Thursday, August 19, 2010

ከንፈራችንን መጠን ብቻ እንዳንተወው

ከአቤል ቀዳማዊ

የቤተ ክህነቱ ችግር እስከነ መፍትሄው መስታወት ሆነህ አሳይተኽናል። አልታደልንምና ብዙውን ግዜ ቤተ ክርስቲያናችን ያለችበት ነባራዊ ሁኔታ ሲነገር ሚስጥራችን በአደባባይ ወጣ የሚል ተቃውሞ ከብዙዎች ይሰማል። ተቃዋሚዎቹ የራሳቸው የሆነ ምክንያት ሊኖራቸው ይችላል፤ አንድም ጥቅመኞች ጥቅማቸው እንዳይነካ በሌላም እውነተኛ ተቆርቋሪዎች በግንዛቤ እጥረት።


እንግዲህ በዚህ ከሁለት ዓመት ወዲህ በአንተው አገላለጽ የቤተ ክህነቱ ችግር “ እንደ ዖዝያን ለምጽ ሊሸፈንበት ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል” ብለሀል። በዚም ምክንያት ያገባኛል የሚሉ አካላትም መነጋገር ጀምረዋል። ይህ አሁን ለእይታ ያበቃኸው የቤተ ክህነቱ ችግር እስከነ መፍትሔው እንደ “ደራሽ ውሃ” ሐውልቱ ሲቆም አይመስለኝም። ብዙ ዓመታት ያጠናኸው ጥናት መሆኑን በሚገባ ያስታውቃል።

አሁንም ፍራቻዬ ይህ ሀሳብ ከንፈራችንን መጠን ብቻ እንዳተወው እሰጋለሁ። ብዙውን ግዜ አብዛኛውን የእኛ ማሕበረሰብ ማለትም ኢትዮጵያውያን ችግሮቻችን ትዝ የሚሉን ዘማሪው ሲያዜመው፣ ሰባኪው ሲሰብከው፣ ገጣሚው ሲገጥመው፣ ዘፋኙ ሲዘፍነው እና ጸሐፊው ሲጽፈው ብቻ ነው። በዘማሪያን፣ በገጣሚያን፣ በሰባኪያን እና በደራሲያን ችግሮቻችን ሰምተን ከንፈራችን በመምጠ ከማዘን ውጪ ችግሮቻችን በዘለቄታው እንዲፈቱ የራስ ጥረት አናደርግም።

አሁንም አንተ ያቀረብካቸው የመፍትሄ ሀሳቦች በአጠቃላይ ለባለ ድርሻው በቀጥታ እንዲደርስ ምን እናድርግ? እዚህ ላይ ባለ ድርሻ ያልኳቸው በጠቅላላ የተዋሕዶ እምነት ተካታዮች ናቸው። ይህ የአንተ ብሎግ ምን አልባት በአሥር ሺህ የሚቆጠሩ የእምነቱ ተከታዮች ያዩት ይሆናል ብዬ እገምታለሁ፤በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩት የእምነቱ ተካታዮች ግን ብሎጉን የማየት እድል አያገኙም። ሥለዚህ እንዴት ይህ ሀሳብ ለሚሊዮኖቹ ባለ ድሻዎች ይድረስ?

፩. በቀጥታ ሕዝባዊ ስልጠናዎች ማዘጋጀት ሥልጠናው ማን ያዘጋጀው? ቢባል፤ በሀገራችን ውስጥ እና ከሀገራችንም ውጪ ብዙ ለቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪ ማኅበራት አሉ። እነዚህ ማኅበራት ጉባኤያት እና ሕዝባዊ ስልጠናዎች የመስጠት አቅም አላቸው። አንተ በስም የጠቀስካቸው ማኅበራት እያንዳንዳቸው የሥራ አስፈጻሚ አካላት እንዳላቸው እርግጥ ነው። በመሆኑም ይህ የቀረበው የመፍትሄ ሃሳብ በሥም ለጠቀስካቸው እና ለሌሎቹም በሥም ላልተጠቀሱትም ማኅበራት የሥራ አስፈጻሚ እና ለሥራ አመራር አካላት እንዲደርሳቸው ቢደረግ ።

ለእነዚህ የሥራ አስፈጻሚ አካላት ሀሳቡስ “ማን ያቅርበው”? እኔ እንደሚመስለኝ ከእያንዳንዱ ማኅበራት የሥራ አስፈጻሚ አካላት ውስጥ ቢያንስ አንድ ሰው ይሄንን ጽሑፍ ያየዋል ብዬ እገምታለሁ፤ አንብቦም እንደ ማንኛውም የችግሩ ተካፍይ “ምን ላድርግ”? ብሎ ራሱን እንደሚጠይቅ እርግጠኛ ነኝ። ታድያ ይህ ጽሑፍ ያየ እና የሰማ ለቤተ ክርስቲያን ህልውና ቆሜያለሁ የሚል የትኛውም ማኅበር የሥራ አስፈጻሚ አካል ከሌሎቻችን በተለየ ሁኔታ የበለጠ ኃላፊነት ይኖርበታል ብዬም አምናለሁ። ኃላፊነቱም ለሌሎቹ ላልሰሙና ላላዩ የማኅበሩ አባላት እና የእምነቱ ተከታዮች የሚደርስበት ሁኔታ ማመቻቸት ነው።

ሥለዚህ ይህ በዚህ በእኛ ዘመን በይፋ ለውይይት እየቀረበ ያለው የቤተ ክርስቲያኒቱ ነቀርሳ ያልዘመነ አስተዳደር በዘለቄታው እንዲቀረፍ ወንድማችን ያነሳቸው የመፍትሄ ሀሳቦች የማኅበራት የሥራ አስፈጻሚ አካላት እና የሥራ አመራር ተወያይተውበት የማወያየት ግዴታ አለባቸው ብዬ አምናለሁ።

፪. ሰንበት ት/ቤቶች እንደ አንድ ሥራ በእቅድ ቢይዙት። ይህንን አንተ ያቀረብክልን የመፍትሄ ሃሳብ ያነበቡ የሰንበት ት/ቤት አባላት በይበልጥ ደግሞ የሰንበት ት/ቤት አመራር አካላት በእቅድ ተይዞ በየ አጥቢያቸው ተወያይተውበት ለሌሎችም የሚዳረስበት ሁኔታ ቢያመቻቹ ለምሳሌ ጽሑፉ አባዝተው በየ አጥቢያቸው ቢያሰራጩ።

፫. የሰማ ቢያሰማ ያነበበም ቢያስነብብ ይህ የአንተ ብሎግ የሚያነብ ሰው ብዛት ፳ ሺህ ቢሆን እያንዳንዱ ሰው ለአንደ ጽሑፉ ላልደረሰው ሰው እንኳ ቢያስነብብ የአንባቢው ቁጥር ወደ ፵ ሺህ ያሳድገዋል። ስለዚህ እያንዳንዱ ይህ የመፍትሄ ሃሳብ ያነበበ ቢያንሰ ይህ ጽሁፍ ላልደረሰው ለአንድ ሰው የማስነበብ ኅላፊነት ቢወስድ። ሌላው ደግሞ በየ አለንበት ቦታ ሆነን አንድም፣ ሁለትም፣ ሶስትም ሆነን በዚህ በቀረብው የመፍሄ ሃሳብ ላይ ውይይት ብንጀምር እና ለተፈጻሚነቱም የግል ጥረት እናድርግ ብዬ አምናለሁ። እግዚአብሔር ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ይጠብቅልን!!! አሜን

3 comments:

 1. danie egziehaber edmena berktun yete yene hasabe yetsfkachw mefte ulu bemtsafe tsfe lenbabeb bebqana leye ateebya betekrstyan ena weche lalutem biserach yeblte teqmeta yenorwal beye asebalwe

  getu ke germany

  ReplyDelete
 2. My brother that is very good idea if it is possibly .We work hardly
  This is Aynalem

  ReplyDelete
 3. ቀኑ ዛሬ እንጂ ነገ አይደለም
  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን
  ሰላም ለናንተ
  ከደብረ ቁስቋም
  ወንድማችን ዲ.ዳንኤል ይህን ብሎግ ከፍቶ የቤተ ክህነቱን ችግር ከነ መፍትሔው አቅርቦልናል እኛም በውስጣችን የታመቀውን ነገር እዚህ ላይ በማቅረብ ተንፈስ ብለናል::አዎ ችግሩ እንዳለ በግልጽ ይታወቃል ደግሞም ችግሩ በአንድና በሁለት ቦታ ላይ ብቻ ወይም በሀገር ቤት በቻ አይደለም ያለው ችግሩ በመላው አለም ቤተ ክርስትያን ባለችበት ቦታ ሁሉ አለ::እናም በብዙዎቻችን ዘንድ መጀመርያ እኛ የመፍትሔ አ ቅራቢዎች መግባባት አለብን የሚል መለክት አዘል ሀሰብ ቀርቡዋል:: ልክ ነው እኛ ሳንስማማ አንድ እርምጃ መራመድ አንችልም {ለዚህም ነው በቤተ ክርስትያን ችግር የተፈጠሬው} ነገር ግን እኛ የምንስማማው ጽሁፍ ጽፎ በመለጠፍ በቻ መሆን የለበትም ጽሁፉን ፕሪንት አድርገን ላልሰማው የቤተ ክርስትየንዋ ልጆች በማዳረስ ና ተሰባስቦ በመነጋገር ነው መፍትሔ ሊመጥኣ የሚችለው ሌላው እኛ እዚህ ብሎግ ላይ ያለንው ሰዎች ለምሳሌ ከአሜሪካ 60 ሰው ከካናዳ 40 ሰው ከኢትዮ 30 ሰው ወዘተ እዚህ ላይ ልንኖር እንችላለን ታድያ ለምን በመጀመሪያ እኛ አንገናኝም እና አንነጋገርም ከዛም መመናንን መሰብሰብ እንችላለን ለምሳሌ በአቡዳቤና አካባቢው ለምንገኝ በዚህ email ብንገናኝ zarenewe@yahoo.com የሚል ኢሜል ለዚሁ ስል የከፈትኩት ነው እናም እንገናኝና መነጋገር እንችላለን::
  እግዚአብሔር ሀገራችንን ና ቤተክርስትያናችንን ይጤብቅ አሜን

  ReplyDelete