Friday, August 20, 2010

ኳሱን አትንኩብን

በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ የጀመርነውን ውይይት ለማሰቢያ ጊዜ እናገኝ ዘንድ ለጊዜው ዐረፍ እንበልና ማክሰኞ ደግሞ የሌሎቻችሁን አስተያየት በመጨመር እንመለሳለን፡፡ ለዛሬው ለማረፊያ እነሆ፡፡
 «ወጣቱ በአውሮፓ እግር ኳስ ነፍሱ ሊወጣ ነው፡፡ የሀገሩን እግር ኳስ እና የሀገሩን ጉዳዮች ከመከታተል ይልቅ በእን ግሊዝ፣ በጣልያን እና በስፔይን የእግር ኳስ ተጨዋቾች ልቡ ተነድፏል፡፡ ሚዲያዎችም ቢሆኑ እንዴው ለአመል ያህል የሀገራችንን ኳስ ነካ ነካ ያደርጉና እጥፍጥፍ ብለው ወደ አውሮፓ ይሻገራሉ» እያላችሁ ታሙናላችሁ አሉ፡፡


ወገኞች ናችሁ እንዴው፡፡ የጨዋታውን ዓይነት፣ የግቡን ልዩነት፣ የታክቲክ እና የቴክኒኩን ነገር ተውት ይቅር ግዴለም፡፡ የተጨዋቾቹን ዝና እና ታዋቂነት፣ የሚያሳዩትን ምትሐት ተውት አይነሣ ግዴለም፡፡ አሁን እኛ ሀገር በእግር የሚመታ ኳስ እንጂ እግር ኳስ አለ ይባላል? እንኳን የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ከመሠረቱት ሦስት ሀገሮች አንዱ ልንመስል እግር ኳስ ከአውሮፕላን ተወርውሮ የነጠረባት ሀገር እንመስላለን? ለመሆኑ እኛ ሀገር ስለ ተጨዋቹ እና ስለ ጨዋታው ከሚነገረው በላይ ስለ ቡድኖቹ ሽኩቻ እና ስለ ፌዴሬሽኑ ውዝግብ የሚነገረው አይበልጥም?

«ወጡ ሳይወጠወጥ ወስከንቢያው ቁጢጥ» ሲባል አልሰማችሁም፡፡ ኳሱ መከራ እያየ፣ እኛ ማን ሥልጣን ላይ ይውጣ የሚለው ነው የሚያወዛግበን፡፡ መጀመርያ ኳሱ ሲኖር እኮ ነው ፌዴሬሽን እና የፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የሚያስፈልገው፡፡ «ጥርስ የላት ትወቀር አማራት» አሉ፡፡ የኢትዮጵያን እግር ኳስ አሁን ካለበት ደረጃ ለማድረስ እኮ ግዴለሽነት እና ክፋት እንጂ ፌዴሬሽን አያስፈልግም ነበር፡፡

ስንት ዋንጫ እየሳሙ፣ስንት ውጤት እያመጡ፣ ስንት ታሪክ እየሠሩ ዓለምን የሚያናውጡ ቡድኖች ያሏቸው ፌዴሬሽኖች ሳይወዛገቡ እኛ ፊፋ ድረስ ሄደን እንካሰሳለን፡፡ «ቅቤ አንጣሪዋ ተቀምጣ ጎመን ቀንጣሿን ምች መታት» አሉ ወይዘሮ ዘርፌ፡፡ ፊፋስ ቢሆን «ማስረጃችሁን አምጡ፣ የፊፋ ሕግ አልተከበረም፣ መተዳደርያው ተጥሷል» እያለ ያለ ደረጃችን ደረጃ ከሚሰጠን መጀመርያ እስኪ ስታዲዮም ገብቼ ስትጫወቱ ልያችሁ፣ እስኪ ቡድኖቻችሁ እንዴት እንደተደራጁ አሳዩኝ፣ እስኪ ስንት ስታዲዮም ገነባችሁ፣ እስኪ ቢሮአችሁ እንዴት እንደ ተደራጀ ልይ» ቢል ኖሮ ውዝግቡ ይህንን ያህል ዘመን መች ይፈጅ ነበር፡፡ በሌለ ነገር እኮ ነው መከራ የምናየው፡፡

«ሥጋ ቁጠር ቢሉት ጣፊያ አንድ አለ» የተባለው ደረሰና ለምንድን ነው ኳሳችሁ የማያድገው? ተብለው ሲጠየቁ «ሕዝቡ የአውሮፓ እግር ኳስ ስለሚያይ ከስታዲዮም ስለ ጠፋ ነው፡፡ ስለዚህም የአውሮፓ ጨዋታ የማይታይበትን መንገድ እንፈልጋለን» አሉ አሉ፡፡ ለሠራነው ስሕተት ራሳችንን ተጠያቂ የምናደርግበት፣ ይህ ነገር ሊከሰት የቻለው ምን ስሕተት ስለሠራሁ ነው? ብለን የምንጠይቅበት ዘመን መቼ ይሆን የሚመጣው፡፡ እንዴው እድሜ ልካችንን ለችግራችን ሁሉ ውጫዊ ምክንያት እንደፈለግን ልንኖር ነው?

የጤፍ ነጋዴ ፓስታ በብዛት ስለተመረተ ገበያ ጠፋብኝ ብሎ ያውቃል? የቢራ ፋብሪካ እዚህም እዚያም ቢከፈት የሀገሬ ጠጅ ቤቶች መች ንቅንቅ አሉ፡፡ እነ ገደል ግቡ፣ እነ ውስኪ ለምኔ፣ ጠጅ ቤት ይሄው ጢም እንዳሉ ናቸው፡፡ ሌላውን ተውት የሀገሬ ሰው በፊልሞቹ ላይ የሚሰጠውን ያንን ሁሉ ትችት እየሰማ እንኳን፣ «ሰው በዐቅሙ ነው የሚጸድቀው» ብሎ ከውጭ ሀገር ፊልሞች እኩል እንዲያውም በላይ፣ የሀገሩን ፊልም እያየ አይደለም እንዴ?

ለመሆኑ ሕዝቡ የአውሮፓ እግር ኳስን ለምን እንደሚወድደው ያውቁታል፡፡ የጨዋታውን ጣዕም እና የቡድኖቹን የብቃት ደረጃ አላነሣውም፡፡ እንዳላስጎመጃቸው ብዬ፡፡ ኧረ ሌላ ሌላውን፡፡ ለመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለ አንድ ቡድን፣ ተጨዋች፣ የቡድን አሰላለፍ፣ የአሠልጣኞች ሁኔታ፣ የክለብ ባለቤቶች እንቅስቃሴ፣ የገቢ እና ወጭ ጉዳይ ለማውራት መረጃ ይገኛል? የተጠናከረ ዌብ ሳይት ያለው ቡድን አለ? የተደራጀ ሙዝየም ያለው ቡድን አለ? የአንድ ተጨዋች ታሪክ፣ ያገባቸው ግቦች፣ መቼ እንዳገባ፣ የት ላይ እንዳገባ? በመዝገብ ይያዛል? በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ በዛሬው ዕለት የዛሬ ሠላሳ ዓመት ምን ተደርጓል? ተብሎ ቢጠየቅ መልስ ያለው ክለብ እና ፌዴሬሽን አለን?

በሐሜት ከሚነገረው በዘለለ የተጠናቀረ፣ሁሉም ሊያውቀው የሚችል እና የሰሚውን ልቡና ሊያረካ የሚችል መረጃ አለ? ስለ አውሮፓ ቡድኖች፣ ፌዴሬሽኖች፣ ተጨዋቾች፣ አሠልጣኞች እኮ ከሚፈለገው በላይ የመረጃ ጎረፍ ይፈስሳል፡፡ ምን በሉ፣ ምን ጠጡ፣ የት ዋሉ፣ የጫማ ቁጥራቸው ስንት ነው፣ የቤተሰባቸው ሁኔታ እንዴት ነው ተብሎ ቢጠየቅ፣ በደቂቃ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡ «የማያውቁት ሀገር አይናፍቅም» ሲባል አልሰማችሁም፣ ታድያ የማናውቀውን እግር ኳሳችንን እንዴት እንውደደው፡፡

አንዳንድ ባለሥልጣናት እኮ መረጃ መስጠት የሚመስላቸው ጋዜጠኛ ጠርተው የሚያስቡትን እና የሚፈልጉትን መናገር ነው፡፡ ይሄኮ ሃሳብን መግለጥ እንጂ መረጃ መስጠት አይደለም፡፡ መረጃ መስጠት ማለትማ መረጃ መሰብሰብ፣ ሊገኝ በሚችልበት ቦታ እና መንገድ ማስቀመጥ፣ በልዩ ልዩ የመረጃ ማስተላለፊያ መንገዶች ወደ ተጠቃሚዎቹ ማድረስ ነው፡፡ ደግሞምኮ እኛ የምንፈልገውን እና የምንወደውን ብቻ እንዲታወቅ የምናደርግ ከሆነ መረጃ መስጠት ሳይሆን ዕንቁልልጮሽ ነው የሚሆነው፡፡

ደግሞስ መረጃ ቢኖርስ ነጻነቱ የት ይገኛል፡፡ የአውሮፓ እግር ኳስን እኮ ብንፈልግ ስለ ተጨዋቹ ፣ብንፈልግ ስለ አሠልጣኙ፣ ብንፈልግ ስለ ክለቡ ባለቤት፣ ብንፈልግ ስለ ቡድኑ ገቢ እና ወጭ፣ ብንፈልግ ስለ ፌዴሬሽኑ የዕለት ውሎ ስንተች፣ ስንተነትን፣ ስንከራከር ብንወል ማን ተቆጭ አለን፡፡ ጋዜጠኞቹ እንኳን ዘና ብለው መዘገብ የሚችሉት የሀገሪቱን ዘገባ ጨርሰው ሜዲትራንያንን ሲሻገሩ ነው፡፡ የሚቆጣቸው ፌዴሬሽን፣ የሚያስፈራራቸው ባለሀብት፣ የሚሰድባቸው ደጋፊ፣ የሚዝትባቸው ክለብ የለ፡፡ እኛ ሀገርኮ ኳሱ ለትንታኔ አይመች፣ የኳሱም ሰዎች ለትንታኔ አይመቹ፡፡

ስለ ጊዮርጊስ ከተቸህ «ፀረ ጊዮርጊስ» ትባልና መቆሚያ መቀመጫ ታጣለህ፡፡ ስለ ቡና ከተናገርክ «ፀረ ቡና» ትባልና ምስህ ዱላ ይሆናል፡፡ እንኳንስ ስትተቸው ስታመሰግነው እንኳን «ሦስት ጊዜ ምስጋና አንዱ ለነገር ነው»ብሎ በሚጠራጠርህ ሰው መካከል ሆነህ እንዴት ነው ስለ ሀገራችን ክለቦች የምትጨነቀውና የምትደግፈው፡፡ «ድጋፍ ተቃውሞን ካልፈቀደ፣ እንጀራ እርሾን ካልወሰደ» ምን ያደርጉልናል፡፡

ሁለት የአውሮፓ ኃያላን ቡድኖች ከመጋጠማቸው በፊት እዚህ አዲስ አበባ ሆነን አሰላለፋቸውን እናውቀዋለን፡፡ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ማን ለማን እንደተሰለፈ በግልጽ ይታወቃል? በዛሬ ጨዋታ ለአርሴናል የተሰለፈው በቀጣዩ ጨዋታ አሠልጣኙ እንኳን ሳይሰማ ለማንቸስተር እየተሰለፈ መከራ አየንኮ፡፡ እዚህ አዲስ አበባ ሆነን የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ሲከፈት ማን ወደ የትኛው ቡድን ሊሄድ እንደሚችል በግምትም፣ በፍንጭም፣ በመረጃም እንናገራለን፡፡ መሄድ አለበት፣ የለበትም እያልን እንከራከራለን፡፡

አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም መስክ ማን ወደ የትኛው ቡድን ለመቀላቀል እንዳሰበ፣ እነማን ማንን እንዳስፈረሙ፣ ማን ከነማን ጋር ለመፈራረም ውስጥ ውስጡን እየመከረ እንደሆነ ማወቅ፣ ካወቁስ በኋላ ሃሳብ መስጠት ይቻላል? ይኼው ስንቶቹ መቼ እንደ ተነጋገሩና፣ መቼ ሃሳባቸውን እንደቀየሩ ሳናውቀው ለሌላ ቡድን ሲጫወቱ አገኘናቸው አይደል እንዴ፡፡ አንዳንዶቹም ጭራሽ የነበሩበትን ቡድን ለቅቀው፣ እንዲያውም አብረዋቸው ከተጫወቱት ጋር ተጋጭተው፣ የሌላ ቡድን አሠልጣኝ ሲሆኑ ያየናቸው በድንገት ነው፡፡ የአውሮፓ ኳስ ቢሆን ኖሮ ቢያንስ ለመገመት በቻልን፣ ከተቻለም ፍንጭ ባገኘን ነበር፡

ለመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ማንንም ሳይፈሩና ሳይሰቀቁ እንደ ልብ ሊያወሩበት እና ሊከራከሩበት የሚችሉት ጉዳይ የአውሮፓ ኳስ መሆኑን ታውቃላችሁ፡፡ ብንደግፍ፣ ብንቃወም፣ የደገፍነውን ቡድን ዓርማ ብናውለበልብ፣ ማልያውን ብንለብስ፤ ስለ እያንዳንዱ ነገር እያነሳን ብንፈልጥ ብንቆርጥ ማን ተቆጭ አለን፡፡ እና እንደዚህ በነጻነት የሚወራ ጉዳይ ከየት ይገኛል ጃል፡፡ አቦ ተውና፡፡

ደጋፊም ተቃዋሚም መሆን እዚህ ሀገር ዕዳ ነው፡፡ የመንግሥት ደጋፊ ነኝ ካልክ ገልማጭህ ብዙ ነው፡፡ ተቃዋሚም ነኝ ካልክ የሚያጉረጠርጥብህ በዚያው ልክ ነው፡፡ የአንዱን ማልያ መልበስ ቀርቶ ልትገዛ ስታገላብጥ ከታየህ መከራ ነው፡፡ እንኳንስ ስለ ተጨዋቾቹ አንሥቶ ለመነጋገር እና ለመተቸት ይቅር እና በቴሌቭዥን ሲቀርቡ እንኳን እነርሱን ትኩር ብለህ ካየህ አንዱ «ምን ታፈጣለህ?» ይልሃል ሌላው ደግሞ «ምነው ሙድ ያዝዥሳ» ብሎ ይተርብሃል፡፡ በአውሮፓ ኳስ ግን፣ ብትደግፉ ተለጣፊ፣ ብትቃወሙ አደናቃፊ የሚላችሁ የለም፡፡

ደግሞስ ደጋፊ እና ተቃዋሚ በአንድ አዳራሽ የሚሰበሰብበት ይህንን የመሰለ ነገር ከየት ይገኛል፡፡ ከመተራረብ፣ ከመተቻቸት ያለፈ ሌላ ነገር የለ፡፡ ርግጥ ነው እግር ኳሱን በፖለቲካው መንገድ ለማስኬድ የሚፈልጉት አንዳንዶች ብጥብጥ እያነሡ ተቸግረን ነበር፡፡ አሁን ግን ጋብ ብለዋል፡፡ በኳስኮ በዚህኛው ጨዋታ ካሸነፋችሁ እየጨፈራችሁ ቤታችሁ ትገባላችሁ፣ አንድ ሳምንት ትተነትናላችሁ፣ ከዚያ በኋላ ለቀጣዩ ጨዋታ መዘጋጀት ነው፡፡ ትናንት አሸነፋችሁ ማለት ነገም ታሸንፋላችሁ ማለት አይደለም፡፡ ብትሸነፉም ለጊዜው ትናደዱና እንደ ገና ለማሸነፍ መሥራት ነው፡፡ ቴክኒክ እና ታክቲክ መቀየር፣ ሥልጠናውን ማጠናከር ብቻ ነው፡፡ ትናንት ለምን እንዲህ ሆነ ብሎ ሙዝዝ ማለት የለም፡፡ ሌላ ሌላውንማ ሲያሸንፍና ሲሸነፍ ምን እንደሚመስል አየነውኮ፡፡

ኧረ ለመሆኑ የአውሮፓ ኳስ ባይኖር ስለ ምን እናወራ ነበር፡፡ ሰው ቋንቋ ኖሮት እንዴት ሳያወራ ይኖራል? ምሳ ሲበላ፣ ሻሂ ሲጠጣ፣ ቡና ሲፈላ፣ በታክሲ እና በአውቶቡስ ሲኬድ ታድያ ምን ይወራ? ሁሉም ነገር ፖለቲካ በሆነበት ጊዜ ታድያ ምን እናውራ፡፡ ጤፍ ተወደደ ፖለቲካ ነው፣ጤፍ ረከሰም ፖለቲካ ነው፡፡ ሀገራችን አደገች ማለት ፖለቲካ ነው፣ ሀገራችን ወደ ኋላ ቀረች ማለትም ፖለቲካ ነው፡፡ እገሌ ተሳስቷል ማለት ፖለቲካ ነው፣ልክ ነው ብሎ መናገርም ፖለቲካ ነው፡፡ ታድያ ምን እንበል?

ምን እባል ይሆን? ማን ሰምቶኝ ይሆን? ተብሎ በሚወራበት በዚህ ጊዜ እንደ ልብ የሚወራ ነገር ማግኘት ቀላል ይመቻል እንዴ! እኛ ተመልካቾች በሂደት አንድ የጥናት ውጤት አግኝተናል፡፡ ቢያንስ ስለ አውሮፓ እግር ኳስ ስታወራ የትኛውም የፓርቲ አባል እንደማይቆጣ፡፡ አውሮፓውያን ኢትዮጵያውያን ቢሆኑ ኖሮኮ በስፔን ቡድን ላይ ትችት ስትሰነዝር የስፔን ኤምባሲ፣ በእንግሊዝ ቡድን ላይ ስትወርድበት የእንግሊዝ ኤምባሲ፣ የጣልያንን ቡድን ስታነሣ ጣልያን ኤምባሲ አያስቀምጡንም ነበር፡፡ አቦ እንኳን ኢትዮጵያውያን አልሆናችሁ፤ ተመችታችሁናል፡፡

24 comments:

 1. God may forgive us.

  ReplyDelete
 2. Dani, tesufehe yemachal
  Yemeche abo
  negere gene Artist Getenet Eenyewe
  "Abo tewuna"be milewe getemu endegeletsewe
  weryachen hulu ye Europe kuse becha endayhone entenkeke
  Azeb ZeMinneseta

  ReplyDelete
 3. Alitemechegnm,

  Michot kemefeleg perspective bicha new yayehewu. Chigirn megafet yasfeligal eko. Wotatu negerochi alitemechugnim bilo erasin bemayireba neger meshewod yalebet ayimeslegnm. Belela agelalets, poletikawu tebelashe, netsanet tefa, federationu aladegem bicha batekalay ethiopia yalew neger alitemechenim. silezih be awuropa football ena bechat erasachinin endebik malet yekefa yeastesaseb ziktet new. who is responsible to get things done? if we are not happy with the situation lets face it courageously to achieve what we want. Leshinfet minim ayinet mikniyat ayiseram.

  yezewotir anibabih

  ReplyDelete
 4. አያልቅበት ዳኒ በጣም የሚገርመው ይህን ያህል ትክታተላለህ እንዴ ኳስ
  ዘ ይገርም

  ReplyDelete
 5. yewah techi "altemechegnim" bilo yitsifal. Ahaha yih tsihuf wusite weyira new. Yemenager netsanet min yahil endeterabin new eyetegeletse yalew. Berta Dn.Dani

  ReplyDelete
 6. Thanks Dani! Your article remind me Artist Getnet Eneyew's poem. I am sharing the online video for your readers.

  http://www.ethiotube.net/video/8006/MUST-WATCH-Artist-Getnet-Enyew-reading-his-poem--YeHabesha-Lijoch

  ReplyDelete
 7. አቦ አስተያየትህ ይመቻል. የሚመለከተው ሁሉ ልብ ይበል.

  የዘወትር የፅሁፎችህ ተከታታይ ሒሩት
  ከአቦ አገር ድ.ዳ.

  ReplyDelete
 8. በስመ ሥላሴ
  ውይ ዳኒ
  የምሬን ልንገርህ
  አያምርብህም፡፡
  ርእሱ ጥሩ ነበር ግን አጻጻፉ የአንተ አይመስልም ማለትም አይመጥንህም፡፡ይህንንም ያልኩበት ምክንያት ከመንፈሳዊ አካሔድ የወጣ ነው ብዬ አይደለም ግን እስኪ በእውነት የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያወራው አጣ ? በየቀኑ የሚከፈቱት ካፌዎች ለምን ይጨናነቃሉ? እንደኔ እንደኔ ከስራ ይልቅ ብዙ ስለምናወራ ይመስለኛል ፡፡
  ለማንኛውም ከመተቸት ይልቅ ማበረታታትም ቢካተትበት ጥሩ ነበር፡፡

  ReplyDelete
 9. Yihe tsihuf anten ayimetinim. the detail has some fallacy and misleading ideas.

  Getnet eniyew betiru huneta askemitotal. Ethiopia wust kuas issue erasu mehon alineberebetim, sint yemiyaschenik ereft yeminesa neger alen. Ena sile europe kuas mawuratachinin bemikiniyat medegef sihtet yimeslegnal. I understand people's hobby though, I'm not saying don't watch soccer but it's toooooo much. we made it like our work....

  ReplyDelete
 10. Ene yemilew gin yemenager mebit be hagerachin silele sayihon chifin degafi weyim chifin tekawami silehone be politica zuriya be ager wust yihun even wuch ager(mebit ale gin hulet yeteleyayu politica yemidegifu abro sile poitica ayawerum) menegager mweyayet kebad new. minalibat tiru(Liki) yehonewun eyedegefin metifo(Liki yalihonewun) eyetekawemin beteley metifo yehonewun endet mefta enichilalen eyalin biniweyay ye politica amelekaket yikeyer neber. Be ahunu gize liki Dani endalew sile kase weyim sile lela(Film) mawirat yikela ke abesha ga be politica kemawurat mikiniyatum ye liyunet mensie eyehone silemeta. Ene advice yemadergew eski behayimanotachin zuriya (Limisale Kiristina endet eninorowalen(How we can apply christiyanity in practice ete...)) biniweyay ke abesha ga sinigenagn tiru yihone hule sile egir kase ena film bich keminawera.

  ReplyDelete
 11. Dear Daniel,
  This was another great observation .I'm not a "soccer person" and I am not sure if I share the same feeling as the character here but I like the insight. Most of all I like your way of writing, it is different from before and keeps the blogs from being monotonous and makes them INTERESTING!! Keep it up, I hope to see all of your blogs as a book in the near future!!

  Stay Blessed!!

  ReplyDelete
 12. +++

  በስመ ሥላሴ ትቀጠቅጥ ከይሴ
  ለማዉቅህ ዳ/ን ዳንኤል

  ርእሱን ይዠ ስጓዝ ስጓዝ ለርዕሱ የሚሆን አላገኝሁበትም::

  ከዝዋይ

  ReplyDelete
 13. አቦ ይመችህ ምን አይነት ጆከር የሆንክ ሰው ነህ እባክህ? ማለት ስለፈለከው ነገር በትክክል መግለጽ ትችላለህ ትልቅ ፀጋ ነው በተለይ ለሶከር ልዩ ፍቅር ስላለኝ አገላለጽህ ተመችቶኛል ቀጥልበት በዓለም ላይ እስከኖርን ድረስ በአለም ውስጥ ስላሉት ነገሮች ሁሉ በቂ እውቀት ቢኖረን ኃጢአት ነው ብየ አላምንም

  ReplyDelete
 14. I appreciate that you try to make your blog interesting and not focus on serious issues only. But, I disagree with your evaluation. I think most people in Ethiopia have gone mad over Futbol. It is not healthy to spend this much energy and time the game. Yes, we don't have a lot of freedom to free discuss other more pressing topics, but we should not just give up and escape to futbol. That will just be submitting to the powers who deny us the freedom to freely express our views.
  If we all decide to give up on the "Politics" and seek refuge in futbol, how do hope to solve the endless problems we face. How are we going to create an Ethiopia where our children can taste true freedom. I say should run from our problems but instead face them.
  D. Daniel, I think this article contradicts your many previous teachings. I have heard you condemn the youth for being lazy, for not fighting to better himself/herself and his country. Instead you condone this out of control craziness about futbol.

  ReplyDelete
 15. If we know God loves us unconditionally first not our love for him but his love for us, our interest and our appetite for sins will be changed and we will be a doer of God's word.
  (1 John. 4:10)
  for further contact mesfinmelesse1@yahoo.com

  ReplyDelete
 16. dear all watch this video!
  it has similar issue with this post

  http://www.youtube.com/watch?v=GA6lpqbGUao&feature=related

  ReplyDelete
 17. mesfin melesse God bless you! i don't think all orthodox believers know unconditional love and conditional love!

  ReplyDelete
 18. Very True.
  Good Observation!

  ReplyDelete
 19. ye igzi'abher selam le ante yhun
  dani abo betam argo yimechih betam arif akerareb new be bizu neger lay yalehn knowledge new miyasayew be hulum negher lay yemitisetew asteyayet ye agerachin guday be hulum menged indemiyaschenkih new yeteredahut krtilbet.
  andanid gize ye menfesawinet astesaseb chigir yalebachew sewoch deacon silehonik bicha ke haymanot wichi lela neger mawrat indelelelebh liyasbu yichilalu bihonm ketilbet hatiyat iskalhone dires indih aynet astesaseb yalew sew ye manibeb chigr yalebet sew silehone ilefew ine gin temechitognal.
  igzi'abher yibarkh
  ke ayin yawtah

  ReplyDelete
 20. አሪፍ ዉስጠ ወይራ ጽሁፍ ናት:: አስተያየቶቻችን ግን እንዴት እንደምናስብ ያሳያሉ:: ላንተም ትልቅ feedback ይመስለኛል:: ስንቱ ማለት የፈለከዉን እንደሚረዳህ ያሳይሃል:: እርሱ የኢትዮጵያ አምላክ ይርዳህ::

  ReplyDelete
 21. Wogen yihe neger sile kuwas endayimeselen!

  Kuwasu semu newu. Worku gin yewetatun chigir yemizekir newu.

  Abet "What an expression" yihe bekuwas yetewosede wetat meche yihone wedelelaw gudayu yemimelesew?
  Amilak hoy Aseben!amen!

  ReplyDelete
 22. thank u for telling z truth 4 z stake holders.if they r able to answer ur questions we can be competitive in football & z football lover returnes to z domestic league.egziabher ysetelen.
  zekaryas

  ReplyDelete
 23. Dear Daniel,

  Thanks for your concern of the church!

  As I was always asking you when I was your student in grade 11 and 12, I am also now asking you about the issue u raised.

  1. In the context of Ethiopia, is it possible to separate the church from the government, practically?

  2. Why do you think the government is interested in the church afairs and in the church itself?

  3. Do you think there is a change in the socio political reality of Ethiopia, evluating the reality in light of the Ethiopians long history of politics and church relation? do you expect any attitudinal change in the near future?

  4. Have you thought over the depth of the issue in light of power politics analysis?

  With Respectedly,

  Your Student

  ReplyDelete