Monday, August 23, 2010

«መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም» ምን ማለት ነው?

ኃይለ ገብርኤል - ከአራት ኪሎ

የተከበራችሁ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆችና የዲ/ን ዳንኤል የጡመራ-መድረክ እድምተኞች ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን። አሜን።

ባለፉት ሳምንታት ወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል በቤተ ክህነቱ ውስጥ ያሉትን፣የብዙዎቻችንን አንገት ያስደፉትንና አብዛኛው ምእመን በሆዱ ይዞ ዘወትር የሚያርበትንና የሚያለቅስበትን የቤታችንን ጉድ ዝምታ መፍትሔ አይደለም በማለት ብቻውን ነጥሮ ወጥቶ ከብዙ በጥቂቱ ለእኛ በሚገባን መልኩ ነግሮናል። ችግሮቹን ከመዘርዘር ባሻገርም መፈትሔ ሊያመጡ ይችላሉ ብሎ ያመነባቸውን ነጥቦችንም በግልፅ አመላክቷል።

እየበሉ እየጠጡ ዝም…… የሚለው የአበው ምሳሌ አንድም በኔ እንዳይተረት አንድም እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነቴ የድርሻዬን መወጣት ስላለብኝ  እነሆ በውስጤ ያለውን እናገር ዘንድ ጀመርኩ።

ዲ/ን ዳንኤል እንዳመለከተው በአሁኑ ወቅት በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ በተፈጠረው ችግር ምክንያት በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ ይመለከተኛል የሚሉ ሁሉ በመነጋገር ላይ ናቸው፡፡ መፍትሔም ይሰነዝራሉ፡፡ ጠቅለል ተደርገው ሲታዩም የሚሰነዘሩት የመፍትሔ አቅጣጫዎች ሁለት መልክ አላቸው ተሐድሶ እና ትንሣኤተሐድሶ ተብዬው ለተፈጠረው ችግር በአንድም በሌላ ተጠያቂ እና ቢሳካለት ለቤተ ክርስቲያን ውድቀት ዘወትር የሚተጋ እንጂ ለሰላሟና አንድነቷ ተጨናቂ አይደለም። ስለዚህም በእኔ እምነት የመፍትሔው አቅጣጫ አንድና ብቸኛ ሲሆን እርሱም ትንሣኤ ነው። የትንሣኤን አቅጣጫ ከግብ ለማድረስ የሚያስችሉና በዲ/ን ዳንኤል የተመለከቱት ሁለት ጉዳዮች ደግሞ አብርሖትና መዋቅራዊ ሽግግር  ናቸው። እነዚህ ሁለት መንገዶች መልካምነታቸው ግልፅ ነው። ይሁን እንጂ ረዘም ያለ ጊዜን የሚጠይቁና የተራብነውን የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት በቅርቡ ላይመልሱልን ይችላሉ ብዬ ሰጋሁ።

ስለዚህም እንደኔ አመለካከት ከአብርሖትና ከመዋቅራዊው ሽግግር ጎን ለጎን መንግስት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንዲወጣ ጠንከር ያለ ጫና ማሳደር ይኖርብናል ብዬ አምናለሁ።

ይህ እምነቴ ግን መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም መባሉን ሳልሰማ ቀርቼ አይደለም። ከመስማትም አልፌ አንብቤዋለሁ ስለሆነም እስቲ ስለዚህ ጉዳይ የሚሰማኝን ልሰንዝር።

ሁላችንም እንደምናውቀው መንግስት በሀይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም። ይህም መሰረቱ በህገ መንግስቱ ምዕራፍ ሁለት አንቀፅ 11 ላይ የሰፈረው ነው። ይኸውም የሚከተለው ነው።

አንቀፅ 11 (የመንግስትና የሃይማኖት መለያየት)

1. መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው።

2. መንግስታዊ ሃይማኖት የለም።

3. መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም። ሃይማኖትም በመንግስት ጣልቃ አይገባም።

መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ማለት ግን ምን ማለት ነው?

 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እኮ የሀገሪቱ ብቸኛ የትምህርት ተቋም በነበረች ጊዜ ለራስዋም ሆነ ለሀገሪቱ የሚሆኑ፣ ምግባራቸው የቀና፣ አንደበተ ርቱዕ፣ በሰውና በእግዚአብሐር ዘንድ የተከበሩ፣ ሀገራችን ዛሬ ለደረሰችበት ስልጣኔ ፈር ቀዳጅ የሆኑ፣ በዓለማዊና መንፈሳዊ ዕውቀታቸው በሁለቱም ጎን እንደተሳለ ሰይፍ የሆኑ ሊቅና ሊቀ ሊቃውንትን በጥራት ስታመርት የኖረች ናት። ይቺ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን ለማፍራት፣ የዕለት ተዕለት መንፈሳዊና ማሕበራዊ ተግባሮቿን ለማከናወን፣ ለቅዳሴው፣ ለማኅሌቱ፣ ለአቋቋሙ፣ ለሰዓታቱ፣ ለትርጓሜው፣ ለቅኔው፣ለድጓው የሚሆን የሰው ኃይል ራስዋ በራስዋ ማንንም ሳትለምንና ሳታስቸግር መሰረቷ በሆነው በልዑል እግዚአብሔር እርዳታ እና ዘወትር ደከመኝና ሰለቸኝ በማይሉና ለዓለም ሙት በሆኑ ልጆቿ ድካምና ጥረት ስታወጣ የኖረችና አሁንም በማውጣት ላይ የምትገኝ ናት።

ይህንን የተቀደሰ ተግባሯንም በሃገራችን ላይ በተለያዩ ዘመናት ስልጣን ጨብጠው ከነበሩ መንግስታት ጋር በመከባበርና በመረዳዳት እየሰራች ነፃነቷን ጠብቃ እነሆ በኢሕአዴግ ዘመነ መንግስት ላይ እንገኛለን። ታድያ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መሰረቷ ፅኑ፣ተግባሯ መልካም፣ አላማዋና ግቧ እንደ ፀሐይ ጮራ ግልፅ፣ ፍሬዋም ለሀገራችን ሐዝቦችና መንግስትም ጭምር ጣፋጭ ሆኖ ሳለ መንግስታችን የህጎች ሁሉ የበላይ በሆነው በህገ መንግስቱ ላይ መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም በማለት በግልፅ ያሰቀመጠበት ምክንያት ምንድነው?

በእኔ አመለካከት መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ማለት፤

1. በተለያዩ የሹመት እርከን ላይ ያሉ የቤተክርስትያን አገልጋዮች ሹመታቸውና የመሿሚያው መስፈርት የሚወጣውና የሚፀድቀው በህገ ቤተ ክርስቲያን እንጂ በመንግስት አይደለም።

2. መንግስት በህገ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እጁን በማስገባት ሰባቱን የአዋጅ አፅዋማት በዙ ብሎ መቀነስ አሊያም

አነሱ ብሎ መጨመር አይችልም።

3. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ ያሬድ አማካኝነት ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጧትን ሶስቱን የዜማ አይነቶች

መንግስት እኔን ደስ አላሰኙኝም በማለት በማናቸውም መንገድ ማሻሻል ወይም መቀየር ፈፅሞ አይችልም አያስበውምም።

4. መንግስት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስርዓተ ቅዳሴ ጣልቃ በመግባት

ሀ. የፀሎተ ቅዳሴው ሰዓት ረዝሟልና አሳጥሩ ወይም አጠሯልና አስረዝሙ፣

ለ. ስትቀድሱ እንዲህና እንዲያ እያላችሁ ቀድሱ፣

ሐ. በሳምንት ይሔን ያህል በወርና በዓመትም ይህንና ያን ያህል ጊዜ ብቻ ቀድሱ፣

መ. ፀሎተ ቅዳሴ በእነዚህ ቀናት እንጂ በዚህና በዛኛው ቀን መፈፀም የለበትም፣

ሠ. በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ተገኘተው ማስቀደስ ያለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎቸ እነ እገሌ እንጂ እነ እገሌ አይችሉም፣

ረ. በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ በአንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መገኘት ያለባቸውን የካህናትና የዲያቆናት እንዲሁም የምዕመኑ ቁጥር ይሄን ያህል ብቻ መሆን አለበት፣ ወዘተ… ብሎ መወሰን አይችልም።

5. መንግስት በቤተ ክርስቲያን ሙዳየ ምፅዋት ውስጥ ምዕመናንና ምዕመናት መጨመር ያለባቸው የገንዘብ መጠን

ቢያንስ ቢያንስ ይሔን ያህል ጣራው ደግሞ ይሄ ነው ብሎ ተመን ማውጣት አይችልም።

6. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በምትመራበት ቅዱስ መፅሐፍ ውስጥ ያሉትን ዓስርቱን ትዕዛዛት 9 ወይም 11 ማድረግ፣እንዲሁም አምስቱን አዕማደ ሚስጥራት 4 ወይም 6 ማድረግ፣ሰባቱን ሚስጥራተ ቤተ ክርስቲያንም 6 ወይም 8 ማድረግ አይችልም።

7. መንግስት በሚስጥረ ቁርባንም ያገባኛል በማለት ቅዱስ ቁርባንን መቀበል የሚችሉት ምዕመናንና ምዕመናት ሊያሟሉ ከሚጠበቅባቸው መንፈሳዊ መስፈርት በተጨማሪ ዲፕሎማና ዲግሪ ሊኖራቸው ይገባል፣ በፖለቲካ አመለካከታቸውም ጀርባቸው እየተጠና መሆን አለበት ብሎ መደንገግ ፈፅሞ አይችልም።

8. ምዕመናንና ምዕመናት ፀሎት ለማድረግ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚሄዱበትን ሰዓት፣ የሚፀልዩትን የፀሎት አይነት፣

የሚያነቡትን የፀሎት መፅሐፍ ዓይነት፣በፀሎት ሰዓት ስለሚኖራቸው እንቅስቃሴ መወሰን አይችልም።

9. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ህልውናዋን ይበልጥ በማጠናከርና ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፋት በምታደርገው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ሐዋርያዊ ተልእኮዋን እንዳትወጣና ለታሪክና ለትውልድ የሚተላለፉ አበይት የሥራ ክንውኖችንም እንዳታስመዘግብ መንግስት በአንድም በሌላ መንገድ እንቅፋት መሆን ወይም መፍጠር የለበትም።

10. ጥንታዊቷና ታሪካዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትናንት የነበረች ዛሬም ያለች ነገም የምትኖር ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ናትና ወቅቱ የሚጠይቀውን መንፈሳዊና ማኀበራዊ አገልግሎት በሚገባ መወጣት ትችል ዘንድ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራች የምታከናውናቸውን ክንዋኔዎች መንግስት ለእርሱ በሚመቸው መልኩ መቃኘት አይችልም።

ወዘተ… ማለት ነው እንጂ፤

1ኛ. ጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ሕዝብ የትምህርትና ሥነ ጥበብ ምንጭ ሆና የኖረች ቤተ ከርስቲያን መሆኗን፣

2ኛ. ከጥንት ጀምሮ ጠቅላላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አንደበቱን የሚፈታው መሠረታዊ የቋንቋና የሥነ ጽሕፈት ዕውቀት የሚያገኘው ከዚች ቤተ ክርስቲያን መሆኑን፣

3ኛ. ዘመናዊው ትምሀርት በሀገሪቱ እስከተዘረጋበት ቅርብ ጊዜ ድረስ ጠቅላላው የትምህርት ቁልፍ በቤተ ክርስቲያኒቱ እጅ ተይዞ የነበረ መሆኑን፣

4ኛ. የቤተ ከርስቲያኒቱ ጥንታውያን የአብነት ትምህርት ቤቶች ለቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለሀገሪቱ ብዙ ሊቃውንትን ሲያበረክቱ የኖሩ መሆኑንና አያበረከቱም መሆናቸውን

በመዘንጋትና እጇን አመድ አፋሽ በማድረግ ህፃናት በጥሩ ሰነ-ምግባር እንዲያድጉ፣ ብሔርና ብሔረሰቦች ተከባብረውና ተዋድደው እንዲኖሩ፣ በተለያዩ የመንግስት የኃላፊነት ቦታ ላይ ያሉ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ለስራቸውና ለህሊናቸው ታማኝ እንዲሆኑ፣ ምእመኑ ቀኑን ሙሉ በፈሪሃ እግዚአብሔር እንዲውል፣ ምእመኑ በመንግስት አካላት በደል ቢደርስበት እንኳን ስሜታዊ ባለመሆንና ትዕግስትን ገንዘቡ በማድረግ ችግሮችን በህጋዊ መንገድ እንዲፈታ ከዚህም ካለፈ ቤተ ክርስቲያን ሄዶ ብሶቱንና መበደሉን ለእግዚአብሔር እንዲያሳውቅ፣ ወዘተ… በማስተማርና በመምከር ለሀገራችን ሕዝቦች እና ለመንግስትም ጭምር የዋለችውን ውለታ በመርሳት

1ኛ. ለብዙዎች ዓለማዊና መንፈሳዊ ጥበብን ዘወትር ሲመግቡ የኖሩትና በመመገብም ላይ የሚገኙት የቤተ ክርስቲያን ጡቶች እና እጆች በአጉራ ዘለል ግለሰቦች ሲነከሱ፣

2ኛ. ህዝበ ክርስቲያኑ ለመንፈሳዊ አገልግሎት እንዲውል ከዕለት ጉርሱ ቀነሶ በሙዳየ ምፅዋት የጨመረው ገንዘብ ሲመዘበር፣

3ኛ. ምዕመኑን በንፁህ ልቦና እና መልካም ኣርዓያነት የሚያገለግሉ አገልጋዮች መብት ሲነካ፣

4ኛ. ለዘመናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትተዳደርበት የነበረው ሕግ እና አስተዳደር ሲጠፋ፣

5ኛ. በቅድስት ቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ የሀገሪቱን መልካም ገጽታ የሚያበላሽ ተግባር ሲፈጸም፣

6ኛ. ጥንታዊቷና ሓዋርያዊቷ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስለ ሕዝቦቿ ሰላምና ፍቅር ዘወትር የሚያለቅሱት አገልጋዮቿ እየተገፉ በምትካቸው በቤተ ክርስቲያን ችግር የሚያተርፉ ሆዳቸው አምላካቸው በሆኑ ግለሰቦች ስትወረር፣

7ኛ. በቅድስት ቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ አይደለም ለቤተ ክርስቲያን ለሌላም የሚተረፍ መንፈሳዊ ጥበብና እውቀት ባለቤት የሆኑ አባቶች እያሉ የመንፈሳዊነትን ትርጉም እንኳን በቅጡ የማያውቁ ግለሰቦች ያልተገባቸውን መነፈሳዊ ስራ እንሰራለን እያሉ ሲያበላሹት፣

8ኛ. በተለያዩ የቤተ ክርስቲያኒቱ የአስተዳደር ቦታዎች ቦታውን የማይመጥን መንፈሳዊነትና ዕውቀት የሌላቸው ገለሰቦች ተቀምጠው ህዝበ ክርስቲያኑ ከቦታው ሊያገኘው የሚገባውን መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳያገኝ ሲደረግ፣ 9ኛ. በቤተ ክህነቱ ውስጥ ተቀምጠው ለሚያጠፉት ጥፋት ተጠያቂ ላለመሆን ራሳቸውን በአንድም በሌላ መንገድ ከመንግስት አካላት ጋር በማቆራኘት መንግስትን ለጥፋታቸው መሸፈኛና ተባባሪ በማድረግ ዘወትር በጥፋት ላይ ጥፋትን የሚጨምሩ፣ መንፈሳዊነትን ለዓለማዊ ጥቅም የሸጡ፣ የቤተ ክርስቲያንን ህግና ስርዓት ሲቆርጡና ሲቀጥሉ የሚውሉ፣ የክህነት ካባ የለበሱ ነገርግን ክህነት በውስጣቸው የሌለ፣ ክርስቲያን ነን የሚሉ የክርስቲያን ምግባር የሌላቸውና ህዝበ ክርስቲያኑን ከመንግስት ጋር ለማጋጨት ሌት ተቀን የሚተጉ ግለሰቦች ሲበራከቱ፣

10ኛ. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ለእምነታቸው ያላቸውን ክብርና ለቤተክርስቲያናቸው ያላቸው መንፈሳዊ ቅንዓት እስከ መስዋዕትነት መሆኑን እያወቁ ምእመኑ ከልጅነቱ ጀምሮ በውስጡ ያደገውን ጨዋነት፣ ህግ አክባሪነት፣ ሰላም ወዳድነት፣ ሆደ ሰፊነትና መንፈሳዊ ትዕግስትን በመፈታተን በውስጣቸው ሸሽገው ለያዙት ርካሽ ዓላማ መጠቀሚያ ለማድረግ ሲሯሯጡ፣መንግስት በቸልታ ማየት አለበት ማለት አይደለም፡፡

የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት ሲደፈርስ አስችሎት በቸልታ ማየት አለበት ማለት አይደለም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቤተ ክርስቲያንን ለማቃጠል የሚለኮሰው እሳት መንግስት እርሱንም እንደማይምረው ጠንቅቆ ያውቀዋል።

ስለዚህ የተከበራችሁ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች በአሁኑ ሰዓት በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የተፈጠረውንና የብዙዎቻችንን አንገት ያስደፋውን ችግር በጊዜያዊ ማሰታገሻ ሳይሆን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከነ ሰንኮፉ ለማስወገድ መንግስት ኃላፊነቱን ሊወጣበት ስለሚችልበት መንገድና ሊወስዳቸው ስለሚገባቸው የማስተካከያ እርምጃዎች በግልፅ እንነጋገር።

“የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር ያከናውንልናል እኛ ባሪያዎቹም ነስተን እንሰራለን” ነህምያ 2፡20

ቸር ያሰማን።

22 comments:

 1. kale hiwot yasemalin. tinitane malet endezih new. Agerin mastedader bilihinetin enji biltabilitinetin ayiteyikimina yemengist akalat meabelu tenesito bizu negerochin kemaferaresu befit direshachewun biwetu melkam new.

  Ye ethiopia Amlak bekachuh bilo le betechrstianachin selamin, menifesawi astedadariwechin yisitilin.

  ReplyDelete
 2. very nice idea.
  i am not clear why church does not critise government in its administarion activity? two farmers ploughing one square does it mean separated? how?
  government is collectin of peoples with public administration from peoples mind, but church's law is from GOD. i acn not agree with the intension even, we are sucessors of our fathers.
  selam lekulikmu

  ReplyDelete
 3. Kelay Wondimachin be zirzir endabraraw huletu akalat(Betekirstianachin ena Mengist) yalachew tisisir nebar(tarikawi) ena huletunim tekami kemehonu bashager andu akal silewedede woyim silalfelege ginugninetu bekelalu yemikuaretibet huneta eskahun yetefetere almeselegnim bifeterim enqua zelaqinet alnberewim lewedefitum bihon endihu tisisiru yemikuaretibet agatami bifeter(minim enqua yemifeteribet huneta endelele kalew nebarawim hone yekedeme tarik antsar metenbey biyaschilenim) bezelakinet tekuarto yikeral yemil emnet yelegnim. Honom bemikahedew tisisirna ginugnunet lay andu akal lelaw lay(betely yerasin tikim-interest- kemaskedem aquaya) awontawi woyim alutawi tetsieno sifeter enayalen lewedefitum endiho yih kistet linor yichilal.

  Besefiw endetegeletsew betekirstian lebetua lijochim hone lehager edgetna biltsigina mekanat yalatin yelake minana(astewatsio) gimit wist sinasgeba ahunim bihon betekirstianachin aydelem yerasuan chigir yehagerin chigirim bihon meftat yemiaschil kulf mina mechawet yematichilibet huneta yale aymeslegnim. Silehonem kelay wondimachin bewananet bakerebew yemeftihe hasab maletim ‘mengist min madrerg alebet aliam mengist bemin melku halafinetun yiweta’ yemilew lay ende ene emnet ahunim bihon betekirstian chigirochuan meftat yemiaschilat hulum giba’atna akim aalat biye aminalehu.

  Tiliku chiger yemimeslegn, Diako Daniel kakerebachew yemeftihe hasaboch Menager bilo endabiraraw, egna tifat bebetachin sifetsem eyayen yegnan dirsha kemewetat yilik Egziabher yewededewin yadirg eyalin hulunim neger lefetari bemetew chigiroch endibabasu mikiniyat yehonin yimeslegnal. Silezih beteley yihe ‘menager’ yetebalew(beteleyaye ababal woyim ye tigbera hidet ligelets yichilal) kegna dirsha wist tilikuna leminbseleselilachew chigiroch mefetat abiy mina endeminorew asibalehu. Abatochin endih bidereg, ezih lay tesasitewal mallet betam yikebdal difretim kemehonu bashager gibizim yasmesilal neger gin sihitet silemehonu be ergit yeminaminina ye betekirstianachin guday yemiakatilen kehone beteleyaye melku yihen madreg enchilalen. Le abinet metkes biasfelig ye niseha abatochachin ga sile bizu neger bigilts meweyayet enchilalen lemenagerim difretu yinorenal…

  Batekalay lemalet yefelegutin bachiru lemaskemet chigiru egna ga eskehone direst meftihe kelela akal kemeshat yilik berasachin meftat yalebin chigiroch lay binatekorim. Fetsimen linfetaw yemanchilew chigir enquan binor begize hidet alima ye andu chiger mefetat lelawim endifeta silemireda yechigiru balebetina bemefetatu be wananet tetekamiw akal (betekirstianachin) lay sile zirzir meftihewina ategebaberu binatokir elalehu. Kezeih befitim endetetekomew ezih ye Diakon Daniel ye tumera gets lay beteketatay yemikerbut tekami tsihufochin(yewondimochin asteyayet chemiro) beteleyaye melku hulum ye betekirstian akalat anbibo bemeredat yebekulun astewatsio madreg endichil betegibar min yidereg yemilewim lay techebach neger mamtat binchil. Le’asebnilet yebetekirstian mekanat ginzabe maschebetu endemejemeria sira hono!!

  Emebetachin Kidist Dingil Mariam Mengedachin yetekana endihon milja, redietina bereketua ayleyen, amen!!

  ReplyDelete
 4. ሰላም ለዚህ ቤትና ለዲ.ዳንኤል
  ከደብረ ቁስቋም
  ወንድማች ሀይለ ገብሬል ያቀረበው ሃሳብ በጣም ጥሩ ሀሳብ ነው::ነገር ግን እውነቱን ለመናገር ይህንን የመንግስት ህግ እንዲህ ሰፋ ባለ ሁኜታ ህብረተሰቡ በደንብ የሚያውቀው አይመስለኝም ስለዚህ ህዝቡን ማስረዳት ያስፈልጋል ይህንንም ፕሪንት አድርጎ መበተን ነው ብዬ አስባለሁ::ለምሳሌ እኔ እያደረኩ ያለሁት ማይክሮ ሶፍት ዎርድ ላይ ኮፒ እያደረኩ የማርችና አፕሪልን አንድላይ በማድረግ 74ቱን ገጽ ባይንድ አድርጜ እንደ አንድ መጽሀፍ ወቶት በማደል ላይ እገኝኣለሁ ደግሞ በሚቀጥለው የሜይ እና ጁንን አንድ ላይ አድርጜ እየሰሩሁት ነው::እንደዚህ ላደርግ የቻልኩበት ምክንያት ጽሁፎቹ አንዼ ተነበው መቅረት ስለሌለባቸው ነው ሌላው አንድ ሰው አንዱን አንብቦ ሲጬርስ ሁለተኝኣው ይሰጤውና የመጀመሪያው ለሌላ ሰው ይሠጥኣል ማለት ነው.እናም ሁላችንም የምንችል እንዲህ ብናደርግ መልካም ነው እላለሁ.በአቡዳቤናአካባቢው ለምትገኝኡ ሁሉ በዚህ ኢሜል መገናኜት እንችላለን zarenewe@yahoo.com
  {ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና}ሮሜ 10;10
  እግዚአብሔር አምላክ የቤተ ክርስትያንን ትንሳኤዋን ያሳየን.

  ReplyDelete
 5. +++

  በስመ ሥላሴ ትቀጠቅጥ ከይሴ
  መንግስት ቤ/ያን ሲጎዳ ምዕመናን ሲበደሉ እያየ ዝም የሚል አይመስለኝም:: ግን መረጃ የሚያቀርብለት ና አቤት የሚልለት ይፈልጋል:: ምናልባት አንዳዶች የመንግስት አካላት የሆኑ ነገሩ ያልገባቸዉ ወይም የእለት ጥቅም ተካፋይ የሆኑ በጎሳ: በአጥንት በጉልጭምት አዞአችሁ የሚሉ ሊኖሩ ቢችሉ እንኳን እዉነትን ስላልያዙ አያዋጣቸዉም ወይም መንግስትን በሥራቸዉ ያስወቅሱታል:: ስለዚ ምእመናን በቅርበት ያላችሁ ስለ እዉነት ብላችሁ ቅዱሳን አባቶቻችን በአጥንታቸዉና በደማቸዉ አጽንተዉ ያቆዩንን ቤ/ያን እየተጎዳች ስለሆነ ጠበቃ እንቁምላት: ምስክር እንሁናት:: ህዝብ ማለት መንግስት ማለት ነዉ:መንግስትም የህዝብ ነዉ:: ስለዝህ መንግስት መረጃ ከቀረበለት ፍርድ ይሰጥበታል:: የመንግስት አካላት እኮ የቤ/ያን አባቶች መንፈሳዉያን ናቸዉ ብሎ እንደ ድሮዎቹ ደጋግ አባቶች ሰለሚያስባቸዉ ያጠፋሉ ብሎ አይገምትም ይሆናል ወይም መረጃ ከባለጉዳዩ እየፈለገ ይሆናል::

  አምላከ ቅዱሳን የቤ/ያንን ጥፋት አያሳየን::
  ከዝዋይ

  ReplyDelete
 6. በስመ ሥላሴ አሜን።

  ሰላመ እግዚአብሔር ይብዛላችሁ ወገኖቼ እንደምን አላችሁ?

  እስቲ ስለእውነት እንነጋገር ፦ ስምኦን ጫማ ሰፊው ምን ነበር ያደረገው? ... ታሪኩን አቀናብሬ ባልጽፈው አትቀየሙኝ ... ታሪክ አተራረክ ባልችል ነው ... ቢሆንም ወሳኙ ቁምነገሩ ነው ... በወቅቱ የነበሩ አህዛብ ክርስቲያኖቹን እምነታችሁ ተራራን ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል ይላል ... ስለዚህ እውነተኛነቱን አሳዩን ባሏቸው ጊዜ ... ለጳጳሱ ያልተቻለው ተአምር የተደረገው ፤ ጽድቁን ከሰው ታይታ ሰውሮ ፤ በሰው ዘንድ በተናቀ ቦታ ላይ በነበረው በስምኦን ነበር ... ሃይማኖታችን እንዲያ ነው ... አዎ ማንም እየተነሳ መፍትሄ አቅራቢ የሚሆንባት ሃይማኖት የለችንም ... አዎ ክርስትናን የሚኖሩ ሰዎች ... እንዲህ እናደርጋለን ... እንዲያ እናስደርጋለን ... አይሉም ... በማስተዋል ፤ ልታይ ልታይ ባለማለት ፤ በአርምሞ ፤ እራሳቸውን ለሰው ሳይሆን ለፈጣሪ እያሳዩ ይኖሩታል እንጅ ... እንዲያም ስለሆነ በንጽህና ስለመኖራቸው ምክንያት እግዜር በነርሱ አስደናቂ ተአምራቶችን ያደርጋል። ...

  አሁን እየተደረገ ያለው ግን ሌላ ነው ፤ የተገላቢጦሽ ... ሁሉም ያወራል ... ሁሉም ይተቻል ... ሁሉም ሆ ይላል ... ሁሉም ... እረ በእግዜር እንዲህ አይደረግም!!! ... ክርስትና ስላልገባን ፤ ለምን ሌሎች ክርስትና እንዲህ ነው እንዴ? ... እንዲሉ እናደርጋለን? ... የመጽሐፍም ይሁን የቅዱሳን አባቶች እና እናቶች ሕይወት የሚያስተምረው እንዲህ ነው እንዴ? ... አንድ ሰው ካገኘው የነፍስም ይሁን የስጋ ዝቅጠት የሚወጣው በእግዜር ቸርነት አይደለም እንዴ? ... በጎ የቸርነት ስራውስ የሚጠየቀው በንጽህናና በቅድስና እየኖሩ ፤ ለመኖር ጥረት እያደረጉ አይደለም እንዴ? ... በሆይሆይታ ፤ በመተቻቸት ፤ በሸንጎ እና በደቦ ክርስቲያን ችግሩን ይፈታል የተባለው ከመቸ ወዲህ ነው? ... መምህራኖቻችንስ ብትሆኑ ፦ ለምን የሚያስደስተንን ፣ የሚመቸንን ትታችሁ እውነታውን ብቻ አትነግሩንም? ... በዘር በቋንቋ ስለተናቆራችሁ ፣ አባቶቻችሁን ስላዋረዳችሁ ፣ ሁሉን እናውቃለን ብላችሁ ስለታበያችሁ ፣ ... ሊሆን ይችላል እንዲህ የሆነው ... ከዚህ ሳይርቁ መፍትሄ መፍትሄ ቢሉት ዋጋ የለውም ፣ ... ለምን አትሉንም? ...

  ማንም ማንንም አያታልልም! ... እርግጥ ወደ እግዜር ማልቀስ ቸግሮናል ... ስለዚህም ከቻላችሁ አልቅሱልን ... ካልቻላችሁ ግን በራሳችሁ ጥበብ እየሮጣችሁ የእግዜርን ምህረት አታዘግዩብን ... ቢገባን እኮ ይህ ጆሮን ጭው የሚያደርግ መዓት ነበር ... እንዲህ ሲሆን ታድያ ሰው በያለበት ወደ አምላኩ ያለቅሳል እንጅ ... የበቃ ፣ የነቃ ፣ ነገር የተገለጠለት ይመስል መንግስት ይግባ ፣ ማኅበር ነገር እናቋቁም ፣ እንቶኔን እናውርደው ፣ ... ቅብርጥሶ ይላል እንዴ? ... ደግሞስ ለስጋ ፈቃድ አደላን ፣ ከእግዜር መንገድ ራቅን ፣ ጽድቅ በመካከላችን ጠፋ ማለት እኮ የክርስትና አስተምህሮ ተለወጠ ማለት አይደለም ...

  ለማንኛውም ... እኔም ፦ እናንተን የሚቃወም ሌላ ማኀበር ይቋቋም ብዬ ልጮህ ፣ የመንግስትን ጣልቃገብነት ልናፍቅ ምናምን አይደለም ... ከእንደዚህ አይነቱ ሀሳብ ትብብር እንደሌለኝ ለመግለጽ ነው ... ታዲያ ይህን ስታነቡ ነገሩ አልገባውም ፤ በተሳሳተ መንገድ ተረዳን ትሉ ይሆናል ... የሚገርማችሁ እኔና መሰሎቼም እንዲሁ ነው የምንላችሁ ... በመጨረሻ ስሜታዊ ሆኜ ባጠፋሁ ይቅር እንድትሉኝ በእግዜር ስም እለምናችኋለሁ።

  የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድለን።

  ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

  ReplyDelete
  Replies
  1. Eski andi tyake lteyikh. mechem haimanotachin hagerachinm eyetefach new. ethiopia wust kehonk yihen lante alasredahm. eski ngeregn lechigru mefthe ante mndn new tlaleh???? yechegeren mefthe amchi enji yemitech ayidelem. mefthe yemtlewun ngeregn. mechem tarik stiteks semchalehu. lehagerna lehaimanotachew silu be adebabayi chok blew eyetenageru, angetachewun deretachewun be adebabayi letorna le seyif eyesetu hzbn siaberetatu sikeseksu haimanotachewun sitebku yeneberu sewochn atawukm??? eski ngeregn man hzbun yaberta man hzbun yimra man lebetekrstianachn alegnita yihunat???? lemans abet yibal??? le egziabher endatlegn. esu egna kalseran zmbleh tekemteh mefthe amta mefthe amta btl yemihon yimeslhal?

   Delete
 7. ምን አይነት ለውጥ ከመንግስት እንዲመጣ እንደምንጠብቅ አይገባኝም አብዛኛው ችግር ከመንግስትና ከተቃዋሚዎች እንደመጣ ሆዳችን እያወቀው። ተመልሰን ለቤተ/ክ ግድ የሌላቸው ሰዎች ጋር ሄደን መፍትሄ ይገኛል ማለት ዘበት ነው።
  መንግስትና ተቃዋሚዎች እኮ ማቴሪያሊስት ናቸው። እኛ ለነሱ የጅሎች ስብስብ ነን፡፡
  እነሱ የሚያስቡት ለኔ ታማኞች ናቸው ወይ? ወይ ጠለቅ ብለው ካሰቡ ethical ሰዎችን የሚያፈልቅ ተቋም ሊሉ ይችላሉ።
  I THINK WHAT WE SHOULD DO IS ASSESS THE SITUATION AND PROBLEMS, CONTEMPLATE HOW WE ARE GOING TO SOLVE THE PROBLEM. THEN LETS GET TOGETHER AND HAVE A BIGGER VOICE SO EVERY BODY COULD LISTEN.
  MAY GOD BE WITH US.

  ReplyDelete
 8. ቀድሞውኑ ለዚህ ሁሉ ችግር ተጠያቂው እኮ መንግስት ተብዬው አይደለም እንዴ ምክንያቱም የመጨረሻው ዘመን ስለሆነ ሁሉም የመንግስት ባለስልጣናት ማለት ይቻላል የእውነተኛዋ ክርስትና (ተዋህዶ) ጠላቶችና የአውሬው ተባባሪዎች መሆናቸው ይጠፋናል ብዬ አልገምትም። በፍጹም ስለቤተክርስቲያን ህልውና ሊጨነቁና መልካም ሊያስቡ አይችሉም። (ከመንፈሳዊ)ከአቅማቸው በላይ ነው። አይተው እንዳላዩ ሰምተው እንዳልሰሙ እንዲያም ሲል በሰበብ ባስባቡ ቤተክርስቲያንን ሲገፉ አይደለም የኖሩት ይህ ነገር (ተዋህዶን መግፋትና ለማጥፋት መሞከር) እኮ የተጀመረው በደርግ ነው። በኢህአዴግ ደግሞ በጣም ተጠናክሮ እየተገፋበት ነው ። አልሆነላቸውም እንጂ ቤተክርስቲያኗን በአንድ ጀንበር ቢያጠፏት ደስታቸው ነው። እኔ በፍጹም ባለው መንግስት ላይ ተስፋ የለኝም። መፍትሄ የሚመስለኝ እያንዳንዳችን ምእመናን መንፈሳዊ ህይወታችንን አበርትተን ወደ እግዚአብሔር መጮህ፤ አርቲፊሻል ኢትዮጵያዊ ሳንሆን እውነተኛ፤መልኩን ያልለወጠ ኢትዮጵያዊ መሆን፤ ታሪካችንን እና ሃይማኖታችንን በሚገባ ማወቅና መተግበር(መንከባከብ)... የመሳስሉትን ማድረግ ጥቂቶቹ የመፍትሄ ሃሳቦች ይመስሉኛል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቀድሞውኑ ለዚህ ሁሉ ችግር ተጠያቂው እኮ መንግስት ተብዬው አይደለም እንዴ ምክንያቱም የመጨረሻው ዘመን ስለሆነ ሁሉም የመንግስት ባለስልጣናት ማለት ይቻላል የእውነተኛዋ ክርስትና (ተዋህዶ) ጠላቶችና የአውሬው ተባባሪዎች መሆናቸው ይጠፋናል ብዬ አልገምትም። በፍጹም ስለቤተክርስቲያን ህልውና ሊጨነቁና መልካም ሊያስቡ አይችሉም። (ከመንፈሳዊ)ከአቅማቸው በላይ ነው። አይተው እንዳላዩ ሰምተው እንዳልሰሙ እንዲያም ሲል በሰበብ ባስባቡ ቤተክርስቲያንን ሲገፉ አይደለም የኖሩት ይህ ነገር (ተዋህዶን መግፋትና ለማጥፋት መሞከር) እኮ የተጀመረው በደርግ ነው። በኢህአዴግ ደግሞ በጣም ተጠናክሮ እየተገፋበት ነው ። አልሆነላቸውም እንጂ ቤተክርስቲያኗን በአንድ ጀንበር ቢያጠፏት ደስታቸው ነው። እኔ በፍጹም ባለው መንግስት ላይ ተስፋ የለኝም። መፍትሄ የሚመስለኝ እያንዳንዳችን ምእመናን መንፈሳዊ ህይወታችንን አበርትተን ወደ እግዚአብሔር መጮህ፤ አርቲፊሻል ኢትዮጵያዊ ሳንሆን እውነተኛ፤መልኩን ያልለወጠ ኢትዮጵያዊ መሆን፤ ታሪካችንን እና ሃይማኖታችንን በሚገባ ማወቅና መተግበር(መንከባከብ)... የመሳስሉትን ማድረግ ጥቂቶቹ የመፍትሄ ሃሳቦች ይመስሉኛል።

   Delete
 9. I prefer to prey to God to assist us.Besides we have to discuss with the leader openly.show the problems and put our solutions.we have to let them know that there is a problem in our mother church.discussions with out including the concerned bodies will be valueless.
  may God help us.

  ReplyDelete
 10. ዲያቆን መሐሪ ገብረማርቆስ

  እንደሚመስለኝ እኚህ ኃይለ ገብርኤል የሚባሉ ሰው ችግራችን የገባቸው አይመስለኝም፡፡ የችግራችን አንዱ ምንጭ እኮ ኃላፊነትን ከመቀበል ይልቅ “እንትና ይሥራው፡፡ ወይም እነ እንቶኔ ይከውኑት፡፡ እኔ የልጆች አሳዳጊ፣ የሽማግሎች ጧሪ፣ የእድር ዳኛ፣ የዕቁብ ጸሐፊ ወዘተ. ነኝ፡፡” እያልን መሸሻችን ነው፡፡ የቤተክርስቲያናችን ችግር እንዲህ ሰማይ እንዲሰቀል ያደረጉት እነማን ናቸውና? ነገሥታቱና የእነርሱ ፈቃድ ፈጻሚዎች ካህናተ ደብተራ አይደሉምን፡፡ የቤተክርስቲያኗ ታሪክ ላደመጠው ዛሬም ይናገራል፡፡ ያድምጡት፡፡

  በመሠረቱ “የቤተክርስቲያንን ችግሮች ነገሥታት መፍታት አለባቸው፡፡” የሚል አስተምህሮ ከየት የተገኘ እንደሆነ አይገባኝም- ነገሥታት አስተዳዳሪዎች (በውድ ወይንም በግድ ሊሆን ይችላል) እንጂ ወንጌል ሰባኪነት ዐቢይ ግብራቸው አይደለምና፡፡ አሁን ያለንበት ችግር ሁሉ ትልቁ መነሻው ጳጳሳት የዘወትር የነገሥታት ግብር በላተኞች፣ ነገሥታት የቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ሆነው ሕዝቡን እግዚአብሔርንና ሕገ እግዚአብሔርን በማስተማር ማበልጸግ ቀርቶ እንደ ገባር መመልከት ሥር ሰድዶ በመኖሩ አይደለምን? ጳጳሳቱ በዋናነት የነገሥታቱን፣ ነገሥታቱም በዋናነት የጳጳሳቱን (የቤተክርስቲያኗን አላልኩም!) ጥቅም በማስጠበቅ ባተሌ ሆነው ወንጌል መስበክ ተዘንግታ፣ ሕዝቡ ችላ ተብሎ በመኖሩ አይደለምን? ቤተክርስቲያንን ግን ቤተክርስቲያን ያሰኛት መሠረታዊው ነገር በክርስቶስ ደም የከበሩ ምእመናን መኖራቸው ነበር፡፡ የትኛው መልእክት ነው ለነገሥታት የተጻፈው? ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለድኾች ወንጌልን በመስበክ እንጂ ነገሥታትን በማባበል አይታወቅም፡፡

  ሕገመንግሥቱን ለመተቸት ወይም ለመተንተን በሞከሩበት ረገድ ደግሞ ይህን ተመልቻለሁ፡፡ አንደኛ ይህች እኔና በእኔ እድሜ ያሉ ወጣቶች የተረከብናት ሀገር ኢትዮጵያ እንደምትባል ብቻ ሳይሆን በውስጧ ክርስቲያኖችም፣ ክርስቲያን ያልሆኑ ሰዎችም በሰላም የሚኖሩባት፣ ልዩ ልዩ ቋንቋችን የሚናገሩ ነገዶች ከነየራሳቸው ታሪክ፣ ባህልና ሥነ ጽሑፍ ጋር ተፈቃቅደው ያሉባት ሀገር ናት እንጂ ነገሥታቱ ጠፍጥፈው የፈጠሯትና ቤተክርስቲያኗ ብቻዋን በትምህርት እየቀረጸች ያሳደገቻቸው ሕዝቦች ያሉባት ሀገር አይደለችም፡፡ በመሆኑም የእነዚህ ሕዝቦች መንግሥት የእነዚህን ሁሉ ሕዝቦች መሠረታዊ ሰብአዊ ፍላጎት ለማሟላት ጥረት ያደርጋል እንጂ በእያንዳንዱ ማኅበረሰብ ሃይማኖታዊ ጉዳይ እየገባ ችግሮችን የመፍታት ታሪካዊም ኅሊናዊም ግዴታም ሆነ መብት የለውም፡፡

  የችግሮቻችንን መነሻዎች ከዲያቆን ዳንኤል ክብረት ጽሑፍ እንዳስተዋልሁት በወረስነው የአድርባይነት (ዛሬን ልኑር ስለነገ አያገባኝም ባይነትን እና እነእንቶኔ ይወጡትን ይጠቀልላል፡፡) ባህልና በመንፈሳዊው ቦታ ላይ የምናየው የመንፈሳዊነት ድርቅ ላይ የሚያጠነጥኑ ሆነው ይታዩኛል፡፡ በመሆኑም መፍትሔው ያለው እኛው እጅ እንጂ ነገሥታቱ ዘንድ አይደለም፡፡ ነገሥታቱማ Athnatius from CA እንዳለው እኛን የሚመለከቱን እንደጅሎች ቤተክርስቲያንንም የሚመለከቱት ብልሆች የሚመሯት በሥነ ምግባር የታነጹ ዜጎችን (ዜጋ ማለት በነገራችን ላይ የድሮ ትርጉሙ ገባር ማለት ነበር፡፡) የምታፈራ የጅሎች መሰባሰቢያ ተቋም አድርገው ነው፡፡ መብታቸው ነው፡፡ እራሳችንን አስተባብረን ለበጎ ነገሮቻችንና ለመልካም ነገዎቻችን መቆም እስካልቻልን ድረስ በማቴሪያሊስቶች ዘንድ እንከፎች ተደርጎ ከመቆጠር አንድንም፡፡

  ዛሬ ለእነዚህ ሰዎች ችግራችንን ፍቱልን ብሎ ማቅረብና መብት መስጠት ነገ በቤተክርስቲያናችን እንደልጅነታቸው ሳይሆን እንደንግሥናቸው ፍትወት እንዳሻቸው እንዲያዙ መብት መስጠት ነው፡፡ ወገን ነገሮችን ከነገው ትውልድ ጋር እናስባቸው እንጂ! ቁጭ ብሎ የሰቀሉት ኮ ቆሞ ለማውረድ ይከብዳል፡፡ “ከታሪካችን የምንማረው ከታሪክ አለመማራችንን ነው” ይላል ፈላስፋ፡፡ አሜሪካ ዛሬ መያዣ መጨበጫ ያሳጧትን ጽንፈኞች የኮሚዩኒስቱን ወገን ያዳክሙልኛል ብላ በፈቃዷ እንዳደራጀቻቸው ልብ በሉ፡፡ ነገሥታት ቤተክርስቲያንን ከጠቀሙት ይልቅ የጎዷት እጅግ ይበዛል፡፡ ታሪኳን ተመልከቱ፡፡

  የቤተክርስቲያን ችግር መነሻው እኛው ዘንድ ነው መፍትሔውም መመንጨት ያለበት ከእኛው ቤተክርስቲያኗን ተጠግተን ከምንኖር ሰዎች ነው፡፡ ወደነገሥታቱ እንመለስ ካልን መፍትሔንም ከእነርሱ ከጠበቅን አለቀ ዑደቱን ሰብረን መውጣት አንችልም፡፡ ይልቅ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባቱን ሕገመንግሥታዊ አቋም እንጠቀምበትና ሰላማዊና ጥበብን በተሞላ መንገድ ቤተክርስቲያናችንን ከሸፈናት የኃጢኣት አቧራ እናጽዳት፡፡ መንግሥት የሚፈልገው አካባቢያዊው ሰላም እንዳይናጋ ብቻ ነው፡፡ ፖሊሲዎቹን እስካልነቀነቅንበት ንቅናቄያችንን አይጠላውም፡፡ “ፖሊሲዎቹ ጉዳዮቻችን አይደሉም፡፡” ማለቴ ሳይሆን ለምጣዱ ሲባል አይጧን ማሳለፌ ነው፡፡

  እናስተውል!!!!

  ReplyDelete
 11. መፍትሄው እግዚኦ ማህረነ ክርስቶስ ስለበደላችን ይቅር በለን ነው፡፡
  አ.ጫ

  ReplyDelete
 12. ያልታከመ መንግስት ቤተክርስቲያንን የማከም ሃላፊነቱን እንዲወጣ መጥራት፤ያልተፈወሰ መንግስት ቤተክርስቲያንን እንዲፈውስ መጮህ፤ያልተባረከ መንግስት ቤተክርስቲያንን እንዲባርክ መማጸን፤ እኛም ሳይታወቀን እንደ ዛሬው መንግስት በጠመንጃና ምድራዊ ሃይል የማመናችን ምልክት ሳይሆን ይቀራል?እንደ ቅዱስ ያሬድ ከሰማይ ለቤተክርስቲያናችን ችግር መፍትሔ የሚያመጣ ሰው ይገኛ ይሆናል ብለን ማመን አቆምን ማለት ነው?የምድሩን እንጂ የሰማዩን ማየት አቆምን ?እንደ ኢያሱ ህዝቡን ይዞ በታቦተ ጽዮን ፊት መቆም እንጂ በመንግስተ ፊት መቆም የሚል ትምህርት ደግሞ ከየት የመጣ ነው?ወይንም ደግሞ የመቆም የመቆም እንደ ሰሜን አሜሪካ ካህናትና ጳጳሳት ጠብደል ያለው የዋይት ሃዉሱ መንግስት ፊት እንቁም።
  አንድም ቀን ስመ እግዚአብሔርን ጠርቶ ለማያውቅ አረማዊ መንግስት የቤተክርስቲያናችንን ጉዳይ ይዞ መሄድ እንዴት ክርሰትና ሊሆን ይችላል?እዚህ ሰሜን አሜሪካ በየመናፍቅና እስላም ዳኛ ፊት የቤተክርስቲያናችንን ጉዳይ እያዝረከረኩ የሚያቃጥሉን ካህናት ተብየወች እንዳይበቁን?
  ጠመንጃ የያዘ ሁሉ የቤተክርስቲያንን ችግር የሚያቀል ከሆነ እኛም ጠመንጃ እንድንይዝ ለምን አታስተምሩንም ታዲያ? ወይስ ይሄ መንግስት በጠመንጃ ሃይል የመጣሳይሆን እንደቀደሙት አጼወች በእግዚአብሔር የተቀባ ነው ልትሉን ፈለጋችሁ?
  አላማችን የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን ወደቀደመ ክብርዋ መመለስ ከሆነ እንደጌታዋ ያለምንም መቃብር ፈንቃይና ድንጋይ አንከባላይ እንደምትነሳ ማመንና ለዚህ መስራትያለብን ይመስለኛል።እውነተኛዋ ቤተክርስቲያን ማንንም ምድራዊ መንግስት ልትደገፍም ሆነ ልትመረኮስ አትችልም።ከተደገፈችና ከተመረኮሰች ግን ምኑን የሃያሉ የእግዚአብሔር ቤት ሆነችው?
  አሁን እንደው ምድራዊና ስጋዊ የሆነው መንግስት ሰማያዊትና መንፈሳዊት የሆነችውን ቤተክርስቲያን እገዛ ሳይጠይቅ የተገላቢጦሸ ቤተክርስቲያን የመንግስትን እገዛ መጠየቅ አያሳፍርም ትላላችሁ?
  ይሄ መፍትሔ የሚያመጣ ሳይሆን ጭራሹንም የክርስትናውን አገልግሎት የሚያስነቅፍ ይመስለኛል።
  እስኪ መማህራን የሆናችሁ ወንድሞቼ በቤተክርስቲያን ታሪክ በዘመነ ሃዋርያትም ይሁን ከነሱ በውሃላ በተነሱት አበው ዘመን በቤተክርስቲያን ውስጥ ችግር ተነስቶ በአላውያን ነገስታት እገዛ የተፈታበት ግዜ ካለ ንገሩን።

  semone K

  ReplyDelete
 13. I am not clear why Government involve our church. first of all our Government is not chirstan and I hope everybody listen what prime Ministry said about the Ethiopian orthodox church. In my opinion it is better pray to God.

  ReplyDelete
 14. ጤና፡ይስጥልኝ፡ውድ፡ወገኖቼ
  እኔ፡Eyob G.የሰጠኸውን፡ሃሳብ፡ጥሩ፡ነው፡እላለሁ፡፡
  አሁን፡አሁንማ፡ሰዉን፡በፀሎት፡እግዚአብሔርን፡ከመለመን፡ይልቅ፡
  በራሱ፡መፍትሄ፡እንዲፈልግ፡የሚያደርጉና፡በፀሎት፡ሊያገኝ፡ከሚችለው
  ነገር፡የሚያርቁትን፡ሃሳቦች፡ቀን፡ከሌሊት፡እየጋቱ፡የባሰ፡መቀመቅ፡ውስጥ፡መክታት፡የብዙ፡ስዎች፡ስራ፡ሆኗል፡፡ይታሰብበት!

  ReplyDelete
 15. Dear Dakon Daniel & Readers,

  Yes, any one understand the problem and a number of ideas, solution and suggestion are forwarded from different corners of the country/worlds.

  But, the issues is who, when and how we all come together and work out our group and individual responsibilities?

  Other wise, we will not only remain with the problem but also pass the worst condition to the next generation.

  Selam,

  Temesgen Kassa, Dire Dawa

  ReplyDelete
 16. Dear all,
  I have tried to go through the main article by Hailegebriel and the comments given by the readers. As to me, some of the comments are irrelevant to the given article and also to the aim of this discussion. What the blogger (Daniel) asked is to give our opinion whether it is positive or negative to what he has proposed as a solution to the problem faced by our church. Some of the comments are just criticisms of comments of others. Why we waste time in this way??? It is possible to criticize what some one commented. But it has to be in a friendly manner and should be accompanied by an alternative solution. Otherwise simply criticizing is for me discouraging others from doing their best just like friction. In fact I understand that all that give comment on this blog may not have similar aim. Though most of them are trying their best for the benefit of the church, there may be some who need the continuity of the problem.Therefore, let us focus on how we can implement the solutions proposed by the blogger.
  Thank u all.

  ReplyDelete
 17. Kale Hiwoten Yasemlen Endiuem Ulunem Yanesaslen Amen!

  EGZIABHER Haymnotachnen Yetbklen Amen!

  ReplyDelete
 18. ሃይለ ሚካኤል ዘአዲስ አበባSeptember 3, 2010 at 11:35 AM

  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

  የተወደዳችው የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች ትላንት የመንግስት አካላት የምንላቸው ቤተክርስቲያን ለድህነት ምክንያት እንደሆነች ሲፈርጁ የነበሩ አዋሳ ላይ በግልፅ ክብራን የነኩ ወዘተ አይደሉም እንዴ
  ከሁሉ አስቀድሞ ሕዝበክርስቲያኑ መረጃ እንዲኖረው ማድረግ ብንችል

  ReplyDelete
 19. መንገዳችንን ለእግዚአብሄር አደራ ሰጥተን ፣እኛም በስጋዊ አቅማችን የምንችለዉን ሁሉ የድርሻችን መወጣት አለብን፣የድርሻህን መወጣት ፣መንፈሳዊ አለመሆን አይደለም ፣ ለዚህ ማስረጃ የያዕቆብን ታሪክ ማየት ያስፈሊጋል

  ReplyDelete