Tuesday, August 17, 2010

ሕዝቤ ዕውቀት በማጣት ጠፋ (ሆሴዕ 4፣6)

ሰሎሞን ይኼይስ - ሚነሶታ

እንደ እኔ እምነት የቤተ ክርስቲያንን ችግሮች ከውጭ ሆኖ መፍታት አይቻልም፡፡ ውኃን ከውኃ ውጭ መዋኘት እንደማይቻለው ሁሉ፡፡ በውስጡ ያሉ አገልጋዮች ችግሩን ተረድተው የመፍትሔው አካል መሆን አለባቸው፡፡ እኛ ከውጭ ያለነው ድጋፍ ሰጭ ነው ልንሆን የምንችለው፡፡

በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የሚገኙ ጳጳሳት፣ መነኮሳት፣ ካህናት፣ ሰባክያን፣ ዘማርያን እና የሰበካ ጉባኤ አመራሮች ሁሉ በቤተ ክርስቲያናችን ያሉ ችግሮች እንዲቀጥሉ የሚፈልጉ አይደሉም፡፡ የችግሩ ተዋንያን ጥቂቶች ተጠቂዎች ግን ብዙዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም የመጀመርያው ነገር ዕውቀቱን እና ንቃቱን መፍጠር መሆን አለበት፡፡

በመሆኑም የሚከተሉትን ነገሮችን መጠቆም እወዳለሁ፡፡

1 ለንስሐ አባቶቻችን እና ለሰበካ ጉባኤያት ኮፒ እያደረግን ብንሰጣቸው እና ብናወያያቸው፡፡

2 ይበልጥ ደግሞ ገንዘባችንን አሰባስበን እነዚህን ጽሑፎች በመጽሐፍ መልክ አሳትመን በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አባቶች እና  አገልጋዮች እንዲደርሳቸው ብናደርግ

ይህ ኅትመት ደግሞ በቀላሉ እንዲዳረስ ከፈለግን የኅትመቱን ወጭ እኛ በመሸፈን በነጻ ወይንም በርካሽ እንዲያገኙት ብናደርግ ጥሩ ነው፡፡

3 የመንግሥት አካላት እነዚህን ሃሳቦች እንዲያገኟቸው መንገዶችን ብናመቻች፡፡ እንደኔ ሃሳብ የመንግሥት አካላት ሁሉ ችግሩን ይፈልጉታል ተብሎ መታመን የለበትም፡፡ ከባለሥልጣናትም ኮ የቤተ ክርስቲያን ነገር የሚያሳስባቸው ይኖራሉ፡፡

4 ሚዲያዎችም እነዚህን ሃሳቦች እንዲያንፀባርቁና ከእነዚህም የተሻሉ ሃሳቦችን እንዲያቀርቡ ብናበረታታቸው፡፡

5 comments:

 1. እኔም በዚህ በሰሎሞን ሃሳብ እስማማለሁ ማለትም ለአባቶችና ለምመናን እንዲደርሳቸው ለማድረግ በሚለው እንዲሁም ለተጠቀሱት አካላት በተለይ ግን ለአባቶች በሚለው። በ አንድ ወቅት ከአንድ ታላቅ የቤተ ክርስቲያናችን አባት ጋር በእግዚአብሔ ርፈቃድ አብረን ውለን አድረን ነበር ታዲያ ለኚህ አባት ከደጀ ሰላምና ከዳንኤል እይታዎች አነብላቸው ስለ ነበር በጣም ነበር የሚያዝኑት እነኝሕ ጽሁፎች በሃገር ቤ ጋዜጣዎች ይወጣሉ ወይ ነበር ያሉት ይሃ ለሁላችንም ጳጳሳስት ቢደርስ መልካም ነበር ያሉት እኛም እንጽፍ ነበር ብለዋል
  ስለዚህ ከእኛ ምን ይጠበቃል አቅጣጫውን ጠቁመን መስመር ማሲያዝ ያስፈልጋል ለመጀመሪያ ባሉበት በፖስጣ በየመንበረ ጵጵስናቸው እያልኩ ሃሳቤን እገታለሁ እናንተም ጨምሩበት

  እግዚአብሔር ቸር ወሬ ያሰማን

  ReplyDelete
 2. በጣም ያሳዝናል በእግርጥ ሰሚ ካለ የሰሎሞን ሀሳብ ይደገፋል
  ሰው ነው ብለህ ስትነግረው አውሬ ሆኖ ታገኘዋለህ

  ማን ነው ዛሬ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ደራሿ? መልስ የለም ሁሉም በሆዱ ማጉረምረም ነው እንጂ እንደ ደጀሰላም የራሳችንን ሳይት ብንከፍት ሁላችንም የምንለውን እንላለን። ቢያንስ በመናፍቁም እንደተነቃበት ያውቃል
  እግዚአብሔር አይለየን

  ReplyDelete
 3. ሰማይ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፡፡ ነህ 2፥20

  ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ፡፡ ያዕ 1፥22

  ከእናንተ ጥበበኛ አስተዋይ ማን ነው? ያዕ 3፥13

  ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን ማለት ይገባችኃል፡፡ ያዕ 4፥15
  Yetwedachu wegnoch melkamun huulu endnadrg yehneon metshaf enbela degmo memhran siastmeru drshachn wastewalen yehun enberta yenh web yekft Amlak yasenan Ke Canada

  ReplyDelete
 4. Yemefithe hsaba eyesetachu yalachuh Egziabher yibarkachuh.

  Ene bebekule kehulum kidimiya lisetew yemigebaw Solomon Yiheyis yakerebew ye D.n Daniel tsihufochin be metsihaf melk astmo maserachetina gilts wuyiyit endidereg madireg new. Enezihin yezemanichin gudoch hulum yawukachewal. Gin defiro meweyayet yemiasfera endehone enawukewalen. Silezih miemenanu endih ayinet wuyiyit endijemir ber mekifet asfelagi new biye aminalehu. bergitegninet ezih ketenesut lay yemichemeru great ideas hizibu yakerbal, especially chigirun ategebu hono elet elet eyedema yalew ye agerbetu miemen.

  Silezih tsihufochu enditatemu yidereg, Bank account tekefito contribute adirgu bibal, i thing no body will complain.

  Egziabher yetegibar sew yadirgen.

  ReplyDelete
 5. በቅደሚያ በቆራጥነት ችግሩን ያለ ፍርሃት ገለጦ በማቅርብ ስለመፍትኄው እንድንውያይ ያደረገን ዲ.ዳንኤልን እግዚአብሔር ይጠብቅልን ።

  የሰለሞን ሃሳብ ጥሩ ነው ሆኖም እንቅስቃሴያችን እንደነ ብ/አ ሳሙኤል ትግል በነሆድ አምላኩ ድል እንዳይደረግ በጥልቀት በተጠና አካሄድ መሄድ ያስፈልገናል ብዪ አምናልሁ።

  እግዚአብሔር እንደ ዮሐንስ አፈወርቅ ያለ አባት ይስጠን

  ፍስሐ

  ReplyDelete