Saturday, August 21, 2010

የሆስፒታል ቫይረስ


በሕክምና እና በሕክምና ባለሞያዎች ዘንድ ካሉት ሥጋቶች መካከል አንደኛው በሆስፒታል ውስጥ ሆስፒታሉን ለምደው እና ወድደው፤ የሚኖሩት ቫይረሶች ጉዳይ ነው፡፡ እነዚህ ቫይረሶች በተለያዩ ሕመምተኞች አማካኝነት ወደ ሆስፒታሉ ይመጡና እዚያ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በመላመድ፣ የሚረጩትን መድኃኒቶች፣ ኬሚካሎች እና የማጽጃ ነገሮች ሁሉ ቀስ በቀስ በመቋቋም ኑሯቸውን በሕክምና ተቋሙ ውስጥ ያደርጋሉ፡፡ በዚህም የተነሣ የሕክምና ባለሞያዎችን እንዲሁም ታካሚዎችን ያጠቃሉ፡፡

እንደዚህ ዓይነቶቹ ቫይረሶች መከላከያዎችንም ሆነ መድኃኒቶቹን ስለተለማማዷቸው እነርሱን በማከም ማሸነፍም ሆነ ማድከም አስቸጋሪ ነው፡፡ ሕክምናው ባለበት በዚያው በሆስፒታሉ ውስጥ ስለሚኖሩም ራሳቸውን እያባዙ እና እንደነርሱው ሕክምናውን የሚቋቋሙ መሰሎቻቸውን እያበራከቱ በመሄድ፣ የሕክምና ማዕከል ተብሎ የተቋቋመውን አካል የማይድኑ በሽታዎች ማምረቻ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡

እንዲህ ዓይነቶቹ ቫይረሶች ለረዥም ጊዜ ከቆዩና በቶሎ ካልተነቃባቸው፣ የሕክምና ማዕከሉን ይቆጣጠሩታል፡፡ መፍትሔውንም ውስብስብና ከዐቅም በላይ ያደርጉታል፡፡ ሆስፒታሉን እስከማስቀየር፤ እስከማቃጠል፣ እስከማፍረስ እና እስከማዘጋት ይደርሳሉ፡፡

በመንፈሳዊ እና በፖለቲካ ተቋሞቻችን ውስጥ ከምናያቸው አልፈቱ ካሉን ችግሮች መካከል አንደኛው የሆስፒታል ቫይረስ ችግር ነው፡፡

ደግነት፣ ቅንነት፣ ትኅትና፣ ፍቅር፣ ሰላም፣ መከባበር፣ ይቅርታ፣ ለጋስነት፣ ራስን መግዛት፣ ይነግሥባቸዋል ተብለው በሚጠበቁት መንፈሳዊ ተቋሞቻችን ውስጥ ትዕቢት፣ጠማማነት፣እኔን ብቻ ይድላኝ ማlት፣ብጥብጥ፣ መናናቅ፣ ቂም በቀል፣ ስስት፣ አፍቅሮ ንዋይ፣ ነግሦባቸው እናያለን፡፡ ለሌሎች አርአያ ይሆናሉ፤ ማኅበረሰቡን በሞራል ሕጎች እና በሥነ ምግባር ይታደጋሉ ተብለው ተስፋ ሲደረግባቸው እነርሱ ራሳቸው የሥነ ምግባር ብልሹነት መገለጫ ቦታዎች ይሆናሉ፡፡

ለሀገሪቱ ዕድገት እና ብልጽግና፣ መሻሻል እና ብርታት፣ አርአያዎች እና ሞተሮች፣ ብቁ እና ታታሪ፣ በሥነ ምግባር የታነፀ እና ሕግ አክባሪ ዜጋ ፈጣሪዎች ሲባሉ የሙስና እና የብልሹ አሠራሮች፣ የኋላ ቀር ቢሮክራሲ እና የአምባገነንነት ምሳሌዎች፣ የሀገሪቱንም እድገት ጎታቾች ሆነው ይታያሉ፡፡ ለምን?

የሆስፒታል ቫይረስ አለ ማለት ነው፡፡ ሰይጣን መንኩሶ፣ ቀስሶ፣ ደቁኖ፣ ሰባኪ ሆኖ፣ ቅኔ ተምሮ፣ ጸጉሩን አስረዝሞ፣ ሼህ እና ቃዲ፣ ዑለማ ሆኖ፤ ፓስተር እና ወንጌላዊ፣ ዘማሪ እና ነቢይ፣ አገልጋይ እና አስመላኪ፣ ሆኖ ራሱ በቦታው ተቅምጧል ማለት ነው፡፡ ስለዚህም ሌሎችን ያድናል ተብሎ ተስፋ የተሰጠው ተቋም ራሱ የበሽታዎቹ መነሻ/ የቫይረሶቹ መኖርያ ሆኗል ማለት ነው፡፡

ሌላ ቦታ ያለው ቫይረስ መድኃኒት የሚፈራ፣ በመድኃኒትም የሚጠቃ፣ በመድኃኒትም የሚድን ነው፡፡ ሆስፒታል ውስጥ የሚኖር ቫይረስ ግን ምንም አይፈራም፡፡ ተለማምዶታላ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ምእመናን ምንም ያህል ቢያጠፉ እና ቢበድሉ፣ ቢሳሳቱ እና ኃጢአት ቢሠሩም መገሠጽ፣ ማስተማር፣ ማስፈራራት፣ የፈጣሪን ስም ጠርቶ መመለስ፣ ቃለ መጽሐፍ ጠቅሶ ልባቸውን መስበር ቀላል ነው፡፡ እነርሱ ጋር ያለው ቫይረስ በመድኃኒት ሊታከም፣ ሊድን ወይንም ሊዳከም የሚችል ነው፡፡

አሁን የቸገረን ሆስፒታል ውስጥ ያለው ቫይረስ ነው፡፡ ትምህርት፣ ጸሎት፣ መቅሰፍት፣ ተግሣጽ፣ ድርሳን እና ተአምር፣ ትንቢት እና መገለጥ፣ ቁርዐን እና ዱአ፣ ባህታዊ እና ልሣን ተናጋሪ፣ ሊፈራ የማይችል፡፡ ጠበል የለመደ ሆኖብን ነው የተቸገርነው፡፡ እግዚአብሔርን የማያውቁ የእግዚአብሔር ሰዎች በዝተው ነው የተሰቃየነው፡፡ ለቤተ እምነት ቅርብ ለፈጣሪ ግን ሩቅ የሆኑ አካላት ናቸው ሊድኑ ያልቻሉት፡፡

አትስረቅ የሚለው አካል ከሰረቀ፣ አታመንዝር ያለውም ካመነዘረ፤ ተፋቀሩ ያሉት ከተጣሉ፣ አንድ ሁኑ የሚሉት ከተከፋፈሉ፤ ሁላችን የአንድ የፈጣሪ ልጆች ነን የሚሉት በዘር እና በጎሣ ከተባሉ፤ የመነኑትን የሥልጣን ጥም ከያዛቸው፤ ሞተዋል የተባሉት የየራሳቸውን ቪላ ከገነቡ፤ የመንግሥተ ሰማያት ቁልፍ የያዙት የቢሮውን ቁልፍ ከዘጉ፤ ሌላ ልሳን እንናገራለን እያሉ የሕዝቡን ልሣን ካላዳመጡ፤ የነገው ትንቢት ተገለጠልን እያሉ የዛሬው ችግር ከጠፋቸው፤ በሽተኞችን እንፈውሳለን እያሉ እነርሱ ራሳቸው የማይፈወሱ በሽተኞች ከሆኑ፤ እንግዲህ «ምላጭ ቢያብጥ በምን ይበጡታል፣ ውኃ ቢያንቅ በምን ይውጡታል» የተባለው ደርሷል ማለት ነው፡፡

ፖለቲካችንም ተመሳሳይ ቫይረስ እያጠቃው ነው፡፡

ሕዝቡን በርእዮተ ዓለም አንቅተው ያሰልፋሉ ሲባሉ እነርሱ ራሳቸው ርእዮተ ዓለም ከሌላቸው፤ ሕዝቡን አደራጅተው እና መንገድ አሳይተው ወደ ዕድገት እና ብልጽግና ያደርሱታል ሲባሉ እነርሱ ራሳቸው መደራጀት እና መንቃት አቅቷቸው መንገድ ከጠፋባቸው፤ ሕዝብን የሥልጣን ባለቤት ያደርጉታል ተብለው ተስፋ ሲጣልባቸው እነርሱ ለራሳቸው ሥልጣን ብቻ የሚያስቡ ከሆኑ፤ ለሌላው ያስረዳሉ፣ ያሳውቃሉ፣ ሲባሉ እነርሱ ራሳቸው የድርጅታቸውን ፕሮግራም፣ ሕግ እና መመርያ ማወቅ እና መተግበር ሲሳናቸው፤ የተወዳደሩበት ዓላማ እና የሚሠሩት ሥራ ሲለያይ፤ የሆስፒታሉ ሻይረስ አለ ማለት ነው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ዘመናዊው የፖለቲካ አካሄድ ከተጀመረ ጀምሮ ሥርዓታት ቢለዋወጡ እንኳን ያልጠፉ ችግሮች ግን አሉ፡፡ የደጋፊውም ሆነ የተቃዋሚው፣ ያለፈውም ሆነ የመጣው፣ የሚጋሯቸው ተመሳሳይ በሽታዎች አሉ፡፡ ከአዲሱ ትውልድ ይልቅ በነባሮቹ ማመን፤ የተወሰኑትን ብቻ የፖለቲካ ተዋንያን ማድረግ፣ በየጊዜው መለያየት እና መሰነጣጠቅ፤ ለችግሮች ምንጊዜም የውጭ ተጠያቂን መፈለግ፤ የማይጨበጥ እና የማይዳሰስ ጠላት መፍጠር፤ ከተሳትፎ ይልቅ ቲፎዞነትን መምረጥ፣ ከአመክንዮ ይልቅ ስሜትን ማዳመጥ፣ ከመሠረተ ሃሳቦች ይልቅ ግለሰቦችን መከተል፤ የፖለቲካ አካሄዶችን ከግላዊ ጥቅም አንፃር መመዘን፤ ስሕተትን መቀበል እንደ ውርደት ማየት፤ ራስን ብቻ ማዳመጥ፡፡

እነዚህ እና ሌሎች መሰሎቻቸው የፖለቲካውን ሆስፒታል ተላምደውት እየኖሩ ያሉ ቫይረሶች ናቸው፡፡ ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ተላምደው፣ መሰሎቻቸውንም ተክተው ተቀምጠዋል፡፡ የሚመጡ መከላከ ያዎችም ሆኑ መድኃኒቶች ሊያጠፏቸው አልቻሉም፡፡ ሆስፒታሉ ውስጥ ከመኖራቸው የተነሣ እነርሱ ራሳቸው የሆስፒታሉ አካላት ሆነዋልና፡፡ እዚህም እዚያም ቢኬድ፣ ይህኛውንም ሆነ ያኛውን አካል ብናይ ይቃወማቸዋል፣ እዋጋቸዋለሁ ይላል፣ ይምላል፣ ይገዘታልÝÝ ነገር ግን ራሱ የችግሩ እንጂ የመፍትሔው አካል ስላልሆነ አያክማቸውም፡፡

እዚህኛው ፓርቲ ውስጥ እንዲህ እና እንዲያ አለ፣ ይህኛው አካሄድ በዚህ እና በዚያ ምክንያት አያስኬድም ብሎ የተሻለ ነገር ሊፈጥር፣ ሌላ አካሄድ ሊያሳይ እንደ አዲስ ይደራጅና ሳያስበው ያንኑ ስሕተት ይወርሰዋል፡፡ ምከንያቱም እነዚህ ችግሮች እንደ ሆስፒታሉ ቫይረስ ቋንቋችንን፣ አሠራራችንን፣ባህላችንን፣ ሕጎቻችንን፣ መመርያዎቻችንን፣ ውሳኔዎቻችንን ተለማምደዋቸዋል፡፡

ባለፈው ሥርዓት ሕዝብ ሁሉ የሚያውቀው አንድ አባባል ነበር፡፡ በሀገሪቱ ውስጥ ኮሚቴዎች በዙ ተብሎ ምክክር ተደረገ፡፡ በመጨረሻም ተመካካሪዎች በአንድ ሃሳብ ላይ ተስማማሙ ይባላል፡፡ ኮሚቴዎችን አጥንቶ የሚቀንስ ሌላ ኮሚቴ ይቋቋም፡፡ እነዚህ ሰዎች ኮሚቴን እንቀንሳለን ብለው ሌላ ተጨማሪ ኮሚቴ እንዲያቋቁሙ ያደረጋቸው ቫይረሱ ነው፡፡ ይህ ችግር ዛሬም እንኳን አልለቀን ስላለ በየመሥሪያ ቤቱ፣ድርጅቱ፣ ማኅበራቱ፣ ወዘተ አንዳች ችግር ተፈጠረ፣ ሕዝብ ተማረረ፣ አሠራር ተበላሸ፣ ተብሎ ሲጠየቅ እንደ መጀመርያ እና ዋና መፍትሔ ተደርጎ የሚቆጠረው ኮሚቴ ማቋቋም ነው፡፡ ያለ ኮሚቴ ማሰብ እና መሥራት የሚቻል አይመስለንም፡፡ ለምን? የሆስፒታሉ ቫይረስ መፍትሔውን ስለለመደው ችግሩን መፍትሔ እያደረገው ይኖራል፡፡

እዚህ ሲያትል ያሉ ሰዎች የነገሩኝን ላውጋችሁ፡፡ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ተዳከመ፡፡ አዳዲሱ ትውልድ ራቀው፣ ነባሮቹ አመራሮች መሥራት አልቻሉም ተባለ፡፡ አመራሩን በአዲስ ለመተካት፤ በተለይም አዲሱን ትውልድ ቦታ ለመስጠት፤ ወጣቶች ገብተው እንዲይዙት ለማድረግ በየቦታው፣ በየሬዲዮው፣ በየጋዜጣው ተደሰኮረና ስብሰባ ተጠራ፡፡ ይሄው ሃሳብም በስብሰባው ቦታ ይበልጥ ተንፀባረቀ፡፡ በመጨረሻ ምርጫ ተደረገ፡፡ የሚገርመው ግን የተመረጡት በሙሉ ሽማግሌዎች፣ ደጃዝማች፣ ባሻ፣ ሻለቃ፣ የተሰኙ½ ብለው ብለው ያልተሳካላቸው ሰዎች ሆኑ፡፡ የተባለው እና የሆነው ነገር ሊገጣጠም አልቻለም፡፡ ይሄ የሆስፒታል ቫይረስ መች በፉከራ ብቻ ይጠፋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎቻችን በርእዮተ ዓለም የተለያየን ነን ይሉና በአደረጃጀት ግን ተመሳሳይ ናቸው፤ በድብቅነት፣ በአመራረጥ፣ ከውጭ ለመጣ ነገር በሚሰጡት ልዩ ቦታ፣ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ትናንት ያልተሳካላቸው ሰዎች ለአሥራ ሁለተኛ እና አሥራ ሦስተኛ ጊዜ መሪነትን የሚሞክሩበት፤ ያጠፉ ሰዎች የሚሸለሙበት ፖለቲካዊ አካሄድ የሁሉም ጠባይ ነው፡፡ ሃሳባቸውን ከመናገር አልፈው ለመጻፍ የማይ ወድዱ፤ ራሳቸውን በራሳቸው ለመተቸት የማይደፍሩ፤ አጠቃላይ ፖለቲካዊ አካሄዱን፣ አስተሳሰቡን፣ ለመለወጥ ከመሥራት ይልቅ ለምርጫ ብቻ የሚሠሩ ፓርቲዎችን መመሥረት ተመሳሳዩ ጠባይ ነው፡፡ በትክክል ቢታይ፣ ፕሮግራማቸው ቢመረመር፣ ዘጠና ስድስቱ የሀገራችን ፓርቲዎች ከአራት እና አምስት አይበልጡም ነበር፡፡ ዘጠና ስድስት ያደረጓቸው ርእዮታቸውና ፕሮግራማቸው ሳይሆን መሪዎቻቸው እና ቲፎዞዎቻቸው ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ መድኃኒት የማያስለቅቀው የሆስፒታል ቫይረስ ነው፡፡

የሆስፒታልን ቫይረስ በተለመደው የሕክምና መንገድ እና አሠራር ማጥፋት፣ ማዳከም እና ማላቀቅ አይቻልም፡፡ ሆስፒታሉን ከመድኃኒቶቹ በላይ ያውቀዋልና፡፡ እርሱኮ በሕክምና በለሞያዎቹ፣ በመድኃኒት መሣርያዎቹ፣ በአልጋዎቹ እና ግድግዳዎቹ፣ በፋርማሲዎቹ እና ላቦራቶሪዎቹ ውስጥ ነው ያለው፡፡ ስለዚህም ሆስፒታሉ ሙሉ በሙሉ በእነዚህ ቫይረሶች ተወርሮ ሥራ ከማቆሙ በፊት ከተለመዱት የተለየ፤ አዲስ እና መሠረታዊ የሆነ መፍትሔ መምጣት አለበት፡፡ ሕክምናው ሐኪሞቹን፣ መሣርያዎቹን፣ አልጋዎቹን፣ ቤቱን ከማከም መጀመር አለበት፡፡
ይህ ጽሑፍ ባለፈው ቅዳሜ በሮዝ መጽሔት የወጣ ነው

16 comments:

 1. I like your analogy here, although it is bacteria, not virus, that is causing problem in the hospitals but that is besides the point.

  You know who is most responsible for controlling and eradicating this antibiotics-resistant bacteria? It is the people who work in the hospitals - the doctors, the nurses etc. Likewise, it is the responsibility of the people who serve the masses in their respective venue, be it religious or secular.

  But if the doctors and the nurses are also infected with this bug, then the masses themselves, the ultimate stakeholders, need to step in. This is what is required in our church and in our government. We can't let this infected people continue spreading their infection while preaching cure. But first, we need to carefully examine ourselves. Are we healthy enough to diagnose disease in others? Have we not become part of the problem? Have we not spread hatred while preaching love? Have we not judged too soon while preaching patience? brake apart churches while preaching unity?
  Before trying to cure others common cold, lets try find out if there is a hidden cancer in our own body.

  May God give us the wisdom to see our own fallacies

  ReplyDelete
 2. ዲ.ዳንኤል እኔን የቸገረኝ ደግሞ የቤተክርስቲያናችን ቫይረስ ነው

  ReplyDelete
 3. ሰላም ለዚህ ቤት
  ከደብረ ቁስቋም
  ዲ.ዳንኤል በውነት ሀሳቡ መልካም ነው::አንተ ብዛቱን በፖለቲካው ላይ አደረከው እንጂ ነገሩ በብዛት አሁን የሚታየው በቤተ ክርስትያናችን ላይ ነው እኜ የምለው ቢኖር እባካችሁ ይህንን የምታነቡ የአብያተ ክርስትያናት አስተዳዳሪዎች ካላችሁ እስቲ እናንተ እንኩዋን የራሳችሁን ለመወታት ሞክሩ::ሌላው እኝኣ ይህንን የምናነብ በሙሉ ቫይረሶቹን ለማትፋት የየራሳችንን ትረት እናድርግ.
  እግዚአብሔር አምላክ ቤተክርስትያናችንን ይተቅ

  ReplyDelete
 4. good vission!!!!!!!!

  ReplyDelete
 5. Thanks Daniel,
  It is very interesting article.
  Why ... Our Political, Religion, Acedemic, ... Institutes leaders and followers act that way? Hmmm ... hard to answer because I can't speak for others.
  But I am more than happy to share my experience. I used to be a person who couldn't take "NO" for an answer and who firmly believed my ideology is "SUPER" , So it was unthinkable to reconcile differences.
  After years of struggle with myself I finally learn to value the views of others. I learn to listen and get the best out of someone or something.I know how hard it is to admit mistakes. It takes a strong personality and gut to take measures on our faults for the better tomorrow.

  ReplyDelete
 6. ይገርማል፡፡ እኛን የረገመን አለ? ወይስ ጂናችን መጠናት አለበት? ከአንዱ አንዱ የማይሻልበት ምክንያት አይገባኝም። ቤተ/ክን ውስጥ የተከሰተው ነገር አንገት የሚያስደፋ ነው። በአሁን ሰአት የተቀመጠ አባት(ዻዻስ)ሁሉ ተጠያቂ የሚሆንበት ነው። መንጋው ተረብሿል ብዙዎች በእነሱ ምክንያት ደክመዋል ጫፍ ላይ የነበሩትም ጥለው ወጥተዋል።
  እነዚህ (anibiotic resistant bacteria) የተባሉ የውስጥ ሰዎች ተሰብስበው እንደገና ዮሀንስ ወንጌልን ቢደግሙ ይሻላቸው ነበር። "እኔ ከእናንተ እንደ ታናሽ ነኝ" ብሎ ማስተማር የሚገባው ለራሱ መታሰቢያ ካቆመ። ያለው ለሌለው ይስጥ ብሎ ማስተማር የሚገባው ለራሱ ምስል million$ ካወጣ ምን እንላለን።
  መቻቻልማ ከየት መጥቶ- ሰውን አስተምሮ እንደመመለስ እከሌ/እከሊት መናፍቅ ነው ማለት ይቀድመናል፡ ይህ ደግሞ ጎልቶ የሚታየው እነዚሁ አዋቂ ተብየዎች ጋር ነው። ሰባኪ ሰባኪን መናፍቅ ይላል፡ አባት አባትን ያቃልላል። አንድ ሰው አጥብቆ ከተከራከረ መናፍቅ ይባላል። አሁንማ ከነገር ውስጥ ጎትተው አውጥተው (out of context) ያልተመቻቸውን ሰው መናፍቅ ማለት ተስፋፍቷል፡ ይህ እኮ እራሱ በሀሰት መመስከር ነው፡፡
  ነገር ላይ ለመፍረድ መቸኮላችንስ- ባለፈው አንድ አባት አዲስ አበባ ውስጥ እንዲህ አደረጉ ሲባል ስልጣን ፈልገው ነው፡ ልታወቅ ብለው ነው ያለው ሰው ብዛቱ። ጭፍን ተቃዋሚ ይሏል ይህ ነው፡፡
  እንዲህ እያልን የሰይጣን መሳርያ ሆነን ይህች የጥንት ቤተ/ክን፡ የምታስተምረው ሳታጣ ሁሉ ተሟልቶላት አለምን ማስተማር ሲገባት እንኳን አለምን ሀገራችንን ማዳረስ አቅቶን ይኸው እንነታረካለን። እንደ ኳሱ- መስራቾች ዃላ ግን ግራ የገባን እንሆን እኛስ?
  ብቻ የሚያሳዝነው እንደ ጥንቸሏ ጊዜ ካለፈ መንቃታችን ነው። ይቅር ይበለን!

  ReplyDelete
 7. Dear Daniel,
  It is very interesting overview. I appreciate the above(yan001) comment. I am sometimes rigid to accept others comment. If you have time, please try to dwell up on the way I and others can totally avoid the rigidness. I am saying this because as you try to point out in the article, we ,Ethiopians, have this problem and this is the main "Virus or Bacteria".

  May God help us on our ways.

  ReplyDelete
 8. Hi all

  I hate to write in Amharic using Latin/English alphabets. Can any one reach me with a link to a free Amharic font?

  Thank you

  ReplyDelete
 9. Dani this is a good analogy, let me add one point, in hospital we use cocktail drugs to eliminate the antibiotic resistant bacteria, why don’t we use cocktail ideas (by discussing various opposing views), to solve our problems both in politics and religion?

  ReplyDelete
 10. Hi Dn. Daniel,
  I love your analysis. Chigirun Kuchi new yarekewu bemigeban melku. I always love your analysis on serious societal issues(religious, attitude, history and culture), not zos about soccer and joke stuffs.

  Ahun min enadirg new tiyakewu? Endet kezih azurit wust eniwuta????
  plz yemefitihe hasab tal tal argubet anbabiyan

  ReplyDelete
 11. ይህቺ ዌብ ሳይትህ እጅግ ታረካለች
  ትንሹን ትልቁን በእውቀት ታንጻለች
  እውነትና ምክር ተግሳጽን ይዛለች
  እሺ በጄ ላለ ቀጭን ጎዳና ነች፡፡

  ይህንን መማሪያ ያላዩ ዌብ ሳይቱን
  ጭራሹን ያልሰሙ መድረኩ መኖሩን

  ብዙ ናቸውና እባክህን ይስሙ፡፡

  ስለዚህ በጋዜጣ ወይም በሬድዮ
  በETV መስኮት አልያም በቪዲዮ
  ብታስተዋውቀው ምን አለ ዳንኤል
  ካስፈለገ ደግሞ ገንዘብ እኛ እንክፈል፡፡

  ReplyDelete
 12. God bless u and please share us some other countries experience about how they have managed such problems.Keep on

  ReplyDelete
 13. ጤና፡ይስጥልኝ፡ዲ.ዳንኤል
  (ሰይጣን መንኩሶ፣ ቀስሶ፣ ደቁኖ፣ ሰባኪ ሆኖ፣ ቅኔ ተምሮ፣ ጸጉሩን አስረዝሞ፣ ሼህ እና ቃዲ፣ ዑለማ ሆኖ፤ ፓስተር እና ወንጌላዊ፣ ዘማሪ እና ነቢይ፣ አገልጋይ እና አስመላኪ፣ ሆኖ ራሱ በቦታው ተቅምጧል ማለት ነው፡፡ ስለዚህም ሌሎችን ያድናል ተብሎ ተስፋ የተሰጠው ተቋም ራሱ የበሽታዎቹ መነሻ/ የቫይረሶቹ መኖርያ ሆኗል ማለት ነው፡፡)በእኔ፡አስተሳሰብ፡እስልምናም፡መናፍቃንም፡ቢሆኑ፡ጥንቱንም፡በሰይጣን፡የተመሠረቱ፡ስለሆኑ፡ይህ፡
  የማስተካከያ፡ሀሳብህ፡እነሱን፡መጨመር፡የለበትም፡ምክንያቱም፡
  እነርሱ፡ራሳቸው፡Virus፡ስለሆኑ፡፡ትክክለኛ፡ሃይማኖት፡አንዲት፡
  የኢ/ኦ/ተ/ቤተ፡ክርስቲያንና፡እርሷን፡የሚመስሉት፡ብቻ፡መሆናቸው፡እንዲታወቅ፡ያስፈልጋል፡፡በዚህ፡መሠረት፡ሌሎቹ፡መጠቀሳቸው፡ሰውን፡ሊያሳስት፡ስለሚችል፡ይታሰብበት፡እላለሁ፡፡

  ReplyDelete
 14. ሼህ ቃዲ ኡላማ ወንጌላዊ አስመላኪ ባለልሳን ምናምን መጥቀስ እዚህ ጋር ለምን አስፈለገ?

  ReplyDelete
 15. እንደምንጊዜውም ጥሩ ጽሁፍ ነው:: እንግዲህ ችግሮቻችን ሁሉ በተለያዩ ጽሁፎች እና አጋጣሚዎች ታውቀዋል: መፍትሄዎቹም ከሞላ ጎደል ተገልጸዋል:: መችም ባህላችን ነውና ሁላችንም ሊቃውንት ስለሆንን ትንተናና መስጠትና መላምት መምታት አልከበደንም:: እንግዲህ ምን ቀረን? ተግባር! ታዲያ መች ይሆን በቃላትና በኮምፒዩተር ላይ የገነባናትን ሀገርና መልካም ማህበረሰቧን ወደ አካላዊ ሃገር የምንለውጣት? እስቲ አሁን ደግሞ እያንዳንዳችን ምን መተግበር እንደምንችል እንወያይና ወደ ተግባር እንሂድ:: የቁጥር መጀመሪያ አንድ ነውና ተግባርም በአንድና በሁለት ሰው ሊጀመር ይችላል:: ከዚያ በሗላማ ፈረንጆቹ እንደሚሉት 'The sky is the limit'!

  ReplyDelete