Wednesday, August 18, 2010

እናንተም አትራቁን ቅረቡን

አባተ ከአዲስ አበባ

ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት

አንዳንድ የብሎጉ አንባብያን በሰጡት ሃሳብ መሠረት ጽሑፎቹን ፕሪንት አድርጌ ለአምስት ብጹአን አባቶች አንብቤላቸው ነበር፡፡ በጣም ነው የተደሰቱት፡፡ በተለይ አንደኛው አባት «ልጆቻችን እንዲህ ማሰብ ከጀመሩ የመፍትሔው ቀን ቀርቧል ማለት ነው» አሉ፡፡

እኔ እንዳየሁት ሁሉም ልብ ውስጥ ቁጭት ይታያል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ችግር ላይ መሆንዋን አምስቱም ሲናገሩ ነበር፡፡ አንደኛው አባትም «እስኪ መንገዱን አሳዩን፣ ምናልባትኮ ለኛ ያልታየን ለልጆች ይታያቸው ይሆናል፡፡ ከሌሎች አባቶች ጋር ሆነን እናነሣዋለን» ብለዋል፡፡

ይበልጥ ያነሡት ነገር ደግሞ ታትሞ ለቤተ ክህነት ሰዎች እና ለሌሎች አባቶች ለመን ግሥትም አካላት ቢደርስ ብለዋል፡፡ በየሄድንበት የምእመናኑ ዓይን ይጋረዳፍ፤ ጥያቄ ይጠይቁናል፤ መልሱን ግን አብረን ነው መፈለግ ያለብን፡፡ ብለዋል፡፡

«እናንተም አትራቁን ቅረቡን፣በግላችንም ቢሆን አወያዩን፤ ፈተናው የሁላችንም ነውና ተረዳድተን የሚቻለውን እናድርግ፡፡ ጳጳስ የሆንነውኮ ይህች ቤተ ክርስቲያን በመኖርዋ ነው፤ የተከበርነው በዚህች ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ዐቅም ጠፍቶ እንጂ ማን ክፉዋን ይመኛል» ብለዋል፡፡

ለሌሎች አባቶችም እንዳነብላቸው ነግረውኛል፡፡ ዕድሉን ካገኘሁ ያሉኝን እነግርሃለሁ፡፡

8 comments:

 1. Good job dear Abate,

  I think it is a good example of an action to be taken by each one of us.For all of us I have one thing to say. We can do the same thing at all levels, they should not necessarily be Bishops. We can start from our family, friends, neighbors, colleagues, sunday schools, mahberats, our soul fathers, church adminstrators, sebeka gubae members, to fathers whom we have some relation. For me the fastest way to disseminate this information is to forward it to the youth in big cities. It is a short memory what they did during the Timqet celebration. Once we can reach them it is gonna be easy to disseminate the information and create awareness.

  May God keep our church safe

  ReplyDelete
 2. የሰ/ት/ቤት ተማሪዎች እያደረጉት ያለው ሊበረታታ ይገባል መልካም ጅምር ነው በአንዳንድ አካባቢ በተለያዩ አጋጣሚ ሲያነቡትና ሲዎያዩበት አየሁ ስለዚህ አሁን ሁኖ ያገኘሁት ጉዳዩ የሁሉም (የሁላችንም )መሆኑን በቀላሉ መረዳታቸውን ነው ስለዚህ መልካም ፍሬ እንደሚያፈራ ከዎድሁ ያስታውቃል ለማንኛውም ይህንን ጅምር ሌሎቸ ማህበራት ሰ/ት/ቤቶች ቢጠቀሙበት መልካም ነው !!

  ReplyDelete
 3. እሌኒ ከሲራክዩስAugust 18, 2010 at 11:50 PM

  + + +

  መፍትሔ ለማምጣት ከራስ መጀመር ይሉሀል እንዲህ ነው!!! በርታ ወንድማችን! ትልቅ ስራ እየሰራክ ነው:: መልሳቸው ተስፋ ሰጪ ነው: ምንአልባትም እኮ እነሱም ውስጥ ብዙ መፍትሔ ኖሮ ነገር ግን እርስ በእርስ እየተፈራሩ ይሆናል::

  አምላክ ብርታቱን ይስጥህ!
  ግርማ ሞገስ ሆኖ አንደበትህን ያከናውንልህ!

  ReplyDelete
 4. Dear Abate,

  Good job! You contributed what is expected from each of us.Keep it up.

  ReplyDelete
 5. Teru New EGZIABHER Yerdeae, Yerdean, EGZIABHER Ante Leay Adreo Begeo Ngren Yasayen

  EGZIABHER Beuleum Fiet Chmreo Germa Mogsen Yeste

  Dakon Daneil
  Egeam Yemitbkbnen Kemdrge Wedewala Lenel aygbeam
  EGZIABHER Yerdean Amen!

  ReplyDelete
 6. በጣም ጥሩ ጅምር ነው አባተ። እኔ በውጭ ሀገር ስለምኖር አንተ እንዳደረከው ባልችልም የብጹአን አባቶችን የፋክስ አድራሻ ብትለጥፉልን መልካም ፁሑፎችን ለአባቶች ፋክስ ማድረግ እንችላለን።

  እግዚአብሔር ያበርታን
  አክሊል ነኝ

  ReplyDelete
 7. +++
  ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን::

  ከዚህ ብሎግ ከሚለጠፈዉ በተጨማሪ መፍትሔ ለማምጣት ማህበራት: ሰንበቴ ማህበራት: የሰ/ት/ቤት: አጥቢያ ምዕመናን ና የጉዞ ማህበራት በአሃገርም ከሃገር ዉጪ ያሉትም በቤ/ያን ወቅታዊ ችግር ቢወያዩበት እና ተወካይ ቢመርጡ እና በችግሩ ዙሪያ ተወያይተዉ አቋም ቢይዙ ከእግዚአብሔር ጋር ችግራችን መፍትሄ ያገኛል የሚል ግምት አለኝ::

  አባት ብለን ልንጠራቸዉ የምንችለዉ አባቶች ቁጥራቸዉ እኮ ትንሽ ነዉ:: አቅማቸዉም ተመናምኗል::
  በገዳም ላሉ አባቶ በጸሎት እንዲተጉ መልክቱ እንዲደርሳቸዉ ቢደረግ ጥሩ ነዉ:: ሌላው የ20ኛ ዘመን የቤተክርስቲያን ችግር በሚል ዕርስ በመጽሐፍ መልክ ቀርቦ ለምዕመናን ቢደርስ: በPDF ቢለቀቅ ብዙ ሰዉ ያነበዋል ዉጤት ይኖረዋል የሚል ግምት አለኝ::

  ጌታ ሆይ የቤተክርስቲያንን ጥፋት አታሳየኝ::

  ReplyDelete
 8. እግዚአብሔር አነዲትን ሀገር ያለ ጠባቂ እይተዉም አይዟችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ በረቱ። አባተ አርያነት ያለው ስራ ነው የሰራህው ። እኔም የበኩሌን በመጠኑ ጀምሬያለሁ። በነገራችን ላይ አብዛኛው ክርስቲያን የለውጡን ሂደት በእጅጉ ይሻላልና ይሳካልናል። ዲ/ን በርታ ድርሻህን ተስፋ ሳትቆርት እነአደተለመደው ለመዎጣን ሞክር

  ReplyDelete