Wednesday, August 25, 2010

የኛን ችግር እኛ እንፍታው

ዲያቆን መሐሪ ገብረማርቆስ

እንደሚመስለኝ እኚህ ኃይለ ገብርኤል የሚባሉ ሰው ችግራችን የገባቸው አይመስለኝም፡፡ የችግራችን አንዱ ምንጭ እኮ ኃላፊነትን ከመቀበል ይልቅ “እንትና ይሥራው፡፡ ወይም እነ እንቶኔ ይከውኑት፡፡ እኔ የልጆች አሳዳጊ፣ የሽማግሎች ጧሪ፣ የእድር ዳኛ፣ የዕቁብ ጸሐፊ ወዘተ. ነኝ፡፡” እያልን መሸሻችን ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያናችን ችግር እንዲህ ሰማይ እንዲሰቀል ያደረጉት እነማን ናቸውና? ነገሥታቱና የእነርሱ ፈቃድ ፈጻሚዎች ካህናተ ደብተራ አይደሉምን፡፡ የቤተ ክርስቲያኗ ታሪክ ላደመጠው ዛሬም ይናገራል፡፡ ያድምጡት፡፡


በመሠረቱ “የቤተ ክርስቲያንን ችግሮች ነገሥታት መፍታት አለባቸው፡፡” የሚል አስተምህሮ ከየት የተገኘ እንደሆነ አይገባኝም- ነገሥታት አስተዳዳሪዎች (በውድ ወይንም በግድ ሊሆን ይችላል) እንጂ ወንጌል ሰባኪነት ዐቢይ ግብራቸው አይደለምና፡፡ አሁን ያለንበት ችግር ሁሉ ትልቁ መነሻው ጳጳሳት የዘወትር የነገሥታት ግብር በላተኞች፣ ነገሥታት የቤተ ክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ሆነው ሕዝቡን እግዚአብሔርንና ሕገ እግዚአብሔርን በማስተማር ማበልጸግ ቀርቶ እንደ ገባር መመልከት ሥር ሰድዶ በመኖሩ አይደለምን? ጳጳሳቱ በዋናነት የነገሥታቱን፣ ነገሥታቱም በዋናነት የጳጳሳቱን (የቤተ ክርስቲያኗን አላልኩም!) ጥቅም በማስጠበቅ ባተሌ ሆነው ወንጌል መስበክ ተዘንግታ፣ ሕዝቡ ችላ ተብሎ በመኖሩ አይደለምን? ቤተ ክርስቲያንን ግን ቤተ ክርስቲያን ያሰኛት መሠረታዊው ነገር በክርስቶስ ደም የከበሩ ልጆች መኖራቸው ነበር፡፡ የትኛው መልእክት ነው ለነገሥታት የተጻፈው? ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለድኾች ወንጌልን በመስበክ እንጂ ነገሥታትን በማባበል አይታወቅም፡፡

ሕገመንግሥቱን ለመተንተን በሞከሩበት ረገድ ደግሞ ይህን ተመልክቻለሁ፡፡ አንደኛ ይህች እኔና በእኔ እድሜ ያሉ ወጣቶች የተረከብናት ሀገር ኢትዮጵያ እንደምትባል ብቻ ሳይሆን በውስጧ ክርስቲያኖችም፣ ክርስቲያን ያልሆኑ ሰዎችም በሰላም የሚኖሩባት፣ ልዩ ልዩ ቋንቋችን የሚናገሩ ነገዶች ከነየራሳቸው ታሪክ፣ ባህልና ሥነ ጽሑፍ ጋር ተፈቃቅደው ያሉባት ሀገር ናት እንጂ ነገሥታቱ ጠፍጥፈው የፈጠሯትና ቤተ ክርስቲያኗ ብቻዋን በትምህርት እየቀረጸች ያሳደገቻቸው ሕዝቦች ያሉባት ሀገር አይደለችም፡፡ በመሆኑም የእነዚህ ሕዝቦች መንግሥት የእነዚህን ሁሉ ሕዝቦች መሠረታዊ ሰብአዊ ፍላጎት ለማሟላት ጥረት ያደርጋል እንጂ በእያንዳንዱ ማኅበረሰብ ሃይማኖታዊ ጉዳይ እየገባ ችግሮችን የመፍታት ታሪካዊም ኅሊናዊም ግዴታም ሆነ መብት የለውም፡፡

የችግሮቻችንን መነሻዎች ከዲያቆን ዳንኤል ክብረት ጽሑፍ እንዳስተዋልሁት በወረስነው የአድርባይነት (ዛሬን ልኑር ስለነገ አያገባኝም ባይነትን እና እነእንቶኔ ይወጡትን ይጠቀልላል፡፡) ባህልና በመንፈሳዊው ቦታ ላይ የምናየው የመንፈሳዊነት ድርቅ ላይ የሚያጠነጥኑ ሆነው ይታዩኛል፡፡ በመሆኑም መፍትሔው ያለው እኛው እጅ እንጂ ነገሥታቱ ዘንድ አይደለም፡፡ ነገሥታቱማ Athnatius from CA እንዳለው እኛን የሚመለከቱን እንደጅሎች ቤተ ክርስቲያንንም የሚመለከቱት ብልሆች የሚመሯት በሥነ ምግባር የታነጹ ዜጎችን (ዜጋ ማለት በነገራችን ላይ የድሮ ትርጉሙ ገባር ማለት ነበር፡፡) የምታፈራ የጅሎች መሰባሰቢያ ተቋም አድርገው ነው፡፡ መብታቸው ነው፡፡ እራሳችንን አስተባብረን ለበጎ ነገሮቻችንና ለመልካም ነገዎቻችን መቆም እስካልቻልን ድረስ በማቴሪያሊስቶች ዘንድ እንከፎች ተደርጎ ከመቆጠር አንድንም፡፡

ዛሬ ለእነዚህ ሰዎች ችግራችንን ፍቱልን ብሎ ማቅረብና መብት መስጠት ነገ በቤተ ክርስቲያናችን እንደ ልጅነታቸው ሳይሆን እንደ ንግሥናቸው እንዳሻቸው እንዲያዙ መብት መስጠት ነው፡፡ ወገን ነገሮችን ከነገው ትውልድ ጋር እናስባቸው እንጂ! ቁጭ ብሎ የሰቀሉት ኮ ቆሞ ለማውረድ ይከብዳል፡፡ “ከታሪካችን የምንማረው ከታሪክ አለመማራችንን ነው” ይላል ፈላስፋ፡፡ አሜሪካ ዛሬ መያዣ መጨበጫ ያሳጧትን ጽንፈኞች የኮሚዩኒስቱን ወገን ያዳክሙልኛል ብላ በፈቃዷ እንዳደራጀቻቸው ልብ በሉ፡፡ ነገሥታት ቤተ ክርስቲያንን ከጠቀሙት ይልቅ የጎዷት እጅግ ይበዛል፡፡ ታሪኳን ተመልከቱ፡፡

የቤተ ክርስቲያን ችግር መነሻው እኛው ዘንድ ነው መፍትሔውም መመንጨት ያለበት ከእኛው ቤተ ክርስቲያኗን ተጠግተን ከምንኖር ሰዎች ነው፡፡ ወደነገሥታቱ እንመለስ ካልን መፍትሔንም ከእነርሱ ከጠበቅን አለቀ ዑደቱን ሰብረን መውጣት አንችልም፡፡ ይልቅ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባቱን ሕገመንግሥታዊ አቋም እንጠቀምበትና ሰላማዊና ጥበብን በተሞላ መንገድ ቤተ ክህነቱን ከሸፈነው የኃጢኣት አቧራ እናጽዳው፡፡ መንግሥት የሚፈልገው አካባቢያዊው ሰላም እንዳይናጋ ብቻ ነው፡፡ ፖሊሲዎቹን እስካልነቀነቅንበት ንቅናቄያችንን አይጠላውም፡፡

 እናስተውል!!!!


12 comments:

 1. ለዲያቆን መሐሪ ገብረማርቆስ
  መቼም ጥሩ ነው ሃሳብህን መግለፅህ ተገቢ ነው። ሀ/ገብርኤል የተባሉት ሰው ያስቀመጡት እኮ እሳቸው በገባቸው መልኩ የተፈጠረውን የቤተ ክርስቲያን ችግር ይፈታል ብለው ያሰቡትን ይመስለኛል። እንጂ አንተ "ችግራችን የገባቸው አይመስለኝም" እንዳልከው አይመስለኝም። አሳቸው ያመላከቱት መንገድ አያስኬደንም አንድ ነገር ችግራችን የገባቸው አይመስለኝም ሌላ ነገር ነው። እኔ እንደተመለከትኩት እሳቸው ዲ/ን ዳንኤል ካመላከታቸው የመፍትሔ ሃሳቦች መካከል አንዱን መርጠው የመንግስትን ጉዳይ ከቤተ ክርስቲያን ችግር አንፃር በሰፊው አብራረተው አቀረቡልን እንጂ አዲስ ነገር አላመጡም። በተጨማሪም በዚህ መድረክ ላይ የተነሳው ጉዳይ የቤተ ክርስቲያን እንጂ የአጠቃላይ የሃገሪቱ አይደለም። ለዚህም ይመስለኛል ፅሑፋቸው Specific የሆነው። እኔና ወንድሞቼ ግን የሳቸውን ሃሳብ እንደ መንደርደሪያ አድርገን የመንግስትን ጣልቃ ገብነት እንዴትና በምን መልኩ ነው መጠቀም ያለብንና ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉት የሚለውን ሃሳብ አየተወያየንበት እንገኛለን። ከፅሑፉ እንደተረዳሁት እኛ ቁጭ ብለን መንግስት ችግሩን ይፍታልን ለማለት የፈለጉ አይመስለኝም ነገር ግን ችግሩን ለመፍታት በምናደርገው እንቅስቃሴ የመንግስትን ድጋፍ ይዘን መሆን አለበት መንግስትም ኃላፊነት አለበትና እንቅስቃሴያችንን ሊቃወም አይገባውም ነው። በመጨረሻም "ሰላማዊና ጥበብን በተሞላ መንገድ ቤተ ክህነቱን ከሸፈነው የኃጢኣት አቧራ እናጽዳው" ብለሃል። እኮ እንዴት????እስቲ ሰፋ አድርገህ አብራራው።

  ReplyDelete
 2. Zewdu Ayalew Abro Shibesh Gubay Latbiye TedlaAugust 25, 2010 at 7:04 PM

  This comment has been removed by a blog administrator.

  ReplyDelete
 3. http://www.dejeselam.org/2010/08/blog-post_4178.html
  http://www.dejeselam.org/
  i hate to live by listening this kind of heinous sin.....................oooooooops God absolve our sins

  ReplyDelete
 4. http://www.dejeselam.org/
  read this site and you have inundated information about our disgrace .........may God Absolve our Sins.............
  http://www.dejeselam.org/2010/08/blog-post_4178.html God forbid us.........spare us out .................

  ReplyDelete
 5. Le Dn. Mehari Gebremarkos Gize setew yihenin tsihuf sladeresun Egziabher yistlen.

  Honom gin yegnan chigir egnaw endinfetaw yakerebut yemeftihe hasab bene amelekaket Dn. Daniel bewananet be part 1 ketekesachew hulet meftihewoch yemejemeriyawin(with red colour) bedingizgiz yemiyasay yimeslal. Sle'andit betechristian eyetsafu "yepapasatun" blew "yebetechristianuan alalkum" maletwo lene gilts aydelem.

  Beketayu lerswo gilts yehonelotin neger leanbabim gilts adirgew bitsfu yeteshale yimeslegnal alezia gin enquanis 'udetun mesber' yikrina...lela udet mefter new yemihonew.

  Egziabher yitebiken.

  ReplyDelete
 6. ወደ ተግባር እንዳንሸጋገር ማን ይከለክለናል. . .? ? ?
  በመጀመሪያ ያንን የጨለማዉን ዘመን አሳልፎ ስለቤተክርስቲያኑ ስለተዋሕዶ ወቅታዊ ችግር የሚቃጠል፣ መፍትሔ ለማምጣት የሚወያይ ወጣት ትዉልድ ያነሳሳ የሰራዊት ጌታ ቅዱስ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።
  ሐሳቦች መንሸራሸራቸዉ መልካም ሆኖ ሳለ ወደተግባር ለመቀየር የሚጠይቁት ዋጋ ግን ጽናትን፣ ትዕግስትንና ሰማዕትነትን መጠየቁ አይቀርም። ለዚህ ደግሞ ከመጀመሪያዉ ንድፈ ሐሳብ ማዘጋጀትና ልቡናችንን ማጨከን ይገባናል። ስለዚህ ከየት እንጀምር? እኔም የተሰማኝን ግልብ ንድፍ/rough sketch/ አስቀመጥሁ።
  1. ከጾምና ጸሎት - ጉዟችን መንፈሳዊ እንዲሆን፣ መንፈስ ቅዱስ እንዲከራከርልን ፣ ከስጋዊ ስሜታዊነት እንድንርቅ ያግዘናል። ስለዚህ ከአዋጅ ጾሞች ዉጭ ለቤተ ክርስቲያን መፍትሔ ባለቤቷ እንዲልክላት የተለዩ ቀናትን ሱባኤዎችን አዉጀን እንያዝ !!! የምንችል በቤተሰብ ፣ በስብስብ የህብረት ጸሎት፣ የምንችል ስግደት ጭምር ...... ከዚህ ቀን እስከዚህ ተብሎ እንደ ነነዌ ሕዝብ ለምን አይነገርም?
  2. ከኢንተርኔት ይልቁንስ በአካል ለመሰባሰብ፣ ከAnonymous(ከብዕር ስም) ይልቅ እዉነተኛ ስማችንን መጠቀም እንጀምር። ለዚህም እዉነተኛ ስማችንን የያዘ ፒቲሽን በመሰብሰብ ጊዜያዊ ኮሚቴ እንምረጥ። የኮሚቴዉ አባላትም እኛ(የተዋህዶ ምዕመናን) የምንሰበሰብበትን፣ የምንወያይበትን፣ ስለቤተ ክርስቲያናችን መፍትሔ የምንሽትበትን መንገድ(ሕጋዊ ፈቃድ፣ ጊዜና ቦታ) ያመቻቻሉ። ሰብስበዉ እንድንወያይ ያደርጋሉ።
  3. ከዚያ በሁዋላ ከቅዱስ ሲኖዶስ አበዉ ጋር የኛን ሐሳብ ይዘዉ ይቀርቡልናል፣ የምዕመንነታችንን መብት በዚህ መንገድ ማስጠበቅ እንችላለን።
  እስኪ በዚህ በሽታ የታመሙና መፍትሔ ያበጁትን ሌሎች አብያተክርስቲያናትን እንመልከት
  1. የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን(እህት ቤ/ክ)
  በግብጽ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ የጉባኤ ካዉንስል /General Congregation Council/ የሚባል የቤተክርስቲያኒቱ አካል አለ። አወቃቀሩ እንደ ኢትዮጵያ ፓርላማ ነዉ። በምእመናን የተመረጡ ምእመናን በፈረቃ/term/ የካዉንስሉ አባል ይሆናሉ። ካዉንስሉን የሚመሩት ፓትርያርኩ ናቸዉ።መንፈሳዊ ባልሆኑ(ከክህነት ዉጭ) ማንኛዉም ጉዳይ ምእመኑን ወክሎ ይቀርባል። ካዉንስሉ አዲስ ፓትርያርክ ሲመረጥ ሱታፌዉ ለቦታዉ የሚመጥኑ አበዉን ይጠቁማል ። ካዉንስሉ እ.ኤ.አ 1954 ዓ.ም አቡነ ዮሴፍ 2ኛን ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር በመምከር ከፕትርክናቸዉ እንዲወርዱ አድርጓል።
  የካዉንስሉ አባላት የሚመረጡት ኦርቶዶክሳዊ መስፈርት ሲያሟሉ ብቻ ነዉ(እድሜ፣ ጋብቻ ፣ ስነ ምግባር ፣ ኢኮኖሚ... )። ጾታ አይለይም።
  በታሪክ ከተለያዩ ፓትርያርኮች ጋር ባለመስማማቱ ጉዳዩ እስከ ግብጽ ፓርላማ ድረስ ቀርቦ ነበር። በአሁኑ ጊዜ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ተስማምተዉ እየሰሩ ነዉ።
  ሌላዉ የምእመናንና የካህናት ሕብረት /Joint Lay-Clerical Committee/ ደግሞ የቤተክርስቲያኒቱን ሁሉንም ቁሳዊ ንብረቶቿን ያስተዳድራል።
  2. የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ(እህት ቤ/ክ) - አንድ ጳጳስ ለመመረጥ የብዙሐኑን ምእመን ድምጽ ማግኘት አለበት፣ ከዚያ በሁዋላ ነዉ በቅ/ሲኖዶስ የሚጸድቅለት።
  3. አርመንያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ(እህት ቤ/ክ)- ወጥ የሆነ ህግ ባይኖራትም አንድ ጳጳስ ለመመረጥ ግን በቤ/ክ ጉባኤ መመረጥ(ብዙሃኑ ምዕመናን ናቸዉ) ፣ በፓትርያርኩ መጽደቅ አለበት።

  እኛ ግን ጳጳስ ለመምረጥ ሳይሆን የምዕመናን ሙቀት አንብቦ ዉሳኔ የሚሰጥ ቅ/ሲኖዶስ፣ ዘመኑን የዋጀ የአስተዳደር ስርአት ያላቸዉ የቤ/ክ መምሪያዎች፣ ወቅቱን ያገናዘበና መንፈሳዊነትን የጠበቀ የክህነት አሰጣጥ ሕግ ... ወዘተ እንዲኖር የኛ ድምጽ/አንደበት የሚሆነን፣ አባቶችን ከምእመናን ጋር በድልድይነት የሚያገለግል የምዕመናን ሕብረት ነዉ የምንፈልገዉ።
  የምዕመናን ሕብረቱ የኛ ገንዘብ ምን ላይ እንደሚዉል ይቆጣጠራል፣ ለኛም ተገቢዉን መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲደርሰን ከሚመለከታቸዉ ጋር ሆኖ ይሰራል።

  መንግስት ሐላፊነቱን መወጣት አለበት - ቢያንስ እኛን መደገፍ አለበት
  መንግስት አለማዊ/ሴኩላር/ ነኝና በራሳችሁ ተወጡት ብሎ ዝም ማለቱ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሐገሪቱ አንድ አካል አይደለችም እንዴ?
  መልሱ መንግስት የሐይማኖት ተቋማትን አካላት የሚያይበት አይን አንድ ስለሆነ ይመስለኛል። ለምሳሌ እኛ ‘ሞሰኑ’ የምንላቸዉ ሰዎችን መንግስት እንዴት ያዉቃቸዋል? ወይ አልተከሰሱ/ቻርጅ የለባቸዉ/። የሕጉን አካሄድ ባላዉቅም መንግስት በሐይማኖት ዘዉ ብሎ መግባትና ‘ሙሰኛ’ ናቸዉ ማለት የሚችል አይመስለኝም። ምክንያቱም ደጋፊና የማይደግፍ ግሩፕ ስለሚፈጠርና ሐይማኖታዊ ይዘት ስለሚኖረዉ መንግስት ከእንደዚህ አይነቱ ችግር መራቅ ነዉ የሚፈልገዉ። እኛ ግን ሕጋዊ የምዕመናን ሕብረት ካለን ሙሰኞችን መክሰስ እንችላለን፣ ከዚያ መንግስት/ሕግ/ ጉዳዩን ማየት ይጀምራል።

  ReplyDelete
 7. Betekrstyanuan Eyemerat Yalew Eko Bemengist Yemiamn Hail New

  ReplyDelete
 8. i like it
  thank you

  ReplyDelete
 9. የሰው ልጅ ሲፈጠር ለፈጣሪ የምስጋና መሰዊያ እንጂ መሰዊያውን ሰባሪ እንዲሆን አይደለም
  እኛ የልዑል እግዚአብሔር ባሪያዎቹ ሳለን በደሙ ያነጻትን ቅድስቲቱን ቤተክርስቲያን
  ለ ምንድ ነው በዘር በጎሳ በፖለቲካ የምን ከፋፍላት ።
  ለፈጣሪ ምስጋናን እንጂ ወደ ቤተክርስቲያ መከፋፈልን ይዘን አይደለም መምጣት ያለብን
  ቅድስት ቤተክርስቲያን ፩ ናት እና ውድ የክርስቶስ ቤተሰቦች ቅዱስ ጳውሎስ በኤሶን መልእቱ እንደጻፈው
  ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።
  መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ።
  እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።
  ኤፌ ፬ ፴ ፴፪
  ይቅር ለእግዚአብሔር ማለት የቱን ክብር ወይስ ዝናን ቀነሰ የምስጋና

  ReplyDelete
 10. negestat betekristianin ketekemuat yilik yegoduat yibezal?........lene gin yetekemuat yibezal yih manm yemiawkew haq silehone tesastehal bay negn 1 neger lib bel yetnantun tiru tiru neger kaladeneqin mechem bihon zare tiru ayhonlnm

  ReplyDelete
 11. tru hasab new gizew newna yh lihon gd hone gn egnam rasachn enya meleyayetn yemnsebk aydeelen

  ReplyDelete
 12. trru haaaasab new egnnnaas slemeleyayet yemmnnnnnnnsebk sewech honenalko

  ReplyDelete