በአንድ ሀገር ውስጥ አንድ ኩሬ ብቻ ነበረ፡፡ የሀገሩም ሰዎች ውኃ የሚጠጡት ከዚያ ኩሬ ነው፡፡ አንድ ቀን የሀገሩ ሽማግሌዎች ለድግስ ተሰብስበው እያለ ውኃ ተቀዳ፡፡ ውኃው ግን ቆሻሻ ነበረ፡፡ ተጋባዦቹ በተቀዳላቸው ውኃ ተበሳጩና ሌላ ውኃ እንዲቀዳላቸው ጠየቁ፡፡ ነገር ግን በድጋሚ የተቀዳው ውኃም ቆሻሻ ነበረ፡፡ በዚህ ጊዜ ተጋበዡ በሃሳብ ለሁለት ተከፈለ፡፡ አንዳንዱ ችግሩ ከብርጭቆው ነውና ብርጭቆው መቀየር አለበት አለ፡፡ ሌላው ደግሞ የለም ሌላ ውኃ እንደገና መቀዳት አለበት አሉ፡፡
ክርክሩ እያየለ በመሄዱ ሁለቱም ነገሮች እንዲደረጉ ተወሰነ፡፡ ብርጭቆውም ተቀየረ፤ ውኃውም እንደገና ተቀዳ፡፡ ነገር ግን አሁንም ውኃው ንጹሕ ሊሆን አልቻለም፡፡ በዚህ ጊዜ አንድ ጠቢብ አዛውንት አንድ ሃሳብ አመጡ፡፡ «እስኪ ውኃው የሚቀዳበት ኩሬ ይታይ» ሲሉ፡፡
እርሳቸው የሰጡትን ሃሳብ ተከትሎ ኩሬው ታየ፡፡ እውነትም ኩሬው ቆሽሾ ነበር፡፡ እኒያ ሽማግሌም «ውኃ እየቀያየርን ስንቀዳ፣ ብርጭቆም ስንቀይር የኖርነው እንዴው በከንቱ ነው፡፡ ችግሩ ከብርጭቆውም፣ ከተቀዳውም ውኃ አልነበረም፡፡ ችግሩ ከምንጩ ነበር» አሉ፡፡ ከዚያም የመንደሯ ሰዎች ተሰብስበው በመውረድ ኩሬውን ከልዩ ልዩ አቅጣጫ መጥተው ካበላሹት ቆሻሻዎች አጸዱት፡፡ የመንደርዋም ነዋሪ ንጹሕ ውኃ መጠጣት ጀመረ ይባላል፡፡
ይህ ታሪክ ከቤተ ክህነታችን ታሪክ ጋር ይመሳሰላል፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክህነት ያጋጠመውን ፈተና በተመለከተ ከምእመናንም ሆነ ከተቆርቋሪ ወገኖች ሁለት ዓይነት መፍትሔዎች ይሰማሉ፡፡ የመጀመርያው ችግር ፈጠሩ የምንላቸውን ሰዎች በሌሎች ሰዎች መተካት መፍትሔ ነው የሚል ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ የቤተ ክርስቲያንዋን ሕንፃዎች፣ቢሮዎች፣ መኪናዎች፣ ወዘተ መቀየር ችግሩን ይፈታል ብሎ የሚያምን ነው፡፡
የሰዎች መለዋወጥ ችግሮችን በመጠኑም ቢሆን አይፈታም ተብሎ አይታመንም፡፡ ከዚህም በላይ የተሻ ሰዎች ለተሻለ ዕድገት የእመርታ መሠረቶችም ይሆናሉ፡፡ ወይንም ደግሞ ዕድገቱን በማፋጠን፣ተፈላጊውን ለውጥ በማቀላጠፍ እና ውጤቱን በማስቀጠል ከፍተኛ ሚናም ይኖራቸዋል፡፡
ነገር ግን የግለሰቦች መለዋወጥ ብቻውን የቤተ ክህነቱን ችግር አይፈታም፡፡ ሕመሙን በመጠኑ ይቀንሰው ካልሆነ በስተቀር፡፡
አንዳንድ ወገኖች የቤተ ክህነቱን ችግሮች ከሥር ከመሠረታቸው ስለማናያቸው አሁን የተፈጠሩ ወይንም በተወሰኑ ግለሰቦች ምክንያት የተከሰቱ፤ ያለበለዚያም ደግሞ እንግዴ ክስተት አድርገን እናያቸዋለን፡፡ ብዙዎቹ ፈተናዎች ግን ዛሬ ተባብሰው፣ ወይንም መኖራቸውን ራሳቸው በራሳቸው ገልጠው፣ ያለበለዚያም እኛ ለማወቅ ችለን ይሆናሉ እንጂ እዚያው ቤተ ክህነቱ ውስጥ ተወልደው ያደጉ ናቸው፡፡
ለምሳሌ ቁልፍ ፈተናዎቻችን የሆኑት ዘረኛነት፣ ፖለቲካዊ ጥገኛነት እና ያልተስተካከለ አሠራር ዛሬ የተጀመሩ ነገሮች አይደሉም፡፡
በቤተ ክህነቱ ታሪክ የሸዋ፣ የጎጃም፣ የጎንደር፣ የትግሬ እየተባሉ የሚነገርላቸው ዘመናት አሉ፡፡ እነዚህ ዘመናት ያለ ሃፍረት ሲነገሩ ስንሰማ ዘረኛነት ሥር ሰድዶ የኖረ ፈተና እንጂ ዛሬ የመጣ ወረርሽኝ አለመሆኑን እንረዳለን፡፡ አልፎ አልፎ እንደነ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልእ ያሉ አበው ከንፍሮ መካከል እንዳመለጠች ጥሬ ይህንን ፈተና ቢያልፉትም ብዙዎች ግን «እገሌ ያገሬ ሰው ስለሆነ» እያሉ በኩራት መናገርን፣ መመካትን እና መጠቀምን ያለ መሸማቀቅ ሲተገብሩት ኖረዋል፡፡
በውጭ ሀገር እየኖረ ይህንን እቃወማለሁ የሚለው ወገኔም ቢሆን ቤተ ክርስቲያኑን በታቦቱ ስም ከመጥራት ይልቅ በወንዙ እና በጎጡ መጥራት የሚቀናው ነው፡፡ «የነ እገሌ ቤተ ክርስቲያን» የሚባል ኑፋቄም፣ ዕብደትም የሆነ አመለካከት እንደልቡ እጁን ከትቶ የሚጓዘው እዚያው ባሕር ማዶ ነው፡፡
አንዳንዱም ቢሆን እነ እገሌ የሚያደርጉትን የሚቃወመው የርሱ ወገኖች ስላልሆኑ እንጂ ተግባሩ ስሕተት ስለሆነ አይደለም፡፡ ያለበለዚያማ «እነ እገሌ እዚያኛው ቤተ ክርስቲያን ሞልተውታል» እያሉ እያማረሩ ለራስ ወገን እና አመለካከት ብቻ ሌላ ቤተ ክርስቲያን ማነፅ መች ይኖር ነበር፡፡ አንዳንዴ እንዲያውም ጥፋቱን ለምን እኛ አላጠፋነውም የሚባል ሁሉ ይመስላል፡፡ ከዚያም ባስ ሲል የአንዳንዶቻችን እምነት «የጎመን ምንቸት ውጣ የሥጋ ምንቸት ግባ» ዓይነት ነው፡፡
ፖለቲካውን መንተራሱንም ቢሆን ከጥንት ለምደነው የመጣን ነው፡፡ ቤተ ክህነቱ ከቤተ መንግሥቱ ጋር መሳ ለመሳ ሆኖ መኖሩ ጠቅሞታል? ወይስ ጎድቶታል? በሚለው ላይ እንወያይ ካልሆነ በቀር አብረው አልሠሩም ማለት ግን አይቻልም፡፡ በርግጥ አንዳንዶቹ ይህንን ክስተት የኢትየጵያ ብቸኛ ክስተት እያደረጉ ሊያወግዙበት ይነሣሉ፡፡ ነገር ግን ቤተ ክህነቱ ቤተ መንግሥቱን ተጠቅሞ ለሀገር ፣ለወገን፣ ለወንጌል መስፋፋት እና ለድኅነት የሚጠቅም ሥራ እስከሠራ ድረስ ለምን አብራችሁ ሆናችሁ ተብሎ ሊወቀስ አይችልም፡፡ ከጥንቶቹ የነአብጋርን እና የነቆስጠንጢኖስን፣ ከሀገራችን የነአብርሃ እና አጽብሃ፣ የነካሌብን እና የነ ገብረ መስቀልን መጥቀስ ይቻላል፡፡
ነገር ግን ቤተ ክህነቱ በቤተ መንግሥቱ አሉታዊ ተጽዕኖ ውስጥ ወድቆ መለካዊ /ፈቃድ ፈጻሚ/ ከሆነ ግን ችግር ነው፡፡ ትናንትም ሆነ ዛሬ በዘመናዊው ዓለም ቤተ መንግሥቱን በማቅናትም ሆነ በማገዝ፣የቤተ መንግሥቱንም እገዛ በመጠቀም የሚሠሩ አብያተ ክርስቲያናት አሉ፡፡ የሩሲያን፣ የአርመንያን፣ የግሪክን አብያተ ክርስቲያናት መጥቀስ ይቻላል፡፡
በሀገራችንም በንጉሡም፣ በደርግም ሆነ በኢሕአዴግ ዘመን ቤተ ክህነቱ ከቤተ መንግሥቱ ጋር ሠርቷል፡፡ ሁለቱም ተከባብረው እና ተጠባብቀው፣ ነጻነታቸውን ጠብቀው እና ተረዳድተው እስከ ሠሩ ድረስ ሁለቱም ይጠቀማሉ፡፡ ይህ ሲፈርስ ግን ወይ ሁለቱም አለያም ቢያንስ አንዱ ይጎዳሉ፡፡
እስካን ባሉኝ መረጃዎች ከቤተ ክህነት ውጭ በሆኑ ጸሐፍት ለፖለቲካ እና ለዘር በነበራቸው አመለካከት የተደነቁት ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ናቸው፡፡ በዘመናቸው የነበሩ የደርግ አባላት በጻፏቸው መጻሕፍት ይህ አቋማቸው በአድናቆት ተዘክሯል፡፡ ለምሳሌ «ነበር» በተሰኘው የዘነበ ፈለቀ ክፍል ሁለት መጽሐፍ ላይ «ለምሳሌ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ብጹእ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እንደራሴ የመሆን ፍላጎት አልነበራቸውም፡፡ በብዙ ልመናና ማግባባት «እሺ እንዳላችሁ ይሁን» ከአሉ በኋላ የእጩ ተመራጭነት ቅፅ እንዲሞሉ ተሰጥቷቸው በመጠይቁ መሠረት በማከናወን ላይ እንዳሉ «ብሔረሰብ» የሚል ረድፍ ላይ እንደደረሱ «አልፈልግም ያልኳችሁ ለዚህ ነው፡፡ እኔ በየትም ቦታ፤ በማንኛውም ጊዜ የምወክለው ሃይማኖቴንና ምእመናንን ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ወኪል የመሆን ተልዕኮ የለኝም፤ እንዲኖረኝም አልፈልግም፡፡» ብለው በማንኛውም ሁናቴ የፖለቲካ ወጋግራ መሆን እንደማይሹ በጠንካራ አንደበት ተናገሩ፡፡በቅጹም ላይ ሳይፈርሙበት «ያውላችሁ» ብለው ሊሄዱ ተነሡ፡፡ «ኧረ ግድ የለም ይተውት ብጹዕ አባታችን» ተብለው ያመኑበትን ብቻ በቅፁም ላይ አስፍረው ያላመኑበትን ትተው ፈረሙ» ይላል፡፡ ገጽ 107
ይቀጥላል
Very interesting
ReplyDeleteKalehiwot Yasemalen Dn. Daniel
ዲ/ን ዳንኤል ሰላም ላንተ ይሁን።
ReplyDeleteይህንን ፅሁፍ ሳነብ በተለይ የብፁዕ አባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት እንደራሴ ያለመሆን ፍላጎታቸው እና "እኔ በየትም ቦታ፤ በማንኛውም ጊዜ የምወክለው ሃይማኖቴንና ምእመናንን ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ወኪል የመሆን ተልዕኮ የለኝም፤ እንዲኖረኝም አልፈልግም፡፡" በማለት የመንፈስ ልጆቻቸውን ከፖለቲካ እና ከዘር በፀዳ ፍፁም አባታዊ በሆነ አመለካከት ማገልገላቸውን ስመለከት ምን እንደመጣብኝ ታውቃለህ?
አንዱ የለም እንጂ አንዱማ ቢኖር፣
ስንቱን እንደገና እንፈጥረው ነበር።
ያሉት የእነዚያ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ያገኘሃቸው ልጆች ጨዋታ ነው በአእምሮዬ የታወሰኝ።
ቕዱስ እግዚአብሔር እንደ ብጹእ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ያሉ ደጋግ አባቶችን ምነው ቢያንስ ቢያንስ እንደ ማቱሳላ 969 ዓመተ ቢያኖራቸው?
ቸር ያሰማን።
this is real! berta Dani.
ReplyDeleteWudi wendime,
ReplyDeleteBe-ewunet tikikilegna asteyayet new yesetehew. Yebetekihinet chigir ahun aydelem yetejemerew yebizu gize zemenat chigir new. yihinin chigir degmo bitinat bitagez yebelete tiru yihonal. Endewendim lante yemimekirew yihinin chigir bitatenana mefitihe bititekum tiru new. Lemisale chigirechu lemtikes: Be bizu ageligayoch(Be teley ye betekihinet timihirt bedemb yaltemaru ageligayoch), Le-abatoch , ke Like Diakon jemiro eske papas , yemisetew kibirye kelik yalefena yewushet, yemasmesel kibir new. Le shumet, lesiltan, Le genzeb yemiset kibir new. Bizu ageligayoch le tikim yekomu enji be' ewunet lehayimanotachesw, lebetekiristiyanachew, le miemenachew gid yelachewum. Bedagim mitsiat Bekistos fit le fird yemikerbum aymeslachewum.Yihin zengitewutal chirash. Bizuwochu mi'emenan benezih wushetegnoch ageligayoch bezer be poletika aquam kemeselwuachew yidegifiwauchewal. minim enquan wushet biyaweu binageru, Dibin yale hatiat biserum. Lemisale Ye abune morkerewos ye americaw patryarik binaye dibin yale hatiat new yeseru. Hizbun tito, sema'etnet fertew(Menist endayigedilachew fertew)hizbun le tekula tilew sihedu America metew ene negn patriyarik silwachew amen bilew tekebeliwachew. Eski egziabher yasayachihu ye Ethiopia hizib wede America eyehede new ke patriyariku libarek Ehadeg eskiwedk dires malet new. Endet bilo lihon yichilal weyis le transport yichilutal. Betam, betam tilik sihitet be Ethiopia tarik. Le Kibrachew, Letikimachew silu hizib kefafelu, kezih befit yalinebere sir'at aderegu. Bizu ageligayoch endezih nachew sirachew. Tikimachew esketekeber dires ye miemenan hiwet yibelash ayibelashim minim ayimeslachewum. Biziwoch Mi emenanin kemeqawem yilike bezer be plotitica ketemesaseliwachew amen biew mekebel new. minim enquan andande me'emenainin binoru betikikil yemikawemu bizu sew gin besimet yemigauzinew yalew. Abetu, O Egziabher amlakachi kezih kesimet weten beteregaga menfes yeminasibibet ena yeminastewulibet menfes adilen. God bless Ethiopia.
Dear Dn. Daniel, it is really an interesting issue and I look forward to read the next part soon.
ReplyDeleteለጊዜው ዉሃዉን እያጣሩ መጠጣት አይቻልም ወይ፡ ምክንያቱም ኩሬውን ለመጥረግ ከፍተኛ ወጪ ይጠይቃል እና
ReplyDeleteሰላም ዲ/ን ዳንኤል፦
ReplyDeleteጥሩ መልእክት ያለው ጽሑፍ ነው እንደተለመደው። ቃለ ሕይወት ያሰማልን - በረከቱን ያብዛልህ።
እኔ እንደሚመስለኝ የዚህ ዓይነቱን ችግር (በቤተክርስቲያናችን) መቅረፍ የሚቻለው ለዘር/ለጎጥ... ወዘተ የቆሙ የቤተክርስቲያን አመራር አባላትን (በየቦታው)በእውነት ለቤ/ክ አንድነትና እድገት በቆሙ ሰዎች መተካት ነው። ይህ ደግሞ በትውልድ /generation/ የሚሠራ ሥራ ነው። ቀስ በቀስ ካልሆነ በአንድ ጊዜ የሚሆን እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ምክንያቱም ለዚህ ሥራ የሚተጉ እውነተኛ ክርስቲያኖችን በዘመናችን ማግኘት በጣም አሰቸጋሪ በመሆኑ (ከላይ ከቤተክህነት እስከ ታች...)ቀስ በቀስ ለመለወጥ መነሣት የሁሉም እውነተኛ የተዋሕዶ ልጅ ኃላፊነት ሊሆን ይገባል።
እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅ ... ሌላ ምን ይባላል - ያልታደልን
አንክሮ ዘደ/ሰ
mechereshachin yasamirew Amlakachin.AMEN
ReplyDeleteThank you dear brother for raising this timely issue. I hope you will write the solutions too and it will show us some kind of direction. See you in part two. And I will say my comments then
ReplyDeleteEgzibher yirdan
+ + +
ReplyDeleteThank you very much! dn.Dani for pointing out the root cause "egna gin eko ke-1 belay minch alen, yeminch ameraretachin ketestekakele ena kureyachinin gedamatin kaderegin chigiru yemefetat tesfa yinorewal"
Amlak minchun yatsidalin!
Selam Dani,
ReplyDeleteTiru eyta newe.Negeren keseru wehan ketru endemibale anteme ye betekerstianene chegere menashawe ke meche jemro mehonune ye jemerekew tsehufe legna be semetawinet le menfered sewoche melakam newena ketelebete.yalwenem melkame ena makam yalhonu negerochen be ye anstaru mekrebu ye anten kale bemewsed/ teyme hasabe/beywlhu
Amelak beretatune eysethe
Azeb Ze Minnesota
እህት ትእግስት ውሃውን ከምንጩ አጣርቶ መጠጣት ስለተቻለማ ነው ጥቂት ጤናማ ሰዎቸን በየብሎጉ እና በየቤታቸው እርር ድብን ሲሉ የምናየው ምንም እንኳን የሚወስዷቸው መፍትሄዎች በሙሉ ትክክለኛ ናቸው ባይባልም እውነተኛውን ዛፍ ለመደበቅ ብዙ የሃሰት ዛፎችን መትከል የዲያቢሎስ ስልት ነው እውነተኛ እና ፍሬአማውን ዛፍ በጥንቃቄ ፈልጎ ማግኘት ደግሞ ለዘመኑ ክርስቲያኖች የተሰጠ ሰማዕትነት ነው::
ReplyDeleteለጊዜው ዉሃዉን እያጣሩ መጠጣት አይቻልም ወይ፡ ምክንያቱም ኩሬውን ለመጥረግ ከፍተኛ ወጪ ይጠይቃል እና
ReplyDeletetigist, እርግጥ ነው ችግርን ከስሩ መፍታት ከባድ ወጭን ይጠይቃል:: ቤተ ክህነቱ አሁን ባለበት ደረጃ ግን ችግሩን ማጣራት የበለጥ ብዙ ወጭን የሚጠይቅ ይሆናል:: ሙስናው፣ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ያልሆኑትን ወደ ውጭ መላኩ ( human trafficing), የባዕድ አምልኮን ማንገሱ፣ የቤተ ክርስቲያናችን ያልሆነውን ይትበሃል ማስገባቱ፣ወደፊት ካሁኑ ይባስ መሪ አልባነትን ማስፈኑ፣ኧረ ስንቱ:: ይህንን ሁሉ እያጣራን እንቀጥል ከተባለ እዳው ከባድ ነው:: በዚህ የሚጠፉ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ቁጥር እዳውን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል:: እንደ እኔ አስተያየት ችግርን ከምንጩነው:: ለዚህ ሁላችንም ልንረባረብ ይገባል::
ReplyDelete@ትግስት
ReplyDeleteእባክሽን እንደገና "የአንድ አባት ምክር" የሚለውን አንብቢው
ዳኒ የሚቀጥለውን በጉጉት እጠብቃለው ሦስተኛ ክፍል እንደሌለው ተስፋ አደርጋለው፡፡እናመሰግናለን ለትብብር
please write detail about this idea. because in one research conference Daniel said speak about this idea(about BETEKIHNET, BETEMENIGIST, & other related ideas)not detiley & also write today in this website not detaily.please write detailed about this idea....
ReplyDeleteplease write detail about this idea(about palace,BETEKIHINET,& ...related ideas).because in one research Daniel will speak about this idea but not speak detaily & not write detaily today in this website.please write detail about this idea.....please....
ReplyDeleteD/n. Berta. Eski hulachininim Asmesayoch ena wedenefesebet yeminadela sayhon ewenetegna kiristiyanoch yadirgen.Amen.
ReplyDeleteወንድሜ ሆይ! ዋናው ችግር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሙሉ በሙሉ ፍጹም እውነት በሆነው በእግዚአብሄር ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ አለመመራቷ አይመስልህም ?!
ReplyDeleteአድናቂና አክባሪህ ነኝ።
kale hiwot yasemalene
ReplyDeleteDear Dani,
ReplyDelete* You put the pre-existed reality perfectly.
* There is saying that "Understanding the problem by it self is solving 50 percent of the problem."
* As you said "YE WENZE LIJ ABAZE" was disturbing the church during Haileselassie I,Derig and current EPRDF regimes.A live evidence to this is the book named YE HIYAW MISIKIR which was written by Abune Melketsedik of America.The book shows how the racial outlook was pushing the church in early times.Such books which stands for one ethnic group point of view is contrary to our TEWAHIDO basic thought.I think when Abune Melketsedik raised the problem of the church in his book he suppose to look from the universal point of view.
Ameseginalehu
Thanks Danie, well said. I am looking forward to reading the next part. History helps us to understand what is really happening how. You are right, the problem we see in EOTC is not new but it is becoming blatant now. It is too significant to compromise. It reminds me the boy’s saying to his mom, who was under penalty after his theft of a cattle..Minew be enkulalu gize begerefishign noro.
ReplyDeleteDear.Dani,it is vary easy to clean the 'Kure' from its dirty tributaries but it is vary hard to clean our self especially if the person doesn't now how much kilos of dirties does he carry .'Yekoyen'.'egeziabher agelegelotken yibarklehe.'
ReplyDeleteማጣሪያውስ ንጹሕ ካልሆነ?
ReplyDeleteDn.Danie
ReplyDeleteGood job you are going to sacrifice to our church.
We always with you .we are going to die for our mother church
God bless you and your family
July 28, 2010 2:34 PM
ReplyDeleteዳኒ approve ማድርግ ቀረ እንዴ? የሰውን አሳብ ማክበር እስከምን ድረስ?
Dear Dani,
ReplyDeleteThank you so much! I look forward reading the next part! Would you please write more about the life of Abune Tekilehayimanot, from which we can learn plenty. Medihani-alem Tsegawun yabzalih.
በእውነት ደስ የሚል እና የሚያስማማ ምልከታ ነው። በቤተክህነት ውስጥ ያለው ችግር ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ የዘር በሽታ ይመስላል። እኔ ብዙ ጊዜ የቤ/ክንን አስተዳደር ሳስብ ተስፋ የምቆርጠው ችግሩ ይህ በመሆኑ እና ለመፍታትም ሌላ ትውልድ ወይም ሥር ነቀል ለውጥ እንደሚያስፈልገው ሳውቅ እና እኔም ይህንን ለውጥ ሳላይ እንደማልፍ ስረዳ ነው። ይህን የምለው ለውጥን ለማየት ከመመኘት ነው። ቤ/ክናችን የዋህ እና አማኝ ምእመን አላት ግን ሰብሳቤ እና የምትኮራበት፡ አርዓያ የሚሆን አባት አጣች።
ReplyDeleteየየዋኃን አምላክ ሁሉንም የስተካክልልን። አሜን።
Well said danny, thanks for posting. I can't wait till u post the next part. I appreciate u. keep it up. let me ask u a qn. u are always posting articles like this, but no action has been taken yet. bezu ngeroch eko sehetete endhonu egname eyayne new. gin endi bidrge teru new maletu sayebje ayeqrem.....anyways, keep it up dear.
ReplyDeleteGod bless our country.
Dear Dani,
ReplyDeleteyour message is really touching. I wish many people visit your blog and read your messages. Soooo important, especially at this critical moment. As the first commentor said, at this time the situation in Awassa is heart breaking. But your messages gives much strength not to go away, but remain within do whatever we can. One day, who knows the Almighty may come to us with a big stick to clear those mafias whose minds are filled with MANY
I hope you would compile your messages into a book for a wider audience in the near future. Those with internet access are limited.
Medihani-alem tsegawun yabizalih
ዳኒ የማይነካውን ነው የነካኽው ባትጀምረው መልካም ነበር እንግዲህ ጨርሰው ። ክፍል ፋይ እየሰጡ ልብ ማንጠልጠሉ ይቅር የአንተን ጽሁፍ ቋንጣ እስኪሆን የመጠበቅ ትእግሥትን በራስዋ የሚፈታተን ነውና።
ReplyDeleteFor july 28,2010 2:34 posted comment
ReplyDeleteDon't mix the issue with the Bible. If you proced even my self I can Scan the virus you have with the anti virus of the Ethiopian orthodox church for religious affairs
Dear D/N Daniel
ReplyDeleteThanks as usual
One of th guys said "the problem is b/se the Church is not established on the true base(Bible)".
This guy has to read the bible that the winds and the storms are pushing the vessel where God is found.
The truth is those people can not practice as per the bible and canons of the Church.
The problem is not the mirror, but the face of the people.
If the case is as you said, where are St. Atnatius, St. TekleHymanot, Pope Shinoda, Arc Bishop Gorgorius(II) etc from? are they not the fruit of this Church?
thank you dani
ReplyDeletethank u dani
ReplyDeleteእንደምን አለህ ወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል?
ReplyDeleteእባክህ ከቻልክ ይህንን ጽሁፍ ቀጥልልን: ቀጣዩን ክፍል በጉጉት እየጠበቅን ነው::
astemarina mekari new, Dn.Daniel EGZIABHER ye agelegelot zemenehen yebarekeleh.Amen
ReplyDeleteዲን ዳኒ እባክህን ወደ ሌላ ከመሔድህ በፊት ይሔንን ጨርስልን. ድንግል ታበርታህ
ReplyDelete" ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥ ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ተጐናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፥ እንድታይም ዓይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ። " ራእ.3:17
ReplyDeleteሰላም ላንተ ይሁን ዲ/ን ዳንኤል
ReplyDeleteይህ ጉዳይ ቤተክህነት ውስጥ ላደግን ሰዎች ምን አልባት አዲስ አይሆንም። ለሁሉም ነገር መንስኤው ምንም አይነት መንፈሳዊነት በውስጣችን አለመኖሩ ነው። በሚገርም ሁኔታ ዘረኝነት የበረታባቸው አንድ አባት ከሌላው ወገን ጋር በመጣላታቸው የተነሳ ከሳቸው ወገን ያልሆንውን ምዕመን በመጥላት ወገኔ ብለው ለሚያስቡአቸው እስማኤላውያን እየነገሩ ሲረግሙ ስሰማ በእጅጉ ገረመኝ። ምንም እንኩአን በጣም የምወዳቸው አባት ቢሆኑም እምነት አስጥሎ ወገኑን እና በክርስቶስ ደም አንድ የሆነን ክርስቲያን መርገም በእጂጉ አሳዝኖኛል...ስለዚህ ትልቁ ዘረኝነት ስለመሆኑ ምንም ሊደንቀን እና ሊያስገርመን አይገባም።
አምላክ ሆይ አንተ ታደገን!!!!
Dear Dn. Daniel,
ReplyDeleteThank you for your effort.
The church is in severe problem. I sometimes feel that it is committing suicide. But it is not something that came as a surprise. It has been there for hundreds of years. Believe it or not,it is this same mess that has given birth to the bigger mess in our country. The best way of healing, is learning from mistakes in the past and try to deal with it properly. I do believe that it can be solved. But I feel that we lack the required set up. Such as:
(a)God's support.
Not because he is not willing. Instead because, we are running without him. OR it may also be becuase this is what the time takes.
(b)well educated and purposeful believers
(c)A pastors sent by God (rasachewin yemiliku sebakiyan sayihon begizabiher yetelakutin)
(d)Political atmosphere (atleast they should now that they should stay away, if they don't have the will to help in solving it)
(e)Responsible religious leaders (those who also live according to their faith). I put this in the end because this is what caused the problem. The church has a clear dogima and cannon, if we have(b) and (c) we can slowly create (e). In addition, to solving things of Administrative manner in the short term.It should be borne in mind that I am not suggesting that there are no leaders at all.
The other alternative is just God's interference but I am not that faithful to ask/suggest for this one. So, I guess we need to try to bring about these required footings. We also should know what we are doing and How it affects the church, our living, our country and so on. Other wise, zimbilo chuhet gedel mamito meliso lemesimat endayihonibin.
selame egizabiher kehulachin gar yihun
Tekle gebriel
Egziabher yistilin, Diakon Daniel. Bizu neger ansitehal endalkewim betekirstiyanachin lezemenat ke mengistat ga sertalech mengistinim tekma tetekimalech. Yihem sihon bebelaynetna yerasuan bilom yehageruan guday lemakanat enji ye mengistatin guday(agenda) lemasifetsem endalhone yitawekal. Fetenanim endihu asalifalech. Betam yemiasazinew degmo yetekeskew zer memiretina wegentegna mehon kedem yale ye betekirstianachin fetena mehonu new. Ene betam yekirb gize chigir yimeslegn neber, beteley gosan yamakele ye mengist astedader ahun kalew agezaz ga ye kirb kurignit kemenoru antsar...Eskahun dires betam yemiasazinegn gin beteley be abatoch alemegbabat tefetiro eyale ke mengist akal(endeshemgay bemehon) lezawim emnet yelelachew sewoch tetertew meftihe felagi endihonu mederegachew sihon ahunim sastawisew erasen yemiamegn kistet new...Emebetachin mengedachinin takana kefetenam endiniweta miljawa ayileyen!! Antenim edme yistilin endetekorkuarinetih degmo semi joro yalewna endihum letegbarawi/ewnetegna lewt abro seri abatochim hone wondimoch ena ehitoch yabzalih,amen!!
ReplyDeleteheyaw egzeabhear yestelen enmesgenalen
ReplyDelete