantastic!
ReplyDeleteMy God! blessed u.
ይሄ ለኔ ነው። የጥበባት ጌታ አሁንም ጥበቡን ጨምሮ ያብዛልህ!
ReplyDeletethankyou Dn.Daniel I
ReplyDeleteEgziabher Yabertah!!!!!
Deacon Ephrem!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteWhere are you? I need to know more about this Dr..
Who was he?
What did he do to the church and the country?
What were his contributions?
What was his occupation?
Although it is not uncommon to hear his name as the writer of Endecherineth, there is almost nothing known about him- particularly by our generation. Can you tell us, PLEASE.
You owe us this much love, big brothers.
Deacon Mehari Gebremarqos
Thanks Dn. Daniel! May God endow you longevity and wisdom!
ReplyDeleteሰው በተናገረ ቁጥር ሁሉም ትክክል እየመሰለኝ ለምደነግጥ ለእኔ ጥሩ መልስ ነውና ረድኤተ እግዚአብሔር አይለይህ
ReplyDeleteGod blessed u!Dn/Daniel betam teru temhrt new berta bezu entebkalen.
ReplyDeletedear Daneil kibret views followers I have got a new sermon of danny from this site. http://multimedia.eotc-mkidusan.org/video/?video=0442929613
ReplyDeleteyewetat awaqi beyehalahu daniya qetelebet
ReplyDeleteDaniel from canda
LEARN SO MUCH THANK U Dn.daniel. bertalene!!!!
ReplyDeletei love it
ReplyDeleteቃለ ህይወት ያሰማልን ዲ.ዳንኤል መልዕክቱ በዚህ ዘመን በየደቂቃው ወሬ እንደ ጅረት ውኃ ለሚወስደን እጅግ በጣም አስተማሪ ብዙ ቁም ነገሮችን የያዘ ማንነትን የሚያሳይ አሰተማሪ ነው ። እግዚአብሔር ይጠብቅህ አሜን።
ReplyDeleteEgziabehar agelglotehen ybarkleh astemary tsehuf nuw.
ReplyDeleteThank you Dani, Very very nice, I learnt a lot.
ReplyDeleteBlessings...
Dn.DANIEL U are great.thank you yeabat ena yeljun tarik yekne wubet (kebede michael) anbbew germogn neber
ReplyDeleteEjig des yemil timihirt new kale hiwet yasemalen
ReplyDeleteDear Daniel,
ReplyDeleteIt has been a few years since I started reading your articles. They are very important for every body. Sometimes the articles become guidelines for day to day life and another time they are reminders and again another time they tend to be an input for developing positive thinking and one more again they become really important for those who would like to follow the right way while communicating with people, working with people and all in all living with people. My last suggestion/comment is all of the articles/advises are really important for every one excluding our religious back ground. All of them are just basic needs for every one.So I suggest you to make them available for every one in different formats such as Audio versions (This time it becomes easy for every one to put a CD and listen for three hours than to read three lines), pocket book, shelf size,Video version. I really appreciate your initiatives and keep up the good job. Sincerely yours, Eyob, Addis Ababa,Ethiopia
የራሳቸው አቋም ለሌላቸው ሰዎች ትልቅ ትምህርት የሚሰጣቸዉ ይመስልኛል።
ReplyDeleteእገዚአብሔር ይባርክህ
Thankyou Dear Daniel.Where can i get the book`mikir bekis`.Sincerely; Markos
ReplyDeleteI wish I read this 11 years ago....
ReplyDeleteGetachew
This is absolutely true for most of our community members in US. Discussion on something meaningful is a good culture. But what is commonly known is the other one. Talk, talk and talk ... over the phone. Most of the time it is about others. Really boring!
ReplyDeletePersonally, I did avoid the source of the nonsense talk(the person)intentionally. Nothing to lose!
Dani if you could answer? The photo you use most of for you’re article did you took the photo by your self or you have special sores. Because I am always amazed by your choice.
ReplyDeleteMAMO
ሰው የሚለውን ሁሉ አልቀበልም ማለትም በሽታ ነው፡፡ ሰው የሚለውን ሁሉ መቀበልም ጦስ ነው፡፡ ሰው ለሚለው ሁሉ ዝም ማለትም በሽታ ነው፡፡ ሰው ለሚለው ሁሉ መልስ መስጠትም ጦስ ነው፡፡ ሰው በተቸ ቁጥር ሃሳብን መቀየር ጅልነት ነው፡፡ ሰው የፈለገውን ቢል ሃሳቤን አልቀይርም ማለትም ግትርነት ነው፡፡ ሰው በተናገረ ቁጥር መናደድ እና ማረርም ቂልነት ነው፡፡ በሰው ንግግር ሁሉ መቀለድም ቂላቂልነት ነው፡፡
ReplyDeleteዳኒ አመሰግናለው
ReplyDeleteግን የአባትየውና የልጁ ታሪክ ላይ በጣም ግራ ከመጋባታቸው የተነሳ አህያውን ሁሉ ተሸክመውት ነበር ያኔም ግን ሰው ያወራ ነበር።
ከላይ አስተያየት የሰጡት አንባብያን(የተወሰኑት) ራሳቸውን የአባትየውና የልጁን(የሚወራባቸው ነው) ያደረጉት ታዲያ የሚያወራው ማን ነው?
Who bought Daniel's book, titled "yehulet hawultoch wog"?
ReplyDeletePlease, let's support him continue publishing his articles and "wogoch" and help our brothers and sisters, who have no access to internet, learn from the great thoughts, ideas, knowledge, personality etc of Dn Daniel.
Dn Daniel i share Eyob's comment
ReplyDeletemamaru from harar
በርግጥም ግመሎቹም ይሄዳሉ ውሾቹም ይጮኻሉ ... ይገርማል…!!!!
ReplyDeleteቃለ ህይወት ያሰማልን
ReplyDeleteስለ ዶክተር ኢሳይያስ ዓለሜ በጥናታዊ ጽሁፍህ ላይ ብታዘጋጅ ደስ ይለኛል፡፡ ብዙ ሰውም እሳቸውን የማወቅ ጉጉቱ ይጨምራል፡፡
እግዚአብሔር ይስጥልኝ
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እግዚአብሄር ይባርክህ፡፡
ReplyDeleteጥልቅ ምክርህ ባደግህባት ባህር ዳር ከተማ በሚታተም ጋዜጣ ሰፍሮ ድረ ገፅ የማግኘት እድሉ ለሌላቸው እንዲደርስ ተመኘሁ፡፡ ነገር ግን ፈቃድህን እንዴት ላገኝ እችላለሁ? ፈቃድህ ከሆነ በኢ-ሜል (bekur1987@gmail.com) መልስ ብትሰጠኝ?
እግዚአብሔር ይስጥልኝ
ኤፍሬሜ..ይህው ጨቀጨቅንህ!..እባክህ ታረካቸውን አውጣልን
ReplyDeletePlease Dn. Efrem? Please.....please....please?
ReplyDeleteThanks Deakon
ReplyDeleteMay GOD bless you;
Dn Ephrem;
You need to write that book; I think there a lot that we can learn from the Dr. Don't hide it.
Thanks
Kale Hiwot Yasemalin Dn. Daniel!
ReplyDeleteDn. Ephrem, please lets hear about ዶክተር ኢሳይያስ ዓለሜ
Ameha Giyorgis
DC
I like this soooooooooo much!
ReplyDeleteGod Bless!
the only time you will not be criticised is if you do noeting,has noeting,say noeting and are noeting;you will end up with a big NOETING!
ReplyDeleteMay God bless u DN Dani.
ReplyDeleteDn Efrem Please hurry up.
ITS BAD
ReplyDeletePlease Dn Ephrem ....Please ...Please
ReplyDeleteDn. Daniel i agree with Bekel Asege's comment ...
It is completely true idea for this nation
ReplyDeletedani ende daniel ke anbesochi menga yawutah
ReplyDeletedani kechalk sile AGEU yetewesene neger beliligni
egzer yistiligni
michael yemata ke wag himra
sekota
Tikikil !!!!
ReplyDeletekalhiwet yasemaln
ReplyDeleteegziabher ybakr !!
please tell us Dr.Essayase Aleme!!!!!!
ReplyDeleteእኔ ነኝ ሁልጊዜ ምንም ነገር ሳይ መተቸት ነው እኔ አላረግውም በጣም አመሰግናለው ዳኒ
ReplyDelete“አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት ምን አጠበች አሉ”
ReplyDeleteሃይ ዳኒ እንዴት ከርመሃል?...ምነው ባክህ ይህን ሳይሞቅ የፈላ በእውቀቱ የተባለ ፀሃፉ ነኝ ባይ ተመፃዳቂ ብትመክረው ...ደግሞ ይመስለኛል ወዳጃሞች ናችሁ ..ታድያ ወዳጅ ሲያጠፋ ዝም ማለቱ በእርሱ ደም አያስጠይቅም ትላለህ?ለማንኛውም ይህን ስድብ አይሉት ምክር የሆነ ጭረቴን አድርስልኝ ...ምናልባት በመልክቴ ውስጥ ሌላ ስርአት ያላቸውን የቤተ ክህነት ውጤቶችን አስቀይሜም እንደሁ ..ይሄው እዚሁ አለሁና ልመከር...መቼም ከቡጢኖቹ የእኔ ይሻላል ይመስለኛል ለማንኛውም አንሆ መልዕክቴ ለጨዋው በዕውቀቱ..
……..ጉድ እኮ ነው….ስው እንደምን ይዳፈራል በሉ?......ደግሞ እኮ መድፈሩ መዳፈሩ የከፋው ከፈጣሪው ወይ ከፈጣሪ የቅርብ ወዳጆች ጋር መሆኑ ደግሞ የነገሩን ክብደት ይጨምረዋል፡፡
ቀጣዩ ክፋት ደግሞ ያጎረሰን እጅ መንከስ ነው። ከዚህም እጅግ የከፈው ያስተማረን የመከረን የገሰፀን እውቀት ያስጨበጠን አካል ማለቴ ሃይማኖት፣ቤተሰብ፣ማህበረሰብ፣ህብረተሰብ ወይም ግለሰብና መንግስት ላይ ዞሮ በአጉል አውቃለሁ ስሌት መመጻደቁ አንድም ከሰውኛ ልኬት ማቅለሉ ሳያንስ ከጌታም ደጅ ውጉዝ ከማርዩስ ማስባሉ የማይቀር ሀቅ መሆኑ እሙን ነው።
አንዳንዴ ከየት አንዴት መጥተው አድገው ይህንን ትልቅ ሀጥያት አይሉት ኩነኔ አንዲሰሩ ካስቻላቸው እውቀት ላይ የመድረሳቸውን ሚስጥር የሚዘነጉና ገና ምኑንም ሳይጨብጡት በቅይጥ አንባቢ ጭብጨባ እና ሙገሳ የዝነኝነት ስሜት የሚሰማቸው ነገን ከዛሬ በተሻለ መልኩ የሚያጨበጭቡላቸውን እጆች ለማብዛት እንቅልፍ አጥተው ያደጉበትን ስርኣት እና ትውፊት እፀፅ የሚያበዙ ያቺን የገብስ ዝንጣይ የምታህል ዕውቀት ይዘው በዚችው ዕውቀታቸው ለመመጻደቅ የሚሹ ብዙዎች ናቸው። ታድያ እነዚህ ስዎች አዋቂ፣ሊቅ፣ጠቢብ እንዲባሉ በዘመናቸው አሳር መከራ ሲያስግጣቸው የነበረውን ድህነት ከመፍታት ይልቅ ሳይማር አስተምሮ ሳያውቅ አሳውቆ ነገን ለልጄ ብሎ ጦሙን አድሮ ቁርስ አብልቶ ያስተማረን ዘመን፣ትውልድ፣ባህልና እምነት መውቀስና መዝለፍ ይቀናቸዋል ከመቅናትም በላይ የተፈላሰፉ የሚመስላቸው አወቅን ባይ በእውቀቱዎች እጅግ በጣም ብዙ ናቸው ፡፡ ይህ ደግሞ ነገን በልጆቹ ተስፋ ያደረገን ማህበረሰብ እጅጉን ያሰከፋል፡፡
ቃል ቢኖር ከማስከፋትም በላይ ………..ይሆን ነበር
ይገርማል………….
ትላንት ፈደልን ከስነ-ምግባር ጋር ያስተማረች ቤተ ክህነት ዛሬ ስለጠንን ባሉ ስልጡን ስይጣኖች ክብሯ መነሳቱ እጅጉን ያበሽቃል…እኔን በግሌ እጅጉን አብግኖኛል፡፡
ትላንት ይበሉት ድርቆሽ አጥተው ይለብሱት ድሪቶ ቸግሯቸው ቀን ከሌት ከአንዱ ቀዬ ወደ አንዱ መንደር እየዞሩ ከውሻው ከውርጩ ….ከፀሐዩ ጋር ተጋፍጠው ሲኖሩ ድህነታቸውን ሳትንቅ ያስተማረችን፣የመከረችን፣የዘከረችና ስነ- ስርዓትም ሆነ ግብረ ገብነት የሞላት ቤተ ክህነት ሁና ሳለች እርሷኑ በሰጠቸው ዕውቀት ራሳቸውን አንደ አዋቂ አስበው መጠሪያቸውን በዕውቀቱ አስብለው ቀን ሲያልፍላቸው መመፃደቃቸው የበዛ ….ቅብጠታቸው ቅጥ ያጣ የዓለም ጭብጨባና ፉጨት ልባቸውን የሰለባቸው ቅብ ሊቆች የመብዛታቸው ነገር እጅጉን ያሳዝናል።
መቼም የዕውቀትን ፍሬ በልቶ መልሶ የዕውቀቱን ባለቤት ዓይን ለመጠንቆል ወይንም አንተ ደደብ መሃይም ለማለት ልብን አቁሞ ብዕር አቅልሞ ለአጉል ፍልስፍና ከመንጠራራት እውቀት የሌለበት መከባበር ወይንም ሳያውቁት የአምላካቸውን ክቡር ቃል የጠበቁ እነርሱ በርግጥም በአንፃራዊ እይታ ሲታዩ አዋቂዎች ናቸው።
አዳም በበላው ፍሬአወቅኩ ሲል ቃል አፈረሰ ትዕዛዝ ተላለፈ……..ልወቅ ባለበት ቅፅፍት ባዶነቱን ከራቁትነቱ ጀምሮ መረዳት ጀመረ ሲቀጥል አወቅኩ ባይነቱ አይወጣው መከራና ስቃይ አመጣበት።
ዛሬም አወቅን ብለው ሲቦጠርቁ ባዶነታቸው የሚሳበቅባቸው አልፎ ተርፎ ያስተማራቸውን አካል ብዕር ሲሰብሩ ያኔ በመማራቸው ያከበራቸው ህዝብ ያቀላቸዋል ከዚህም በላይ ዛሬ ለቆሙበት የዝና ማማ ላይ እንዲወጡ መወጣጫ የደረደረላቸው ህብረተሰብ ሲያወርዳቸው በመጡበት መወጣጫ እንኳን እንዲወርዱ እድሉን አይሰጣቸውም…..ያኔ የተመፃደቁበት ዕውቀታቸው ከመሬት የስብት ህግ ከልሎ አያኖራቸውምና ወርደው እንደ እንቧይ ሲፈርጡ መታየታቸው የማይቅር ሀቅ ነው፡፡
መቼም ከቀጣ የመከረ ይሻላልና እንደስው እንመክራቸው/እንዘክራቸው/ ዘንድ ግድ አለብን እሰቡ የምንመክራችሁ ከስተታችሁ እንድትማሩ ብቻም ሳይሆን ስታጠፉ ስናይ ዝም ብንል ከጥፋታችሁም በላይ እኛም ተጠያቂዎች ነንና እንሆ ከደማችሁ ንፁ ለመሆን አንሆ ልንመክራችሁ ….ልናስመክራችሁ ግድ አለብንና እባካችሁ ተመከሩ፡፡
በተለይ ….በተለይ አንተ ማነህ ….ራስህን በዕውቀቱ ብለህ የጠራህ ጀግና ….መቼም ካንተ ወዲያ አዋቂ፣ፀሐፊ፣ተራኪ፣ገጣሚ እንደሌለ ውስጥህ ከኔ ወዲያ ፉጨት አፍ ማሞጥመጥ ነው እያለ እንደሚተርክልህ በግብርህ ብናውቅም …ብታንስም አናውቃለንና ስማነ
“በአፍ ይጠፉ በለፈለፉ”
መቼም የዚህን ፍቺ ላንታ ማስረዳት አዋቂነትህን ከመሻገርም በለይ በተደፍርኩ ስሜት ሊያስቆጣህ ቢችልም ያንተ መቆጣትና መናደድ እጁን ከነከስከው ህዝብ ብዛት አይልቅምና ስማነ እንደሰማንህ…..ማንም ይከበር ይፈልግ ቀድሞ ማክበር ይጠበቅበታልና እባክህን የከዚህ በፊቱ ድፍረትህና ንቀትህ ይብቃ…….መከበር በከንፈር ነውና እባክህ ሰይጣናዊ ስልጡንነትህን ለራስህ በልብህ ይዘህ ኑር፡፡
የስንትን ዘመን ታሪክ ያላትን ቤ/ክ ታሪኳን ትውፉቷን ልትተች ቀርቶ ልታስበው አይገባህም ….ቢገባህም እንኳን በልብህ ይዘህ ኑር፡፡ ልብ በል ከዚህ ማህበረሰብ ጋር መጣላት ማለት ዓሳ ሳለህ ከባህር እንደመውጣት ነውና እባክህ ተከበር።መቼም ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ ነውና ተረቱ ……በፈጠረህ እንከባበር …….መቼም አንተ ጌታ የለህምና በጌታ አንልህም ……ትፈራውም ትሰጋውም ነገርህ የሰማይ ሳይሆን የምድር ህግ ነውና በህግ እንከባበር !! አደግመዋለሁ አ-ን-ከ-ባ-በ-ር!!!!!!
በነገራችን ላይ ነገር ካልገባህ በምሳሌ ማውራት እንችላለን አንችላለን ስንል ግን እንዳትንቀን …ይህን ማለታችን ካንተ አጉል አዋቂነት የሚሻል መስሎን እንጂ…..ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ እንዲባልም እናውቃለንና እስካሁን የተተየበው ካልገባህ እንካችሁ በምሳሌ…….
“አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል”
እናልህ ዘንዶው የወጣ ቀን ግን ማጠፊያው ያጥርሃል …….ባህሩ ውስጥ ያለ አንደ ምን ከዛ ዘንዶ ያመልጣል?እንጃ..
ለማንኛውም ብዙ እመከርህ እዘክርህ ቢኖረኝም እዚህ ላይ ላብቃ ምክንያቱም ለአዋቂ አንዲት ቃል በቂው ናትና።
አንተ ደግሞ ከአዋቂነትም ከምግባርህም በላይ አዋቂነትህን በስምህ ገልጠሃልና ለዛሬው በዚህ ላብቃ።
በዕውቀቱ የሰማይ ጌታ የዕውቀትህም የስምህም ባለቤት ልብ ይስጥህ….ይስጠን
አሜን!!!!!!!
ሚያዝያ 8/03 ዓ.ም በቀድሞው ሮዝ በአሁኑ አዲስ ጉዳይ የመጋቢት ዕትም ላይ ከአሜን ባሻገር በሚለው አምድ ስር በዕውቀቱ “እግር አልባው ባለ ክንፍ” በሚል ርዕስ ለፃፈው ድፍረት የተሞለበት ፅሁፍ ካነበብኩ በኃላ የተሰማኝን እንሆ ለፀሃፊው ምላሽ ይሆን ዘንድ ዳዴ ባለለ የስነ-ፅሁፍ ችሎታዬ ፃፍኩት፡፡ይቅርታ ጫርኩት።
Ye enatu lij
daniel gave as his view about the matter that strikes him and thanks.it is up 2 us to evaluate and take good points and leave what we didnot agree.but one fool above me talk irrelevant things about others who express their view freely.
ReplyDeleteif u dislike that person s writting forget it.tesabi athun be daniel tsuhf lay....
Don´t take anything personally, in short
ReplyDeleteWhat ever people say or do is not because of you.
The four Agreements, by Don Miguel Ruiz
D.Daniel berta....
ReplyDeleteTolessa Kebede
ReplyDeleteAs to me you are the heart of orthodx tewahido church God bless you.
Hi Dn. Daniel
ReplyDeleteI really appreciate your talent. I want to say you please keep going keep going brother. I was following your preach in video recorded document and i was happy with that at that moment. Now, I am following your articles and I am happy with this again.
God bless you!!!!!!
tnxs
ReplyDeleteReally it help to know and increase the understanding of the reality of in this world what happens in this time.
ReplyDeleteThank you Dn. Daniel mikirh betam tiru new.Hulachinim alubaltan titen keseran yihch hager yet endemitiders megemet ayakitim. Dn. tsihufihin bedenb anebebkut ena and tiyake yecharebign " sew hulu and ken altefeterem ende?" yikirta his lemawtat felge sayhon andand gize sanawkew tiyake lifetir yemichil neger silemininager new. Ene yemawkew sew hulu be elete arb endetefetere ena gizewun tebiko endemiweled new. Lemitaberekitachew menfesawim honu alemawi tsihufochih salameseginih alalifim Egziabher be edmena tena yitebikih elalehu. Ameseginalehu
ReplyDeleteGod bless Dn.daniel! thank you so much by the name of God
ReplyDeleteDn. Daniel beTam new ynemameseginih tsihufochihin anbibiewalehu be-andilay kebabi meqi bizu negerochin agichiebih alehu yemameseginew gin amlake qidusan le welajachin ena abatachin yasadegun abune gorgoriwos (aba mezigebe silasie) ye ziway hamere brihan q.gebrael gedam lanesasachew ena gedamuwan lemeseretat cheru medahanie-alem yikiber yimesigen lantem Admiena Tieninet yagonatsifih ye-Amebietach fiqruwan ataqwarTibih tanurlih
ReplyDeleteGod bless you
ReplyDeleteyes
Deletenice please quickly present for us
ReplyDelete