ሰሞኑን የሁላችንንም ተስፋ ከፍ ከፍ አድርጎ የነበረ ነገር ሲጨልም አይተናል፡፡
በአባቶች መካከል የተፈጠረው መለያየት በዕርቅ ሊፈታ ነው ተባለ፡፡ ሽማግሌዎች ተሰባሰቡ ተባለ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ እና በዝርወት ያሉት አበውም ፈቃደኛ ሆኑ ተባለ፡፡ ቀን ተቆረጠ ተባለ፡፡ ከአዲስ አበባ የተወከሉ ልኡካን አሜሪካ ገቡ ተባለ፡፡ አዲስ አበባ ከሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ተመድበው አሜሪካ የሚገኙት ሊቃነ ጳጳሳት ሳያውቁት እና ሳይሳተፉበት ሽማግሌዎች ተቀበሏቸው ተባለ፡፡ በሀገረ ስብከቱ መንበረ ጵጵስና ሳይሆን ሆቴል ዐረፉ ተባለ፡፡ አንዳንድ ሽማግሌዎች ራሳቸው እዚህ ከነበሩት አበው ጋር አይስማሙ ነበር ተባለ፡፡ ዳላስ አውሮፕላን ማረፊያ የደረሰውን ልኡክ ለመቀበል በነበረው መርሐ ግብር ላይ ፍቅር ሳይሆን መቃቃሩ በግልጽ ታይቶ ነበር ተባለ፡፡
ሽማግሌዎቹ ምሥጢር ላለማውጣት ተማምለዋል ተባለ፡፡ ዋናው መፍትሔ ነገሩን ከባለቤቱ ሕዝብ መደበቅ ነው ተባለ፡፡ ከአዲስ አበባ ልኡካን አንዱ ከኛ ጋር ሊነጋገር አይችልም ብለው አሜሪካ ያሉት አባቶች አቋም ያዙ ተባለ፡፡ ሽማግሌዎቹ እያግባቡ ነው ተባለ፡፡ ይህ ከልኡካኑ አንዱ የሆነ ሰው ይቅርታ መጠየቅ አለበት ተባለ፡፡ በመጨረሻም እርቁ ሳይጀመር ተጠናቀቀ ተባለ፡፡ ከዚያም መግለጫ ወጣ፡፡ እኛም አነበብን፡፡
ብዙዎቹን ነገሮች ተባለ «ተባለ» እያልኩ የምዘረዝረው እርቁ ለምን አስፈለገ? ዓላማው ምንድን ነው? ሽማግሌዎቹ እነማን ናቸው? እንዴት ተሰባሰቡ ወይም ተመረጡ? ከዚህ በፊት ያላቸው ችሎታ እና ልምድ ምንድን ነው? እነማን ተወከሉ? ውይይቱ የት እና መቼ ይጀመራል? በምን በምን ጉዳዮች ሊነጋገሩ ወሰኑ? ወዘተ ለሚሉት ጥያቄዎች በተባራሪ ከሚሰሙት ነገሮች በስተቀር እኔ ባይ አካል ምንም ነገር ለማለት ስላልደፈረ ነው፡፡
ምክንያቱም ቦታው የሚዲያ አሠራር እና ጥቅም የማይታወቅበት፤ ነገሮች ከሕዝብ ተነጥለው የሚሠሩበት አሜሪካ ነውና፡፡
እኔ ግን አንድ ነገር እጠይቃለሁ፡፡ ለመሆኑ እነዚህ አካላት መታረቅ ነው መታረቅ ያለባቸው? መታረቅ የሚለው ቃል ሲጠብቅ እና ሲላላ ትርጉሙ ይለያያል፡፡ ሲጠብቅ «መቃናት፣ መገራት፣ መስተካከል፣ መታረም፣» ማለት ነው፡፡ ሲላላ ደግሞ «መስማ ማት፣ መግባባት፣ ይቅር መባባል» ማለት ይሆናል፡፡
እኔ ግን መጀመርያ መገራት፣ መቃናት፣ መስተካከል፣ መታረም ይቀድማል ባይ ነኝ፡፡ ይህ ቢኖር ኖሮ ስንት የተለፋበት ዕርቅ ባልፈረሰ ነበር፡፡
መጀመርያ መታረቅ የሚያስፈልጋቸው እንዲህ ያለውን ነገር ለመሸምገል የሚነሱ አካላት ናቸው፡፡ እነዚህ አካላት በመንፈሳዊነት እና በአካሄድ መታረቅ አለባቸው፡፡ ለምሳሌ ይህ ሽምግልና ሲጀመር ራሳቸው ሽማግሌዎቹም ሆኑ ሕዝቡ ጸሎት እንዲያደርጉ መነገር ነበረበት፡፡ የፍቅር ጠላት የሆነውን ሰይጣን ያለ ጸሎት ማስወጣት ይቻላል ብሎ ማሰብ የወንጌሉን ቃል ማስተሐቀር ነው፡፡ ዓላማቸውን ገልጠው «እኛም ሱባኤ ይዘናል እናንተም ጸልዩልን» ቢሉን ኖሮ ከመካከላችን እግዚአብሔር የሚሰማው አንድ ሰው ባልጠፋ፤ የዚህም ሰው ጸሎት የተወያዮቹን ልብ ባስተካከለው ነበር፡፡ ከዚህም ታልፎ ጸሎት ሕይወታቸው ወደ ሆኑ ገዳማውያን አበው መባውን በመላክ በጸሎት አስቡን መባል አለበት፡፡ በፍቅር እስከ መቃብር የፊታውራሪ አሰጌን እና የፊታውራሪ መሸሻን ለጦርነት የደረሰ ጠብ ያበረደው የዲማ ጊዮርጊስ እና የብቸና ጊዮርጊስ ካህናት ጸሎት እና ልመና መሆኑን ሊቁ ሐዲስ ዓለማየሁ ነግረውን ነበረ፡፡ መቼም ሁለቱ ተወያዮች ከፊታውራሪ መሸሻ እና ከፊታውራሪ አሰጌ የተሻለ ዕውቀት እና መንፈሳዊነት አይጠፋባቸውም፡፡ ነገር ግን ፍቅር እስከ መቃብር የተጻፈውና የታተመው ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ስለሆነ ለነማንዴላ እንጂ ለኛ ዕርቅ አይጠቅምም፡፡
ሁለተኛው ደግሞ በአሠራር መታረቅ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ሽምግልና ወይ ባህላዊውን አለያም ዘመናዊውን የሽምግልና አካሄድ ያለ በለዚያም ሁለቱንም መያዝ አለበት፡፡ በባህላዊው ሽምግልና የሚፈሩ እና የሚታፈሩ ሽማግሌዎች ያስፈልጋሉ፡፡ ተው ቢሉ የሚሰሙ፣ ቢራገሙ የሚያደርሱ፣ ቢናገሩ የሚያሳምኑ ሽማግሌዎች፡፡ እኔ እንዳየሁት ግን አሁን ተጀምሮ የነበረውን ውይይት ያስተባበሩት ሽማግሌዎች ከአንድ እና ሁለት ሰዎች በቀር ይሄ ያንሳቸው ነበር፡፡
በዘመናዊው የሽምግልና አካሄድ ደግሞ የቴክኒክ ኮሚቴ እና አማካሪዎች ያስፈልጋሉ፡፡ የቴክኒክ ኮሚቴው ሽምግልናው ከመደረጉ በፊት ቦታውን፣ ተወያዮችን፣ አጀንዳዎችን፣ አካሄዶችን፣ ችግር ቢያጋጥም የመፍቻ መንገዶችን፣ ወዘተ ቀድሞ በሚገባ የሚሠራ የባለሞያዎች ቡድን ነው፡፡ በዕርቅ እና ድርድር ጉዳዮች ልምድ ያካበቱ፣ መፍትሔ ማመንጨት የሚችሉ ባለሞያዎች ይካተቱበታል፡፡ እነዚህ ባለሞያዎች ከሁለቱም ወገን አማካሪዎች ጋር በመሆን መንገዱን እንደ ዮሐንስ ይጠርጉታል፡፡
አማካሪዎቹ ተወያዮቹን ወክለው በዝርዝር ጉዳዮች ላይ ቀደም ብለው ይነጋገራሉ፤ የሚያስማሙትን እና የሚያለያዩትን ይለያሉ፤ ከቤተ ክርስቲያን ሕግ እና ሥርዓት፣ ከታሪካዊ እና ባህላዊ ጉዳዮች አንፃር ነገሮችን ይገመግማሉ፡፡ የማስማሚያ ሃሳብም ያመነጫሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ዋኖቹ ተወያዮች ሲመጡ እነርሱ አማካሪ በመሆን ውይይቱን ያሣልጣሉ፡፡
ሌላው መታረቅ የሚገባቸው ተወያዮቹ ናቸው፡፡ አባቶች ናቸው፤ ቤተ ክርስቲያንን የሚመሩ ናቸው፤ ለመንጋው ኃላፊነት ያለባቸው ናቸው፤ ሌሎችን ያስታርቃሉ ተብለው የሚጠበቁ ናቸው፤ በዕድሜም ሽማግሌዎች ናቸው፡፡ በዕውቀትም የበለጸጉ ናቸው፡፡ በመሆኑም ችግሩን ለመፍታት እና ውይይቱ እንዲሳካ የቻሉትን ሁሉ ማድረግ አለባቸው፡፡
አሁን እንደታየው ግን በሁለቱም ተወያዮች ዘንድ ያልታረቁ ነገሮች ነበሩ፡፡
ከአዲስ አበባ የመጡት ተወያዮች እዚያ ለሚገኘው ሕዝብ ምንም አልነገሩትም፡፡ በተባራሪ ከሰማው ነገር በቀር፡፡ ጉዳዩን የቤተ ክህነቱ ሰዎች እንኳን ጥርት ባለ መልኩ አያውቁትም፡፡ እዚህ አሜሪካ ያሉት ሊቃነ ጳጳሳትም በዌብ ሳይት እና ሀገር ቤት በመደወል ከሰሙት በስተቀር በመዋቅሩ መሠረት አልተነገራቸውም፡፡ የሂደቱ አካልም አልነበሩም፡፡ «ባለቤት ያቃለለውን አሞሌ ባለ ዕዳ አይቀበለውም» ይባላል፡፡ ቤት ውስጥ የቀሩት ልጆች እየተናቁ፣ ከቤት ወጠተዋል የተባሉትን ለማምጣት የሚደረግ ውይይት እንዴት ውጤታማ ይሆናል?
በአሜሪካ ከነበሩት አባቶችም ያልታረቀ ነገር ነበር፡፡
በመጀመርያ ደረጃ ልኡካኑን በተመለከተ ማለቅ ያለበት መጀመርያ ነው፡፡ በሌላም በኩል አንድ አካል ወኪሉን ከላከ እርሱኑ ተቀብሎ መነጋገር ይቻል ነበር፡፡ በመግለጫው ላይ የቀረበው ስሞታ ቀድሞ ሊያልቅ ይገባው የነበረ እንጂ የውይይቱ ማፍረሻ መሆን አልነበረበትም፡፡ ለመሆኑ አንደኛው ወገን ስለሌላው ወገን ሲጽፍ፣ ሲናገር፣ ሲያወግዝ አልኖረም እንዴ) ቅዱስ ሲኖዶስ ባወጣው መግለጫ፣ በጻፈው ጽሑፍ እና በወሰነው ውሳኔኮ ሁሉም አበው አሉበት፡፡ እዚህ ያሉት አባቶችም ሲጽፉ፣ ሲያወግዙ ነው የኖሩት፡፡ እንዴት አንድ ሰው ብቻ የጉዳዩ ባለቤት ሊሆን ቻለ?
በሌላስ በኩል መለያየት፣ መወጋገዝ፣ መጻጻፍ እና መተቻቸት ባይኖር ኖሮ የዕርቅ ውይይትስ ያስፈልግ ነበር? የተጋደሉ፤ የተታኮሱ፤ የተጨፋጨፉ ሰዎችኮ በፖለቲካው መድረክ ተወያይተዋል፤ ታርቀዋል፡፡ እንኳንስ የሃይማኖት ሰዎች፡፡ ደግሞስ መንፈሳዊ ሰው ይቅርታ ልጠይቅ ይላል እንጂ እገሌ ይቅርታ ይጠይቀኝ ማለት የጀመረው ከመቼ ወዲህ ነው? ይቅር በለው የሚል እንጂ ይቅርታ እንዲጠይቅህ አስደርገው የሚል ወንጌል ተጻፈ እንዴ?
እስከ ዛሬ በታሪክ እንደታየው በመንበር ላይ የተቀመጠ እና ሥልጣኑን የተቆናጠጠ አካል ነበር ምክንያት እየፈጠረ ዕርቅን እና ውይይትን የሚያደናቅፈው፡፡ አሁን ግን ያኛው ወገን ለእምቢታ ቸኮለ፡፡ ብዙ ሰዎች የደነቃቸው ቅዱስ ሲኖዶስ ዕርቁን መደገፉ፣ አሜሪካ ድረስ ልዑካን ልኮ ለመነጋገር መፍቀዱ ነበር፡፡ ይህንን መልካም ዕድል ተጠቅሞ፤ ፈተናዎችን ሁሉ በመቋቋም ለቤተ ክርስቲያን አንዳች ጠቃሚ ነገር መሥራት እዚህ ያሉት አበው ድርሻ ነበር፡፡ ግን አልታደልንም፡፡
ሌላው ቀርቶ ነገሩን በዓለማዊ መንገድ ካየነው ከአዲስ አበባ አሜሪካ ድረስ መመጣት አልነበረበትም፡፡ ወይይቱ በኣማካይ ቦታ መሆን ነበረበት፡፡ ነገር ግን ችግሩ ወዳለበት ቦታ ያኛው አካል መምጣቱ በራሱ አንድ ሊደነቅ የሚገባው ርምጃ ነበረ፡፡ «እናንተ ኬንያ ኑና እንወያይ» ከሚለው ትዕቢት ይልቅ «ያላችሁበት መጥተን እንወያይ» ማለቱ አዲስ ጅምር ነበር፡፡ ምናለበት እንደ በላዔ ሰብእ ጠብታ ነገር ስናገኝ እንደ ሰይጣን ከመድፋት፣ እንደ ድንግል ማርያም ጥላችንን ብንጥልበት እና ሚዛን እንዲደፋ ብናደርገው?
አንዳንድ አካላት የችግሮችን መኖር ይፈልጓቸዋል፡፡ ጭር ሲል አይወዱም፡፡ በችግሩ እያመካኙ የፖለቲካ ሂሳብ መሥራት፤ ገንዘብ መሰብሰብ እና ድጋፍ መሰብሰብ ለምደዋል፡፡ ችግሩ ከተፈታ የመታገያ አጀንዳ እናጣለን ብለው ይፈራሉ፡፡ ውይይቱ ሊካሄድ ነው በተባለበት ሰሞንና በሚካሄድበት ጊዜ ሁሉ የሚሰሙ ድምፆች ነበሩ፡፡ ትላልቅ የሚባሉ አባቶች ሳይቀሩ ለምን ውይይት ይደረጋል? እያሉ ጫና ሲያሳድሩ ነበር፡፡ የአሜሪካው ልኡካን ይህንን ጫና መቋቋም የቻሉ አይመስለኝም፡፡ ይህ ልብ ቀድሞ መታረቅ ነበረበት፡፡
ምንም እንኳን በቂ መረጃ ባለማግኘቱ ሊወቀስ ባይችልም፤ ሕዝቡ በተባራሪ የሰማውን በመያዝ አይዟችሁ በርቱ፤ ከጎናችሁ ነን፤ ይህ እና ያ ሃሳብ አለን እያለ ማበረታታት ነበረበት፡፡ መጸለይ ነበረበት፡፡ ሽማግ ሌዎቹንም የት ደረሰ? እያለ በግድም ቢሆን መጠየቅ ነበረበት፡፡ አሠራራቸውን እንዲያስተካክሉ እርማት መስጠት ነበረበት፡፡ ልኡካኑ ላይ ጫና ማሳደር ነበረበት፡፡ እንዴት በተልካሻ ምክንያት ይህንን ትልቅ ዳቦ ሊጥ ታደርጋላችሁ? ብሎ መቆጣት ነበረበት፡፡ ዋንጫ እንዲመጣ ከመጫወት ይልቅ ዋንጫ እንዲመጣ የመጠበቅ አካሄድ እስከ ዛሬም አላዋጣን፤ ዛሬም አላዋጣን፡፡ ቀድሞ መታረቅ የነበረበት አንዱ ነገር ይህ ነበር፡፡
እነዚህ ሁሉ ሳይታረቁ ዕርቁ ተጀመረና፤ እንደተጀመረ አለቀ ተባለ፡፡ ከዚያም መግለጫ ወጣ ተባለ፤ ለመግለጫውም መልስ ተሰጠው ተባለ፡፡ ሕዝቡም የሚያወራበት አጀንዳ አገኘ ተባለ፡፡ ችግራችንም ይቀጥላል ተባለ፡፡
ESTI YIHUN ! BICHA SALMOT TARKEW BAYEHUACHEW
ReplyDeleteመቼስ የእርቅን ዜና መስማታችንም መልካም ነው እሱ ያለው ቀን ሲደርስ ሁሉም ሙሉ ይሆናል።
ReplyDeleteThank You Dn.Danny
' "ይሁን እስቲ" አሉ ባላባራስ ትልቁ ቤታቸው ሲወረስ ' ይል ነበር አባቴ የበኩር ልጁ የማይመስል ነገር ሳደርግ እና አትድረሱብኝ ስል። የባሰ አታምጣ ነው ነገሩ።
ReplyDeleteመቼም በጎ ነገር እንዳንሰማ የተፈጠርን ሳንሆን አይቀርም ከቀን ቀን መልካም ዜና እርቆናል። የክርስቶስ እንደራሴ ነኝ የሚል መንፈሳዊ አባት እርቅን እንቢ ካለ እንዴት ሆኖስ ነው በሌሎቹ ላይ መፍረድ የምንችለው? ምንስ ማለት እንችላለን ? ...የባሰ አታምጣ እንጂ...።
ዳኒ አንተ ግን በርታልን።
What an insight..May God move you from Grace to Grace!
ReplyDeleteMay God give us His PEACE! We never expect one from the flesh!
Where are we? What are we doing? What is going on? Why these religious leaders always go down in alarming rate? Oh! God please leave one wonderful leader for your children. Amen!
ReplyDeletei have no word
ReplyDeleteimebrehan iskemeche zim tiynalesh yebelaeseb inat direshiln .........
HIZIBU HULETUNIM YESINODOS ABALATOCHE KESHUMETE AWRIDO LAELA ABATOCHE BESHMISE MIN LIHONU NEWE. BACHIRU BETAREQU YISHALACHEWAL LEHULETUM......
ReplyDeleteየጉድ ሀገር ገንፎ እያደር ይፋጃል አሉ? ተባለ…ተባለ… ቡበዛበትም ጥሩ መረጃ ነው፡፡ ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡:
ReplyDeleteወንድም ዳንኤል እግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስጥህ
ReplyDeleteዘመኑ ቀና ልቦና የጠፋበት እና የግልን ሃሳብና ምኞት ብቻ
በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ሆነን ማንፀባረቅ ሌላው ክፉ ነገር
እልህ እነዚህ ናቸው ቤተ ክርስትያንን እየጎዱ ያሉት አነዚህ
ክፉ ነገሮችን አጥፍተን በቀና ልቦና በአንድ ልብ ሆነን ለአንዲት እምነት
የምንነሣበት ግዜ አምላክ ያቅርብልን
menfesawi abatoch teblew mirakachewn yewatu sewoch nachew teblew,yetetala sew yastarkalu teblew,ye chigroch meftihe yihonalu teblew............. but chigroch rasachew ,irik mayfelgu rasachew ,ye tilik lij yehonut rasachew ,mirakachewn witewal teblew iskezare ye kim ina tilacha mirak mitefut rasachew..................
ReplyDeletedingil hoy fitshin wedegna azurilin igna wedanchi banazorim[mazor biyaktenm]
I would be surprise if there were an agrement. As you said they did not follow spritual way.It was what i expected.Let us pray on the coming st mary fast.
ReplyDeleteይህ ሽምግልና ሲጀመር ራሳቸው ሽማግሌዎቹም ሆኑ ሕዝቡ ጸሎት እንዲያደርጉ መነገር ነበረበት፡፡ የፍቅር ጠላት የሆነውን ሰይጣን ያለ ጸሎት ማስወጣት ይቻላል ብሎ ማሰብ የወንጌሉን ቃል ማስተሐቀር ነው፡፡ ዓላማቸውን ገልጠው «እኛም ሱባኤ ይዘናል እናንተም ጸልዩልን» ቢሉን ኖሮ ከመካከላችን እግዚአብሔር የሚሰማው አንድ ሰው ባልጠፋ፤ የዚህም ሰው ጸሎት የተወያዮቹን ልብ ባስተካከለው ነበር፡፡ ከዚህም ታልፎ ጸሎት ሕይወታቸው ወደ ሆኑ ገዳማውያን አበው መባውን በመላክ በጸሎት አስቡን መባል አለበት፡፡
ReplyDeleteThis is the main thing that we lost!
ሠላም ላንተ ይሁን ዲ. ዳንኤል
ReplyDeleteከትንሽ እስከ ትልቅ የሁላችንም ልብ ለምን እንደሚደነድን አይገባኝም በጉጉት ስንጠብቀው የነበረው ዕርቅ በዚህ መልኩ ከተጠናቀቀ ነገ ይህችን ቤተ ክርስቲያን ምን እንደሚጠብቃት ለማወቅ ያዳግታል ብቻ ግን እንደኛ ሳይሆን እንደርሱ ጥሎ አይጥላትም ወድቃም አትወድቅም እንጂ በየዘመኑ የሚገጥማት ፈተና ከባድ ነው፡፡ እርሱ መንጋውን አስወጥቶ ቤቱን ያፀዳ ዕለት ግን ወየው ለራሳችን ….. እግዚያብሔር እንደ አንት ያሉትን ጠባቂ እንደማያሳጠት ግን በሙሉ ልብ አምናለሁ፡፡ ፈጣሪ የሰጠህን ፀጋ ያብዛልህ…
መሠረት
Every one of them is bent not to be straightened. A trail of straightening will broke them down.
ReplyDeleteእርቅ ከራስ ይጀምራል
ReplyDeleteእርቅ ለማውረድ ሰላምን ለማምጣት አስታራቂው ሰው፣ታራቂው ወገን መጀመሪያ ከራሳቸው ጋር መታረቅ አለባቸው፡፡ መጀመሪያ በቅን መንፈስ ከውስጣቸው ጋር አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ልቡናቸው ሊግባባና የቤተክርስቲያናችንን ሁኔታ በጥልቀት ሊያገናዝቡ በተገባ ነበር፡፡
እርቁ ለይስሙላ፣ ለመገናኛ ብዙሃን ፍጆታ ማዋያ ወይም ህሊና ለሚጠይቀው የተወሰነ ጥያቄ ሞክሬአለሁ ብሎ ምላሽ ለመስጠት ወይስ ከልብ የወንጌልን ቃል ለመፈጸም፡፡
ሲጀመር እርቁ በምን ተነስቶ ምንላይ እንሚያተኩር አልታወቀም ግን የአገር ቤቱ ተደራዳሪ ልዑኩን አሜሪካ የላከው መንግሥት ከተለያዩ ተቃዋሚዎች ጋር እያደረገ ያለውን ድርድር መንፈሳዊ ራቁትነቱ ስላስቀረውና ስላሳፈረው እንዲያም ሲል በቤተመንግሥቱ ጥያቄ ሲነሳበት ሞክሪያለሁ ለማለት እና ምላሽ ለመስጠት ይመስለኛል፡፡
የአባ ጳውሎስ ቡድን ከልቡ እርቅ ለማውረድና ለመስማማት ይችላል ብዬ በፍጹም አልገምትም ምናልባት እንዲዚህ አይነት ሙከራዎችን የሚያደርገው ከመንግሥት ከሚሰጠው ምክረ ሃሳብ እና ራሱን ጣዖት አድርጎ ለማቆየት ካለው ጽኑ ፍላጎት የተነሳ ነው ብል ማጋነን አይመስለኝም፡፡
የአባ ጳውሎስ ቡድን መንግሥት ካለ ሥልጣኔ አይነካም ብሎ ለቤተመንግሥቱ ከሚጸለይና የቤተክርስቲያኒቷን ክብር ዝቅ ከሚያደርግ ተግባር ታቅቦና ከራሱ ጋር ታርቆ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መጸለይ ቢችል የተሻለ ነበር፡፡
አሜሪካ ያለውም በስበብ አስባቡ ወደ አገር ቤት ላለመምጣት እና ከዚያ ያለውን ምቾትና ቅንጦት እንዲዘልቅ ከመናፈቅ ይልቅ ወደ አገር መጥቶ በቤተክርስቲያናችን ያለውን ነገር ተካፍሎ ለመነኮሱበት ቆብ ሞትን ቢሆን በሥጋ ተቀብሎ ክብር ተቀዳጅቶ ማረፍ የተሻለው ነበር፡፡
ዘመኑም፣ሥልጣኑም ሁሉም ያልፋል የማያልፈው ሰማያዊ የእግዚአብሔር መንግሥት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ክብር የሚያስገኘውን እርቅ ሁሉም በእልህ ሸሽተዋታል፡፡ የሰላም ደጅ በሆነችው ቤተክርስቲያን ተመልሰው እርቅን የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው እያሉ የተለመደ ወይም ከልብ ያልተቀበሉትን ነገር ግን እንደካደሬ በተለመደው ንግግራቸው ምዕመናን ያሰለቻሉ፡፡
ለሁሉም ልብ ይስጣቸው እኛ ግን ወደ አምላካችን እንጸልይ እርሱ በዝምታው ውስጥ መልስ ይሰጠናል፡፡ ሁሉም ነገር እየተፈጸመ ነው፡፡
እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችን ከዘረኞች፣ከመናፍቃን እና ከዘራፊዎች እና ከአስመሳዮች ይጠብቅልን፡፡
ዳኒ! ሀሳባችን እንድንተነፍስ ላቀረብክልን የመወያያ መድረክ በእጅጉ አመሰግናለሁ፡፡
እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን እና አንድነታችን ይጠብቅልን፡፡
Egziabhere lebetekristiyanachin andinetin, leabatochim fikirin, simiminetin yamitalin, Amen!
ReplyDeleteMin Yidereg Alemawinet kemenfesawinet liko Synodosun silemimeraw new. Eski esu yirdan
ReplyDeleteሁሉ ለስጋው አደረ እና ችግር ሆነ እነዚህ መንፈሳዊ ነን የሚሉ እንዲ ካሉ ምመናኑን አውደምህረት ላይ ቆመው ምን ሊያስተምሩ ነው
ReplyDelete+++
ReplyDeleteYe Enae Tiyakae,
Lemehonu Dn. Daniel endakerebihew, Besuba'e, Betselot, Mebe'a wudegedamat liko asibun bemalet yemiaminu abatoch alune yihone?! Hul Gizae Yemigerim new yeminsemaw ena yeminayew!
Be politica sewoch enquan yemayidereg eko new yemideregew!
Ersu Be'ewnet Hulun betigist yemiaye Amklake kiduan yirdan!
Ebakachihu Abatoch Le Bete-kiristiyan Bilachehu Liyunetachihun Aswegedu!
ReplyDeletemulugeta from harer,
ReplyDeleteLehulum neger AMLAK YIFKED lezih degmo tsome tselot yasfelgal.
ALADELENIM ENDALKE BAYADILEN NEW.
ReplyDeleteOne thing I want to mention is that individuals who are within the North America churches with political attitude have a big impact on this process. Church Fathers who live in the US/Canada usually influenced by those individuals and it is very common these days for these individuals to use church as their media to express their ideology. It is very sad and for those individuals-EGZEABHAIR YESIRACHEWIN YISTACHEW
They will never agree forever, becouse they making thier money from this problem.US's fathers
ReplyDeletepays thier morgage ( some of them has two houses for rent)from the result of this problem, Addis's fathers also keeping their high salery or getting best position.So how could expect their agreement to be real?
Kedmownus Semen ena Debub waltan magenagnet (machbabet) endet yichalal bilew jemerut?
ReplyDeleteበስመ ሥላሴ አሜን።
ReplyDeleteሊያሳስበን የሚገባ ሌላ ጉዳይ ...
የቤታችንን ችግር አስመልክቶ የተለያዩ ነገሮችን በተለያየ መንገድ ከተቆርቃሪዎችም ሆነ ግድ ከሌላቸው ወገኖች ብዙ ሰምተናል ... ከአንዳንዶቹም ጋር አብረን መክረናል ... ችግር ፈጠሩ ያልናቸውን አካላትንም ኮንነናል ፤ ወቅሰናል ... መፍትሔ ስለምንለውም ነገር ብዙ ብለናል ... ነገር ግን አሁን በፊታችን ተገልጦ የምንጯጯህበት ይህ የቤተ-ክህነት ችግር እኛ ባሰብነውም ይሁን በሌላ ዘዴ ቢፈታ ወይም የተፈታ ቢመስል እንኳ ትቶት ሊያልፈው ስለተዘጋጀው ጠባሳ ስንቶቻችን እናውቃለን?
በምንኖርባት በዚች አለም መሪዎች በተመሪዎች ላይ ቀንበር ሲያከብዱ ፤ ግፍን ሲያደርጉ ተመሪዎቹ በመሪዎቹ ላይ መነሳታቸው ፤ በተወሰኑትም መስዋዕትነት ሌሎቹ ነፃነታቸውን እንደሚያገኙ ታሪክ ምስክር ይሆናል ፤ ... ነገር ግን ይህን መሰሉ ክስተት የሚሰራው በአለም ነው! ... ምንም እንኳ እኛ ምዕመናን በአለም ውስጥ የምንኖር ቢሆንም ... በእግዚአብሔር ቤት አካሔዱ የተለየ ነው ... ሊለይም ይገባዋል ... ምክንያቱም አልቻለን እያለ ቢቸግረን ነው እንጅ ልንፈጽመው የምንወደው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ነውና ... ሀገራችንም በሰማይ ነውና ... በመሆኑም የቤተ-ክህነት ችግር መፍትሔ በምስኪን ምዕመናን መስዋዕትነት ወይም ዋጋ ሊታሰብ አይገባውም ... ለዚያውም መስዋዕት ስለሆኑበት ነገር በውል በማይረዱበት ሁኔታ ...
በየገጠሩ በስሚ ስሚ ፤ በየክፍላተሃገራቱ ካልተጣራ የወሬ ምንጭ ከሰሙት የተነሳ የሚስቱትን ወገኖቻችንን እንኳ ትተን በአዲስ አበባ ለቤተ-ክህነቱ ቀረብን ፤ ነገሩንም ከተለያዩ ምንጮች ሰማን የምንል ሰዎች የምንሰጣቸውን አስተያየቶች ለአፍታ ብንመለከት ከቤተ-ክህነቱ ችግር ባልተናነሰ ልንነጋገርበት ፤ መፍትሔ ልናፈላልግበት የሚገባ ጉዳይ እንዳለን ማስተዋል አይቸግርም። እንደ ሕዝብ፦ ችግሮችን በቀና መንፈስ የምንረዳበት ፤ ከአሉባልታ በፀዳ መልኩ ለመፍትሔ የምንረባረብበት ፤ መፍትሔን ለመፈለግ በሚደረግ ሂደት የሚመጣን ማንኛውንም በጎ እና ክፉ ነገር በኃላፊነት በፀጋ የምንቀበልበት ልማድ እንደሌለን ... ከዚህ በተጨማሪም ክርስቲያኑ ምዕመን በመንፈሳዊ ደረጃው እና ብርታቱ አንዱ ከሌላው እንደሚለያይ ይታወቃል ... በመሆኑም ምስኪኑ ምዕመን ከሚያየው ነገር የሚስተው ይበቃዋልና ... ምንም ያህል እንኳ የቤተ-ክህነቱን ችግር ያወቅን ፤ የጠነቀቅን ቢመስለን፦ የምናደርጋቸው ፤ የምንናገራቸው ፣ እና የምንፅፋቸው ነገሮች ሌሎችን እንዳያስቱ ፤ ልንጠነቀቅ ይገባናል ... እኛ እግዜር እድሜ ለንስሃ ከሰጠን ፤ መሳታችንን በተረዳንና በገባን ጊዜ ልንመለስ እንችላለንና ... ስለእውነት ለመነጋገር ስንቶቻችን ካየነው ፣ ከሰማነውና ፣ ካነበብነው የተነሳ የእግዚአብሔርን የቸርነት ስራ ተጠራጥረናል? ... ስንቶቻችን ስለመንፈሳዊ ሕይወት ያለን ግንዛቤ ተዛብቶብናል? ... ስንቶቻችን መልካሞቹን አባቶቻችንንና መምህራኖቻችንን ከክፉዎቹ ጋር ጨፍልቀን የማይገባውን ተናግረናቸዋል? ... ስንቶቻችን ወደቤተ-እግዚአብሔር ለመሔድ አፍረናል? ... እኛ ስለራሳችን መልካምን ልንል እንችላለን ... ነገር ግን ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ያያል ... ስለራሳችን እንዲህ ካሰብን ደግሞ ... በእምነት ከእኛ ስለሚደክሙ ... እግዚአብሔር ግን አጥብቆ ስለሚሻቸው ... ስለነርሱ ደግሞ ልናስብ ያስፈልገናል ... ስንቶቹ ይሆኑ ለንስሃ አባቶቻቸው ያላቸው ፍቅር የሚቀንሰው? ... ስንቶቹ ይሆኑ ለድካማቸው ምክንያት ይህንን ነገር የሚያደርጉት? ...
በርግጥ፦ ምዕመናን በሌሎች ሰዎች አስተሳሰብና አካሔድ እየተነዱ ከመንገድ ከመውጣት ፤ በጎ እና ክፉን በራሳቸው ህሊና ሊመረምሩ ፤ በጎውንም ሊከተሉ ይገባቸዋል። .... እንዲያም እንኳ ቢሆን እግዚአብሔር መምህራንን ማስቀመጡ እንዲህ ለሚደክሙት መንገድን ይመሯቸው ዘንድ ነውና የመምህራንን ፍለጋ መከተል እንግዳ ነገር አይደለም ... በመሆኑም የሚከተሉ የሚከተሉትን መመርመር እንዳለባቸው ሁሉ ... የሚከተል ያላቸውም ለሚከተላቸው የማይገባ መንገድን ማሳየት የለባቸውም ... ምክንያቱም ይህ ክርስትና ነውና!!! ... በክርስትና ደግሞ ሁለቱም ወገኖች ይመረመራሉ ... ከስራቸው የተነሳ ይፈረድባቸዋልም ... አንዱም ስለሌላው ይጠየቃል። ... ይህም ማለት እኛ የምንናገራቸውና የምንፅፋቸው ሌሎችን ከእግዚአብሔር መንገድ የሚያወጡ እንዳይሆኑ መጠንቀቅ ይኖርብናል ... የምናደርጋቸው ፣ የምንናገራቸውና ፣ የምንፅፋቸው ነገሮች የፈለገውን ያህል ሰላም የሚያመጡ ቢሆኑ ... የቱንም ያህል አስተማማኝ መፍትሔ ቢይዙ ... የተወሰኑ ምዕመናንን የሚያጠፉ ስላለመሆናቸው እርግጠኞች ልንሆን ያስፈልገናል ... ምክንየቱም የአምላካችን ቅዱስ ፈቃድ ሁሉ በሰላም በእቅፉ ውስጥ ይሆኑ ዘንድ እንጅ አንድስ እንኳ እንዲጠፋ አይደለምና ..
ይህም ሲባል ስለመፍትሔው መነጋገሩንና መወያየቱን አንዳች የማይገባ ነገር ለማድረግ አይደለም ... እንዲያውም ይህ የመላው ምዕመናን የውዴታ ግዴታ ነው ... እንዲህ ማለቴ ... በዚህ ችግር ውስጥ የመፍትሔ አካል ለመሆን ከታሰበ እያንዳንዱ የቤተክርስቲያኒቷ ልጅ የራሱን ድርሻ ጠንቅቆ ሊያውቅ ይገባዋል ለማለት እንጅ ... እንዲህ ካልሆነ ሁሉም ነገር ለሁሉም በመሰለ ሁኔታ እየተነገረ ያለ የመፍትሔ ሀሳብ መፍትሔ አቅራቢውንም ፣ ምዕመናኑንም ፣ ቤተክርስቲያኒቱንም አይጠቅምም!!! ... አንዱን ለማልማት ሌላውን ቢጎዳ ነው እንጅ ... እንደ ካህን ምን ይጠበቅብኛል? ... እንደ ሰበካጉባኤ አባልነቴ ምን ይጠበቅብኛል? ... እንደ መምህርስ? ... እንደዘማሪስ? ... ያልን እንደሆነ እና ያንኑ የድርሻችንን ከተወጣን ግን በቂ ነው። ... ምንም ቢሆን ቤቱ የእግዚአብሔር ቤት ነውና ...
በቀረውስ፦ ምንም በጫና ውስጥ ብንሆን ፤ ምንም የምናየውና የምንሰማው እምነታችንን የሚፈታተን ቢሆን ፤ እግዜር የማይወደውን ከማድረግ እንቆጠብ ... በሃይማኖታችን አስተምህሮ ለትዕግስት ወሰን የለውምና ... እንታገስ ... ክፉን ከማድረግ እንታገስ ... መልካምን ብቻ እያደረግን የአምላካችንን የምህረት ስራ እንጠብቅ ... ከዚህም ጋራ ለራሳችን፦ “ በመከራችን ጊዜ እግዚአብሔር የትዕግስትን ፍፃሜ ይሰጠን ዘንድ ስለነፍሳችን ትዕግስት እንማልዳለን “ እንበል ... ስለአባቶቻችንም ደግሞ፦ “ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች እነሱ ናቸውና እግዚአብሔር እነሱን ለረጂም ወራት ይሰጠን ዘንድ ያለ ነውር በንፅህና ሁነው በዕውቀት የሃይማኖትን ቃል ያቀኑ ዘንድ ስለ ጳጳሳቶቻችን እንማልዳለን “ እንበል።
የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይቅረበን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር።
" ...እነዚህ ውኃ የሌለባቸው ምንጮች በዐውሎ ነፋስም የተነዱ ደመናዎች ናቸው።"
ReplyDelete2ጴጥ.2:17
Kale Hiwoten Yasemlen Bedmey Betsgea Yetbklen Anten Dakon Daneil
ReplyDelete+++
ReplyDeleteበውስጣቸዉ ያለዉን ችግር ሳይፈቱ እንዴት እርቅ ሊፈጸም ይችላል:: በደላችን ይቅር በለን እኛም የበደሉንን ይቅር እንድንል ነዉ የሚለዉ እኮ:: ስለዚህ መጀመሪያ ራሳቸዉን ቆም ብለዉ ጎዶሎአቸዉን ያስተካክሎ ለቅዱሳን አምላክ እና ላስተማራቻቸዉ ቅድስት ቤተክርስቲያ ን ሲሉ:: እኛም እባካችሁ እንጸልይ::
መርከቧ ስትናወጥ አይገድህም ሊንጠፋ ነዉ እንበለዉ ምዕመናን::
Gebire E
ከዝዋይ
እኔ ግን አንድ ደስ የሚለኝን ነገር ልንገራችሁ?! ...ይህች ቤተክርስቲያን እየነጋላት ነው:: ሊነጋጋ ሲል በጣም ይጨልማል ሆኖ ተቸገረች እንጂ ጊዜው ደርሶአል:: ... እያያችሁ ነው: አሁን እኮ ሰው ሁሉ የሚመካበት ጠፍቶ "አምላክ ሆይ ምነው ተውከን: እመብርሃን ምነው ዝም አልሽን.. እስከመቼ ነው?" እያለ ነው እኮ:: በቃ ይሄ አይደል የሚፈለገው: ትምክህታችን እግዚአብሔር ከሆነ እርሱም ይረዳናል:: ደሮም እኮ ፈጣሪ የሚፈልገው ይሄንን ነው:: ወገኖቼ አይዞአችሁ የፈጠረን አምላክ አይረሳንም:: እንዲህ ሆድ ብሶን ስንንገላታ ያያና ይራራልናል:: ... ተመስገን እኔ የምናፍቀው ይህን ጊዜ ነበር:: በሰው ያለንን ዕምነት ትተን ተስፋ ቆርጠን እግዚአብሔርን ".. ምን ተሻለን?" ስንለው ማየት:: በተረፈ አሁን የቀረው ጊዜ ትንሽ ነው ብቻ እንዲህ በቤተክርስቲያናችንም ላይ በሰውም ላይ የተጫወታችሁ ሁሉ "...ወየው ለኔ ለበደለኛው!!"
ReplyDeleteቃለ ህይወት ያሰማልን ዲያቆን ዳንኤል! እኔ ግን አንድ ጥያቄ አለኝ? የእርቅ ትርጉሙ በጠፋባቸው ኣባቶቻችን ምክንያት በተለይም ከሀገር ውጭ ያለነው ምእመናን ተለያይተን የጎሪጥ እየተያየን የምንኖረው እስከመቼ ነው? በኣባቶች መካከል የተፈጠረው ያለመግባባት ምንም ዓይነት መንፈሳዊ ምክንያት እንደሌለው እውን እየሆነ በመጣ ቁጥር ምእመናን በኣባቶቻችን የተገነባውን የመለያየት ግንብ ደርምሰን ወደ አንድነት መምጣት አንችልም ወይ? ዳኒ እስቲ በዚህ ሃሳብ ዙሪያ ጻፍ እኛም እንወያይ!
ReplyDeleteይቅርታ ይደረግልኝና ዕርቁ እንኳን ቀረ ባይ ነኝ።
ReplyDeleteምክንያቱም ገና እዚህ ያለው ሶኖዶስ መቼ ታረቀና ነው ሌላውን ወገን ለማስታረቅ የሚሄዱት
መጀመሪያ እነሱ ይታረቁ በመካከላቸው ፍቅር ይኑር ያን ጊዜ ፍቅር ራሷ ታስማማቸዋለች
የሠላም ባለቤት መድኃኒዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ሠላሙን ያድለን
ለመሆኑ ግን ካልደፈረሰ ይጠራል እንዴ? ከላይ ሰፊ ትንታኔ የጻፍከዉ ወንድማችን ለሌሎች ወንድሞቻችን እንድናስብ መምከርህ ጥሩ ነዉ። ግን እንደኔ አመለካከት በተለይ አደጋ የሚሆነዉ ነገሩን በደንብ ሳንወያይበት ተሸፋፍኖ ሲቀር ነዉ። ዩኒቨርሲቲ በቆየሁባቸዉ አመታትም የተረዳሁት ነገርም ይሄ ነዉ። ይልቁንስ እስከታች ያለዉ ምእመን ነገሩን ጥርት አድርጎ እንዲረዳዉ ለማድረግ ቢሞከር ጥሩ ነዉ ይመስለኛል። አብዛኛዉ ሰዉ የተቸገረዉም አሁን ያለዉ የቤተክርስቲያንን አስተዳደራዊ ችግር የሰዎች መሆኑን ሳያዉቅ ቀርቶ የቤተክርስቲያኗ የራሷ አስመስሎ ማየቱ ነዉ። ነገሮች በደንብ በተብላሉ መጠን ብዥታ ይተናል ፣ እዉነትም ጥርት ብሎ ለመታየት ዕድል ያገኛል። ሁሉም እዉነቱን ከተረዳ ደግሞ ማን ይወድቃል?
ReplyDeleteከዚህ በተጨማሪ ግን ዺ/ን ዳንኤል እኛን/ጨዋ ምእመናንን/ የሚገስጽ ፣ ከእኛ ምን እንደሚጠበቅብን ... ወዘተ ባላንስ የሚፈጥር ሌላ ጽሁፍ እንደሚያወጣ ተስፋ አለኝ።
እናንተዬ፤
ReplyDeleteአሁንስ ነገሮች ተደበላለቁብኝ፤ አሁን አሁን ለአንዳንዶች የመንፈሳዊነትና ዓለማዊነት ትርጉም የተቀራረበ ይመስላል (መዝገበ-ቃላት ባያዉቀዉም)። ከአባቶች የሰማሁት "ወይ መሆን ወይ አለመሆን" የሚባለዉ ነበር ዛሬ ግን ሶስተኛዉ 'አመሆን'(መሆንም አለመሆንም) የተፈጠረ ይመስላል። የምን ማስመሰል ነዉ የሚጫወቱብን? ምን አለበት ይህቺን ቤተክርስቲያን ለእዉነተኞች የቤተክርስቲያን ሰዎች ቢተዉት፤ እኛንም ቢተዉን፤ እግዚአብሔርን እናመስግንበት። በየዕለቱ በቤተክርስቲያን ስም የሚደረጉ ነገሮች ሀሳባችንን ሰብስበን እንዳንኖር እያደረጉን በመናገርም በመጻፍም ሀጥአት እንድንፈጽም ለምን ይገፋፉናል? መጀመሪያዉኑም ራሳቸዉ ተጣላን አሉ የሚያጣላቸዉ ሳይኖር (መጣላት ከመንፈሳዊነት ጋር ምን ህብረት አለዉና?) አሁን ደግሞ ልንታረቅ ነዉ አሉ አሉ (ምን አዲስ ነገር ተገኝና?) እሺ ታረቁ ተባሉ፤ የተገላቢጦሽ አባቶች በምዕመናን ሊታረቁ!!! መጨረሻ ላይ "ከመረቁ አዉጡልኝ ከስጋዉ ጦመኛ ነኝ" ብለዉ ጨረሱት ተባለ።
ደግሞስ...ይህ የ'መግለጫ' ጉዳይ ሊገባኝ አልቻለም...ቤተክርስቲያን እንደመንግስት 'መግለጫ' ማዉጣት መቼ እንደጀመረች አላዉቅም (ዲ/ን ዳንኤል አንድ በለኝ) እኔ ግን እንዲህ ዓይነት አሰራር ነፍሴ አልተቀበለችም። እኛ መግለጫ ምን ያደርግልናል፡ አባቶች አንድ ሀሳብ እንዲሆኑ ነዉ የፈለግነዉ። ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ ነው?
ቆይ እንጂ...ማን ነን? ማን ነበርን? የት ነዉ ያለነዉ? ስለምንድነዉ የምናወራዉ? ሃይማኖት? መንፈሳዊነት? እባክህን አትቀልድ! ለምንድነዉ አባቶች ከምዕናን መሻል ያልቻሉት? እኔ የማዉቀዉ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች ሌሎችን ለማስታረቅ ሲገባበዙ እንጂ ላለመታረቅ መግለጫ ሲያወጡ አልነበረም። ኡ ኡ ኡ የመንፈሳዊ አባት ያለህ!
ለነገሩ ደካማ ምዕመናን ሆነን ነዉ እንጂ መታረቅ የማይፈልገዉን አባት "ወደ ቤተክርስቲያናችን አይግቡ፡ እኛ ከእርስዎ ምንም እየተማርን አይደለም፡ ቤተክርስቲያናችንን ለጠላትና ለሚዲያ አጋለጡት" ብለን ብንከለክላቸዉ ምን ይመጣል? ምዕመናንን የሚያዉክ ስራ ከተሰራ ምዕመናን ቤተክርስቲያናቸዉን የመጠበቅ ሃላፊነት አለባቸዉ። 'ዉሃ ሽቅብ ይፈሳል ወይ እንዳትሉኝ...' ታዲያ ምን ይደረግ ...መንግስት በጠብመንጃ ስለሚያስተዳድር ነዉ የማንናገረዉ ...ቤተክርስቲያን ግን የእግዚአብሔር ደጅ ናት። የአቡነ እገሌ ብቻ አይደለችም ... እስቲ እመብርሃን አትለየን። መጪዋን ሱባዔ ይቀበለን እንደሆነ እንበርታ።
ከብሪታኒያ
“ጢሞቲዎስ ሆይ በውሸት ዕውቀት ከተባለ ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍና መከራከር እየራቅህ የተሰጠህን አደራ ጠብቅ” ጢሞ ፮:፳
ReplyDeleteወንድሞቼ አንድ ነገር እስቲ እናስብ በቤተክርስቲን ይህ ወጀብ የተነሳው በማን ሃጢአት ነው?
ReplyDeleteበአባቶች(በጳጳሳት) በደል ነው?እንዴት ብሎ... ዘመናቸውን በሙሉ ለእግዚአብሔር ሰጥተው በነሱ ትፈተናለች?ቢሆንስ ከነሱ በተሻለ ቃሉን፣ መንፈሳዊነቱን ልንረዳና፣ልንተነትን እንችላለን?ለቤተክርስቲያንስ እንቆረቆራለን ብለን ልንል እንችላለን?እኔ ግን ይከብደኛል!
በሰባኪያን እጥረት ነው?ከፍተኛ መንፈሳዊ ተቋማት፤ሰ/ት/ቤቶች፣የስብከተ ወንጌል ማኅበራት፤የአንድነት ጉባኤያት፤በተስፋፉበት እንዴት እጥረት ምክንያት ይሆናል?!
እንደው በጠረፍና በውጭ(ብዙ ካህናት በሌሉበት) ካሉ ወገኖች በስተቀር እኛ ቃለ ወንጌልን ከመቸውም ጊዜ በላይ በብዛት አልተሰበከልንምን?
የገዳም አባቶች ጸሎት ተቋርጦ ነው?ገዳማውያኑ ምግባቸው ምን ሆነና!እሱስ ቢቀር የዘወትር ቅዳሴ መች ታጎለ በእንተ ቅድሳት መች ተዘለለ!
ግድ የላችሁም ወዲህ ነው ነገሩ!
ይህ መከራ የመጣው በኔ ይሆንን? እንበል፡፡ግድየላችሁም ነው፡!!!ማንንም አንኮንን
አባቶችን እንዲህ ከፈተነ ሰይጣን እኛንማ እንዴት ያበጥረን ይሆን?
መልካም ዜና ከእመብርሃን ጋር በዚህ ጉዳይ የምንነጋገርበት ጾመ ፍስለታ እነሆ ከፊታችን፡፡እንጠቀምበት፡፡
ዳንኤል ስለሁሉም ምስጋና ላቅርብ፡፡እኔን የሚያሳስበኝ እስከመቼ ይሆን የአህዛብ መወያያ የምንሆንው
ReplyDeleteከ አዲስ አበባ
“ሚስቴ አትረባ ፤ልጄ አትረባ፤ወንበሬ አይረባ እኔ እራሴ አልረባም” አለ ክበበው ገዳ።
ReplyDeleteየሚረባ ካህን የሚረባ ጳጳስ የሚረባ ምእመን የሚረባ መነኩሴ በአጠቃላይ የሚረባ ሰው ጠፍቶአልና እግዚአብሔር
አሕመድ ግራኝን ይጥራ ወይስ ዮዲት ጉዲትን ያስነሳ?
ሰው የሚዘራውን ያንኑ ያጭዳልና እንደ ስራችን ከሆነ ፍሬአችን ከግራኝና ዮዲት ጉዲት የከፍ ካልሆነ የተሻለ ሊሆን አይችልም።
Firdu hulu le Egziabher yihun !
ReplyDeleteዲ /ን ዳንኤል ስለ ቀናውና ጥርት ያለው አመለካከትህ
ReplyDeleteእጅግ አከብርሃለሁ
""መታረቅ ወይስ መታረቅ "" ያልኸው ነው ዋናው ነጥብ ::
ስለዚህ ጉዳይ አንዳንድ ነገሮችን ብናይ
1ኛ , ጥሉ በራሱ የዞረ ድምር እና ከአገር ፖለቲካ ጋር በቀጥታ ተያይዞ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ነው ::
ቀደም ሲል በነበሩት የሩቅ ዓመታት : ነገሥታቱ የቤተ መንግስቱንም ሆነ የቤተ ክሕነቱን ሥልጣን ጠቅልለው ይዘው :
የውስጥ አገልግሎቱንና የክሕነቱን ተግባር ብቻ የሚመሩ ጳጳሳትን ከግብጽ በማስመጣት እስከ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት አዝዝልቀውናል ::
ዐፄ ኃ /ሥላሴም , አንዳድንድ ቀና ቀደምት ነገሥታት ሲደክሙበት የነበረው ተምኔት /ምኞት ተፈጽሞላቸው : ቤተ ክርስቲያኗን ከኮፕት የበላይነት ነጻ አውጥተው : በራሷ አባቶች እንድትመራ አደረጓት ::
ከዚሁ ጋር በተያያዘ : የመጀመሪያውም ሆኑ ሁለተኛው ፓትርያርኮች ሲመረጡ : ከአባትነታቸው በተጨማሪ ለንጉሡ ቀራቢዎች እንደነበሩ ይነገራል ::
መዘዙ የጀመረው እዚሁ ጋ ሳይሆን አይቀርም ::
ምክንያት
ሀ , ደርግ ሲነግሥ : ""ምንም ሃይማኖት የለሽ ቢሆን "" ሕዝቡንና ቤተ ክሕነቱን ለመቆጣጠር ስለፈለገ : ፓትርያርኩን አስሮ : ይመቹኛል ብሎ የገመታቸውን : ከአንዴም ሁለት ጊዜ እንዲሾሙ ማድረጉ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰወረ አይመስለኝም ::
ለ . ሶስተኛውና አሁን በስልጣን ያለው ገዢ መንግስትም ቀደምቱ በከፈቱለት መንገድ ቀጠለና ""የደርግ "" ያላቸው አባት በጫና አውርዶ : ራሱ የፈለጋቸውን ፓትርያርክ እንዲሾሙ አደረገ ::
አሁን በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ ያለው ችግር : በዚህ መስመር የተላለፈና መሠረታዊ ሥር ነቀል ለውጥ የሚያስፈልገው ዓቢይ ጉዳይ ነው ::
ግን እንዴት ሆኖ ? ይህ ነው ዋናው ጥያቄ !!!
አገራችን ውስጥ ያለው : የአባ ጳውሎስ አስተዳደር እየፈጠጠ ከመጣው እውነታ እንደተረዳነው : በመንግሥት ኃይል እየተደገፈ : ማፊያ ቡድን በማደራጀት :
. ደጋግ አባትቶችን የሚያንገላታና የሚገድል
. በቅንነት ለማገልገል የሚነሱትን ሁሉ ቅስማቸውን የሚሰብርና ጀርባቸውን የሚያገብጥ :
. የቤተ ክርስትቲያኗን ሀብት እንደ ጠላት ገንዘብ : በጠራራ ፀሀይ ለጋለሞታዎችና ለወሮበላዎች የሚናኝ ;
. በቤቱ ውስጥ መንፈሳዊነትና ፈሪሃ እግዚአብሔር ተረስቶ : ውንብድናና ዘላንነት እንዲነግሥ የሚያበረታታና የሚያደራጅ ኃይል ሆኖ አርፎታል ::
በአጠቃላይ : የክርስቶስ ቤት ሳይሆን : የተወሰኑ ግለሰቦች ህ ጥፉና ክፉ ተግባር የሚካሄድበት : የግል አክሲዮን እየመሰለ በመሄድ ላይም ነው ::
""ይህ መንግሥት እስካለ ድረስ : ማንም አይነካኝም "" እያሉ በመሳሪያ የሚመኩት አባ ጳውሎስ የሚመኩበት መንግሥት : እሳቸው በሕይወት እስካሉ እንዲቀጥልም : ታጋይ ካድሬዎችችን በቤተ ክርስቲያኗ ታላላቅ የመምሪያ ቦታዎች እስከ መሰግሰግ ድረስ : ሽንጣቸውን ገትረው ይሟገቱለታል ::
2ኛ , በውጭ ራሳቸውን ስደተኛ ... ብለው የተደራጁት አባትቶችችም ; ይህን በሚገባ ያውቁታል ::
እነሱ የሚፈልጉት አሁን በሥልጣን ያለው ገዢ መንግሥት : በሆነው መንገድ ተወግዶ ሌላ መንግሥት ሥልጣን ሲይዝ : መብታችንን አስከብረን : በተራችን ሥልጣኑን እንይዛለን ብለው የሚቋምጡ ናቸው ::
ለዚህ ህልማቸው ያግዛቸው ዘንድም : ጠንካራ ተቃዋሚ መስሎ የታያቸውን ሁሉ ከመደገፍ ጀምሮ : ረጃጅም ቀሚሳቸውንና ቆባቸውን ለብሰው , መስቀላቸውን ቀስረው ,..... ሰላማዊ ሰልፍ ከመውጣት ወደ ኍላ እንዳላሉ ባለፉት ዓመታት ታዝበናቸዋል ::
ስደተኛ እየተባለ የሚጠራውን : ቤተ ክርስቲያን በቦርድ አስተዳደር ገብተው የተቆጣጠሩትም እኒሁ የተቃዋሚ ፖለቲካ ሰዎች መሆናቸው ፀሀይ የሞቀው , አገር ያወቀው የአደባባይ ምሥጢር ነው ::
ማጠቃለያ :
ያለምንም ጥርጥር : ቤተ ክርስቲያኗ ከሁለት የተከፈለቺው በፖለቲከኞች ጣልቃ ገብነት ነው ::
ኢ .ሕ .አ .ዲ .ግ . ሲገባ : ከአባ መርቆሬዎስ ጋር አልሰራም ባይል ኖሮ : ቤተ ክርስቲያኗ ቀጥ ብላ በሰላም ትሄድ ነበር ::
አቡነ መርቆሬዎስ "ሥልጣኔን ለቅቄያለሁ ቢሉም ባይሉም "" ከመንበራቸው ላይ የተነሱት ግን : በመንግሥት አስገዳጅነት እንጅ በፈቃዳቸው አለመሆኑን መቸም ቢሆን የማንክደው ሀቅ ነው ::
ወይ በአገሪቱ ውስጥ ነጻ አስተዳደር ካልተመሠረተ : አለያም , ፖለቲከኞች በቤተ ክርስቲን አስተዳደር ውስጥ ጣልቃ መግባታቸውን ካላቆሙ :
ቤተ ክርስቲያን , መቸም ቢሆን ነጻ አትወጣም : ሰላም አታገኝም ::
እነ አባ ጳውሎስ እንታረቅ ቢሉም
የመንግሥትን ፖሊስ ካልተከተሉ በቀር : የማይሞክር ጉዳይ ነው
እነ አባ መርቆሬዎስ እንስማማ ቢሉም
አጅበዋቸው ያሉት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች አያፈናፍኗቸውም : ሊፈቅዱላቸውም አይችሉም :: [/b]
አገራችን : ነጻ አስተዳደር ሲኖራት : ያኔ ቤተ ክርስቲያናችንም ነጻ ትወጣለች ::
ማሳሰቢያ
የተለያዩ ፈተናዎች ከውስጥም , ከውችጭም ቢኖሩም ::
ማኅበረ ቅዱሳን : በያዘው ቀጥተኛ መንገድ : መቀጠል አለበት ::
Great article ! Qale hiwot yasemalin..
ReplyDeleteTo tell you the truth, I never believed that the 'negotiations' would bear fruit. Never. The so called 'fathers' in America can't afford to come to a united Church, because the thing is broken beyond repair. I don't think both parties are willing to bend a little to accommodate the other. I don't think anything could happen as long as the 'big' players are alive.May be in the next generation...if we (the concerned
"mi'emenan") are working on it today, united! Sorry to say this but there is no other way... believe me! Remember we are Ethiopians, born to fight.
God bless,
Ankiro
Z-Gebriellua
ReplyDeleteስለእርቅ የምትሰብኩን ስለፍቅር ½ስለሰላምና አንድነት እለት እለት የምታስተምሩን ተግባር ተግባሩን ግን ለኛ የምትተውልን አእይንተ እግዚአብሔር አበው ሆይ! ለናንተስ ይህንን የነገራችሁንን አስተምህሮ ተግባር ላይ እንድታውሉት በነዌ ተማፅኖ አላአዛር ከሙታን ተነስቶ ይስበክላችሁን? ወይስ የሁሉም ባለቤት የሆነው መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደገና ተወልዶ ስለሰላም ስለፍቅር ስለእርቅ ሲል በመስቀል ላይ ተቸንክሮ ይታያችሁን?
ዳንኤል ምንድን ነው ጥፋተኛን ማቆሻበል። በሰማነው መፍረድ አለብን። ጥፋተኛዉ ስደተኛው ሲኖዶስ ነው። ያላወቃችሁት አለ ካሉ ይንገሩን። ወይ መንፈሳዊ አለበለዚያ አለማዊ ይሁኑ። እንዲያቀላቅሉ ከፈቀድን ጥፋቱ የራሳችን ነው ፣ ማላዘኑንም ፈጣሪን ማማረሩንም እናቁም።
ReplyDeleteዳንኤል ምንድን ነው ይሄ ጥፋተኛን መደበቅ፣ሌሎቹን ማነካካት። በሰማነው መፍረድ ይገባናል። ያላወቃችሁት አለ ካሉ ይንገሩን። ጥፋተኛው ስደተኛው ሲኖዶስ ነው። ወይ መንፈሳዊ አለበለዚያ አለማዊ ይሁኑ። እንዲቀላቅሉ ከፈቀድንላቸው ጥፋቱ የራሳችን ነው ፣ ማላዘኑንም ፈጣሪን ማማረሩንም እናቁም።
ReplyDeleteThe initiative should be appreciated,but i believe the response given by the religious leaders in USA is not acceptable to their status and our orthodox beliefe.It mimics like Mengistu`s responce in his recent book saying `weyane ena shabiya yikrta teyikewgnal`.we expect religious fathers to behave better.
ReplyDeleteEgziabeher yebarkeh danny ante yedershahen eyetewetah neew lehulum lib yest KE ABU DHABI
ReplyDeleteDanny, ante endalkew enezih "tilikun dabo lit" yaderegu sewoch bitarekus yitsenalu bileh tasibaleh? Menfesawinet sayinor be-erik menor yeminor ayimeslegnim. . . .
ReplyDeleteDanny ante gin Berta, MEDHANEALEM yabertah
Dan first I like to say 10x a lot 4 what U did till 2day, but till to day I was expecting one journal about "TEADROS II" please share us what U have in Ur mind,...
ReplyDeleteለእውነት እንቁም ለሰላም ለፍቅር
ReplyDeleteነገ ለሚመጣው መመለስ ሳይቸግር
እርቅን የማይወዱ ፍቅር የሌላቸው
ቃሉን የዘነጉ ባዶ ጋኖች ናቸው፡፡
የለህም ቢሉትም ዝምታውን አይተው
አይፈርድም ቢሉትም ትዕግስቱን ረስተው
ነገ ትነጋና መኖሩን ያውቁታል
ፍርዱም ብድራቱም ከቶ መች ይቀራል፡፡
ለሁላችንም ማስተዋሉን ይስጠን፡፡
I don't understand the problem with the Ethiopia sinodos. They already send their representative. They want to discuss and solve because there is a problem. It wasn't necessary to point their finger in one peron from the four representative. Please Dani and other EOTC followers come to the truth. Eskemechenew rasachin yeminatalilew. The problem is with the foreign Sinodos and with most diaspora. Leselam Minim kidme-huneta ayasfeligim. God only knows their thinking. We can't judge on the Ethiopia sinodos because they already send their representative. Metsihaf yemilew eko wendimih bibedilih hideh yikirta teyikew new yemilew. Lemetarek sihedu eneziyawochu eshi malet neberachew. Gins metarek silemayifeligu ketareku Ethiopia wuste hidew patryaric mehone silemayichilu embi alu. This is the true reason.
ReplyDeleteዳኒ የእርቅ ነገር መነሳቱ በ ራሱ ጥሩ ነገር ነው፡፡ ሆኖም ተቻኩሎ መግለጫ ማውጣቱ ተገቢ አይመስለኝም፡፡ ለሰላም ውውይቱ መቋረጥ ዋናው ምክንያት ምን እንደሆነ አስታራቂው ቡድን ከሰጠው መግለጫ መረዳት ይቻላል፡፡ አሁንም እከሌ ጥፋተኛ ነው ፡፡ አይደለም እከሌ ነው ጥፋተኛ፡፡ ብንል ለማንም አይጠቅምም፡፡በተለይ ለቤተክርስቲያን ሰላም ብለን መወገኑን እንተው፡፡ በዛ ላይ ከሶስቱም ወገኖች መግለጫ መረዳት እንደቻልነው አሁንም የስላም በሩ አልተዘጋም ብቻ እኛ ተስፋ መቁረጥ የለብንም በጸሎት መበርታትና አግዚአብሔር እንዲረዳን መለመን ብቻ ነው ያለብን፡፡መተቻቸቱ ለማንም አይጠቅምም፡፡ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንጸልይ! መልካም ሱባዔ።
ReplyDeletedany kale hiywot yasemalin
ReplyDeleteDo you think Ezhi Ethiopia yalut Abatoch ready for Erk? If they were ready there are a number of good abatoch to settle the issue. However they were not ready.Because they sent the person the Americans don't want to see. Ye wechochu look like they are ready because they notified in advance the person shouldn't be included. There fore abatoch wede America yemetut they now it won't be successful. What surprizes me is that this article didn't include this fact.May be in the future you may grow to see the full picture of the issue rather than saying one thing. Please let's be part of the solution.Trying to influence your opinion is something unacceptable. By the way do you have all the facts? If you have why didn't you include in your article? At least read the 3 meglechas. If you don't better not to rush to write article like this.
ReplyDeleteDaniel,
ReplyDeleteGood article.
However, I think you seem to be biased against the fathers in exile. You seem to misrepresent their position about one of the delegates from Addis. The fathers in exile alledge that the particular person had a position that he did not acknoweledge Patriarch TekleHaimanot and Patriarch Merkorios. If that person really believed that this is true, he was attempting to erase a two decades history of our church. This belief also is a corruptted attempt to legitimize Aba Paulos as the 3rd and cannonical patriarch.
Both Daniel and the readers above have chosen not to address this fact. If one of the delegates from Addis did not acknowledge the existence of Patriarch Teklehaimanot and Patriarch Merkorios in our church history,is it not legitimate to ask that person to reconsider his position or he be excluded from the discussion?
I notice we the laity have two problems. We are ill informed of the motives of the government's hand through Aba Paulos. Secondly, we are misguided to believe that Aba Paulos came to power in cannonical order. When rules are violated, anarchy prevails. The turmoil in our church is because of the violation of the Churches cannon.
Lets not fear to state the truth bluntly. Lets not blame the victims of injustice. Lets not belittle the issues of the fathers in exile as merely a question of power.
Genuin reconcilation will only be achieved if we objectively address the problem.
May the Lord safeguard oure beloved Orthodox Tewahido Church.
May God bless us all.
Dani,
ReplyDeleteMost of the time you write credible artilces. but in this article you are shy to face the facts. I would strongly recommend you to listen German radio at least. Many people is hoping to see the unity of our Church.This is a very delicate issue. From your articles you seem you don't want to see the union of the Church. If you do you couldn't have written the information in part.Lebona yisten lela min yibalal.
Hello Daniel,
ReplyDeleteYou are one of the guy for being witness with pretext to support Aba Paulos. You messed up many things in North America without having a knowledge on the matter or probably just siding for Aaba Paulos and dividing the people. You, just throuh your insult on some fathers without knowing your stage. Please be advised that you shall talk for the thing you only KNOW. Besides, please know your level.....You just behave not as Dn. but as apop.
Lib yistih
Emebetachin tirdan enji lela min yibala yalnebere yebete kirstian tarik sifeter, fetenan malef yaltechalew ...
ReplyDeleteAs I understand from the readers and writer of the article they fear the union of the church fathers. Because they put themselves in category A and B. So when A+B the result will be whole. But those in A don't like B's conversely B's don't like A's. It's what is.Little minds discuss people or groups. Great minds discuss issues. Hope next time Daniel can discuss the issues rather than fight for the group he is sided according to his article.
ReplyDeleteBetam Yigermal yehone interview lay anden neger sakerbe megemeriya mrejawochen esebesebalehu belehe neber gin yahunu laye mereja alayehem mekineyatume eniya le ereku mefarese mikneyat yehonute sew yadereguten neger min endehone eyaweke ende kelale neger weyem endalawek alefehale yehe betam asazenognale yeza sewe neger demo Amlake bemiyawekewe huneta alefuwale.
ReplyDeleteመዘጋት ካለበት ይኬ ወሬኛ ማህበር ነበር መዝጋት ለትርፍ የተቁዋቁዋመ አጭበርባሪ ማህበር
ReplyDeleteሳሙኤል ዘ ገዳመ ዋሊ
ReplyDelete