Tuesday, July 20, 2010

የአንድ አባት ምክር

በአንድ ወቅት በዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም ተገኚቼ ነበር፡፡ በዚያ ገዳም የሚኖሩ አባት የነገሩኝ ነገር ለሕይወት መመርያ የሚሆን ነው፡፡ አሁን ከደረስንበት ወቅት ጋር የሚሄድ ነውና ላካፍላችሁ፡፡

በወቅቱ እንደ ዛሬው በቤተ ክርስቲያን ላይ የፈተና ማዕበል ተነሥቶ ነበር፡፡ ያ ወቅት የፖለቲካው ማዕበልም እጅግ ያየለበት ጊዜ ነው፡፡ አንዳንዶቻችን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የምንሰጠው አገልግሎት ምን ፋይዳ ይኖረዋል? ምንስ ለውጥ ያመጣል? ችግሩ እንደሆነ እየባሰው እንጂ እየተሻለው አልሄደም፤ ታድያ ጊዜያችንን፣ ገንዘባችንን እና ዕውቀታችንን ዝም ብለን እየከሰከስን ይሆን? አሁን የኛ ልፋት የክፉ ሰዎችን ክፋት ለመሸፈን እና በክፋታቸው እንዲቀጥሉ ለማድረግ ካልሆነ በቀር ችግሩን ይፈታዋል? ወዘተ፣ ወዘተ፣ ጥያቄዎች ይነሡ ነበር፡፡

ያን ጊዜ እኒህ አባት እንዲህ አሉን፡፡

«ብዙ ልጆችን የወለደች የምትወድደው ባሏ የሞተባት አንዲት እናት ነበረች፡፡ ቤተ ዘመዶቿ ምንም ሳይራሩ ያለ ፍላጎቷ ለአንድ ክፉ ባል አጋቧት፡፡ ይህ ባል ግዴለሽ፣ ገንዘብ ወዳድ፣ ጠጥቶ ከመስከር፣ በልቶ ከመጥገብ፣ በስተቀር ሌላ ሞያ የለውም፡፡ ሲወጣ ሲገባ ይደበድባታል፡፡ እንጨት ሽጣ፣ ኩበት ለቅማ፣ እንጀራ ጋግራ፣ ጠላ ጠምቃ ያጠራቀመቻትን ገንዘብ ነጥቆ ይወስድባታል፡፡ ለዘመዶቹም ይበትነዋል፡፡

የት ትሂድ? የሠፈሩ ሕግ፣ ባህሉ እና ልማዱ፣ በሙሉ የእርሷን ሮሮ እና ልመና የሚሰማ አልሆነም፡፡ እርሱን እንደ ሕጋዊ ባልዋ ነው የሚቆጥሩት፡፡ የት ሂዳ መከራዋን ትናገር፡፡ የትስ ሂዳ ከችግሩ ትገላገል?

ይህ ክፉ ባልዋ እርሷን ብቻ ሳይሆን ልጆቿንም ያሰቃያቸው ነበር፡፡ እነርሱም በዚያ ቤት ውስጥ መከራውን እና ስቃዩን፣ ረሃቡን እና ጭቅጭቁን እየሰሙ መኖር መረራቸው፡፡ በዚያ ቤት ሰላም ጠፋ፡፡ ፍቅር ጠፋ፡፡ ምንጊዜም የሚሰማው ክፉ ነገር እና ልብ የሚያደማ ነገር ሆነ፡፡ ሰው ሁሉ ስለዚያ ቤት ያወራል፡፡ መንገድ ላይ ሲያገኛቸው ስለ ቤታቸው ይጠይቃቸዋል፡፡ እነርሱም በሃፍረት ይሸማቀቃሉ፡፡ ስለዚህም እናታቸውን ጥለው ወደ ሌላ ቦታ መሄድና ስለዚያ ቤት ከማያስቡበት እና ከማይሰሙበት ቦታ መድረስ ፈለጉ፡፡ የሚችሉትን ያህል እየሠሩ፣ ለራሳቸው የሚበቃቸውን እየኖሩ፣ መከራውን መገላገል እና እፎይ ብለው መኖር አሰኛቸው፡፡

ታድያ ይህንን ሃሳባቸውን ለአንድ ሽማግሌ ጠቢብ ሰው ነግረው ገንዘብ እና ሃሳብ እንዲሰጣቸው ፈለጉ፡፡ ሄደውም አማከሩት፡፡ ያም ሽማግሌ ሃሳባቸውን ሁሉ ከሰማ በኋላ እንዲህ አላቸው፡፡

«ልጆቼ ልክ ናችሁ ሩቅ ሀገር ሄዳችሁ፣ የምትችሉትን ያህል እየሠራችሁ፣ የራሳችሁን ኑሮ በመኖር ችግሩን ሁሉ መርሳት እና መገላገል ትችላላችሁ፡፡ ምን ያስጨንቃችኋል? ቤት ያለው እዚህ ብቻ ነው እንዴ? ሀገርስ ያለው እዚህ ብቻ ነው እንዴ? ግን አንድ ነገር አስቡ፡፡ እንዲህ ማድረጋችሁ ራሳችሁን ብቻ ከችግሩ ታወጣላችሁ እንጂ ችግሩን አትፈቱትም፤ እናንተ ችግሩን ትረሳላችሁ እንጂ ችግሩን አታስወግዱትም፡፡

«ደግሞም የእንጀራ አባታችሁ እናታችሁን የበደለውን ያህል እናንተም ትበድሏታላችሁ፡፡ እስኪ አስቡት ለዚህች ለእናታችሁ ከእናንተ በቀር የደስታዋ ምንጭ ማን ነው? ሁሉም ነገርዋ የሚያሳዝን እና የሚያስመርር ነው፡፡ እናንተ ግን የደስታዋ ምንጮች ናችሁ፡፡ የእንጀራ አባታችሁ እናታችሁን ያሳዝናታል፤ የእናንተ ጥላችኋት መሄድም ያሳዝናታል፤ እርሱ ብቻዋን እንድትለፋ ትቷታል፤ እናንተ ጥላችኋት ስትሄዱም ያለ አጋዥ ትተዋታላችሁ፤ እርሱ በመስረቅ ዘረፋት፣ እናንተም ባለ መስጠት ዘረፋችኋት፤ ታድያ ከእርሱ በምን ተሻላችሁ?

እናንተኮ ያሰባችሁት ለእናታችሁ ሳይሆን ለራሳችሁ ነው፡፡ እናታችሁ ስለተቸገረች አይደለም ያዘናችሁት፣ ችግሩ እናንተን ስለነካ ነው፤ እናታችሁ ስለተራበች አይደለም ያዘናችሁት ረሃቡ ስለነካችሁ ነው፡፡ በእናታችሁ ላይ የደረሰው ችግሳይሆን ስለችግሩ ከየሰው አፍ መስማት ነው የሰለቻችሁ፤ ችግሩን ለመቅረፍ አይደለም መሄድ የፈለጋችሁት፤ ችግሩን ላለማየት እና ላለመስማት ነው፡፡

ከዚያ ይልቅ ሥራ ሠርታችሁ ገንዘብ አግኙ እና ለእናታችሁ ምግብ ስጧት፤ የሚያስርባትን የእንጀራ አባታችሁን በዚህ ትቃወሙታላችሁ፣ ልብሷን ቀይሩላት፣ የሚያሳርዛትን አባታችሁን በዚህ ትቃወሙታላችሁ፣ ስትታመም አሳክሟት፣ የሚያሳምማትን የእንጀራ አባታችሁን በዚህ ትቃወሙታላችሁ፤ የወግ እቃዎቹን ሰብስቡና አስቀምጡላት፤ዝክረ ታሪኳን ሊያጠፋ የተነሣውን የእንጀራ አባታችሁን በዚህ ትቃወሙታላችሁ፤ እርሱ እያረጀ ሲሄድ እናንተ ግን እያደጋችሁ ነው፡፡ ስለዚህም እየበዛችሁ እና እየመላችሁ ሂዱና ይህንን ቀፍድዶ የያዛትን የመንደሩን ሕግ አስተካክሉት፡፡ ምናልባት የእንጀራ አባታችሁ ቢሞት ሌላ የእንጀራ አባት ደግሞ እንዳይተካ፡፡ እንደዚያ ካደረጋችሁ እናንተ የእናታችሁ ልጆች ናችሁ፡፡ ያለ በለዚያ ግን የእንጀራ አባታችሁ ተባባሪዎች ናችሁ፡፡

ሸረሪት ታውቃላችሁ፡፡ ከሰው ቤት ግድግዳ ላይ ድር አድርታ፤ ወልዳ ከብዳ ትኖራለች፡፡ ቤቱ በእሳት ሲያያዝ ግን ከቤቱ ወጥታ ቀድማ የምትሮጥ እርሷ ናት፡፡ ቤቱ የኖርኩበት ነው፡፡ ወግ መዓርግ ያየሁበት ነው፤ እሳቱን በማጥፋት አስተዋጽዖ ማድረግ አለብኝ አትልም፡፡ መሸሽን ብቻ ነው የምትፈልገው፡፡ ለራስዋ ብቻ ነው የምታስበው፡፡ ይህ ከሸረሪትነቷ የመጣ ነው፡፡

እናንተ ግን ሰዎች እንጂ ሸረሪቶች አይደላችሁም፡፡ ሰዎችን እያያችሁ ከሀገራችሁ እና ከቤተ ክርስቲያናችሁ ልትርቁ አትችሉም፡፡ አያገባንም ልትሉ አትችሉም፡፡ እሳቱን ማጥፋት ትታችሁ ከእሳት ለማምለጥ ብቻ ልትሮጡ አትችሉም፡፡ ይህንን ካደረጋችሁ ሸረሪቶች እንጂ ሰዎች አይደላችሁም፡፡» አሏቸው

ይህንን ሰምተው ልጆቹ ወደ እናታቸው ተመለሱ፡፡

እስኪ እኔም አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፡፡ የዚህች ሀገር እና የዚህች ቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ፍላጎት ምንድን ነው? ይህች ሀገር እና ይህች ቤተ ክርስቲያን ያለ ረዳት እንዲቀሩ ማድረግ አይደለምን?  እናንተም እንተዋት፣ እናቁም፣ እንሽሽ ስትሉ ያለ ረዳት እያስቀራችኋት ነው፡፡ የእነርሱ ፍላጎት ኢትዮጵያን እና ተዋሕዶን ተስፋ ማስቆረጥ አይደለምን? እናንተም ተስፋ ከቆረጣችሁ ተሳካላቸው ማለት ነው፡፡ ልጆቻቸውን እያስመረሩ ማስኮብለል አይደለምን? ከኮበለላችሁ ተሳካላቸው ማለት ነው፡፡ ታሪክን፣ ቅርስን፣ ክብርን፣ ልዕልናን መመዝበር እና ማራከስ አይደለምን? እናንተም ታሪኩን፣ ቅርሱን፣ ባህሉን፣ ክብሩን ርግፍ አድርጋችሁ ትታችሁ በራሳችሁ ዓለም ብቻ ስትቀሩ የእናንት ፍላጎት ሳይሆን የእነርሱ ፍላጎት ተሳካ ማለት ነው፡፡

ታድያ አሁን እናንተ መመለስ ያለባችሁ አንድ ጥያቄ ነው፡፡ የምትፈልጉት የጠላቶቿ ፍላጎት እንዲሳካ ነው ወይስ በመከራ ውስጥ ያለችውና ቀን የጣላት የእናታችሁ ፍላጎት እንዲሳካ ? ምረጡ፡፡እነሆ ይህ ጥያቄ ሁሌም ይመጣብኛል፡፡

88 comments:

 1. kalhiwot yasmalin. Bego zena sitefa tesfa yaskortal. Slezih endezih wone keskash yehonu tshuf bahunu gize kanante bejigu enfelgalen. Mimenan tesfachew ena woniachew endaykosis yh aynetu neger yketil. keShibr wore minim anaterfim. Le abatochachin tibebin yadlilin! Lemimenan tsinatun ena wonewn ystilin!

  ReplyDelete
 2. oh DN Daniel , thanks for the clear and easy to understand lesson u have posted here .... if we have clear and neat heart to know the truth ... to fight the truth .... to live for truth...this is an alarming call for all us ...us u said we are going away from church in this critical time by blaming others for the problems ....by letting others to do the work so that we can appriciate or critisize their work ....this will definetely put us with those Anti-tewahido Groups directly and indirectly ....
  any way May God bless u for this ..... i will see my self from inside and i will realy try to be with my church in God's will to me

  Gebremariyam
  Gondar, Ethiopia

  ReplyDelete
 3. :'( Kale Hiwoten Yasemlen
  Awo Wedtem Lenhed Aygbeam Bentchen Bet Lenkorfe Aygbeam

  EGZIABHER Anten Yetbklen Tsloten Yesmealen
  Endante Yaleu Bezu Harywochen Yabezalen Amen!

  ReplyDelete
 4. በመጀመሪያ ቃለ ህይወት ያሰማልን

  ሰው ክቡር ፍጡር ነው! ስለዚህም ሸረሪት መሆንን የሚመርጥ አለም ብዬ አልደፍርም፡፡ ህይወት ምርጫ እንጂ ፍላጎት አደለም ፍላጎቱ ወደ ምርጫ ቢወስደውም ፍላጉት ብቻውን ግን ውሳኔ/ምርጫ/ ሊሆን አይችልም "የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ.." እንደተባለው፡፡ አንድ ስብከት ላይ እንደሰማሁት "ወኔ የሌለው፤ውሳኔ የሌለው ክርስትያን መሆን አይችልም/ምስክር መሆን አይችልም/ሰማዕት ዘደም ወይም ዘእንበለ ደም መሆን አይችልም፡፡ ክርስትናም አልጋ ነው መንገዱ የሚል መዝሙር የለንም፡፡ እኔ ውሃውን መርጫለሁ መስራት ያለብኝንም ጭምር፡፡

  አንተንም ላስተማሩህ
  ለአንተም
  እንዜአብሄር መልካሙን ያስመርጣችሁ
  እኔን፣እሱንም .................. ሁላችንንም በመረጥነው ያፀናን፡፡

  ReplyDelete
 5. Kalehiwot yasemalin!

  ReplyDelete
 6. THANK YOU FOR YOUR GREAT ADVICE.AT THE TIME OF CRISIS MOST PEOPLE ARE DESPERATE TO CHOOSE THE RIGHT DECISION.THIS ADVICE WILL BE USEFUL TO RETHINK THEIR THOUGHT.

  ReplyDelete
 7. Thanks, well said! May God helps us to learn and take note of this!

  ReplyDelete
 8. Dani,
  Thank you for your commendable message!
  I am really eager to read daily your instructive articles.
  Glad to be the first to comment,as you said it is during time of hardship that we reckon whether we are true believers or not.Indeed we need to face the reality that our mother church has now entangled with.We should never be desparated and hopeless.Rather the revival of our glorious aniquity church is coming.
  More than ever now we are at the crossroad.we should be tolerant of this abominable things.We need to pray dedicatedly to our God.

  God bless Ethiopia!!!

  ReplyDelete
 9. DANIEL God blees you.

  ReplyDelete
 10. Dear Daniel,
  What an inspiring story and a true reflection of the state of quagmire that we are in. The moral of the story have the ability to take one's spirit out of the well-entrenched feeling of despair that most of us are in. Thank you for sharing this wonderful story!

  ReplyDelete
 11. Actually we need our beloved mother but we totally hate the arrogant step father!

  How could we live with mom without looking him?

  I think the better solution is a divorce!!

  ReplyDelete
 12. ቃለ ሕይወት ያሰማልን እግዚአብሔር አንተንና እውነተኛ የተዋሕዶ ልጆችን ሁሉ ሀሰተኛ ከሆኑ ሰዎች ሴራና ተንኮል ይጠብቅልን ሰማያዊ ዋጋህን ምድራዊ በሆነ ውዳሴ ከንቱ ላለመጉዳት ስል ብዙ ማመስገን ባይኖርብኝም በዚህ በጭንቅ ጊዜ በትክክል ምን ማድረግ እንዳለብን ስለመከርከን (ስላስተማርከን) እግዚአብሔር ይስጥልን በርታ አይዞህ ድንግል ማርያም ትጠብቅህ

  ReplyDelete
 13. dn.daniel geta eyesus kirstos abzito yibarkik! ye betecrstian tebake adrgo geta shomokal!!!!

  ReplyDelete
 14. dani kale eywot yasemalene ynjera abatachene kenelegochu enatacen laye benesu engname yekurte kene yenatachene lejoche alene enbelat.  dani from dire dawa

  ReplyDelete
 15. i am very happy 2 write 1st person on this issue.it tells us 2 think and to make action.let us pray together 2 find solution and to do our best ASAP.

  ReplyDelete
 16. Kalehiwot Yasemalene Dn. Daniel

  it is a very nice lesson
  i will choose my mother church and country

  ReplyDelete
 17. Egziabher amlak yistilign, endiuhum betsega bebereket yotebikiln. Be enena beguadegnoche chinkilat simelales yenebere hasab ahun yetemelese yimesilegnal. Yihin timihirt abaziche adarisewalehu. Egiziabiher yibarkilin Memihir Daniel.

  ReplyDelete
 18. ሰሚ ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ!

  ReplyDelete
 19. Dear Dn Daneil,May God bless you more & more. this kind of advice is what every one needs at this difficult time so thank you but we need more & it should be availabel to every one.Most people i talk are hopeless & dormant.

  ReplyDelete
 20. where is my comment,?Dani

  ReplyDelete
 21. Betam tiru mikir new.

  ReplyDelete
 22. ዘቡልጋ
  ግሩም ነው ዳኒ!
  ልቦና ያለው መስማትን ይስማ አይደል የተባለው!!!

  ReplyDelete
 23. Bewnet tesfa koriche neber gen lemen yene tesfa mekuret lenesu yalama mesakat endehone ahun teredahu Igeziabehir edemehin yarzimelen........

  ReplyDelete
 24. KeleHiwet. Thank you.

  ReplyDelete
 25. Dani, if I were to write my comment yesterday, which i tried and stopped as i didn't like my idea myself since it was against this article, i would have regretted it now. the point is I am not in addis now and the strongest part of the article is the last line and that lacks evidence for me. but today i read the news http://www.newsdire.com/entertainment/1051-yemeskelu-sir-kumartegnoch-statue.html and get lost totally. Dani, to be honest I am lost now and confused. please dani, in most of your articles you mention the problems but not the solutions and some type of guidance. most people asks that but u r not responding to that part. please do and show us the way how to react for such big issues with the help of God.

  ay God bless us all!

  ReplyDelete
 26. Qalehiwot yasemaln dear brother

  Yes we need to show them our perseverance by staying in our church and serving to the best of our potential. We will never give up because of what these people are doing to our church. I was saying to my wife this is the time to stick to our church and strengthen our service and contribution. We should not give any chance for hoplessness and despair. That is what these anti-Tewahedo elements are looking for. I feel more determined and inspired to continue my participation in my Sunday school and the church. Let us stand up together with more committment and strength and show them we are there being more strong and determined to do our best what ever it takes. Thank you dear brother again for this timely message and I agree totaly with you. That is the only choice we have and God will help us as far as we hold the truth. And that is standing for our church not for our ambitions ans personal desires.

  May God protect our church
  May God bless the true church servants and Me'emenans

  ReplyDelete
 27. *CHRISTIAN ENA MISMAR SIMETUT YITEBKAL*
  YEBELETE LE AGELGLOT METGAT AHUN NEW!!!

  ReplyDelete
 28. ጤና ይስጥልን ዲ/ዳንኤል፡፡ትምህርትህን እንወደዋለን፡፡ይህን አሁን የከፈትከውን አዲስ የትምህርት ብሎግም እጅግ በጣም ጥሩና አስተማሪ ነው፡፡ በቅርቡ ወደ አሜሪካን እንደምትመጣ ሰምተናል፡፡ በነሐሴ መጨረሻ በ28፤29 እና 30( Sep 3,4&5) ላይ በዳላስ ከተማ ውስጥ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባዔ ለማዘጋጀት እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡ በዚህ ጊዜ ወደኢትዮጵያ የማትመለስና የተያዘ ሌላ ፕሮግራም ከሌለህ ልንጋብዝህ አስበናልና እባክህ መልስህን በብሎጋችን የአስተያየት ሳጥን በመላክ አሳውቀን ፡፡ ሰላመ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን ፡፡ ወደ አሜሪካንም በሰላም ግባ፡፡ selam-tewahedo.blogspot.com

  ReplyDelete
 29. Dear Dakon Daniel, I know you very well not physically but by what you did for Ethiopian Orthodox church and I rely appreciate your contribution too and let GOD Bless you.

  Keep it up.

  It is today that I start to access your website and able to look the above message which tells us to do and perform our assignment rather than only living with our name.

  Wish you all the best.

  Temesgen Kassa, Dire Dawa

  ReplyDelete
 30. may god bless your ageleglot

  ReplyDelete
 31. በስመ ሥላሴ አሜን።

  የእግዚአብሔር ሰላም ይብዛልህ መምህር ... እንደምን አለህ?..ይህንን ጽሑፍ ማንበብ እንደፈፀምኩ በቅፅበት ዘወትር በህሊናዬ ሲመላለስ የነበረ እና ከዚህ አንተ ከጻፍከው ጋር ተያያዥነት ያለው አንድ አብይ ሀሳብ ትውስ አለኝና ይህንኑ ልጽፍልህ ወደድሁ ... ዐብይ አልኩት ለኔ ዐብይ ነውና። ... ብቻ ነገሩ እንዲህ ነው ...

  በታላቁ መጽሐፍ ፤ በመጸሐፍ ቅዱስ ፤ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ዕብራውያን ሰዎች በላከው መልዕክቱ ላይ ፦ አስቀድመው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንና ደቀመዛሙርቱን ፤ ወንጌልን ስለማስተማራቸው ምክንያት ይቃወሟቸውና ይጠሏቸው ስለነበሩ ፤ ከዚያም ጌታ ካረገ በኋላ በሐዋርያት ቃል የሚደረገውን ተአምራት ባዩ ጊዜ ወደ ማመን ስለመጡ ዕብራውያን እና አህዛብ የተነገረውን ቃል ፦ " ... የምስራች ተሰብኮላቸዋል ፤ ነገር ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር በእምነት ሥላልተዋሃደ አልጠቀማቸውም። " ዕብ 4 ፦ 2 ... ባነበብኩት ቁጥር ፤ በዚህ ዘመን ላለው ለእኛ እምነት ተምሳሌት እንደሆነ ይሰማኝ ነበር ፤ በተለይ ያንተን ጽሑፍ ካነበብኩ በኋላ ተዛምዶው የጎላ እንደሆነ ታየኝ። ... ሐዋርያው ስለነዚህ ሰዎች የእምነት ጉድለት እንዲህ ማለቱ እንደ አባቶች ትርጓሜ ፦ እምነታቸው ሕገ-ወንጌልን ለሕገ-ኦሪት ተጨማሪ ሕግ በማድረግ ፤ ሕገ-ኦሪትን ከሕገ-ወንጌል አብልጠው መጠበቃቸው ሳይቀር ስለነበረ ነው።

  በዚህ በእኛ ዘመንም የብዙዎቻችን እምነት እንዲህ ከላይ እንደተወቀሱት ሰዎች አይነት ፤ ጎዶሎና ፤ የማይጠቅም የሆነብን ይመስለኛል። ... እንዴት ቢሉ ፦ በእግዚአብሔር ከመታመናችን ጋራ አዳብለን የያዝናቸው በአይነት እና በመጠን እንደጣት አሻራዎቻችን የተለያዩ ሚጢጢ የየግል " እምነቶች " ስላሉን ነው። ... እኩሌታችን ፦ በእግዚአብሔር የምናምነው ፤ ገንዘብ ፦ የማይናቅ ጉልበት እንዳለው ከማመን ጋራ ነው። ... እኩሌታችንም የወፋፍራም ዘመዶቻችንን ትከሻ ከመደገፍ ጋራ ፤ ሌሎቻችንም ለራሴ ራሴ አውቅላታለሁ ከሚል ትምክህት ጋራ ፤ ሌላም ሌላም ... ጋራ ነው። ስለዚህም በእግዚአብሔር መታመናችን ፣ ለርሱ መገዛታችን በሌላ አላስፈላጊ ቆሻሻ ተመርዟልና አይጠቅመንም። ... እዚህ ላይ የእግዚአብሔርን የምህረትና የቸርነት ሥራ እንደሌለ ፤ እንደዚህ ባለ ሁኔታ ውስጥ ያለን ሰዎች ፈፅሞ የተጣልንና ፈላጊ የሌለን አስመስዬ ማቅረቤ አይደለም ፤ ... የድርሻችን የሆነው ፤ ከእኛ የሚጠበቀው ጎድሎናል ለማለት ፈልጌ እንጅ ...

  መምህር፦ አሁን በፅሑፍህ መጨረሻ ላይ ወደጠየቅከው ጥያቄ ልምጣ ... በርግጥ በጥያቄው ለቀረበው ምርጫ ምላሽ " እናቴን " የምንል ብዙዎች እንደምንሆን ተስፋ አደርጋለሁ ፤ ግና ይህ ምላሽ ሥሜታዊነት የወለደው ይሆናል ብዬ ደግሞ እሰጋለሁ። ... እርግጥ በአሁኑ ወቅት በሀገር እና በሕዝብ በተለይም በቤተክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለው ጥፋት ጀርባ የሚሰጥበት ፣ ያወጣ ያውጣው የሚባልበት እንዳልሆነም አምናለሁ ፤ ... ነገር ግን የእናትዬዋ ልጆች የእናታቸውን ችግር ከስር መሰረቱ የሚነቅሉበት ፣ ቢያንሰ ቢያንስ የሚያስታግሱበት አካላዊ ብርታት ፣ ምጣኔ ሀብታዊ አቅም ፣ የመንፈስ ዝግጁነት ፣ ወኔ ፣ እልህ ፤ ወዘተ እስከሌላቸው ድረስ አባታቸው ሰክሮ በሚመጣበት ምሽት ፤ እናታቸውን በሚደበድብበት ፣ ገንዘቧን በሚነጥቅበት ወዘተ ዕለት ብቻ አገር ይያያዝ ቢሉ የቤታቸውን ችግር ከድጡ ወደማጡ ከመውሰድ የዘለለ የሚፈይዱት አንዳች ነገር የሚኖር አይመስለኝም።

  ምንም እንኳን ሀገራችንና ቤተክርስቲያናችን ከችግር ተላቀው ባያውቁም እንደልማድ ይዘነው እያንዳንዱ ችግር በተከሰተ ወቅት ብቻ ስለችግሩ ብዙ አውርተን ፣ ብዙ ጉድ ጉድ ብለን ወደ ቀደመ አኗኗራችን እንመለሳለን ፤ ... ችግሩን የፈታነው ይመስል። እኔ ግን ይህ ልማድ እራሱ ጥልቅ መሰረት አለው እላለሁ ...

  እንዲህም ስለሆነ ፦ በእግዚአብሔር አምናለሁ የሚል ሕዝብ የደስታውንም ሆነ የሀዘኑን ወራት ከእርሱ ( ከፈጣሪው ) ጋር ሊያሳልፈው ይገባዋል ብዬ አምናለሁ። እምነታችን ፣ በእግዚአብሔር መደገፋችን ከሁለንተናችን ጋራ ተዋህዶናል ብዬ አላምንምና በአሁኑ ወቅት እየሆነ ላለው ክፉ ነገር መፍትሔ ለማግኘት በትክክለኛው መንገድ ውስጥ አይደለንም ብዬ አስባለሁ ...በርግጥ መፍትሔ የሚሰጥ እርሱ እግዚአብሔር ብቻ ነው ፤ ቢሆንም እኛ እና እርሱ በእጅጉ እንደተራራቅን ልብ ልንል ያስፈልገናል። ... እኛ ግን ያስተዋልን አይመስለኝም ፤ ስለዚህም ሐዋርያው " ...በእምነት ስላልተዋሃደ ... አልጠቀማቸውም " እንዳለ ወቅታዊ ከሆኑ ችግሮች መነሻነት ፣ ስሜታዊነት በወለደው እልህ አማካኝነት ለመፍትሔ ብንወጣ አይጠቅመንም።

  አምላካችን ገባሬ ኩሉ ፣ ቤተክርስቲያንም የእርሱ ፣ እኛም ልጆቹ ስለመሆናችን ፈፅመን ካመንን ፤ በዚህም ላይ ጥቂት የልጅነት ተግባር ከፈፀምን ለኛ እንዲህ ከብዶ የታዬ ችግር ከስሩ ይነቀላል ፤ ውሉ የጠፋ የመሰለው ቋጠሮ ይፈታል።...ለሚያምን ሁሉ ይቻላል ተብሏልና።

  በዚህ ሒደት ውስጥም እናንተ መምህራን ሕዝቡ በመንፈሳዊም ሆነ ስጋዊ ሕይወቱ ሳንካ እየሆነበት ላለው ችግር መንስኤውን እንዲያውቅ ፤ ስለመፍትሔውም ትክክለኛ እና የሚገባ አካሄድን እንዲመርጥ ጥቁምታ በመስጠት ረገድ ላቅ ያለ አስተዋፅኦ አላችሁና በርቱ ። ...ለዚህም እግዜር ከእናንተ ጋር ይሁን።

  አምላከ ቅዱሳን እግዚአብሔር ያስበን።

  አሜን።

  ReplyDelete
 32. Dn Daniel:

  Kalehiwot Yasemalegn!Zerehen yebarkew. Betkirstianachen meech arfa tawkalech ? Egnam telenat leenehed ayegebam. Ewenet new. Melkamun endenareg egziabhaer yerdan. Redeate Egziabhaer Ayeleyene. Amen!

  Ze-Canada:

  ReplyDelete
 33. Dear dn.Dani, I think ye-enatachin filagot endisaka mefelegachin ayateyayikim neger gin ahun balew huneta esuan mulu lemulu desitegna lemadreg yeminichil ayimeslim (bemin bekul?) amlak be Ezekiel 34:10 lay begebalin kal meseret fitun kalmeleselin besteker.

  Ezekiel 34:2:- "woe to the shepherds of Israel who only take care of themselves! shouldn't shepherds take care of the flock? you eat the curds, clothe your selves with the wool and slaughter the choice animals but you don't take care of the flock.........they were scattered b/c there was no shepherd and when they were scattered they become food for all the wild animals"
  God has that prophecy to Ezekiel and it has been fulfilled today but don't worry brothers & sisters God has a good promise for the people (flock or sheep)& he said..
  Ezekiel 34:10 "I am against the shepherds, will hold them accountable for my flock & they can no longer feed themselves, I will rescue my flock from their mouths, I myself will search my sheep & look after them" It really shows us the current situation but the good thing is God has a promise to rescue us, we should just seek his face for the repentance of us & the shepherds.

  Amlak bemihiretu yigobignen!

  ReplyDelete
 34. Dear Dn Daniel, I can only say ehhhhhhhhhhhh!!!! I agree running away is not a solution but I do not think being submissive is the solution either!! Hope am not blamed for picking the enemies sword but honestly there is a limit for every nonsense!

  ReplyDelete
 35. I don't agree with most of the comments!

  I am sure that the central idea of the article is clear and everybody might agree with that. But I don't think it is a solution for this problem.

  I stick on my idea which is a DIVORCE!!!

  By the way have you heard the satire on the statue? It says “THE POPE NEED TO SEE HIS PORTRAITE WITH STONE"

  ReplyDelete
 36. Yetbarek Amlake Abewine.

  Bewnet Dn Dani this is timely, touching and exact message for our brothers and sisters in our church.
  Yastemaren Egzeabeher yemsegen!!!

  ReplyDelete
 37. waw i am very lucky 2 post the first.betame yemgereme negere new pls all of us lets think twice before we do any action.it teaches us a lot

  ReplyDelete
 38. መልካም እይታ ነው::

  ReplyDelete
 39. Dear Daniel Kibret
  KALE HIYWOT YASEMALIN WENIDEMACHIN
  Even if we are far from our beloved church country and people we still love and try our best to support our church individually as well as a group.
  We are doing our best fighting with tehadeso, who is trying to distorted our true faith and religion (yabatochachinin)using our name. They are the one very dangerous, Our true tewahedo people have to wake up and ask ourselves and do research ask and read.
  DANI KALEHIWOT YASEMALIN
  DINGILE TIKETELEHE
  KIDUS MICHAEL EYEKEDEMEH YEMIRAH
  YAGELIGLOT ZEMENUHUN YARZIMILIN

  ReplyDelete
 40. Qale hiwoten yasemalen Amen!!! selam daniel selameh yderesen .

  enen betam gera yegebag neger binor manen ensema manen enketel Betekerseteyanachen ye ahzab mesakiya ye menafekan mekelega honechebn eko yemisemaw neger betam yekebedal selehmentu telk ewket yelelew hezeb eko bemenafekan abalenet simezegeb weym hulum men yaderegelegal belo bealmawi hiwoten yalekeresetena eyehede new yalew lezih hulu teteyakiw manew ? egas men maderg new yaleben zem belen mesemat mayet ? weys ende and yebetekertsetyan legenet maderg yaleben neger ale ? kale ebakeh betley betam gera gebetog eyetefetere yalew cheger gera eyagabag eyakateleg newna yalew yemetelgn beleg elalew . EGZIABHER AMELK esu aytewen aynaken becha yemetawen mekera becherentu yemeleselen Amen

  ReplyDelete
 41. Thanks Dany this lesson is what's really expected from a real precher, presenting a timely teaching.
  Stay blessed and take care!

  ReplyDelete
 42. DIVORCE!!! DIVORCE!!! DIVORCE!!!
  you guys must understand first the mindless, mad and drunk "Ye'Enjera Abat" is not single person. They are too many. we all agree on the statment of the problem however I, personaly dont agree to stay at home and wathc what the drunk and mad step Father is doing on my Mom. fight for MOM !!!

  ReplyDelete
 43. it is a very nice story it teaches me a lot We should choose our mother church and country including you. do you leave your mother country or not?

  ReplyDelete
 44. Kalhiwot yasemalen
  Actually it is not only at the time of danger we Christians stand up for our church as well as ourselves but always since it has already been said "begizewum yalegizewm tsina".

  ReplyDelete
 45. ዲ/ዳንኤል በቅድሚያ የከበረ መንፈሳዊ ሰላምታየ ይድረስህ፤
  በጻፍከው የአንድ አባት ምክር አስመልክቶ የተሰማኝን ማለት ፈለኩኝ
  “ንቁም በበኅላዌነ እስከ ንረክቦ ለአምላክነ”
  ይህን ቃል የተናገረው ሁላችን እንደምናውቀው
  የእግዚአብሔር ባለ ሟል የሆነውና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡
  በመላእክት ከተማ ዘንድ ሁከትና ረብሻ በመፍጠር ፈጣሪአችሁ እኔ ነኝ እኔ ፈጠርኳችሁ እኔንም አምልኩ የሚል
  የሐሰት አባት በተነሣ ጊዜ ሁላቸውም ሲታወኩ እውነተኛው አምላካቸውና ፈጣሪያቸው
  እስከሚገለጥላቸው ድረስ በያሉበት ፀንተው በትግዕሥት ፈጣሪአቸውን እንዲጠባበቁ የሰበከ
  ላቸውና ትግዕሥትን ያስተማራቸው ቅዱስ ገብር ኤል እንደሆነ እንረዳለን፡ዛሬም ቤተ ክርስቲያናችን
  ይህን መሰል ሁከት በመፍጠር ገዣችሁ እኔ ነኝ እኔን ብቻ አምልኩኝ የሚል ሣጥናኤል መሰል አዋጅ ሲታወጅ
  ለክርስቲያኖች የሚያስፈልገው አምላካችን ተገልጦ አለሁ እስከሚለንና አምልኩኝ ባዩንና ተከታዮቹን መንጸፈ ደይን እስከሚያወርዳቸው
  በያሉበት ሆኖ በትግ ዕሥት መጠባበቅ የኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ድርሻ ነው፡፡ከዚያ ባለፈ መማረሩ መበሳጨቱና
  አቅጣጫን ሥቶ ከእናት ቤተ ክርስቲያን ማፈንገጡ ለማናችንም አይጠቅመንም፡ በተለይ ባለንበት ሃገር ሰሜን አሜሪካ
  ምክንያት ያድን ይመስል ወቅታዊ ችግር ሲኖር ያንን ተከትሎ እናት ያልሆነችውን በስም ብቻ እናት የምትባለዋን፡ነገር ግን በግብርና
  በመልክ የማትመሳሰለዋን እናቴ ማለት ተለምዷል ይህ መፍትሔ ሊሆን አይችልም፡ መፍትሔው እግዚአብሔር አምላካችን በጊዜውና
  በሰዓቱ ሥራውን እስኪሰራ ድርስ ያልተረጋጉትንና የታወኩትን ያፅናና መልአክ ቅዱስ ገብርኤል እንደአስተማረን በያለንበት ሆነን
  በመጸለይ በእናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር ጸንተን ልንኖር ይገባናል፡፡ የዲያብሎስን ኃይሉን ያድክምልን፡

  ReplyDelete
 46. One of Her Son From Minnesota

  IF our mother divorce our setp father as we all know that everybody has paln to be her husband ,My mother has no one in her heart, but due to the so called friend , social life , differnet reasones ,Adviser========Belive that Just being Hunsabd of my mother there a lot of benefit ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, if she divorce our setp father , I do not think We Will be okay there are a lot of dangrous setp father around her My plan Let Us Go to Our Realy father (mekaber ) pray please Give us father that will protect our mother and us or please come and see us !

  Dn cherinet

  ReplyDelete
 47. Deacon Daniel,

  Thank you for your wise words. But the problem with our Church is that there are also leba qesawust and diaqonat who recite chapter and verse from Genesis to Revelation but who have chosen to collaborate with those destroying the church. The truth is that the augly ethnic politics that Woyane imposed on Ethiopia has found its way into our church: I think armed struggle is the way; let us join Ginbot!

  ReplyDelete
 48. Dn Daniel,

  Thank you very much for addressing such regretibly deafening complacence most of us have chosen in the face of a mounting trouble our mother is faced with.

  Our step father is lawlessly breaking our mother's heart. And her children are helplessly stunned by their step father's misbehaviour.

  My question is what next? What should we do if our step father daringly brings his mistress to our mother's house?

  Should the children rise up in unison and force their step father out of their mother's home?

  In our history, our church had been in deep challenges before. One such instance was, Atse Susinios declaring Catholisim as the official religion. What did the faithful do then?...read history.

  May the Lord guide in this difficult time.

  ReplyDelete
 49. Keep it up Dani, May God be with you to tell us the truth!

  ReplyDelete
 50. good job dani, I am with you!!!!

  ReplyDelete
 51. ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ያስባት!!

  ReplyDelete
 52. ዲ/ዳንኤል በቅድሚያ የከበረ መንፈሳዊ ሰላምታየ ይድረስህ፤
  በጻፍከው የአንድ አባት ምክር አስመልክቶ የተሰማኝን ማለት ፈለኩኝ
  “ንቁም በበኅላዌነ እስከ ንረክቦ ለአምላክነ”
  ይህን ቃል የተናገረው ሁላችን እንደምናውቀው
  የእግዚአብሔር ባለ ሟል የሆነውና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡
  በመላእክት ከተማ ዘንድ ሁከትና ረብሻ በመፍጠር ፈጣሪአችሁ እኔ ነኝ እኔ ፈጠርኳችሁ እኔንም አምልኩ የሚል
  የሐሰት አባት በተነሣ ጊዜ ሁላቸውም ሲታወኩ እውነተኛው አምላካቸውና ፈጣሪያቸው
  እስከሚገለጥላቸው ድረስ በያሉበት ፀንተው በትግዕሥት ፈጣሪአቸውን እንዲጠባበቁ የሰበከ
  ላቸውና ትግዕሥትን ያስተማራቸው ቅዱስ ገብር ኤል እንደሆነ እንረዳለን፡ዛሬም ቤተ ክርስቲያናችን
  ይህን መሰል ሁከት በመፍጠር ገዣችሁ እኔ ነኝ እኔን ብቻ አምልኩኝ የሚል ሣጥናኤል መሰል አዋጅ ሲታወጅ
  ለክርስቲያኖች የሚያስፈልገው አምላካችን ተገልጦ አለሁ እስከሚለንና አምልኩኝ ባዩንና ተከታዮቹን መንጸፈ ደይን እስከሚያወርዳቸው
  በያሉበት ሆኖ በትግ ዕሥት መጠባበቅ የኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ድርሻ ነው፡፡ከዚያ ባለፈ መማረሩ መበሳጨቱና
  አቅጣጫን ሥቶ ከእናት ቤተ ክርስቲያን ማፈንገጡ ለማናችንም አይጠቅመንም፡ በተለይ ባለንበት ሃገር ሰሜን አሜሪካ
  ምክንያት ያድን ይመስል ወቅታዊ ችግር ሲኖር ያንን ተከትሎ እናት ያልሆነችውን በስም ብቻ እናት የምትባለዋን፡ነገር ግን በግብርና
  በመልክ የማትመሳሰለዋን እናቴ ማለት ተለምዷል ይህ መፍትሔ ሊሆን አይችልም፡ መፍትሔው እግዚአብሔር አምላካችን በጊዜውና
  በሰዓቱ ሥራውን እስኪሰራ ድርስ ያልተረጋጉትንና የታወኩትን ያፅናና መልአክ ቅዱስ ገብርኤል እንደአስተማረን በያለንበት ሆነን
  በመጸለይ በእናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር ጸንተን ልንኖር ይገባናል፡፡ የዲያብሎስን ኃይሉን ያድክምልን፡

  ReplyDelete
 53. Lijoch - miemenana

  yeinjera abat - aba paulos, aba fanuel, aba sawiros....

  inat - betekristian

  this is the right and timely lesson we obtained

  ReplyDelete
 54. ኃ/ገብርኤልJuly 22, 2010 at 3:52 PM

  ይህ የቤተ ክርስቲያነ የድረሱልኝ ተማፅኖ ነው።

  ReplyDelete
 55. ለካስ ሃዉልት ኖፘል፡

  በሰንበት በጧት ቤተክርስቲያን ልሳለም፣
  እግሬ እንደመራኝ ሄድኩኝ መድኃኔዓለም፣
  ገና ከሩቅ ቆሜ አንድ ነገር ታየኝ፣
  ወደፊት ተራመድኩ ፈራ ተባ እያልኩኝ።
  ዝም ብዬ እንዳላልፈዉ መስቀል ይታየኛል፣
  ወይ እንዳልጠጋዉ በአየር ላይ ተተክሏል፣
  ምነዉ የማይባርክ እጅ መስቀል መሸከሙ፣
  አይሳለሙት ነገር አደባባይ መቆሙ፣
  ብዬ ሳሰላስል ይበልጥ እየገረመኝ፣
  ምንነቱ ጠፍቶኝ ስጨንቀኝ ስጠበኝ፣
  ለካስ ሃዉልት ኖፘል አባት የመሰለኝ።

  (ለአባ ጳዉሎስ ሃዉልት ማስታወሻ)
  ከብሪታኒያ

  ReplyDelete
 56. Diakon Daneal Egziabher yebarkeh lela men enelalen "beabatochis metek legoch tewledulesh" teblo tesefual

  ReplyDelete
 57. አምደ ሚካኤልJuly 26, 2010 at 11:54 AM

  ዳኒ በእውነት ነው የምልህ እኔ ተስፋ ቆርጬ እግዚአብሔር ያደረገው ያድርግ ብዬ ከቅርብ ጊዜ በኋላ ቤተክርስቲያን መሄድ አቆምኩኝ።ከሩቅ ሆኜ ተሳልሜ መሄድ ብቻ ሆነ።ምኑም ላለመስማትና ላለማየት።በተለይም በአሁኑ ወቅት አዋሳ ላይ የሚደረገው ድርጊት በጣም ያሳዝናል።ያስለቅሳልም።
  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናንናምዕመናት ራሳችን መፈተሽ ያለብን ሰዓት ቢኖር ጊዜው አሁን ነው።
  ተስፋ ቆርጬ ነበር ተስፋዬን ቀጠልከው
  እግዚአብሔር ይስጥልኝ

  ReplyDelete
 58. Kale Hiwote Yasemaline!

  “ንቁም በበኅላዌነ እስከ ንረክቦ ለአምላክነ”:-( Egziabhair Yirdan

  Ameha Giyorgis & Fikrte Mariam
  DC/VA Area

  ReplyDelete
 59. እግዚአብሔር ይስጥልኝ

  ReplyDelete
 60. እጅግ ታላቅ ሀላፊነት ነው የተጣለባችሁ ካልበረታችሁ ግባችሁን አልመታችሁም ማለት ነው ስለዚህ ጅምር ብቻ እንዳትሆኑ በርቱ ሀገራችሁም ቤተክርስቲያናችሁም ከምን ጊዜውም በላይ ትፈልጋችሃለች ያለዚያ ተረት ሆናችሁ መቅረታችሁ ነው ተረት

  ReplyDelete
 61. zat is realy touches my mind. may GOD bless you.

  ReplyDelete
 62. diacon danieal betam turu tegenzibahale,letyekew tiyake gene ande neger yalgebange alle esume enatune tilo yemhede shereyt new balkew beyne asteyayet kenatu wetyoto bedure beberha begorebet hager weyme beweche alem lehaymanotu yemyagelegle sayresa lenate hageru nesanet yemetagel deha betesebun yemyerda shereryte yebalal weyes ayebalem? bemesafe kidus weste kidusane alyesededum meswat becha new yehonut?

  ReplyDelete
 63. Ethiohenok GODOLYAS

  Kalehywot yasemalen! lantem mekerun lesetuh abatm. bedmea betega yetebekelen endenante aynetun lekomneger hodu yesefa medehanyalem ayasatan. yetechegernew eko hodo lemebel yesefa sew beztoben new 1000 hunelegn emebatea dengel maryamen tebarek.
  babybelee@yahoo.com
  10godolyas@gmail.com

  ReplyDelete
 64. kalehiwot yasemalin
  dani ibakih yaniten ateyayetoche betam iwedachewalew,inam ibakih kalasichegeriku beygizew yemitawetachewin b E-mail post bitaderigeligne,my e-mail is musae_bd@yahoo.com
  igziabehare tsegawin yabizalih!!

  ReplyDelete
 65. Daniel May God be with u always.

  ReplyDelete
 66. Bewunetu Egzabher yale tebaki hizbochun ayitawachewum bezhi zemen anten yemitastemribet andebet yesetah amlake Israel simu lezelealem yetemesegane yihun amen. Dani le antem rejim edime na tena yistih egziabher eskamechareshew ye tewahidon lijochin iyatsnanah indtnor yirdah.
  Bewunet newu yemilih beahunu sa't yetayazew strategy tesfa maskoreti newu enem tesfa eyakoretiku neber ahun gin yeand abat mikir yemlawun kanebebku behale hail agnchealehu.
  Bedgam Leoul Egziabher kalehiwot yasemalin.
  ETHIOPIAN YIBARKAT AMEN+ FROM DIRE DAWA

  ReplyDelete
 67. Oh my God !!!I have been thinking by spider mind!!! Now i am about to back to my human brain!Your truthful idea forced me to do this!
  Tnx dani!!! long life with God's holly sprite !!!
  Egiziabihear dagna new!!!!!Yiferdilinal!
  Yehawariyat geta alemin beblogh ewinet yemitkedinibetin kidus menifes yafisilih!Amen!

  ReplyDelete
 68. betam tiru new kal hiywetn yasemalin mengste semayatin yawarsilin.

  ReplyDelete
 69. ወንድም ዳንኤል
  እጅግ ከፍ ባለ ትህትና የማክበር ሠላምታዬን አቀርብለሁ፡፡
  በተለያየ አጋጣሚዎች የምታቀርባቸውም ጽሁፎች ከኢንተርኔት ከመፅሄትና ከመጽሀፍህ ያገኘሁትን ያህል ለማንበብ ሞክሬአለሁ፡፡ በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የምታነሳቸው ሀሳቦች መልካም ጎናቸው ከፍ ያለ ነውና በዚሁ እንድትቀጥል መልካም ምኞቴ ነው፡፡ ብዙም ግላዊ የሆነ ትውውቅ ባይኖረንም "የብላቴ ዘማቾች ጊዜ"ትውልድ ውስጥ ከሚካተቱት አንዱ ወንድም እንደምትሆን እገምታለሁ፡፡ ይህ ላነሳው ከምፈልገው ሀሳብ ጋር ምንም የቀረበ ግንኙነት ባይኖረውም ቢያንስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነውን አምልኮንና እምነት ምን ሊሆን እንደሚገባው ለመረዳት ያለህ የማንበብና ልዩ ልዩ ቦታዎችን ለመጎብኘት ያገኘኸው እድል እንዳለህ እርግጠኛ እንድሆን ያሳየኛል፡፡
  ይህ እየሆነ ከሆነ ደግሞ እምነት ነክ በሆኑት ጽሁፎችህ ላይ የማየው ወገኝተኝነት ያደላበት አቀራረብ እውነት ከሆነው ከእግዚአብሔር ቃል /መጽሐፍ ቅዱስ/ ወገንን የሚያርቅ እንዳይሆን አስተውሎ ማየቱ መልካም ይመስለኛል፡፡ ይህንን ስል እንዲያው ለመቃወም ሀሳብህን ለማጣጣል ብዬ አይደለም፡፡ አንዳንድ ጊዜም ቢሆን በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሚታዩትን አብዛኛውን ምዕመንንም ከወንጌልና ከእየሱስ ክርስቶስ ትንሽም ቢሆን ዘወር የሚያስደርጉ ልምዶችና ባህሎች እንደሌሉ፤ ሁሉም ትክክል እንደሆነ እንዲታሰብ የሚያደርጉ የመቆረቆር አቀራረቦችን በጽሁፎችህ ላይ በማየቴ ነው፡፡ ከልብ ከመነጨ ትህትና የምገልፅልህ እኔም እራሴ ወገንተኛ መስዬህ እንዳልታይህ አደራዬ የጠበቀ ነው፡፡
  ወንድሜ ዳንኤል
  የክርስትና መሠረት ዋና ምሶሶ መጽሐፍ ቅዱስ የሚገልፀው ጌታችን መድሃኒታችንና አዳኛችን እየሱስ ክርስቶስ ብቻ እንደሆነና ከዚህ ፈቀቅ የሚደርግ ትምህርት ሁሉ መጨረሻው መልካም እንደማይሆን ለአንተ ወንድሜ ማስረዳት ድፍረት ይሆንብኛል፡፡ ትኩረታችን ከመፅሐፍ ቅዱስ ዋና መልዕክት ላይ መሆን ያለበት ይመስለኛል፡፡ ይህ ደግሞ አገራዊ ፍቅርን የሚጎዳበት ምንም መንገድ የለም፡፡ እኔ እነዚህ ነገሮች በደንብ መግለጽ ብቃቱ አለኝ ብዬ ለመናገር ከበድ ይልብኛል፡፡ እንድታነባቸው በትህትና የምጋብዝህ በዲያቆን አግዛቸው ተፈራ የተፃፉትን እንደ "የለውጥ ያለህ" ያሉትን መጻህፍትና ከቻልክ ደግሞ አንድ የይሁዳን መልዕክት የሚያስተምር ስብከት ከሜክሲኮ ወደ ገነት ሆቴል ስትሄድ በስተ ግራ ባለ ኬኬር ህንጻ ላይ አንደኛ ፎቅ ካለ "የእውነት ቃል አገልግሎት"ከሚባል የመጽሐፍ መሸጫ ድርጅት "የይሁዳ መልዕክት" የምትል ሲዲ ገዝተህ ከልብ በሆነ መሰጠት ብትሰማው የበለጠ መልካም ይመስለኛል፡፡ ግራ ቀኙን መመልከት እንደ አንተ ላለ የንባብ ሰው አስቸጋሪ የሚሆን አይመስለኝም፡፡ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡
  በትዕግስት ስላነበብልኝ እጅግ አመሰግንሃለሁ
  ወንድም ዳንኤል
  እጅግ ከፍ ባለ ትህትና የማክበር ሠላምታዬን አቀርብለሁ፡፡
  በተለያየ አጋጣሚዎች የምታቀርባቸውም ጽሁፎች ከኢንተርኔት ከመፅሄትና ከመጽሀፍህ ያገኘሁትን ያህል ለማንበብ ሞክሬአለሁ፡፡ በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የምታነሳቸው ሀሳቦች መልካም ጎናቸው ከፍ ያለ ነውና በዚሁ እንድትቀጥል መልካም ምኞቴ ነው፡፡ ብዙም ግላዊ የሆነ ትውውቅ ባይኖረንም "የብላቴ ዘማቾች ጊዜ"ትውልድ ውስጥ ከሚካተቱት አንዱ ወንድም እንደምትሆን እገምታለሁ፡፡ ይህ ላነሳው ከምፈልገው ሀሳብ ጋር ምንም የቀረበ ግንኙነት ባይኖረውም ቢያንስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነውን አምልኮንና እምነት ምን ሊሆን እንደሚገባው ለመረዳት ያለህ የማንበብና ልዩ ልዩ ቦታዎችን ለመጎብኘት ያገኘኸው እድል እንዳለህ እርግጠኛ እንድሆን ያሳየኛል፡፡
  ይህ እየሆነ ከሆነ ደግሞ እምነት ነክ በሆኑት ጽሁፎችህ ላይ የማየው ወገኝተኝነት ያደላበት አቀራረብ እውነት ከሆነው ከእግዚአብሔር ቃል /መጽሐፍ ቅዱስ/ ወገንን የሚያርቅ እንዳይሆን አስተውሎ ማየቱ መልካም ይመስለኛል፡፡ ይህንን ስል እንዲያው ለመቃወም ሀሳብህን ለማጣጣል ብዬ አይደለም፡፡ አንዳንድ ጊዜም ቢሆን በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሚታዩትን አብዛኛውን ምዕመንንም ከወንጌልና ከእየሱስ ክርስቶስ ትንሽም ቢሆን ዘወር የሚያስደርጉ ልምዶችና ባህሎች እንደሌሉ፤ ሁሉም ትክክል እንደሆነ እንዲታሰብ የሚያደርጉ የመቆረቆር አቀራረቦችን በጽሁፎችህ ላይ በማየቴ ነው፡፡ ከልብ ከመነጨ ትህትና የምገልፅልህ እኔም እራሴ ወገንተኛ መስዬህ እንዳልታይህ አደራዬ የጠበቀ ነው፡፡
  ወንድሜ ዳንኤል
  የክርስትና መሠረት ዋና ምሶሶ መጽሐፍ ቅዱስ የሚገልፀው ጌታችን መድሃኒታችንና አዳኛችን እየሱስ ክርስቶስ ብቻ እንደሆነና ከዚህ ፈቀቅ የሚደርግ ትምህርት ሁሉ መጨረሻው መልካም እንደማይሆን ለአንተ ወንድሜ ማስረዳት ድፍረት ይሆንብኛል፡፡ ትኩረታችን ከመፅሐፍ ቅዱስ ዋና መልዕክት ላይ መሆን ያለበት ይመስለኛል፡፡ ይህ ደግሞ አገራዊ ፍቅርን የሚጎዳበት ምንም መንገድ የለም፡፡ እኔ እነዚህ ነገሮች በደንብ መግለጽ ብቃቱ አለኝ ብዬ ለመናገር ከበድ ይልብኛል፡፡ እንድታነባቸው በትህትና የምጋብዝህ በዲያቆን አግዛቸው ተፈራ የተፃፉትን እንደ "የለውጥ ያለህ" ያሉትን መጻህፍትና ከቻልክ ደግሞ አንድ የይሁዳን መልዕክት የሚያስተምር ስብከት ከሜክሲኮ ወደ ገነት ሆቴል ስትሄድ በስተ ግራ ባለ ኬኬር ህንጻ ላይ አንደኛ ፎቅ ካለ "የእውነት ቃል አገልግሎት"ከሚባል የመጽሐፍ መሸጫ ድርጅት "የይሁዳ መልዕክት" የምትል ሲዲ ገዝተህ ከልብ በሆነ መሰጠት ብትሰማው የበለጠ መልካም ይመስለኛል፡፡ ግራ ቀኙን መመልከት እንደ አንተ ላለ የንባብ ሰው አስቸጋሪ የሚሆን አይመስለኝም፡፡ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡
  በትዕግስት ስላነበብክልኝ እጅግ አመሰግንሃለሁ

  ReplyDelete
 70. What is the relevance of "TABOT" in the Orthodox Tewahido Church? I am now very surprised when people worship the "TABOT" after I received JESUS as my personal savior? God enlightens your mind and heart. God bless you all.

  ReplyDelete
 71. But who is the mother in this metaphor? Is it just the land and sea and the flag? Or the image almost all of us have of a beautiful tall woman wearing 'Habesha Kemis' and pouring coffee? Who is the mother?

  Isn't it the people themselves? Everyone under the name 'Ethiopian'? And when you find that the people (most people) have long forsaken God and would rather hate than love, is it still sensible to stay?

  Most people go out of their country when they finally lose hope and find that even the 'mother' would rather persecute those who would like to help/save her.

  Only God can save the 'mother' who has forseken him when the right time comes through his mercy. Until that time, all our efforts are proving futile!

  Emebet Sabela

  ReplyDelete
 72. ዲያቆን ዳንኤል፡ ያቀረብከው ጽሑፍ እናት ቤተክርስቲያንን አትሸሹዋት በሚለው ጎኑ ተቀብለነዋል፡፡ በዚህ በመከራ ጊዜስ ከእርስዋ ሌላ ምን መሸሻ መደበቂያ መጽናኛ ሊገኝ! ለእርስዋ ሳይሆን ለራሳችን ብለን አንሸሽም በአጸድዋ ሆነን በእነሊቀመላእክት ቅዱስ ገብርኤል አድረህ ዓለመ መላእክትን ያጸናህ አምላክ አጽናን ብለን እናለቅሳለን፡፡ ሀገር ላልከው ግን መኖር ካልቻልን!ትንፋሻችን እንዳይቋረጥ፣ የቤተሰቦቻችንን የተራበ ሆድ ጩኸት ለመሸሽ እንጀራ ፍለጋ እንሰደዳለን፡፡ በተስፋዋ ቀን እንመጣለን፡፡ ውድ ዳንኤል፡ አንተ የቤተክርስቲያኒቱ ውጤት ነህ፡፡ እኛም የምናምንህ ወንድማችን አካላችን በማለት ነው፡፡ ነገር ግን ከላይ የተቀመጡ አይነት አንዳንድ አጽራረ ቤተክርስቲያን ጽሑፎችን በብሎግህ እያስተናገድክ እናት ቤተክርስቲያንን ታስደበድባለህ፡፡ እንደማስታወቂያም ታገለግላለህ!ዲሞክራሲ መሆኑ ነው ዘመናዊነት፡፡ በእውነት አዝነንብሃል፡፡ የእኛ ሀዘን ቤተክርስቲያን ሀዘን እንዳይሆንብህ አደራ ፡፡

  ReplyDelete
 73. Ante silet TABOT(sign of Seal) yetsafikewu above
  Afih yigemal eshi, If you have question you can ask, but from educated and disciplined man , it is not expected.
  Betam newuregna neh eshi, We blieve in love

  ReplyDelete
 74. Kalihiwot Yasemalin.

  May God bless your service.
  Girmay W.

  Sacramento, CA

  ReplyDelete
 75. Thanks Dn Daniel! For sharing what you observed to us. Because I observed so many people who think for our country, Ethiopia. Those who came from abroad (those who follow their philosophy/ ….) even do not like to call her. Always they blame her and our grand fathers', who protect her from colonization.

  ReplyDelete
 76. ዳኒ ያቀረብከው ጽሁፍ አሁን ቤተክርስቲያንን አትሸሹዋት በሚል ነዉ በዚህ በመከራ ጊዜስ ከእርስዋ ሌላ ምን መሸሻ መደበቂያ መጽናኛ ሊገኝ! ለእርስዋ ሳይሆን ለራሳችን ብለን አንሸሽም በአጸድዋ እንድንሆን አምላክ ጽናቱን ይስጠን፡፡

  ReplyDelete
 77. ድንቅ ነው ዳኒ we need more from you!!!!!!!!!!!!1

  ReplyDelete
 78. ድንቅ ነው ዳኒ ቃለህይወት ያሰማልን

  ReplyDelete
 79. kele hiwet yemalna d daniel

  ReplyDelete
 80. kale hiwot yasemalin!
  Ayi Dani, weden meselehi yeminisheshewu, beahun wekit yeminayewu $ yeminisemaw neger bewunetu ejege yasazinal zare telatochachin $ asdajochachin yerasachin yebet chiristian lijoch honubin eko,wudi mimenan kiwuch lemimeta telat hulem zigju neni gin betachin wusit yalewu new ....... beahunu seat A.A (alembank)kiduseGebireal betkiresityan wusit yemidergewu ejig yasazinal ebakachu mimenu,yesenibetitemariwu enidihun kahinatu sayikeru betehadiso tekebewal ewunetun lemayet kefelegachuhu 19 yekidusGebireal werawi beal metitachuhu yemitadelew minayinet metsihafkidusi enidehon aregagitu ebakachihu erasachin $ betkiresitiyan enadin,alamachewin yegebaw sayiwed betekirsitiyanun eyesheshe new,ebakachihu biyanis erasach keziyam kalef betekiresitiyan enidiresilat. beteley eneDn.Dani bizumesirate alebachihu.
  Egzabihire ethiopian yibarek amin!

  ReplyDelete