ግሪኮች እንዲህ ይላሉ፡፡
በድሮ ዘመን የአቴና ሰዎች መልካም መሪዎችን በማጣታቸው ምክንያት ይማረሩ ነበር፡፡ አንድ ቀን ወደ ኦሊምፐስ ተራራ ወጥተው የአማልክት ንጒሥ የሆነውን ዜውስን ለመኑት፡፡ «እባክህ ከመንደራችን እስከ ሀገራችን ድረስ ባሉት ቦታዎች በመልካም የሚያስተዳድሩ መሪዎችን ስጠን» አሉት፡፡ ዜውስም «ፊንቄያውያን መጥተው ይግዟችሁን?» ሲል ጠየቃቸው አቴናውያንም «አንፈልግም» አሉ፡፡ «ካርታጎዎች መጥተው ይግዟችሁን?» አላቸው ዜውስ አሁንም «በቅኝ መገዛት አንፈልግም» አሉ፡፡ እንደገናም «ሮማውያንን አምጥቼ በላያችሁ ልሹምባችሁን?» ሲል ጠየቃቸው፡፡ አቴናውያን በዚህም ሊስማሙ አልቻሉም፡፡
ዜውስ ባቢሎናውያንን፣ ፋርሶችን፣ ኬጢያውያንን እና ጢሮሳውያንን አምጥቶ በአቴና አውራጃዎች ለመሾም ፈቃዳቸውን ጠየቃቸው፡፡ አቴናውያን ግን ፈጽሞ አይሆንም አሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ዜውስ «ታድያ ከየት አምጥቼ ነው መልካም መሪዎችን የምሰጣችሁ?» ሲል ጠየቃቸው፡፡ «ከመካከላችን ስጠን» ብለው መለሱለት፡፡ በዚህ ጊዜ ዜውስ አዝኖ እንዲህ አላቸው፡፡ «ጥሩ በሬ ለማግኘት ጥሩ ጥጃ፣ ጥሩ ጠቦትም ለማግኘት ጥሩ ግልገል፣ ጥሩ ወፍ ለማግኘት ጥሩ ጫጩት፣ ጥሩ ዶሮም ለማግኘት ጥሩ ዕንቁላል ያስፈልጋል፡፡ እናንተ በመልካም ያላሳደጋችኋቸውን ልጆች እኔ እንዴት አድርጌ በመልካም እሾማቸዋለሁ፡፡ እኔ ሰውን ፈጠርኩ፤ መሪዎቻችሁን ግን እናንተ ፍጠሩ፡፡»
መሪን ማን ይፈጥረዋል?
ፓርቲ? ድርጅት? ትግል? ሰላማዊ ሰልፍ? ንግግር? ምርጫ? ወይስ ሌላ? እንደ ዜውስ ምክር ከሆነ ሕዝብን አምላክ፣ መሪን ግን ሕዝብ ይፈጥረዋል፡፡ መሪዎች የሕዝቡ ሥዕሎች ናቸው፡፡ ከተወለዱበት ቀን እስከ ተሾሙበት ቀን ድረስ በማኅበረሰቡ መካከል ሲኖሩ ሕዝቡ በአንድም በሌላም መልኩ የሳለባቸውን ሥዕል ነው በሥልጣን ወንበር ላይ ሆነው የሚያሳዩን፡፡
መሪዎቻችን የተረቶቻችን፣ የዘፈኖቻችን፣ የአባባሎቻችን፣ የእምነቶቻችን፣ አመለካከቶቻችን፣ የአኗኗራችን የአበላላችን እና የአጠጣጣችን ውጤቶች ናቸው፡፡
ወላጅ ሳሎን ሲመገብ ጓዳ ውስጥ ግቡ ይባሉ ከነበሩ ልጆች ግልጽነትን መጠበቅ፣ ከወላ ጆቻቸው ጋር በአንድም ጉዳይ ሳይወያዩ እና በሃሳብ ልዕልና ለውሳኔ ሳይበቁ ከሚያድጉ ልጆች ተወያይቶ መግባባትን እና ከኃይል እና ከሥልጣን ይልቅ በሃሳብ ልዕልና መተ ማመንን መጠበቅ፣ ልጅ እና ፊት አይበርደውም እየተባሉ ከሚያድጉ ልጆች መካከል የሕፃናትን መብት የሚያከብሩ መሪዎች መመኘት፤
ወላጆቻቸው ችግሮቻቸውን ተነጋግረው፣ተከራክረው እና ጊዜ ወስደው ከመፍታት ይልቅ በትንሽ በትልቁ ሲደባደቡ እና ሲፋቱ እያዩ ካደጉ ልጆች መካከል የክርክር እና የውይይት ባሕል ያለው፣ ልዩነቱን አቻችሎ የሚኖር፣ ጊዜ ወስዶ ችግሮችን የሚፈታ እና በትንሽ በትልቁ ፓርቲውን ጥሎ የማይወጣ መሪ መጠበቅ፣ ሴቷ ልጅ በቤት ሥራ ስትዳፋ እያየ እርሱ ሲራገጥ ከሚውል ልጅ መካከል የጾታ እኩልነትን የሚያሰፍን መሪ መሻት፣ ከየቢሮው እና ከየፋብሪካው፣ ከመንግሥት ካዝና እና ከቤተ እምነት ሙዳየ ምጽዋት፣ ከግብር እና ከቀረጥ፣ በተመነተፈ ገንዘብ ከሚያድግ ልጅ መካከል የሀገሩን ገንዘብ የማይበላ መሪ መፈለግ፣
በቤተሰቡ መካከል በሚነገሩ አባባሎች እና ተረቶች፣ ስድቦች እና ርግማኖች አንዱ ብሔረሰብ ከሌላው ተለይቶ ሲሳቅበት እና ሲቀለድበት፣ሲተረትበት እና ሲሾፍበት፣ ሲናቅ እና ሲንቋሸሽ እየሰማ ያደገን ልጅ አድገህ የብሔር ብሔረሰቦችን እኩልነት የምታሰፍን መሪ ሁን ብሎ ያለ ዐቅሙ ማሸከም፣ አስተማሪውን እያንጓጠጠ፣ እየተደባደበ እና በትምህርት ሰዓቱ እየቀለደ የሚያድግን ልጅ ማይምነትን ከሀገር የምታጠፋ መሪ ሁን ማለት፣
ታናናሽ ወንድሞቹን እና እኅቶቹን እያንቆራጠጠ፣ የሠፈር ሴቶችን መቆሚያ መቀመጫ እያሳጣ፣ ለምን ቀና ብላችሁ አያችሁኝ ብሎ የሸሚዙን እጅጌ እየሰበሰበ ያደገን ልጅ ዴሞክራሲያዊ መሪ እንዲሆን መመኘት ያልዘሩትን ማጨድ ነው፡፡
በሀገራችን ጀግንነት ስለሚደነቅ፣ ጀግናም ስለሚከበር፣አንበሳ እና አጋዝን፣ ነብር እና ዝሆን መግደል ስለሚያሸልም፣ በባሕላዊው ትምህርት ፈረስ ጉግስ እና ጦር ውርወራ፣ ሽመል ስንዘራ እና ጋሻ ምከታ፣ ውኃ ዋና እና ዝላይ ከልጅነት ጀምሮ ይሰጥ ስለነበር ሀገራችን አያሌ የጦር ሜዳ ጀግኖችን አፍርታለች፡፡ በጠላት ላይ አስደናቂ ድል የሚቀዳጁ፣ ድንበራቸውን ለአፍታም የማያስደፍሩ፣ ጀግንነት ከነጭ እና ቀይ የደም ሴላቸው ጋር ሦስተኛ ሕዋስ የሆነላቸው አርበኞችን አፍርታለች፡፡
ነገር ግን የአመራር፣ የአስተዳደር እና የአሠራር ጀግኖችን፣ የዴሞክራሲ እና የሰብአዊ መብት ጀግኖችን፣ የክርክር እና የውይይት ጀግኖችን ገና አላፈራችም፡፡ የመቻቻል አና የመደማመጥ፣ ተቃራኒን ሃሳብ፣ የማንደሰትበትን ውሳኔ፣ የምንጠላውን አመለካከት እንደ በጎ የሚቀበሉ መሪዎችን ገና አላገኘችም፡፡ አንድ ሰው እንዳለው «ኮምፒውተሩ ባልተጫነበት ሶፍት ዌር ሊሠራ አይችልም»፡፡
ለመሆኑ፤ ከሠፈር እድር እስከ ቤተ መንግሥት፣ ከቀበሌ እስከ ፓርላማ፣ ከአንደኛ ክፍል እስከ ዩኒቨርሲቲ ኢትዮጵያ የምትፈልጋቸውን ዓይነት መሪዎች ለማፍራት የሚያስችል ዘፈን፣ ተረት፣ አባባል፣ ጨዋታ፣ ብሂል፣ ወግ፣ ባሕል፣ ሥርዓት አለንን? እንደ ኢትዮጵያ ባለች ሚዲያ እና ንባብ፣ ትምህርት እና ለዘመናዊ ሥልጣኔ መጋለጥ ውሱን በሆነባት ሀገር፤ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜያቸውን ከአካባቢያዊ ባሕላቸው እና ወጋቸው ጋር ነው በሚያሳልፉባት፤ ካነበቡት መጽሐፍ የሰሙት ተረት፣ ከተማሩት ትምህርት የበሉት ድግስ፣ ከተከታተሉት ሚዲያ የዋሉበት ጨዋታ፣ ካገኙት ሥልጠና ያመሹበት የልቅሶ ድንኳን በሚበዛበት ማኅበረሰብ ውስጥ፤ ኅብረተሰቡ የሚፈልጋቸውን መሪዎች ለመፍጠር የሚያስችል ባሕል አለውን?
አባቱ አንድም ቀን ጋዜጣ ሲያነብ ያላየው፣ እንዲያነብም ያላደረገው፣ በቤታቸው ውስጥ ከትምህርት መጻሕፍት በቀር ሌላ መጽሐፍ ሲገዛ አይተው የማያውቁ፣ እናቶች ከብበው ቡና ላይ፣ አባቶች ከበበው ጠጅ ቤት እና ልቅሶ ቤት ሲያውካኩ እንጂ መጽሐፍ ሲያነብቡ፣ ባነበቡት እና በተረዱት ነገርም ሲከራከሩ ያልሰማን ልጅ፣ ነገ አድጎ ስለ ፕሬስ ነጻነት ዘብ ይቆማል የሚለው ማን ደፋር ነው?
ስሞቻችን እንኳን «በለው ፣ቁረጠው፣ ፍለጠው፣ አንቆራጥጠው፣ ግዛቸው፣ ዋኝባቸው»፣ በሆኑበት ሀገር፣ መሪነትን ሲያስብ ጉልበትን የማያስብ መሪ ከየት እናመጣለን?
ቤተሰቦቻችን፣ እድሮቻችን፣ ዕቁቦቻችን፣ የትምህርት ክፍሎቻችን፣ የጽዋ ማኅበሮቻችን፣ ሰንበቴዎቻችን፣ መጅሊሶቻችን፣የእምነት ተቋሞቻችን፣ የወጣት እና የሴት ማኅበሮቻችን፣ የሞያ እና የሲቪክ ማኅበሮቻችን፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶቻችን፣ ምን ዓይነት መሪዎች አሏቸው? ስለ ፓርላማው እና ስለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ስለ ካቢኔው እና ስለ ምክር ቤቱ ከመነጋገራችን በፊት በዕለት ተዕለት ኑሮአችን ታላቁን ቦታ ስለ ሚይዙት ስለ እነዚህ ተቋማት አሠራር፣ አመራር፣ የመሪዎች አመራረጥ፣ ድምጽ አሰጣጥ እስኪ እንነጋገር፡፡
ለመሆኑ በዕድር እና በዕቁብ የምረጡኝ ዘመቻ አለ? በየትምህርት ቤቱ የክፍል ኃላፊን ስም ጠሪ መምህር ይመርጠዋል፣ ወይስ ሃሳቡን አቅርቦ ብትመርጡኝ ለክፍላችን እንዲህ እና እንዲያ አደርጋለሁ ብሎ ተማሪው ይመርጠዋል? ለመሆኑስ በክፍል ኃላፊ ምርጫ ተማሪዎች በኮሮጆ ውስጥ ድምጽ ይሰጣሉ? በእድር እና በዕቁብ ሊቀመንበር እና ሰብሳቢ ምርጫ ጊዜ ድምጽ እንዴት ነው የሚሰጠው፣ ምርጫው ዲሞክራሲያዊ፣ ግልጽ እና የማይጭበረበር ነው?
የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች፣ ዲኖች፣ የዲፓርትመንት ሊቃነ መናብርት ሃሳባቸውን አቅርበው፣ ምረጡን ብለው፣ ተወዳድረው፣ የምረጡን ዘመቻ አድርገው፣ ተከራክረው በድምጽ አሰጣጥ ሥርዓት ተመርጠው የሚመሩበት ዘመን መቼ ነው የሚመጣው? ተማሪዎችስ የተማሪ ምክር ቤቶችን መሪዎች፣ የፓርላማ አባላት በሚመረጡበት ሥርዓት የሚመርጡት እና ለወደፊቱ የፖለቲካ እና የመሪነት ሕይወታቸው ልምድ የሚቀስሙት መቼ ነው?
ታድያ እነዚህን ሁሉ እንደዋዛ ዘልለን የሀገር መሪ ከየት እናገኛለን፡፡ ዜውስ እንዳለው እኛ ያልፈጠርነውን መሪ ፈጣሪ ከየት ያመጣዋል? ከአፍሪካ? ከአውሮፓ? ከአሜሪካ? ከቻይና? ወይስ ከላቲን አሜሪካ? ለምን መንደራችንን በተገቢው መንገድ ከማስተዳደር አንጀምርም፡፡ በኮንዶሚኒየም ሕንፃዎች፣ በሪል እስቴት መንደሮች፣ በአፓርትመንቶች፣ ግልጽ ምርጫን፣ አንዳች የለውጥ ዕቅድ ይዞ ተመርጦ መሥራትን፣ በየጊዜው ሪፖርት ማድረግን፣ ተሰብስበን ሥራን መገምገምን፣ በሚገባ የሠራውን መሸለምን፣ በሚሰጠን አካባቢያዊ ኃላፊነት ያለ ቸልታ ማገልገልን ለምን እንጀምረውም? መሪዎችን ለምን አንፈጥርም? መሪነት ፓርላማ ከገቡ፣ ከተሾሙ እና ሥልጣን ከያዙ በኋላ እንዴት ይጀመራል? ሰዎች እየመሩ ቆይተው ወደ ሥልጣን መምጣት አለባቸው እንጂ ወደ ሥልጣን መጥተው መሪነትን መማር የለባቸውም፡፡
የዕድሩ ሙሴ ከተመረጡ ስንት ጊዜያቸው ነው? ሥልጣናቸውስ ገደብ አለው? የዕቁቡ ዳኛ ለስንት ዓመት ነው በዓመት አንድ ዕጣ በነፃ እየበሉ የሚኖሩት? የሥልጣናቸው ገደብ እስከ መቼ ነው? የሰበካ ጉባኤው ምክትል ሊቀ መንበር፣ የአካባቢው መጅሊስ ሊቀ መንበር፣ የወጣቶች ማኅበር ሰብሳቢው፣ የሴቶች ማኅበር ሊቀ መንበር፣ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት፣ የኮሚኒቲው ሰብሳቢ፣ የቦርዱ ሊቀ መንበር፣ የኮሚቴው ሊቀ መንበር፣ የክለቡ ፕሬዚዳንት፣ የድርጅቱ ፕሬዚዳንት፣ የሥልጣናቸው ገደብ ይታወቃል? እዚያ ቦታስ ከተቀመጡ ስንት ጊዜ ሆናቸው? የሚተካቸው ሰው ስላጡ ነው? እርሳቸው ተቀብተው ነው የተቀመጡት? ለመሆኑስ እንዴት እንደሚቆዩ እያሰቡ ነው የሚኖሩት ወይስ ጥሩ ሥራ ሠርተው እንዴት ለሌላው እንደ ሚያስረክቡ? ታድያ በጊዜ ገደብ ሥልጣን ላይ የሚወጡ፣ ጊዜያቸው ሲደርስ ሪፖርታቸውን አቅርበውና የሚገባቸውን ሠርተው ወንበራቸውን ለሌላው የሚያስረክቡ መሪዎች ከየት ነው የምናገኘው? ከመካከላችን ያልፈጠርናቸውን ከየት እናስመጣ?
ኑ በየአካባቢያችን የነገ መሪዎቻችንን እንፍጠር፡፡ ሕዝብ ነው መሪውን በአርአያው እና በአምሳሉ የሚፈጥረው፡፡ መሪ በአንድ ቀን ምርጫ፣ በአንድ ሰሞን ንግግር አይፈጠርም፤ መሪ በሂደት የሚገኝ ነው፡፡ ባሕሩ ያልያዘውን ዐሣ መረቡ አያጠምደውም፡፡ ኩርንችት ተዘርቶ በለስ፣ እሾህ ተዘርቶም ወይን የሚያበቅል መሬት የለም፡፡
I agree with this Idea 100%, Dani really u are good thinker... u see every thing from different side...thank u very much God bless u
ReplyDeletelet's start simply from our home & our family.
ReplyDeletegood analysis Daniel.
የጸና አቋም ይኑረን፤
ReplyDeleteጣት መጠቋቆሙ፣
ምንድነዉ ትርጉሙ፣
የአቋም መግለጫ፣
ራስን ማጋለጫ፣
በሌላዉ ማላገጫ።
ኸረ አባቶች ሆይ፦
ራሳችሁን መርምሩ፣
መስቀሉን አክብሩ፣
በወንጌል ተመሩ፣
የመንፈስ ፍሬ አፍሩ፣
ጌታችሁን ምሰሉ፣
ካባ አታቅልሉ።
ኸረ እንጠንቀቅ፣
ቦታችንን እንወቅ፣
መንጋ እንዳይበተን፣
የጸና አቋም ይኑረን።
ከብሪታንያ
Hi dani, This is what I told you the other day. Write on this kind of issues man. Issues that can change our society's attitude. I really like it, like it and like it. Egzer tsegawun yichemirlih, as I always say. I've read all your articles and love most of them.
ReplyDeleteYe zewotir anbabih negn, ke USA.
ጥሩ ዕይታ ነው ዲ/ ዳንኤል የሃይማኖት መሪዎችንም በዚሁ መንገድ ነው መፍጠር የምንችለው::ጸጋ ዘአብና እግዚእ ሐረያ ናቸው አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ያስገኙት ከእሾህ በለስ አይለቀምምና
ReplyDeleteWhat a fantastic idea, txs Dani.God bless u.
ReplyDeleteThe Issue raised is not only for those who live at home but also to those who are living abroad and thinking that they are out of this mess up. Since they are creating new generation which doesn't know about it's own culture, language, social problems and Identity.So they are creating another problem. So let's try to creat Men and Women. I'm trying to follow you as much as possible elder brother. May God be with you...
ReplyDeleteTanshu Wondimih
The Issue raised is not only for those who live at home but also to those who are living abroad and thinking that they are out of this mess up. Since they are creating new generation which doesn't know about it's own culture, language, social problems and Identity.So they are creating another problem. So let's try to creat Men and Women. I'm trying to follow you as much as possible elder brother. May God be with you...
ReplyDeleteTanashu Wondimih
The Issue raised is not only for those who live at home but also to those who are living abroad and thinking that they are out of this mess up. Since they are creating new generation which doesn't know about it's own culture, language, social problems and Identity.So they are creating another problem. So let's try to creat Men and Women. I'm trying to follow you as much as possible elder brother. May God be with you...
ReplyDeletetanashu wondimih
Kale Hiwot Yasemalen Dn, Daniel
ReplyDeleteIt is an interesting article.So often most of us practise what we criticize to have been not right.Keep it up the good work.
ReplyDeleteit is wonderfull idea and view. what i understood from your idea is that i myself need to behave myself so as pave the way for good leaders and to develope tolerance for differnces.definately , with God willings and help, i will teach my children the wisdom of respect and tolerance an secretes of unity.
ReplyDeleteIt is amizing!!!!
ReplyDeletewowwwww
ReplyDelete' Egizihabiher tena, selam ena edime yistih'. I Thank you so much. Keep it up!!! Really good job which tells more than what it is!!!
ReplyDeleteCompletely an excellent opinion and truth, but Dn. Daneil, to tell the truth is not worth for Ethiopian's because we don't want to hear the truth. God bless your brain, I wish Ethiopia have few like you, a light through the long tunnel.
ReplyDelete...ኑ እንፍጠር...
ReplyDeleteበጣም ጥሩ ሃሳብ ነው።
ReplyDeleteዐርከ መሐይምናን መስተናግር ለጻድቃን ወማኅደር ለንጹሐን
ወለእለ በጽድቅ ይጼውዕዎ ሰማኢ ለመበለት ከዳኒ ወበላሒ
ለእጓለ ማውታ ዘይሁብ መርሐ ርቱዓ ለቤተክርስቲያን
very inspiring observation, and can't help but self reflect. I heard the saying from BBC scientific documentary "give me a child for 5 years and i will give you a man". what we do today determines the very fate of the next generation that is to take over their country. This is the best bet we have for our country; giving the most of love, respect, honor, tolerance to each other, and passion for country
ReplyDeletethank you for the provoking observation
Fikru
wonderful idea!!!
ReplyDeletelet us ready for change.let us develop positive thinking.
ዺ/ን ዳንኤል ሰላም ላንተ ይሁን።
ReplyDeleteእንዲህ አይነቱ እይታ ሁላችንም ግንባር ላይ ካለው የስጋ እይን አይደለም። በውስጥ ካለውና በግብሩ በፍሬው እንጂ ፊት ለፊት በማየት ከማይታወቀው ዓይነ ልቦና ነው። እግዚአብሔር አምላክ ጨምሮ፣ ጨምሮ፣ ጨምሮ ብሩህ ያድርግልህ።
ቸር ያሰማን።
dani you see this things not only from different angel you see the from the bottom to the top you have a great mind.
ReplyDeleteMamo
It is not too late still to teach ourselves and our kids to be benevolent leaders but not dictators of any sort.
ReplyDeleteደፈርከኝ፡አትበለኝና፡በመጀመሪያ፡ደረጃ፡የዲያቢሎስ፡ወገኖች፡በሆኑ፡ በጣኦት፡አማልክት፡ማለት፡ዜውስ፡አርጤምስ፡...ወዘተ፡ምሳሌ፡መስጠት፣ትምህርት፡ማስተማር፡ካንድ፡ክርስትያን፡አስተማሪ፡የሚጠበቅ
ReplyDeleteአይደለም፡፡ሁለተኛ፡ደግሞ፡በፅሁፉ፡የተጠቀሰው፡
1-እኔ ሰውን ፈጠርኩ፤ መሪዎቻችሁን ግን እናንተ ፍጠሩ፡፡»
2-እንደ ዜውስ ምክር ከሆነ ሕዝብን አምላክ፣ መሪን ግን ሕዝብ ይፈጥረዋል፡፡
ለእኔ፡እንደገባኝ፡ዜውስ፡በፈጣሪ፡መልክ፡እንደተቀመጠ፡ነው፡፡
እንደዚህ፡አይነቱ፡ትምህርት፡ወይም፡ምሳሌ፡በየትኛውም፡መንገድ፡ ባአለማዊ፡ሆነ፡በመንፈሳዊ፡ወደ፡ክህደት፡የሚመራ፡ነው፡፡ባስተያየት፡አሰጣጡ፡ላይ፡እንደሚታየው፡ብዙው፡ሰው፡የዜውስን፡ማንነት፡ የተገነዘበው፡አይመስለኝም፡፡
አደራ፡እናስብበት፡ቢስተካከል፡ጥሩ፡ነው፡፡
Dani betam tigermaleh egziabeher lehulum tsega setetwal yante degmo leyet yilal tileku neger mesetetu bicha sayehon metekemum neew ,tsegachewen ketetekemubet tekit sewoch mehal bikotereh maganen endayehonebegn.bihonem gin lezich betekerestian yemikorekoru bizu asabiwoch binorum endezih kemyategeb meles gar makreb eyakatachew bezuwoch jemerew bemnged kertewal silezih yeh yante menged gin betam betam des yasegal berta...bemcheresha enefelegehalen tetenekek yaluten anbabi hasab enem selemegaraw Dingel maryam tetebekeh elalehu ke UAE (ABU DHABI)NEEW CHER ENESENBET
ReplyDeleteDear Ato 'Mahibere kristian':
ReplyDeleteThis article he (Dn Daniel) used (in blue) is just an example to forward his main message. It is not meant to be read and taken literally. Get it? Don't jump to conclusions ! if u understood the message , don't think others are unable to (give us some credit). I understood it, may be tell us if u didn't...
God bless,
Ankiro
By the name of God of all!
ReplyDeleteDear dani
በሮሜ 13 ቁጥር 1 ጋር ተምታታብኝ፡፡ስልጣን ከአምላክ እንደሆነ ማንኛውም ባለስልጣን ከአምላክ እንደሆነ በግልጽ አስቀምጦታል፡፡ይህ ነገር እንዴት አየሀው?ከሃሳብህ ጋር አይጋጭም?ምናልባት እኛ የምንጠብቀው ሰው ያስተማረውን ሊሆን ይችላል፡፡ሚያስፈልገንን ግን አምላክ ያስተማረው እንደ ዳዊት ያለ አምላክ በራሱ መንገድ ያስተማረው ነው፡፡ምንም እንኳን ሃሳቡ ልጆቻችን በመልካም ስነምግባር ማሳደግ ለራቸው ለህዝብ ለአገር የሚጠቅሙ ሰለሆኑ አስተዳደግ ላይ መስራት እንደሚገባን በሌላ ገፁ ቢገልፅም፡፡ እኛ ስራ ፈታን እንጂ እምላክስ 7000 ለጣኦት ያልሰገዱ አዘጋጅቻለሁ እንዳለው ለኤልያስ አሁንም አምላክ አገራቸው መምራት የሚችሉ ቢያንስ እኳ ከ60000000 ቢያንስ አንድ ያስተምራል፡፡ያለተማርነው ግን እኛ ነን ለመሮዎቻችን አልተመቸንም፡፡
ውድ ዲን. ዳንኤል
ReplyDeleteሠላም ላንተና ለአጋዦችህ በሙሉ ይሁን
ጥሩ ግምት ያለው አቀራረብ ነው ግን አንድ የግል ሃሳብ ልጠቁምህ:: ሥራዎችህ በሂስ ብቻ እንዳይቀሩና ወደፊትም በተግባር ታይተው ለፍሬ የሚበቁበትን መንገድ በደንብ ብታስብባቸው መልካም ነው::
ሌላው ዳኒ አንዳንድ አስተያየቶችን ቀለል አድርገህ አትለፋቸው:: ለምሳሌ በዚህ አርዕስት ላይ “ማኅበረ ክርስቲያን” የጠየቀህ ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ የሚፈልግ ነበረ:: እኔም ይህንን የምልህ ያለምክንያት አይደለም-ብዙ ጊዜ ከመድረክ የሚታዩ ሰዎች “ከዓይን ያውጣህ” የሚባል የሀገራችን የተለምዶ አባባል ስላለ ነው ::
ስለሁሉም ግን እማምላክ ካንተ ጋር ትሁን በርታ በማንኛውም መልኩ እንረዳሃለን እላለሁ
ታናሽህ ከሮማ
Dear Mr. 'Mahibere kristian".
ReplyDeleteJust read between the lines.I guess I did not understand the concept of the article.
You don't have to read to criticize and Just read and understand it, then positive criticisms will follow.
I ,too,indeed know what you are trying to point out. I kindly invite you to read the article once again.
May God bless all of us.
Dn. Daniel Egziabher birtatun yisteh.
ReplyDeleteI appreciate Mahibere christian's comment as well as the article. Because be'antsaru'amen amen' yemil anbabi(yeshimdeda temari) endayifeter madreg yemigeba ymeslegnalna new. Bemehonum "hulum akababiwen biyatseda ketemachin titsedalech" endemibalew yale neger new.
Kale hiwot yasemalen.
tanks dani! I read this letreture befor one year in ADDISS NEGER news.
ReplyDeleteSomehow I agree with your idea. But I don't think this idea include all innocent Ethiopian. I take this as ignoring and insulting those innocent Ethiopian. because you are dealing with the country as the whole. Let say Ethiopian peoples are what you said. by the same concept think of all leads of the world and there people. Are all those Leads all are from good peoples???? Any way even though your idea have some facts I don't think your article expresses the reality of our country.
ReplyDeleteOne has to ask why we are backward. The answer is as lucid as Daniel agreeably stated because we have backward culture. We have a culture that do not instigate for education, for thinking, innovation and for widespread of creativity at all level. Advanced culture is unimaginable without predominance of education. Our ancestors were understandably patriotic for foreign invaders, but spring mattress for home-grown tyrants. If patriotism is not accompanied with sense of justice, it is nothing but unpolluted racism. Societies who have sense of justice could not end by fighting aloe foreign aggressors.
ReplyDeleteThat is why we became vulnerable for ethnic politics rather than social justice at the era of globalization.
I appreciate Dani.
.
Thank You
ReplyDeletelidetu dagne from kirkos ,it is a wonderful idea i accepted
ReplyDeletea very powerful message Dani!!!! Thank you so much
ReplyDeleteበመጀመሪያ ዳኒ እናመሰግናለን፡፡
ReplyDelete@ማህበረ ክርስትያን
ለምን ብልጥ አነሆንም "ወሰዳ"
አንደኛ የሚጠቅመንን ነገር ከምንም ቢሆን ብንወስድ ምን አለበት?(በጥንቃቄ እነ አሰፈላጊ ከሆነ)በትምህረት ቤት የተነገረን ነገር ሁሉ ትክክል ነው? ጠቃሚ ነው?...
ሁለተኛ ታሪክ ታሪክ ነው አባባሎችን ጨምሮ(መጥፎም ጥሩም)ስለዚ እኛ ተማርንበት አልተማርንበት እነሱ ማለታቸውን አያቆሙ(ይላሉ ስለተባለ)ላንቀይረው ለምን አንማርበትም?
ሌላው "አንድ ቀን ወደ ኦሊምፐስ ተራራ ወጥተው የአማልክት ንጒሥ የሆነውን ዜውስን ለመኑት" እንዲ ተብሎ ተቀምጦ ከልተረዳን ችግር ነው...መደጋገም ይሻል ይሆን?
በጣም ይቅርታና "በሮሜ 13 ቁጥር 1 ጋር ተምታታብኝ" ብለው አስተያየት ለሰጡት ጥቅሱ መሉ እንዲ ይላል፡
"ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው።"
ሀሉን የሚያደርግ አግዚያብሔ ነው(አነክድም አንጠራጠርም) ግን እንዲ ከሆነ የሰው ደርሻ የለም ልንል ነው?የተሰጠን ነጻ ፍቃድስ? አላዛር እንዲነሳኮ ሐዋርያት ድንጋዩን ማንሳት ነበረባቸው አቅቶት ነው? የሚከብደው የቱ ነወ? ድንጋይ ማንሳት ወይስ ሙት ማስነሳት የውም በንግግር የት እንዳለ ሁሉ ጠይቆዋል ስለማያውቅ ነው?
አስፈላጊ ከሆን አንድምታውን ዳኒ ይሰጠናል(አይደል?)
ዳኒ በእርግጥ እግዚአብሔር በየጊዜው የሚያዘጋጀው መሪ አለ፡፡ ነገር ግን እኔ ይህን ጽሁፍ የተረዳሁት ሠው የራሱን ድርሻ ይስራ በሚለው ነው ስለሆነም ጽሁፉ ተመችቶኛል፡፡ ሌላው ለአስተያየት ሰጪዎች አስተያየት መስጠት የምፈልገው አስተያየት ስንሰጥ እኔ ይህንን የተረዳሁት በዚህ መልኩ ነው ብለን ሌሎችን ለማቅናት መንገዱን ማሳየት እንጅ ለምን እንደዚህ ተረዳኸው ብለን ሌላውን አስተያየት ሰጭ ከማስረዳት ውጭ መኮነን እና መንቀፍ ያለብን አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ ማህበረ ክርስቲያን የሰጠው አስተያየት በራሱ እንደመረዳቱ መጠን ስለሆነ ትክክል ነው ባይ ነኝ እንደውም ለዳኒ መልዕክቶቹን ሲያስተላልፍ እንደዚህ አይነት መረዳቶችን ሊቀርፍ በሚችል መልኩ ብዕሩን እንዲያስተካክል ይረዳዋል ብዬ አስባለሁና፡፡በዚያ ላይ በማስረዳት ወይም በመረዳዳት እንጅ በእንደዚህ አይነት መድረክ ላይ በመነቃቀፍ የሚመጣ ጥሩ ነገር አይታየኝም፡፡
ReplyDeleteዲንፕል ነኝ
Thank you!!!!
ReplyDeleteselam Dani,mikirih temechitognal gin andande betiyake melk lemikerbileh teyake melsun beteset tiru new zem atebel.
ReplyDeleteHulachinm yalkewn betemesasay melku lanreda silemenechel ebakehen betesasate melku tereditenh asteyayet sensetih bedigami asredan.
Egziabher Yibarikih.
I don't agree with your idea. First of all you should not teach chirstians by giving such example /Taot/. Every thing is given to us by God. If we pray hard God will give us a good leader we can not make it by our selves.
ReplyDeletevery true Dani!!!
ReplyDeleteዲ/ን ዳኒ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን
ReplyDeleteጹሁፉ የድርሻችንን እድንወጣ የሚያነቃቃን ስለሆነ ለእኔ በጣም አስተማሪ እንደ ሆነ ተገንዝቤዋለሁ። ሌላው ማህበረ ክርስቲያን እንደተረዳው የራሱን አስተያየት ለመስጠት ሞክሯል። የመሰለውንም ጽፏል፣ ጥሩ ነው። እኔ ግን በሀሳቡ አልስማማበትም ፣ምክንያቱም ይሄኮ ፈሊጥ እንጂ እዉነተኛ ታሪክ አይደልም። ይህኮ በባህላችን በጣም የተለመደ ጉዳይ ነው፡፡ ለምሳሌ አነበሳ የአራዊት ንጉስ ሆኖ፣ ታሞ ሲጠይቁት ፣ ተጣልተው ሲዳኛቸው …..እናነባለን፤ ታዲያ እንደዚህ ከሆነ እንሰሳት እንደዚህ አድርገው ያውቃሉ? ይናገራሉ? በጭራሽ ተያይተው እንኳ ሊነጋገሩ ቀርቶ….። ለምን እንዲህ አልክ ማለቴ እንዳልሆን ግን ይታወቅልኝ፣ በዚህ መልክ ተረዳው ለማለት እንጅ፡ መፍትህ ነውና ።
ቸር ነገር ያሰማን
ደታ ዘባሕርዳር
Dn daniel tsgawen yabezaleh,fetsamehen medhanialem yasamere,dekameh yenfse waga yadrgeleh, egnam semeten anbeben hiyewtachin lemekeyer Medhanialem yerdan Amen.
ReplyDeleteWoldemchieal.
ጤና፡ይስጥልኝ፡ወንድሜ፡ዲያቆን፡ዳንኤል፣ወንድሞቼና፡እህቶቼ፡ውድ አንባብያን፣
ReplyDeleteአንዳንድ፡አንባብያን፡በአስተያየቴ፡ያልተስማማችሁ፡አላችሁ፡ጥሩ፡ነው
እኔ፡አዋቂም፡ሰው፡አይደለሁ፡ነገር፡ግን፡የማስበውን፡ለመፃፍ፡እንደምትፈቅዱልኝ፡አልጠራጠርም፡፡
እኔ፡ዲ.ዳንኤልን፡ለመንቀፍ፡ለማዋረድ፡ወይንም፡ለመተቸት፡በማሰብ
ሳይሆን፡የፃፍኩት፡ነገሩ፡እንዲታሰብበት፡ነው፡፡ማለት፡የፈለግሁትን፡
አሁንም፡እንድትረዱኝ፡እጠይቃልሁ፡፡
እነ፡ዜውስ፡አርጤምስ፡አፍሮዲት፡...ወዘተ፡ከዚህ፡ጊዜ፡እስከዚህ፡ጊዜ፡
የነገሡ፡የመሩ፡የሚባልላቸው፡አይደሉም(ከተሳሳትኩ፡አርሙኝ)፡፡እኔ፡
የማውቀው፡ጣዖታት፡እንደሆኑ፡ነው፡፡ማለት፡ሰዎች፡በጣዖት፡መልክ፡ እንደሚያመልኳቸው፡ነው፡፡ታሪኩን፡ፀሐፊዎቹም፡እነሱው፡(ግሪኮቹ)፡
የጣዖት፡አምላኪዎች፡ነበሩ፡፡ታዲያ፡እኛ፡ዲ.ዳንኤል፡ላነሳኽው፡ጉዳይ፡
በማስተማሪያነት፡ሊነሱ፡የሚችሉ፡ጥቅሶች፡ከመፅሐፍ፡ቅዱስ፡ወይም፡ ሌላ፡ተገቢ፡መፃህፍት፡እያሉን፡ለምን፡ይህ፡ቀረበ፡ብዬ፡ነው፡ሀሳቤን፡ የሰነዘርኩት፡፡
ሌላው፡ዲያቢሎስም፡ሆነ፡በሱ፡ምክንያት፡የተገኙ፡ጣዖታትን፡ስናነሳ፡ የእነሱን፡ክፋት፣ከእኛ፡ጋራ፡ስምምነት፡እንደሌላቸው፡ለማስተማር፡ ባጠቃላይ፡መጥፎነታቸውን፡ለመግለፅ፡ነው፡መሆን፡ያለበት፡እንደኔ፡
ሀሳብ፡፡
ይህን፡ስል፡ ግን፡ዲ.ዳንኤል፡ሰው፡ለማሳሳት፡ፃፈ፡ብዬ፡እንዳልሆነ፡ እንድታውቁልኝ፡እፈልጋለሁ፡፡
ቸር፡ይግጠመን!!!
በስመ ሥላሴ አሜን።
ReplyDeleteቃለ ሕይወት ያሰማልን መምህር።
ግን ...
አሁን አሁን ይቅርታ ይደረግልኝና መንፈሳዊውን አኗኗር እንድንጠራጠር እየተደረገ ነው ... መሪን ማን ይፈጥረዋል? ... ሕዝብ ራሱ? ... እንደ አለም አሰራር አዎ ... ከውጭ የሚታይን የተንቆለጳጰሰ ንግግር ... ምናምን አይቶ ሰው መሪውን ይመርጣል ... መልካም እሴቶችን የገነባ ሕዝብ መልካም መሪዎችን ይፈጥራል ... ይህም ልክ ነው ግን ... የሚሸወድም ሕዝብ አለ ... ሌላው ቅዱስ መጽሐፍ፦ እስራኤላውያን እንደነ ሙሴ እና እያሱ ያሉ መሪዎች የነበሯቸው በጊዜው መልካም አኗኗር ፤ ባህል ፤ ምናምን ስለነበራቸው ነበር ይላል እንዴ? ... የሰለጠኑ በምንላቸው ሀገራትስ ፍትሃዊ የሆነ ምርጫ ፤ የጾታ እኩልነት ፤...ምናምን ለመኖሩ ምን ያህል እርግጠኞች ነን? ... እርግጠኞችም እንሁን እንበል ጥሩ ምጣኔ ሀብት ስላላቸው ፤ ፖለቲካዊ ሰላም ስላላቸው ፤ ... ሁሉነገራቸው መልካም ነው ያስብላልን? ... እግዜርን እኮ አያውቁም። ...ለምን እንዲህ ባሉት ሰዎች እንድንቀና ግድ እንባላለን? ... ባይሆን እናውቀዋለን የምንለውን እግዚአብሔርን እንዴት ውዱን ፤ ትእዛዙን እንደምንፈጽም መንገድ እንመራለን እንጅ ... እንዴ እንደዚህ ከሆነማ ላይ ላዩን የማያይ እግዚአብሔር ፤ ሕዝቡ ለራሱ ከሚያስበው በላይ ለሕዝቡ የሚያስብ እግዚአብሔር የለም ማለት አይሆንም እንዴ? ... እንዲህ መናገር ባያስፈልግም ነገሮች እንዲህ የሚያስብሉ እየሆኑ ነው ...
ደግሞስ የእግዜሩን እንተወውና ሕዝብንስ የምናስተምረው ሁልጊዜ አትረባም ፤ መልካም የሚባል ነገር የለህም ፤ ምናምን እያልን ነው እንዴ? ... በመልካም መሬት ላይ ያለን አረም መኖሩን ማየት ምልካም ነው ... አረሙን ለመንቀል ግን መሬቱን ባድማ ማድረግ አይገባም ... ይህ ይህ ነገራችን መልካም ነው ይሔኛው ነገር ደግሞ ቢታከልበት የበለጠ መልካም ይሆናል ቢባል አይበቃም? ... ነው ሕዝቡ እንዲህ ቢባል አይገባውም?
እሽ እንዲህም ይሁን አንረባም አሉ ... ጥሩ የሚባል ነገርም የለንም አሉ ... ታዲያ እንድንረባ ምን እናድርግ? ...ጥሩ የሚባልስ ነግር እንዲኖረን ምን ይደረግ? ...
ወስብሃት ለእግዚአብሔር።
ዲ/ን ዳንኤል፣
ReplyDeleteከትንሽ ቆይታ በኋላ ወደገጽህ ስመለስ ካገኘኋቸው አዳዲስ ጽሑፎች መካከል ይህኛው በጣም ግሩም ድንቅ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። አብዛኛው የጠቀስካቸው ነገሮች እኛ ኢትዮጵያውያን ብዙ የምንኮራባቸው እሴቶች እንዳሉን ሁሉ እነዚህ ደግሞ ፍጹም እውነት የሆኑ ልንለወጥባቸው የሚገባ እንከኖቻችን መሆናቸውን በማያሻማ መንገድ የሚጠቁሙ ናቸው። በፍጹም ያልዘራነውን ልናጭድ የማንችል መሆኑን የእግዚአብሐር ቃል ይነግረናል።
ደቡብ አፍሪካን ከመሰለ ሃገር ኔልሰን ማንዴላ ቢገኝም ያልተለመደ በመሆኑ ነው አለም የሚደነቅበት። እንደተአምር ማለት ነው። ለኢትዮጵያ ተአምር ሊደረግላት ቢችልም መልካም መሪዎች እንድናገኝ ከእኛ የሚጠበቀውን ድርሻ እንድናደርግ ነው ጽሑፍህ የሚጠቁመው።
"መሪዎቻችን የተረቶቻችን፣ የዘፈኖቻችን፣ የአባባሎቻችን፣ የእምነቶቻችን፣ አመለካከቶቻችን፣ የአኗኗራችን የአበላላችን እና የአጠጣጣችን ውጤቶች ናቸው፡፡" በማለት ከህጻናት ጋር በተያያዘ በሰፊው ያብራራኸውን ሳነብ አሁን በቅርቡ ያታዘብነውን ልጽፍልህ አሰብኩ።
ለልጆቻችን እንዲሆኑ ብለን የአማርኛ የተረት መጻሕፍት ከኢትዮጵያ ተልከውልን ስናነባቸው በአብዛኞቹ ይዘትና አጻጻፍ የተሰማንን ሃዘን በቃላት ለመግለጽ ይከብዳል።
ስለፓሊዮ ክትባት አስፈላጊነት ለማስተማር ታስቦ በሚመስል የተጻፈ ታሪክ የአካል ጉዳተኛ ልጆችን ሌሎች ልጆች እንዴት ብለው እጅግ በሚጎዳ የስድብ ቃል እንደሚናገሩዋቸው በገጸ ባሕሪያቱ ምልልስ እያደረገ የያዘው ክፍል የታሪኩ 70 በመቶ መሆኑን ስናይና ያው መጽሐፍ ደግሞ በትምሕርት ሚኒስቴር አማካኝነት በየትምህርት ቤቱ የተሰራጨ መሆኑን ከኋላው የውስጥ ሽፋን ባገኘነው ምልክት ስንረዳ በጣም ነው ያዘንነው። ስድቡ ምን ያህል የአካል ጉዳተኞችን ቅስም ሊሰብር እንደሚችልም ሆነ ልጆች ከእንዲህ አይነት ተግባር እንዴት መቆጠብ እንደሚገባቸው ምንም ሳይጠቅስ ታሪኩ ይደመድማል። ለልጆች "እንዲህ የአካል ጉዳተኛ ሆናችሁ እንዳትሰደቡ ተከተቡ" ለማለት ከሆነ የማስተማሪያ ዘዴው እጅግ ኋላ ቀር ከመሆኑም በላይ አሁን በአካል ጉዳተኝነት ያሉትን ልጆች ስሜት የዘነጋና ኅላፊነት የጎደለው ነው።
ሌላው መጽሐፍ ደግሞ "እግዚአብሔርን ምናባክ በይው" በሚል የተጻፈ እናት በተናገረችው ምክንያት ልጆቿ በተለያየ ጊዜ ለሞትና ለተለያየ የማይረባ ነገር ተላልፈው እንደተሰጡባት የሚናገር ነው። በመጀመሪያ "እግዚአብሔርን ምናባክ በይው" የሚለውን ነገር ልጆች እንዴት ነው የሚተረጉሙት? የሚለውን ማሰብ አይቀርም። ፈሪሃ እግዚአብሔርን በዚህ መንገድ ማስተማር ይቻል ይሆን ወይ? ብሎ ማሰብም ይኖራል። ከዚያስ በላይ ልጆች እንደሰው የሳሉትን ለዚያውም የህጻን ገጸ-ባሕሪ ድንገት ሞተ ስትላቸው ምን ሊሰማቸው እንደሚችል እንዴት ሳንገምት ቀረን የሚያሰኝ ነው። ደግሞስ በወላጅ ኅጢአት ልጅ ይቀጣል የሚለው ነገር እውነት ነው እንኳን ብለን ብናምንበት ለልጆች ምን አድርጉ ብለን ነው አሁን በመጽሐፍ አትመን እየነገርናቸው ያለው? ሌላም ሌላም በጣም ብዙ አሉታዊ ነገር ነው ያለው። የውጭውን አደነቅህ ካላልከኝ እዚህ በውጭ አገር ለህጻናት በሚታተሙት መጻሕፍት ውስጥ የሚደረገውን ጥንቃቄ አይተህ የእኛን መጻሕፍት ስታይ ብዙ የሚያስደነግጥ ነገር ታገኛለህ።
የሆነው ሆኖ ያንተን መልዕክት ለማጠናከር እንደምሳሌ ይህን ብቻ አነሳሁ እንጅ በጸሐፍት በኩል የተደረገውን ጥረት ለማንኳሰስ አይደለም። በፍጹም። እንዲያውም ከደራስያኑ መካከል በጣም የምናከብራቸውና ለሃገር ባለውለታ የሆኑም አሉበት። የሚረዳቸው ስላጡ ብቻ የሆነ ነገር አድርጌ ነው የማስበው። የተጠናከረና ብቃት ያለው እንቅፋት ለመሆን ሳይሆን ሥራቸው ለሕዝብ ከመሰራጨቱ በፊት ከእነርሱ ጋር እየተመካከረና ከተለያየ አቅጣጫ ሙያዊ እርዳታ እያደረገ የበሰለ ሥራ እንዲወጣ የሚያደርግ አካል ስለሌለ ይመስለኛል።
ዋናው ነገር ይህም ሆነ ሌሎቹ በጽሑፍህ የጠቀስካቸው ነገሮች መለወጣቸው ለሃገርና ለትውልድ ብዙ ጥቅም እንጅ ምንም ጉዳት የላቸውም ለማለት ነው። ያ እንዲሆን በመጀመሪያ ችግሩ መኖሩን በቅንነት መቀበል ያስፈልጋል። ይህ እንዲመጣ እንዲህ እንዳንተ አይነት ጽሑፎች ያላቸው አስተዋጽዖ በጣም ትልቅ ነው።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ። ጥረትህን እግዚአብሔር ይባርክልህ!
hi d/danial egiziabher thigawne yabzlihe. THAT WAS WONDERFUL IDEA.
ReplyDeletekale hiwot yasemalign dn dany it is good but mahibere christian comment should be considred
ReplyDeleteI just want to express my appreciation for the three comments posted by 1)ማህበረ፡ክርስቲያን (two comments), 2)ዲንፕል ነኝ and 3)Eyob G..
ReplyDeleteThey are disciplined. By doing that way you are teaching if there is a wise child who thirsts to learn. That is what it mean to fear God which is the beginning of wisdom.
Thanks.
Ethiopian Child
I agree with the one who said it doesn't represent for all peoples of Ethiopia specially the names like Belachew, Gizachew...it is related with specific Ethinic group not all but with some peoples specially those who have the interest to lead and suffer peoples. Leaderships is a responsiblity not to suffer for a people. We have to focus on development for our country not on debating leadreship this that ethinic group should rule. Yesilitan filagot le Abune Merkorewos enquan altekemachewum Hizbin kefafelu ye hayimanot sirat abelashu enji yesiltan filagot baynorachew yihe hulu chigir, me'at ayimetam neber. So please let us come to bright. Forget about leadership let us talk together about development, peace and friendship of our poor people. Eskemeche new be siltan filagot chelema yemininorew. This is the big problem in our country specially lemekefafel wanaw mikiniyatu Ye zemene Mesafint le agerachin, le betekiristiyanachin altekematim. Egziabher yishomal egziabher yanesal enibel. Amlake kidusan besiltan filagot yetawere libonachin yabiralin. Selam fikir andinet yisten.
ReplyDeleteSelam Dani,
ReplyDeletewhen you collect comments last time, I recommended to raise some of our positive things, but still you are humming as with our bad behaviour. I doubt if this bring change...
The other thing, if possible try to digest the examples... some times they may damage...
at all I appreciate your effort , your initiation.. what I have done?????
ሰላም ለዚ ጡምራ ተሳታፊዎች: ቃለህይወት ያሰማልን ዲ/ን ዳንኤል::
ReplyDeleteበኔ እስተሳብ ይህ ጽሁፍ ለማለት የፈለገው እግዚአብሄር መሪን አይፈጥርም ለማለት ሳይሆን ጥሩ መሪ ለማግኘት በስነ ምግባር የታነጸ ማህበረሰብ ያስፈልገናል መሪ ከመሃበረሰቡ ነውና የሚዎጣው ለዚህም የበኩላችንን አስተዋፅዖ እንዎጣ ለማለት እንደፈለገ ነው የገባኝ:: መልካሙን ነገር እግዚአብሄርን አያውቁም ከምንላቸው ምዕራባዊያንስ ብንማር ምን ክፋት አለው? እኛም መልካሙን ኢትዮጵያዊ ባህል እና እምነታችንን እንድንጠብቅ እራሳችንንም እንድናይ የሚያድርግ ጽሁፍ ''ቅኝ አልተገዛንም'' በሚለው ጽሁፉ ነግሮናል::
መድሃኒአለም ማስተዋሉን ያድለን::
ጥሩ እይታ ነው: እስማማበታለሁ:: እኔ ከዚሁ ጋር የተያያዘ ተጨማሪ ሃሳብ አለኝ::
ReplyDeleteእርግጥ ነው መሪ የማህበረሰቡ አሰራር ውጤት ነው:: ነገር ግን ከከንቱ ትውልድም መሃል ቢሆን እጅግ ብርቅ የሆኑ: በተፈጥሯቸው ካላቸው የተሻለ የማገናዘብ ችሎታም ይሁን ያገኙትን ልዩ አጋጣሚ በመጠቀም: ልዩ የአመራርና የአስተሳሰብ ብቃታ ያላቸው ዜጎች አይታጡም:: ታዲያ በዛ ያለው የዘመኑ ማህበረሰብ ክፍል እነዚህን ድንቅ ስጦታዎች በአግባቡ ከመጠቀም ይልቅ እድሜ ዘመናቸውን ሁሉ እንደ 'ጉዱ ካሳ' እያየ የራሱንም የመጪውንም ትውልድ ተስፋ ገሎ ያልፋል:: ከሚያነብ ይልቅ የሚኮርጅ: ከሚሰራ ይልቅ የሚሰርቅ: ከሚያስብ ይልቅ የሚናገር: ከሚፈጥርና ከሚመራመር ይልቅ በዘልማድ የሚኖር በበዛበትና በከበረበት ማህበረሰብ ውስጥ ለውጥን ማሰብ እጅግ ይከብዳል::
ዳንኤል እንዳለው ትውልዱ መሪዎችን የማፍራት ባህል ማጣቱ/አለማዳበሩ ይሳስብኝል:: ከዚህም ይልቅ የሚያሳስበኝ ግን ከትውልድ አንዴ ለሚገኙትና ሃገሪቱን መለወጥ ለሚችሉት ብርቅዬዎች እድል መስጠት አለመቻሉ: ይልቁንም ከመንደር እስከ ሃገር እነርሱን ለማጥፋት መቸኮሉም ነው:: የዓለምን ታሪክ የለወጡት ጥቂቶች ናቸው: ሃገራችንንም የጥቂቶች ሃቀኝነትና ቆራጥነት ሊለውጣት ይችላል:: እነዚህን ብርቅዬዎች በቤታችን: ከጎረቤታችን: ከትምህርት ቤታችን: ከቤተ-ክርስቲያናችን: ከመስጊዳችን: በመንጋችን: በስራ ቦታችን ወዘተ እናገኝቸዋለን:: ስለዚህ: ከቻልን ከጎናቸው ቁመን የታሪክ አካል እንሁን:: ካልቻልን ደግሞ ቢያንስ መንገዳቸውን አንዝጋ!
Lord Greetings!
ReplyDelete"...ማህበረ ክርስቲያን የሰጠው አስተያየት በራሱ እንደመረዳቱ መጠን ስለሆነ ትክክል ነው ባይ ነኝ እንደውም ለዳኒ መልዕክቶቹን ሲያስተላልፍ እንደዚህ አይነት መረዳቶችን ሊቀርፍ በሚችል መልኩ ብዕሩን እንዲያስተካክል ይረዳዋል ብዬ አስባለሁና፡፡በዚያ ላይ በማስረዳት ወይም በመረዳዳት እንጅ በእንደዚህ አይነት መድረክ ላይ በመነቃቀፍ የሚመጣ ጥሩ ነገር አይታየኝም፡፡"
I agree with ዲንፕል, no writer forces you to swallow everything what he writes. There are things you accept fully and there are some you dont accept at all and need to argue to reach on agreement. In my opinion "Mahiber Christian" has just forwarded his thought and no one has to criticize why this thing came to his mind. I strongly oppose one of the attender who urged Mahiber Chirstian to read back the article in a negative way. That is an offensive attack!!!Please be urged to view anyone's comment positively. The writer has full right to approve or discard any comments coming from the readers before anyone see them. And when it comes to "Mahiber Christian's" comment, the writer approved it whether he agrees with idea or not and we have to respect that. We have to let more people to forward their opinions.
Coming back to the article, I have still the memory of one story in grade one amharic text book.The title of the story was "Zeberga Aleka temerete". It matches with the idea in here.
Egziyabher agerachenen yitebek!
Great observation -- along the same line check out a book called "Medlot" by Lidetu Ayalew.
ReplyDeleteIt is written in Amaharic and it goes deep into the topic that Danni is talking about.
SR
It is really nice we all like and appreciate BUT it is difficult to speak confidently such words in a country where people can be killed or imprison with out any justification.
ReplyDeleteI am afraid for you as they may kill you at any time
DANI we all love your words and braveness but take care.
DANDEW
kale heyewt yasemalen D.DANEAL
ReplyDeleteteleck melecket bemigeban ckuwaneckuwa ena bemenenorew anuwanarn yetegelese maneneten mafereiya hasab new .AMELACKE tebebun yabezalehe,ezihe andaned wendemoch leyet yale YEGZIABEHERN deresha yemigafa bemimesel melecku yeteredu alu,neger gen bemesehaf ckedus laye ,teleleck abatochen,lemesale MUSEN benayew mananetun ckenatu,astedaderen ckeferon bet,temero yadegena EGZIABEHER ,beterwena hezeb eseraelen bebeckat merto ,ckesu ckber yeleck lehezebu yemizzen meri eseckemehon ,asetedadegum chemer new ,behadise wenegelem .behawareyat sera meraf6-3,edetegelesew (bemeleckam yetemeseckerelachewen ckenate meretu...)yelale bateckalaye ,yedi,danel eyeta bemanenetachen laye siyanetatere anedeneget amenen meseteckackel engi esu ckeckalu weche ena emenetn bemifeten melecku yegeba ayemeselegnem ,lehulum amelacke tsgahen yabezalehe ,emeberehan ckanetgare tehun,..ROBI
I really liked it. God bless you Dan.
ReplyDelete