Wednesday, August 11, 2010

የመፍትሔ ሃሳቦች

ባለፈው ሳምንት የቤተ ክህነታችንን ተግዳሮት አንሥተን ተወያይተን ነበር፡፡ በስተ መጨረሻም አጠቃላይ መፍትሔዎችን ለመጠቆም ተሞክሯል፡፡ በዚህኛው ጽሑፍ ደግሞ ዝርዝር የመፍትሔ ሃሳቦችን እናያለን፡፡ እነዚህ መፍትሔዎች በአዘጋጁ የታዩ ናቸው፡፡ አንባብያን ደግሞ የመፍትሔ ሃሳቦችን መሰንዘር አለባቸው፡፡

ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮች

ለቤተ ክርስቲያን የሚያስፈልጋት ምን ዓይነት መፍትሔ ነው?

በአሁኑ ጊዜ የቤተ ክህነቱ አሠራር ሥርዓትን እየለቀቀ የመጣበት ጊዜ ነው፡፡ እንደ ዖዝያን ለምጽም ግንባር ላይ ወጥቷል፡፡ ንጉሡ ዖዝያን በእግዚአብሔር ላይ በሠራው የድፍረት ኃጢአት ምክንያት እግዚአብሔር በለምጽ መታው፡ መጀመርያ ለምጹ በሰውነቱ ላይ ብቻ ስለነበረ በቀሚስ እና ካባ፣ በወርቀ ዘቦ እና በብር ዝርግፍ ሸፈነው፡፡ ኃጢአቱ እየባሰ ሲመጣ ግን ለምጹ ግንባሩ ላይ ወጣ፡፡ እርሱም ኃጢአቱን በንስሐ ከማስወገድ ይልቅ ለምጹን በሻሽ ለመሸፈን ሞከረ፡፡ ለተወሰነ ጊዜም ተሳካለት፡፡ በደሉ እና ግፉ እየባሰ በመምጣቱ ግን ለምጹ ሻሹ ላይ ወጣ፡፡ ከዚህ በኋላ ለመሸፈን አልቻለም፡፡

አሁን አሁን ነገራችን እንደ ዖዝያን ለምጽ ሊሸፈንበት ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ራሱ ችግሩም «አለሁ፣አለሁ» ብሏል፡፡ የለህም ብንለውም ራሱን በራሱ ያስመሰክራል፡፡

በዚህም ምክንያት በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ ይመለከተኛል የሚሉ ሁሉ በመነጋገር ላይ ናቸው፡፡ መፍትሔም ይሰነዝራሉ፡፡ የመፍትሔ አቅጣጫዎቻቸውን ስናይ ሁለት መልክ አላቸው፡፡ ተሐድሶ/reform/ ትንሣኤ /renaissance/ ፡፡

ተሐድሶ

ይህንን መንገድ የሚመርጡት አካላት በቤተ ክርስቲያን ላይ ሥር ነቀል አብዮት መምጣት አለበት ይላሉ፡፡ ይህ አብዮት ዶግማዋን፣ ቀኖናዋን፣ትውፊቷን፣ ቅዳሴዋን፣ ጸሎቷን፣ ገዳማዊ ሕይወቷን፣ ወዘተ የሚመለከት ነው ባይ ናቸው፡፡ እነርሱ የሚያቀነቅኑት መንገድ ከ500 ዓመታት ጀምሮ ምዕራብ አውሮፓውያን እና አሜሪካውያን በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያቀነቀኑት መንገድ ነው፡፡ በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በአስተዳደርዋ ላይ ይታይ በነበረው የሞራል ውድቀት፣ብኩንነት፣ አምባገነንነት፣ ሥርዓት አልበኝነት እና ዓለማዊነት ምክንያት ሕዝቡ ተማረረ፡፡ የወሰደው መፍትሔ ግን ችግርን በችግር የሚተካ ሆነ፡፡ የካቶሊክን ማንኛውንም አስተምሕሮ በመቃወምና በማፍረስ ሌላ ዓይነት አስተምህሮ ተካ፡፡ ከዚያም አልፎ ክርስትናን ርግፍ አድርጎ እስከ መተው ደረሰ፡፡

ተሐድሶ ውጤቱ ይሄው ነው፡፡ ምክንያቱም ነባርዋን ቤተ ክርስቲያን አፍርሶ በለዘብተኛነት በኩል ወደ ጽንፈኛ ዓለማዊነት ያደርሳታልና፡፡ ተሐድሶ መነኮሳት አጠፉ ብሎ ምንኩስና ሕይወትን ለማጥፋት ይነሣል፤ ጳጳሳት አጠፉ ብሎ ጵጵስናን ለማስቀረት ይጥራል፤ በአንዳንድ ቀሳውስት ችግር ቅዳሴን ያስቀራል፤ በሰባክያን ጥፋት ስብከት ይቅር ይላል፤ በተንዛዛ ድግስ ምክንያት ዝክር አያስፈልግም ይላል፤ በአጠቃላይ የሥነ ምግባር ችግሮችን ከመሠረተ እምነት ጋር ይቀላቅላቸውና ቤተ ክርስቲያንን ከመሠረቷ ይንዳታል፡፡

«መነሣት»

ይህ የመፍትሔ አቅጣጫ የሚነሣው በክርስትና ሕይወት መዳከም፣ መዛል እና ዓላማን መሳት ሊያጋጥም ይችላል፡፡ ከበጎች ጋር ተኩላዎች፣ ከስንዴ ጋር እንክርዳድ ሊቀላቀል ይችላል ከሚለው ነው፡፡ በመሆኑም የደከመውን ማጽናት፣ የላሉትን ማጠንከር፣ የተቀላቀሉትን መለየት፣ የተረሱትን ማስታወስ፣ የተበላሹትን ማስተካከል ይገባል ነው፡፡ በአጠቃላይ ቤተ ክርስቲያንን ወደ ጥንት ክብርዋ መመለስ ማለት ነው፡፡

ይህንን ለማድረግ ደግሞ ሁለት መሠረታዊ ጉዳዮች አሉ፡፡

የመጀመርያው አብርሖት ነው፡፡ ሕዝቡ በትምህርት መንገዱ እንዲበራለት ማድረግ፡፡ የቤተ ክርስቲያኑን ማንነት፣ መሠረተ እምነቷን፣ ታሪኳን፣ ሥርዓቷን ያጋጠማትንም ፈተና ዐውቆ፤ ራሱንም የቤተ ክርስቲያን አካል ማድረግ አለበት፡፡ ቤተ ክርስቲያን ተፈተነች ስንል ራሳችን ተፈተንን ማለታችን ነው፡፡ መከራ ገጠማት ስንል መከራ ገጠመን ማለታችን ነው፡፡ እየተነጋገርን ያለነው ከኛ ውጭ ስለሆነ አካል አይደለም ብሎ ማመን አለበት፡፡ ያላወቀ፣ ያላመነ እና ያልቆረጠን ሕዝብ ለትንሣኤ ማዘጋጀት ከባድ ነው፡፡ አስቀድሞ ሕማማትን ለማለፍ የሚያስችል ብቃት ይጠይቃልና፡፡

ሁለተኛው መዋቅራዊ ሽግግር /structural transformation/ ነው፡፡ መዋቅራዊ ሽግግር ማለት ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደ ጥንት ክብርዋ የሚመልስ ደረጃውን የጠበቀ እና ዘመኑን የሚዋጅ አሠራር፣ መዋቅር፣ አስተሳሰብ መመሥረት ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት ክህነቱ ሳይሆን አሰጣጡ እና አኗኗሩ፤ ጵጵስናው ሳይሆን አሰጣጡ እና አሠራሩ፤ ምንኩስናው ሳይሆን አሰጣጡ፣ አነዋወሩ፤ ብሕትውናው ሳይሆን አነዋወሩ፤ ቅዱሳት መጻሕፍቱ ሳይሆኑ አገባባቸው፤ የቤተ ክርስቲያን ናቸው ተብሎ የሚመዘኑበት መመዘኛ፣ አተረጓጎማቸው፣ ለምን ለምን ጥቅም እንደሚውሉ፤ በዓላቱ ሳይሆኑ፣ ብዛታቸው፣ አከባበራቸው፣ ድንጋጌያቸው፤ ሲኖዶሱ ሳይሆን አሠራሩ፣አወቃቀሩ፤ ወዘተ ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል ማለት ነው፡፡

መዋቅራዊ ሽግግር ሆ ተብሎ በአብዮት አይመጣም፡፡ አስቀድሞ ችግሩን በመረዳት፣ ከዚያም የችግሩን አንኳር /center of gravity/ በመለየት፣ ከዚያም ደረጃ በደረጃ በመፍታት የሚመጣ ነው፡፡ መግባባትን፣ለአንድ ዓላማ መነሣትን እና ሁሉ ዐቀፍነትን ይጠይቃል፡፡

ለቤተ ክርስቲያን ትንሣኤዋን እንጂ መለወጧን ለማምጣት የምንሠራ ከሆነ በክርስቶስ መሠረት ላይ ሳይሆን በኛ ፍላጎት ላይ የተመሠረተች ሌላ ቤተ ክርስቲያን ለመገንባት እየሞከርን ነው ማለት ነው፡፡

እናም እኔ የመፍትሔ ሃሳቦችን የምሰነዝረው ለቤተ ክርስቲያን የሚያስፈልጋት ተሐድሶ ሳይሆን ትንሣኤ ነው፡፡ በምእመናኑ ሕይወት እና ጉዞ፣ በአባቶች ሕይወት እና ጉዞ፣ በገዳማት ሕይወት እና ዐቅም፣ በአብያተ ክርስቲያናት አስተዳደር እና ዐቅም፣ በቤተ ክህነቱ አስተዳደር፣መንፈሳዊ ሕይወት እና አሠራር ላይ ዝለት አለ፤ ድክመት አለ፤ የዓላማ መሳት አለ፡፡ ስለዚህም መነሣሣት፣ ወደ ጥንቱ መመለስ እና እንደገና ቀና ማለት ያስፈልጋል በሚለው እምነት ነው፡፡

1 ጉዳዬ ብሎ መጸለይ

ብዙ ጊዜ ስለ ቤተ ክርስቲያን ፈተና ሲነገር ብዙዎቻችን እንጸልይ እንላለን፡፡ ልክ ነው፡፡ ያለ ጸሎት እና ጾም ሰይጣን አይወጣም፡፡ እኛ ግን ይህንን የምንለው አንድም ለማምለጫ፣ አንድም ለምዶብን፣ አንድም መቼም ማንም አያየንም ብለን ነው፡፡ እስኪ ስንቶቻችን ደረታችንን እየደቃን እንደ ራሔል እናለቅሳለን? እስኪ ስንቶ ቻችን ከልባችን እንደ ዳዊት ተዋርደን እግዚአብሔርን ጠየቅነው? የምንጸልየውም ጸሎት የፎርማሊቲ ጸሎት ነው፡፡ ቀድሞ ከምንጸልይበት መንገድ የጨመርነው አንዳች ነገር የለም፡፡

በእውነት የቤተ ክርስቲያንን ትንሣኤ ማየት ከፈለግን ግን ቀልዳችንን አቁመን ለጸሎት እንነሣ፡፡ ለራሳችን ሱባኤ እንግባ፣ ራሳችንን በምንችለው መንገድ እናዋርድ፤ ይህንን ጉዳይ ሳንረሳ እናስበው፡፡

በየገዳማቱ ለሚገኙት አበውም ችግሩን ከማስረዳት ጋር ጸልዩ እንበላቸው፡፡ ባለ ማቋረጥ መባ እየላክን እግዚአብሔርን እንዲማልዱ እናድርግ፡፡ እናቶቻችንንም እንንገራቸው፡፡ ይህች ቤተ ክርስቲያን እና ሀገር ተጠብቃ የምትኖረው በየዋሐን እናቶች ጸሎት ነው፡፡ የእናቶች ጸሎት እንደ ራሔል በቶሎ ይሰማልና ለጉዳዩ እንዲያስቡበት፣ እንዲያዝኑ በትና እንዲያለቅሱበት እናድርግ፡፡

ብጹአን አበውም በውይይት እና በስብሰባ ችግሩን ለመፍታት ካልቻላችሁ ሌላውን ነገር ትታችሁ ወደ ጸሎቱ ፊታችሁን አዙሩ፡፡

2 ከቲፎዞነት መውጣት

በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ጥብቅና ልንቆም የሚገባው ወገንተኛም ልሆን የሚገባው ለቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ይህም ማለት ለዶግማዋ፣ለሥርዓቷ እና ለትውፊቷ ማለት ነው፡፡ ስለ ሰዎች የምንነጋገረው ከእነዚህ ነገሮች አንፃር መሆን አለበት፡፡ እኛ ሰዎችን በቤተ ክርስቲያን በኩል አገኘናቸው እንጂ ቤተ ክርስቲያንን በሰዎች በኩል አላገኘናትም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርኮችን፣ ጳጳሳትን፣ ቀሳውስትን፣ ዲያቆናትን፣ ሊቃውንትን፣ ሰባክያንን፣ መዘምራንን አፈራች እንጂ እነርሱ አላስገኟትም፡፡ በመሆኑም የሰዎች እና የቡድኖች ቲፎዞ በመሆን ዶግማዋን ፣ሥርዓቷን እና ትውፊቷን ከማፍረስ መቆጠብ አለብን፡፡

ሰውን መውደድ፣ ማድነቅ እና ማክበር መልካም እና ክርስቲያናዊ ምግባርም ነው፡፡ ያ ማለት ግን ክፉ ሥራውን መውደድ፣ማድነቅ እና ማክበር ማለት አይደለም፡፡ ቅዱስ ቄርሎስ ለንስጥሮስ በጻፈው ደብዳቤ «ንስጥሮስ ሆይ አንተን እወድድሃለሁ፤ ኑፋቄህን ግን እጠላለሁ» ያለውን መርሳት የለብንም፡፡ እገሌ የሀገሬ ልጅ ነው፣ ውለታው አለብኝ፤ የኔን ፖለቲካ ያራምዳል፣ ይወደኛል፣ ይጠቅመኛል፣ አብሮ አደጌ ነው ወዘተ እያልን ጥፋታቸውን በዝምታ ያለፍናቸው ሰዎች ተቀምጠን የሰቀልነውን ቆመን ማውረድ እንዳንችል አድርገውናል፡፡

ታላቁ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ ወልደ ነዌ በአንፃረ ኢያሪኮ በተገለጠ ጊዜ ኢያሱ «ከኛ ወገን ነህ ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን?» ሲል ጠይቆት ነበር፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ግን የወገንተኛነትን ጥያቄ አልመለሰም፡፡ «እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ» ነበር ያለው፡፡ «የእግዚአብሔር ከሆነው ጋር ነኝ» ማለቱ ነበር፡፡ በመሆኑም መመዘኛችን ከእግዚአብሔር ጋር የሆነ ማን ነው? የሚለው እንጂ የኔ ወገን ማን ነው? የሚለው መሆን የለበትም፡፡

በሌላም በኩል እኛ የክርስቶስ ነን ማለትን መልመድ አለብን፡፡ የአቡነ እገሌ፣ የቄስ እገሌ፣ የአባ እገሌ፣ የባሕታዊ እገሌ፣ የሰባኪ እገሌ፣የዘማሪ እገሌ፣ የማኅበረ እገሌ፣አይደለንም፡፡ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የትግሬ፣ የወሎ፣ የሸዋ፣ የወለጋ፣ የሲዳሞ፣ የከፋ፣ የሐረር፣ የባሌ፣ የጉሙዝ፣ የአፋር አይደለንም፡፡ እኛ የክርስቶስ ነን፡፡ የክርስቶስ ከሆኑት ጋርም አብረን እንቆማለን፡፡ የሚያገናኘን ሃይማኖት እንጂ ዘር፣ፖለቲካ፣ ወንዝ፣ ተራራ፣ አብሮ አደግነት፣ ጉርብትና፣ አይደለም ብለን ለራሳችን ማሳመን እና መቁረጥ አለብን፡፡

ቲፎዞነት ጭፍን ድጋፍ እና ተቃውሞን ያመጣል፡፡ ነገሮችን በሰከነ መንፈስ፣ በሕግ እና በሥርዓት አንፃር፣ከታሪክ እና ከቅዱሳት መጻሕፍት አንፃር፣ ከተጠየቅ እና ከማስረጃ አንፃር ከመገምገምና አቋም ከመያዝ ይልቅ እነማን አሉበት? እነማን ተናገሩ? ወገኖቼ ናቸው አይደሉም? በሚል መመዘኛ ብቻ ወደ መቃወምና መደገፍ ይወስደናል፡፡ ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ የመከረውን ትቶ አኪላስ አርዮስን ለመሾም የበቃው አብረው የተማሩ የትምህርት ቤት ጓደኞች በመሆናቸው ከሕጉ ዝምድናው በልጦበት ነበር፡፡ ነገር ግን አኪላስም በመንበሩ አልሰነበተም፣ ለቤተ ክርስቲያንም ነቀርሳ አተረፈላት፡፡ ቲፎዞነትም ውጤቱ ይኼው ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የዳዊትን እና የዮናታንን ወዳጅነት እናስብ፡፡ ዮናታን የንጉሡ የሳኦል ልጅ ነው፡፡ አባቱ ቢሞት ወራሽ ነው፡፡ ዳዊት ደግሞ መንበሩን ይወርሳል የተባለ ሰው ነው፡፡ ዮናታን የአባቱ ቲፎዞ ሆኖ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ከመጋጨት ይልቅ እግዚአብሔር አብሮት ከሆነው ከዳዊት ጋር መሆንን መረጠ፡፡ በሥጋ፣ በዝምድና እና በጥቅም ሳኦል ይሻለው ነበር፡፡ ዳዊት የአባቱን መንበር እንደሚወስድ እያወቀ እንኳን ሥልጣን ሳያጓጓው ለእውነት መቆምን መረጠ፡፡

ግሪኮች ዲዮስቆሮስ ያለ ሕግ ሲባረር እና ሃይማኖት በኬልቄዶን ስትፈርስ የሮም ቲፎዞ ሆነው አጨበጨቡ፡፡ ከአምስት መቶ ዓመታት በኋላ ግን እነርሱ ራሳቸው ከሮም ተለዩ፡፡ መጀመርያውኑ ከቲፎዞነት ይልቅ ለሃይማኖት ቢያደሉ ኖሮ ይህ ሁሉ ባልደረሰ ነበር፡፡

3 መንገር

ብዙ ምእመናን በቤተ ክርስቲያን ላይ በደረሰው ፈተና ያዝናሉ፡፡ የቤተ ክህነቱን መመሰቃቀል እያዩ ይናደዳሉ፡፡ ሚዲያው እና ወሬው ሁሉ ስለሚወድዷት ቤተ ክርስቲያን ሲሆን ዘመኑን ይኮንናሉ፡፡ አሁን ግን ይህ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ ኃላፊነት ላለባቸው አካላት መንገር ያስፈልጋል፡፡ ፓትርያርኩን፣ ጳጳሳቱን፣ መነኮሳቱን፣ ቀሳውስቱን፣ የሚቀርቡ ምእመናን አሉ፡፡ እነዚህ ምእመናን ኃላፊነት አለባቸው፡፡ የሚያውቁትን እና የሚሰሙትን መንገር ይገባቸዋል፡፡

ወደ አባቶች ዘንድ መባውን እና ፍትፍቱን ብቻ ሳይሆን የቤተ ክርስቲያንንም ነገር መውሰድ አለባቸው፡፡ ምእመናኑ ምን ያህል ምሬት ላይ እንደ ደረሱ፤ ሁኔታው ካልታረመና በዚሁ ከቀጠለ መጨረሻው ምን ሊሆን እንደሚችል ማስረዳት አለባቸው፡፡ አባቶችን ማማት መፍትሔ አያመጣም፡፡ እነርሱ በሌሉበት ማውገዝ እነርሱ ባሉበት አቦ አቦ ማለት ውጤት አላመጣም፡፡ የምንወዳቸው ከሆነ እንንገራቸው፡፡ እናሳስባቸው፡፡ መስተዋት እንሁናቸው፡፡

ለኛ ለልጆቻችሁ ፈተና ሆናችሁን፤ ስለ እናንተ ክፉ መስማት ሰለቸን፤ ልጆቻችን እየጠየቁን ነው፤ ለምን ዝም ትላላችሁ እያልን ለመፍትሔ እንዲነሡ መቀስቀስ ይገባናል፡፡ በግብጽ ቤተ ክርስቲያን በአቡነ ሺኖዳ እና በአንድ ሌላ ጳጳስ መካከል ልዩነት ተፈጠረና ቤተ ክርስቲያኒቱ አደጋ ላይ ወደቀች፡፡ ሁለቱ አበው በየራሳቸው መንገድ እየሄዱ መሥመሩ ተበላሸ፡፡ በዚህ ጊዜ ምእመናኑ መክረው ተነሡ፡፡

አንድ ቀን ሁለቱ አበው በየራሳቸው ወደ ቅዳሴ ሲገቡ ምእመናኑ በር ላይ ጠበቋቸው፡፡ እርስ በርሳችሁ ተጣልታችሁ አትቀድሱም፤ እኛም አናስቀድስም፤ መጀመርያ ታረቁ፤ አሉ፡፡ ሁለቱም ለጊዜው እምቢ አሉ፡፡ ምእመናኑን ካልታረቃችሁ ብለው መሬት ላይ ወደቁ፡፡ በመጨረሻም ሁለቱም አባቶች ቀርበው ይቅር ተባባሉ፡፡ ከዚያም አብረው ቀደሱ፡፡

ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ ያሉትን አበው የሚቀርቡ እናቶች እና ሽማግሌዎች፣ ባለ ሀብቶች እና ባለሞያዎች አሉ፡፡ እነዚህ አካላት አባቶቻችን የቤተ ክርስቲያንን ችግር እንዲፈቱ መጠየቅ አለባቸው፡፡ እናንተ የሰላም እና የፍቅር አርአያ ካልሆናችሁ፣ ችግር በመፍታት እና ስሕተትን በማረም አርአያ ካልሆናችሁ፤ የእድገት እና የብልጽግና አርአያ ካልሆናችሁ፣ ተወያይቶ የመስማማት እና የመግባባት አርአያ ካልሆናችሁ፣ ግብረ ሰላሙን ለምን እናመጣለን?  ማለት አለባቸው፡፡

4 ከዚህ በኋላ ሹመት ቢቆም

የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ለ10 ሚሊዮን ክርስቲያኖች ከ50 በላይ ጳጳሳት ሲኖሯት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ግን ከ45 ሚሊዮን ለሆነው ሕዝቧ ጳጳሳቷ ከአርባ አይበልጡም፡፡ እናም ገና አባት ያላገኘ ሕዝብ መኖሩ የማይካድ ነው፡፡

በቤተ ክርስቲያናችን አስቸኳይ መፍትሔ ከሚያሻቸው ነገሮች አንዱ የሲመት አሰጣጥ ጉዳይ ነው፡፡ ከሲመተ ዲቁና እስከ ጵጵስና ከሕገ ቤተ ክርስቲያንን አንፃር ችግሮች መኖራቸውን በየጊዜው የተካሄዱ የአጠቃላይ የሰበካ ጉባኤያት የአቋም መግለጫዎች ሁሉ ይናገራሉ፡፡ በሲኖዶስም በተደጋጋሚ ተነሥቷል፡፡ ነገር ግን እርምት አልተሰጠውም፡፡

ቤተ ክርስቲያን ዲያቆናትን፣ካህናትን እና መነኮሳትን ሠፍራ ቆጥራ አታውቃቸውም፡፡ እያንዳንዱ አባት ክህነት የሚሰጠው በተለያየ መመዘኛ ነው፡፡ የክህነቱ መታወቂያ በቀላሉ ፎርጅድ ሊሠራ የሚችል ነው፡፡ አበው ክህነት የሰጡትን ሰው ስለማይመዘግቡት ለማን ምን እንደሰጡት አያስታውሱትም፡፡ አንዳንዶች ፈትነው ይሰጣሉ፤ አንዳንዶች በዕውቂያ ያደርጉታል፡፡ አንዳንዶች በአደባባይ አንዳንዶች በድብቅ፡፡ አንዳ ንዶቹ በሀገረ ስብከታቸው፤ አንዳንዶቹ ከቀኖና ውጭ ያለ ሀገረ ስብከታቸው፡፡

የምንኩስናውም እንደዚሁ ነው፡፡ ዋልድባ የመነኮሰውን መርካቶ ከመነኮሰው መለየት አልተቻለም፡፡ ገዳማቱ የታወቀ መዝገብ የላቸውም፡፡ በቤተ ክርስቲያኒቱ ዳታ ቤዝ የለም፡፡ የምንኩስናው መታወቂያ በቀላሉ ፎርጅድ ሊሠራ ይችላል፡፡ እነማን የማመንኮስ ሥልጣን እንዳላቸው በትክክል ተለይቶ አይታወቅም፡፡

በመሆኑም እነዚህን መሰል ችግሮችን በአስቸኳይ መቅረፍ ካልተቻለ ያለ ሕግ የመነኮሱ፣ ያለ ሥርዓት የተካኑ ሰዎች ወደ ትልቁ መዓርግ ወደ ጵጵስና መድረሳቸው የማይቀር ነው፡፡ ይህ ደግሞ የቤተ ክርስቲያንን ክብር የሚነካና የማይሽር ቁስል ጥሎ የሚያልፍ ነው፡፡ በመሆኑም ሲኖዶሱ ይህንን ችግር እስኪፈታ ድረስ ሲመተ ጵጵስና ለጊዜው መቆም አለበት፡፡

አሁን አሁን ለሲመተ ጵጵስና ከሃይማኖት እና ምግባር፣ ከዕውቀት እና ችሎታም ሌላ ሌሎች መተያያዎች እየመጡ ነው፡፡ የወርቁ ቁልፍ ሁሉንም በር እየከፈተው ነው፡፡ እናም ቤተ ክርስቲያን ያሏት ችግሮች ይበቋታል፡፡ ሌላ ችግር መጨመር የለባትም፡፡ መጀመርያ አሁን ያለው ችግር ይፈታ፡፡

አራት ኪሎ ቆሞ ለሚያይ ወደዚህ ትልቅ መዓርግ ለመምጣት በእጅ እና በእግራቸው የሚፋጠኑትን ሰዎች መታዘብ ይችላል፡፡ አንዳንዶቹ እንደ ተመራቂ ተማሪ «ልሾም ነው» እያሉ ያስወራሉ፡፡ ሌሎቹም ልብሱን ገዝተው ቀናቸውን ይጠብቃሉ፡፡ እንዴው አሁን ይሄ የጤና ነው?

5 መንግሥት ተገቢውን ሥራ መሥራት አለበት

ልዩ ልዩ መዋቅሮችን በማስተካከል፤ ቢ ፒ አርን በመተግበር፤ በሥልጠና እና በሞያ ማሻሻያ፤ አያሌ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ተሻሽለዋል፡፡ ቀበሌ እንኳን ተሻሽሎ ወረፋ እና ቢሮክራሲ ብርቅ ሆኗል፡፡ እስካሁን በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ዓይነት አስተዳደራዊ መሻሻል ያልነካው ቤተ ክህነትን ነው፡፡

ቤተ ክህነቱ አሁን ያለበት ደረጃ ለሀገሪቱ ደረጃ የሚመጥን አይደለም፡፡ ሲሆን እንደ ጥንቱ ከሀገሪቱ እድገት ቀድሞ መምራት ነበረበት፡፡ ካልሆነ ደግሞ በእኩል መሄድ፡፡ ለዚህ ደግሞ ሀገሪቱን የሚመራው መንግሥት ኃላፊነት አለበት፡፡

በመጀመርያ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሀገሪቱ አካል በመሆንዋ፤ እንደገናም የሀገሪቱ አንዷ መገለጫ በመሆንዋ፤ ከዚህም በተጨማሪ በሀገሪቱ ታሪክም ሆነ ሥሪት ውስጥ የማይተካ ሚና ስላላት ለመንግሥት የቤተ ክርስቲያን ነገር ሊገድደው ይገባል፡፡ በርግጥ መግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገባ ሕግ ያግደዋል፡፡ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባት ማለት ግን ትክክለኛ ትርጉም ያስፈልገዋል፡፡

ገንዘብ ሲመዘበር፣ የአገልጋዮች መብት ሲነካ፣ ሕግ እና አስተዳደር ሲጠፋ፣ የሀገሪቱን መልካም ገጽታ የሚያበላሽ ተግባር ሲፈጸም ዝም ብሎ ማየት ጣልቃ አለመግባት አይመስለኝም፡፡

ቤተ ክርስቲያኒቱ ደረጃውን የጠበቀ የሠራተኛ አስተዳደር እንዲኖራት፤ ደረጃውን የጠበቀ የሂሳብ አሠራር እንዲኖራት፤ ደረጃውን የጠበቀ የፍትሕ አሰጣጥ ሥርዓት እንዲኖራት፤ ደረጃውን የጠበቀ መዋቅር እንዲኖራት ማስገደድም፤ ማበረታታትም፣ መርዳትም ይገባዋል፡፡ ይህች ቤተ ክርስቲያን በተፈለገው መጠን ካልተራመደች ከግማሽ በላይ የሆነችው ኢትዮጵያ እንዳልተራመደች ይቆጠራል፡፡

ለምሳሌ የእምነት ተቋማት ከቀረጥ ነጻ ቢሆኑም በውጭ ኦዲተር የተመሰከረለትና ደረጃውን የጠበቀ የሂሳብ ሪፖርት ከማቅረብ ግን ነጻ መሆን የለባቸውም፡፡ ገንዘቡ የሕዝብ ገንዘብ ነው፡፡ ይህ ገንዘብ ደግሞ ለትክክለኛው ተግባር እንጂ ሀገርን እና ሕዝብን ለሚጎዳ ተግባር መዋል የለበትም፡፡ ይህም የሚረጋገጠው በአሠራር ነው፡፡ በአብዛኛው የዐለም ሀገሮች የእምነት ተቋማት ከቀረጥ እና ግብር ነጻ ናቸው፡፡ ነገር ግን የሂሳብ ሪፖርት የማስገባት ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ደግሞ ሕዝቡ ነጻ የሆነ እና የታመነ ሪፖርት የማግኘት መብቱን ያረጋግጥለታል፡፡

6 አለመተባበር

ምስጉን ነው በክፉዎች መንገድ ያልሄደ

በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ

በኃጥኣንም መንገድ ያልሄደ /መዝ1፣1/

አንድ ሰው ችግሩን መፍታት ካቃተው ቢያንስ የችግሩ አካል ከመሆን መራቅ አለበት፡፡ ዛፎቹ ተሰብስበው መጥረቢያ ጨረሰን ብለው ተመካከሩ ይባላል፡፡ ብዙዎቹ ዛፎች መጥረቢያ ይቃጠል፣ ገደል ይጨመር፣ ይታሠር ወዘተ እያሉ ሃሳብ ሰጡ፡፡ አንድ ሽማግሌ ዛፍ ግን «ለመጥረቢያ እጀታ ሆነን ራሳችንን ያስጨረስን እኛ ነን አሉ ይባላል፡፡ አሁንም ለችግሩ መባባስ የምእመናንም አስተዋጽዖ አለበት፡፡

መነኮሳቱ በገዳም እንዳይጸኑ ከተማ እናመጣቸዋለን፤ አጉራ ዘለል ባሕታውያንን ተከትለን መሥመር እናስወጣቸዋለን፤ ገንዘባችንን ጥቅም ላይ በማይውልበት ቦታ እናፈስሳለን፡፡ በየአጥቢያችን የሰበካ ጉባኤያቱ ሲፈርሱ እና ሲዳከሙ ዝም እንላለን፡፡ ሪርት ቢቀርብ ባይቀርብ ግድ የለንም፡፡ የልማት ሕንፃ መሠራቱን እንጂ እንዴት ጨረታ ወጣ? እንዴት ኮንትራክተሩ ተመረጠ? እንዴት ሕንፃው ተከራየ? አንጠይቅም፡፡ ግን በየቤቱ እናማለን፡፡

ገንዘብ መስጠታችንን እንጂ በትክክል መስጠታችንን በተግባርም መዋሉን አንጠይቅም፡፡ ደረሰኝ አለመቀበል ትኅትና የሚመስለን፤ ሽጉጥ አድርጎ መስጠት ከከንቱ ውዳሴ መራቅ የሚመስለን ብዙዎች ነን፡፡ ነግር ግን በቤተ ክርስቲያን ጥፋት እየተባበርን ነው፡፡

በአንዳንድ አጥቢያዎች ጧፍ እና ሻማ የአይጥ መዋያ ነው፤ ሌሎቹ ደግሞ በጉሎ ዘይት ይቀድሳሉ፤ በአንዳንድ አጥቢያዎች ልብሰ ተክህኖውን ቤት ጠብቦታል፣ ሌሎቹ ደግሞ በሴት ቀሚስ ይቀድሳሉ፤ በአንዳንድ አጥቢያ ብሩ ሞልቶ ተርፎ ለመኪና ይዋጣል፤ ሌሎቹ ለካህናት ደመወዝ የሚከፍሉት አጥተዋል፤ እኛ ደግሞ ላለው ይጨመርለታል ብለን በብኩንነት ላይ እንጨምራለን፡፡

በአሁኑ ጊዜ የአዲስ አበባ አድባራት ከመጠን በላይ በሰው ኃይል ተጨናንቀዋል፡፡ በአንድ ደብር ትንሹ የሰው ኃይል ሰማንያ ሲሆን ከፍተኛው 300 ነው፡፡ አንዳንድ የአዲስ አበባ አድባራት አገልጋዮች ሰሞነኛነት ሳይደርሳቸው ዓመት ይሞላቸዋል፡፡ ሌላ ቦታ እየሠሩ ለደመወዝ ብቻ የሚመጡም አሉ፡፡ በእነዚህም ላይ ደጀ ጠኚ እየተባለ በየጊዜው ይመደብባቸዋል፡፡ ለምን? ነው ጥያቄው፡፡

በአዲስ አበባ የተከማቸ ገንዘብ አለ፡፡ ስለዚህም ሥጋ ባለበት አሞሮች ይሰባሰባሉ በተባለው መሠረት ሁሉም ወደ አዲስ አበባ ይጎርፋል፡፡ አምስቱ አእማደ ምሥጢር፣ ሰባቱን ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን እና አሥሩን ትእዛዛት እየተጠየቀ ይገባል፡፡ ከዚህም ከፍ ካለ ባለ ሠላሳ፣ ባለ ስድሳ እና ባለ መቶ ፍሬ መሆኑን አይተው ያስገቡታል፡፡

መንግሥት በፌዴሬሽን ምክር ቤት አማካይነት በሚያወጣው ቀመር መሠረት የሀገሪቱን ሀብት ያመጣጥናል፡፡ ቤተ ክህነት ግን ይህንን ማድረግ አልቻለችም፡፡ በርግጥ አንዳንድ ሀገረ ስብከቶች የበጀት ድጎማ ያገኛሉ፡፡ ያ ግን ሊያመጣጥነው አለቻለም፡፡ አንድ የገጠር ካህን አሥር ብር ሲከፈለው፤ አንድ የአዲስ አበባ ካህን አማካይ ደመወዝ ግን አንድ ሺ ብር ነው፡፡ በመካከል ያለው ክፍተት ከሰማይ እና ከምድርም ይሰፋል፡፡

ቤተ ክህነቱ ይህንን እስኪያመጣጥን ድረስ እኛ ማመጣጠን አለብን፡፡ ለምንድን ነው ገንዘባችንን ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት፣ ለተጎዱ ገዳማት እና አድባራት፣ እንዲሁም ለተረሱት የአብነት ት/ቤቶች የማና ውለው? ለምንድን ነው ውጤት በሚያመጣበት ቦታ የማናፈስሰው? ተቀብለው አቡነ ዘበሰማያት ለሚደ ግሙ ምስኪን ካህናት ለምን አንሰጥም?

ይቀጥላል

57 comments:

 1. ምጥው ለአንበሳAugust 11, 2010 at 10:02 PM

  ይበል ያስብላል ዳኒ ግሩም አቀራረብ ነው እኔም የምለው አለ ትንሽ ጊዜ ያ ስፈልገኛል አስተያየቴ ን ለመጻፍ እመ አምላክ ከአንተ ጋር ትሁን።

  ReplyDelete
 2. Dn. Daniel, Egziabher tsegawun yabizalih. Whenever, i visit your page, i get inspired. Tesfa batanibet gize yetesfa chilanchil endinay tadergenaleh. Fetari yitebikih.

  ReplyDelete
 3. ዳኒ እባክህን ይሄንን ፅሁፍ አባቶቻችን እና የሚመለከታቸው ሁሉ የሚያነቡበትን መንገድ ፈልግ ሌሎቻችንም እንደዚሁ

  ReplyDelete
 4. ዲን እንደ ምን ጊዜውም ድንቅ ፅፈሃል። ፀጋውን ያብዛልህ።

  ReplyDelete
 5. Dear Daniel

  Indeed you are the icon of our church.Your keen observation needs to be distributed to all concerned bodies(Church fathers,sunday school students ,the masses).Hope the future might be promising in case we implement it on the ground.
  God bless your work!

  ReplyDelete
 6. ዉድ ዲ/ን ዳንኤል፡

  እግዚአብሔር ይስጥልን፤ ቃለ ህይወት ያሰማልን። በተጠቀሱት መፍትሔዎች መቶ በመቶ እስማማለሁ፡ እንደእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ የበኩሌን ድርሻ ለመወጣት እሞክራለሁ።

  በተለይ በተለይ ምዕመናን የሚሰጡት ገንዘብ ምንም እንኩዋን የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ቢሆንም ገንዘቡን ለሚገባዉና በሚገባዉ ሁኔታ መስጠት ክርስቲያናዊ ግዴታችን ይመስለኛል።

  የእኔ ፍራቻ ግን ... ስንቱ ነዉ ይህንን ችግር የተረዳዉ? የአዲስ አበባ አንዳንድ ምዕመናን ብቻ ተረድተዉ ሊሆን ይችላል፣ ለሌሎቹ እንዴት እናድርስ? እነዚህን የመፍትሔ ሀሳቦችስ እንዴት ለምዕመናን ማድረስ ይቻላል? የዚህን ብሎግ መኖር ለማያዉቁትና ኢንተርነት ማግኘት ለማይችሉ ቢያንስ በጋዜጣ መልክ የሚወጣበት መንገድ ቢመቻች የተሻለ ነዉ እላለዉ።

  ከብሪታኒያ

  ReplyDelete
 7. ልብ ያለው ልብ ይበል!

  ReplyDelete
 8. Thanks dani it is a good solution,God helps us to perform this task.this issue is to all ortodox,so please let's pray.dani god bless u.thanks again.

  ReplyDelete
 9. "ስጋና ደም ይሀን አልገለጡልህም" ብቻ እግዚአብሄር ይጠብቅልን ሌላ ምንም አልል :: እኔ ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ ከራሴ ጀመሮ ለማቀው ሁሉ እንዲያነቡት በማድረግ የበኩሌን እወጣለሁ::

  ReplyDelete
 10. Thanks Dn Daniel,
  I think 'MOST' EOTC members who are informed enough about the current problems of the Church know that there must be some kind of Biblical-reform (structural or moral )needed... but the problem is ...nobody cares enough to actually do something about it. We go to our 'atbia' churches regularly because we think that is what is required of us. But being involved in the 'everyday' business of the church...is not our job. That is what I see in my area... no one cares...not really. Everyone likes to talk about it but no one is there to 'walk the walk' (as they say).
  So, may be we need some kind of horror (may be when islam and protestantism are the majority and Christianity becomes a rare sight in Ethiopia like Egypt... to shake us out of the 'non-chalant' state we are in.
  May be then we will start to work together and see that a united and strong Church is better...
  I don't see any other way for the moment ...we just don't care enough beyond the usual empty talk...My hope is on the few undefiled 'menekosat' here and there in the 'gedamat' that are praying for all of us... I think it is only their prayers that is keeping us from being wiped out by the wrath of God, do we think we merit His blessing ? Because the so called 'fathers' or 'leaders' of the church are oblivious to the seriousness of the problems.

  Hope u understand my point...

  God bless His church and the true followers,

  Ankiro

  ReplyDelete
 11. too much mugesa! Dn. Daniel is doing what is expected from him. Let us do our parts instead of admiration which has long been a great enemy to our church. Yemewedis meat kemibeza 1 dingay enaqebil beyalenibet.

  ReplyDelete
 12. ዲ/ን ዳንኤል ግሩም የመፍትሔ ሃሳብ ነው ነገር ግን ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት ለተጎዱ ገዳማትና አድባራት ለተረሱ የአብነት ት/ቤቶች ገንዘቡ የሚደርስበትን መንገድ መጠቆም ይገባል የሚል እምነት አለኝ ምክንያቱም ይህንንም አለማወቅ በራሱ ለሌላ ጥፋት ስለሚዳርግ ለእነዚህም ቢሆን በአግባቡ ሊደርስና ለተገቢው ጉዳይ ሊውል በሚችልበት መልኩ ማድረስ ይገባል እላለሁ እግዚአብሔር ብርታቱን ያድልህ::

  ReplyDelete
 13. Aznleu Alkesaleu Selbdele.. Yemilew Mezmure Tezi Aleg Yaslkeseal

  Eshi Ene Yebkulen Kemdrge Wedewala Alelem Yhen Tsufe Lebzeu Sew Lemsweke Etraleu Lelawe Malkse Ena Metsley New Mine Yebaleal
  Kale Hiwoten Yasemlen Anten Ye EGZIABHEREN Awryea Yetbklen Tebkei Melakten Yelkle, EGZIABHER Yelben Meseat Yadrglen Amen!

  ReplyDelete
 14. በስመ ሥላሴ አሜን።

  ቃለ ሕይወት ያሰማልን መምህር።

  እንደኔ እንደኔ መፍትሔው አንድ እና አንድ ነው ... እርሱም አንተ እንዳስቀመጥከው ሁሉን ማድረግ ወደሚችል አምላክ አቤት ማለት ...ወደርሱ መቅረብ ... ሲጀምር ወደርሱ ያልቀረበ ሰው ሕይወቱ ከቲፎዞነት አይወጣም ... ምንም ያህልም ከበላይ ያሉ አባቶችን የሚቀርቡ ሰዎች እየሆነ ስላለው ነግር እንዲያሳስቡዋቸው ፍላጎታችን ቢሆን ሰዎቹ እግዚአብሔርን መፍራት ከሌላቸው ፤ ካላወቁትም ያሰብነውን አይሳኩም ... ሌላም ሌላም

  የመንግስት ጣልቃገብነት ጉዳይ እንደኔ ችግሩን የሚያባብስ እሳት ቢሆን እንጂ እንደ አንድ መፍትሔ ሊቀርብ የሚችል አይደለም እላለሁ ... በርግጥ ቤተክርስቲያኗ የሀገሪቱ አካል እንደመሆኗ መጠን እንደመንግስት አብሮ ሊሰራባቸው የሚገቡ አያሌ ስራዎች አሉት ... " በቤተክርስቲያን አስተዳደር መሃል መግባት " ግን ... በፍፁም የሚያገባው አይደለም ... አሁንም እንደኔ መንፈስቅዱስ የሚመራውን ቤት ... በዚህ በዚህ ጉዳይ የሚያውቅለት መንግስት ነው ሊባልም አይገባውም ... በጥንቶቹ አባቶቻችን ዘመን የነበረውን መልካም ታሪክ አንስተን በአባቶቻችን አድሮ የሰራውን መንፈስቅዱስን እንዳመሰገንን በችግርም ወቅት እርሱ የወደደውን ማየት እንፈልጋለን ...

  ተሳስቼ ከሆነ አርሙኝና መንግስት ብለን ደፍረን የምንናገርላቸው ሰዎች አሰራራቸው እንዴት ነው? ... በዘር ለመናከሳችን ምክንያት የምናደርጋቸው ፤ በሙያ ብቁ ሆነን የድርጅት አባል ስላልሆንን መድሎ ተፈፀመብን እያልን የምንከሳቸው ፤ የነገ አገር ተረካቢዎች በእውቀት ታንፀው የሚወጡባቸውን የከፍተኛ ተቋማት ደረጃ አወረዱ ብለን የምንወቅሳቸው ፤ ... ሰዎች አይደሉም እንዴ? ... ነው ሌላ የማናውቀው መንግስት አለ? ... በርግጥ መምህራችን " ቀበሌ እንኳን ተሻሽሎ ወረፋ እና ቢሮክራሲ ብርቅ ሆኗል " ... ብለኸናል ... እውን እንደዛ ነው? ... እና ይህ መንግስት ነው የቤተክርስቲያንን ችግር የሚፈታው? ... በሙስና የተበላሸ አሰራር ሰፍኖበታል የምንለው መንግስት ነው ነጻ የሆነ እና የታመነ የሒሳብ ሪፖርት የማግኘት መብታችንን የሚያረጋግጥልን? ... እንዴት ነው ነገሩ ወገኖቼ?

  ለምን እራሳችንን እናታልላለን? ... ይልቅስ መምህራችን እንዳለው ቀልዳችንን አቁመን ለጸሎት እንነሣ ... አጥፍተናል ... በድለናል ... ከእግዜር መንገድ ወጥተናል ... ስለዚህ የሆነው ሁሉ ሆነብን እንበል ... ከዛም አምርረን እናልቅስ ... እርሱም ይምረናል ...እኔ እስከገባኘ የእግዚአብሔር ቤት አሰራር ይሔው ነው ... በጣም ቀላል ... በጣምም ከባድ ... አካሔዱ ገብቶን በተሰበረ መንፈስ ወደርሱ ስንመለስ የሚቀል ... ከርሱ ረቀን በሩቁ ስንጣራ የሚከብድ

  ወገኖቼ ስለዚህ ልንመለስ ያስፈልገናል ... እንድንመለስም የሚያሳስበንም ጭምር ያስፈልገናል።

  እግዚአብሔር አምላክ መልካሙን ጎዳና ያመልክተን።

  ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

  ReplyDelete
 15. selam D.D.i was so crying when i read oll comments.becouse some body said my felling. last time i was try to tell you but i wasn't fell free that's why i am so sad.God bless you forever............

  ReplyDelete
 16. Hi dani, betam arif tsihuf new. hulem tsegawun yabizalih. chigiru bebete kirstian bicha yetewosene ayidelem, behager dereja new. Teyakim teteyakim yelem behulum aserarachin. Wode wusti teliko yimeleketegnal bilo meteyek kerito, report lemadamet enkuan tigist yelelen bizu sewoch nen. beyebetu hamet mawuratin gin eniwodalen.

  Ante gin berta ayizoh, egzer yirdah. Beta berta berta...and ken negerochi yilewotalu.

  ReplyDelete
 17. Almost 12 years ago I stop giving money to Addis Ababa churches because most of them have a lot of money however, they don't help the poor churches in rural area. So what I do is as a conserned Christians I make sure the churches & monastories in rural area get my part.

  God bless Dani
  Your brother in Canada.

  ReplyDelete
 18. 'Egizhihabiher Edime, Tena, Tibebun Yabizalih..Le Ethiopiam endanite yalu Elif lijoch Egizihabiher yisitat' Kalehiyiwet yasemalin!!

  Til
  Maryland, US

  ReplyDelete
 19. +++
  Kalehiwot Yasemalin,

  Melikam Meftihae!

  Dirshachinin eniwota!

  ReplyDelete
 20. በእውነት እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልህ::

  በዚህ በሱባዔ ሰዓት ስለ ቤተ ክርስቲያናችን አብዝተን እንጩህ::

  ReplyDelete
 21. እሌኒ ከሲራኪዩስAugust 12, 2010 at 7:36 AM

  + + +

  ቃለ ህይወት ያሰማልን!!! ዲ/ን ዳኒ፣ መፍትሔዎች ላይ እንድናተኩር የሚያደርግ መልዕክት ነው፦ የሚያንጸውም ችግር የሚፈታውም እንዲህ አይነቱ ነው:: ብንችል ሌሎችን አስነብበን ባንችል ግን እስኪ እኛው እራሱ የተሰነዘሩትን መፍትሔዎችን ከያዝነው ሱባዔ ጀምሮ ለመተግበር እንድንሞክር አምላክ ይርዳን! በተጨማሪም ቤ/ክንን ተጠግተው ያሉ ነዳያንን በተመለከተ እንደመፍትሔ፦ ምጽዋትን አስተባበሮ ጾም ሲያዝ ሲፈታ ወይም በበአል በቻ ሳይሆን በቋሚነት ምግበ ስጋ ምግበ ነፍስ የሚያገኙበትን አሰራር ብንቀይስ የብዙ አብያተ ክርስቲያናትን ህይወት እንታደጋለን

  ReplyDelete
 22. ዳኒ ልቤን አነሳሳሀው እኔስ ተስፉ ቆርጨ ነበር የሚገባኝን ለማድረግ እጥራለው

  ReplyDelete
 23. I am of the opinion that Government's involvement should be limited to demanding audit reports, further involvement will compromise the church's independence.Bekerews joro yalew mesmaten yisma, God bless you Dani!

  ReplyDelete
 24. አምደ ሚካኤልAugust 12, 2010 at 11:21 AM

  ቃለ ሕይወት ያሰማልን
  ዲ ዳን በእውነት አሁን እዳልኸው ለቤተክርስቲያን የሚያስፈልጋት ትንሣኤ ነው
  ግን ተሐድሶዎች በፊት በሰንበት ት/ቤት ነበር የተሰገሰጉት አሁን አሁን ደግሞ አባቶችንም ይዘዋል
  እኔም መፍትሔ የሚመጣው በመጸለይ ነው እላለሁ ነገር ግን ንጹህ ሕሊና ከየት ይምጣ?
  ሌላው እየተሸነፉ ማሸነፍ በሚለው መርሕ እስማማ ነበር።ይህም ፈጽሞ ጠፋ አሁን
  እውነቴነው የምለው የተሀድሶ ዓላማቸው እኔ ላይ ሰርቷል ማለት እችላለሁ
  ምክንያቱም አባቶቼን ሁሉ መጠራጠር ጀምሬአለሁ። በፊት በእየመንገዱ ቆብ ያደረገ መነኩሴ፣ ጥምጣሙን የጠመጠመ ቄስ ሳይ መስቀሉን ለመሳለም እርጥ የነበርሁት እኔ ዛሬ ግን ይህ ሁሉ እየጠፋ ነው።በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ኃጢዓት እየሰራሁ መሆኑን ይታወቀኛል።በእርግጥ ብዙ ክርስቲያኖች ሰዎችን መመልከት ትተዋል።አያገባኝም እንዳልል ቤተክርስቲያንን ለዘራፊዎች አሳልፎ መስጠት እንደማለት ነው። ለምሳሌ
  እኔ የማውቀው አንድ ሰው የአንድ ቤተክርስቲያን እስከ 500000(አምስትመቶ ሺ) ብር መብላቱን እናውቃለን
  ይህንን ስታይ አያስችልህም። በቤተክርስቲያኒቱ ገንዘብ ት/ቤት፣ፋረማሲ፣ዳቦቤት፣መኪና የገዛ አንድ ግለስብ አለ የሌሎቹን ብንዘረዝር ጉድ ትላላችሁ ስለዚህ እናት ቤተክርስቲያን ምን ያህል ሀብቷ እየተዘረፈ መሆኑን ማወቅ ይቻላል። እባችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናንና ምዕመናት ንጹሕ ህሊና ያላችሁ ጸልዩ እንላለን
  ጸልዩ በእንተ ሀዋሳ

  ReplyDelete
 25. ዘ ሐመረ ኖህAugust 12, 2010 at 12:29 PM

  የእግዚአብሔር ሠላም ከዳኒና ከሕዝበ ክርስቲያኑ ጋር ይሁን አሜን ዲ/ን ዳኒ ቃለ ሕይወት ያሰማልን እኔ በEyob G ሃሳብ በከፊል እስማማለሁ በርግጥ በቤተ ክህነት ካለው ንቅዘት ይልቅ በመንግስት ወሰጥ ያለው ንቅዘት በእጅጉ ይበልጣል በርግጥ የቆሸሸ ነገር በንጹሕ ውሃ ነው መታጠብ ያለበት ሆኖም መንግስት እነደ ዲ/ን ዳኒ ምስክርነት...ዳኒ ያለ በቂ መረጃ እንደ ማትጽፍ እምነቴ ስለሆነ...አጠቃላይ የመዋቅሩን ጽዳት ከቀበሌ ጀምሮ ከሆነ የአሰተዳደር ስራዎችን ማሻሻል ጀምሮ ከሆነ ቢ ፒ አርን መተግበር ጀምሮ ከሆነ በስልጠናና በሙያ ማሻሻያ በርግጥ ጥሩ የሆነ ለውጥ መታየት ከጀመረ ወይም ነቀዙ እራሱን በራሱ ሳይበላው በፊት መባነን ጀምሮ ከሆነ መንግስት ቤተክህነት ያላትን ሃገራዊ ጥቅም መጠበቅ ስላለበት የራሱን ድርሻ እንዲወጣ ማሳሰብ ተገቢ ነው ሁሉም ድርሻውን ይወጣ ለማለት ነው እንጂ ዋናው መፍትሄማ ከመንፈስ ቅዱስ መሆኑ ተሰውሮ አይደለም ችግሩን ለአባቶች መንገሩ ለቀባሪው አረዱት እንደሚባለው ቢሆንም ነገር ግን አባቶች ሥጋዊ ጥቅምን ትተው ከሕዝቡ ጋር መንፈሳዊ ተጋድሎ እንዲጋደሉ ተጽእኖ ማድረግ በመንፈሳዊ ተጋድሎ ያሉትንም አባቶችና ምእመናንንም ማገዝ የወቅቱ ግዴታ ነው በውጭ ያለው ሕዝበ ክርስቲያን እንደ ግብፅ ክርስቲያኖች በውጭ ያለውን መብት ተጠቅሞ አባቶቻችን ካልታረቃችሁልን እናንተም አትቀድሱም እኛም አናስቀድስም በማለት እግር ላይ መውደቅ ይኖርበታል በሃገር ቤት ይህንን መሞከር ሰይፍና ቆመጥ ሊያመጣ ቢችል እንኳ ከነብያት ከሐዋርያትና ከአባቶቻችን የተማርነውን ሰማእትነት መተግበር የግድ ነው ከተራ ምእመን ጀምሮ ከዲያቆናት ከቀሳውስት ከመነኮሳት ከባሕታዊ እስከ ብፁአን አባቶች ከሰበካ ጉባዔ እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠውን የዳኒን መፍትሄ በእጅጉ እስማማበታለሁ እንደዚሁም በዋናነት ከእንደኔ አይነቱ ጀምሮ ቲፎዞነትን ዘረኛነትን ጥላቻንና መለያየትን አስወግደንና ወደ ልባችን ተመልሰን በቅድሚያ ከራሳችን ጋር ከታረቅን በኋላ ከዚህ በፊት ለመግለጽ እንደ ሞከርኩት በሃገር ቤትም ሆነ በውጭ ያለውን ሕዝበ ክርስቲያን አስተባብረን ሱባዔ መያዝ ለመንገስት ለብፁአን አባቶችና ለሁሉም መባል ያለበት ከተባለ በኋላ ሁሉም የተባለውን ተቀብሎ እያንዳንዱ ወደ ጥሩ መፍትሄ ይመጣ ዘንድ እግዚአብሔርን ለፎርማሊቲ ሳይሆን በጽኑ ጾምና ጸሎት ማቅ ለብሰን አመድ ነስንሰን በለቅሶ መጠየቅ ይኖርብናል እግዚአብሔር ዲያቆን ዳኒንና መሰል ወንድሞችን ያቆይልን ያበርታልንም አሜን ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክበር

  ReplyDelete
 26. ዳኒ እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልህ! በአገልግሎት ያጽናህ! ይህን ትልቅ ሃሳብ ግን በብሎግ ላይ መቅረት የለበትም። እያንዳንዱ ለቤተክርስቲያኑ የሚቆረቆር ኦርቶዶክሳዊ ማንበብ ይገባዋል። ስለዚህ እባካችሁ አገር ቤት ያላችሁ ውድ የተዋህዶ ልጆች ይህንንና ባለፈው የወጣውን ጽሑፍ ለምዕመናን እንዲዳረስ አድርጉ። እያንዳንዱ ሰው 10 ኮፒ ቢያዘጋጅ ከዚያ ሁሉም ፎቶ ኮፒ እያደረገ ያነበዋል። ለሁሉም መዳረሱ ትልቅ ጥቅም አለው። ምክንያቱም አሁን ቤተክርስቲያን ያለችበትን ሁኔታ ሁሉም እኩል ከተረዳ ለመፍትሔው ዝግጁ ይሆናል። በተለይም በአንድ ልብ ሆነን ይህችን የተቀደሰች የጾም ወቅት በብዙ ምልጃ በትጋት ለማሳለፍ ጥሩ አጋጣሚ ነው። አቤቱ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ በአንድ ልጅህ በጌታችንና በአምላካችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በክቡር ደሙ የዋጀሃትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንህን ጠብቃት!!! እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ! በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ!

  ReplyDelete
 27. Very well stated. But this article is limited for few people, means people who have only this site access, not more than five hundred people. EOTC members are in million. Every EOTC members are responsible for those situations and have to bring some solution, so pls try to publish in news paper or something else. Yetenbitu mefetemia endanehon segahu...
  Dn. Daniel you are the only one stated the problem of our church officially to come up to the solution. God Bless you. I personally ask different people who are really attach to Betekehnet, but the respond is really sad. They all says, "Beserachew Egziabher yeteyekachew" To me those words doesn't make sense. People who really connection with "Patriarc" should let them know how people suffering with what is going on Betkehenet Aserar.Bless out heart! May God bless our religion

  ReplyDelete
 28. dani this is A+ solution for the big problem agin let those in top to read this.
  Mamo

  ReplyDelete
 29. Selam Wendmachn, melkamun huulu wed lebonachn yadrgeln yehnen tsehun end Egiziabher fekad lemawkachw Abew Papasat lemadrs Qale egbalhun! Berta Yetsenawn asbu Kemlew Sebkath tesnsh Chemerbet lemketlaw. Tsegawn yabzaleh

  ReplyDelete
 30. Most things are covered by Dn Dani. Here are my idea for the solution
  1. Let us first start from ourelves(Me'emenan). Let us stop judging on our fathers let approac them and suggest what we feel, what we think good is for our church. But when we approach them it should be with respect not fearness or afraid. Mekebaber tilik neger silehone sinikerareb andande menanak silemimeta we should be careful.so our approach should be with mutual respect.
  2. Let us forget our interest of leadership saying of this people that people should lead. Let us believe every one from any region or society who have the capacity to lead with the help of God can lead our church. Say always Egziabher yishomal egzibher yishiral. Sew bisiraw enji be maninetu animezinew. Kezih ayinet dinkurina astesaseb eniwta. this is our big problem.

  3. Those peoples who don't have enough knowledge of our church but who are stealing/robbing our church money by saying Aba, Bitsue, kidus...for our fathers(Abatochachin be mamogos bicha yeminoru), I mean those talkative we have to advice them otherwise if they keep doing such we have to resist them that is Kebetekiristiyanachin ageligilot eske mabarer bemikir kaltemelsu malete new.
  4. Wudase kentu kebetekiristiyanchin enatifa.

  Let us bring idea, solution instead of thanking Dn Dani only. Kentu wudase Lebetekiristiyanachim altekematim. Wendimachinim be kentu wudase endanitilew. It is doing what he sholud, have to do. We have to do the same we have a responsiblity.

  To be continued...

  ReplyDelete
 31. እንደተለመደው በጹሁፉ ጥበብ ተደስቻለሁ:: አስተዋይ በጠፋበት በእኔ ዘመን አንተን ያስነሳ እዚአብሔር ይመስገን:: "ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ ልብ ያለው ቢኖር ያስተውል" ነውና ሌላ ማለት አልፈልግም::

  ReplyDelete
 32. Kale Hiwot Yasemalen Dn. Daniel

  ReplyDelete
 33. I do appreciate the initiatives of the above comment.

  Please let us share ideas and pray to God to opt for best idea as God is solution for every thing.

  I guess everybody says pray and pray however we all forget about to say "subaea".

  The writer of the article is center for decision and generating idea and I call up on all readers to take a step towards solution and come up with new ideas.

  May God Bless the writer

  ReplyDelete
 34. የቅዱሳን አምላክ ይጠብቅህ ጸጋውን ያብዛልህ!

  በጠቅላላው ክምታነሳቸው ርእሰ ጉዳዮች ከምታወጣቸው ጽሁፎቸ ቢያንስ አንዱን ጉዳይ የሚፈጽም ሰው አይጠፋምና በርታ:: በሂደት ለቤተክርስቲያን ለውጥ ወይም ትንሳኤ እናመጣለን:: መፍትሄዎቹ ግሩም ናቸው::
  ሁላችንንም የተግባር ሰዎች ያድርገን::

  ReplyDelete
 35. ዲ/ን ዳንኤል፤

  በድጋሚ እግዚአብሔር ይስጥልን። በየራሳቸዉ የመፍትሄ ሀሳብ ባይሆኑም እንደአቅጣጫ ልንጠቀምባቸዉ የሚገቡ ሁለት ነጥቦችን ለመጠቆም ወደድሁ፦

  1. በዚህ ብሎግ ላይ እየታተሙ ያሉት የመፍትሄ ሀሳቦች የቤተክርስቲያን ልሳን በሆኑ መጽሔቶችና ጋዜጦች (ለምሳሌ ሐመር መጽሔት፣ ስምዓጽድቅ ጋዜጣ፣ መለከት መጽሔት) በተከታታይ ቢታተሙ በተሻለ መልኩ ምዕመናንንና አባቶችን ይደርሳል የሚል እምነት አለኝ። ለምሳሌ ብዙ ብጹዓን አባቶች እነዚህን ህትመቶች ያገኛሉ ብዬ አስባለሁ።

  2. የተነሱትን ችግሮችና የመፍትሔ ሀሳቦች ለሚመለከታቸዉ ለማስረጽ እንዲሁም ተጨማሪ ሀሳቦችን ለማግኘት እንዲረዳ በሀገር ቤትና በዉጭ አገር በየደረጃዉ ተከታታይ ወርክሾፖች (workshops) ቢዘጋጁ መልካም ይመስለኛል። እንዲህ ዓይነት ወርክሾፖችን ማዘጋጀት ቀላል ባይሆንም አጋጣሚዉ ከተገኘ ግን በተለይ ዲ/ን ዳንኤል እዚህ ያቀረባቸዉና ሌሎች ጥናታዊ ጽሁፎች ቢቀረቡ ቢያንስ አብዛኞቻችን ተመሳሳይ እይታ እንዲኖረንና ለሚቀርቡት የመፍትሔ ሐሳቦች ተመሳሳይ ምላሽ እንዲኖረን ያስችለናል።

  እስቲ እንበርታ፤ እግዚአብሔር ይርዳን።

  ReplyDelete
 36. Dear D.Daniel

  NO MORE BAIL OUT FOR CORRUPTED,GREEDY,SELFISH church leaders, Preachers,Zemaryan and Mahaberati.It is time to expose them, to replace them and move on with clean leaders.If u keep acting like they can be forgiven, wrong learn from the corrupted new-york wall street greedy people they buncrupt and destroy the country so in my eye some of our church leaders are not less than this dirty,selfish people.Sorry to be harash but that is the reality we live in unless u say leban laba kalalinew they will never get it.

  ReplyDelete
 37. ዳኒ መፍትሄ ብለህ ያስቀመጥካቸው ጥሩ ሀሳቦች ናቸው፡፡ከሁሉም ገንዘባችን የት ላይ መዋል እንዳለበት ሁላችንም ማስተዋል ይገባናል ቤተክርስቲያን ደሃ ስለሆነች አይደለም በገጠር ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በችግር የሚገኙት ሁላችንም የምናውቀው ጉዳይ ነው በከተማም ያሉ አባቶቻችን እራስ ወዳድ ሆኑ በክርስቶስ ወንድሞቻቸው የሆኑትን በገጠር የሚገኙትን እንዳያዩ ምን እንደጋረዳቸው እናውቃለን፡፡ስለዚህ ሁላችንም መንቃት አለብን የአብነት ትምህርት ቤቶች በትልቅ ችግር ውስጥ ነው ያሉት በዚህ ከቀጠለ በሚቀጥሉት ጥቂት አመታት ተተኪ አባቶችን እንደምናጣ ይታየኛል እባካችሁ ሀይላችንን ወደ ገጠሩ አብያተ ክርስቲያናት እና የአብነት ትምህርት ቤቶች እናድርግ የቀደሙት አባቶቻችን በግራኝ መሃመድ ሰልመው ቢሆን ኖሮ ዛሬ ሁላችንም እስላም ነበርን ነገር ግን ብዙዎቹ ሰማእትነትን ተቀብለው የቀሩትም በብዙ መከራ ውስጥ አልፈው ለኛ አቆዩልን እኛ ደግሞ ያለውን መጠበቅና ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ ይጠበቅብናል በዚህ ላይ አንድ ነገር መፍጠር አለብን ገንዘባችንን እንዴት በተገቢው ቦታ ላይ እናውለው???????????

  ReplyDelete
 38. dekon. dani egzabhere ybarki berta egzabhere haylihi yhune

  ReplyDelete
 39. yeminer sew betefabet yihin be makirebih egziabiher be mengistu ya sibih

  ene yemilew ahun yanesahewun le madireg ene bebekule be muyaye data base mazegagetim hone lela softwre mazegajet kechalku lelawum beye muyaw bideraji bekelalu listekakel yichilal


  ke Adama ehtiopia

  ReplyDelete
 40. "Egziabher zerin bayaskerlin noro ende sodomena endegemora betefan neber". You always disclose the truth, the standard, what is best for our religion, etc. Thank you and long live for you.

  Daniel, I have one thing to share with you: If you want better environment, then chenge yourself first (I know you are changed) then the people around you like your family, relatives, friends, etc. Additionally, tell them to change the thoughts of peoples around them....this will go until we can see better environment from our religion. If we give your money for those who is in need of help and told our close friends and family to do so; if we preach about the standard, the rule the structural transformation of BPR, what is the difference between the people who serve the religion and the religion, what should be protest and what should non be protest or accepted, what to do and what not to do, etc then we can get a better environment in our beloved religion. Therefore, it is the responsibility of you, me, and other follower who are longing to see the real Orthodox Thewahido of Ethiopia.

  Egziabher regim edme ena tena yistilin

  ReplyDelete
 41. “ቤተ ክህነቱ ይህንን እስኪያመጣጥን ድረስ እኛ ማመጣጠን አለብን፡፡ ለምንድን ነው ገንዘባችንን ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት፣ ለተጎዱ ገዳማት እና አድባራት፣ እንዲሁም ለተረሱት የአብነት ት/ቤቶች የማና ውለው? ለምንድን ነው ውጤት በሚያመጣበት ቦታ የማናፈስሰው? ተቀብለው አቡነ ዘበሰማያት ለሚደ ግሙ ምስኪን ካህናት ለምን አንሰጥም? ”
  እውነት ነው ዳኒ የአምስትም ሳንቲም ምጽዋት እና ኣስራት በኩራትም ቢሆን ለተወሰነ ጊዜ አዲስ አበባ ለሚገኙ አድባራት እንዳይሰጥ መስራትስ አይቻልም ወይ? እኔ ማድረግ ጀምሬአለሁ እቀጥላለሁም !!እናንተስ ምን ታስባላችሁ?
  ድንግል አትለይህ!! በርታ!!
  ዲምፕል

  ReplyDelete
 42. +++

  ስለእዉነት ለአስተዋለዉ በጣም አስተማሪ ነዉ:: ግን ልባችን ድንጋይ ስለሆነ አናስተዉለዉም:: እግዚአብሔር አንብበን ተቀብለን ልንሰራበት የሚያስችለን የመንፈስ ልብ ይስጠን::
  የእያንዳንዱ ምዕመናንና መዋቅር ድርሻ በዚህ ዘመን ለቤተክርስቲያን በጣም ያስፈልጋል::
  ፩ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት (ከአለና እየሰሩ ከሆነ)ቤተክርስቲያን የሰጠቻቸዉን ትክክለኛዉን አደራ መወጣት አለባቸዉ:: ሰማዕትነት ካስፈለገም ለሰማዕትነት መብቃት አለባቸዉ:: አባቶች ጳጳሳት ስለቀደስት ቤተክርስቲያን እና ስለ ቅዱሳን ተጋድሎ እያሰቡ ቢሰሩ የተሰየሙት በቀዱሳን ስምና አጽም ስለሆነ::
  ፪ ቤተክርስቲያን በደረጃ ያስቀመጠቻቸዉ ሰራተኛ በሙሉ ለስጋ ሳይሆን በእዉነት የደጋጎቹን አባቶች ተጋድሎ በማሰብ ቤተክርስቲያን ልናገለግል ዘንድ ይገባል::በታሪክ በስጋም በነፍስ እንዳንወቀስ::እንደ እነ ከሌ አታድርገኝ ብለን እንስራ::
  ፫ የአድባራት እና የገዳማት አስተዳዳሪዎች: ካህናት ዳቆናት ወዘት ለቤተክህነቱ ሳይሆን ለቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን እናገልግል
  ፬ የሰበካ ጉባዔ አስተዳደር በቃላ ዓዋዲዉ መሰረት ቤተክርስቲያን ቢያስተዳድሯት:: አጥቢያቸዉን ቢያስተካክሉ ሌላዉም ይማራል::
  ፭ ሰ/ት/ቤት ለቤተክርስቲያን ዘብ ቢቆምላት (እለት እለት የሚያስጨንቀኝ የአቢያተ ክርስቲያናት ጉዳይ ነዉ እንዳለዉ ቅ/ጳዉሎስ::አባላትን ማፍራት የቤተክርስቲያንና የሃገርን ችግር በማስጨበጥ ጭምር ነዉ::
  ፮ ሰባኪያን የቤተክርስቲያን ችግር እንደርዕስ አድርገዉ ማስተማር አለባቸዉ::የማያዉቀ እንዲያዉቅና የሚያዉቀዉም መፍትሄ እንዲሰጥ ለቤተክርስቲያን ዘብ እንዲቆም እንዲጸልይ ማሳወቅ::
  ፯ ማህበራት በችግሩ ዙሪያ በመወያየት መፍትሄ በመያዝ አባቶችን በተወካይ ማነጋገር በማህበር መጸለይ የተጎዱ ገዳማት እጣነ ጸሎት እንዲያደርሱ የቤተክርስቲያን ችግር መንገር ና እንዲጸልዩ ማስደረግ::
  ፰ ምዕመናን በአጥቢያቸዉ ስርዓት ሲጓደል ዝም አለማለት:: እግዚኦታ ማድረግ
  ፱ ማንኛዉ የቤተክርስቲያን አባላት በሃገር ዉስጥ በዉጭም ያሉት አሁን ትልቅ የተጋረጠ ችግር ቤተክርስቲያኗ እየወደቀች ስለሆነ በሚቻለዉ ሁሉ COMMUNICATION MEDIA በመጠቀም የወቅቱን የቤተክርስቲያን ችግር ማሳወቅ አለብን::ቤተክርስቲያንን እለት እለት እናስባት::ህይወታችን ነችና እንደህወታችን እናስብላት::
  ፲ መንግስት ዳር ቆሞ መመልከት የለበትም መንግስት ማለት ኢትዮጵያ :ኢትዮጵያ ማለት ደግሞ መንግስት ማለት ነዉ::የታሪክ ባለቤት የሆነች ቤተክርስቲያን ታሪኳ ሲጠፋ ዝም ማለት የለበትም::ግርግር ከመፈጠሩ በፊት ተወካይ ልኮ ችግሩን ማስፈታት አለበት እንደዉ አንዳንዶች የቤ/ያን ሰዎች መንግስት ከጎናችን ነዉ እናሳስራቸዉ አለን እናስደበድባቸዉ አለን ወዘተ የሚሉም አሉ እየተባለም ነዉ አተንዋል::ይህ ደግሞ መረጠኝ ለተባለዉ ህዝበ ጥሩ ስሜት አይሰጥም:: ሌላ አምስት ዓመት ቅርብ ነዉ:፡ ግርግር ሲፈጠር ብቻ በአንድ ወገን ማጎር ብቻ መሆን የለበትም::ስለዚህ መንግስት በትኩረት ሊፈትሸዉ ይገባል::

  ሁሉን የሚያይ የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ከመዋረድ ይጠብቅልን::

  ከዝዋይ

  ReplyDelete
 43. ዲምፕል-
  በሀሳብህ እስማማለሁ ነገር ግን ይህን ተግባራዊ ለማድረግና ውጤታማ ለመሆን በተቀናጀ መልኩ መስራት ይጠበቅብናል፡፡ለምሳሌ እንደ ማህበረ ቅዱሳን ያሉ በገጠር ያሉትን አብያተ ክርስቲያናትን እና የአብነት ት/ቤቶች መልሶ በማጠናከር ትልቅ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ ከጎናቸው ብንሰራ ለውጥ ማምጣት እንችላለን፡፡
  ብዙዎቻችሁ ዲያቆን ዳንኤል የጻፈውን በእውነት አንብባችሁ ተረድታችሁታል?አይመስለኝም ምንድነው ይሄ ሁሉ የምስጋና ጋጋታ የመፍትሄ ሃሳብ ተጠየቃችሁ ለዚህ መልስ ፈልጉ እንጂ ቃለ ህይወት ያሰማልን እድሜ ይስጥልን ምናምን፡ወንድማችን ከኛ ይሄንን ለመስማት አይደለም የቤተክርስቲያናችንን ችግር አውርተን ማለፍ መፍትሄ ስለማይሆን የራሱን ሀሳብ እንደ መንደርደርያ አስቀመጠልን፡ ሀሳብ አመንጩ አሊያም የተቀመጡትን ሀሳቦች እንዴት ወደስራ እንደምንለውጠው እንወያይ?እባካችሁ እንለወጥ ተራኪዎች ብቻ አንሁን፡፡፡፡፡፡፡፡

  ከላስ ቬጋስ

  ReplyDelete
 44. Contiued from yesterday..
  4 Wudase kentu matifat kebetekiristiyanachin. This mean we don't have to exaggerate things specially for church servants. We can give recognition for good things but it should not be too much For example when we say for one spititual Servant you are very good servant, No one is like you etc we are bringing him to obstacle. At that time he will feel as there is no like him. Mekurat, Ti'ebit ... bezan gize yijemiral. So let us stop wudase kentu.

  5 Giving Recognition for strong side and opposing/advicing weak side. If we always tell for a person his negative side only he can't accept our idea. First we have to start from his strong side then tell him his weak side. every person at least he will have one strong side. 100% can't do always bad things. So let us do the same to our fathers. For example there are some changes in terms of building school, construction, Clinics in Addis abeba hagere-sibket(Kidus-Gebriel school in bete-mengist, kidist silasse school in 4 killo, construction in Kidus Ragueland Ura'el, clinik in Lideta, and construction in menbere pipisna kidist mariya and Master lemastemar addis Hintsa 4 killo theology tesrto alkewal..) this good thing becoming independent financially so let us tell them first this are good things and to expand those thing to churchs in rural areas as well after that let us tell them the weak sides(For example Corruption, wegen tegninet, administration problem....) then they can improve their weak side. By mentioning only negative side(by talking always weak side) we can't bring a change. Ok Let us say we remove them from their power by saying like that but we are going to loose many likawunt. For example let us know how many thing we loos by the death of Megabe biluy Seyife silasse. The main thing is to advice and bring them to real service. I appreciate what Dn Dani proposed the solution. But don't say, Dn Dani peoples who approach for the fathers tell them. Why don't you become an example for us by telling them why don't you approach them? they are our fathers and your fathers as well why do u leave this assignmetns only to us. only writing here can't bring a solution. The main thing is to go in face and tell them their strong and weak sides. Kidus Yohannes metimik eko Le Chekagnu Nigus Herodse mote sayifera eko new betemengistu dires hido yewendimih mist litageba atichilim yalew. why don't we become like Kidus Yohannes with the help of God. Yihinnin sil gin lante le Dn Dani liwekse felige sayihon(Lemewukes akim yelegnim ene degmo man negn)but if you want to see in practice the solution what you propose go and tell them in face. For sure God will help you. Let all of us do like this.

  ReplyDelete
 45. 6. Training our Spiritual servant in Management, Accounting... Associations in our church (like Mahibere-Kidusan...) should involve in helping our church they don't have to work alone this associations. For example they can solve the problem of administration in our church by giving training for Spiritual Servants(Fathers, Deacon,..) like adminstration, Management, Accounting(Yehisab ayayaz)..To tell you the truth most our church leaders they don't know how to administer because they didn't learn secula education(Zemenawi timihirt), though some they have administration gift. they pass their life in learning ye abinet timihirt not zemenawi timihirt. So let us show them how to have long time Plan(For Example 5,10 years), how to lead... Due to administration problem in our church talkative persons have most powerful than educated peoples. Balefew Dn Dani endakerebew ye Betekiristiyan demoz yemibelut enesu nachew yemenager chilota yalachew yetemare ma tsomu new yemiydirew. Silezih Wuchi huno kemenkef kerben enamakirachew, yalen chilota enasayachew. Teleyayito bemesirat lewte simeta alayenim abro bemesirat enji. Mahiberat ye betekiristiyachin chigir lemekiref eske temesertu dires they have to work together with our fathers church. with the help of God everything is possible. Mesrat alichalinim eyetebale lebicha mesirat tilik sihitet new. ke abatoch ga begorit eyeteyayu eyetenekakefu mewal mader lewte aymetam lewti yemimate abro bemesrat, bewuyiyit new. Teb sinore mahiberatum sirachewin lemesrat kebad new yemihonew. Be Mahibere-kidusan eyedere yalew fetena metkes yichalal minim enquan fetenaw eyalefe mahiberu bizu sirawoch biseram neger gin ke abatoch ga beselm tefakiro bisera degmo yebelete yiseral biye amnalehu. Lelochum mahiberat endeza mehon alebet.
  To be continued..

  ReplyDelete
 46. Very well said,
  The issue requires a very detailed and calculated strategy. Information is a key. How many of us are on the same picture and understanding? I believe we have enough information to share in terms of our church existing problems, current problems, possible solutions and possible approaches. We pretty much know the audience- this writing helps us to see people in different roles and responsibilities. Now, what we need is how to disseminate this information. This project seems a long term and ongoing project. I don’t see a quick and easy solution in the short term. I don’t think this should be done by a specific group of people but believe that should be lead by specific people of course. The internet media serves only a limited number of people. To me these should be the steps to go forward:
  1. Who should be the audience?
  2. What is the information we would like to deliver and educated people?
  3. Multiple Dissemination media options
  4. Start educate people and disseminate information
  5. Study and develop strategies in parallel

  ReplyDelete
 47. and yalgebagn neger "yewerq qulf" yemilew new:: Diro katolikochu yisheTut yeneberew new weyis lela? yegebaw kale biasredagn::

  Kale Hywet yasemaln

  ReplyDelete
 48. "Yewereq qulf" = money

  ReplyDelete
 49. dani lemin enezihin begenzeb liredu yigebalu yemitilachewn akalat merejawochin atakebilenm egnam yebekulachinin endinareg hunetawochin bimechachu harif yimeslegnal...abizagnaw sew min ayinet info silelelew new negerochin hulu addis ababa lay yemiyaregew...thanx

  ReplyDelete
 50. selam lekemu ejeg betam teru hasab yedelewo beyalehu m ke abu dhabi

  ReplyDelete
 51. biruk alemayehu (doni)August 14, 2010 at 11:13 PM

  dani it is a good idea! I completly agree with you. keep it up !

  ReplyDelete
 52. very nice solutions
  God Bless you Dn. Daniel
  after reading part 1 and part 2 as an ordinary church member i will try to implement the solution number 1,2,8,& 17 to be a part of a solution.
  God Bless our Tewahedo Church

  ReplyDelete
 53. Exactly!!! I am really touched with the last few sentences.."ለምንድን ነው ገንዘባችንን ለገጠር አብያተ ክርስቲያናት፣ ለተጎዱ ገዳማት እና አድባራት፣ እንዲሁም ለተረሱት የአብነት ት/ቤቶች የማና ውለው? ለምንድን ነው ውጤት በሚያመጣበት ቦታ የማናፈስሰው? ተቀብለው አቡነ ዘበሰማያት ለሚደ ግሙ ምስኪን ካህናት ለምን አንሰጥም? "
  ለምንድን ነው? ለምንድን ነው? ለምንድን ነው? That every one of us shall answer.

  Bless you Daniel!

  ReplyDelete
 54. Money that is solicited to help poor churches and their servants and would be servants of our church is used to build a luxurous office building! Sorry to say but it is not only wrong, it is also SIN! Where millions of children are orphaned,where those who served their church beg in the streets,traditional church schools closed,hermites displaced because of hunger,etc building a luxurous office where it is going to cost more for utility,furniture,salary for employee,etc,is SIN in deed!
  So who do we trust to work for our church? NOBODY.

  ReplyDelete
 55. ለሁሉም አምላክ ይርዳን እራሳችንን ዝቅ እንድናደርግ
  ሰው እራሱን ዝቅ አድርጎ ለአምላኩ ከተገዛ ዲያብሎስን ድል ያደርጋልና

  ReplyDelete
 56. besimeab weweld wemenfes kidus ahadu amlak amen!
  memihir daniel, ur ideas are realy nice.but peoples are giving too much misgana...please dont give it attention!...god will pay u for all this!
  tsegawin yabzalih

  ReplyDelete