Tuesday, August 17, 2010

መጀመሪያ መሰማማት ብንጀምር


ዲያቆን መሐሪ ገብረ ማርቆስ
የእነዚህ ሁሉ መፍትሔ ሐሳቦች መነሻ መሆን ያለበት መጀመሪያ መሰማማት ስንጀምር ይመስለኛል፡፡ የተማረው የቤተክርስቲያን ትውልድ ማድረግ መጀመር ያለበት ነገር መጀመሪያ ማድመጥ ነው- መጽሐፍ ለማድመጥ የፈጠናችሁ ለመናገር የዘገያችሁ ሁኑ እንዲል፡፡

የትኛውንም ችግር ለመፍታት መጀመሪያ ችግሩ ምን እንደሆነ በአግባቡ መረዳት አለብን፡፡ ከዚያ ያን ችግር ለመፍታት “ምን ምን ጥሬ ሀብቶች አሉን?” ብለን መጠየቅ ይገባናል፡፡ ከዚህ በኋላ ነው ከብዙ አማራጭ መፍትሔዎች መካከል በጥቂት ቤዛ የተሻለ ስኬት የምናገኝበትን መምረጥ የምንችለው፡፡ ይህንን ለማድረግ መጀመሪያ የዚህ ትውልድ አባላት መደማመጥ ያለብን ይመስለኛል፡፡

ምን እናድምጥ?

መጀመሪያ በዚህ ረገድ የተሠሩ ጥናቶችን እናገላብጥ፡፡ አልተሠሩ እንደሆነም ማኅበረ ቅዱሳን የምርምር ወጪያቸውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ሸፍኖ አጥኚዎች ችግሩን ከሥሩ እንዲያጠኑት ይደረግ፡፡ የተሠሩትም ሆኑ ወደፊት የሚሠሩት ጥናቶችም ለሰፊው ሕዝብ የሚደርስበት መንገድ ይመቻች፡፡ ጥናቶቹና ውጤቶቻቸው በየደረጃው ካለው የተማረ ሰው አንሥቶ እስከ እያንዳንዷ መበለት ቤት የሚገቡበትን መንገድ መፍጠር ያስፈልገናል፡፡

 ለዚህም ከኢንተርኔት እስከ የቡናላይ ወሬ ያሉ ስትራቴጂዎች አገልግሎት ላይ ይውላሉ፡፡ በዚህም ችግሩ የአባ ጳውሎስና የአባ መርቆሬዎስ ወይም የእበላባዮችና የግብር አግቢዎቻቸው ብቻ ሳይሆን የነገውን ትውልድ አምላክ የሚነሣ፣ ቤተክርስቲያን የሚያሳጣ፣ ቅርስ የሚነፍግ፣ ማንነትን የሚያጥል፣ ተነቅሎ መጣል ያለበት መራራ ሳንክ መሆኑን እንዲሰማው ማድረግ የሚቻል ይመስለኛል፡፡ የኛ ጥረት መሆን ያለበት ሰዎቹ እንዲሰማቸው ማድረግ ሳይሆን ያለውን መረጃ ማሳወቅ ነው፡፡ የችግሩ ምሬት በራሱ የማንንም ስሜት ሳይቆነጥጥ (ባያንገሸግሽ እንኳ) አይቀርምና፡፡

ይህ የማሳወቅ ተግባር መፍትሔውን ወደማሰብ መምራቱ አይቀሬ ነው፡፡ መፍትሔዎቹንም ከቀደሙትም፣ ከካህናቱም፣ ከምእመናኑም ማድመጥ ተገቢ ይሆናል፡፡ ከዚያ በኋላ የተሻለውንና በአመክንዮ የተደገፈውን መፍትሔ አጽድቆ ወደ ተግባር መግባት ይቻላል፡፡ የትግበራው አካላት የሚሆኑት ሁሉም የቤተክርስቲያኗ ልጆችም የመፍትሔውም ምንጮች ስለሆኑም ሁሉም በባለቤትነት ስሜት ሥራውን ሊያከናውን ይችላል የሚል እምነት አለኝ፡፡

ነገሮች ቀላል ይናሉ ብሎ መገመት ሞኝነት ይመስለኛል- በተለይ ሲጀመር፡፡ ግን በእግዚአብሔር ይቻላል፡፡ አትርሱ! የእግዚአብሔርና የጌዴዎን ሰልፍ ነው፡፡ እግዚአብሔርም ብቻውን አልተሰለፈም፡፡ ጌዴዎንም ብቻውን አላሸነፈም፡፡

8 comments:

 1. እሌኒ ከሲራክዩስAugust 17, 2010 at 9:29 PM

  + + +

  በደንብ ያስማማል ዲ/ን ዳኒ

  ReplyDelete
 2. ጥሩ ጅምር ነው እኔም የምደግፈው "ከመስማማት በፊት መሰማማት" መንገዱን ቢያቀናው ... ጥርጊያውን ቢያዘጋጀው ፍጻሜው መልካም ይሆናል የሚል እምነት አለኝ። ለዚህም የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን።

  ReplyDelete
 3. መፍትሔ ብዬ የማምነው እራስን በትህትና ዝቅ ማድረግ እና ለሰዎች ቦታ መስጠት ነው ብዬ አምናልሁ።

  ላለመደማመጥ እና ላለመስማማት የተስማማ ትውልድ ሆነናል።

  ReplyDelete
 4. Yikirta yideregilignina ene bebekule "research yisera" yemilew lay alsimamam. research gelemele eyetebale yemitefa gize yale ayimeslegnim. "The problem, the causes of the problem, some solutions" kulich bilew eyetayun research madireg min ametaw. The basic thing is action. May be we can research on the effect of our action and learn from it in an on-going manner to improve our strategies. I think D.n Danial has beriefly presented his research although he didn't describe the method (which is not necessary for this audience, i think).

  ReplyDelete
 5. Unless we all speak out the true cause of the mess we are in,the truth that God knows,our hearts know,any attempt to resolve it remains impossible! Because God is God of truth.This is a matter of church,house of God where only truth should be spoken. Others before this refreshed attempt to bring about unity and peace, tried their calculated solution to the problem,but to no avail.
  The EOTC was a dominant factor in the history of Ethiopia in the past.Infact,Ethiopia had always had central governments that were highly linked to the church and its matters.They were also 'protectors'of the church.Except Yodit gudit,Gragn Mohammed,Deregue and the present government,Ethiopia was always governed by christian kings and Emperors.During the time of these four 'alaweayan negestat' our church was in trouble in many respects.It is no wonder to be in such a testing time once again as the very cause of the mess our church is now in is linked to the palace and to its opposition. Thus,any solution we seek is tied to the good will of those bodies too.Therefore,I personally agree with the assertion by some that unity of our fathers is possible only if there is a national reconciliation. And I also believe that this is possible if our fathers on both sides push the leaders in the palace and in the opposition side to compromise and forgive one another for the sake of our church,our country and the people.
  It is only then the other performance issues of 'betekihinet' can be addressed.Those trouble maker hands in the church there and here have linkages to the palace and its opposition rspectively.

  ReplyDelete
 6. እኔ በበኩሌ በ ዳ/ን ዳንኤል ውጥን ሀሳብ ሙሉለሙሉ እስማማለሁ የመጀምረያ ትልቁ ችግር አለማዳመጥ፤አለመደማመጥን ያስከትላል አለመደማመጥ ደግሞ ያለመከባበርንና እና ችግሩን አለመዳመጥ ያስከትላል ተደማምጠን ችግሩን ካልዳመጥነው ችግሩ ከልላመ ከልተብላላ ለችግሩ መፍትሄ ማግኘት እየከበደን ይመጣና ጭራሽ እየሻከረ መዳመጥ አስቸጋሪ ይሆንብናል።ስለዚህ ክብሩ ይስፋ ፈጣሪ አምላክ እንድንደማመጥ እንድንተባበር እንድንከባበር አንድ እንድንሆን አዘዘ አስተማረን እንጂ እንድንለያይ አላዘዘም አበው እንዲሉ"ነገርን አዳምጦ እህልን አላምጦ"።ምክንያቱም ለማንኛውም ችግር መንስዔ እንዳለው ሁሉ እንዲሁም ለማንኛውም መንስዔ ላለው ችግር እንዲሁ መፍትሄም አለው። መፍትሄውን ለማግኘት ደግሞ(1)መከባበር/መደማመጥ/ዕቅድ ውጥን/ጥናት/ተግባር/ውጤት።"ላንድ ብርቱ ሁለት መድሃኒቱ"ነውና ኦርቶዶክስያውያን በሙሉ በቅን አስተሳሰብና ያላሰለሰ ጥረት ከእግዛብሄር እርዳታ ጋር ውጤት።አሜን የእመቤታችን አማላጅነት የቅዱሳን ጸሎት አይለየን አሜን።

  ReplyDelete
 7. Thank you Dn mahri,

  In addition to the solution mentiond, let us live christanity. How can I expalin dears? am I going as the God will? If any one answer 'yes', the one who say 'yes' can sove this problem...

  ReplyDelete
 8. First Thank God for everything then for helping us discuss, read or write about this matter especially ( by the initiation of Dn Daniel)
  I think first let us repent ourselves and save our live for all what we did, the reason I said this is as the bible "The King- Metshafe Negist" sailites get bad king and removed from their place when the peoples sin alot. It happened to us now because of our sin that we end up having these kind of battel on authority. In general let us repent first then second let us have "subaea" and cry for our fathers who are losing thier "Mekelit" and being Yetenbit Mefetsemia" so that God will show what they are doing and what their fathers did before them.

  ReplyDelete