አንዳንድ ጊዜ በሕይወታችን የዕለት ተዕለት ተግባራት የሚያጋጥሙንን ነገሮች ካስተዋልናቸው በትምህርት ቤት የማናገኛቸውን ዕውቀቶች እንገበይባቸዋለን፡፡ መደበኛውን ሥራችንን እንኳን ቢሆን በማዳመጥ እና በፍቅር ከሠራነው ለዕድሜ ልክ የሚሆኑ ዕውቀቶችን እግረ መንገዳችንን እናገኛለን፡፡ አንዲት አሜሪካዊት ነርስን ያጋጠማት ነገርም እንደዋዛ ነበር ሕይወቷን የቀየረው፡፡
አንድ ቀን አንድ ሽማግሌ ታካሚ ሰው ከነርሷ ፊት ለፊት ተቀምጠው አሁንም አሁንም ይቁነጠነጡ ነበር፡፡ አሁንም አሁንም ደጋግመው ሰዓታቸውን ያያሉ፡፡ ነርሷ ገረማትና ረጋ ብለው ሕክምናቸውን እንዲከታተሉ ነገረቻቸው፡፡ ሃሳቧን ተቀብለው ለጥቂት ሰኮንዶች ረጋ ቢሉም አሁንም የቀደመ ነገራቸው ተመለሰ፡፡
«ለምንድን ነው ይህንን ያህል ያልተረጋጉት? ያጋጠመዎ ችግር አለ?» አለቻቸው፡፡
«ፈጽሞ፤ ምንም ዓይነት ችግር አላጋጠመኝም»
«ታድያ ለምን ይቁነጠነጣሉ፤ መረጋጋትኮ አልቻሉም» አለቻቸው፡፡
«ይቅርታ» አሉና አንገታቸውን ደፋ አደረጉ፡፡ ነገር ግን ወዲያውኑ ሰዓታቸውን ደግመው ተመለከቱት፡፡
«ሐኪሙን ለማግኘት የቸኮሉበት ምክንያት አለ?» አለቻቸው ነርሷ የሰውዬው ሁኔታ እንግዳ ሆኖባት፡፡
«አዎ፤ በቶሎ እርሳቸው ጋር ቀርቤ ብጨርስ ጥሩ ነው» አሏት፡፡
«ሌላ ሐኪም ጋር ቀጠሮ ይዘዋል» አለቻቸው፡፡
«ፈጽሞ፤ ሌላ ሐኪም ጋርስ ቀጠሮ የለኝም» አሉ ታካሚው፡፡
«ታድያ ወዴት ለመሄድ ነው ይህንን ያህል የቸኮሉት፡፡»
«ከባለቤቴ ጋር አምስት ሰዓት ላይ ቀጠሮ አለኝ» አሉ ታካሚው፡፡
«ኦ፤ ከባለቤትዎ ጋር ከሆነማ ነገሩ ቀላል ነው፤ ማስረዳትም ይችላሉ፤ ባለቤትዎም ቢሆኑኮ የርስዎን ታክመው መዳን ይፈልጉታል፡፡ እናም እባክዎ አሁን በቂ ጊዜ ስለ ሌለዎ ይደውሉላቸውና አንድ አሥራ አምስት ደቂቃ እንደሚያረፍዱ ይንገሯቸው» አለች ነፍሷ እፎይታ እየተሰማት፡፡
«ባለቤቴ ጋር መደወል አልችልም፡፡ እርሷ ብደውልላትም መደወሌን አታውቅም፤ መደወሌንም አታስታውስም» አሉ በኀዘን ስሜት፡፡
«እንዴ ለምን?» አለች ነርሷ አሁን እንደገና ግራ እየተጋባች፡፡
«እርሷ ታምማለች፡፡ ያለችውም በአረጋውያን መጦርያ ነው፡፡ ሁሉንም ነገር አታስታውሰውም፡፡ አልዛይመር የተባለው በሽታ በጣም አጥቅቷታል፡፡» አሉና ታካሚው ሰዓታቸውን ተመለከቱ፡፡
«ታድያ በዚህ ዓይነት እርስዎንስ ያስታውሱዎታል እንዴ?» አለች ነርሷ በተሰበረ ልብ፡፡
«የኔ ልጅ እርሷኮ እኔንም አታስታውሰኝም፡፡ ፈጽማ ረስታኛለች» አሉ ታካሚው፡፡
«ማንነትዎን አያስታውሱዎትም፤ አያውቁዎትም ማለት ነው?»
«አዎ አታውቀኝም፡፡ የምታስታውሰው ነገርም የላትም፤ ፈጽማ ረስታኛለች፤ የምገዛላትን፤ የማደርግላትን ነገር ሁሉ ረስታዋለች፡፡ እኔ አሁን ማን እንደሆንኩ አታውቅም»
«ታድያ እንደዚህ የማያስታውሱዎ ከሆነ ለምን ቸኮሉ?» ለእርሳቸውኮ አምስት ሰዓትም ሆነ ሰባት ሰዓት ያው ነው፡፡ በሉ ቀስ ብለው ሕክምናዎን ጨርሰው ይሂዱ» አለች ነርሷ ነገሩን በማቅለል፡፡
«የለም የኔ ልጅ፤ እንደዚያ አይደለም፡፡ እኔ እርሷጋ ዘወትር እሑድ በአምስት ሰዓት መሄድን አስለምጃለሁ፡፡ ከርሷ ጋር በዚህ ሰዓት ቀጠሮ አለኝ፡፡ ብታውቀውም ባታውቀውም፤ ብታስታውሰውም ባታስታውሰውም ቀጠሮዬ ግን አይቀርም፡፡ ዋናው ነገር የርሷ ማስታወስ አይደለም ልጄ፤ የኔ ማክበር ነው፡፡ ይህ ለእኔ እና ለእርሷ ፍቅር ከሚከፈሉት መሥዋዕትነቶች አንዱ ነው፡፡ እርሷ አታውቀኝም፤ እኔ ግን አውቃታለሁ፡፡ ትናንት እንደዚህ አልነበረችም፡፡ እኔ የትናንትናዋን ሚስቴን ነው የማስታውሰው፡፡ ስለዚህ በሰዓቱ መሄድ አለብኝ፡፡
«ያኔ አታዬኝም፤ አትሰማብኝም ብዬ ምንም ነገር ተደብቄያት አድርጌ አላውቅም ነበር፡፡ ዛሬም አታውቅም ብዬ ምንም ነገር ላደርግ አልፈልግም፡፡ በሰው አለማወቅ መጠቀም ይበልጥ አላዋቂነት ነው ልጄ፡፡»
«ለመሆኑ ካላስታወሱዎት አሁን ሂደው ምን ያደርጋሉ?» አለች ነርሷ የኒህን አስገራሚ ሰው የኑሮ ምሥጢር ለማወቅ ጓጉታ፡፡
«ልብሷን እቀይርላታለሁ፤ የቤቷን አበባ እቀይራለሁ፡፡ ወደ ውጭ አወጣትና ብታስታው ሰውም ባታስታውሰውም ዝም ብዬ በዚህ ሳምንት የሆነውን ነገር አወራታለሁ፤ ያለፈውን ትዝታ እያነሣሁ አጫውታታለሁ፡፡ ብትስቅም፣ ባትስቅም አንዳንድ ጊዜ ቀልድ እነግራታለሁ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ አጫጭር ታሪኮችን አነብላታለሁ፡፡ ይህ ሁሉ ድሮ ደኅና እያለች የማደርግላት ነው፡፡ አንዳችም አላጓድልባትም፡፡ አየሽ ልጄ፣ እኔ ያኔ ስንጋባ ቃል የገባሁት ለሚስቴ እንዲህ እና እንዲያ አደርግላታለሁ ብዬ እንጂ እርሷ እንዲህ እና እንዲያ ታደርግልኛለች ብዬ አይደለም፡፡ ይህንን ቃል የገባችው እርሷ ናት፡፡ እርሷ ደግሞ እስከ ምትችል ድረስ ይህንን ነገር አክብራ ፈጽማለች፡፡ አሁን ግን አትችልም፡፡ እኔ ግን ቃል የገባሁትን መፈጸም እችላለሁ፡፡ ስለዚህ ለምን አስቀርባታለሁ፡፡ አንቺ ለምን የራስሽን አታደርጊም? ያንቺን ጥሩነት እና መጥፎነት ለምን ሰዎች ይወስኑልሻል? አንቺ ራስሽ መወሰን አትችይም?»
«አምስት ደቂቃዎን ብቻ ልውሰድብዎት፤ ይህንን ሁሉ እንደሚያደርጉላቸው ውለታዎን የማያስቡልዎ ከሆነ፤ ከርሳቸውም አንዳች ምላሽ የማያገኙ ከሆነ፤ ምን ይሁነኝ ብለው ይደክማሉ?» አለች ነርሷ አገጯን በመዳፏ ደግፋ፡፡
«እኔ ለሚስቴ አንዳች ነገር የማደርገው ውለታ ፍለጋ ብዬ አይደለም፡፡ የኔ ደስታ ሳደርግ እንጂ ሲደረግልኝ የሚገኝ አይደለም፤ በመስጠት እንጂ በመቀበል አይገኝም፤ በመሞት እንጂ በመግደል አይገኝም፤ እኛ አብረን ለመኖር ተስማማን፤ ቃል ገባን እንጂ፤ በደኅንነታችን ጊዜ ብቻ አብረን ለመሥራት ኮንትራት አልተፈራረምንም፡፡ ለኔ በደጉ ጊዜም ሚስቴ፣ ናት በክፉው ጊዜም ሚስቴ ናት፡፡ ሳትታመምም ሚስቴ ናት፤ ታምማም ሚስቴ ናት፡፡ ሌላው ቀርቶ ስትሞትም ሚስቴ ናት፡፡ እርሷ ብታልፍም እኔ ግን ትዝታዋን አግብቼው እቀጥላለሁ፡፡ ከዚያም ደግሞ በሞት እከተላታለሁ፡፡ ስለሚቀጥለው ዓለም አላውቅም፡፡ ከቻልኩ ግን እዚያም ብትሆን ሚስቴ ናት፡፡ እኔ ባልዋ ስሆን ለርሷ የባልነት ግዴታዬን ለማድረግ እንጂ ከርሷ ለመቀበል አይደለም፡፡ እርሷም የርሷን ለማድረግ እንጂ ከኔ ለመቀበል አይደለም፡፡ ልጄ ከሰጡሽ ተቀበይ እንጂ ለመቀበል ግን ስትይ ግን አትስጭ፡፡ አሁን ይብቃኝና እባክሽን ሐኪሙ ጋር ቶሎ አገናኝኝና ልሂድ፡፡» አሉ ታካሚው አሁንም ሰዓታቸውን እያዩ፡፡ ነርሷ ተገረመች፡፡
«ካላስቸገርኩዎ እባክዎን የባለቤትዎን ስም ይንገሩኝ» አለች ነርሷ በሶፍት ዓይኖቿን እየጠረገች፡፡
«ባለቤቴ ባርባራ ትባላለች፤ የኔ ከመዝገቡ ላይ አለልሽ» አሏት፡፡
«አዎ ሚስተር ስቴፈን» አለችና ማወቋን ገለጠችላቸው፡፡
ቀዳሚው ታካሚ ከሐኪሙ ጋ ለመውጣት ሲዘገዩ እኒህኛው ታካሚ ተነሡና ሄዱ፡፡ «እባክዎን ቆዩ» ለማለት ነርሷ ልብ አልቀረላትም፡፡
ነርሷ ፈቃድ ወሰደችና ለአሥራ አምስት ቀናት ያህል ቤቷ ተቀመጠች፡፡ እኒያ አረጋዊ ታካሚ የነገሯትን ነገር ደግማ ደጋግማ አምሰለሰለችው፡፡ በእርሳቸው ሕይወት ውስጥ ያለውን መመርያ መረመረችው፡፡ ከራስዋም ጋር ለማዛመድ ሞከረች፡፡ በአሥራ አምስተኛው ቀን አንድ ሃሳብ መጣላት፡፡ ሰዎች በራሳቸው ተነሣሽነት ከማንም ዋጋ እና ውለታ ሳይጠብቁ በጎ ነገርን እንዲያደርጉ የሚያበረታታ፤ የሚያስተባብር እና የሚያስተምር ተቋም መመሥረት፡፡
እጅግ ብዙ ሰዎችን በዚህ ዓላማ ያሰለፈ አንድ ትልቅ ተቋም መሠረተች «ባርባራ እና ስቴፈን» ይባላል፡፡
ይህንን ታሪክ ሳነብብ ብዙ ነገሮች ታወሱኝ፡፡ አንተ እንዲህ የማታደርግ ከሆነ እኔም እንዲህ አደርጋለሁ ብለው በእልህ ዥዋዥዌ የሚጫወቱ ባል እና ሚስት፡፡ ከእገሊት ጋር ስለሄደ ከእገሌ ጋር ሄጄ ልኩን እሰጠዋለሁ ብለው የሚጠዛጠዙ ፍቅረኞች፡፡ ሌላው ሰው ቀጠሮ ስለማያከብር የኛ ቀጠሮ ማክበር ምን ዋጋ አለው ብለው አርፋጅ የሆኑ ሰዎች፡፡ የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ እንደሚባለው ሌላው ሰው እየዘረፈ የኔ ሐቀኛ መሆን ምን ዋጋ አለው ብለው ራሳቸውን በሌሎች ምክንያት ያበላሹ ሰዎች፡፡
ተማሪዎቹ ለትምህርቱ ትኩረት ካልሰጡት እኔ ምን አግብቶኝ እጨነቃለሁ ብለው የተማሪዎቻቸው ቸልተኛነት የተጋባባቸው መምህራን፡፡ የሠፈሩ ሰው ቆሻሻ የትም እየጣለ እኔ ብቻዬን ብጠነቀቅ ምን ዋጋ አለው ብለው እነርሱም ከበራቸው ላይ ቆሻሻ መከመር የጀመሩ ሰዎች፡፡
እገሌ ከኔ ሠርግ አልመጣም ብለው ከሰው ሠርግ የቀሩ፤ እገሌ ልቅሶ ሳይደርሰኝ ቀረ ብለው ከሰው ልቅሶ የቀሩ፡፡ እገሌ ታምሜ አልጠየቀኝም ብለው ሲታመም በመቅረት ብድር የሚመልሱ ሰዎች፤ እገሌ ሰላም አላለኝምና ሰላም አልለውም ብለው ሰላምታ ያቆሙ ሰዎች፤ ሌሎቹም ሌሎቹም፡፡
እገሌ አስቀይሞኛልና ከዕድር ከማኅበር ተለይቻለሁ፤ እገሌ እንደምጠብቀው አልሆነልኝምና ከዛሬ ጀምሮ አልመጣም፡፡ ከመንግሥት ጋር ተጣልቻለሁና ከንግዲህ ለሀገሬ አንዳች በጎ ነገር አልሠራም፡፡ ፓትርያርኩ ሊሰሙ አልቻሉምና ከንግዲህ ስደተኛ፣ ገለልተኛ፣ ቁሪተኛ፣ ስሞተኛ ሆኛለሁ፡፡ እነ እገሌ ለምሠራው ሥራ፣ለምሰጠው አገልግሎት፣ለማደርገው አስተዋጽዖ ግምት አልሰጡትምና ትቼዋለሁ፤ የምንለውን ሰዎች ሚስተር ስቴፋን ቢሰሙ ምን ይሉ ይሆን?
እኒያ ታካሚ ሽማግሌ እንዳሉት ለምን ይሆን ግን የኛን ማንነት ሰዎች የሚወስኑት? ፀሐይ ትወጣለች፤ ነገር ግን እኛ እንድንሞቃት አስባ አይደለም፡፡ እርሷ ግን ምንጊዜም ትወጣለች፡፡ ነፋሱም ይነፍሳል፤ እኛ እህል ብናበራይበትም ባናበራይበትም ይነፍሳል፡፡ መሬት በፀሐይ ዙርያ ትዞራለች፤ በብርሃኑ እና በጨለማው ጊዜ ሰዎች ቢጠቀሙም ባይጠቀሙም ትዞራለች፡፡ እነዚህ ሁሉ የእነርሱን ድርሻ ይወጣሉ እንጂ የኛን ምላሽ አስበው አይለወጡም፡፡
ታድያ እኛ ምነዋ!
KALE HIWOT YASEMALIGN WUDU DN.DANNY BO EZIN SEMI'A LEYISMA'E.EMITITSIFACHEW TSHUFOCH BEEGZIABHIER CHERNET TEGBARAWINETACHEW ETEBIKALEHU(Amlak bandim belielam yinageralina) ante gin metsafikin ketilibet.EMEAMLAK KANTE GARA TIHUN.
ReplyDeleteእኛማ፡-እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል የሚለው ስለተጠናወተን።
ReplyDeletebe iwnet rasen betam tazebkut mikinyatum milash tebaki negnina
ReplyDeleteigzi'abher yirdagn
wow nice meassage! kalehiwot yasemaln.
ReplyDeletewell said Dani.Egziabher yibarkih.
ReplyDeleteDear Diakon Daniel, you wrote a very nice article
ReplyDeleteI don't have words to express my feeling.
Simply I want to say:
Egziabher Tsegawn Yabzalih
ቃለ ሕይወት ያሰማልን
ReplyDeleteመቼም እግዚአብሔር በየ ዕለቱ እየነገረን እየመከረን ነው አቤት ለኔ ሳነበው የሰጠኝ ትርጉም ከመናገር በላይ ነውና። ግን አንድ ጽሁፍ እንዳስታውስ አድርጎኛል በሐመር መጽሔት የሚያዚያ ፪ሺህ፪ እትም የአቡነ ጎርጎሪዮስ ትምህርት ሥራህን ሥራ የሚለውን፡
ጽሁፉንም ለመላክ እሞክራለሁ
ታድያ እኔ ምነዋ!
ReplyDeleteታድያ እኔ ምነዋ!
ታድያ እኔ ምነዋ!
አሁንም
ታድያ እኔ ምነዋ!
ፍቃድ ወስዳ እንዳሰበችው ደጋግሜ አነበዋለው ደጋግሜ አስበዋለው ከዚያም ታድያ እኔ ምነዋ! እላለው
ሌላው አንዳንድ ጊዜ በሕይወታችን የዕለት ተዕለት ተግባራት የሚያጋጥሙንን ነገሮች ካስተዋልናቸው በትምህርት ቤት የማናገኛቸውን ዕውቀቶች እንገበይባቸዋለን፡፡ መደበኛውን ሥራችንን እንኳን ቢሆን በማዳመጥ እና በፍቅር ከሠራነው ለዕድሜ ልክ የሚሆኑ ዕውቀቶችን እግረ መንገዳችንን እናገኛለን፡፡
አመሰግናለው ዳኒ ተመችቶኛል
ዲ/ን ዳንኤል
ReplyDeleteምክር ሠናይት ለኩሉ ዘይገብራ
ለተንኮል ነው እነጂ ለቁም ነገርማ መች ብሎን
እኛ ኢትዮጵያውያን ፣ያልታደልን ፍጡሮች ነን(ጠባያችን ማለቴ ነው)
ብዙ ተጻፈልን፣ ብዙ ተነገረን፣ ብዙ ተሰበክን ግን የማይገባን የማንለወጠው ከሠይጣን በላይ ተኮለኞች ሆነን የተገኘነው ለምንድን ነው ብዬ ራሴን ብዙ ጊዜ እጠይቃለሁኝ
ሰይጣን የማይሰራው ተንኮል፣ትቢትናቅናት ግን እኛ ኢትዮጵያውያን ስንሰራው እንታያለን
ሁልጊዜ የተለመደው በሰይጣን ማሳበብ ሆነ
እኛ ሰይጣንን በተኮል እየመራነው እንጂ
ሰይጣን በተንኮል እየመራን እይደለም
ዕድሜ ከጤና ጋር ሰጥቶ አንተን ያቆይልን
ዋ! ዳኒ በእርግጥም ሽማግሌው የፍቅር ሰው ናቸው እና እራሴን አየሁት ጎደሎ መሆኔን አውቄአለሁ ፡፡
ReplyDeleteትልቅ ትምህርት!! እግዚአብሔር ይስጥልኝ!
DANY IT IS REALLY WONDERMENT.............MAY GOD BLESS US........MAY GOD SPARE US OUT FROM FRAGILITY..................GOD BLESS YOU AND YOUR FAMILY.................
ReplyDeleteአንቺ ለምን የራስሽን አታደርጊም? ያንቺን ጥሩነት እና መጥፎነት ለምን ሰዎች ይወስኑልሻል? አንቺ ራስሽ መወሰን አትችይም?»...
ReplyDeleteእኛ አብረን ለመኖር ተስማማን፤ ቃል ገባን እንጂ፤ በደኅንነታችን ጊዜ ብቻ አብረን ለመሥራት ኮንትራት አልተፈራረምንም፡፡
BTW, do u think that give and take principle no importance at all?
ReplyDeleteዲ/ን ዳንኤል ሰላም ላንተና ለዚህ ብሎግ ታዳሚዎች ይሁን።
ReplyDeleteበጣም ደስ የሚል፣ ልብን የሚነካ፣እኔ ማነኝ እንድንል የሚያደርግ ፅሑፍ ነው።
"እኔ ለሚስቴ አንዳች ነገር የማደርገው ውለታ ፍለጋ ብዬ አይደለም፡፡ የኔ ደስታ ሳደርግ እንጂ ሲደረግልኝ የሚገኝ አይደለም፤ በመስጠት እንጂ በመቀበል አይገኝም፤ በመሞት እንጂ በመግደል አይገኝም፤ እኛ አብረን ለመኖር ተስማማን፤ ቃል ገባን እንጂ፤ በደኅንነታችን ጊዜ ብቻ አብረን ለመሥራት ኮንትራት አልተፈራረምንም፡፡ ለኔ በደጉ ጊዜም ሚስቴ፣ ናት በክፉው ጊዜም ሚስቴ ናት፡፡ ሳትታመምም ሚስቴ ናት፤ ታምማም ሚስቴ ናት፡፡ ሌላው ቀርቶ ስትሞትም ሚስቴ ናት፡፡ እርሷ ብታልፍም እኔ ግን ትዝታዋን አግብቼው እቀጥላለሁ፡፡ ከዚያም ደግሞ በሞት እከተላታለሁ፡፡ ስለሚቀጥለው ዓለም አላውቅም፡፡ ከቻልኩ ግን እዚያም ብትሆን ሚስቴ ናት፡፡ እኔ ባልዋ ስሆን ለርሷ የባልነት ግዴታዬን ለማድረግ እንጂ ከርሷ ለመቀበል አይደለም፡፡ እርሷም የርሷን ለማድረግ እንጂ ከኔ ለመቀበል አይደለም፡፡ ልጄ ከሰጡሽ ተቀበይ እንጂ ለመቀበል ግን ስትይ ግን አትስጭ፡፡" ይህ በእውነቱ በየትኛውም ዓይነት የትምህርት ቦታ የማይገኝ ታላቅ የህይወት ትምህርት ነው።
በጣም የሚገርም ነገር ነው በቅርብ ያጋጠመኝን ነው የነገርኝ፡፡ ከሰው መልስ በመጠበቄ ግንኙነቴን ምን ያህል ችግር ውስጥ እንደከተተው አሳይቶኛል! ቸር ውሬ ያሰማልኝ፡፡ በአንድም በሌላም መንገድ ይናገራል፡፡
ReplyDeleteበእውነተ ትልቅ ትምህርት ነው የሰጠኅን እግዚአብሔር ይባርክህ።
ReplyDeleteTemesgen endih Ayinet Mekari yeseten Amlak!
ReplyDeletefor me i have no Answer, i have seen myself empty!
Kaleb ZeAxum
ሰሚ የለም እንጂ ሰሚ ቢኖር ከዚህ በላይ ምን ትምህርት ያስፈልጋል? ችግሩ የኛ ሰው እንደ ጥብርያዶስ 5 ገበያ ህዝብ ይሰበሰባል፣ ይስቃል፣ያጨበጭባል፣ እልል ይላል እንጂ የሚነገረውንና የሚመከረውን ልብ አይለውም። ወንድም ዳንኤል አንተ ግን ዋጋህ ሰማያዊ ነውና ከፊት ይልቅ ትጋ። አምላከ ቅዱሳን ፀጋውን ያብዛልህ። አሜን።
ReplyDeleteWondime Daniel egziabher yitebikilin,eyandandua melikt hulum sew lib lilut yemigebaw new. esti kene jemiro erasachenen enleut biance egna minoldachewn ena bakrabiachen yalutin sewoch melewot enchilalen ena.
ReplyDelete+++
ReplyDeleteበስመ ሥላሴ ትቀጠቅጥ ከይሴ
ከ12 ዓመት በላይ የትዳር ህይዎት አሳልፊአለሁ እራሴን ባዶ ነዉ ያደረገኝ ደነገጥኩ:: አሁን አስተካክላለሁ ብየ ቃል ገብቻለሁ:: በዙሪዪ የሚፈታተነኝ ብዙ ነገር ቢኖርም እግዚአብሔር ኃይል እንዲሰጠኝ እለምናለሁ እናንተም በጸሎታችሁ አስቡኝ::"እኔ ለሚስቴ አንዳች ነገር የማደርገው ውለታ ፍለጋ ብዬ አይደለም፡፡ የኔ ደስታ ሳደርግ እንጂ ሲደረግልኝ የሚገኝ አይደለም፤ በመስጠት እንጂ በመቀበል አይገኝም፤ በመሞት እንጂ በመግደል አይገኝም፤ እኛ አብረን ለመኖር ተስማማን፤ ቃል ገባን እንጂ፤ በደኅንነታችን ጊዜ ብቻ አብረን ለመሥራት ኮንትራት አልተፈራረምንም፡፡ ለኔ በደጉ ጊዜም ሚስቴ፣ ናት በክፉው ጊዜም ሚስቴ ናት፡፡ ሳትታመምም ሚስቴ ናት፤ ታምማም ሚስቴ ናት፡፡ ሌላው ቀርቶ ስትሞትም ሚስቴ ናት፡፡ እርሷ ብታልፍም እኔ ግን ትዝታዋን አግብቼው እቀጥላለሁ፡፡ ከዚያም ደግሞ በሞት እከተላታለሁ፡፡ ስለሚቀጥለው ዓለም አላውቅም፡፡ ከቻልኩ ግን እዚያም ብትሆን ሚስቴ ናት፡፡ እኔ ባልዋ ስሆን ለርሷ የባልነት ግዴታዬን ለማድረግ እንጂ ከርሷ ለመቀበል አይደለም፡፡ እርሷም የርሷን ለማድረግ እንጂ ከኔ ለመቀበል አይደለም፡፡ ልጄ ከሰጡሽ ተቀበይ እንጂ ለመቀበል ግን ስትይ ግን አትስጭ፡፡" በእውነተ ትልቅ ትምህርት ነው የሰጠኅን እግዚአብሔር ይጠብቅህ::
ውድ ዲ/ዳንኤል ቃለ ህይወት ያስማሀ::
ReplyDeleteThank you Brother Dani. I have to just make one comment, a lot of people above when giving comments are blaming the general public hizbachinin. If we change, If I change i could change those around me. Why are we all so pessimistic, this blog or any lesson is not geared to change all and every one. Let us all please remember Lida from the bible, she was changed with only one sermon from st. Paul. Why do we need to see a major change at once in every one, that doesn't happen. Let us change our own self, then positivity will win. So please don't just give up and blame the mass. Sorry for my harsh statments.
ReplyDeleteDani I am amazed not only your writing skill I admire the way of choosing photo it can tell thousands of massage. You are not explain about the photo the photo explain the article.
ReplyDeleteMamo
Thanks Dn Daniel.It is so touching , but i will never forget this message from ur article
ReplyDelete"ልጄ ከሰጡሽ ተቀበይ እንጂ ለመቀበል ግን ስትይ ግን አትስጭ፡፡"
very powerful sentence
kale hiywot yasemalin
ዲ/ን ዳንኤል ቃለ ህይወትን ያሰማልኝ
ReplyDeleteይህ ብሎግህ ለእኔ ትምህርት ቤት እየሆነ ስለመጣ ለጊዜው ከመሳተፍ ይልቅ በጉጉት እየጠበቅሁ ማንበብን መረጥሁ፡፡ አምላካችን አስተዋይ አዕምሮ እና ቅን ልቡና ይስጥህ ይስጠን! በርታ………
Betham Dess yemil Tarik new.
ReplyDeleteየዳንኤልን ትምህርት ለማቃለል አይደለም፡፡ ግን አስተማሪ መቼ ጠፋ፡፡ ተማሪ እንጂ፡፡ ትልቁ ዩኒቨርሲቲ ህይወት ነው እንል የለ፡፡ ባፍም… በመጣፍም… በመኖርም… ብዙ ተማርን (መማር ትርጉሙ ይለያያል!)ግን ስንቶቻችን ነን የተማርነውን ነገር በተግባር ተረጎምነው? በበኩሌ ያደረግሁዋቸውን መጥፎ ነገሮች ሳስብ አብዛኞቹ ጥፋት መሆናቸውን የማውቃቸውን (ባለማወቅ ያይደለ)ነው ያደረገሁት፡፡ የኔ ማንበብ መስማት ምን ጠቀመኝ ? በቃ ! ዳኒ እግዜር ይስጥልኝ ምናምን ከማለት ያለፈ ነገር ማሰብ የጠበቅብናል፡፡ ለመለወጥ እንዘጋጅ!!!!
ReplyDeleteJigsa የተላለፈው መልእክት አልገባህም መሰለኝ፤ አንተ ለምን ሰው ትጠብቃለህ፤ ሰው ቢለወጥ ባይለወጥ አንተ ምን አስጨነቅህ ነው እየተባልክ ያለኸው፡፡ አንተ መለወጥ ከጀመርክ በቃ፡፡ ፀሐይ ብትሞቃት ባትሞቃ ትወጣለች፤ ቀኑን ብትጠቀም ባትጠቀም ቀኑ ቀን ነው፤ ጨለማውም እንደዚህ፤ ዝናቡም እንደዚህ፡፡ በአጭሩ ተፈጥሮ እንኳን እንደዚህ ከሆነ፤ እኛ ምነው ከተፈጥሮ ………….
DeleteDear Daniel I aperciate you more than the message
ReplyDeleteቃለ ሕይወት ያሰማልን!
ReplyDeleteእኛማ ስንፎካከር እንኖራለን፡፡ እያንዳንዱ ሰው የድርሻውን ይወጣ፡፡ ለራሱ ቃል ይግባ፡፡ ሌላውን ለመቀየር ከመሞከር ይልቅ ራሳችንን ለመቀየር እንጣር፡፡ ለውጥ ከራስ ይጀምራልና!
ዲ/ን ዳንኤል ቃለ ህይወትን ያሰማልን!
ReplyDeleteአምላካችን አስተዋይ አዕምሮ እና ቅን ልቡና ይስጥህ ይስጠን! በርታ………
+ + +
ReplyDeleteእራሳችንን ስላልካድን ይሆን? ወይም የማስመሰል እንጂ እውነተኛ ፍቅር አልገባን ይሆናል፣ አምላክ ልባችንን ይስበርልን!
Ohh....I don't have words to say .....except Thanks to our heavenly father that he always teachs us in different way.
ReplyDeleteOh GOD please give us your usual grace and open our heart to be a reall person.
This is Gebremeskel from far East Asia (East Timor Leste, Dili.
Dn. Dani, Let God gives you all his strength.
I think these listed problems r not unique problems Shown By Ethiopians .Its Common Problem Just appreciating ourselves is useful .Let think Positive then We Will Get Interesting Positive.
ReplyDeleteLong Live Ethiopians
wow what a great story .... and what a great advice
ReplyDeleteIt is really nice message. if we change ourselves according to this article, it will not be far to see a good, peaciful, lover and wisfull generation of Ethiopian People. Ebakachihu "azim yaderegebin" neger ke Egziabher gar hunen ashikentiren enitalewuna beteley bemimetaw adis amet adis menfes adis astesaseb yizen rasachin tekeyiren, betesebachin, gaudognochachin na lijochachin lemelewet eninesa ebakachihu ebakachihu. Ke Egziabher gar hulu yichalal. So Let us start from today practicing what our brother advice us. Lehulum Egziabher yirdan. Please write a lot Dn Danel such interesting and educational article. Kale hiwet yasemalin lewendimachin.
ReplyDelete+++
ReplyDeleteDeacon Daniel, Kalehiwot Yasemalin!
Egzeabiher Astway liboba Yadilen!
Kehulum Yamenibetin Melkam sira ketaynet bealu endinisera Amiklak Yirdan!
i don't know what i have to say no words will experss my heart felling.pls everybody don't only undrstand this reading to give comment.let us put in our mind to remember through our life time.God bless us.
ReplyDeleteለካ አውነትነው ሰው በብዙ ነገር ይማራል የሚባለው ለማንኛውም ዳንኤል በጣም አመሰግናለሁአግዜአብሔር ያበርታህ
ReplyDelete!!ኢትዮጵያውያን(ባሁኑ ጊዜ ያለነው) በመጥፎ ጠባያችንና በመጥፎ ግብርችን የታወቅን ብንሆንም፤ ደገኞቹ ኢትዮጵያውያን(የድሮዎቹ ግን) ለያንዳንዱ ለጥሩውም ሆነ ለመጥፎውም ሳይቀር በቅኔ፣ በዘይቤ፣ በፈሊጥ፣ በተረትና ምሳሌ፣ በግጥምም ሳይቀር ይህንንና ይህን የመሰለውን ጽሑፍ አንብቦ ራሱን የማይወቅስ ሰውን ‹‹ አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይነቃም! ›› ይሉናል፨ እውነትም አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይነቃም!! አይነቃም!! አይነቃቃም!!! አይነቃቃም፨!!! በተረፈ ዲ.ን ዳንኤል ክብረት የአባቶች ትልቁ ምርቃት የሆነውን ፍጻሜህን ያሳምርልህ፨
ReplyDeleteAbet men yebalal ? yerasen dekemet eziu anebebekut selene yetetafe hulu eskimeseleg Abet endetetetetekut memeles endechel melete ene yemesetew endimeleseleg beye endayehon copy aderge lemekerebew mesete felegealew temehert sechi selehone hulm kedekemetu endimarebet
ReplyDeleteAmen AMELAKACHEN ERSU YERDAN Amen
Qale hiwoten yasemalen Amen tsegawen yabezalh wendemachen Dani
በሰው አለማወቅ መጠቀም ይበልጥ አላዋቂነት ነው !
ReplyDeleteዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር ይባርክህ
ReplyDeleteእኛማ እኛ ነን
በእውነት እጅግ በጣም አስተማሪ ነው እንዲህ አይነት ሰዎች ብንሆን ኖሮማ መልካምነት የበዛበት ሰው እንሆን እና ሐጢያት ባልኖረ አምላካችንን ባስደሰትን ነበር፡፡
ሳነበረው በጣም ውስጤ ገባ አምላኬን የምለምነው ጊዜያዊ እንዳይሆንብኝ ለዘለቄታው ውስጤ ገብቶ በቀረ ነው፡፡ ሁሉችንንም አምላክ ይርዳን እንዲህ እንድንሆን አሜን
የምሥራች ገብርኤል
Egziabher ybarkh kalehiwot yasemalin
ReplyDeletehi Dn Dani! I read your text and i found it so touching I really like it!It teaches me a lot! thank my brother!
ReplyDeleteKalehiwot yasemalin.Kedus egzabehare edemahen yarzemelen.
ReplyDeletewhat can i say it is hard to experes my feeling but i promis i will do it in my life .thank u for ur advice.egziabeher kante gar yehun.
ReplyDeleteyetesebere leben amelake yadelen...kale heyeweten yasemalen!!!
ReplyDeletegreat !!!i learn a lot.
ReplyDeletetnx
wow
ReplyDeleteit is more than my two degrees ,
ReplyDeleteዳኒ እግዚአብሔር ይባርክህ፤ ትልቅ ትምህርት ነው ያገኙሁት፤ ሀገራችን ከድሆች ተርታ እንኳን ስትሰለፍ ውራ የሆነችው አንድም በዚሁ ምክንያት ይመስለኛል፡፡ ማስተዋል ይስጠን፡፡ መንግስትም ምነው ሆድ የባሰው መንገድ እየሰራ ባህር ላይ ተሻገሩ ከሚለን የሰው አእምሮን ቢለማ፤ የለማው አእምሮ መንገዱን በደንብ አድርጎ ይሰራው ነበር፡፡ ግን ምን ይደረግ…
ReplyDelete