Friday, July 23, 2010

ንጉሡ ራቁታቸውን ናቸው

ሁለት እራት አግባ ብልሃተኞች ወደ አንድ ንጉሥ ግቢ ያመሩና ደጅ ይመታሉ፡፡ የግቢው ጠባቂም አቤት ይላል፡፡ እነዚያ ብልሃተኞችም «ለንጉሡ ኃጢአተኛ ሰው የማያየው አዲስ ልብስ ልንሠራ መጥተናል» ይላሉ፡፡ ግቢ ጠባቂውም ሲሮጥ ሄዶ ለንጉሡ ጉዳዩን ያቀርባል፡፡ ንጉሡ ይፈቅዱና ሰዎቹ ገብተው እጅ ነሡ፡፡ «ምን ዓይነት ልብስ ነው የምትሠሩት» አሉ ንጉሡ፡፡ ብልሃተኞቹም «ኃጢአት የሠራ ቀርቶ ያሰበም ሰው ሊያየው የማይችል አዲስ ዓይነት ልብስ ነው» ሲሉ ማብራርያ ሰጡ፡፡ ንጉሡም በነገሩ ተደስተው የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ መድበው ልብሱን እንዲሠሩላቸው አዘዙ፡፡

በወርቅ እና በብር የተንቆጠቆጡት፣ ልዩ ድርጎ እና ቤት የተሰጣቸው እነዚያ ብልሃተኞች ቤቱን ዘግተው ሥራ ጀመሩ፡፡ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ንጉሡ አንዱን ባለሟላቸውን ሥራው የት እንደ ደረሰ እንዲያይላቸውት ላኩት፡፡ ብልሃተኞቹም ተቀብለው አስተናገዱት፡፡ ባለሟሉ ወደ ቤታቸው ሲገባ የሚያየው ነገር አልነበረም፡፡ ባዶ የልብስ መሥሪያ ማሽን፣ ባዶ ጠረጲዛ እና ባዶ አዳራሽ፡፡ ግራ ተጋባ፡፡ ከብልሃተኞቹ አንዱ ወደ ጠረጴዛው አመራና «አዩ ጌታው፤ እጀ ጠባቡ እያለቀ ነው» አለው ባዶውን ጠረጴዛ እያሳየ፡፡ ባለሟሉ ግን እንኳን እጀ ጠባብ ብጫቂም ጨርቅ በጠረጴዛው ላይ ለማየት አልቻለም፡፡ ነገር ግን «ኃጢአት የሠራ ሰው ልብሱን ማየት አይችልም» ተብሏልና «አላየሁም» ቢል ኃጢአት ስለ ሠራህ ነው የሚለው እንጂ የሚያምነው ስለሌለ «በጣም የሚገርም እጀ ጠባብ ነው፡፡ መቼም ንጉሣችን ሲያዩት ይደሰታሉ» ብሎ ራሱን እየነቀነቀ አደነቀ፡፡ በልቡ ግን ግራ እንደተጋባ ነበር፡፡

«ንጉሥ የሚያምረውን እንጂ የሚያምርበትን፣ ንጉሥ የሚፈልገውን እንጂ የሚያስፈልገውን አይነግሩትም» ይባላልና ወደ ቤተ መንግሥቱ ተመልሶ ለንጉሡ «እጅግ የሚገርም፣ ዓይን ያላየው ጆሮም ያልሰማው ልዩ የሆነ እጀ ጠባብ ተሠርቷል፡፡» ሲል ሪፖርቱን አቀረበ፡፡ አሁንም ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ንጉሡ ሌላ ባለሟላቸውን ላኩት፡፡ ያም ባለሟል ወደ ብልሃተኞቹ ቤት ገብቶ አካባቢውን ሲያይ ደነገጠ፡፡ እንኳን የተሰፋ ልብስ የተዘረጋ ክር የለም፡፡ ነገር ግን የቀድሞው ባለሟል አየሁ ብሎ ይሄኛው አላየሁም ቢል ከጓደኛው ማነሱ ነው፡፡ ብልሃተኞቹም ወደ ጠረጴዛው ወስደው «እጀ ጠባቡ ይህንን ይመስላል፤ ሱሪው ደግሞ በመሰፋት ላይ ነው፡፡ የሚቀረን ጫማው ነው» እያሉ ማስጎብኘት ቀጠሉ፡፡

ባለሟሉ እንኳንስ አዲስ የተሠራ እጀ ጠባብና የተሰፋ ሱሪ ቀርቶ አሮጌ ልብስ እንኳን እንኳን ለማየት አልታደለም፡፡ ነገር ግን ኃጢአተኛ ከሚባል «እንደ ዘመኑ ይኖሩ እንደ ንጉሡ ይናገሩ» ነውና «ይህንን ነገር ለማየት በመታደሌ ፈጣሪዬን አመሰግነዋለሁ፡፡ ይህንን ነገር ለማየት ፈልገው ያላዩ ስንት አሉ፡፡ በሥራችሁ ንጉሡ እንደሚደሰቱ ርግጠኛ ነኝ» ብሎ አመስግኗቸው ወጣ፡፡ በልቡ ግን «እነዚህ ሰዎች ያሾፋሉ እንዴ፤ ምን ዓይነት ነገር ነው እየሠሩ ያሉት» እያለ ያጉተመትም ነበር፡፡ ለንጉሡም ድንቅ ነገር ማየቱን ከዚያኛው አስበልጦ አንቆለጳጵሶ አቀረበ፡፡

በመጨረሻ ራሳቸው ንጉሡ የሥራውን ማለቅ ለማየት ከባለሟሎቻቸው ጋር መጡ፡፡ እነዚያም ብልሃተኞች እንደተለመደው ወገባቸውን አሥረው ማስጎብኘት ጀመሩ፡፡ «ይሄ እጀ ጠባቡ፣ ይሄ ሱሪው፣ ይሄ ካባው፣ ይሄ ጫማው ነው» እያሉ ያሳያሉ፡፡ ንጉሡ ምንም ነገር ለማየት አልቻሉም፡፡ ነገር ግን የእርሳቸው ባለሟሎች አየን ብለው እያወሩ እርሳቸው አላየሁም ቢሉ ራሳቸውን ማስገመት ነው፡፡ ሕዝቡስ ምን ይላል? ደግሞም ዋናው ነገር እርሳቸው አየሁ ማለታቸው እንጂ ማየታቸው አይደለም፡፡ ይህንን ሁሉ አስበው «በሕይወቴ ላየው የምፈልገውን ነገር ነው ያየሁት፡፡ በነገሥታት ታሪክ እንደዚህ ያለ ልብስ መልበሱ የተነገረለት ንጉሥ የለም፡፡ ልዩ የሆነ ሽልማት ይዘጋጅላችኋል» ብለው አድናቆታቸውን ገለጡ፡፡ አጅበዋቸው የመጡትም ምንም ነገር ለማየት ባይችሉም ኃጢአተኛ እንዳይባሉ ሲሉ አደነቁ፤ አመሰገኑ፡፡

«ንጉሥ ሆይ» አለ አንደኛው ብልሃተኛ «ሕዝቡ ሁሉ በዐዋጅ ተጠርቶ ይህንን ልብስ ለብሰው ማየት አለበት»፡፡ የንጉሡም ባለሟሎች «እውነት ነው፤ ይህንን መሰሉ ልብስማ የቤት ልብስ አይሆንም» ብለው እያዳነቁ ሃሳቡን ደገፉት፡፡ ንጉሡም ተስማሙ፡፡

ዐዋጅ ታወጀ፡፡ «ንጉሡ ኃጢአት የሠራ ሰው ሊያየው የማይችል ልብስ ስላሠሩ እንዲህ ባለ ቀን፣ እንዲህ ባለ ቦታ፣ በዚህ ሰዓት ወጥታችሁ እንድታዩ» ተባለ፡፡ በተባለውም ቀን ሕዝቡ ጉድ ለማየት ግልብጥ ብሎ ወጣ፡፡ ንጉሡም ወደ ብልሃተኞቹ ዘንድ መጡ፡፡ ሁለቱ ጓደኞች እየተረዳዱ ንጉሡን ማልበስ ቀጠሉ፡፡ እነዚያ ብልሃተኞች ንጉሡ የለበሱትን ልብስ ሙልጭ አድርገው አውልቀው «አሁን ሱሪውን፣ አሁን እጀ ጠባቡን፣ አሁን ካባውን» እያሉ አለበሷቸው፡፡ ንጉሡም እየሳቁ፣ፈገግ እያሉ፤ በዙርያቸው የተሰለፉትም ራሳቸውን እየነቀነቁ ልብሱን ለበሱ ተባለ፡፡ ንጉሡም በልባቸው «ራቁቴን ሊያስኬዱኝ ነው እንዴ?» ይላሉ፡፡ ግን አይናገሩትም፡፡ ተከታዮቻቸውም «እኒህ ሰውዬ ሊያብዱ ነው እንዴ፤ ራቁታቸውን ናቸውኮ» ይላሉ ግን አይናገሩትም፡፡ አፍ እና ልብ እንደ ተለያዩ ንጉሡ ለብሰው ጨረሱ ተባለ፡፡

ከዚያም ሠረገላው ቀረበና ንጉሡ በትረ መንግሥት ጨብጠው ቆሙ፡፡ ባለሟሎቻቸውም ሰግደው አጨበጨቡ፡፡ ከዚያም ሠረገላ ነጅው እንደ ዛሬ ንጉሡን ራቁታቸውን አይቷቸው ስለማያውቅ ሳቅ እያፈነው ሠረገላውን መንዳት ጀመረ፡፡ ወደ አደባባዩም ወጡ፡፡ ሕዝቡ ሁሉ አጨበጨበ፡፡ አንዱ ለጓደኛው «ግሩምኮ ነው፤ ከየት አገኙት ባክህ» ይላል፡፡ ኃጢአተኛ እንዳይባል፡፡ በልቡ ግን «በቃ ስምንተኛው ሺ ማለት ይሄ አይደለም እንዴ፡፡ ንጉሥ ራቁቱን ሲሄድ ከማየት በላይ ምን ምልክት አለ» ይላል፡፡ ሌላው ደግሞ «ተመልከት፣ ተመልከት እጀ ጠባቡ ሲያብረቀርቅ፣ ንጹሕ ሐር እኮ ነው» ይልና በውስጡ ግን «አብደዋል፣ አብደዋል እንጂ፤ ደኅና ዘመድ አጥተዋል» ብሎ ያማል፡፡ ሁሉም ራሱን ላለማዋረድ እና ኃጢአተኛ ላለመባል ሲል ያላየውን እንዳየ እያደረገ ይጨዋወታል፡፡ በልቡ ግን ግማሹ ይስቃል፣ግማሹ ያፍራል፣ ግማሹ ይራገማል፣ ቀሪውም ያማል፡፡

ንጉሡም ከሕዝቡ የሚቀርብላቸውን ልክ የሌለው ሙገሳ እየሰሙ፤ የባለሟሎቻቸውን ውዳሴ እያዳመጡ ሰውነታቸው በሙሉ ጥርስ በጥርስ ሆነ፡፡ በውስጣቸው ግን ብርዱ አላስቆም አላቸው፡፡ ነፋሱ ይቀጠቅጣቸው ጀመር፡፡ «ምን ዓይነት ሞኝ ብሆን ነው የነዚያን አጭበርባሪዎች ምክር የሰማሁት፤ አሁን የውስጤን ብናገር ማን ያምነኛል» ይሉ ነበር፡፡

በዚህ መካከል እናቱን ተከትሎ የመጣ አንድ ሕፃን ልጅ «እማዬ፣ እማዬ እይ፣ ንጉሡኮ ራቁታቸውን ናቸው» አለና ጮኸ፡፡ በዙርያው የነበሩ ሁሉ «ዝም በል፤ ይሄ ገና ከልጅነቱ ኃጢአት የወረሰው፡፡ ምን የዛሬ ዘመን ልጆች እንዲህ ያለው ግሩም ነገር አይታያችሁ፡፡ ዝም በል፤ የተረገመ» እያሉ ተረባረቡበት፡፡ እናቱም አፈሩ፡፡ በዚህ ሰዓት ካፊያ እየጣለ ነበር፡፡ ንጉሡ ግን ፈገግታቸው እየጨመረ፣ ስቃያቸውም እያየለ ሄደ፡፡ ያ ሕፃን ልጅ ከእናቱ እጅ አፈትልኮ ወጣና ሠረገላውን እየተከተለ «ኧረ ንጉሡ ራቁታ ቸውን፤ ኧረ ንጉሡ ራቁታቸውን» እያለ መጮኽ ቀጠለ፡፡ ሕዝቡም በኃጢአተኛነቱ እያዘነበት፣ ርግማኑንም እያዥጎ ደጎደበት፣ ዝናሙም እያየለ፣ ንጉሡም እንደቆሙ ትእይንቱ ቀጠለ፡፡

ሕዝቡ ያጨበጭባል፣ ባለሟሎችም እንጀራቸው ነውና ሕዝቡ እንዲያጨበጭብ ያስተባብራሉ፡፡ ቀራቢዎቻቸው እጅ ያውለበልባሉ፤ ንጉሡም የሚቀርብላቸውን ሁሉ በደስታ ይቀበላሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሕዝቡም ያማል፡፡ በዚህ ዘመን መፈጠሩን ይረግማል፡፡ በንጉሡ እብደት ይናደዳል፣ ይዝታል፡፡ ባለሟሎቻቸውም በውስጣቸው አፍረዋል፡፡ በነዚያ ሁለት ብልሃተኞች ድርጊት ተበሳጭተዋል፡፡ እንዲህ ባለው ዘመን ባለሟል በመሆናቸው ራሳቸውን ይረግማሉ፤ ዘመኑንም ይረግማሉ፣ በውስጣቸውም ያማሉ፡፡ ግን ምኑንም አይናገሩትም፡፡ እንዲያውም በተቃራኒው ሥራቸው ነውና ሳያጨበጭብ ቆሞ የሚያዩትን ሰው «አጨብጭብ፣ ኃጢአተኛ!´ እያሉ ይቆጣሉ፡፡

ብርዱ እየከፋ፣ ዝናሙ እየጨመረ መጣ፡፡ ንጉሡም ጥርሳቸውን እያፋጩ፣ ሰውነታቸው በብርድ እየተርገፈገፈ፣ ብርዱ አጥንታቸው ድረስ እየሠረሠራቸውም ቢሆን ከመሳቅና፣ ፈገግ ከማለት፣በደስታ እጃቸውን ለሕዝቡ ከማንሣትና ራሳቸውን ከመነቅነቅ አልተቆጠቡም፡፡ ያ ሕፃን ልጅ ብቻ ከኋላ ከኋላ እየተከተለ «ኧረ ንጉሡ ራቁታቸውን ናቸው፣ ኧረ ንጉሡ ራቁታቸውን ናቸው» እያለ ይጮኻል፡፡ በርሱ ላይ የሚደርሰው ርግማኑና ቁጣውም አሁንም እንደ ቀጠለ ነው፡፡

በመጨረሻ ግን ንጉሡ አልቻሉም፡፡ ብርዱ እና ዝናቡ ከዐቅማቸው በላይ ሆነ፡፡ ሰውነታቸው መርገፍገፍ፣ ጥርሳቸውም እንደ ገጠር ወፍጮ መፋጨት ጀመረ፡፡ ውጫዊ ማስመሰያ ውስጥን ሸፍኖ መቆየት የሚችለው ጥቂት ጊዜ ነውና ንጉሡም የውስጣቸው ሕመም እንደልብ ፈገግ ለማለት እና ደስተኛ ለመምሰል አላስቻላቸውም፡፡ የሆነውን ሳይሆን እንዲሆን የሚፈልጉትን ተቀብሎ መዝለቅ አይቻልም፡፡ ሽል ከሆነ ይገፋል፣ ቂጣ ከሆነ ይጠፋል፡፡

በድንገት ንጉሡ ሠረገላ ነጅውን «አቁም!» ብለው በቁጣ ተናገሩት፡፡ እርሱም ሳቁ ወደ ድንጋጤ ተለወጠበትና አቆመ፡፡ «ያ ሕፃን ልጅ ብቻ ነው እውነተኛ፡፡ አዎን እውነት ነው እኔ ራቁቴን ነኝ፡፡ ሁላችሁም ውሸታችሁን ነው፡፡ እኔም ውሸቴን ነው» አሉና ተቀመጡ፡፡ ባለሟሎቻቸውም የቀድሞ ካባቸውን ሰጧቸው፡፡

አንዳንዶቹ ባለሟሎች «እኛ ምን እናድርግ ራሳቸው ናቸው ለዚህ የበቁት» አሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ «ጥፋተኞቹ እኛ ሳንሆን ያኔ ተልከው ያላዩትን እንዳዩ አድርገው የተናገሩት ናቸው» ብለው ወቀሱ፡፡ የቀሩትም «ሰሚ አጥተን ነው እንጂ ኧረ እኛስ ተናግረን ነበር» ብለዋል፡፡ ከሕዝቡም አንዳንዶቹ «አላልኳችሁም፣ እኔ ቀድሞም ተናግሬ ነበር» ያሉ አሉ፡፡ «ድሮም ነገሩ አላማረኝም ነበር» ያሉም ነበሩ፡፡

አንደኛው ሰውዬ ደግሞ ሁሉንም ያስደነቀ ነገር ተናገረ፡፡

«ለዚያ ሕፃን ልጅ ንጉሡ ራቁታቸውን መሆናቸውን የነገርኩትኮ እኔ ነኝ» ሲል፡፡

እነዚያ ሁለት ብልሃተኞች ግን ብራቸውን ይዘው የት እንደ ደረሱ እስካሁን አልታወቀም፡፡62 comments:

 1. በጣም መልዕክት አዘል ታሪክ ነው። ጸጋውን ያብዛልህ። አንዲት ማስተካከያ "ቂጣ ከሆነ ይገፋል፣ ሽልም ከሆነ ይጠፋል" የሚለው የቦታ መቀያየር ስህተት አለበት"ቂጣ ከሆነ ይጠፋል፤ ሽልም ከሆነ ይገፋል" ተብሎ ቢስተካከል

  ReplyDelete
 2. Wonderful king, bravo!!!

  So many leaders by now did not accept the reality and truth even at last.

  And I also appreciate HIM in the aspect that he got the truth from one small child, seems foolish for many leaders...that is why things become difficult.

  ReplyDelete
 3. Thank you Dani,

  "ENDE HITSANAT KALHONACHIHU MENGISTE SEMAYAT ATIGEBUM" ENDALEN GETACHIN
  "EGZIABHER BANDIM BELELAM YINAGERAL SEW GIN AYASTEWILIM" YALEW EYOB LE ENE ENA LE EGNA NEW.

  ReplyDelete
 4. በጣም የሚገርም ነው:: ለእውነት ከመቆም ይልቅ ምን ይሉኛልን በማለት የምናደርገው ነገር ምን ያእል እንደሚጎዳን የሚያሳይ ነው::
  ባጣም ላመሰግን እፈልጋለው:: እውነትን መናገር ትልቅነት ነው::
  እግዚያብሔር እውነትን የምንናገርበት አንደበት ይስጠን::

  ReplyDelete
 5. ዲ/ን ዳንኤል
  እግዚአብሔር ይባርክህ። ይህ በእዉነቱ አሁን በቤተክርስቲያናችን አከባቢ እየተደረገ ያለዉን ድራማ የሚገልጽ ስነ-ጽሑፍ ነዉ። እንደ አቡነ ሳሙኤል ያሉ የህፃኑ ተምሳሌት እዉነት የሚናገር ጠፍቶ፤ ያልሰሩትን ሰርተዋል ሲሉአቸዉ 'አዎን በጣም እንጂ' እያሉ በዉስጣቸዉ ግን አንድም ጥሩ ነገር እንዳልሰሩ እያወቁ የቁም ሃዉልታቸዉን "ባርከዉ" የከፈቱ የንጉሱ ተምሳሌት "አባት" መቼ ይሆን ወደ ልባቸዉ ተመልሰዉ እንደ ንጉሱ ንስሐ የሚገቡት? ? ? አዎ ብርዱ እያየ፤ ሲመጣ ምዕመናን ቁጣቸዉን ሲያሳዩ፤ በንጽህት ሃይማኖታቸዉ ፀንተዉ ሲቆሙ፤ በፀሎት ሲተጉ፤ ያኔ አምላካችን የእንጀራ አባታችንን በወላጅ አባታችን ይተካልናል።
  አምላከ ቅዱሳን ለሁላችንም አስተዋይ ልቡና ይስጠንን፤ በአደባባይ ራቁት ከመቆም ያድነን፤ አሜን።

  ከብሪታኒያ

  ReplyDelete
 6. Dn.Dani it is very interesting story that reflects the current situation what is happening in our country and mother church .
  " ewunet ena nigat eyader yigeletsal ayidel felixu... endih hono mechem ayiker ,ajabiwoch yibetenalu, baledebawochim yigaletalu, fit awurariwochim endalineberu yihonalu,alakawum endezihu wa ..yiblagnilachew lenezih mekeregnoch. hizibuma ewunetun amlak yimatsenal .Amlakachin betekiristiyanin yitebikilin.
  Ahunim mistirun yigletsilih Dani "
  DT z bahirdar

  ReplyDelete
 7. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡
  ታሪኩ በተለያየ መልኩ ሊመነዘርና ለተነተን የሚችል አስተማሪ ነገር ነው፡፡ ለእኔ ግን ይሄ ታሪክ ከፓትርያርኩ ጋር ተመሳሰለብኝ ፡፡ በዙሪያቸው ያሉ ጅቦች ሁለመናው ጥሩ ነው ያምርበዎታል!፣ ጻድቅ ነዎት!፣ ቅዱስ ነዎት!፣ እያሉ እሳቸውም በልባቸው ያልሆኑትን መሆን ስለሚፈልጉ ብቻ ፎቶቸውን ሲያሰቅሉ ፣ያለደም ሰማዕት ነዎት ሲሏቸው ይገባል እያሉ በሲሚንቶ ሐውልት ሲያቆሙላቸው እየፎከሩ ራቆታቸውን መሆናቸውብ እያወቁት ግን በዙሪያቸው ያሉት ይግብዎታል እያሉ ሳይነግራቸው በቅተዋል፣ ክንፍ አወጥተዋክ፣ ሊበሩነው ሊያርጉ ነው እያሉ በሞተር ብስክሌት እያሳጀቡ በቤተመንግሥት እንኳ እንደዚህ አይነት ቅሌት ባልተደረገበት ሁኔታ በመንፈሳዊነት ስም መንፈሳይ አድርገው እንሆ ሰውዬው እያበዱ ነገር ግን አላበዱም እያሉ እናያጅቦም ያልሆነ ጥቅስ እየጠቀሱ እነሆ በሕዝብ ፊት እያሳበዷቸው ይገኛሉ፡፡
  ፓትርያርክ ነኝ ባዩም ትንሽ ቆይተው ምናልባት እግዚአብሔር ልብ ከሰጣቸው በዙሪያ ያላችሁ ሁሉ የምትሰሩት ሁሉ አቁም እስከ አሁን ሕዝበ ክርስቲያኑ የሚናገረው ሁሉ ትክክል ነው ለካ አብጃለሁ ብለው ለጸሎት ለሱባኤ ለይቅርታ ገዳም እንደሚገቡና ጥቂት ለነፍሳቸው እና ለአእምሮቸው እረፍትን የሚያገኙበትን መንገድ ይፈልጋሉ ብዬ አስባለሁ፡፡ በዙሪያቸው የነበሩትም ድሮም እኮ እያበዱ እንደሆነ ነግረናቸው ነበር አልሰሙንም ሳይሉ አይቀሩም፡፡ ጅቦችም ሆዳችው በቀላሉ የሚሞላ አይደለም እና ሰውዬን ወዴት እንደሚመሯቸው አይታወቅም እና አሁንም እራቁታቸውን በእግዚአብሔርም በሰውፊትም መሆናቸውን የሚነግራቸው መካሪ ዘመድ ማጣታቸው ያሳዝናል እግዚአብሔር ለሁሉም ልቡና ያድልልን አሜን፡፡

  ReplyDelete
 8. ኃ/ገብርኤልJuly 23, 2010 at 2:12 PM

  ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር አምላክ ፀጋውን ያብዛልህ። እኚህ ንጉስስ ብርድና ዝናቡ ሀሰት አያውቁምና በንጉሱ ቆዳ ዘልቀው ንጉሱን ከተኙበት የሀሰትና የቅሌት ባህር ቀሰቀሷቸው። የእኛዎቹ አይደለም ዝናብ፤ በረዶ እየወረደ ምንም የማይሰማቸው ከ አዞ ቆዳ ነው እንዴ የተሰሩት???

  ReplyDelete
 9. Dn Daniel,
  Egziabher kalhiwot yasemaln. Abune Samuel bicha yezia hitsan temsalet nachew. Abune Paulos gin mechewunim bihon ende nigusu yemineku ayimeslegnim. Kehonem kemotu behuala new.

  G/Egziabher

  ReplyDelete
 10. እግዚአብሔር ይስጥልኝ!!!!! ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ!!!!!!ቅድስት ቤተክርስቲያን ጠበቃ ሰለቆመክላት የቤተክርስቲያን አምለክ በቸርነቱ ይጠብቅህ!!!!!!
  ንጉሡን ያልገሠጸዉ ነቢይ በለምፅ እንደተቀጣ ያስተማራችሁ ፤ ነገር ግን ያልገሠጻችሁ የመድረክ ንጉሦች፡ የማይክራፎን ወዳጆች፡ ድምፀ አዉራዎች፡ የሙዳይ ምጽዋት ዘራፊዎች ፡ በድሀ አሥራት ና በኩራት ገንዘብ ኪሳችሁን ያደለባችሁ ፤የሐዋርያት ተምሳሌነታችሁ የተሻረዉ የይሁዳ ብቻ የሆነባችሁ ፈርሳውያን የሐሰት ረበናት(መምህራን)፤ ያኔ አታፍሩም በንጉሡ ላይ ለመፍረድ አፋችሁን ትከፍቱ ይሆናል፡፡ ባይሆን ንጉሡ እልፍ እኛም ሺህ ዘርፈናል ብላችሁ ስበኩ፡፡ ንስሐ ግቡ፡፡

  ReplyDelete
 11. Dani ....God bless u it is realy very interesting history ....and shows the current situations of our country in every sector be it political or religions ....beteley yewistachinin eyawekin hilinachinin eyegorebeten bizu yeminasmesil egnan betam erasachinin endinay yemiyadergen yihonal biye asibalehu .....very very inteserting ...DN Dani keep it up ...i am waiting to learn more and more from this Blog

  Dinigil Mariyam kante gar tihun!!!

  Gebre
  Gondar Ethiopia

  ReplyDelete
 12. Dn. Daniel Kalehiwot Yasemalen

  ReplyDelete
 13. አይ የሰው ነገር ፡፡ ስንት ጉድ ተሸክመን በአደባባይ እንዞራለን፡፡
  ‹‹ሀጢአቱ የተከደነችለት ምስጉን ነው ››
  ቃለ ህይወት ያሰማልን ! በርታ፡፡

  ReplyDelete
 14. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡
  ታሪኩ በተለያየ መልኩ ሊመነዘርና ለተነተን የሚችል አስተማሪ ነገር ነው፡፡ ለእኔ ግን ይሄ ታሪክ ከፓትርያርኩ ጋር ተመሳሰለብኝ ፡፡ በዙሪያቸው ያሉ ጅቦች ሁለመናው ጥሩ ነው ያምርበዎታል!፣ ጻድቅ ነዎት!፣ ቅዱስ ነዎት!፣ እያሉ እሳቸውም በልባቸው ያልሆኑትን መሆን ስለሚፈልጉ ፎቶቸውን ሰቀሉ ፣ያለደም ሰማዕት ነዎት ሲሏቸው ይገባኛል አሉ፣ በሲሚንቶ ሐውልት ሲያቆሙላቸው የበለጠ ራቆታቸውን መሆናቸን ረሱት፣ እራት አግባዎች ግን ይግብዎታል እያሉ ቅዱስነትዎ በቅተዋል እኮ፣ ክንፍ አወጥተዋል እኮ፣ ሊበሩነው ሊያርጉ ነው እኮ እያሉ በሞተር ብስክሌት እያሳጀቡ ቦሌ ይዘዋቸው በረሩ፡፡
  በቤተመንግሥት እንኳ እንደዚህ አይነት ቅሌት ባልተደረገበት ሁኔታ በመንፈሳዊነት ስም መንፈሳይ አድርገው እንሆ ሰውዬው እያበዱ ነገር ግን አላበዱም እያሉ እራት አግባዎች ያልሆነ ጥቅስ እየጠቀሱ እነሆ በሕዝብ ፊት ራቁታቸውን ሆነው እንዳልሆኑ ሕዝቡም እውነታውን እንዳይናገር ጫና በመፍጠር የቁም ሐውልት ገትርው የሰውዬን እራቁትነት በዘይቤ ተናገሩ ከተሰበሰቡት ሕፃናት መካከል አንዷ እረ ፓትርያርኩ አብደዋል የማይንቀሳቀስ በድን ሆነው ቆመዋል አይናገሩም እንዴ ብላ ስትናገር እናቷ አፏን አፈነቻት፡፡
  ፓትርያርክ ነኝ ባዩም ትንሽ ቆይተው ምናልባት እግዚአብሔር ልብ ከሰጣቸው በዙሪያ ያላችሁ እራት አግባዎች የምትሰሩት ሁሉ አቁም እስከ አሁን ሕዝበ ክርስቲያኑ የሚናገረው ሁሉ ትክክል ነው ለካ አብጃለሁ ብለው ለጸሎት ለሱባኤ ለይቅርታ ገዳም እንደሚገቡና ጥቂት ለነፍሳቸው እና ለአእምሮቸው እረፍትን የሚያገኙበትን መንገድ ይፈልጋሉ ብዬ አስባለሁ፡፡ በዙሪያቸው የነበሩትም እራት አግባዎች ድሮም እኮ እያበዱ እንደሆነ ነግረናቸው ነበር አልሰሙንም ይላሉ፡፡ እራት አግባዎች ወይም ጅቦች ሆዳችው በቀላሉ የሚሞላ አይደለም እና ሰውዬን ወዴት እንደሚመሯቸው አይታወቅም፡፡ ለማንኛውም ፓትርያርኩ እራቁታቸውን እንደ ሐውልቱ በእግዚአብሔርም በሰውፊትም ቁመዋልና የሚነግራቸው መካሪ ዘመድ ማጣታቸው ያሳዝናል እግዚአብሔር ለሁሉም ልቡና ያድልልን አሜን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለዲ/ዳኒኤል ክብረት በእውነት ቃለ ህይወት ያሰማልን::የኣገልግሎት ዘመንህን እግዚአብሔር ያርዝመው::እንደዚህ ዓይነት አስተማሪና ምክር አዘል ጽሁፎች ለህይወያችን በጣም ወሳኝ ነገሮች ስለሆኑ ለወደፊት ብዙ ነገር ካንተ እንጠብቃለን እግዚአብሔር ይባርክህ:: እነዚያ በአባቶች ላይ አስጸያፊ ቃላት የሚናገሩ ልጆች ግን አስፈላጊ ምክር ብትሰጣቸው በጣም ደስ ይለኛል ::

   Delete
 15. The same story is there in the Ethiopian Orthodox Tewahido church leaders. Amazing, this is a very good view towards this point. But they can't read it and can't learn from. Their relatives couldn't tell them this story. They may tell the reverse of what has been said. And if they have the chance to read this story, they may be familiar with it by making it sensible for them that is my second horror.

  ReplyDelete
 16. Really personally I appropriate your courage on the method of your teaching,it is targeted and current issue.GOD may bless your service!. keep your way!!!
  TGT hawassa Ethiopia.

  ReplyDelete
 17. ቃለ-ህይወት ያሰማልን ዲ/ን ዳኒ። ልብ ያለው ልብ ይበል። ማስተዋሉን ያድለን።

  ReplyDelete
 18. Daniel Kibret

  You are the small child, The mad leader of the ortodox church is the king,......who am I?

  ReplyDelete
 19. ዲ/ን ዳንኤል

  እመቤቴ ትባርክህ!!!

  እ.ተ.ፍ

  ReplyDelete
 20. ቃለ ህይወት ያሰማልን
  እኛም ዛሬ እውንትን ለመናገር ፈርተን ስልምንኖር እውነቱን እውነት ሀሰቱን ሀሰት ብለን እንድንኖር ያድርገን

  ReplyDelete
 21. This week I read a piece of the biography of his glorious pope KERLOS THE 6TH of the Coptic church on HAMMAR and impressed by his life.

  We also know how glorious the present pope SHENODA THE 3RD is.

  But the church is waiting until it becomes 50 years from his death to ordinate KERLOS as a SAINT.

  Our fathers are saints, martyrs,apostles and everything while they are alive and EVEN WITHOUT ANY TYPE OF GLORIEOUS WORK COMPARABLE TO EGYPTIANS.

  let God gave us this day fathers of those type.

  ReplyDelete
 22. ዲ.ዳንኤል ባለፈው ለጻፍሁት አስተያየት መልስ አግኝቻለሁ እግዚአብሒር ይስጥልኝ። "አንቺ ክምር ያለሽ መስሎሻል....." የሚለው እንደሚቀጥል ተስፋ አደርጋለሁ። እግዚአብሒር ከክፉ ይጠብቅህ።

  ReplyDelete
 23. Egziabeher Lebetekrstianachin Be'Menfese Kidus Yemimeran Abatochin Yisten. Dn. Daniel lantem tibebunena abzito yestih. Ye'egziabeher Menfese Kidus lezelalemu bantelaye yeder!

  ReplyDelete
 24. Ye'Egziabeher menfes Kidus abzito yedrbeh!!!

  ReplyDelete
 25. Thank you dear brother,

  It is a good reflection of what is going on now a days. Since this kind of articles express what most of us are feeling their importance is paramount. I encourage you to keep up the good work.

  Dear readers,
  I believe that we need to pray for our brother and others who are serving our Holly Church with a lot of sacrifice. In addition to that we need to support them in any aspect we can. I am saying this because doing such credible work has a lot of cost now a days, not only in finance but also in many ways, which I do not want to write here. I also believe that we need to pray for those who are destructing our church, to give them a good heart to do good things rather than such a horrible thing.

  Once again dear Dn. Daniel keep up the good work. May GOD bless you, may the prayer of our Holly mother protect you and your family.

  Tesfa

  ReplyDelete
 26. Dawit N.
  Dear Dani,thank u vary much,Dani it has great theme for both leaders i.e for our church leader and also for other leaders in every aspects,it is good to say keep it up ,Dani

  ReplyDelete
 27. First, we think that who we are? why we evaluate the activities of other?why we live our life?

  ReplyDelete
 28. Lmindnew abatochachinin bebierh yemitgerfachew? daniel betam aziniebhalehu sewe yabatun hatiyat yishofinal ante endedabilos tigeltaleh gin egiziabhier yishofinal degimom feraje geta newu enji ante ayidelehim woyis ende hitsanu lige tegeletelih? ante tsadik ayidelehi?
  beterefe alemawi teretihin kmenfesawi gara atidebelalik.

  ReplyDelete
 29. መልካም መስታወት

  ReplyDelete
 30. for the last anonymos
  yeabatoch hatiyat medebeq alekew. yih new hul gize bietekrstiyanachinen sigoda yenorew. hatyat hulun tatefalech. zem kalnat , kedebeqnat betam teseletnalech. lelawunm talamdewalech. selezih tekikil yehonen tekikil, tekekel yalhonene degmo adelem malet yinorbnal. hatyatachewun eko yemndebkew yemidebek kehone new. ahun daniel yebolewun dengia bemen yidebqew beleh new. endayidebeq yemifelgut erasachew nachew. enesu beadebabay yalaferubeten, tekikil new ayidelem belo menager men yasferal. yilkes keagul Bahil telaqen ewunetn ewunet enbel atleast.

  ReplyDelete
 31. Dear Dani,
  May our mother, the mother of all, be with you and give you the grace, wisedom and strength to keep up your work. Thank you so much! Medihani-alem tsegawun yabzalih!!
  It is now high time for us to pray alot to our Lord, asking forgiveness to our sins and give us spritual fathers!! It is hadly possible to get them at the moment!!

  ReplyDelete
 32. Last anonymous i think you realy do not what you are talking here. He is not exposing thier sin they reviled thier owen sin to the world by buliding the statu like Feron.He just wrote it in a better way what every one knows "Alem yawokew tsehaye yemokew".So please do not be blind.

  ReplyDelete
 33. Dn.Daniel nurilin
  emebete titebikih hule ewnet tanagrih
  kale hiwot yasemalin

  ReplyDelete
 34. The one who says D/n Daniel
  "Lmindnew abatochachinin bebierh yemitgerfachew? daniel betam aziniebhalehu sewe yabatun hatiyat yishofinal ante endedabilos tigeltaleh gin egiziabhier yishofinal degimom feraje geta newu enji ante ayidelehim woyis ende hitsanu lige tegeletelih? ante tsadik ayidelehi?
  beterefe alemawi teretihin kmenfesawi gara atidebelalik."
  is not just to say is our fathers story but is besd on yours on description!

  ReplyDelete
 35. ሳሙኤል፡ዘአሰቦት፡said...

  በዓለም፡ላይ፡በመሰልጠን፡የሚገኘው፡የጥፋት፡ርኩሰት፣ሌሎ
  ቹን፡በሥጋቸው፡ሲፈታተናቸው፣እኛ፡ዘንድ፡ግን፡ጠልቆ፡እ
  ቤተ፡መቅደስ፡በመግባቱ፣ተዋሕዶኢትዮጵያንና፡ልጆቿን፡
  በእምነት፡እየተገዳደረን፡አሁን፡ከምንገኝበት፡ግልጥ፡ብሎ፡
  በጣዖት፡ምስሉ፡"እኔን"እመኑ፤"በሚል፡መታበይ፡መድኃ
  ኔ፡ዓለም፡ድጅ፡ላይ፡ቆሞ፡የጥፋት፡ሥራውን፡እየፈጸመ፡ነው።

  የሐሰት፡ሰባኪያኑም፡ቃለ፡እግዚአብሔርን፡እያጣመሙ፡ጣ
  ዖቱ፡ተቀባይነት፡እንዲያገኝ፡በቅጥፈት፡ጽሑፍና፡በማስፈራ
  ራትም፣በዱላም፡ሥራቸውን፡ተያይዘውታል።

  በጥፋት፡ሃይል፡እንደተራቆተውና፣በእግዚአብሔር፡ሃይል፡እ
  ንደነቃው፡ንጉሥ፡እኛንም፡ኢትዮጵያውያንን፡አንቅቶን፡ከጽ
  ዮን፡ደጅ፡ላይ፡የተከመረውን፡ድንጋይና፡ከውስጥም፡የተለጠፉ
  ትን፡የጣዖቱ፡ምስሎች፡ሁሉ፡ጠራርገን፡ለመጣል፡ያብቃን።

  አምላከ፡ተክለ፡ሃይማኖት፡ያበርታህ፣ይጠብቅህ፡ዲያቆን፡ዳንኤል።

  ጊዜው፡በሞሆኑ፡አግጦ፡የወጣውን፡ግድፈትና፡ሕገ፡ቤተ፡ክርስቲያ
  ንን፡አፍራሽ፡ተንግዲህ፡ማንም፡አደባብሶ፡ሊያልፈው፡አይችልም፤
  አይገባምም!እናስተውል!!!

  በካራ፡የወደቁት፡የተዋሕዶ፡ልጆች፡አምላክ፡ይታረቀን፤የሠማዕ
  ታትን፡ብርታት፡ለግሶን፡እኛንም፡ለተዋሕዶ፡እምነታችን፡በረ
  ከት፡ለማቅረብና፡በረከት፡ለመሆን፡ያብቃን! አሜን።


  ሳሙኤል፡ዘአሰቦት

  ReplyDelete
 36. wenime kelay asteyayet yesetehew.Sewoch sisasatu abatochim chimir memker megesets mindinew hatiatu.Abatochachin ye Nistrosin hatiat lemin alshefenum new yemitilen? Nebiyu Natan ye kidus Dawitin hatiat lamin alshefenem new yemitilegn? ene Dn.Danielin ke Nebiyatina abatochachin gar mamesasela adelem gin tsehay yemokewin be eyegazetaw yetetsafewin(Addis admas,Awramba,...)minu yidebekal.Endiawim zimita sint ye betechrisitan lijochin, miemenanin endemiasenakil atawkim? Ene Danielin "be akal ayichew alawkim" gin yetsafut lemikir ena letegsats yihonalu biye gin asibalehu.

  ReplyDelete
 37. All the member of EOTC, Pls let us pray to all, because we have a God that can do everything

  ReplyDelete
 38. አምደ ሚካኤልJuly 26, 2010 at 11:58 AM

  እግዚአብሔር ይስጥልኝ
  መልካም መልዕክት አለው

  ReplyDelete
 39. `Let it be the will of God`.May i ask u one question?I was waiting `Yedigital Leboch`.I am eager to read it.will it be available?

  ReplyDelete
 40. ኃ/ገብርኤልJuly 26, 2010 at 1:02 PM

  The one who wrote the above comment on July 25, at 11:27 AM, Shame on you.I am so sorry for this type of thinking at this time.You said "Lmindnew abatochachinin bebierh yemitgerfachew?" Are you saying this from your heart??? I do not think so. Or may be you are just getting some benefit from their wrong doings. Let me ask u one Q. Do u know BIBLE? Have u ever read it? I think never!! You said also "sewe yabatun hatiyat yishofinal ante endedabilos tigeltaleh" Are u sure? Which brand of Diyabilos do this? As to me Diyabilos encourage people to do sin more and more by giving them a lot of covering reasons for their wrong activities. Telling someone that he is in the wrong way is what we learn from our father Jesus Christ. You said also "ante tsadik ayidelehi?" Who are you to say that? To select persons based on their spiritual performance is not given to you. You said "alemawi teretihin kmenfesawi gara atidebelalik." Do you know really what alemawi and menfesawi mean? My bro/sis please let me tell u one thing. Just try first to learn. As I can see from what you wrote, there are a lot things that you have to know first before you even think to write such silly things. May God bless You.

  ReplyDelete
 41. Dani it has a good lesson for the leaders of our country & even for ourselves.

  ReplyDelete
 42. ቃለ ሕይወትን ያሰማልን።
  ልብ ያለው ልብ ያድርግ'
  ይሀ ነገር በብዙ ነገር ሊተረጎም ይቻላል።
  በየደረጃው ሁሉም ተጠያቂ የሚሆንበትም መልዕክት አለው።በአንዱ ላይ መጠቆሙን ትተንይልቅ ለሀጋረችንና ለቤ/ያናቸን የሚጠቅመውን ጸሎት እናድርግ።
  እ/ሔር ይባርክህ።
  ድንግል ትጠብቅህ።

  ReplyDelete
 43. Amazing history for our unbelivable dirty action in our heveanly home EOTC.
  Please Ethiopians and our Church family pls Pray daily simply start from SELAM LEKI on this issue.

  ReplyDelete
 44. I think all these scenes are seen when the good thing is about to happen. I hope some revolution will happen in "GLORIOUS ETHIOPIAN ORTHODOX CHURCH". The devilish statue erected in Bole will be down with the pope in no time. Many thanks Dani.

  ReplyDelete
 45. ጥሩ እይታ!! እውነትም ንጉሱ ራቁታቸውን ናቸው፡፡ ግን ለምን እሳቸው ራቁታቸውን ሆነው ቤተክርስትያንን ራቁቷን ለማድረግ ይደክማሉ እርሷ እንደሆነ በክርስቶስ ደም ነው የተመሰረተችው፡፡

  ReplyDelete
 46. Daniel,I thank you very much in did for your effort. ይህ ታሪክ ጤናማ አዕምሮ ላለው ሰው ሁሉ አስተማሪ እና ግልጽ ነው፤፤ ለኛይቱ ቤተክርስቲያን መሪዎች አግባብ ያለው ምሳሌ ነው ነገር ግን ከዚሀም በላይ ናቸው ብየ አስባለሁ ወይንም የአመለካከት ልዩነታችን ሰፍቶአል፤፤ ይህ ታሪክ የሚያሳየን ጊዜው ለእውነት ሳይሆን ለውሸት፤ ለህሊና ሳይሆን ለሆድ፤ ለአእምነት ሳይሆን ለነዋይ አገልጋይ መሆናቸውን ነው፤፤ ለመሆኑ የሚሰሩት ስራ ከህሊናቸው አያጣላቸውም፤ ለነገሩ ምን ህሊና አላቸው፤፤ እግዚዓብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ አሜን፤፤
  Abreham

  ReplyDelete
 47. ሲገልጡ እንዲህ ነን

  ReplyDelete
 48. GOD BLESS YOU DN.DANIEl.EGIZIABHER SIRAWOCHIH YIBARK KIDIST DINIGIL MARIAMIM KANTENA BEASRAT BETESETECHAT ETHIOPIA GAR TIHUN

  ReplyDelete
 49. Dn. daniel,
  it is very matchured way of calling for people who're sold for money or something else. May God keeps you safe!
  little John

  ReplyDelete
 50. ዳኒ ይህ አዲስ የአማርኛ ቅኔ ነው:: መልዕክቱን ለማግኘት ሳቅን መቆጣጠር ብቻ ነው:: ከመልዕክቱ በተጨማሪ አጻጻፉ ልዩ ነው:: ቀልብን ሙሉ ለሙሉ ይቆጣጠራል:: ልዩ የአጻጻፍ ዘዴ ነው:: እነ እንትና ( ብዙ ናቸው ) አጻጻፍ ከዚህ አይነት ጽሁፍ ይማሩ ይሆናል ብየ አስባለሁ:: ለነገሩ እኔ ሞኝ ነኝ እነሱ ለካ አይማሩም መማርም አይፈልጉም ለካ::
  እውነተኛ መሆን ግን ከባድ ነው:: እንደ ህጻኑ ልጅ ካልሆኑ::

  ReplyDelete
 51. wow it is wonderful story!

  but may i guess that this King is from Africa & two persons are from Europe.

  ReplyDelete
 52. Daniel really I learn many things from your statements. Most of us like this only being wondered out of the reality. this is a best refelction for what is being done on the moment. let us wait when the rain, the cold becomes severe he will tell the realty that he is bare with out cover. but let's pray him to come back to his original cloth before he has finished his bad journey.
  let us try to tell the truth as a child

  ReplyDelete
 53. mulugeta from harer,
  peace and Grace fore you.
  God bless you forever;i learnt many things from what you are post.
  inChrsts Love.

  ReplyDelete
 54. egzabher ethiopian yitebik

  ReplyDelete
 55. አወ ለብዙዎቻችን የምትሆን ጥሩ ተረት ናት ወሬ ወረት እበላ ባይነት በዛ የዱሮዉ የአባቶቻችን አርቆ አሳቢነት አስተዋይነት እርጋታ የት እንደገባ አናውቅም አሁን አነዚህ ነገሮች እንደሃላ ቀርነት እየታዩ ነው ይህን ትውልድ የሚዋጅ ጠንካራ አረያነት አስፈላጊ ቢሆነም ይህንን እያደረጉ ያሉት የሀገር ልጆች እጅግ ጥቂት ከመሆናቸውም በላት መስዋእት ሲሆኑ ማነም ዞሮ አያያቸውም የቅዱሳነ አምላከ እግዚአብሄር ማስተዋል ይስጠን
  አቤቱ ደግ ሰው አልቀል

  ReplyDelete
 56. interesting story and comments.

  ReplyDelete
 57. Egzer yistilign dani....Anonymusuinim(who wrote about the patriaric) ameseginalew

  ReplyDelete
 58. THAK YOU D/N DANIEL!It is so surprising that it is happening today!
  "EGZIABHER YABERTAH DINGL TITEBKH"

  ketilbet!

  ReplyDelete