Monday, August 16, 2010

«ጨለማን ዘወትር ከመውቀስ ቁራጭ ሻማ መለኮስ »

በዲን. ዮሐንስ መኮንን

ለውድ የዲያቆን ዳንኤል ብሎግ ታዳሚዎች

እንኳን ለጦመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ ሱባኤው የግል እና የቤተክርስቲያናችን ችግሮቻችንን መፍቻ ያድርግልን፡፡

ወንድማችን ዲ.ን ዳንኤል ብዙዎቻችን ፈራ ተባ ስንልበት የነበረውን የቤተ ክህነቱን ጉዳይ ለአደባባይ አብቅቶታል፡፡ ምንም እንኳን ሰው ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ቢሆንም!! ለውይይት ክፍት ለማድረግ ቀዳሚውን ሰማዕትነት (ምስክርነት) ከመውሰዱም ሌላ በበኩሉ የታዩትን የመፍትሔ ሀሳቦች ሰንዝሯል፡፡

 ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በርካታ ኦርቶዶክሳውያን ወጣት ምሁራን የመጀመሪያ የሁለተኛና የሶስተኛ ዲገሪ ማሟያ ጥናታቸውን በቤተ ክርሰቲያን ዙርያ ማድረግ እየተለመደ መጥቷል፡፡ አንድ ወዳጄ ታዲያ ጥናቱን በቤተ ክርስቲኒቱ ዙሪያ ማድረግ ፈልጎ የመነሻ ችግር (statement of the problem) ማግኘት ይቸገረው እና ፕሮፌሰሩ ዘንድ በመሄድ የገጠመውን ችግር ይነገራቸዋል፡፡ መምህሩም «እንዴት የመነሻ ችግር ታጣለህ? ቤተክስቲያን ማለት በራሱ ችግር አይደለም ወይ?» በማለት መልሰውለታል፡፡ አሁን አሁን ከችግሮቹ ብዛት፣ ስፋት እና ጥልቀት የተነሳ «ቤተ ክህነት» ማለት «ችግር» የማለት ያህል ሆኗል፡፡

• በዲ.ን ዳንኤል ሐሳቦች ላይ ተጨማሪ አስተያየቶች

ወንድማችን ዲ.ን ዳንኤል ባቀረበው የቤተክህነቱ ችግሮች ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ፡፡ ነገር ግን በእኔ አተያይ ችግሮቹን እንጂ ጥልቀታቸውን (magnitude of the problem) አላሳየንም፡፡

የቀረቡት ችግሮች ጥቅል በመሆናቸው ግለሰባዊና ተቋማዊ ጉዳዮችን መለየት አላስቻለንም

ዳንኤል ያቀረባቸው አብዛኞቹ የመፍትሔ ሃሳቦችም የወል በመሆናቸው እኔ ባይ ተጠያቂ ባለቤት እንዳይኖራቸው ያደርጋል፡፡

የመፍትሔ ሃሳቦቹም ዝርዝር የአፈጻጸም መርሐግብር ሊዘጋጅላቸው በሚችል መልኩ መሰናዳት ይኖርባቸዋል፡፡

በግል የታዩኝ የመፍትሔ ሃሳቦች

• ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ከወሰንን ፤

• ከሃገር ውስጥ እና ከሃገር ውጭ ከሚገኙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ምሁራን፣ ምእመናን የተውጣጣ የችግሮቹን ዓይነታቸውን እና ጥልቀታቸውን (magnitude of the problem) የሚጠና እና የመፍትሔ ሃሳቦችን የሚያሰባስብ ጉባኤ (council ) ብናቋቁም፡፡ ጉባኤውም ቤጊዜው የደረሰበትን ለምእመናን የሚያሳውቅበት መንገድ መቀየስ፡፡

• ሙሉ ጊዜያቸውን ለዚሁ ሥራ ማዋል፣ ማስተባበር እና መምራት የሚችሉ የሰው ኃይል እና ቁሳቁስን ማደራጀት፡፡

• ችግሮቹን በቅደም ተከተል መፍታት የሚያስችለን የአገልግሎት መዋጮ (levis fund) የሚሰበሰብበትን እና በአግባቡ ገንዘቡን የታለመለት ጉዳይ ላይ ብቻ ወጪ መደረጉን የምንቆጣጠርበትን መንገድ መቀየስ፡፡

• የአጭር ጊዜና የረጅም ጊዜ ዕቅዶችን በመለየት የሚያስፈልገንን የሰው እና የቁሳቁስ ልክ ብናዘጋጅ

• ዕቅዶችን የመፈፀሚያ ዝርዝር ቅደም ተከተል እና የሥራ ክፍፍል (manual ) ማዘጋጀት

ይህንን ማድረግ ካልቻልን ችግሩን ከመተረክ አልፎ የተጨበጠ ሥራ ሳንሠራ እንቀራለን፡፡ 

                                                                         «ጨለማን ዘወትር ከመውቀስ ቁራጭ ሻማ መለኮስ »

ከአዘጋጁ
ሌሎች አንባብያንም አስተያየቶቻችሁን እና የመፍትሔ ሃሳቦቻችሁን ሠንዝሩ፡፡ እየበሉ እየጠጡ ዝም .......


8 comments:

 1. Whatever solutions come-up with any entity,"Betekehenet" must be accept it to be effective. Dn.Yohannes ideas work only if there is willingness in part of "Betekehenate" to accept solutions presented by external volunteer groups. I don't think it's the case. I think it's more helpful to assist technically and financially a section on " Betekehenet" structures oversee such issue.I hope Betekehenate may listen there own section suggestions.

  ReplyDelete
 2. selam lenanet yehun.ene endemigebagne chegeru yemijemerew kegnawu ke memenane newu esum.
  qoreto alemenesate maletem ande neger lemeserat senenesa mewesen aleben kalebeleziya beteneshum betelequm eneqotalen kezam hulun neger wedmetew enehedalan selezih qoreto menesat aleben.lelaw wendemachen yalekew teru new egziabeher lehulachenem selamun yesten d.d tebarek enamesegnalen.mesin ke abu dha

  ReplyDelete
 3. In the name of Trinity One God amen
  I agree with Dn. Yohannes and Dn. Daniel Solutions. There is always something that every one can contribute in the problem. In my opinion this is the right time to enlighten every one with rich information to address the things that he/she can do to reduce the problem.

  I believe money is power. It can influence either negatively or positively. With in the past few years there has been some tradition adopted and now taken as norm of the church which has opened the door for corruption. Church songs, spiritual books and preachings have been published and released with private sectors(independent groups). The people (miemenan)are not well informed if the books and CDs they buy are indeed published under the church. This has helped the cheaters to make money under the name of God. Cheaters have now got enough wealth and they are now working for other self-interests including business under the church name. They are certain they can manipulate the people to which ever purpose they want.

  With our money we have created rich "preachers" ( I would rather say...motivators) who do not care to the people and the church. And I think we can make a difference here. Lets start this from our home...create awareness to every of our family members not to buy books and Cds which are published and released with out a recognized authority assigned by the church. This is something that every one of us can influence to cleanse the problem.

  Together we can make a difference!

  Yakoyen!

  ReplyDelete
 4. ሲሎንዲስ ዘአውሮፓAugust 17, 2010 at 1:04 AM

  This comment has been removed by a blog administrator.

  ReplyDelete
 5. ዘ ሐመረ ኖህAugust 17, 2010 at 1:42 AM

  ሰላም ለሁላችሁ ይሁን አሜን የዲን ዮሐንስ መኮንን ሃሳብ እንዳለ ሆኖ ወደ ተግባር ከመግባታችን በፊት እንደተባለው የመፍትሄ ሀሳብ ከመፈለግ ጀምሮ አቅጣጫ በመጠቆም በቅድሚያ በሃገር ቤትም በውጭም የሚገኘው ሕዝብ ከአንድ ምእመን እስከ ብፁአን አባቶች ለመዘምራን ለሰባኪያን ለዲያቆናት ለካሕናት ለተለያዩ መንፈሳዊ ማህበራት ወዘተ የዚህ ብሎግ ዓላማና ግብ ኢንተርኔት ለማይጠቀመው ወገን ሁሉ እንዲደርሰው ማድረግ የዚህ ብሎግ የታዳሚ ቁጥር ቀላል ባይሆንም ይህንን ብሎግ የማያገኘው ሕዝብ ቁጥር እንደሚበዛ መገመት አያስቸግርም ስለዚህ ዓላማው በቅድሚያ ለመላው የተዋህዶ ልጆች በልዩ ልዩ የብዙሀን መገናኛ ዘዴዎች ለምሳሌ በግል ጋዜጣ ወይም እያንዳንዱ ሰው ፎቶ ኮፒ እያደረገ በተገኘው መንገድ ሁሉ በማዳረስ ወይም የውጭ ሀገር የነጻ አስተያየት መስጫ ሬዲዮኖችን በመጠቀም የመፍትሄ ሀሳብ ከሁሉም እንዲመጣ ማድረግ ኢንተርኔት ለማይጠቀመው ሰው ሀሳቡን የሚገልጽበትን መንገድ እንደ የፖስታ ሳጥን አድራሻ አዘጋጅቶ መሰብሰበ ያንን ጨምቆ የበሰለውን ነገር በመያዝ እግዚአብሔርን በዖምና በፀሎት ጠይቆ ወደ ተግባር መግባት ወደ ተግባር ስንገባም እንደኔ ሀሳብ በውጭም በሃገር ቤትም ያለውን ሕዝብ በክፍለ ሃገርና በዞን ማዋቀር የየክፈለሃገሩ ወይም የየዙኑ ተወካይ መመረጥ እነዚህ ተወካዮች አንድ ጠንካራና ይህን ዓላማ የሚያስፈጽም ኮሚቴ ማቋቋም በተቻለ አቅም ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው አሰራር ለመስራት በገንዘብም ሆነ ለዓላማው ታማኝ በሆኑና በደንብ በሚታወቁ ሰዎች ለመስራት መጣር ለዚህ ስራ የሚያስፈልገውን ገንዘብ መዋጮ የየዞኑ ተወካዮች አሰባስበው ለዚህ ጉዳይ ብቻ በሚከፈት አካውንት ማስገባትና የተቋቋመው ኮሚቴ ብቻ የሚያዝበት ማእከላዊ አሰራር መዘርጋት ችግሩ ጊዜ የማይሰጥ ደረጃ ላይ ስለደረሰ ይህንን በተቻለ ፍጥነት ነገር ግን በጥንቃቄ ብናደርግ ምክንያቱም በሃገር ቤትም በውጭም በቤተከሀነት ችግር ተጠቃሚዎች ስላሉ ዓላማውን እንዳያከሽፉ ወይም አቅጣጫውን እንዳያስቀይሩ መጠንቀቅ በዚህ ላይ መናፍቃኑና እስማኤላውያኑ መሀከላችን መኖራቸውን ለሰከንድ እንኳን መዘንጋት የለብንም እስከዛሬ ላለው ዲን ዳኒ ብቻውን እየደከመ ስለሆነ በሰው ኃይልም በገንዘብም የምንረዳበት መንገድ እንፈልግ አይዞአችሁ በእግዚአብሔር ኃይል ለውጥ እናመጣለን ቸር ይግጠመን

  ReplyDelete
 6. Samuel ZeAsebot said...

  ለዲያቆን፡ዮሃንስ፡መኮንን፤

  አርዕስተ-ውይይታችን፡ገና፡የጀመረ፡በመሆኑ፡መቀጠል፡
  አለበት።የችግራችን፡ሁሉ፡መፍትሔ፡በመዋቅርና፡በገን
  ዘብ፡ብቻ፡ሊፈታ፡የሚችል፡አይመስልም።

  ጮሌዎች፡መዋቅሩንም፡ብሩንም፡ወዲያውኑ፡ይጠልፉታ
  ል።ብዙ፡አይተናል፣ሰምተንማል።በጥንቃቄና፡በብቃት፡ጊ
  ዜው፡ሲደርስ፡ሁለቱም፡እንደሚያስፈልጉን፡ግን፡እናውቃ
  ለን።

  እያንዳንዳችን፡ያለን፡መረጃ፡የተሟላና፡በትምህርት፡የታ
  ነፀ፡ነውን?የቅድስት፡ቤተ፡ክርስቲያናችንን፡አመራር፡በሽ
  ንገላ፣በወንዝ፡ልጅነት፣በዝምድናና፡ከዚያም፡አልፎ፡በገንዘ
  ብ፡ለማይገባቸውም፡"ይደልዎ"እየተባለ፡እስታሁን፡በመ
  ፈጸሙ፡እወደቅንበት፡አዘቅት፡ውስጥ፡እንገኛለን።

  የመዋቅሩ፡ሁሉ፡ሕመም፡ከዚህም፡አንፃር፡ገና፡በደንብ፡ሊ
  መረመር፡ይገባዋል።በዱለኞችና፡በጣዖት፡ገንቢዎች፡የበ
  ላይነት፡ቤተ፡ክርስቲያናችን፡መያዟን፡እናስተውል!

  ብዙ፡የማናውቃቸውን፡ችግሮች፡ግልጥ፡አድርጎ፡መወያየቱ፡
  ገና፡መጀመሩ፡ስለሆነ፣ዲያቆን፡ዳንኤል፡በጀመረው፡ላይ፡ተ
  ጨማሪና፡እውቀታችንን፡ሊያበለጽጉ፡የሚችሉ፡ውይይቶች፡
  ይደረጉ፡ዘንድ፡እጅጉን፡አስፈላጊ፡ነው።

  ዲን.ዮሐንስ፡አንድ፡ያቀረብከው፡አስተያየት፡እንዲህ፡ይላል፦

  "ወንድማችን ዲን.ዳንኤል ባቀረበው የቤተክህነቱ ችግሮ
  ች ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ፡፡ ነገር ግን በእኔ አተያይ
  ችግሮቹን እንጂ ጥልቀታቸውን (magnitude of the problem) አላሳየንም፡፡

  እስቲ፡አንተm፡ስለ፡ችግሮቹ፡ጥልቀት፡የምታውቀውን፡አስተም
  ረን።ይህ፡ደግሞ፡ባንተ፡ብቻ፡አይወሰንም።ሁላችንም፡ገና፡ብዙ፡
  ማወቅ፡የሚገባን፡የዝግጅት፡ትምህርቶች፡አሉ።

  እስተዚያው፡ድረስ፡ሁላችንም፡በያለንበት፡ትምህርታዊ፡ምን
  ባባትን፡በማባዛትና፡በማሰራጨት፤ውይይቶችም፡እንዲደረጉ፡
  መጣር፡ይገባናል።ይህም፡በመጠኑ፡እየተሞከረ፡እንደሆነ፡በያለ
  ንበት፡እናውቃለን።

  በጎ፡ትምህርት፡ጀምረናል።ሳንቻኮል፡በትዕግስት፡የጠለቀ፡መረ
  ጃና፡ዕውቀት፡እንዲኖረን፡እንትጋ።በመድኃኔ፡ዓለም፡ቸርነት፣በ
  ጥራትና፡በንቃት፡የምንሠራው፡ሁሉ፡ለተዋሕዶኢትዮጵያ፡ትን
  ሳኤ፡ታላቅ፡አስተዋፅዖ፡ሊኖረው፡ይችላልና!


  እግዚኦ፡መሐረነ፡ክርስቶስ፤
  በእንተ፡ማርያም፡መሐረነ፡ክርስቶስ።አሜን።


  ሳሙኤል፡ዘአሰቦት።

  ReplyDelete
 7. I disagree with some of the issues that Samuel zeasebot mentioned. I think the very idea of founding council is to pinpoint the problems, come up with founded evidence of the core problem. Then, we move on to the next step. I think this is very important but also very sensitive. So we have to be very careful how we persue. Finding the problem is solving half of the problem.
  As it looks right now. It is for sure going to have opositions from many fronts mainly from the "bete kihenet". This thing needs sacrifice, it may knock on individual doors. But if we are careful and plan ahead, it is managable.
  I belive the benefit of this council would be:
  1 Avoids rumors and gives clear view of the problem.
  2 Brings genuine people together.
  3 Initiate the solution from the bottom up.
  we will wait your next steps.
  May God be with you.

  ReplyDelete